Leaguesport
前往频道在 Telegram
2 357
订阅者
-224 小时
-117 天
-4430 天
帖子存档
2 357
መቐለ 70 እንደርታ እግር ኳስ ክለብ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን እና የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ.ማ. ላይ ለCAS/ለስፖርት ግልግል ፍርድ ቤት/ ያቀረበው ክስ ውድቅ ሆኗል።
መቐለ 70 እንደርታ እግር ኳስ ክለብ የክለቦች የክፍያ ስርዓት አስተዳዳር መመሪያ በመጣሱ እና የቅድመ ክፍያ ከፍሎ በመገኘቱ የካቲት 17, 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የፋይናንስ አሰራር ተቆጣጣሪ ኮሚቴ በክለቡ ፣ በተጫዋቹ እና በክለቡ አመራሮች ላይ በየደረጃው የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፎ ነበር።
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የፋይናንስ አሰራር ተቆጣጣሪ ኮሚቴ በወሰነውን ውሳኔ ላይ ክለቡ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ይግባኝ አቅርቦ መጋቢት 23, 2017 ዓ.ም ይግባኙ ውድቅ መሆኑ ይታወቃል።
ክለቡም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ የወሰነውን ውሳኔ በመቃወም ሚያዚያ 9,2017 ዓ.ም ለCAS/ለስፖርት ግልግል ፍርድ ቤት/ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ.ማ. ላይ ክስ መስርቶ ነበር።
የክሱም ሂደት ረጅም ጊዜ የወሰደ ቢሆንም CAS/ስፖርት ግልግል ፍርድ ቤት/ በመዝገብ ቁጥር 2025/A/11381 ከዚህ በታች የሚከተሉትን ውሳኔዎች ዛሬ መስከረም 19,2019 ዓ.ም አስተላልፏል።
1. መቐለ 70 እንደርታ እግር ኳስ ክለብ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ የወሰነውን ውሳኔ በመቃወም ሚያዚያ 9,2017 ዓ.ም ለCAS/ለስፖርት ግልግል ፍርድ ቤት/ያቀረበው ክስ ውድቅ ተደርጓል።
2. የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ በመጋቢት 23, 2017 ዓ.ም ያስተላለፈው ውሳኔ ፀንቶ እንዲቆይ ተወስኗል።
3. የስፖርት ግልግል ፍርድ ቤት የሚያሳውቃቸውን ከፍርዱ ሂደቱ ጋር የተያያዙ ወጪዎችን መቐለ 70 እንደርታ እግር ኳስ
2 357
+1
በ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ሁለተኛ የምድብ ጨዋታ ሴኔጋል ከ ኢትዮጵያ የመጀመርያ አሰላለፍ
ጨዋታው 10፡00 ይጀምራል።
ድል ለኢትዮጵያ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
2 357
🇪🇹 የጨዋታ ቀን ! ⚽️
በ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ሁለተኛ የምድብ ጨዋታ የኢትዯጵያ ብሔራዊ ቡድን በሜዳው ባህር ዳር ስታዲየም ሴኔጋልን ከቀኑ 10፡00 ላይ ይገጥማል።
- የስታዲየም መግቢያ ቲኬት በኦንላይን ለመግዛት - eff-tickets.com
- በአካል ለመግዛት - አዝዋ ሆቴል፣ የተባበሩት፣ ዴፖ፣ አዲሱ መነሐርያ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ዓባይ ማዶ ያገኛሉ።
ድል ለኢትዮጵያ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
2 357
+8
በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ሁለተኛ የምድብ ጨዋታ በነገው ዕለት ሴኔጋልን የሚገጥመው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመጨረሻ ልምምዱን በባህር ዳር ስታዲየም አከናውኗል።
2 357
የኢትዮጵያ እና ሴኔጋል ጨዋታ የልምምድ መርሐ ግብር እና ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅታዊ መረጃ
- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ልምምድ 11:00 የሚጀምር ሲሆን የመጀመርያዎቹ ደቂቃዎች ክፍት መሆናቸውን እንገልፃለን። ልምምድ ከመጀመሩ አስቀድሞ ባሉ ደቂቃዎች ውስጥ አጭር የጋራ የሚዲያ ቆይታ ከሁለት የተመረጡ ተጫዋቾች ጋር ማድረግ ይፈቀዳል።
- የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን የልምምድ መርሐ ግብር 10:00 ላይ ይከናወናል።
- የሁለቱ ቡድኖች ቅድመ ጨዋታ ጋዜጣዊ መግለጫ ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ ይሰጣል።
2 357
+4
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን መረጃዎች
- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በብሉ ናይል ሪዞርት ሆቴል ማረፊያውን ያደረገ ሲሆን በዛሬው ዕለት የመጀመርያ ልምምዱን በባህር ዳር ስታዲየም አከናውኗል።
- መስፍን ታፈሰ ከሱዳን ጋር በተደረገው ጨዋታ የማስጠንቀቂያ ካርድ በመመልከቱ በሁለት ቢጫ ካርድ ቅጣት ምክንያት ከሴኔጋል ጋር ከሚደረገው ጨዋታ ውጪ ሆኗል።
- የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ምሽቱን ባህር ዳር ደርሷል። የልዑክ ቡድኑ ደጃዝማች በላይ ዘለቀ አየር ማረፍያ ሲደርስም አቀባበል ተደርጓላቸዋል።
- ኢትዮጵያ ከ ሴኔጋል የሚያደርጉትን ጨዋታ የስታዲየም መግቢያ ቲኬት በኦንላይን እየተሸጠ ይገኛል። ለመግዛት - https://eff-tickets.com
2 357
+3
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ባህር ዳር ደርሷል።
ቡድናችን ከደቡብ ሱዳን ረፋድ ላይ ተነስቶ አዲስ አበባ ከደረሰ በኋላ በቀጥታ ወደ ባህር ዳር በማምራት 11:30 ገደማ ባህር ዳር ደርሷል። ቡድኑ ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አየርአቀፍ አየር ማረፍያ ሲደርስ የኢ/እ/ፌ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ዳኛቸው ንግሩ (ዶ/ር)፣ የአማራ ክልል ባህልና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ መልካሙ ጸጋየ እና አመራሮች፣ የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ጎሹ እንዳላማው እና አመራሮች፣ የአማራ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሸን ፕሬዝዳንትና ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት፣ የባ/ዳ/ከ/አስ/ባ/ቱ/መምሪያ ኃላፊና ስራ ሂደት አስተባሪ፣ የባ/ዳ/ከ/እግር ኳስ ፌዴሬሸን ፕሬዝዳንት እንዲሁም የብሉ ናይል ሆቴል በጋራ ደማቅ አቀባበል አድርገዋል።
