1 739
订阅者
-124 小时
+17 天
-730 天
帖子存档
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የቴክኖሎጂ ሽግግር ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ስራ ሂደት በስሩ ለሚገኙ አሰልጣኝ መምህራን እንደ ተቋም በሂደቱ በኩል በወረደው ዕቅድ ዙሪያ የግንዛቤ ስልጠና ሰጠ::
ሂደቱ በዛሬው እለት ባዘጋጀው መድረክ ላይ የ2016 ዓ.ም የቴ/ሽ/ኢ/ኤ አገልግሎት ዕቅድ ዙሪያ በሂደቱ እስተባባሪዎች ሰፋ ያለ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና የተሰጠ ሲሆን በተጨማሪም የሂደቱ ፈፃሚ አሰልጣኝ መምህራን የግል እቅድ ዝግጅትና አተገባበር ላይም ያተኮረ ስልጠና ያካተተም ነበር::
የስልጠናው ተሳታፊ እሰልጣኝ መምህራንም በተሰጣቸው ስልጠና ላይ ያላቸውን ሀሳብ በማጋራት ውይይት ያደረጉ ሲሆን በመጨረሻም በስራ ሂደቱ ሃላፊ ማብራርያ ተሰቶባቸው መድረኩ ፍፃሜውን አጊኝቷል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
ጥቅምት 27/2016 ዓ.ም
现已上线!2025 年 Telegram 研究 — 年度关键洞察 
