es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

Ir al canal en Telegram
2 370
Suscriptores
+324 horas
+937 días
+36430 días
Archivo de publicaciones
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ በክቡር አቶ ዳንኤል ተሬሳ የተመራ ልዑክ ቡድን በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ድጋፋዊ ሱፐርቪዥን እና የስራ ጉብኝት አካሄደ:: ልዑካን ቡድኑ በኮሌጁ የተጀመሩ የሪፎርምና የመደበኛ ሥራዎች ተግባራዊነትን ለመከታተልና ለመደገፍ የሚያስችለውን ጉብኝ ለማድረግ እንደተገኘም ነው የተገለፀው:: በነበረው መርሃ-ግብርም የኮሌጁ ማኔጅመንት በኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ በኩል ለልዑካን ቡድኑ ባለፉት ስድስት ወራት በኮሌጁ የተከናወኑ የሪፎርም ስራዎችን በተለይም የትምህርትና ስልጠና፣የኢንተር ፕራይዝ ድጋፍ እንዲሁም የቴክኖሎጂ ልማትን በተመለከት ኮሌጁ ያለውን አፈፃፀም ትኩረት በማድረግ ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን የቀረበውን ሪፖርት መነሻ በማድረግም ከልዑካን ቡድኑ ጋር ውይይት ተደርጏል። በተጨማሪም ልዑካን ቡድኑ በኮሌጁ የሚገኙ ስልጠና የሚሰጥባቸውን ዲፖርትመንቶችና ወርክሾፖች ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን በዚህም የተለያዩ የለውጥ ስራዎችንና ፕሮጀክቶችን መመክከት ችለዋል:: የዚህ ድጋፋዊ ሱፐርቪዥን ዓላማም በትግበራ ወቅት የሚታዩ ማነቆዎችን ለመፍታት እና ድጋፍ የሚፈልጉ ሥራዎችን ለይቶ በመደገፍ በተቋማዊ አቅም ግንባታ፣ በክህሎት ልማት፣ ከቴክኖሎጂ ልማት እና የኢንዱስትሪ ግንኙነት ላይ የተቀመጡ ግቦች እንዲሳኩ መደላድል ለመፍጠር የሚያስችል ድጋፋዊ ጉብኝት መሆኑም ተመላቷል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ሚያዝያ 08/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1445ኛው የዒድ-አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ ይላል:: ዒድ-ሙባረክ
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1445ኛው የዒድ-አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ ይላል:: ዒድ-ሙባረክ

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በጎ አድራጎት ክበብ የረመዳን ፆምን ምክንያት በማድረግ ለአቅመ ደካሞች ድጋፍ አደረገ:: የበጎ አድራጎት ክበቡ ከኮሌጁ ጋር በመተባበር ይህን ድጋፍ ያደረገ ሲሆን በድጋፉም በማህበረሰቡ ጥቆማ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ተብለው ለተለዩ 20 እቅመ ደካሞችን የአስቤዛና የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ ተችሏል:: ክብቡ እንደገለፀውም ይህ ተግባር ቀጥሎም በጣይ ቀናት የዐቢይ ፆምን ምክንያት በማድረግ በተመሳሳይ ድጋፍ የሚደረግም ይሆናል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ህዝብ ግንኙነት መጋቢት 30/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ሰራተኞች የረመዳን ፆምን በማስመልከት የኢፍጣር መርሀ-ግብር አካሄዱ::      ይህ መርሃ-ግብር ድሬዳዋን በተለየ መልኩ የሀይማኖት አብሮነትና መደጋገፍ ያለባት ከተማ እንደሆነች የሚያጠናክር እንደሆነ የገለፁት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ አክለውም በዚህ በረመዳንና በዐቢይ ፆም ወቅት ያሳየነውን መደጋገፍና አብሮነት በስራችን ላይም በማጠናከር ውጤታማነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ አስታውሰው የዛሬውን የኢፍጣር መርሀ-ግብር ላዘጋጁና ለተሳተፉ የኮሌጁ ማህበረሰብ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።     በኢፍጣር መርሃ-ግብሩ ላይም የኮሌጁ አመራሮች፣ አሰልጣኝ መምህራንና አስተዳደር ሰራተኞች እንዲሁም ከተቋሙ ጋር በጋራ የሚሰሩ ባለድርሻ አካላትን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳታፊ ሆነዋል ። የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ህዝብ ግንኙነት መጋቢት 28/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አመራሮችና ሰራተኞች በዛሬው እለት በለገሐር አደባባይ ''ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም '' በሚል መሪ ቃል የተካሄደውን የድጋፍ ሰልፍ አካሄዱ፡፡

የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ  "ብቃት" የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት ሁለተኛ ዙር ትግበራ የመጀመሪያ ዙር የህይወት ክህሎት ስልጠና ያጠናቀቁ የሰልጣኞች የምርቃት መርሃግብር በኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ላይ በድምቀት ተካሄደ፡፡ በዚህም የሰልጣኞች የምርቃት መርሃግብር ላይ የቢሮው አመራሮች የተገኙ ሲሆን የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ ለሰልጣኞች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን በስልጠናው ያገኙትን እውቀት በቀጣይ በስራ ላይ ለሚኖራቸው ስልጠና እንዲጠቀሙበት በማሳሰብ የሚመጡ እና የሚገጥሟቸን ፈተናዎች በጥንካሬ በማለፍ ለራሳቸውና ለሃገራቸው የሚጠቅሙ ዜጎች እንዲሆኑ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ በቢሮው የሥራ ዕድል ፈጠራ እና አንድ ማዕከል ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት አቶ ሰኢድ አሊ  በበኩላቸው ባለፉት 10 ቀናት የህይወት ክህሎት ስልጠና በኮሌጆቹ ውስጥ ሲሰጣቸው የቆየ ሲሆን ይህንንም ሲያጠናቅቁ በመረጡት የሙያ ዘርፍ በአስተዳደሩ በሚገኙ አምራችና አገልግሎት ሰጪ ኢንደስትሪዎች ላይ የኪስ ገንዘብ እየታሰበላቸው በተግባር እየሰሩ እውቀትና ክህሎታቸውን የሚያዳብሩ እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡ በስልጠና ቆይታቸውም በኮሌጆቹ የህጻናት ማቆያ ቦታዎች ተዘጋጅቶላቸዋል በዚህም የልጅ እናት የሆኑ የፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎች ስልጠናውን ሳይስተጓጎሉ እንዲወስዱ መቻሉን በማስታወስ ለዜጎች ሁሉን ተደራሽ የሚያደርግ የስራ ዕድል ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስራዎች በመሰራት ላይ ለመሆናቸው ይህ መርሃግብር ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል። የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት መጋቢት 25/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የአድራ ኢትዮጵያ(ድሬዳዋ) ፕሮጀክት አመታዊ የአፈፃፀም ሪፖርት እና የኮሌጁ የ EASE ፕሮጀክት ማስጀመርያ ሰነድ ለኮሌጁ ቦርድ አቀረበ:: በዕለቱ በቅድሚያ በቀረበው ሪፖርት ስለ አድራ ኢትዮጵያ(ድሬዳዋ)ፕሮጀክት አላማ እና እስካሁን የተሰሩ ስራዋችን እንዲሁም ዘርፉ ያጋጠመውን ችግሮች እና መፍትሄዋቻቸው በፕሮጀክቱ ሀላፊዎች ለቦርድ አባላት በዝርዝር ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል:: በመቀጠልም በአድራ ኢትዮጵያ(ድሬዳዋ) የተሰራውን የSolar Labor Market እና በድሬደዋ TVT Agency አማካኝነት የተሰራውን የSolar PV Street Light Value Chain Analysis in DD City ለቦርድ አባላት በማቅረብ የGreen Tvt Approach ትኩረት እንዲያገኝ የሚያስችል ሰፊ ገለፃና ማብራሪያ ተሰጥቶበት የቀጣይ አቅጣጫዎችንም ተቀምጠዋል:: በመጨረሻም በመድረኩ የቀረበው የኮሌጁ የEASE ፕሮጀክት Strategic Investment Plan(SIP) የቀጣይ አምስት አመት የፕሮጀክቱን ማስጀመርያ ስራዎች ሰነድ ለኮሌጁ ቦርድ አባላት ለማፀደቅ በኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ የቀረበ ሲሆን የቦርድ አባላቱም የቀረበውን ሰነድ በጥልቀት ከገመገሙ በኃላ ሰነዱን በሙሉ ድምፅ በማፅደቅ መድረኩ ፍፃሜውን አጊኝቷል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፓሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን መጋቢት 23 2016 ዓ.ም

በብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት ተጠቃሚ ለመሆን በአስተዳደሩ የወረዳ አንድ ማዕከላት የተመዘገባችሁ ሰልጣኞች ከመጋቢት 16/2016 ዓ.ም ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት የህይወት ክህሎት ስልጠና የምትወስዱ ሲሆን ሰኞ ከጠዋቱ 2:00  የምትጀምሩ ይሆናል። በዚህም 👉 በወረዳ-1 አንድ ማዕከል 👉 በወረዳ-2 ዋናው አንድ ማዕከል 👉 በወረዳ-2 ቅርንጫፍ-1  አንድ ማዕከል የተመዘገባችሁ ወጣቶች ስልጠናችሁ በኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ሲሆን፤ ---------------------------------------------------------- 👉 በወረዳ-2 ቅርንጫፍ-2  አንድ ማዕከል 👉 በወረዳ-4  አንድ ማዕከል የተመዘገባችሁ ደግሞ በድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ ተገኝታችሁ ስልጠናውን የምትወስዱ ይሆናል። ማሳሰቢያ፡- የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ  እና 2 ፎቶ ግራፍ ይዛችሁ እንድትገኙ፡፡ የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ

Repost from N/a
photo content
+8