ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

前往频道在 Telegram
2 370
订阅者
+324 小时
+937 天
+36430 天
帖子存档
Repost from N/a
የዛሬ ውሎ ተጨማሪ ምስሎች ፎቶ- ከንቲባ ቢሮ

በስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር በክብርት ወ/ሮ ሙፈርሃት ካሚል የተመራው የፌደራል መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የሱፐርቪዥን ቡድን በዛሬው ዕለት በኮሌጃችን የመስክ ምልከታ አካሂዷል። የሱፐቪዥኑ ቡድን በ ኮሌጁ ሲደርስ በኮሌጁ አመራሮች ደማቅ አቀባበል የተደረገለት ሲሆን በነበራቸው ቆይታም በተቋሙ የተከናወኑና እየተሰሩ ያሉ የለውጥ ስራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል:: ኢትዮ-ጣሊያን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን መጋቢት 13.2016 ዓ.ም

የኢትዮ- ጣሊያን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የውጤት ተኮር ትምህርትና ስልጠና የስራ ሂደት በስሩ የሚገኙ ዲፓርትመንቶችና የስራ ክፍሎችን በተከለሰው የውጤት ተኮር አሰራር ሰነድ መሠረት የ2016 ዓ.ም የአንደኛ ተርም አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ አካሄደ።   በመድረኩ የሁሉም ዲፓርትመንት ተጠሪዎች ሪፓርታቸውን ያቀረቡ ሲሆን በቀረቡት ሪፓርቶች ላይም ከተከለሰው የውጤት ተኮር አሰራር ሰነድ አኳያ የታዩ ጠንካራ ጎኖችን እና ክፍተት የተስተዋለባቸው ተግባሮች ላይ በመድረኩ ሀሳቦች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል።     በዚህም በአፈፃፀም ወቅት የታዩ ጠንካራ ጎኖች በቀጣዩ ተርምም በተሻለ ጎልብተው እንዲቀጥሉ አፅዕኖት የተሰጠባቸው ሲሆን እንዲሁም በአፈፃፀም ወቅት የታዩ ክፍተቶች ላይ ትኩረት በመስጠትና ተቀናጅቶ በመስራት ትምህርትና ስልጠናውን በታለመለት አግባብ ለማስኬድም መግባባት ላይ ተደርሷል:: በተጨማሪም በዋና ስራ ሂደቱ በስሩ ለሚገኙ ክፍሎች ባለፉት ቀናት ሲያካሂድ የቆየውን የቴክኒካል ሱፐርቪዥን መርሃ-ግብር አጠናቆ ሪፖርት/ግብረመልስ የተሰጠበት ሲሆን በመጨረሻም እንደ ውጤት ተኮር ትምህርትና ስልጠና የስራ ሂደት የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ መድረኩ ፍፃሜውን አጊኝቷል። የኢትዮ-ጣሊያን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን መጋቢት 12.2016 ዓ.ም

Repost from N/a
photo content

Repost from N/a
photo content
+9

Repost from N/a
photo content
+9

Repost from N/a
በድሬዳዋ አስተዳደር የሳቢያን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች በኮሌጁ ጉብኝት አደረጉ። መጋቢት 10 2016 ዓ.ም       በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ቀደም ሲል ከተለያዩ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ጋር በተደረሰው የጋራ መገባባትና በተዘጋጀው የጋራ ዕቅድ መሰረት በዛሬው እለት የሳቢያን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የቴክኖሎጂ ክበብ አባል ተማሪዎችን በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በምህንድስና እና በሂሳብ ማለትም(STEM) ግንዛቤ ለማስጨበጥ በኢትዮ ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እንዲጎብኙ ተደጏል፡፡ በዚህም ተማሪዎቹ በኮሌጁ የተግባር ስልጠና የሚሰጥባችውን ዲፓርትመንቶች ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን በሰልጠና ክፍሎች የሚገኙ አሰልጣኝ መምህራንም ለጉብኝት ለመጡት ተማሪዎቹ የተግባር ስልጠና የሚስጥበትን ክፍሎች(workshops) በማስጎብኘት እንዲሁም በየዲፖርትመንቱ ስለሚሰጡ ሙያዎች በቂ ማብራሪያ እንዲያገኙ አስችለዋል:: በተጨማሪም ተማሪዎቹ በኮሌጁ ዲኖች ስለ ቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ተጨማሪ ግንዛቤ ማስጨበጫ ገለፃ የተደረገላቸው ሲሆን ተማሪዎቹም በኮሌጁ የተፈጠረላቸውን ግንዛቤ እንደ ቴክኖሎጂ ክበብ በሚማሩበት ት/ቤት ለሚገኙ ሌሎች ተማሪዎችም ግንዛቤ እንዲፈጥሩ ሃላፊነት ወስደው ጉብኝታቸውን አጠናቀዋል፡፡   ድሬዳዋ መጋቢት 10/2016 የኢትዮ ጣሊያን ኮምንኬሽን

የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሴት አመራሮችና ሰራተኞች ዘንድሮ በዓለም ለ133ኛ በሃገራችን ለ48 ጊዜ እየተከበረ የሚገኘው ዓለማቀፉ የሴቶች ቀንን "ሴቶችን እናብቃ፤ ልማትና ሰላምን እናረጋግጥ!" በሚል መሪ ቃል በተለያዩ መርሃ-ግብሮች አከበሩ፡፡ በመርሃ-ግብሩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፈቲህያ አደን በዓሉን ስናከብር የሴቶችን ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ በመስራት ሊሆን ይገባል ብላዋል፡፡ የቢሮው ም/ኃላፊና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ በበኩላቸው የሴቶችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነትና ተሳታፊነት ለማሳደግ በርካታ ስራዎች በመሰራት ላይ መሆኑን ጠቅሰው የሴቶችን ቀን በዓመት 1 ቀን ከማክበር ባሻገር የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነታቸውን በማረጋገጥ መሆን እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ በበዓሉ አከባበር ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፈቲህያ አደን፣ ም/አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ከሪማ አሊ እንዲሁም የአስተዳደሩ የፉይናስና ኢኮኖሚ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሙሉካ መሀመድ የተገኙ ሲሆን ልምድና ተሞክሯቸውን በሰፊው ለታዳሚዎች አካፍለዋል፡፡ የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት የካቲት 28/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ባለፋት ቀናት በስራ ሂደቶችና ስራ ክፍሎች ላይ ሲያካሂደው የቆየውን የ2016 ዓ.ም የመጀመርያ 6ወር አፈፃፀም ድጋፍና ክትትል ግብረ መልስና ማጠቃለያ ሪፖርት መድረክ አካሄደ:: በግብረ መልስ አሰጣጥ መድረኩ ላይ ድጋፍና ክትትል ሲደረግባቸው የነበሩ ዋና ስራ ሂደቶች እና ስራ ክፍሎች የተገኙ ሲሆን በዲን ፅ/ቤት የሚመራው የድግፍና ክትትል ቡድንም ትግበራውን በማጠናቀቅና ግብረ መልሶችን በማዘጋጀት በኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ ለተሳታፊዎች ቀርቧል:: በመድረኩ በቀረበው ማጠቃለያ ግብረ መልስም ዋና ስራ ሂደቶና ስራ ክፍሎች በድጋፍና ክትትል ወቅት ከተሰጣቸው ተልዕኮ አንፃር የታዩባቸውን ክፍተቶችና ጥሩ ተመኩሮዎች በዝርዝር በማስቀመጥ ግብረ መልስ መስጠት ተችሏል:: በተጨማሪም በሪፖርት መልክ ከተሰጠው ግብረ መልስ በተጨመማሪ ለሁሉም ስራ ሂደቶችና ስራ ክፍሎች በተደረገው ድጋፍና ክትትል መሰረት የፅሁፍ ግብረ መልስ የተሰጣቸው ሲሆን በዚህም የታዩ ክፍተቶችን በቀጣይ አፅኖት ሰተው ለመተግበር እንደ መነሻ ይሆናልም ተብሏል:: በመጨረሻም በተቋሙ ካሉት የስራ ሂደቶችና ክፍሎች በክትትልና ድጋፍ ወቅት በአንፃራዊነት ልቆ የተገኘው የ አይ.ሲ.ቲ ትምህርትና ስልጠና ክፍል በመድረኩ ለሌሎች የስራ ሂደቶችና ክፍሎች ተሞክሮውን እንዲያክፍል የተደረገ ሲሆን ይህም የስራ ክፍሎቹ በቀጣይ የነበሩ ውስንነቶችን በመቅረፍ እንደ ተቋም ለሚመዘገው ውጤት ጉልህ አስተዋፇ እንዲያበረክቱ እንደሚያግዝም ታምኖበታል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን የካቲት 27/2016 ዓ.ም

Repost from N/a
እንኳን ለ128ኛው የዓድዋ ድል በዓል አደረሰን!
እንኳን ለ128ኛው የዓድዋ ድል በዓል አደረሰን!

ላለፉት 2 ቀናት “ከዕዳ ወደ ምንዳ” በሚል ርዕስ የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ እና ሁለቱ የመንግስት ኮሌጅ አስተዳደር ሰራተኞች እና አሰልጣኝ መምህራን ሲሰጥ የቆየው የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቀቀ። የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው ስልጠናው በተለያዩ ሀገራዊ እና አስተዳደራዊ የመንግስት ነባራዊ ሁኔታዎችን መሰረት በማድረግ በተዘጋጁ የስልጠና ሰነዶች ዙሪያ ላይ ያተኮረ ሲሆን የመንግስት ሠራተኛውን አቅም በማጎልበት ኢትዮጵያ ብሎም አስተዳደሩ ለጀመሩት የእድገትና ለውጥ ጉዞ ወሳኝ ሚናቸውን እንዲወጡ የሚያስችላቸው ግንዛቤ እንዲይዙ የሚያስችል አቅም የተፈጠረበት ስልጠና ነው ብለዋል።  በተመሳሳይ የቢሮው ምክትል ኃላፊና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ የቢሮው የመንግሥት ሠራተኞች በአጠቃላይ ስልጠናው ሠራተኛው ራስን ከመምራት ጀምሮ ህዝብን በሚገባ ማገልገል እንዲችልና በሠራተኛው ዘንድ የተግባርና የሀሳብ አንድነት በማምጣት ቀጣይነቱ የተረጋገጠ ጥራት ያለውና ፍትሀዊ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችልና የሚያስረዳ ግንዘቤ መፍጠሩን ተናግረዋል። በስልጠናው ማጠናቀቂያ ሰልጣኝ የቢሮውና የኮሌጆች አስተዳደር ሠራተኞች እና አሰልጣኝ መምህራን በስልጠናው የቀረቡ ሰነዶች ላይ ግልጽነት የሚያስፈልጋቸውን ነጥቦች በማንሳትና በመጠየቅ ከመድረክ ሰፊ ማብራሪያ እና ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል በመጨረሻም ሰልጣኞች በተሰጣቸው የግንዛቤ ማጎልበቻ ስልጠና መደሰታቸውን ገልጸው መንግስት የጀመረውን እድገትና ለውጥ እንዲያስቀጥል በማሳሰብ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት የካቲት 7/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ