ch
Feedback
ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር

ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር

前往频道在 Telegram

Official ERA Telegram Channal በዚህ የቴሌግራም ቻናል የመንገድ ዜናዎችን የስራና የመንገድ ጨረታ ማስታወቂያዎችን የመንገድ ፎቶዎች እና አጫጭር ቪዲዮችን ያገኛሉ።

显示更多

📈 Telegram 频道 ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር 的分析概览

频道 ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር (@ethioroads) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 13 313 名订阅者,在 交通 类别中位列第 1 759,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 546

📊 受众指标与增长动态

невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 13 313 名订阅者。

根据 16 六月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 90,过去 24 小时变化为 8,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 40.85%。内容发布后 24 小时内通常能获得 15.40% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 5 439 次浏览,首日通常累积 2 050 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 17

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
Official ERA Telegram Channal በዚህ የቴሌግራም ቻናል የመንገድ ዜናዎችን የስራና የመንገድ ጨረታ ማስታወቂያዎችን የመንገድ ፎቶዎች እና አጫጭር ቪዲዮችን ያገኛሉ።

凭借高频更新(最新数据采集于 16 六月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 交通 类别中的关键影响点。

13 319
订阅者
+824 小时
+217
+9030
帖子存档
በድሬዳዋ - መልካ ጀብዱ መንገድ ፕሮጀክት የአስፋልት ንጣፍ እየተከናወነ ነው ድሬዳዋ፣ ግንቦት 22፣ 2017 (ኢ መ አ):- በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር 7 ነጥብ 2 ኪሎሜትር በሚረዝመው የድሬዳዋ - መልካ ጀብዱ መንገድ ፕሮጀክት የአስፋልት ንጣፍ እየተከናወነ ነው። የመንገድ ፕሮጀክቱ ከዚህ ቀደም በሀገር በቀል የሥራ ተቋራጭ ሲከናወን ቆይቶ ከወሰን ማስከበር ጋር በተያያዘ ችግር ግንባታው ተቋርጦ እንደነበር ይታወቃል። አሁን ላይ ችግሩ በመፈታቱ የግንባታውን ቀሪ 2 ነጥብ 1 ኪሎሜትር ሥራ ማጠናቀቅ እንዲቻል በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የድሬዳዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ፕሮጀክቱን ተረክቦ እየሠራ ይገኛል። በአሁኑ ወቅት ከአስፋልት ንጣፍ ሥራው በተጨማሪ የአፈር፣ የሰብቤዝ፣ ቤዝኮርስ እና የውኃ መፋሰሻ ቱቦ ሥራዎች በመከናወን ላይ ናቸው። የመንገድ ግንባታውን አበረታች አፈጻጸም በማስቀጠል በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ ዕቅድ ተቀምጦ በትኩረት እየተሠራ ይገኛል። በኮንክሪት አስፋልት ደረጃ እየተገነባ የሚገኘው የመንገድ ፕሮጀክቱ በሁለት አቅጣጫ መኪናዎችን ከማስተላለፉም ባለፈ የእግረኛ እና የብስክሌተኞች እንዲሁም የአረንጓዴ ሥፍራን ጨምሮ 50 ሜትር የጎን ስፋት ይኖረዋል። ለመንገድ ፕሮጀክቱ የተመደበው 1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በፌደራል መንግስት ይሸፈናል። ቤዛ ኢንጅነሪንግ ሊሚትድ ኬኒያ የማማከር እና የቁጥጥር ሥራውን ያከናውናል። የመንገዱ መገንባት የኅብረተሰቡን የመሠረተ-ልማት ጥያቄ ከመፍታቱም ባለፈ የድሬዳዋ ከተማን የማኅበራዊ እና የምጣኔ ሀብታዊ ዕድገት የሚያፋጥን ነው። በተጨማሪም መንገዱ ከድሬዳዋ ኢንዱስትሪ መንደር፣ ከኢትዮ - ጅቡቲ ምድር ባቡር ጣቢያ እንዲሁም ከድሬዳዋ ነጻ ንግድ ቀጠና ጋር የተገናኘ በመኾኑ የምጣኔ ሀብት ትስስሩን ያጠናክራል። መንገዱ በራስ-ኅይል እንደመገንባቱ መጠን በቀጣይ ለሚኖሩ ሥራዎች በርካታ ልምድ እና ተሞክሮ የተገኘበት መኾኑም ተመልክቷል። በተጨማሪም › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢሜል communication@era.gov.et › ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads

የጉደር-አምቦ ከተማ የመንገድ ፕሮጀክት በማጠናቀቂያ ምዕራፍ ላይ ይገኛል። በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ  የሚገኘው  የጉደር -አምቦ የአስፋልት  ኮንክሪት መንገድ እየተሰራ ሲሆን በአሁኑ ወቅት  የፕሮጀክቱ አጠቃላይ አፈጻጸም  88.66 በመቶ ደርሷል። ከጉደር ከተማ በመነሳት አምቦ ድረስ የሚዘልቀውን ይኸው የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ 19.132  ኪሎ ሜትር ይሸፍናል። በእስካሁኑ የመንገድ ግንባታ ስራ  የአስፋልት ንጣፍ፣ አፈር ቆረጣ እና ሙሌት ፣  የድሬኔጅ ስራዎች፣ ሰብ ቤዝ ንጣፍ ፣ ቤዝ ኮርስ ንጣፍ ፣ እንዲሁም የስትራክቸር ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛል። ለግንባታ  ማስፈጸሚያ የሚውለውን ገንዘብ  1,038,722,506.06 (አንድ ቢሊዮን፣ሰላሳ ስምንት ሚሊዮን፣ሰባት መቶ ሃያ ሁለት ሺህ፣አምስት መቶ ስድስት ብር፣ከስድስት ሳንቲም) ብር የሚሸፍነው  የኢትዮጵያ መንግስት ነው ። የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቱን እያከናወነ የሚገኘው  አገር በቀሉ ኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የስራ ተቋራጭ ሲሆን የማማከርና የቁጥጥር ስራውን ደግሞ ፕሮሚነንት ኢንጅነሪንግ ሶሉሽን እያከናወነው ይገኛል። መንገዱ ካለው ዘርፈ-ብዙ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ፋይዳ አንፃር በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ ነው እየተገነባ የሚገኘው ። የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ በጉደር ከተማ ያለውን ትልቅ የገበያ  ትስስር በመፍጠር አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ያደርጋል። መስመሩ ሀገር አቋራጭ የመንገድ መስመር በመሆኑ የጉዞ ጊዜን  በማሳጠር ወደሚፈለግበት መዳረሻ ለመድረስ ያስችላል።  ግንባታው ሲጠናቀቅ ቶኬ ኩታዬ ቀበሌዎችን እና በአምቦ ወረዳ ጉደር እና አምቦ ከተማን በአስፋልት ኮንክሪት የሚያገናኝ ይሆናል። ከዚህ ቀደም በተሽከርካሪ ለመጓዝ ይወስድ የነበረውን  የአርባ አምስት ደቂቃ  ግንባታው ሲጠናቀቅ ወደ ሃያ ደቂቃ በማሳጠር የጉዞ ጊዜን ያቀላጥፋል።  የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቱ  የጎን ስፋት ትከሻን ጨምሮ   በከተማ 23.8 ሜትር፣ ሲሆን በገጠር 19.5 ሜትር ስፋት እንዲኖረው ተደርጎ በመገንባት ላይ  ነው። በተጨማሪም › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢሜል communication@era.gov.et › ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads

20ኛው የዓለም የሥራ ድርጅት አህጉራዊ ጉባዔ ተጠናቀቀ አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2017 (ኢ መ አ):- ከግንቦት 11 - 15 በአዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየው 20ኛው የዓለም የሥራ ድርጅት አህጉራዊ ጉባዔ በስኬት ተጠናቅቋል። የዘንድሮው ጉባዔ በከተማ እና መሠረተ ልማት ሚንስቴር፣ በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር እና የዓለም አቀፉ የሥራ ድርጅት የጋራ ትብብር መካሄዱ ይታወቃል። በጉባዔው ማጠቃለያ ላይ በወጣው መግለጫ፣ ኢትዮጵያ የተሳካ ጉባዔ ማካሄዷ ተገልጿል። በሩዋንዳ ኪጋሊ በተካሄደው 19ኛው ጉባዔ ላይ የተነሱ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ምቹ የሥራ ምህዳር ላይ ያተኮሩ ጉዳዩች ላይ መድረኩ በስፋት ተወያይቷል። ከጥናት እና ውይይት በዘለለ በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ጤናማ የሥራ ከባቢ በመፍጠር እንዲሁም ማኅበራዊ ፍትህን በማረጋገጥ ረገድ የአፍሪካ ሀገራት በጋራ መሥራት እንደሚገባቸው የአቋም መግለጫው አሳስቧል። ከዚህም ባለፈ ብልሹ አሠራር እና ሙስናን እንዲሁም ኢ-ፍትሀዊነትን በመዋጋት ረገድ ሀገራቱ በጋራ መቆም እንደሚኖርባቸው ተጠቅሷል። በጉባዔው ላይ በርካታ ጠቃሚ ልምዶች መገኘታቸውን የገለጹት የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚንስትር ጫልቱ ሳኒ፤ ለተግባራዊነቱ ሁላችንም ኃላፊነት አለብን ብለዋል። ጉባዔው በስኬት እንዲጠናቀቅ ያልተቆጠበ ድጋፋቸውን ያደረጉትን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ የአፍሪካ ሕብረት፣ የዓለም ባንክ እና ሌሎች አጋር ድርጅቶችን ሚንስትሯ አመስግነዋል፡፡ ከ2ሺህ በላይ ተሳታፊዎች በዘንድሮው ጉባዔ የተካፈሉ ሲኾን፣ ከመድረኩ ጎን ለጎን በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ በርካታ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል ። በመጨረሻም ዛምቢያ ከሁለት ዓመት በኋላ የሚካሄደውን 21ኛውን የዓለም የሥራ ድርጅት አህጉራዊ ጉባዔ እንድታዘጋጅ በመድረኩ ተመርጣለች። በተጨማሪም › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢሜል communication@era.gov.et › ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads

ILO Regional Conference For Labor-Based Practitioners (Day 4) Live Stream https://www.youtube.com/live/zo6imcUBAW4?si=vlo66Ma6f8lxiV13

የጉባኤው ተሳታፊዎች በከተማዋ የተከናወኑ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19 ፣ 2017 (ኢ መ አ):- ሦስተኛ ቀኑን በያዘው የ20ኛው የዓለም አቀፉ የሥራ ድርጅት አህጉራዊ ጉባኤ ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ ከተማ የተከናወኑ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል። ከተለያዩ የዓለም ሀገራት የተውጣጡት ጎብኚዎቹ የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ፣ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን፣ የእንጦጦ ፓርክ እንዲሁም የኮሪደር እና የወንዝ ዳርቻ ልማት አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ ተዘዋውረው የጎበኙ ሲኾን፣ በከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ገለጻ ተደርጎላቸዋል። ጎብኝዎቹ በተደረገላቸው አቀባበል ያመሰገኑ ሲኾን፣ በምልከታቸውም ደስተኛ መኾናቸውን ተናግረዋል። በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በምርት ሂደት፣ በገበያ ትስስር እንዲሁም ከተማዋን ውብ እና ጽዱ ለማድረግ የተከናወኑ ተግባራትን አድንቀዋል ። በተለይም በአርንጎዴ ልማት በኩል የተሠሩ ሥራዎች በርካታ ልምድ የሚወሰድባቸው መኾኑን አንስተዋል። የሥራ ቦታን ለሠራተኛው ደኅንነት ምቹ እና ተስማሚ በማድረግ በኩል የተከናወኑ ሥራዎችም አመርቂ መኾናቸውን ጎብኘዎቹ ተናግረዋል። አህጉራዊ ጉባኤው በነገው ዕለትም በሚካሄዱ የተለያዩ ሁነቶች ቀጥሎ ይውላል። በተጨማሪም › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢሜል communication@era.gov.et › ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads

በአዲስ አበባ እየተካሄደ የሚገኘው 20ኛው የዓለም የሥራ ድርጅት በሥራ ላይ የተመሰረተ የባለሙያዎች ሌበር ቤዝድ ፕራክቲሽነርስ አህጉራዊ ጉባኤ እውነታዎች:- 👉 ጉባኤው በሁለት ዓመት አንዴ የሚካሄድ ሲኾን፣ በአዲስ አበባ እየተካሄደ የሚገኘውን የዘንድሮው ጉባኤ በዓለም አቀፉ የሥራ ድርጅት (ILO)፣ የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በጥምረት የተዘጋጀ ነው። 👉 የመጀመሪያው አህጉራዊ ጉባኤ የተካሄደው እ.ኤ.አ በ1990 በታንዛኒያ ነበር። 👉 ኢትዮጵያ 20ኛውን አህጉራዊ ጉባኤ እንድታዘጋጅ በከፍተኛ ድምጽ የተመረጠችው እ.ኤ.አ በ2023 በሩዋንዳ ኪጋሊ በተካሄደው ጉባኤ ወቅት ነበር። 👉 ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም እ.ኤ.አ በ2017 የተካሄደውን 17ኛውን አህጉራዊ ጉባኤ በድምቀት አስተናግዳለች። 👉 የዚህ ዓመት ጉባኤ "የማይበገር ማኅበረሰብ እና ጤናማ አካባቢ፦ የሰው ኃይልን በብዛት የሚጠቀሙ የኢንቨስትመንት ፕሮግራም አካሄዶች" በሚል መሪ ሐሳብ እየተካሄደ ይገኛል። 👉 በጉባኤው ላይ ሚንስትሮች፣ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ ተወካዮች፣ ዓለም አቀፍ የልማት አጋሮች፣ የሥራ ተቋራጮች እና አማካሪ መሀንዲሶች፣ እንዲሁም የዘርፉ ምሁራንን ጨምሮ በአጠቃላይ ከ1ሺህ 500 መቶ በላይ ተሳታፊዎች ይታደማሉ። 👉 የዘርፉ ተመራማሪዎች፣ ፖሊሲ አውጭዎች እና ባለሙያዎች በሳል የጥናትና ምርምር ሥራዎቻቸውን ያቀርባሉ። 👉 ከዋናው ጉባኤ በተጓዳኝ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ የጎን ለጎን ሁነቶች ይከናወናሉ። 👉 ጉባኤው ኢትዮጵያ በመሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ በአካባቢ ጥበቃ እንዲሁም በአካታች እና ዘላቂ ልማት ረገድ እያስመዘገበች ያለችውን ውጤት ለአፍሪካ እና ለዓለም ለማስተዋወቅ እድል የምታገኝበት ይሆናል። በተጨማሪም › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢሜል communication@era.gov.et › ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads ቀጥታ ለመከታተል https://www.youtube.com/live/U5nGTg-XaE4?si=f_9UIRFE1LHlH6PA