ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር
前往频道在 Telegram
Official ERA Telegram Channal በዚህ የቴሌግራም ቻናል የመንገድ ዜናዎችን የስራና የመንገድ ጨረታ ማስታወቂያዎችን የመንገድ ፎቶዎች እና አጫጭር ቪዲዮችን ያገኛሉ።
显示更多📈 Telegram 频道 ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር 的分析概览
频道 ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር (@ethioroads) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 13 971 名订阅者,在 交通 类别中位列第 1 696,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 547 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 13 971 名订阅者。
根据 25 十月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 146,过去 24 小时变化为 2,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 35.85%。内容发布后 24 小时内通常能获得 17.39% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 5 008 次浏览,首日通常累积 2 430 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 25。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“Official ERA Telegram Channal
በዚህ የቴሌግራም ቻናል
የመንገድ ዜናዎችን
የስራና የመንገድ ጨረታ ማስታወቂያዎችን
የመንገድ ፎቶዎች እና አጫጭር ቪዲዮችን ያገኛሉ።”
凭借高频更新(最新数据采集于 26 十月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 交通 类别中的关键影响点。
13 971
订阅者
+224 小时
+277 天
+14630 天
帖子存档
13 976
በ2018 በጀት ዓመት የ580 ኪሎ ሜትር አዳዲስ መንገዶች ግንባታ መከናወኑ ተገለጠ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም (ኢመአ)፦ በ2018 በጀት ዓመት የ580 ኪሎ ሜትር አዳዲስ መንገዶች ግንባታ እና 12 ሺህ 882 ኪሎ ሜትር የሚሸፍኑ የተለያዩ የመንገድ ጥገና ሥራዎች መከናወናቸው ተገለጸ። ተቋሙ የ2018 በጀት ዓመት አጠቃላይ አፈጻጸም እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድን አስመልክቶ በዓለምገና ኢንጅነሪንግ እና ማኔጅመንት ማሠልጠኛ ማዕከል ከአመራሮችና ከሠራተኞች ጋር አጠቃላይ ዓመታዊ የውይይት መድረክ አካሂዷል።
በተቋሙ ፕላንግና ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት በቀረበው ሪፖርት መሠረት፤ በበጀት ዓመቱ የ238 ኪሎ ሜትር የነባር መንገዶች ደረጃ ማሻሻል እንዲሁም የ16 ኪሎ ሜትር የነባር መንገዶች ማጠናከር ሥራዎች በስኬት ተከናውነዋል። ተቋሙ በበጀት ዓመቱ የምህንድስና ግዢ፣ የዲዛይን ፕሮጀክቶች እንዲሁም የተቋማዊ አቅም ግንባታ ተግባራትን ማከናወኑ ተገልጿል።
በተጨማሪም በበጀት ዓመቱ 24 የመንገድ ፕሮጀክቶች ሙሉ በሙሉ ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት የሆኑ ሲሆን፤ ከእነዚህም መካከል የኢተያ - አርሲ ሮቤ፣ የእስቴ - ስማዳ፣ የድሬዳዋ ባይፓስና ሽንሌ፣ የጅግጅጋ ከተማ ማለፊያ (ባይፓስ) መንገድ እንዲሁም የሳውላ - ቃቆ መንገድ ፕሮጀክቶች በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው። ተቋሙ በተያዘው አዲስ በጀት ዓመት ከ1 ሺህ 67 ኪሎ ሜትር በላይ አዳዲስ መንገዶችን ለመገንባት እና ከ16 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ የሚሸፍኑ የተለያዩ መንገዶችን ለመጠገን አቅዶ ወደ ተግባር መግባቱ ተመላክቷል።
የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር መሐመድ አብዱራህማን (ኢንጅነር) በወቅቱ ባስተላለፉት መልእክት፤ የ2018 በጀት ዓመት ተቋሙ የተመሠረተበትን 75ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓል በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ያከበረበት ልዩ የታሪክ ምዕራፍ መሆኑን አስታውሰዋል። ተቋሙ ባለፉት 75 ዓመታት ሰፊ የመንገድ መሠረተ-ልማት አውታሮችን በመዘርጋት ኢትዮጵያን እርስ በርስ ማስተሳሰር የቻለና ለአገሪቱ ሁለንተናዊ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የማይተካ የበኩሉን አስተዋጽኦ ያበረከተ መሆኑንም ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም፣ በ2019 በጀት ዓመት በመንገድ ዘርፉ የተጣሉትን አገራዊ ግቦች በውጤታማነት ለማሳካት የተጀመረው ተቋማዊ ሪፎርም ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር የአሠራር ሽግግሮችንና የዲጂታላይዜሽን በአግባቡ ከመተግበር ጎን ለጎን የሥራ ባህልንና የበጀት አጠቃቀምን በተጠያቂነትና በግልጽነት መንፈስ መምራት እንደሚገባ በጥብቅ አሳስበዋል፡፡
በተጨማሪ
› አጭር መልዕክት 8561
› ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770
› ድህረገጽ www.era.gov.et
› ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et
› ቴሌግራም https://t.me/ethioroads
› ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd
› ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads
› ኢሜል communication@era.gov.et
› ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads
13 976
የጎንጂ-ቆለላ አስፋልት መንገድ ፕሮጀክት 98.82 በመቶ አፈጻጸም ላይ ደረሰ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም (ኢመአ)፤ በጎንጂ ቆለላ ወረዳ የሚገነባው የቆሬ - አዲስ ዓለም የአስፋልት መንገድ ፕሮጀክት በአሁኑ ወቅት የ10.59 ኪሎ ሜትር ግንባታን በማጠናቀቅ 98.82 በመቶ አጠቃላይ አፈጻጸም ላይ ደርሷል። ከባህር ዳር ወደ ሞጣ በሚወስደው መንገድ ላይ ከምትገኘው ቆሬ ቀበሌ ተነስቶ ምስራቅ አቅጣጫ በመጓዝ ሂዳሴ መንደርን አቋርጦ አዲስ ዓለም ከተማ የሚገባው ይህ ፕሮጀክት፣ በአጠቃላይ 10.74 ኪሎ ሜትር ርዝመት አለው። ቀድሞ የነበረውን የጠጠር መንገድ ወደ አስፋልት ደረጃ የሚያሳድገው ይህ ግንባታ፣ የመንገዱ ስፋት በገጠር 10 ሜትር፣ በቀበሌ 12 ሜትር እንዲሁም በወረዳ 21.5 ሜትር ሆኖ እየተገነባ ይገኛል።
ግንባታው ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ሲሆን በአካባቢው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ አዲስ ተስፋ ይዞ ይመጣል። በተለይም አርሶ አደሩ በአካባቢው በስፋት የሚያመርታቸውን እንደ ጤፍ፣ ሰሊጥ፣ በርበሬና ማሽላ ያሉ የግብርና ምርቶችን ያለምንም እንግልት በወቅቱ ወደ ገበያ ለማቅረብና የቱሪዝም መዳረሻዎችን በቀላሉ ለማገናኘት ጉልህ ሚና ይኖረዋል። ከዚህም በላይ ነዋሪዎች ቀድሞ ለመጓጓዝ ይወስድባቸው የነበረውን የጉዞ ጊዜ በአንድ ሰዓት ያህል በማሳጠር የዕለት ተዕለት ህይወታቸውን ያቀልላቸዋል።
ይህ ታላቅ ተስፋ የተሰነቀበት ፕሮጀክት ግንባታው እስከአሁን ድረስ ያጋጠሙና በሥራው ፍጥነት ላይ ጫና ያሳደሩ እንደ የጸጥታ፣ እና የወሰን ማስከበር ችግሮች እንዲሁም የነዳጅ እጥረት ተግዳሮቶችን ቀርፎ አሁን ያለበት ደረጃ ደርሷል። ሥራው እንዳይቋረጥ ከተለያዩ የመንግስት አካላት ጋር በቅንጅት በመሥራት፣ ለግንባታው የሚሆን ነዳጅ በቅድሚያ እንዲያገኝ በማድረግና ከፍተኛ ክትትል በማድረግ የተከለሰው የፕሮጀክቱ ማጠናቀቂያ ቀን በጥቅምት ወር 2019 ዓ.ም እንዲሆን ተደርጓል።
የበጀት ፍሰቱን በተመለከተ ቫትን ጨምሮ ከ333 ሚሊዮን ብር በላይ የተመደበለት ሲሆን፣ የስራ ተቋራጭነቱን ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ሲያከናውነው የሃይዌይ ኢንጂነርስ ኤንድ ኮንሰልታንትስ ኃ/ተ/ግ/ማ ደግሞ የአማካሪነት ሚናውን እየተወጣ ይገኛል። ተቋራጩ አፈጻጸሙን እንዲያሻሽልና ቀሪ ሥራዎችን በተያዘው የበጀት ዓመት እንዲያጠናቅቅም በየደረጃው ከፍተኛ ክትትልና ድጋፍ እየተደረገለት ነው።
በአሁኑ ወቅት የጠረጋ፣ የአፈር ቆረጣና ሙላት፣ የሰብ ቤዝ፣ የቤዝ ኮርስ ንጣፍ እንዲሁም ሙሉ የ10.74 ኪሎ ሜትር የአስፋልት ንጣፍ ሥራዎች 100 በመቶ ሙሉ በሙሉ ተጠናቀዋል። በተጨማሪም የፍሳሽ ማስወገጃ (ድሬኔጅ) ሥራው 98.58 በመቶ ላይ የደረሰ ሲሆን፤ እንደ እግረኛ መንገድና የመንገድ ምልክቶች ያሉ ቀሪ ሥራዎችንም 50 በመቶ በማድረስ ፕሮጀክቱን ሙሉ በሙሉ ወደ ማጠናቀቂያው ምዕራፍ ለማሸጋገር የመጨረሻ ደረጃ ሥራዎች በከፍተኛ ፍጥነት እየተከናወኑ ይገኛሉ።
በተጨማሪ
› አጭር መልዕክት 8561
› ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770
› ድህረገጽ www.era.gov.et
› ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et
› ቴሌግራም https://t.me/ethioroads
› ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd
› ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads
› ኢሜል communication@era.gov.et
› ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads
13 976
9ኛው የመንገድ ጥናትና ሥርፀት ኮንፈረንስ ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22/2018 ዓ.ም(ኢመአ): የመንገድ ልማትና አስተዳደር ሥራዎችን በሳይንሳዊ ምርምርና በቴክኖሎጂ ለማገዝ የተዘጋጀው 9ኛው የመንገድ ጥናትና ሥርፀት ኮንፈረንስ ተካሂዷል።
በኮንፈረንሱ መክፈቻ ላይ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር መሀመድ አብዱራህማን፣ የፕሮጀክት ዴቨሎፕመንት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሂሩት ዮሐንስ እና የቀድሞው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዛይድ ወልደገብርኤልን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የዘርፉ ባለሙያዎችና ተመራማሪዎች ተገኝተዋል።
ባለፉት ስምንት ዓመታት የተካሄዱት ተከታታይ የምርምር ኮንፈረንሶች በሀገሪቱ የመንገድ ልማት ላይ ውጤታማ ለውጦችን ማምጣት ችለዋል። በአሁኑ 9ኛ ኮንፈረንስም በርካታ ጥናታዊ ጽሑፎች የቀረቡ ሲሆን፣ ተያያዥ አውደርዕይም ተካሂዷል። በጥናቶቹ በሌሎች አገራትና ፕሮጀክቶች ላይ ተተግብረው ውጤታማ የሆኑ የመንገድ ግንባታና አስተዳደር ልምዶች የተዳሰሱ ሲሆን፣ እነዚህ ተሞክሮዎች ለሀገሪቱ የመሠረተ ልማት ዕድገት አዳዲስ ዕድሎችን ይዘው ይመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በተለይም በአሁኑ ወቅት በዘርፉ ላይ ፈተና እየሆኑ ያሉትን እንደ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ እና የመንገድ መሸራተት (ናዳ) ያሉ ዋና ዋና ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ ተግባራዊ የመፍትሔ ሐሳቦች በኮንፈረንሱ ላይ በስፋት ተመክሮባቸዋል። ከተቀመጡት የመፍትሔ አቅጣጫዎች መካከልም ዘላቂነትን ለማረጋገጥ በሲሚንቶ ኮንክሪት በሚሠሩ መንገዶች ላይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሠራ በጥናት ተመልክቷል።
በመድረኩ የተሳተፉ ባለሙያዎች በኮንፈረንሱ ያገኟቸውን አዳዲስ ዕውቀቶች፣ ቴክኖሎጂዎችና ፈጠራዎች በመጠቀም በመንገድ ግንባታ፣ ዲዛይን፣ ጥገና እና አስተዳደር ሥራዎች ላይ የላቀ ሙያዊ አስተዋጽኦ ያበረክታሉ ተብሎ ይታመናል።
በተጨማሪ
› አጭር መልዕክት 8561
› ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770
› ድህረገጽ www.era.gov.et
› ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et
› ቴሌግራም https://t.me/ethioroads
› ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd
› ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads
› ኢሜል communication@era.gov.et
› ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads
13 976
የጣርማበር - መለያያ ሰፌድ ሜዳ የጠጠር መንገድ ጥገና እየተካሄደለት ነው
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21/2018 (ኢመአ)፦ ከጣርማበር መለያያ እስከ ሰፌድ ሜዳ ለሚዘልቀው የጠጠር መንገድ ጥገና እየተደረገለት ይገኛል። ጥገናው የሕዝቡን የትራንስፖርት ችግር ለማቃለል ታስቦ በትኩረት እየተከናወነ ያለ ሥራ ነው።
ይህ አጠቃላይ 118 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ ያለው የመንገድ ፕሮጀክት፣ ከዚህ ቀደም በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ አማካኝነት ግንባታው ሲካሄድ የነበረ ቢሆንም በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ሳይጠናቀቅ ተስተጓጉሎ ቆይቷል። በአሁኑ ወቅት ግን ለትራንስፖርት እጅግ አስቸጋሪ በሆነው 21.6 ኪሎ ሜትር የመንገዱ ክፍል ላይ ሰፊ የጥገና ሥራ እየተሠራ ይገኛል።
እስካሁንም በማሽን የቦይ ማጽዳት፣ የድንጋይ ሙሌት፣ በጭቃ የተበላሹ አካባቢዎችን የማስወገድ እንዲሁም በግሬደር የመንገዱን አካል የማስተካከልና የማጠናከር ሥራዎች ተከናውነዋል። የጥገና ሥራውን የኢመአ የዓለምገና መንገድ ጥገና ዲስትሪክት በራስ ኃይል እያከናወነው ሲሆን፣ የማማከርና የቁጥጥር ሥራውን ደግሞ የዓለምገና መንገድ ኔትወርክ ማኔጅመንት ቅርንጫፍ ቢሮ በበላይነት እየተከታተለው ነው።
የዚህ መንገድ መጠገን ማኅበረሰቡን ለእንግልትና ለትራንስፖርት መጉላላት ከዳረጉ ችግሮች የሚያላቅቅ ሲሆን፣ የትራፊክ አደጋን ከመቀነስና ጊዜን ከመቆጠብ ባሻገር የግብርና ምርቶችንና የተለያዩ ግብዓቶችን ወደ ገበያ ለማቅረብ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።
በቀጣይም ከዚህ ቀደም ይስተዋሉ የነበሩ ማነቆዎችን በመቅረፍ ሙሉ የግንባታ ሒደቱን በቀጣዩ በጀት ዓመት ለማቀላጠፍ በትኩረት እየተሠራ ነው።
በተጨማሪ
› አጭር መልዕክት 8561
› ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770
› ድህረገጽ www.era.gov.et
› ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et
› ቴሌግራም https://t.me/ethioroads
› ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd
› ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads
› ኢሜል communication@era.gov.et
› ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads
13 976
የሶዶ መንገድ አውታር አስተዳደር የ2018 በጀት ዓመት 1,890 ኪሎ ሜትር የመንገድ ጥገና አከናወነ፤ አፈጻጸሙም 96.3% ሆኖ ተመዝግቧል
ሶዶ፣ ነሐሴ 18 ቀን 2016 ዓ.ም(ኢመአ): በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ስር የሚገኘው የሶዶ መንገድ አውታር አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት በ2018 በጀት ዓመት ያቀዳቸውን የፊዚካልና የፋይናንሻል የሥራ ግቦች በስኬት አጠናቀቀ። ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ በበጀት ዓመቱ በአጠቃላይ 1.81 ቢሊዮን ብር በጀት መድቦ የነበረ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 1.56 ቢሊዮን ብሩን (86.18%) ለተለያዩ የጥገናና መሰረተ ልማት ሥራዎች ማዋል ችሏል።
በፊዚካል አፈጻጸም ረገድም ከተቀመጠው 1,963 ኪሎ ሜትር የጥገና ዕቅድ ውስጥ 1,890 ኪሎ ሜትር በማጠናቀቅ 96.3% አፈጻጸም አስመዝግቧል።
ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ በአሁኑ ወቅት በአጠቃላይ 3,242.5 ኪሎ ሜትር የመንገድ ሽፋን ያስተዳድረል፡፡ ከዚህም ውስጥ 68 በመቶው (2,196.5 ኪ.ሜ) የአስፋልት ኮንክሪት ሽፋን ሲሆን ቀሪው 32 በመቶው (1,046 ኪ.ሜ) በጠጠር የተሸፈነ መንገድ ነው። በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ ዋና ዋና የጥገና ሥራዎች ዝርዝር አፈጻጸም እንደሚከተለው ቀርቧል፡-
መደበኛ ጥገና፡ በበጀት ዓመቱ በከፍተኛ ትኩረት የተከናወነ ሲሆን በፋይናንሻል በኩል ከተመደበው 920.46 ሚሊዮን ብር በላይ 983.30 ሚሊዮን ብር (106.83%) ወጪ ተደርጎበታል። በፊዚካል በኩልም 1,731.02 ኪ.ሜ መንገድ በመጠገን የ98.33% አፈጻጸም ታይቷል።
ወቅታዊ ጥገና፡ በቅርንጫፉ የራስ ኃይልና በግል ተቋራጮች በጋራ የተከናወነ ሲሆን፣ በአጠቃላይ 445.41 ሚሊዮን ብር ወጪ በማድረግ 157.57 ኪሎ ሜትር መንገድ ወቅታዊ ጥገና ተደርጎለታል።
ከባድ ጥገና፡ 1.20 ኪሎ ሜትር መንገድ የተጠገነ ሲሆን 67.03 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበታል።
የድልድይ መልሶ ግንባታ፡ ከተመደበው 3.23 ሚሊዮን ብር በጀት 100% ሙሉ በሙሉ ጥቅም ላይ በመዋል ተጠናቋል።
የደህንነትና የመሬት ናዳ መከላከል፡ ለድንገተኛ አደጋዎችና ለመሬት ናዳ መከላከያ ሥራዎች ከ44 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገ ሲሆን፣ የአካባቢው ማህበረሰብ ከአደጋ ስጋት ነጻ እንዲሆን አስችሏል።
ጽሕፈት ቤቱ በበጀት ዓመቱ የተለያዩ የግብዓት እጥረቶች ቢያጋጥሙትም፣ የኪራይ መሣሪያዎችን በመጠቀምና የውስጥ አቅምን (የራስ ኃይልን) በማጠናከር ችግሮቹን መፍታት ተችሏል። ለ2019 በጀት ዓመትም በበጀት ዓመቱ የተገኙ መልካም ተሞክሮዎችን (የቡድን ሥራ፣ የሠራተኞች መዝናኛና የሕፃናት ማቆያ ግንባታዎችን ማጠናቀቅን ጨምሮ) እንደ ግብዓት በመውሰድ ለዋና ዋና መንገዶች (Trunk Roads) ልዩ ትኩረት በመስጠት ለመስራት ታቅዷል።
በተጨማሪ
› አጭር መልዕክት 8561
› ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770
› ድህረገጽ www.era.gov.et
› ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et
› ቴሌግራም https://t.me/ethioroads
› ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd
› ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads
› ኢሜል communication@era.gov.et
› ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads
13 976
የቢሻን ጉራቻ - ሐዋሳ ኃይሌ ሪዞርት መገንጠያ መንገድ መልሶ-ግንባታ ፕሮጀክት በትኩረት እየተከናወነ ነው
ሐዋሳ፣ ነሐሴ 12/2018 (ኢ መ አ)፦ በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በሻሸመኔ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት በራስ-ኃይል እየተገነባ የሚገኘው የቢሻን ጉራቻ – ሐዋሳ ኃይሌ ሪዞርት መገንጠያ የመንገድ መልሶ-ግንባታ ፕሮጀክት አፈጻጸም 40 በመቶ መድረሱ ደርሷል።
ይህ 1.1 ኪሎ ሜትር ርዝመት እና 26 ሜትር ስፋት ያለው የመንገድ ፕሮጀክት፤ በሐዋሳ ከተማ መግቢያና መውጫ እንዲሁም በሐዋሳ ሐይቅ ዳርቻ አካባቢ ቀደም ሲል በክረምት ወቅት ይታዩ የነበሩትን የጎርፍ መጥለቅለቅ፣ የውኃ ክምችት እና የመንገድ መበላሸት ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ያለመ ነው። በአካባቢው ከሐይቁ አቅጣጫ የሚመጣው ውሃ ነባሩን የመንገድ መዋቅር አልፎ መሄድ ባለመቻሉ፣ መንገዱ በውሃና በደለል ተውጦ ለነዋሪዎችና ለተሽከርካሪዎች ከፍተኛ ችግር መፍጠሩ ይታወሳል። ይህም በከተማዋ የቱሪስት መስህብ ገጽታና ውበት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ አሳድሮ ቆይቷል።
ይህንን የጎርፍ መጥለቅለቅ ችግር ለመቅረፍ የመንገዱ ከፍታ ከቀድሞው በ2 ሜትር ከ40 ሴንቲሜትር ከፍ እንዲል ተደርጎ እየተገነባ ይገኛል። በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ የሙሌት፣ የኮሪደር እና የውኃ ማፍሰሻ ሥራዎች በትኩረት እየተከናወኑ ናቸው።
በሰኔ ወር 2018 ዓ.ም አጋማሽ ላይ በሙሉ አቅም የተጀመረው ይህ ግንባታ በአጭር ጊዜ ውስጥ 40 በመቶ አፈጻጸም ላይ ደርሷል። የነዳጅ እና የግብዓት እጥረት ተጽዕኖዎች ቢኖሩም፥ ዋና ዋና ሥራዎችን እስከ መስከረም ወር 2019 ዓ.ም ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሠራ ይገኛል። ለዚህ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ በፌደራል መንግሥት 334 ሚሊዮን ብር በጀት የተመደበለት ሲሆን፥ እስከአሁን ለ200 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር ችሏል።
የመንገድ ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ በክረምት ወቅት ያጋጥም የነበረውን የትራፊክና የእግረኛ መስተጓጎል በዘላቂነት ይቀርፋል። ከዚህም ባለፈ፣ ውብ በሆነው የሐዋሳ ሐይቅ ዳርቻ ላይ የሚገኝ በመሆኑ የከተማዋን የቱሪዝም፣ የኮንፈረንስ እና የኢንቨስትመንት ማዕከልነት ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግረዋል ተብሎ ይጠበቃል።
በተጨማሪ
› አጭር መልዕክት 8561
› ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770
› ድህረገጽ www.era.gov.et
› ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et
› ቴሌግራም https://t.me/ethioroads
› ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd
› ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads
› ኢሜል communication@era.gov.et
› ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads
