ch
Feedback
EEP Communication

EEP Communication

前往频道在 Telegram

EEP Communication

显示更多

📈 Telegram 频道 EEP Communication 的分析概览

频道 EEP Communication (@eepcommuication) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 15 533 名订阅者,在 技术与应用 类别中位列第 8 368,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 174

📊 受众指标与增长动态

невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 15 533 名订阅者。

根据 30 六月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 10,过去 24 小时变化为 -6,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 24.86%。内容发布后 24 小时内通常能获得 16.87% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 3 862 次浏览,首日通常累积 2 620 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 9

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
EEP Communication

凭借高频更新(最新数据采集于 01 七月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 技术与应用 类别中的关键影响点。

15 533
订阅者
-624 小时
-207
+1030
帖子存档
photo content
+3

በሪጅኑ በኤሌክትሪክ ተሸካሚ ምሰሶዎች ላይ በተፈፀመ ሥርቆት ከ 9 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ኪሳራ ደርሷል ……..///…….... በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማዕከላዊ ሪጅን 1 የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች መምሪያ በሚያስተዳድራቸው የከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ተሸካሚ ምሰሶዎች ላይ በተፈፀመ ሥርቆት ከ9 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ኪሳራ ደረሰ፡፡ መምሪያው እንዳስታወቀው በአዲስ አበባ ከተማ እና በዙሪያው በሚገኙ የከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ ምሰሶዎች ላይ በበጀት ዓመቱ ሦስት ወራት ውስጥ 1 ሺህ 771 ብረቶች እና 7 ሺህ 84 ብሎንና የብሎን ማሰሪያዎች በሌቦች ተሰርቀዋል፡፡ ሥርቆቱ በዋናነት የተፈጸመው ከገጣፎ - ቃሊቲ እና ከለገጣፎ - ሱልልታ በተዘረጉ ባለ 230 ኪሎ ቮልትመስመሮች እንዲሁም ከቃሊቲ - ገፈርሣ እና ከቃሊቲ - ወረገኑ በተዘረጉ ባለ 132 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ ነው፡፡ በዚህም ተቋሙ በ3 ወር ውስጥ ብቻ በተፈፀመ ስርቆት ምክንያት የተቋረጠውን የኢነርጅ መጠን ሳይጨምር ጉዳት ለደረሰባቸው የተለያዩ የኃይል ተሸካሚ ምሰሶ አካላት መልሶ መተኪያ 8 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር ወጪ ማድረጉን ገልጿል፡፡ በጥገና ወቅት የሚያስፈልጉ የጉልበት ሠራተኛ፣ የነዳጅና የተለያዩ ግብዓቶችን ለማሟላት ደግሞ 720 ሺህ ብር ወጪ ማድረጉን ያስታወቀው ሪጅኑ ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ በኤሌክትሪክ መሰረተልማት ስርቆት ከ9 ሚሊዮን ብር በላይ ኪሳራ መድረሱን መምሪያው አመልክቷል፡፡ የመምሪያው ዳይሬክተር አቶ ወንደሰን ወልደማርያም በሰጡት አስተያየት የከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ ምሰሶዎችና ሽቦዎች ስርቆትን ለመከላከል በሚደረገው እንቅስቃሴ የፀጥታ አካላት ምላሽ ፈጣን አለመሆን ችግሩ እንዲባባስ ምክንያት ሆኗል። ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ተከሰው በሚቀርቡ ወንጀለኞች ላይ የፍትህ አካላት የሚጥሉት ቅጣት አስተማሪ አለመሆኑና ግብዓት ለማግኘት ሲሉ ስርቆቱን የሚደግፉና የሚረከቡ የብረታ-ብረት ፋብሪካዎችና ባለሀብቶች እንቅስቃሴ ሊፈተሽ እንደሚገባም ዳይሬክተሩ አሳስቧል፡፡ "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@Ethiopianelectricpower ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ጥቅምት 08 ቀን 2016 ዓ.ም

photo content
+1

photo content
+9

የፕሮጀክቱ አጠቃላይ አፈጻጸም 82 በመቶ ደርሷል .......////....... ለአዋሽ- ወልዲያ- ሀራ ገበያ የባቡር መስመር የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ በመገንባት ላይ የሚገኘውን የማስተላለፊያ መስመር እና ማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክት በተያዘው በጀት ዓመት ለማጠናቅ እየተሰራ መሆኑን የፕሮጀክቱ የሳይት ሥራ አስኪያጅ ገለፁ። ሥራ አስኪያጁ አቶ ተክለወይኒ ብርሃነ እንደገለፁት በፕሮጀክቱ ላይ 206 ነጥብ 6 ኪሎ ሜትር የማስተላለፊያ መስመር ግንባታ እና በመተሃራ፣ በደብረ ብርሃን፣ በሸዋ ሮቢት እና በከሚሴ ማከፋፈያ ጣቢያዎች ላይ የማስፋፊያ ሥራዎች ይከናወናሉ። በፕሮጀክቱ ላይ ከሚተከሉ 553 የማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ ምሶሶዎች መካከል የ175 ምሶሶዎች ተከላ እና የ427 የምሰሶ መትከያ የመሠረት ቁፋሮ ሥራዎች መከናዎናቸውን አቶ ተክለወይኒ ተናግረዋል፡፡ የማከፋፈያ ጣቢያዎቹ የማስፋፊያ ሥራ መጠናቀቁን የገለፁት ሥራ አስኪያጁ የባቡር ጣቢያዎችን (Traction Station) ከተቋሙ የብሔራዊ የኃይል ቋት ጋር የሚያገናኙ የኮሙዩኒኬሽን መሳሪያዎችን ለማስቀመጥ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ፈቃድ እየተጠበቀ እንደሚገኝም አብራርተዋል፡፡ እንደ አቶ ተክለወይኒ ገለፃ ለፕሮጀክቱ ግንባታ ሥራ ከሚያስፈልጉ ዕቃዎች ውስጥ 84 ነጥብ 1 በመቶ የሚሆነው ተመርቶ ወደ ፕሮጀክቱ ሳይት የገባ ሲሆን የካሳ ክፍያ ሥራው ደግሞ 96 በመቶ ተጠናቋል፡፡ የማከፋፈያ ጣቢያዎቹ የሙከራና የፍተሻ ሥራ በቅርቡ እንደሚከናወን ያነሱት አቶ ተክለወይኒ በአሁኑ ወቅት የፕሮጀክቱ አጠቃላይ አፈፃፀምም 82 በመቶ ደርሷል ብለዋል፡፡ እንደ ሥራ አስኪያጁ ገለፃ በምድር ባቡር በኩል የሚከናወኑ የትራክሽን ጣቢያዎች ግንባታ አለመጠናቀቅና ወደ ተጠናቀቁ ጣቢያዎች ለመግባት የመግቢያ ፈቃድ አለመገኘቱ በፕሮጀክቱ የግንባታ እንቅስቃሴ ላይ ችግር እየፈጠረ ነው፡፡ ፕሮጀክቱን በማጠናቀቅ ለባቡር መስመሩ አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ በኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን በኩል የሚከናወኑ ሥራዎች በወቅቱ ሊፈጸሙ እንደሚገባ አቶ ተክለወይኒ ጠቁመዋል፡፡ ከመተሃራ ማከፋፈያ ጣቢያ አስከ አዋሽ ብሔራዊ ፓርክ ድረስ ያለው የፕሮጀክቱ ሥራ በአካባቢው ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት ለአንድ ዓመት ያህል ተቋርጦ መቆየቱን ያስታወሱት አቶ ተክለወይኒ የግንባታ ሥራውን ለማስቀጠል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መግባባት ላይ በመደረሱ ተቋራጩ በቅርቡ ሥራውን እንደሚጀምር አስታውቀዋል፡፡ ፕሮጀክቱን በተያዘው በጀት ዓመት ለማጠናቅ ርብርብ እየተደረገ ቢሆንም በፕሮጀክቱ ላይ እየተፈፀመ ያለው ስርቆት እና በአንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋለው የፀጥታ ችግር በተያዘለት መርሃ ግብር ለማጠናቀቅ እንቅፋት ሊሆኑ እንደሚችል ተናግረዋል። የፕሮጀክቱን የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ግንባታ ፒንጋኦ ግሩፕ (Pinggao Group) እንዲሁም የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች የማስፋፊያ ሥራን ቲ.ቢ.ኤ (TBEA,Co.Ltd) የተሰኙ ሁለት የቻይና ኩባንያዎች እያከናወኑት የሚገኝ ሲሆን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኢንጂነሪንግ የሥራ ክፍል ደግሞ በማማከር ሥራው ላይ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡ የፕሮጀክቱ የፋይናንስ ወጪ ከ16 ነጥብ 85 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር እና ከ174 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ሲሆን የፋይናንስ ወጪው ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የሚሸፈን ነው፡፡ "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@Ethiopianelectricpower ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ጥቅምት 07 ቀን 2016 ዓ.ም

photo content
+1