የጥበብ ማዕድ
前往频道在 Telegram
📈 Telegram 频道 የጥበብ ማዕድ 的分析概览
频道 የጥበብ ማዕድ (@yetbebmead_ab) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 16 293 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 5 235,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 082 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 16 293 名订阅者。
根据 07 七月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 611,过去 24 小时变化为 -4,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 2.54%。内容发布后 24 小时内通常能获得 2.06% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 413 次浏览,首日通常累积 335 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 12。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“ዝም ብለህ ተቀላቀል!”
凭借高频更新(最新数据采集于 08 七月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。
16 293
订阅者
-424 小时
+1507 天
+61130 天
帖子存档
16 308
አንዳንድ የባስ ሹፌሮች ህዝቡን ሲያሳፍሩ ሳይሆን ሲያሯሩጡ ነው መሰል ስራ የሠሩ ሚመስላቸው! ደግሞ እንደዛም ተሮጦ ጥለውት ሚሔዱት ነገር!😕
16 308
፡
Code 10 - bible
ምን ላርግልሽ
ፈገግታሽ እንዳይነጥፍ
እምባሽ እንዳይረግፍ
የልብሽ ሃዘንሽ በርትቶ
ቅስም እንዳያሳጣሽ ከቶ
ምን ላርግልሽ
ምኔን ልለግስሽ
ጥርሴን ልስጥሽ እንድትስቂ የኔንም?
ልቤን ልስጥሽ እንድታይ ሁለት ዓለም?
ሰባሪ ሲመጣ ልብን የሚያጨልም
ያንቺን ተንከባክበሽ የኔ እንዲቀድም?
አይኔንስ ትወስጂው እምባሽ ከመጣ?
የኔን አሞጭሙጨሽ ያንቺ ለዛን እንዳያጣ
ምኔን ልስጥሽ
እሺ ወይም ውሰጂው እምነቴን ላንቺ
የኔን እንድትሰጪያቸው እንዳይጠፋ ያንቺ
ቆይ ምኔን ልስጥሽ ምኔ ይገባሻል
ሃዘን መከራሽን ምኔ ይወስድልሻል
እስኪ ይሄን ስጠኝ በይ አይተሽ ከሁሉ
ላንቺ ቀርቧል አካሌ ከታህት እስከ ላእሉ
........
ወይ ደሞ ሞክሪ እስኪ እኔን ወስደሽው
ክፉው ሲመጣ ይውሰደው ከፊት እያረግሽው
16 308
፡
Code 9 - Mahlet
ሀገሬ ኢትዮጵያ እንዴት ነሽ ልበልሽ
እያየው ስትሆኚ ልጆች እንደሌለሽ
ልጆችሽ ሆነን የእናት ጡት ነካሽ
እርስ በርሳችን እየተበላላለን
እርስ በርሳችን እየተወቃቀስን
እየኖርን ነው እርስ በርሳችን እየተገዳደ
አሁንም ሀገሬ ይሉሻል በማደግ ላይ ያለሽ
ግን አይቀርም አንድ ቀን አደገች መባልሽ
በአድዋ ሜዳ የፈሰሰው ያባቶቻችን ደም
ሳይፈሩ ተዋግተው ብለው ኢትዮጲያ ትቅደም
አኖሩሽ አቆሙሽ አጥንታቸውን ከስክሰው
ግና ምን ያረጋል ይህ ሁሉ ልፋታቸው
መና መቅረቱ ነው በገዛ ልጆቻቸው
እንኳን ሊዋጉ ኢትዮጵያ ትቅደም ብለው
አቃታቸው መኖር እርስ በርስ ተዋደው
ትንሳኤሽን ያሳየን
16 308
፡
Code 8 - Eldana
ቢሆን ኖሮ
ቢሆን ኖሮ ብዬ አስባለሁ
ያኔ ባደረኩት ብዬ አብሰለስላለው
በራሴው ምክንያት አዝናለው
እራሴው ባደረኩት ነገር እወቃቀሳለው
ምን ይሻለኝ ይሆን ምን ይሆን ትዝብቴ
ቢሆን ኖሮ ብዬ ሆነብኝ ፀፀቴ
ቢሆን ኖሮ ማለት የኋላ ህልም ነው
ቢሆን ኖሮ ማለት ያለፈ ነገር ነው
ቢሆን ኖሮ እያሉ በልብ ከመቆጨት
በሱ ቦታ የወደፊት ህልምን ቢያስቡበት
፡
16 308
አንዳንዴ እብዶች ተብዬ የልባችንን እውነት ሲናገሩ ከስንት አንዴ ጤነኛ እንደሆኑ እናስባለን! ግን እለት በእለትስ የሚያወጡት ቃል የብዙሃኖችን እውነት ቢሆንስ? አልያም እኛ ስንረዳ ተሳስተን ቢሆንስ?የእነርሱ ቃል እውነታን ያዘለ ከሆነ ሁሌ ምን አልባት እኛ ስተናል!!!
16 308
፡
Code 7 - Abay
ህይወት ግን?
ህይወት ግን አንዳንዴ ወንዝ ይሆንብኛል
ድንጋዩም እንጨቱም ሚርመሰመሱበት፣
አፈር እና ውሀ ሚደባለቁበት፣
በፊትም በኃላ
አንዳንድ ገባር ወንዞች ሚገማሸሩበት፣
ድንጋዩም እንጨቱም ስሜታችን ሁኖ፣
አምስቱ ህዋሳት
ባቃረቡት ሁሉ የሚሄድ ተጭኖ፣
አፈር እና ውሀው ደስታና ኀዘን ነው፣
ህይወታችን ቅርፁን
መልክና ይዘቱን በአንዴ ሚቀይረው፣
የገባሩ ወንዝ ግን እንጃ ምን እንደሆን፣
ያልተገለጠልኝ
ፍቹን ያላወቁት
ምናልባት በድንገት ሰለገባ ይሆን።✍✍
@abay
16 308
፡
Code 6 - Tsegi
ማን ነኝ ?🤔
ከስሜ በስተቀር መጠሪያ የሌለኝ
ማንነቴ የሆነው ኢትዮጽያዊ ሴት ነኝ
እስኪ ማን ልበለው ማን ነሽ? አንቺ አለኝ
ኸረ ጉድ ፍረዱኝ ይሄ ምን መልስ አለው
ሰው ከመሆን በላይ ማንነት ምንድነው
አዎ.....እኔ ሰው ነኝ የአዳም ዘር የሆንኩኝ
አምሳያው እንድሆን አምላክ የፈጠረኝ
ሰው መሆን ያልገባው ሰውነት የሌለው
ማን ነሽ? አንቺ አለኝ ብሄርሽ ምንድነው
ለዚ መልስ ያለው እስኪ ምን ልበለው?
16 308
፡
Code 5 - Glamor
እወዳት ነበረ
:
እሺን እስክትሰጠኝ
ከአልጋዬ እስክትገኝ
እጓጓ ነበረ
:
ግልፅ እስክትሆንልኝ
ውበቷን እስካገኝ
አከብራት ነበረ
:
ክብሯን እስክትሰጠኝ
በጠራኋት ቁጥር አቤት እስክትለኝ
በቅታኛለች አሁን
:
እኔም አድጊያለው ጡንቻዬ ፈርጥሟል
ይሄ ሁሉ ብስለት ሚስት ያስፈልገዋል
እሷን እንዳትሉ
:
ከጋብቻ ቀጣይ ሊኖሯት ሚገቧት
አንዱም የለም አብሯት
ቻውን ነው ምሰጣት!!!
©Glamor
16 308
፡
Code 4 - Yordi
ግድርድር ፍቅር
ትመጣለህ ብዬ ትመጣለች ብለህ😍
ስጠብቀኝ ስጠብቅህ⏰
ያንተ ጀንበር ጠልቃ ቀናችን ተቋጨ🌄
ያልጀመርነው ፍቅር ሳይነካ ተቀጨ🩶
አብሮነትን በተነው ተረጨ😭
አሁን ምን ጠቀመን???💔
፡
16 308
፡
Code 3 - Abrham
ያለውበትን ስሜት እንዴትስ ልለየው
ብቻዬን አውሬቼ ብቻዬን ስቃለው
አሁን ተደስቼ ወድያው አኮርፋለው
እነደዚ ዓይነት ስሜት ምንድነው ሚባለው?🤔
ስሜቴን ለማውቅ በግጥም ላሰፈረው
ቃላቶቹ ጠፍቶኝ ከዪት ወዴት ላረገው
በምንስ ጀሜሬ ግጥሙን እንዴት ልዝጋው?
ብዬ ብጠይቀው እራሴን መልሼ
መልሱ ጠፍቶበት ነው መስል አይምሮዬ ሸሸ
የቀረኝ ልቤን ነው እሱንም ጠየኩት
ምን ዓይነት ስሜት ነው አሁን ያለውበት??
ንገረኝ ልወቀው ራሴን ልረዳበት
ብዬ ብጥየቀው የጎዳው ልቤን
ፍቅር ነው ስሜቱ ብሎ ነው የነገረኝ
ለካስ አፍቅሬ ነው እንደዚ ሚያረገኝ
አይምሮዪ ከብዶት ልቤ እንደ አስረዳኝ
በንግግሩ ሁሉ አንቺን ነው የጠቆመኝ
ገጣሚ አብርሃም
@Azeguuu
16 308
፡
Code 1 - Tsion
አይ ሰው ከንቱ😣
ብሔር ሀይማኖትን ዘርን እየለየ
ሀገርን ለመሸጥ ጥቅምን እያዋየ
ታዲያ ይሄ ሰው ነው
ወይስ የሰው ከንቱ
ሀገርን አቃጥሎ ለመኖር ካለመ
ከብር ብር ላይ መቀጠል ካሰበ
እውነት ልንገራችሁ ይሄ ህልም ነው
እውነት ላይሆንለት ከንቱ ልፋት ነው
ለዚች ለጥቂቷ ለትንሻ እድሜ
መከባበር እንጂ አይበጂም ጭካኔ
አረተው ስማኝ አረተው ወገኔ
በመጨካከን አይገኝም ወኔ🙏
16 308
ይህንን ያውቃሉ⁉️
ደቡብ ኮሪያ ሰዎች እና ፍቅረኛሞች አብረው ረጅም ጊዜ እንዲያሳልፉ በማሰብ ሰራተኞች በሳምንት አራት ቀን ብቻ እንዲሰሩ አደርጋለች .... አራቱን ቀን በስራ ያሳልፋሉ ቀሪዋን ሶስት ቀን ደሞ ሰዎች ከፍቅረኛቸው ፣ ከጎረቤታቸው እንዲሁም ከሚወዱት ጋር ጊ እንዲያሳልፉ አድርጋለች ❤️🩹
16 308
ይህንን ያውቃሉ ⁉️
ጎግል የተሰኘው ገፅ የሰዎችን ድምፅ ብቻ እየሰማ ምን አይነት በሽታ እንደያዛቸው የሚናገር አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ [ AI ] እየሰራ እንዳለ አሳወቀ ፤ ይህ AI ድምፅ በመስማት ብቻ ከ135 በላይ በሽታዎችን የሚናገር ሲሆን አያይዞም የመከላከያ እና የመዳን መንገዶቹንም ይነግረናል 😬
ይህ ገፅ ባሳወቀው መሰረት AI በተወሰነ መልኩ የሰውን ልጅን ስሜት ፣ ሀሳብ እና ያለበትን ሁኔታ የሚረዳበትን ሶፍትዌር አዘጋጅተው እንደጨረሱ ተገልጿል 😯
በAI ልንታከም ነው
16 308
ይህንን ያውቃሉ⁉️
የሴቶች የወሲብ ፍላጎት ከወንዶች ፍላጎት በስምንት እጥፍ የተሻለ ነው .... ሴቶች ከወንዶች ጋር ሲነፃፀሩ የርሃብ ፍላጎት በሁለት እጥፍ ፣ አይናፋርነት በአራት እጥፍ ፣ ደፋርነት በስድስት እጥፍ እና የወሲብ ፍላጎታቸው በስምንት እጥፍ የተሻለ እንደሆነ ጥናቶች ያረጋግጣሉ
16 308
ይህንን ያውቃሉ ⁉️
በ6ተኛው ክፍለ ዘመን ሴቶች ብዙውን ጊዜ ቆዳቸው የገረጣ እንዳይሆን ለማድረግ እና ቆንጆ ለመሆን ሲሉ ራሳቸውን እያቆሰሉ እንደሚያደሙ ታሪክ ይናገራል
በ21th ደሞ ሜካፕ !
16 308
በመክበርህ መክበርና መከበር ሚሻ በጽልመት ቀንህ መቼም አጠገብህ አታየውም! ግን የተሻለ ነገር ባገኘህ ሰዓት ዙሪያህን ቆሻሻ እንደሳበው ዝንብ አብዝቶ ይወርሃል።
