የጥበብ ማዕድ
الذهاب إلى القناة على Telegram
📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام የጥበብ ማዕድ
تُعد قناة የጥበብ ማዕድ (@yetbebmead_ab) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 16 269 مشتركاً، محتلاً المرتبة 5 242 في فئة الدين والقيم الروحية والمرتبة 2 083 في منطقة Ethiopia.
📊 مؤشرات الجمهور والحراك
منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 16 269 مشتركاً.
بحسب آخر البيانات بتاريخ 08 يوليو, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار 677، وفي آخر 24 ساعة بمقدار 51، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.
- حالة التحقق: غير موثّقة
- معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 2.58%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 2.05% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
- وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 420 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 333 مشاهدة.
- التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 12.
📝 الوصف وسياسة المحتوى
يصف المؤلف القناة بأنها مساحة للتعبير عن الآراء الذاتية:
“ዝም ብለህ ተቀላቀል!”
بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 09 يوليو, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة الدين والقيم الروحية.
16 269
المشتركون
+5124 ساعات
+1727 أيام
+67730 أيام
أرشيف المشاركات
16 259
፡
Code 12 - ቃል
አለኝ እኮ ተስፋ
ምንም ቢያደክም ምንም ቢያለፋ
ከሩቅ አልሜ በተስፋ ሰንቄ
ይሆNaል አምNaለሁ ይታየኛል ሳቄ
👩🎤✍ ለነዚህ ህልሞቼ መጓዝ አላቆምም🙅♀️
ገNa ብዙ አለኝ የምሰራው ለአለም
ደግሞ አልፈራም መከታጋሻዬ
አለልኝ እኮ ለኔ ፈጣሪዬ🙏
፡
16 259
፡
Code 11 - Bzuayehu
በድቅድቅ ጨለማ በክረምቱ ወራት
አይኔን አንጋጥጨ ጨረቃዋን ሳያት
አንችን መሰለችኝ ሰላምታ ሰጠኋት
ግና ምን ዋጋ አለው ብጠራት ብጠቅሳት
ባለቅስ ባላዝን ውዴ ፍቅሬ ብላት
እንደ አድስ ሙሽራ ከዋክብት ከበዋት
መልስም አልሰጠችኝ ለአይኗም አልታየኋት
ላይታዩ ማንባት ላይሰሙ ጩኸት
ክብሬ ላያቆመኝ ከፊታውራሪ ፊት
እረ ተወኝ ልቤ ጎንበስ ልበልበት
፡
16 259
፡
ዛሬ ሊጠናቀቅ የነበረውን ውድድር አንድ ቀን ጨምረን ነገ እንዲሆን አድርገነዋል፡፡
ስለሆነም ተወዳዳሪዎች ግጥማችሁን እስከ ነገ ከምሽቱ 3:00 ድረስ ድምፅ ማሰጠት ትችላላችሁ፡፡
መልካም ዕድል
መልካም ቆይታ🙏
፡
16 259
💕ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይ ፈ ል ጋ ሉ ? 🔔 💕
[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪ አቤል መክብብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
🌷👥 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧
16 259
💁 እኔ ኦርቶዶክስ ነኝ የሚል/ሀይማኖቴን ማወቅ ፈልጋለው የሚል የተዋሕዶ ልጅ ብቻ ✝️OPEN✝️ የሚለዉን ይጫን !!!
እኔ ኦርቶዶክስ ነኝ የሚል ብቻ 👇👇👇
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
16 259
አንዳንድ የባስ ሹፌሮች ህዝቡን ሲያሳፍሩ ሳይሆን ሲያሯሩጡ ነው መሰል ስራ የሠሩ ሚመስላቸው! ደግሞ እንደዛም ተሮጦ ጥለውት ሚሔዱት ነገር!😕
16 259
፡
Code 10 - bible
ምን ላርግልሽ
ፈገግታሽ እንዳይነጥፍ
እምባሽ እንዳይረግፍ
የልብሽ ሃዘንሽ በርትቶ
ቅስም እንዳያሳጣሽ ከቶ
ምን ላርግልሽ
ምኔን ልለግስሽ
ጥርሴን ልስጥሽ እንድትስቂ የኔንም?
ልቤን ልስጥሽ እንድታይ ሁለት ዓለም?
ሰባሪ ሲመጣ ልብን የሚያጨልም
ያንቺን ተንከባክበሽ የኔ እንዲቀድም?
አይኔንስ ትወስጂው እምባሽ ከመጣ?
የኔን አሞጭሙጨሽ ያንቺ ለዛን እንዳያጣ
ምኔን ልስጥሽ
እሺ ወይም ውሰጂው እምነቴን ላንቺ
የኔን እንድትሰጪያቸው እንዳይጠፋ ያንቺ
ቆይ ምኔን ልስጥሽ ምኔ ይገባሻል
ሃዘን መከራሽን ምኔ ይወስድልሻል
እስኪ ይሄን ስጠኝ በይ አይተሽ ከሁሉ
ላንቺ ቀርቧል አካሌ ከታህት እስከ ላእሉ
........
ወይ ደሞ ሞክሪ እስኪ እኔን ወስደሽው
ክፉው ሲመጣ ይውሰደው ከፊት እያረግሽው
16 259
፡
Code 9 - Mahlet
ሀገሬ ኢትዮጵያ እንዴት ነሽ ልበልሽ
እያየው ስትሆኚ ልጆች እንደሌለሽ
ልጆችሽ ሆነን የእናት ጡት ነካሽ
እርስ በርሳችን እየተበላላለን
እርስ በርሳችን እየተወቃቀስን
እየኖርን ነው እርስ በርሳችን እየተገዳደ
አሁንም ሀገሬ ይሉሻል በማደግ ላይ ያለሽ
ግን አይቀርም አንድ ቀን አደገች መባልሽ
በአድዋ ሜዳ የፈሰሰው ያባቶቻችን ደም
ሳይፈሩ ተዋግተው ብለው ኢትዮጲያ ትቅደም
አኖሩሽ አቆሙሽ አጥንታቸውን ከስክሰው
ግና ምን ያረጋል ይህ ሁሉ ልፋታቸው
መና መቅረቱ ነው በገዛ ልጆቻቸው
እንኳን ሊዋጉ ኢትዮጵያ ትቅደም ብለው
አቃታቸው መኖር እርስ በርስ ተዋደው
ትንሳኤሽን ያሳየን
16 259
፡
Code 8 - Eldana
ቢሆን ኖሮ
ቢሆን ኖሮ ብዬ አስባለሁ
ያኔ ባደረኩት ብዬ አብሰለስላለው
በራሴው ምክንያት አዝናለው
እራሴው ባደረኩት ነገር እወቃቀሳለው
ምን ይሻለኝ ይሆን ምን ይሆን ትዝብቴ
ቢሆን ኖሮ ብዬ ሆነብኝ ፀፀቴ
ቢሆን ኖሮ ማለት የኋላ ህልም ነው
ቢሆን ኖሮ ማለት ያለፈ ነገር ነው
ቢሆን ኖሮ እያሉ በልብ ከመቆጨት
በሱ ቦታ የወደፊት ህልምን ቢያስቡበት
፡
16 259
አንዳንዴ እብዶች ተብዬ የልባችንን እውነት ሲናገሩ ከስንት አንዴ ጤነኛ እንደሆኑ እናስባለን! ግን እለት በእለትስ የሚያወጡት ቃል የብዙሃኖችን እውነት ቢሆንስ? አልያም እኛ ስንረዳ ተሳስተን ቢሆንስ?የእነርሱ ቃል እውነታን ያዘለ ከሆነ ሁሌ ምን አልባት እኛ ስተናል!!!
16 259
፡
Code 7 - Abay
ህይወት ግን?
ህይወት ግን አንዳንዴ ወንዝ ይሆንብኛል
ድንጋዩም እንጨቱም ሚርመሰመሱበት፣
አፈር እና ውሀ ሚደባለቁበት፣
በፊትም በኃላ
አንዳንድ ገባር ወንዞች ሚገማሸሩበት፣
ድንጋዩም እንጨቱም ስሜታችን ሁኖ፣
አምስቱ ህዋሳት
ባቃረቡት ሁሉ የሚሄድ ተጭኖ፣
አፈር እና ውሀው ደስታና ኀዘን ነው፣
ህይወታችን ቅርፁን
መልክና ይዘቱን በአንዴ ሚቀይረው፣
የገባሩ ወንዝ ግን እንጃ ምን እንደሆን፣
ያልተገለጠልኝ
ፍቹን ያላወቁት
ምናልባት በድንገት ሰለገባ ይሆን።✍✍
@abay
16 259
፡
Code 6 - Tsegi
ማን ነኝ ?🤔
ከስሜ በስተቀር መጠሪያ የሌለኝ
ማንነቴ የሆነው ኢትዮጽያዊ ሴት ነኝ
እስኪ ማን ልበለው ማን ነሽ? አንቺ አለኝ
ኸረ ጉድ ፍረዱኝ ይሄ ምን መልስ አለው
ሰው ከመሆን በላይ ማንነት ምንድነው
አዎ.....እኔ ሰው ነኝ የአዳም ዘር የሆንኩኝ
አምሳያው እንድሆን አምላክ የፈጠረኝ
ሰው መሆን ያልገባው ሰውነት የሌለው
ማን ነሽ? አንቺ አለኝ ብሄርሽ ምንድነው
ለዚ መልስ ያለው እስኪ ምን ልበለው?
16 259
፡
Code 5 - Glamor
እወዳት ነበረ
:
እሺን እስክትሰጠኝ
ከአልጋዬ እስክትገኝ
እጓጓ ነበረ
:
ግልፅ እስክትሆንልኝ
ውበቷን እስካገኝ
አከብራት ነበረ
:
ክብሯን እስክትሰጠኝ
በጠራኋት ቁጥር አቤት እስክትለኝ
በቅታኛለች አሁን
:
እኔም አድጊያለው ጡንቻዬ ፈርጥሟል
ይሄ ሁሉ ብስለት ሚስት ያስፈልገዋል
እሷን እንዳትሉ
:
ከጋብቻ ቀጣይ ሊኖሯት ሚገቧት
አንዱም የለም አብሯት
ቻውን ነው ምሰጣት!!!
©Glamor
16 259
፡
Code 4 - Yordi
ግድርድር ፍቅር
ትመጣለህ ብዬ ትመጣለች ብለህ😍
ስጠብቀኝ ስጠብቅህ⏰
ያንተ ጀንበር ጠልቃ ቀናችን ተቋጨ🌄
ያልጀመርነው ፍቅር ሳይነካ ተቀጨ🩶
አብሮነትን በተነው ተረጨ😭
አሁን ምን ጠቀመን???💔
፡
16 259
፡
Code 3 - Abrham
ያለውበትን ስሜት እንዴትስ ልለየው
ብቻዬን አውሬቼ ብቻዬን ስቃለው
አሁን ተደስቼ ወድያው አኮርፋለው
እነደዚ ዓይነት ስሜት ምንድነው ሚባለው?🤔
ስሜቴን ለማውቅ በግጥም ላሰፈረው
ቃላቶቹ ጠፍቶኝ ከዪት ወዴት ላረገው
በምንስ ጀሜሬ ግጥሙን እንዴት ልዝጋው?
ብዬ ብጠይቀው እራሴን መልሼ
መልሱ ጠፍቶበት ነው መስል አይምሮዬ ሸሸ
የቀረኝ ልቤን ነው እሱንም ጠየኩት
ምን ዓይነት ስሜት ነው አሁን ያለውበት??
ንገረኝ ልወቀው ራሴን ልረዳበት
ብዬ ብጥየቀው የጎዳው ልቤን
ፍቅር ነው ስሜቱ ብሎ ነው የነገረኝ
ለካስ አፍቅሬ ነው እንደዚ ሚያረገኝ
አይምሮዪ ከብዶት ልቤ እንደ አስረዳኝ
በንግግሩ ሁሉ አንቺን ነው የጠቆመኝ
ገጣሚ አብርሃም
@Azeguuu
