ch
Feedback
የጥበብ ማዕድ

የጥበብ ማዕድ

前往频道在 Telegram

ዝም ብለህ ተቀላቀል!

显示更多

📈 Telegram 频道 የጥበብ ማዕድ 的分析概览

频道 የጥበብ ማዕድ (@yetbebmead_ab) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 15 974 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 5 411,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 116

📊 受众指标与增长动态

невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 15 974 名订阅者。

根据 25 六月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 604,过去 24 小时变化为 -23,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 2.64%。内容发布后 24 小时内通常能获得 2.10% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 419 次浏览,首日通常累积 334 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 10

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
ዝም ብለህ ተቀላቀል!

凭借高频更新(最新数据采集于 26 六月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。

15 974
订阅者
-2324 小时
+1447
+60430
帖子存档
ዛሬ እንዴት እንደሆነ አላወኩም ግን ራሴን ቤተክርስቲያን ደጅ አገኘሁት እኔ ማለት ሰው የሚፀየፈኝ፣ ይሄን ልጅና ሽንት ቤትን በሩቁ ብለው የሚተርቱብኝ ፣ ጎረቤት ገብቸ እንኳን እንደ ሰው ኖር ኖር ተብሎ ቦታ ማይሰጠኝ እኔ አንድ ቀበሌ ሚያክል ዘመድ ኑሮን ብቸኛ የሆንኩ እኔ ። እንዴት እንደሄድኩ አላውቅም ግን ራሴን ቤተክርስቲያን አገኘሁ ። እኔ ማለት የሰፈራችን ወላጆች ልጆቻቸውን ከዚህ ከይሲ ልጅ ጋ እንዳትውል እያሉ የገፉኝ ፣ የተደገፍኩት ፣ አለኝ ያልኩት እንደ ሸምበቆ ተሰብሮ ሲወጋኝ አየሁ። ራሴን ቤተክርስቲያን አገኘሁ ቤተክርስቲያን ደጃፍ ብቻዬን ቁጭ ብዬ እያለቀስኩ የሆነ ድምፅ መጥቶ ሲያወራኝ ታወቀኝ ። አይዞህ ልጄ! ሰው ባያውቅህም እኔ አውቅሃለሁ ፣ ሰው ቢገፋህም እኔ አሁን ክንዶቼን ዘርግቻለሁ ና ና እቅፌ ውስጥ ግባ ። አንተ ተውከኝ እንጂ እኔ አልተውኩህም ለዘላለምም አልለቅህም ። አሁን እኔ የልብ ወዳጅህ ነኝ የውስጥህን ለኔ ተናገር ። እነሱም አንተን ወደ እኔ ነው ያመጡህ በማንም ላይ ቂምም ሆነ በቀል እንዳይኖርብህ ። በል እንባህን ጥረግና በሰላም ወደ ቤት ሂድ አለኝ ። ከተቀመጥኩበት ብድግ ብየ ተነሳሁ እንባዬን ጠራርግ ለራሴ እንዲህ አልኩኝ .... ለካ እግዚአብሔር እንደሚያውቀኝ ማንም አያውቀኝም ።🙏🙏🙏🙏🙏 ✍ Henok

እንግሊዛዊ ደራሲና ፈላስፋ Alduos Huxley ስለ ምሁራን ከተናገረው :- ከብዙኃኑ በተለየ መልኩ ፣ ምሁራን ምክኒያታዊነትንና በእውነታዎች ላይ ፍላጎት አላቸው ። የአስተሳሰብ ትችታቸው በብዙኃኑ ላይ በጥሩ ሁኔታ የሚሰራውን አይነት ፕሮፖጋንዳ እንዲቋቋሙ ያደርጋቸዋል ።

ሳይኖረኝ ጦረኛ ከጎኔ መሳፍንት ወጣው ለጦርነት እንዲሁ ለብቻዬ ሰራዊት ላይ ልዘምት ምሽግ ምን ሊረባኝ ኣልሆንም ምርኮኛ ኣቅም ስላነሰኝ ኣያስፈልገኝም ሰገባ ለሰይፌ በኩራት ሞታለው ብቻ ተሰልፌ meron

የአንዳንድ ሰው እድል ትንሳዔ ያለው ሲመስል ፤ የአንዳንዱ ደግም ከእትብቱ ጋር አብሮ የተቀበረ ይመስላል።

ብዙ ግዜ የሰቀልከው ተስፋ ጋ ለመድረስ መንጠራራት ተስፋውን ከመጨበጥ በላይ ደስታ አለው ። ጉልበትና የተስፋ ስንቅ ያጅቡታል ። 📖 ጠበኛ እውነቶች

፡፥፡ አስኳላ ፡፡፥፡፡
ሁለት ሎሌዎች ተመሳሳይ መጠን በሚይዙ ሁለት ጋኖች ውሀ እንዲቀዱ ይታዘዛሉ። አንደኛው ችኩል፣ስልቹ፣እናም ያን ያህል ለነገሮች ትርጉም የማይሰጥ ስለነበር በቅርቡ ካለችዋ ምንጭ ለመቅዳት ይወርዳል፤ ያችውም ከብቶች እና ውሾች ያረከሷት ብትሆንም ሎሌው ርቆ መሄድ አልፈለገም። ይህም ለጌታው በፍጥነት ውሀውን ይዞ ተመለሰ።  ሌላኛው ሎሌ ግን ህሊናውን የገዛ፣ ነገሮችን የሚመዝን ስለነበር እንዲሁ የረከሰውን ለክቡር ጌታው ማቅረብ አልፈለገም። እናም በሩቅ ከሚገኝ ንፁህ እና ለጤናም ተስማሚ የሆነውን ውሀ ከባሕር ቀድቶ ይመለሳል ። ታዲያ ጌታው ጐርበጥ አድርጎ በማየት የት ቆየህ ብሎ ይወቅሰዋል፣ይቀጣውማል ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እኩል ለመታየት ሲል ቀድሞ በመሄድ ከባህር ቀድቶ ከምንጯ ከቀዳው ጋር እኩል መድረስ ስለቻል እኩል እይታን አግኝቷል። Our learning style don't judge or evaluate our mind or perspective rather it's all about showing the ultimate result!!!
✍ Tewodros D.

አንዳንዶቻችን የሰው መለማመጥ በራስ መተማመን ሚመስለን አለን መፈለጋችን የተለየ ማንነት የተላበስን እስኪመስለን ድረስ!      ያ ግን አብዝቶ ገዳይ ነው ሲፈልግህ የቆየ ሁሉ ለሁል ጊዜው በዛ ጥያቄ ውስጥ አይቀጥልም!!!      ፈላጊ ያጣህ ቀን እንዳንተ ከነበረበት የሚወርድና ድጋሚ ራሱን መገንባት ሚያቅተው አይኖርም!      ስለዚህ በሰው ስሜት ላይ ሳይሆን በራስ መቻል ላይ በራስ መተማመንህን አኑር።

አንዳንድ ችግሮቻችንን ጊዜ ፈታው ስንል ጊዜ መፍትሔ በራሱ ሰጠው ማለት አይደለም!      በጊዜ ውስጥ የተፈጠረው መረጋጋታችን እንጂ መፍትሔ የሆነው!!!       ስለዚህ በቀላሉ መረዳት ያለብን በየተኛውም ሁኔታ ውስጥ መረጋጋት መፍትሔ ሰጪ ነው።

እያንዳንዱ ሰው ውስጡ ላይ የሆነ ማዕበል አለው ። ይህም ማዕበል እኛን ሊሰራንና ሊያጠነክረን እንጂ ሊገድለን ወይም ሊያጠፋን የመጣ አይደለም ። ማዕበል እንደ ማዕበልነቱ ይለያያል አንዳንዴም ጠራርጎ የሚወስደን ማዕበል ሊመጣ ይችላል ። አንድ መርከበኛ ችሎታው የሚለካው ፀጥ ባለ ውሃ ላይ በመቅዘፍ ሳይሆን የሱ ፈተናው እና ችሎታው የሚታየው ማዕበሉ ውስጥ ቀዝፎ ከተሻገረ ነው ። ያኔ ማዕበሉ እሱን ጎበዝ ቀዛፊ ያደርገዋል ። በህይወታችንም ላይ የሚገጥሙን ማዕበሎች እኛን ይሰሩናል ያጎብዙናል እንጂ አያጠፉንም ። የህይወትህን መስመር ማዕበሉ የሚመጣበትን አቅጣጫ አይተህ መሪህን ዞር አድርገህ እለፈው ። አለበለዚያ በህይወት መንገድ ላይ እንደገና የሚባል ነገር የለም ዙርያህን ቃኝ በምን አይነት ማዕበል ውስጥ እንዳለህ አይተህ መሪህን ወደ ሌላ አቅጣጫ አዙረውና በሰላም ሂድ ። አይዞህ! ፈጣሪህን ብቻ ያዝ ታልፋለህ 🙏🙏 ✍ Henok

"ሄኒ ምንድነው በጣም የምትወደውና የሚያስፈልግህ ነገር "? አለችኝ ትከሻዬ ላይ ራሷን ጥላ ሁሌ ምሸት ለ sun set አዘዉትረን የምንቀመጥቀት ቦታ ላይ በሰዓቱ ተገኝተን እንዴ ! ሜሉ አንቺና አንቺ ነሻ አልኩኝ ከፏ ወዲያው ተቀብዬ እሺ ከኔ ቀጥሎ ? አለች ካንቺ ቀጥሎ 🤔 ትንሽ አሰብኩና ማስተርሴን መማር አልኩኝ እሺ ሌላስ አለችኝ ውስጤ ላይ የቀረ ነገር መኖሩን ያወቀች ይመስል ሌላው ከዚህ ላቅ ያለ ነው ኢትዮጲያ ውስጥ አለ የለም የተባልኩ የዩንቨርስቲ መምህር መሆን ነው ምፈልግ አልኳት አየህ ሄኒዬ አሁን በምናብህ ያሰብከው እውን የሚሆነው አንተ ስትንቀሳቀስ ነው። ያመለጡህን ነገሮች እርሳቸው አንዳንዴ እያስፈለገንም አለመፈለግ ጥሩ ነው ። ብላ ሳም አድርጋኝ ተነሳች ። እንዴ 🤔 የሚያስፈልጉንን ነገሮች አለመፈለግ ይቻላል እንዴ ? ✍ Henok

፡፡፤፤፡ አዲስ ሕይወት ፡፡፤፤፡
ህይወት እንደ ዛፍ በተመሳሳይ ነፋስ ተመሳሳይ እንቅስቃሴ ማሳየት ስትጀምር ፤ የመሻት አቅሟ እየተሟጠጠ ፣ መሰላቸት እየፀና ይመጣል። ወዳጄ የምታማርረው እና ነገ በእራሷ ብርሃን ሆና ሳለ ዓይንህን ጋርዶ በብርሃኗ መሻትክን እንዳትዘራ ያሰረህ ዛሬ ላይ የምታደርገው ተመሳሳይ እንቅስቃሴ ነው። ይህን ደግሞ መቀየር የምትችለው አንት ብቻ ነህ። ነገሮች ህይወትህን ተመሳሳይ ሊያደርጉብህ ቢሞክሩ እንኳን ነገሮችን ተጠቅመህ ህይወትህን አዲስ ማድረግ። እስረኞች ዓለም ፣ ቤተሰብ ፣ አካባቢ ፣ ጓደኛ ከመራቃቸው በተጨማሪ ህልማቸውን ይነጠቃሉ።ሁሌም ተመሳሳይ ምግብ ፣ ልብስ ፣ ድምፅ ፣ ምኞት፣....ኡፍፍ..ፍፍፍ...አሰልቺ ነው። ታዲያ ብልሆቹ ፍቱን መድሀኒት አግኝተዋል ...መ..ፅ...ሐ..ፍ ማንበብ። መፅሐፍ... ሰውሰራሽ ካቦች የጋረዱት ዓይንህን በማገዝ አዲስ አለም ፣ ህይወት ፣ ተስፋ ፣ የዛፎች እንቅስቃሴ ፣ የወፎች ዝማሬ ፣ ...ሁሌም አዲስ ህይወት ያጎናፅፍሃል። ብቻ አዕምሮህ አዲስ ህይወት ማየት የሚችልበትን መንገድ ተጠቀም ...ያኔም ሕልምህ ያቆጠቁጣል ፣ ዓላማህ እራሱን ግልፅ ያደርጋል ፤ ብርሃን ለእናንተ!!!
Simple and new way of life lets you survive on the way to your goal,let yourself progress through reading or an action that makes you sense new smells, and feel new all. ✍✍ T,,,,,,D.....

፤፥፡አለመማር መቃጠል ነው ፡፡፤
ባለፈው አንዱ ተማሪ "መማር መቃጠል ነው" ሲል ሰማሁት። እኔም በቅርበት ጠየቅሁት ፣ እንዴት? አልኩት። እርሱም በብስጭት ... እንዴት ትለኛለህ ... መዓት.. X... እያነደደኝ ይለኛል። እኔም ለማረጋጋት እየሞከርኩ ... እርሱማ የሁላችንም ነው ... እእ.. ግን እንዴት መማር መቃጠል ሊሆን ቻለ? አልኩኝ ባለመሰልቸት። X..ከየት ሊመጣ ቻለ አልኩት? አይይ... እኛ እምናነበው እና እሚያስተምሩን ቆሎ ቆሎውን,... እ.., ፈተና እሚያመጡት .. ያልበሰለ ጥሬውን ... የበሰለ ቆሎ መብላት ለምደን ... ማብሰሉን ከየት እናምጣው.. ሳንማረው? ታዲያ ጀግኖቹ ቆሎ ሲሰጧቸው የት እና እንዴት እንደበሰለ ይጠይቃሉ? ይህ ነው ማወቅ ... ለካስ እየተማርን አልነበረም... መማር ማሰብ ነው እንጂ የሰጡትን መቀበል አይደለም። ቆሎ ሲሰጡህ የት መጣ በል? ከሰማይ እንዳልሆነ ታውቃለህ... ያኔ አዕምሮህ ስራውን ይጀምራል ... የጥርስ ስራን ..ለጥርስ
Learning is analyzing, not burning bro

ውጪ እንደ ዘመዱ የተላፋህ ውሻ ነው ቤቱ እግርህን በቀዳዳ ሚነቅስህ።       መቼ እንደሚቀየሩ አታቃቸውም!

።።።። ዝምታ ከመረጥን ባፍ ከፋቾች መሀል በደበዘዙት ፊት ደምቀን ከተገኘን በአንካሶች መሀል በእግሮቻችን ከቆምን ከህዝበቱ ጋራ ካልተመሳሰልን ለሁሉም ጠላት ነን አርቀን ካስተዋልን በእውሮች መሀል ሁሉም ሰው ያማናል ሁሉም ይዘልፈናል ደህና መሆን ባልሆኑት ውስጥ ያስነቅፋል ያስገልላል ለምን?  ቢባል በሽታን  ለለመደ                ጤነኝነት በጣም ያማል       .meron

አንተ ሁለነገርህን ታውቀዋለህ እነሱ ደግሞ ያሳየኻቸውን!           አንተ ምትፈልገው የጎደለህን አይደለም እንዲኖርህ እንጂ! እነሱ ደግሞ የእነሱን መሻት እንድታሟላ ነው።     የምሬን አንዳንድ ሰው ሊሰራህ ሲሞክር እያስተካከለህ አይምሰልህ እንደራሱ ሊቀርጽህ ነው እንጂ!!!

ያውቃሉ ለመባል እውቀትን ለፈለግን በልጦ ለመታየት ሰውን ላሳነስን ነበሩ ለመባል ግን ኖረን ላልጠቀምን ይብላኝልኝ ለኛ ሰው መስለን ግን ላልሆን #meron

ቤተሰቦች የስነ_ጽሁፍ ችሎታና የጻፋችሁት ካላቹ በቻናላችን በመለጠፍ ለአንባቢያን ቤተሰቦች ስራዎቻችሁን ማስገምገም ትችላላቹ!!! አድሚን እንሰጣለን።

ሁሉም እንደሚያምርብህ ማሰብ በራስ መተማመን ነው! አንዳንዴ ብቻ ትንሽ ራስን አለማወቅ ሊገባበት ይችላል እንጂ።

አበባን ያሳመራት ፍሬዋ ብቻ አልነበረም ፈንቅላ የወጣችውም ጭቃ እንጂ!

ለአንድ ጎል አስራ አንዱን መጣል ግድ ነው።

የጥበብ ማዕድ - Telegram 频道 @yetbebmead_ab 的统计与分析