EthioTube
前往频道在 Telegram
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ። Follow us on other our social media networks: Facebook.com/EthioTube Twitter.com/EthioTube Youtube.com/EthioTube Instagram.com/EthioTube
显示更多7 981
订阅者
-224 小时
-277 天
-9230 天
帖子存档
7 982
ህወሓት ጀነራል ጆን መዲድ “ክህደት መጽመዋል” አለ
የቀድሞው የፌደራል መከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ መኮንን እና የትግራይ ኃይሎች ደቡባዊ ግንባር አዛዥ የሆኑት ሜጀር ጄነራል ዮሐንስ ወልደጊዮርጊስ (ጆን መዲድ) ለኢትዮጵያ መንግሥት “እጅ መስጠታቸው” ከተሰማ በኋላ ህወሓት ጄነራሉን “በከሃዲነት” ፈርጇል።
ጄነራል ጆን መዲድ በትግራይ መንግሥት ተልዕኮ ተሰጥቷቸው የነበረ ቢሆንም ኃላፊነታቸውን በሚገባ አለመወጣታቸውን ህወሓት በመግለጫው አሳውቋል።
በዚህ ሳቢያ ከማዕከላዊ ኮማንድ ተነጥለው እንዲቆዩ መደረጉንም መግለጫው ይጠቅሳል። በዚህ ቆይታቸው ጄነራሉ “ከጠላት ጋር ግንኙነት በመፍጠር ተቀላቅለዋል” ሲል ህወሓት ገልጿል።
ሜጀር ጄነራል ዮሐንስ በተያዙበት ጊዜ የደኅንነት ጠባቂዎቻቸው፣ የኮሎኔል ማዕረግ ያላቸው ሰባት አዛዦች እና ሌሎች በርካታ መኮንኖች ከእርሳቸው ጋር እንደነበሩ ቢቢሲ ዘግቧል።
"ጆን መዲድ" በሚል ቅጽል ስም የሚታወቁት ሜጀር ጄነራል ዮሐንስ፣ በትግራይ ኃይሎች ወታደራዊ መዋቅር ውስጥ ከሚገኙ ከፍተኛ የጦር አመራሮች መካከል አንዱ ነበሩ።
#Ethiopia #Tigray #TPLF #GeneralYohannis #JohnMedid
7 982
በአርሲ ጥቃት የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 60 ደረሰ - የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባዔ በኦሮሚያ ክልል አርሲ በሚገኙ ወረዳዎች በተለያየ ቀን በደረሰው ጥቃት 60 ምዕመን መገደላቸውን በመግለጽ ጥቃቱን “በጽኑ እንደሚያወግዝ” አስታውቋል።
በሸርካ ወረዳ 46 እና በመርቲ ወረዳ 14 ምዕመናን “ግፍ በተሞላበት ጭካኔ” መገደላቸውን አረጋጧል። የ 20 ምዕመናን መኖሪያ ቤት ሙሉ ለሙሉ እንደወደመ እና 20 ሰዎች ደግሞ በጥቃቱ ተጎድተው ሕክምና ላይ መሆናቸው ተመላክቷል።
ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባዔ ፤ በአርሲ አገረ ስብከት እና በሌሎችም አካባቢዎች “ኦርቶዶክሳውያን ንጹኃን ልጆቻችን ላይ የሚፈጸመው እጅግ አሰቃቂና ዘግናኝ ጭፍጨፋ፣ መፈናቀል፣ የአካልና የንብረት ጉዳት ተከታታይነት ባለው ሁኔታ፣ ያለማቋረጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ” መጥቷል ብሏል።
“በሕገ መንግሥቱ የተረጋገጠውን በሕይወት የመኖርና በነጻነት የማምለክ መብትን እንዲያስከብሩልን” ሲል ጠይቋል።
ድርጊቱን የፈጸሙትን “ወንጀለኞች ለሕግ በማቅረብ የሕግ የበላይነትን ከማረጋገጥ በተጨማሪ እንዲህ ዓይነቱ አረመኔያዊ ተግባር ከእንግዲህ በኋላ እንዳይደገም አስፈላጊውን የሕግ ከለላ” እንዲሰጥ ሲኖዶሱ አሳስቧል።
የኦሮሚያ ክልል በበኩሉ በጉዳዩ ላይ በሰጠው መግለጫ “ጽምዶ” በሚል ጥምረት የፈጠሩ ኃይሎች እንደፈጸሙት ገልጿል።
#Ethiopia #EOTC #Arsi #Oromia #EthiopianOrthodox
7 982
በምሥራቅ አርሲ ዞን በርካታ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች መገደላቸው ተገለጸ
በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ አርሲ ዞን ሸርካ ወረዳ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ላይ “ከፍተኛ ጥቃት መድረሱን” ቤተክርስቲያኗ አስታውቃለች።
በአካባቢው እየተፈጸመ ያለው ጥቃት ተባብሶ በመቀጠሉ እስካሁን ድረስ የደረሰው የሞት አደጋ በውል መታወቅ እንዳልቻለ ቢገለጸም የሟቾች ቁጥር ከ 40 በላይ እንደሆነ ተዘግቧል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መገናኛ ብዙኃን እንደዘገው ትላንት ጥቅምት 14 ቀን 2019 ዓ.ም. ከማለዳ ጀምሮ በወረዳው በሚገኙት ጠሬታ፣ ቢርቦና ጮሌ እና ሶሌ ዲገሉ በተባሉ ቀበሌዎች ከፍተኛ ጥቃትና ግድያ ተፈጽሟል።
ጥቃቱ ድንገተኛ ብቻ ሳይሆን ስልታዊ በሆነ መልኩ በኦርቶዶክሳውያን እና በአብያተ ክርስቲያናት ላይ ያነጣጠረ መሆኑን የአካባቢው ምንጮች ተናግረዋል ሲልም አመልክቷል።
የምሥራቅ አርሲ ዞን ሸርካ ወረዳ ከ2016 ዓ.ም. ጀምሮ በኦርቶዶክሳውያን ላይ ተደጋጋሚ ጥቃቶች ሲፈጸሙ እንደቆዩ ዘገባው አስታውሷል።
#Ethiopia #EOTC #EthiopianOrthodox #Arsi #Oromia
7 982
ሱዳን የትግራይ ተዋጊ ኃይሎችን ድሮን ማስታጠቋን አቶ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ
በቀድሞ ጦርነት ወቅት “ግብጽ 500 መቶ ሺህ ዶላር ሰጥታናለች”
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አማካሪ የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ተዋጊ ኃይሎች ከሱዳን የተላከ ድሮን ታጥቀው እንደነበር ገልጸዋል።
ሆኖም የድሮን አጠቃቀሙን “በደንብ ስላልተለማመዱ ብዙ[ድሮን] እንደታሸገ ነው የተያዘው” ብለዋል። አቶ ጌታቸው አክለውም በፕሪቶሪያ ስምምነት በተቋጨው ጦርነት ወቅት አባል የነበሩበት ህወሓት ከግብጽ የ 5 00 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ጠይቆ እንደነበር ገልጸዋል። ይሁን እንጂ ይህ ገንዘብ ብዙ በመሆኑ 500 ሺህ ዶላር ተሰጥቶናል ብለዋል።
አቶ ጌታቸው፤ በአሁን ወቅት መከላከያ ሰራዊት ከኤርትራ ድንበር በአምስት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኝ “አዲ ፍታው” የተባለች ቦታ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በሁለቱ ሀገራት ድንበር ላይ በሚገኙ አካባቢዎች ግጭት ቢፈጠር “የኤርትራ ምሽግ የመሰበር እድሉ ሰፊ ነው። ምሽጉ ከተሰበረ በኋላ አስመራ ለመግባት የሚወስድ በጣም አጭር ጊዜ ነው” ብለዋል።
#Ethiopia #GetachewReda #Tigray #Sudan #TPLF
7 982
ባለቤቱንና የአንድ ዓመት ሕፃን ልጁን በ25 ጥይቶች የገደለው ግለሰብ በ25 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ
በምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ፍኖተ ሰላም ከተማ ባለቤቱንና የአንድ ዓመት ሕፃን ልጁን በጥይት በመግደል የተከሰሰ ግለሰብ በ25 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ የምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት መወሰኑን የፍኖተ ሰላም ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አስታወቀ።
የፍኖተ ሰላም ከተማ አስተዳደር ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ምክትል ኮማንደር አለህኝ አለባቸው እንደገለጹት፤ ወንጀሉ የተፈጸመው ነሐሴ 3 ቀን 2018 ዓ.ም. ከምሽቱ 1፡30 ገደማ በፍኖተ ሰላም ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 01 ልዩ ስሙ ሰፈር 3 በተባለ አካባቢ ነው።
ተከሳሹ ይናገር ደመላሽ ሁነኛው፣ "በውሃ ቅዳ" እና "ልብስ እጠቢ" በሚል ጉዳይ በተፈጠረ አለመግባባት ተነሥቶ በእጁ በነበረ ታጣፊ ክላሽንኮቭ ጠመንጃ 25 ጥይቶችን በመተኮስ ባለቤቱንና በእቅፏ የነበረውን የአንድ ዓመት ሕፃን ልጃቸውን በግፍ ገድሏል።
ግለሰቡ ከዚህ አሰቃቂ ድርጊቱ በፊትም በባለቤቱ ላይ ተደጋጋሚ ድብደባና ጥቃት ያደርስ እንደነበር በምርመራ መረጋገጡን ኃላፊው አክለው አብራርተዋል።
ወንጀሉ ከተፈጸመ በኋላ ፖሊስ ተከሳሹን ወዲያውኑ በቁጥጥር ሥር በማዋል፣ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን አደራጅቶ መዝገቡን ለዞኑ ፍትህ መምሪያ ማስተላለፉን ምክትል ኮማንደር አለህኝ ጠቁመዋል።
የፍትህ መምሪያው ዐቃቤ ሕግም የምርመራ መዝገቡን ከመረመረ በኋላ፣ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 539(1)(ሀ) መሠረት በከባድ ሰው ግድያ ወንጀል ሁለት ክሶችን በመመሥረት ጉዳዩን ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቧል።
በችሎት ሂደትም ተከሳሹ የተከሰሰበትን ድርጊት ቢክድም፣ ዐቃቤ ሕግ ባቀረባቸው ማስረጃዎች ወንጀሉን መፈጸሙ በማያወላዳ ሁኔታ በመረጋገጡ ፍርድ ቤቱ የጥፋተኝነት ውሳኔ አሳልፎበታል።
7 982
+3
1ኪሎ ስጋ በ1200 ብር?
በቦሌ ክፍለ ከተማ ጥራቱን የጠበቀና በቂ የስጋ ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረበ ነው።
በክፍለ ከተማው የሚገኙ መሰረታዊ የኅብረት ስራ ሸማቾች ማኅበራት ለኅብረተሰቡ ጥራቱን የጠበቀና በቂ የስጋ ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ላይ ናቸው።
የመሰረታዊ ሸማቾች ኅብረት ስራ ማኅበራቱ የገበያ ዋጋን ለማረጋጋት በሚያደርጉት ጥረት የኅብረተሰቡን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ንፅህናው የተጠበቀ የስጋ እያቀረቡ የሚገኙ ሲሆን፣ ተጠቃሚዎችም ቀልጣፋና ተመጣጣኝ የሆነ የአገልግሎት አሰጣጥ እያገኙ መሆኑን ገልጸዋል።
የማኅበራቱ አመራሮችም ይህ አቅርቦትና አገልግሎት ሳይቋረጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ግልፀዋል።
ዘገባው የአዲስ አበባ ከተማ ኮምንኬሽን ቢሮ ነው።
#Ethiopia #AddisAbaba #Meat
7 982
አሳፋሪው የማንችስተር ዩናይትድ ሽንፈት በቻምፒዮንስ ሊግ
ማይክል ካሪክ ይባረሩ ይሆን?
#championsleague #manchesterunited
7 982
የዘንድሮው የሀጅ አጠቃላይ ክፍያ 827 ሺህ ብር ነው ተባለ
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዘንድሮው የሀጅ አጠቃላይ ክፍያ 827 ሺህ ብር መሆኑን አስታውቋል። ይህን ገንዘብ የመክፈል አቅሙ ያላቸው ምዕመናን ቶሎ እንዲመዘገቡ ጥሪ ቀርቧል።
የሀጅ ምዝገባው ጥር 10/2019 እንደሚጠናቀቅ አስታውቋል። ምክር ቤቱ የሐጅ አገልግሎት ዋጋ ተመን የወጪ መጠንን ለመቆጣጠርና ጥራቱን ለማሻሻል የሳዑዲ ዓረቢያ አገልግሎት አቅራቢ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ ማወዳደሩ በመግለጫው ጠቁሟል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ የፕሬዝዳንት ዋና ጽህፈት ቤት ዋና ኃላፊ ዑስታዝ አቡበከር አህመድ በበኩላቸው ሀጅ የማድረግ አቅሙ ያላቸው ምእመናን በመዘግየታቸው ምክንያት እድሉን እንዳያጡና በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ጫና እንዳይፈጥሩ በጊዜ እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርበዋል።
ጋዜጣዊ መግለጫውን በንባብ ያቀረቡት የጠቅላይ ምክር ቤቱ የአስተዳደር ጉዳዮችና የተቋማዊ ልህቀት ምክትል ፕሬዝዳንት ዑስታዝ ተምኪን አብዱላሂ የሐጅ ምዝገባ የልዩ መስተንግዶ (VIP) እና የትውልደ ኢትዮጵያ (ዲያስፖራ) የሐጅ አገልግሎትን በተመለከተ በቀጣይ ማብራሪያ እንደሚሰጥ ጠቅሰዋል።
#Ethiopia #Hajj
7 982
የፌደራል መንግሥቱ በትግራይ ክልል ጦርነቱ መጠናቀቁን ገልጾ የባለአደራ አስተዳደር መመሥረቱን አስታወቀ
በትግራይ ክልል ላለፉት ሦስት ሳምንታት የተካሄደው ጦርነት መጠናቀቁን ገልጾ ባለአደራ አስተዳደር መመስረቱን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።
የተቋቋመው የትግራይ ክልል የፊዴራል መንግሥት ባለአደራ አስተዳደር፣ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት ትግራይን የሚያስተዳደር ነው።
ዛሬ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ይፋ ያደረገው ባለአደራ አስተዳደር አምስት ዋና አስፈጻሚዎች ያሉት ነው።
=
1. አቶ አሰፋ አብርሃ ሐጎስ የአስተዳደር እና የሕዝብ አገልግሎት ዋና አስፈጻሚ
2. ዶክተር ቴዎድሮስ አረጋይ ወ/ሥላሴ - የኢኮኖሚ እና መልሶ ግንባታ ዋና አስፈጻሚ
3. ብ/ጄ ገብረ እግዚአብሔር በየነ ኃይሉ - የጸጥታና ሰላም ዋና አስፈጻሚ
4. አቶ ረዳኢ ኃለፎም ወ/ሥላሴ - የፖለቲካ እና ሕዝብ አደረጃጀት ዋና አስፈጻሚ
5. ዶክተር ሽሻይ አማረ - የመቐለ ከተማ ከንቲባ በመሆን ተሹመዋል።
ባለአደራ አስተዳደሩ በትግራይ ክልል የፈረሱ የመንግሥት መዋቅሮችን መልሶ መዘርጋት፣በጦርነት ምክንያት የተጎዱ መሠረተ ልማቶችን በመጠገንና ፈጥነው ወደ ሥራ እንዲገቡ ማድረግ፣የተፈናቀሉ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ወደየቀያቸው መመለስ የሚሉ እና ሌሎች 10 ኃላፊነቶች ተጥለውበታል።
#Ethiopia #Tigray
7 982
በግድያ ወንጀል በተጠረጠረው ኢዮብ እንዳለ ላይ ምርመራው ቀጥሏል
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 04 ቀን 2019 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ ተጠርጣሪ ኢዮብ እንዳለ ይባላል፤ የወንጀል ድርጊቱን የፈፀመው መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ/ም በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ ሠባት ልዩ ቦታው ብሔራዊ ቤተ መፃህፍትና ቤተ መዛግብት ( ወመዘክር ) ቅጥር ግቢ ውስጥ ከምሽቱ 2፡10 ሠዓት አካባቢ ነው፡፡
ፖሊስ ከተከሳሽ ቃል መረዳት እንደቻለው በግድያ ወንጀሉ የተከሰሰው ወጣት ኢዮብ እንዳለ ከሟች ዮርዳኖስ አምበሉ ጋር ከአንድ ዓመት በላይ ትውውቅ እንዳላቸውና በፍቅር ግንኙነት እንደቆዩ የገለጸ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ የሰው መግደል ወንጀሎች ምርመራ መምሪያ ኃላፊ የሆኑት ኮማንደር ኃይሉ ኡምኔሳ አስታውቀዋል፡፡
ከጊዜ ወደ ጊዜ የባህሪዋ መለዋወጥና በስልክ የምናደርገውን የድምፅ ድውውሎሽ ወደ ፅሁፍ መልዕክት በመቀየሯ በሌላ ሰው እንድጠረጥራት አድርጎኛል ያለው ተከሳሽ ኢዮብ፤ ሌላም ጊዜ ወደምንሄድበት ብሔራዊ ቤተ መፃህፍትና ቤተ መዛግብት (ወመዘክር) ለመገናኘት ከቀኑ 10፡00 ሠዓት አካባቢ ቄራ አካባቢ ተቀጣጥረን ነበር ብሏል፡፡
ቄራ አካባቢ በቀጠሮአችን ሰዓት ስላረፈደች የሽንኩርት መክተፊያ ቢላዋ በመግዛት ደብቆ ይዞ የጠበቃት ሲሆን ሟች ስትመጣም የራይድ ከፍላ ወደ ተባለው ወመዘክር ሄደዋል፡፡
ተከሳሽ ከዚህ ቀደም ከሟች ጋር ወደ ምንቀመጥበት ቦታ ላይ አረፍ ብለን ስናወራ ነበር ብሎ በመሀላችን በንግግር ያለ መግባባት በመፈጠሩ እና በሌላ ሰው ጥቃት ልታደርስብኝ ትችላለች በሚል ጥርጣሬ ለወንጀሉ ድርጊት በገዛሁት ቢላዋ አራት ቦታ ወግቻታለሁ ብሏል፡፡
#Ethiopia #AddisAbaba #YordanosAmbelu
7 982
በህወሓት ታጥቂዎች ሥር የነበሩት ጀነራል ታደሰ እና አራት ባለሥልጣናት አምልጠው በመከላከያ እጅ ገቡ
የቀድሞ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደን ጨምሮ፣ አራት የቀድሞ ባለሥልጣናት ከኤርትራ ድንበር አቅራቢያ በህወሓት ታጣቂዎች ቁጥጥር ሥር ከነበሩበት እስር ቤት አምልጠው በኢትዮጵያ ሠራዊት እጅ ከገቡ በኋላ ወደ መቀለ መመለሳቸውን ተናገሩ።
ዳግም የተቀሰቀሰው ጦርነት ከመጀመሩ በፊት በቀድሞ ጓዶቻቸው ከየቤታቸው ታግተው የተወሰዱት ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ፣ ኮሎኔል ተወልደ ገብረትንሳኤ፣ ኮሎኔል ዓለምሰገድ ገብረእግዚአብሔር እና አቶ ኢሳይያስ ታደሰ ላለፉት ሳምንታት የነበሩበት ሳይታወቅ ቆይቶ ነው ነጻ መውጣታቸው የተገለጸው።
ቢቢሲ ከታሳሪዎቹ አንዱ ከሆኑት ኮሎኔል ተወልደ ገብረትንሳኤ እና ከሌሎቹ የቅርብ ሰዎች እንዳረጋገጠው የቀድሞ ባለሥልጣናቱ ከህወሓት ታጣቂዎች ቁጥጥር ሥር አምልጠው ወደ መቀለ ተመልሰዋል።
በህወሓት አመራሮች ውሳኔ ተይዘው መቀለ በሚገኝ ሆቴል ውስጥ ቁጥጥር እየተደረገባቸው የቆዩት ባለሥልጣናት ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ በኋላ በኃይል ከሆቴል እንዲወጡ ተደርገው ከዋና ከተማዋ መቀሌ ውጪ ወደ ተለያዩ ቦታዎች መወሰዳቸውን ኮሎኔል ተወልደ ገብረትንሳኤ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ከአራቱ ታሳሪዎች አንዱ የሆኑት የቀድሞው የትግራይ ኃይሎች ወታደራዊ መረጃ ኃላፊ ኮሎኔል ተወልደ ገብረትንሳኤ ለቢቢሲ ትግርኛ በሰጡት ቃለ ምልልስ መከላከያ ሠራዊት እና አጋሩ የትግራይ ሰላም ኃይል ወደ ከተማዋ ከመግባታቸው ቀደም ብሎ ምሽት 5፡00 ከሆቴል ክፍላቸው አስወጥተው እንደወሰዷቸው ተናግረዋል።
#Ethiopia #Tigray #TPLF #TadesseWorede
7 982
+7
በብዙ ድራማ የታጀበው ታላቁ የሊቨርፑል ከማንችስተር ሲቲ ጨዋታ በ114 ክስ ጥፋተኛ በተባለው ሲቲ የበላይነት ተጠናቀቀ
ሲቲ ከሊጉ ይባረር ይሆን?
#PremierLeague #Liverpool #ManCity
7 982
ጌታቸው ረዳ ከ 19 ወራት ቆይታ በኋላ መቀሌ ገብተዋል
የቀድሞ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ከ 19 ወራት በኋላ ወደ መቀሌ ገብተዋል። አቶ ጌታቸው ከ ዶ/ር አብርሃም በላይ ጋር በመሆን ነው ወደ ከተማዋ መግባታቸው የተገለጸው።
ከህወሓት አመራሮች ጋር በነበራቸው አለመግባባት እና የሃሳብ ልዩነት ምክንያት ከመቀሌ ወጥተው ወደ አዲስ አበባ የመጡት አቶ ጌታቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አማካሪ በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ።
በአሁን ወቅት ስምረት የተሰኘ የፖለቲካ ፓርቲ በማቋቋም በፕሬዝዳንትነት እየመሩ ነው።
#Ethiopia #Tigray #Mekelle #GetachewReda
7 982
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቀለ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ እሁድ ይጀምራል
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀለ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ጥቅምት 1/ 2019 ዓ.ም. እንደሚጀምር አስታወቀ።
አየር መንገዱ በፌስቡክ ገጹ ዛሬ ዓርብ መስከረም 29/2019 ዓ.ም ባወጣው አጭር መግለጫ ከቀጣዩ እሁድ ጀምሮ የመቀለ በረራውን እንደሚጀምር ገልጿል።
የትግራይ ታጣቂ ኃይሎች መስከረም 13/ 2019 ዓ.ም. በክልሉ የሚገኙትን ሦስት አውሮፕላን ማረፊያዎች መቆጣጠራቸውን ተከትሎ አየር መንገዱ ወደ ትግራይ ክልል የሚደረጉ በረራዎችን ለጊዜው አቋርጦ ቆይቷል።
ከሁለት ሳምንት በላይ የተቋረጠው በረራ ከነገ በስቲያ እሁድ ይጀምሯል ተብሏል። ይሁን እንጂ በሌሎች የትግራይ ከተማዎች የተቋረጠው በረራ መቼ ይጀመራል የሚለውን አስመልክቶ አየር መንገዱ የገለጸው መረጃ የለም።
#Ethiopia #Tigray #Mekelle #EthiopianAirlines
7 982
+2
“ሁሉም ሚኒስትሮች ከፍተኛ ሚስጥራዊ ክትትል ሲደረግባቸው ነበር” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ መስከረም 28 አዲሱን ካቢኔያቸውን ይፋ አድርገዋል። በዚህ ካቢኔያቸው 22 ሚኒስትሮች የተካተቱ ሲሆን። አዳዲስ ሰዎች ወደ ሥልጣን መጥተዋል።
ሹመቱን በተመለከተ ዐቢይ ሲናገሩ፤ “ሁሉም ሚኒስትሮች እና ሚኒስትር ዴኤታዎች ላለፈው አንድ ዓመት ከፍተኛ ሚስጢራዊ ክትትል ሲደረግባቸው ነበር” ብለዋል።
ክትትሉ “በኢንተለጀንስ የተደገፈ” ነበር ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ያላቸው እንቅስቃሴ፣ ፣በልጆቻቸው፣በሚስቶቻቸው፣በአጎቶቻችው ከሚገናኟቸው ሃብታሞች ጋር በሙሉ የመረጃ ክትትል ይደረግ ነበር” ሲሉ ተናግረዋል።
የዛሬው ሹም ሽር የተደረገው በዚህ ግምገማ መሆኑን አስታውቀዋል። በዚህ ግምገማ ጥፋት የተገኘባቸው ሚኒስትሮች የካቢኔ አባላት አለመደረጋቸውን አስረድተዋል።
በዛሬው ሹመት ከሚኒስትርነት የተነሱ ባለሥልጣናት
👉የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር በለጠ ሞላ
👉 የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሐመድ
👉 የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል
👉የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)
👉 የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብርሃም በላይ(ዶ/ር)
👉የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ
👉 የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል
👉 የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)
👉 የሴቶችና ማኀበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)
👉የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ
👉የማዕድን ሚኒስትር አቶ ሃብታሙ ተገኝ ናቸው።
#Ethiopia
7 982
+2
ኤርትራ የኢትዮጵያን ድንበር ጣሰች - የኢትዮጵያ መንግሥት
የኤርትራ ወታደሮች የኢትዮጵያን ድንበር አልፈው በተለያዩ የትግራይ ከተማዎች መግባታቸውን የኮሙኒኬሽን ሚኒስትር እናታለም መለሰ ተናግረዋል።
ሚኒስትሯ ለ ብሉምበርግ በሰጡት መረጃ የኤርትራ " ወታደሮች ሉዓላዊ ግዛታችንን ጥሰው ገብተዋል። በአፋጣኝ መውጣት አለባቸው" ብለዋል።
ዛሬ መስከረም 27/2019 ዓ.ም በርካታ የዓለም አቀፍ መእናኛ ብዙኃን ትኩረት በዚህ ጉዳይ ላይ ሆኗል።
የፈረንሳይ ዜና ወኪል AFP ነዋሪዎችን ጠቅሶ እንደዘገበው የኤርትራ ወታደሮች በአዲግራት ከተማ በኩል በስተደቡብ ወደ ማዕከላዊው የትግራይ ክፍል መሰማራታቸውን ገልጿል።
የጀርመን ድምጽ ራዲዮ “የኤርትራ ጦር የኢትዮጵያ ድንበርን አቋርጦ ዘልቋል” ሲል ዘግቧል።
ወታደሮቹ የዓዲግራት ከተማንጥሰው በማለፍ ወደ ዕዳጋ ሓሙስ መግባታቸውን ነዋሪዎችን ጠቅሶ አስነብቧል።
ዘገባው አክሎ “ስማቸው እንዳይጠቀስየገለጹት የትግራይ የሰላም አዛዥ እንደሚሉት ዕዳጋ ሓሙስ ከገቡትየኤርትራ ወታደሮች ወደ አፅቢ ወንበርታ አቅጣጫ በ2 የጭነት መኪኖችተጭነው በሚጓዙበት ወቅት በድሮን ተመተዋል” ማለታቸውን ጠቅሷል።
ቢቢሲ በበኩሉ 40 የጭነት ተሽከርካሪ የኤርትራ ወታደሮችን ጭኖ ወደ ትግራይ ክልል መግባቱን ከነዋሪዎች መሰማቱን ገልጿል።
#Ethiopia #Eritrea
7 982
የኑሮ ውድነትና የብድር ጫና በዜጎች ላይ የደቀኑት ጭንቀት
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ በሰፊው እየታየ ያለው የኑሮ ውድነትና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣው የብድር ጫና፤ በዜጎች ዕለታዊ ሕይወት ላይ ከፍተኛ የፋይናንስ ጭንቀት (Financial Stress) እየፈጠረ እንደሚገኝ ሪፖርተር በዘገባው አመላክቷል።
የዕለታዊ ፍጆታ ዕቃዎች ዋጋ መናር፤ የቤት ኪራይ ጭማሪና የተበደሩትን ገንዘብ በተወሰነለት ጊዜ መመለስ አለመቻል፤ በዜጎች የአዕምሮ ሰላም፣ በማኀበራዊ ሕይወትና በሥራ ምርታማነት ላይ አሉታዊ ጫናን የሚያሳርፍ መሆኑን በመጥቀስ በቤተሰብ አስተዳደርና በወደፊት ተስፋ ላይም ትልቅ ሥጋት የሚፈጥር መሆኑን የምጣኔ ሐብት እና የሥነ ልቦና ባለሙያዎችን ሃሳብ አንጸባርቋል።
የሥነ ልቦና ባለሙያና የቤተሰብ አማካሪ ነቢያት ነቢሳ እንደገለጹት፤ የኑሮ ውድነትና የብድር ጫና ዜጎችን ለከፍተኛ ጭንቀት በመዳረግ በሕይወት የመቆየት ተስፋንም የሚያሳጣ ነው።
ለችግሩ መፍትሔ መኖሩን በመገንዘብ ዜጎች የተሻለ አምራች መሆን እንዲችሉ ማድረግ እንደሚቻልም ተናግረዋል።
የኑሮ ውድነትና የብድር ጫናን መቋቋም አለመቻል የሰዎችን ምርታማነትና የኢኮኖሚ አቅምን የሚያመናምን በአጠቃላይም ሕይወትን የሚያቃውስ በመሆኑ በቀላሉ ቸል መባል የለበትም ብለዋል።
የሥነ ልቦና ባለሙያው አክለውም የኑሮ ውድነት በየትኛውም ዓለም ላይ ባሉ ዜጎች ሥነ ልቦና ላይ ከፍተኛ ጫና እንደሚፈጥርና ሰዎች የተሻለ አቅም አውጥተው እንዳይሠሩ ትልቅ ፈተና እንደሚሆንባቸው አስረድተዋል።
ብድርን መልሶ አለመክፈል ዜጎችን ለከፍተኛ ወለድና ንብረት በሐራጅ መሸጥን የሚያስከትሉ ፈተናዎችን ያስከትላል። ይኸም ለከፍተኛ የሥነልቦና ጭንቀት በመዳረግ ጤናን እንደሚያቃውስና ተስፋን እንደሚያሳጣ ገልጸዋል።
#Ethiopia
7 982
+1
ሁለት ሚኒስትሮች አፈጉባዔ ሆነው ተሾሙ
የገንዘብ ሚኒስትር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ አሕመድ ሽዴ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ሆነው ሲመረጡ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባዔ በመሆን ተሹመዋል።
አቶ አሕመድ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ የነበሩት አቶ ታገሰ ጫፎን ተክተው ለቀጣይ አምስት ዓመታት የሚሠሩ ይሆናል።
ሙፈሪያት ደግሞ አቶ አገኘሁ ተሻገርን ይተካሉ። የቀድሞ የሲዳማ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ደስታ ሌዳሞ የወ/ሮ ሙፈሪያት ምክትል ሆነዋል።
#Ethiopia
