ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
الذهاب إلى القناة على Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
إظهار المزيد2 955
المشتركون
+1424 ساعات
+247 أيام
+38330 أيام
أرشيف المشاركات
አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር ከፍተኛ የአመራርና የክፍለ-ጦሮች የምክክር መድረክ አደረገ!!!
አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር የአፋብን ፖለቲካ መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ፕሮፌሰር ጌታ አስራደ እና ሁሉንም ክፍለ-ጦር ስራ አስፈጻሚዎችን ያካተተ የተልዕኮ ግምገማና የስትራቴጂክ አቅጣጫ ማስቀመጫ መድረክ አካሂዷል።
ከአፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ ካሉ የውጊያ ቀጠናዎች በከፈለው ከፍተኛ መስዋዕትነትና በጀግንነት ታሪኩ የሚታወቀው 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር ተቋማዊ ሪፎርም መስራቱን ተከትሎ የሰራዊቱን የውጊያ ዝግጁነትና የዕዝ ሰንሰለት ይበልጥ ወደላቀ ደረጃ ማሸጋገሩ ይታወቃል። ይህ የምክክር መድረክም በሪፎርሙ ማግስት የተመዘገቡ ስኬቶችን ለመገምገምና የቀጣይ ስምሪቶችን እና ስልታዊ ግቦችን ለመቅረጽ ነበር።
በዚሁ መድረክ ላይ ባለፉት ሁለት ወራት በኮሩ የኃላፊነት ቀጠና ውስጥ የተከናወኑ ወታደራዊና አስተዳደራዊ ተግባራት በጥልቀት ተገምግመዋል። ኮሩ በስትራቴጂ፣ በሎጅስቲክስ አቅርቦትና በኃይል ግንባታ ረገድ ያስመዘገባቸውን ውጤቶች የመዘነ ሲሆን፣ በተለይም የሰራዊቱን የውጊያ ስነ-ምግባርና ዝግጁነት በዘላቂነት ለማስቀጠል የሚያስችል አዲስ የኮሩ መተዳደሪያ ደንብና የዲስፕሊን መመሪያ ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።
በመጨረሻም፣ መድረኩ የቀጣይ ወራትን ስልታዊ የክወና ዕቅድ ያጸደቀ ሲሆን፣ ወቅታዊ በሆኑ ቀጠናዊ የፀጥታ አጀንዳዎችና ስጋቶች ፣ የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎችን ፈተና ማስፈጸም ላይም ጥብቅ ወታደራዊ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።
የአካባቢውን አስተማማኝ ሰላምና ደህንነት ለማስከበር በየደረጃው የሚገኘው የክፍለ-ጦር አመራርና መላው የኮሩ አባላት የተሰጣቸውን ግዳጅ በላቀ የውጊያ ጥበብና ቁርጠኝነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን በድጋሚ በማረጋገጥ፣ መድረኩ የተቀመጡትን ስልታዊ ግቦች በውጤታማነት ለመተግበር የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ ተጠናቋል።
ድል ለአማራ ህዝብ !!!
ድል ለአማራ ፋኖ !!!
አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር ቃል አቀባይ ክፍል!!!
ዋግኸምራ ምድር ሐሙሲት ግምባር 303ኛ ኮር 14ኛ ክፍለጦር በጠላት ላይ ታላቅ ድል ተቀዳጁ!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ 303ኛ ኮር 14ኛ ክፍለጦር አካል የሆነችው ሁለተኛ ማንኩሽ ሻለቃ በዋግኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን መቀመጫ ሰቆጣ ከተማ በስተደቡብ ምስራቅ 35 ኪሎ ሜትር ርቀት ከምትገኘው ሰቆጣ ዙሪያ ወረዳ ሐሙሲት ከተማ ላይ በመግባት ታላቅ ጀብዱ ፈፅመዋል።
ሰኔ 05 ቀን 2018 ዓ/ም ከንጋቱ 10:00 ሰዓት እስከ ረፋዱ 4:00 ሰዓት በተደረገ የደፈጣና ሽምቅ ውጊያ ዙሪያውን ከበባ በማድረግና በማፈን እንዲሁም መብረቃዊ ጥቃት በመፈፀም በአገዛዙ ሚሊሻ አባላትና ራሳቸውን ስምረት ብለው በሚጠሩ በጌታቸው ረዳ የሚመሩ ኃይሎች ላይ ከፍተኛ የሆነ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ በማድረስ በጠላት ላይ ድል ተጎናፅፈዋል።
ራሱን ስምረት ብሎ የሚጠራው ኃይልም ሞርታር-82 ወደ ሐሙሲት ከተማ ሁለት ጊዜ በማስወንጨፍ ንፁሃንን የጨፈጨፈ ሲሆን በተወረወረው ቅምቡላ ስድስት ንፁሃን ውድ ህይወታቸውን ሲያጡ ከአስራ አምስት በላይ ንፁሃን ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው እና ወደ ሰቆጣ ሆስፒታል ሪፈር እንደተባሉ የአይን እማኞች መረጃውን አድርሰዋል።
በተደረገው አውደ ውጊያ 15 ተደምስሶ፣ ሰድስት ሲቆስል፣ ሁለት ሚሊሻ ተማርኳል ፤ እንዲሁም ሁለት ጂምስሪ(GM-3)፣ አንድ ኤምፎርቲ(M-40) እና ዘጠኝ ክላሽንኮፍ በመማረክ ወደ ክፍለ ጦሩ ካዝና ገቢ መደረጉን የ14ኛ ክፍለ ጦር ቃል አቀባይ አርበኛ ሐብቱ ማሞ (ራስታው) አስታውቋል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የ303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ሰኔ 05/2018 ዓ.ም
በ2እጅ እነሴ ወረዳ ጥሩሰላም ቀበሌ (አራጢ) ላይ በወቅታዊ ጉዳዮች ከህዝቡ ጋር የክ/ጦር አመራሮች በመገኘት ውይይት ተካሄደ።
^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^
ሰኔ05/2018ዓ.ም
የአፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 54ኛ ክ/ጦር በ2እጁ እነሴ ወረዳ ጥሩሰላም ቀበሌ {አራጢ} በጀግኖች የትውልድ ቀዬ የአመራር ውይይት አካሔደ።
የአብይ አህመድ ሰራዊት አራጢን ሲያስብ እንቅልፍ አይተኛም፤ጉልበቱ ይርዳል።
ቀጠናው በአማራ የትግል አብዮት ውስጥ ታሪክ ከሚዘክራቸው የእኔ ተፈራ ደምጤ(ተፌ) እና ሌሎች የትውልድ ቀዬ ነው።
ከ2ኛ ተፈራ ዳምጤ እስከ 54ኛ ክ/ጦር የቀጠለው የቀጠናውን ጀብደኝነት በወትሮው ግለት ማስቀጠል ብሎም ማሻሻል ላይ ከጥሩ ሰላም ቀበሌ ተዋጊ ኃይል ጋር የጋራ ውይይት ተደርጓል።
በቀጠናው የቀበሌ መዋቅርና ህዝባዊ አስተዳደርን ጨምሮ የተገመገመና የወደፊት አቅጣጫ የተቀመጠበት መድረክም ሲሆን
በውይይቱ የህዝባችንን የትግል አረዳድና ቁርጠኝነት የተረዳንበት መድረክ ነበር።
እናደራጃለን ! እንመክራለን! እንፈፅማለን!!
አዲስ ትውለድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!!
አፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
📌የአገዛዙ 59ኛ ክፍለ ጦር የብልጽግና ታጣቂ ወታደሮች የፋኖ አባላትን መቀላቀላቸው ተገለፀ‼️
=========================
ሰኔ (5/2018ዓ.ም)
አፋብን ሰሜን አማራ በላይ ዕዝ ሜ/ጄኔራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ጉና ክፍለ ጦር ስር
አናብስቶችን የስርዓቱ ቡችላዎች ፀረ-አማራ የነበሩ ሃይሎች እስቴ ዴንሳ ብርጌድ ፋኖን እንዲቀላቀሉ ተደርገዋል=====!!
በእስቴ ዴንሳ ብርጌድ አናብስቶች በተደጋጋሚ በደረሰባቸው ብርቱ ምት እና የአገዛዙ ስርዓትን አስከፊነት የተረዱ የኦህዴድ አገልጋዮች አሁንም ቢሆን አልመሽም በማለት እውነተኛውን የትግል መስመር በመምርጥ ዘመን ተሻጋሪና ተራማገጅ የትግል ጉዞ ተቀላቅለዋል።
👉ሁለት/2/ አድማ ብተና
👉አራት/4/ መከላከያ
በአጠቃላይ ስድስት/6/የአገዛዙ ታጣቂ ሃይል በዛሬው ዕለት እንደ ሰማይ ኮከብ የምትወረወረውን የእስቴ ዴንሳ ብረጌድ አካል ሁነዋል።
📌 የአገዛዙ ታጣቂ ሃይሎች ሰማቸው እንደሚከተለው ተዘርዝርዋል፦
👉ይመር እሽቱ ➔ አድማ ብተና
👉 መንግስቱ ዳንኤል ➔ መካላከያ
👉፲ አለቃ ክፍሌ ሃይሌ➔ መከላከያ
👉ኮንስታብል አለባቸው ስዩም➔ አድማ ብተና
👉ቀነኔሳ ደጀኔ ➔መከላከያ
👉ያሬድ አብዲ ➔ መከላከያ
ሲሆኑ ፣ሌሎች የታጠቁ የአገዛዙ ወታደሮች የፋኖን መንፈስ እንዲለበሱ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
ሜ/ጀኔራል ውባንተ አባተ፩ኛ ኮር ጉና ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ
መምህር ያሬድ ገደፍው
የአፄ አምደ ፅዮን ኮር በስሩ ለሚገኙ የክፍለጦርና የሻለቃ የህዝብ ግንኙነት ክፍል አመራሮች መሰረታዊ የICT ክህሎት አጭር ስልጠና ሰጥቶ ማጠናቀቁን አስታወቀ።
አፋብን ሸ/ጠ/ግ/አ/ዕዝ
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አካል የሆነው የአፄ አምደ ፅዮን ኮር በስሩ ለሚገኙ የክፍለጦርና የሻለቃ የህዝብ ግንኙነት ክፍል አመራሮች ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ እንዲሁም ቀልጣፋ የመረጃ ልውውጥን ለማሳለጥ ታሳቢ ያደረገ መሰረታዊ የአይሲቲ (ICT) ክህሎት ስልጠና በመስጠት ማጠናቀቁን ኮሩ ለዕዙ በላከው የስራ ሪፖርት መረጃ አስታውቋል።
ለተጀመረው የህልውና ትግል ዘመናዊ አሰራርን በማጎልበት በኮሩ ስር የሚገኙ ንዑሳን ክፍሎችን እያበቃ መሆኑን የገለፀው የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የአፄ አምደ ፅዮን ኮር በስሩ ለሚገኙ የክፍለጦርና የሻለቃ የህዝብ ግንኙነት ክፍል አመራሮች ለተከታታይ ቀናት የሰጠውን ስልጠና በስኬት ሲያጠናቅቅ ለስልጠናው የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን በሟሟላት ለሰልጣኞች ስምሪት መሰጠቱን ኮሩ ገልጿል።
''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት''
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
ሰኔ 05/2018ዓ.ም
አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ መሀመድ ቢሆነኝ ኮር የአስቴ ጎማ ተራራ ክፍለ ጦር ሰራዊትጥልቅ ውይይት እና ግምገማ አደረገ!!
ሰኔ 4 ቀን 2018 ዓ.ም
የአስቴ ጎማ ተራራ ክፍለ ጦር ሰራዊትና ከክፍለ ጦሩ ከፍተኛ አመራሮች፣ የአፋብን ወታደራዊ ቃል አቀባይአርበኛ አበበ ሙላቱ እና የሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ምክትል ዘመቻ መሪ መቶ አለቃ ኤርሚያስ ግጨው በቦታው በመገኘት በተደረገ ሰፊ ውይይት የሰራዊት የስነልቦና ግንባታ ስራ በመስራት ለቀጣይ ማንኛውም ድርጅታዊ ተልዕኮ ዝግጁ መሆኑን አረጋገጠ።
ዛሬ በተካሄደው በዚህ የውይይት መድረክ ላይ የአመራር አካላቱና አርበኞቹ ከሰራዊቱ ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በዝርዝር የመከሩ ሲሆን፣ ሰራዊቱ የተሰጠውን ኃላፊነት በላቀ ብቃት መወጣት በሚችልበት አቅም ላይ ሰፊ ግንዛቤ ተፈጥሯል።
በተለይ በየሻለቃው ለሚገኘው ሰራዊት የተደረገው የስነ-ልቦና ማነቃቂያ መድረክ በከፍተኛ ስሜት ቀስቃሽነትና አነቃቂነት የተሞላ ነበር። ሰራዊቱም በተደረገለት በዚህ ሁለንተናዊ የማነቃቂያ ውይይት ታላቅ ደስታ እንደተሰማውና ዝግጁነቱን ይበልጥ እንዳጠናከረ ታውቋል።
ከውይይቱ ማጠናቀቂያ በኋላ የሰራዊቱ አባላት ባስተላለፉት መልዕክት በተደረገላቸው ወቅታዊና ስነ-ልቦናዊ ማነቃቂያ ውይይት መሪወችን አመስግነው በሂደቱም እጅግ መደሰታቸውን ገልጸዋል። በቀጣይም ይህ ግንባታና ማበረታታት ይቀጥል። እኛም የድርጅታችንን ግብ ለማሳካት የዕዝ ሰንሰለት በመጠበቅ ነገም እንደ ትላንቱ ታሪክ መስራታችን ይቀጥላል። ሲሉ በሙሉ እምነትና በልበ-ሙሉነት ተናግረዋል።
የክፍለ ጦሩ አመራሮች በበኩላቸው ሰራዊቱ ላሳየው ከፍተኛ ተነሳሽነትና ልበ -ሙሉነት ምስጋናቸውን አቅርበው፣ መሰል የውይይት መድረኮች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።
''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት''
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !!
ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
ሰኔ 04/2018 ዓ.ም
የብልፅግና አገዛዝ ቡድን እርስ በርሱ መተኳኮስ እና መበተኑን ቀጥሎበታል !!
ሰኔ 04/2018 ዓ.ም
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ብትር መቋቋም ያቃተው የአገዛዙ ሀይል በመጨረሻመም እርስ በርሱ በመጠራጠር እየተመታታ እየተበተነ መሆኑን የግንባር መረጃወቻችን ጠቁመዋል።
በመፈራረስ ላይ የሚገኘው የብልፅግናዉ ዘራፊ እና ጨፍጫፊ ቡድን በደብረ ብርሃን ከተማ እርስ በርስ በመተኳኮስ መጠፋፋቱ እንደቀጠለ ሲሆን ይህንንም ክፍተት በመጠቀም ቀኜ የሚፈለገው ሀይል ላይ እርምጃ ወስዷል።
ትናንት ማለትም በቀን 03/10/2018 ዓ/ም ከረፋዱ 5:30 ገደማ ላይ በደብረ ብርሃን ከተማ ስር በሚገኙት በሁለቱ ክፍለ ከተሞች ማለትም፡ በአፄ ዘርዓያዕቆብ ክፍለ ከተማና በእቴጌ ጣይቱ ክፍለ ከተማ በነበረ የአገዛዙ የእርስ በርስ ተኩስን በመጠቀም ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸውን የማንጠቅሰው የውስጥ ቀኜ አባሎች በወሰዱት እርምጃ የቆሰሉ እንዳሉ ቢታወቅም ፤ በነበረው የተኩስ ልውውጥ 2 የሚሊሻ አባላት እና 1 የፖሊስ አባል ሲገደሉ ፤ በነበረው የተኩስ ልውውጥ ውስጥ በውር ድንብር መውጫ መግቢያ የጠፋው የአገዛዙ ሀይል ከጉዳዩ ጋር ምንም ከማያገናኛት አንድ ንፁሃን የከተማ ነዋሪ ላይ በመተኮስ ያቆሰላት መሆኑ እና በህክምና እርዳታ ውስጥ እንዳለች መሆኑ ተረጋግጧል።
ይህ የአገዛዙ ሀይል ወደ አለመተማመን የገባና በመጨረሻም እርስ በርሱ መጠፋፋቱ ወደ ለዬለት መተኳኮስ የሚያመራና የማይቀር በመሆኑ አሁንም ወደ ቤተሰብ የመቀላቀል ዕድላቸውን እየተጠቀሙ ወደ ፋኖ የሚገቡ የሚሊሻ እና አድማ ብተና አባላት ቁጥር እንደቀጠለ ነው። ይህን ዕድላችሁን ሁላችሁም የአገዛዙ መጠቀሚያ ሀይል አባላት ትጠቀሙ ዘንድ ውስን ጊዜ አላችሁ።
''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት''
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !!
ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ሰኔ 04/2018 ዓ.ም
50 አለቃ ካሳሁን ኃይሌ በመሐል ሳይንት ግንባር የአፋብን ወሎ ቤተ_አማራ ምኒልክ ዕዝ 105ኛ 47ኛ ክ/ጦር #አትሮንስ_ሻለቃን ተቀላቀለ:: 50 አለቃው የዲሽቃ ምድብተኛ ሻንበል መሪ ነበር።
50 አለቃ ካሳሁን ኃይሌ ስለጠላት አሁናዊ ቁመና ሲናገር "ለምንና በምን ምክንያት እንደሚዋጋ የማያውቅ፤ ዓላማ የሌለውና የጥቂት ግለሰቦችን ሥልጣን ለማስከበር መተኪያ የሌላትን አንድያ ህይወቱን የሚገብር በመሆኑ፣ መላው ሠራዊት በደመ_ነፍስ የሚቅበዘበዝ ሆኗል። ሞራሉም ዋዥቋል፤ ወታደር የሞራል ስንቅ ካልታጠቀ ደግሞ በየአውደ_ውጊያው የሽንፈትን ፅዋ ቢጎነጭ የሚደንቅ አይደለም" ብሏል።
የአፋብን ወሎ ቤተ_አማራ ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር የዘመቻ መምሪያ ም/ኃላፊው አርበኛ ጎሹ ታረቀ ኮብላዩን በክብር ተቀብሎታል!
ምንጭ:- የአፋብን ወሎ ቤተ_አማራ ምኒልክ ዕዝ 105ኛ 47ኛ ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ Eyob Ashenafi
ከ"ዘመቻ ህፃን አንሻ ሰይድ" ማግስት የብልፅግና ሰራዊት መፍረሱን ቀጥሏል!
ለብልፅግና የዙፋን መንበር በማወቅም ይሁን ባለማወቅ እየታተረና እየተጋ የሚገኘው ብልፅግና መራሹ ጦር በዘመቻ ህፃን አንሻ ሰይድ በከባድ ሚዛን በፋኖ ክንድ የተመታው ሰራዊት ከአሐዱ በመፍረስ ፋኖ ወደሚገኝበት ቦታ ሁሉ እየተቀላቀለ ይገኛል።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ 303ኛ ኮር አካል የሆነውን 19ኛ ክፍለ ጦርን የተቀላቀሉት አስር አለቃ አማረ ተፈራ እና ጓደኛው ከ34ኛ ክፍለ ጦር አራተኛ ሬጅመንት በመውጣት የፋኖን ቤት የተቀላቀሉ ሲሆን መከላከያ አሁን ባለው ቁመና የመዋጋት አቅም እንደሌለውና ሰራዊቱም በፍፁም መሰላቸትና በከባድ የስነ-ልቦና ውድቀት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።
በሌላ መረጃ 303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር አካል የሆነውን 30ኛ ክፍለ ጦርን የተቀላቀሉት የ13ኛ ዕዝ ኦፕሬተር የነበሩት:-
1ኛ. መሰረታዊ ወታደር ማርይሁን ጌታ
2ኛ. መሰረታዊ ወታደር ዮሴፍ አዱኛው
3ኛ. መሰረታዊ ወታደር ቴዎድሮስ ጥላሁን
ሁላቸውንም ቤተሰቦቻቸው ልከው ከሚያስተምሯቸው ኮሌጅ ላይ በማፈን ወደ ማሰልጠኛ በማስገባት ተገደው የገቡ እንደሆኑ ገልፀው የአገዛዙን ጓዳ ከፈተሹና ከመረመሩ በኋላ ለቤተሰቦቻችንና ወንድም እህቶቻችን ማጥፊያ ስርዓትና ተቋም አናገለግልም በማለት ፋኖን እንደተቀላቀሉ ተናግረዋል።
ስቦ በማስከዳት ስርዓቱን ከማፍረስ ጋር ተያይዞ ከመስከረም 14/2018 ዓ/ም ዘመቻ አደም አሊ (አባ ናደው)ን ጨምሮ ለተከታታይ ስምንት ወራት ከ850 በላይ የአገዛዙ ሰራዊት መከላከያ፣ አድማ ብተና፣ ፖሊስ፣ ሚሊሻና ስርዓቱን አገልጋይ ካቢኔ አባላት 303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር ፋኖን የተቀላቀሉ ሲሆን አሁንም አልረፈደምና ቀሪው የአገዛዙ ሰራዊት በፍጥነት ፋኖን በመቀላቀል ህይዎቱን እንዲታደግ ሲል የኮሩ ፖለቲካ መምሪያ ኃላፊ አርበኛ በሪሁን ደምሌ ጥሪ አቅርቧል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የ303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን መምሪያ
ሰኔ 04/2018 ዓ.ም
አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ወገንን የማንቃት እና ጠላትን የማፍረሱን ስራ ዛሬም እንደ ትላንቱ ቀጥለውበታል!
የኦህዴድ/ብልፅግና ሥልጣን ጠባቂ ቅጥረኞች ከአመራር እስከ መሠረታዊ ወታደር እንደ እንቧይ ካብ እየተናደ ነው። 11ኛ ዕዝ 104ኛ ኮር 9ኛ ክ/ጦር እንደ ጨው እየሟሟች ነው። ይህ ወንጀለኛ ቡድን ሥልጣኑን ለማራዘም በመሰዊያው አምድ ላይ ለማቆም በትምህርት ቤትና በሌሎችም ቦታዎች እያፈሰ ያስገባቸው ወታደሮች "በእኛ ውድ ህይወት የአንባገነኖችን ሥልጣን አናፀናም" በማለት ወደ ወገን መቀላቀላቸውን ቀጥለዋል።
ዛሬ 03/10/2018 ዓ.ም አትሮንስ ሻለቃን የተቀላቀለው 50 አለቃ ካሳሁን ኃይሌ የዲሽቃ ምድብተኛ ሻንበል መሪ ነው። ሃምሳ አለቃ ካሳሁን ኃይሌ ስለጠላት አሁናዊ ቁመና ሲናገር "ለምንና በምን ምክንያት እንደሚዋጋ የማያውቅ፤ ዓላማ የሌለውና የጥቂት ግለሰቦችን ሥልጣን ለማስከበር መተኪያ የሌላትን አንድያ ህይወቱን የሚገብር፣ በመሆኑ መላው ሠራዊት በደመ-ነፍስ የሚቅበዘበዝ ሆኗል። ሞራሉም ዋዥቋል፤ ወታደር የሞራል ስንቅ ካልታጠቀ ደግሞ በየአውደ-ውጊያው የሽንፈትን ፅዋ ቢጎነጭ የሚደንቅ አይደለም " ብሏል።
በዚሁ ምዕራብ ወሎ ቀጠና በጃማ ወረዳ 33ኛ ዋሲል ክፍለጦር ነፃ ባወጣው አህያፈጅ ቀጠና ከአሉ የአባት አርበኞች ጋር አመርቂ ውይይት አካሄደ። በዚህ ውይይት አሁናዊ የአማራ ሕዝብ የትግል ቁመና፣ የአማራ ትግ የደረሰበት ደረጃ እና ወቅታዊ የአገዛዙን ውድቀት ላይ ጥልቅ ውይይት ከአባት አርበኞቹ ጋር ተካሂዷል። የብልፅግናው አገዛዝ ሊያደርገው የነበረውን የማደናገሪያ ምርጫ በአባት አርበኛው ንቁ ተሳትፎ እንደከሸፈ በዚህም የአፋብን ወታደራዊ ፍርድ ቤት ሰብሳቢ አርበኛ አለባቸው ቀስቅሴ ምስጋና አቅርበዋል። አርበኛው አያይዘውም በመጭው ወራት አማራ ጠሉን ጥቁር ናዚ ስርዓት ሙሉ በሙሉ እናፀዳዋለን ብለዋል። ለዚህም ሁሉም የአማራ ህዝብና የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ደጋፊ ኢትዮጰያዊ ራሱን ለመጨረሻው የለውጥ አብዮት ያዘጋጅ ብለዋል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ሰኔ 03/2018 ዓ.ም
