ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
الذهاب إلى القناة على Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
إظهار المزيد4 418
المشتركون
+1224 ساعات
+287 أيام
+1 15930 أيام
أرشيف المشاركات
ጓዶቻቸው በአማራ ፋኖ የተሰነበቱባቸው የአገዛዙ ስልጣን አስጠባቂ ወጣቶች አሁን ላይ ያሉበት ሁኔታ😰
እኛም በሰላም እጅ ስጡ እና ወደ እናት፣አባቶቻሁ
በክብር እንሸኛችሁ ብለናል…እንቢ አሻፈረኝ ካላችሁ ግን እንደናተ ንፁሀን እናት፣አባ እና እህት፣ወንሞሞቻችሁን በግፍ በአሰቃቂ ሁኔታ በመግደል ሳይሆን በእውነት፣ስለ እውነት ታግለን ከዚህ በከፋ ሁኔታ ቅስማችሁን💪🏽 በመስበር ገና ደም፣እናስለቅሳችሁአለን!😭😭
ይህ ነው የሰው መከራ መሰረታዊ ምክንያት፡፡
ከራሱ በተቃራኒ የተከፋፈለ ሰው ገሀነብ ውስጥ እንደሆነ ነው የሚቀረው፤ ገነት የምትወለደው ሰው ከራሱ በተቃርኖ ካልተከፋፈለ ብቻ ነው፡፡
የተከፋፈለ ሰው ማለት መከረኛ ማለት ሲሆን ውህድ የሆነ ሰው ማለት የተባረከ ሰው ማለት ነው፡፡
እስካሁን የሰው ልጅ ብትንትኑ የወጣ ሆኗል፡፡ ምክንያቱም ብዙ ጊዜ ተፈጥሯዊ ሰብዓችሁን እንድትኮንኑ፣ እንድታስወግዱ፣ እንድትክዱ ተነግሯችኋል፡፡
እናም እነዚሀ ተፈጥሯዊ ነገሮችን ለማስወገድ፣ ለመካድ በመሞከር ልታጠፏቸው አይቻላችሁም:: እነዚህ ተፈጥሯዊ ነገሮች ከስር ብቻ ነው የሚጓዙት፣ ከያልነቃው አዕምሯችሁ ውስጥ ነው የሚሰሩት፤ እናም የእውነት በጣም አደገኞች ናቸው፡፡
ሰው ተፈጥሯዊ እና ምሉዕ ነው፡፡ እናም እግዝሀብሄር ለሰው የሰጠው ሁሉም ነገር ጥቅም ላይ መዋል አለበት፡፡ አንዳች ነገር ሊካድ አይገባም፡፡ የሰው ልጅ ኦርኬስትራ መሆን ይችላል፤ የሚፈለገው ብቸኛ ነገር በራሳችሁ ውስጥ ሰላማዊ ህብራዊነት የመፍጠር ጥበብን መለማመድ ብቻ ነው፡፡ ዴቭ
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
እጅግ ያሳዝናል ! 😭
ይህ ወጣት ልጅ ልገንዘበው አቦ ይባላል ። ተወልዶ ያደገው በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን አሰኮ ወረዳ፡ ጨፋ ቁዮ ቀበሌ ነው ። ይህ ወጣት በግል ስራ እየታተር ይተዳደር ነበር ።
ከሰሞኑ ታዲያ በቀን 28/01/2018 ዓ.ም ለስራ ጉዳይ በሚንቀሳቀስበት ወቅት በመርቲ ወረዳ፡ ቢጮ በትምባል ልዩ ቦታ አማራ ስለሆነ ብቻ በኦነግ ሸኔ ታግቶ በአሰቃቂ ሁኔታ መገደሉ ተሰምቷል ።
- የአገዛዙ መንግሥት ስለ ፋኖ በየሚዲያው ኡ...ኡ...ኡ... ሲል እየዋለ፤ ስለ ሸኔው ግን አንዳች አይተነፍስም ። እናም የአንድ ዓላማ እጆች ተባብረው አማራን እና ኦርቶዶክስን ማጥፋት ምግባራቸው ከሆነ ሰነባብቷል ።
"አማራውን እርስ በእርሱ ደም አቃብተነዋል"
ጥሬ ስጋ እየቀለብን አሰልጥነን ያስቀመጥነው ሰራዊት አለን (የኦሮሚያ ልዩ ሀይል) ፈተን እንለቅበታለን።
ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ
ሚሊሻ ሆኖ ከፋኖ ቤተሰብ ያልገደለ የለም በተመሳሳይ ፋኖ ሆኖ ከሚሊሻ ቤተሰብ ያልገደለ የለም ። በአማራ ባህል ደግሞ ደም ሳይመልሱ መቅረት እንደነውር የሚቆጠር ነገር አለ ፣ ስለዚህ አሁን ላይ ዕርስበርስ ለግድያ የሚፈላለጉ ደመኞች ሆነዋል፥ ፋኖን አጥፋልን ብለን የምንለምነው ሚሊሻ አይኖረንም ለራሱ ሲል የራሱን ህይወት ለማትረፍ ሲል ያለምንም ክፍያ ፋኖን ያሳድድልናል።በእንደዚህ አይነት መንገድ እጃችንላይ ያለውን ገንዘብ ለሚሊሻ ከመበተን ድነናል፣ ገንዘቡን ለገዳ ልዩ ኮማንዶ ማሰልጠኛ እና መሳሪያ መግዣ ይውላል። አማራ ከዚህ በሗላ ከነሙሉ ክብሩ በአባገዳ ልጆች ፊት የሚቆምበት ዘመን አብቅቷል ማንም አባከና የሚለው ሰው አይኖርም። ቀደም ብየ እንደነገርኳችሁ አማራ ከዚህ በኋላ እስከምፅዓት ድረስ ምንም አይነት የፖለቲካ ወሳኔ ሰጭነት ሚና እንዳይኖረው አድርገን ሰርተናል አንዳንዶች ይሄን ስንል መታበይ ይመስላቸዋል ነገር ግን ፖለቲካውን የሰራነው ሰዎች ስለምናውቀው ነው። ከእንግዲህ ኦሮሞ ማድረግ ያለበት ስትበድለው ከነበረችው ሚኒሊክ ሰራሽ ሐገር ቁጭ ብሎ ካሳ መቀበል ብቻ ነው። ከኦሮሞ ጋር ሰላም ፈጥሬ እኖራለሁ የሚል አካል ካለ እሱን እንቀበላለን ነገር ግን አካሔዱ የሚሆነው ኦሮሞ በሚወስንለት ማነኛውም ህግና ድንጋጌ ሊመራ እና ሊተዳደር አምኖ ከተቀበለ ብቻ ይሆናል። ይሄን ካልተቀበለ ጥሬ ስጋ እየቀለብን አሰልጥነን ያስቀመጥነው ሰራዊት አለን (የኦሮሚያ ልዩ ሀይል)ፈተን እንለቅበታለን ማለት ነው።
-ሽመልስ አብዲሳ ❗የኦሮሚያ ገዳ ልዩ ኮማንዶ የምርቃት ስነስርዓት ላይ የተናገሩት።
የአማራ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር በዘመቻ ኮማንዶ ደምሰው ከተማው ከፍተኛ የጦር ሜዳ ድል አስመዘገበ::
በምዕራብ ወሎ ግንባር መሀል ሳይንት ወረዳ ውስጥ ከትናንት ማለትም መስከረም 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ዛሬ እኩለ ቀን ድረስ በተደረገው ትንቅንቅ የንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ሰራዊት የመሀል ሳይንት ወረዳ መቀመጫ የሆነችው ደንሣ ከተማ ውስጥ መግባቱ ተርጋግጧል::
ከኮሩ ሰራዊት መካከል የአማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለ ጦር፣ የመብረቅ ክፍለ ጦር እና የኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለ ጦር የተወሰኑ አሃዶች ተውጣጥተው በሰሩት ኦፕሬሽን እስካሁን በደረሰን መረጃ መሰረት ከ30 በላይ ጠላት የተደመሰሰ ሲሆን 1 የአድማ ብተና ሻለቃ መሪ እና 1 ሻምበል መሪ እንዲሁም 3 የወረዳ አመራሮችም አብረው እስከወዳኛው ተሸኝተዋል:: የተደመሰሰው ጠላት ቁጥር ሊጨምር እንደሚችልም ይገመታል::
በኦፕሬሽኑ 11 የጠላት ምርኮኛ እንደተያዘም ነው ለማረጋገጥ የተቻለው::
በምኒልክ ዕዝ ም/ዘመቻ መሪ ኮሎኔል ፈንታው መኩዬ፣ በዕዙ ም/ወታደራዊ አዛዥ ሻለቃ ሀብታሙ ደምሴ እና በንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር አዛዥ በአርበኛ አብነው ታደሰ እንዲሁም በዕዙ ወታደራዊ አማካሪ በሻለቃ ክንዱ ሰውነት የተመራው የደንሣው ኦፕሬሽን የጠላት 4 ከባድ ምሽጎች የተሰበሩበት መሆኑም ታውቋል:: በከተማይቱ ዳር ማለትም በጎራደ ሽነት፣ በዙሀ፣ በጎጃም በር እና በሙያ እና ቴክኒክ ጠላት ያዘጋጃቸው ምሽጎች ሙሉ በሙሉ ተሰብረዋል::
ጠላት ሲጠቀምባቸው የነበሩ ቁሳቁሶች እና ሌሎች ንብረቶች በኮሩ ሰራዊት እጅ ገብተው ወደ ፋኖ የጦር ሰፈር የተወሰዱ ሲሆን በኮሎኔል መብሬ የተመራው የጠላት ኃይል ከእስከዛሬው በበለጠ አኳኃን ከባድ ሰብአዊ ኪሳራ ጭምር እንደደረሰበት ነው የውስጥ ወታደራዊ ምንጮች የገለፁት::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥቅምት 2 ቀን 2018 ዓ.ም
አገዛዙ ሊረዳው ያልቻለው ጉዳይ!
ነጮቹ ''Accepting defeat is a beginning of victory/ሽንፈትን አምኖ መቀበል የድል ጅማሮ ነው!'' ይላሉ።
አሜሪካዊው ሊዮን ብሎደር ''When Accepting Defeat Is Winning'' በሚል መጣጥፉ ላይ '' ..እየተዋጋህ ወደፊት ለመቀጠል የሚያስችል አቅሙና ጥንካሬው ባይሟጠጥብህ እንኳ የተጓዝክበትን የሽንፈት መንገድ እየደገምክ መቀጠልህን ከተረዳህና አላስፈላጊ ዋጋ መክፈል መሆኑን ከተገነዘብክ በጊዜ ሽንፈትህን አምኖ መቀበል ከአሸናፊነት የማይተናነስ ውጤት አለው። ሁኔታው እንግዳ ቢመስልም ፣ ራስን በማግለል እፎይታን የሚያቀዳጅ ብሎም የተሻለ መፍትሔ እንዲመጣ በር የሚከፍት ውሳኔ ነው!'' ሲል የሚገልፀውም ይህንኑ ነው።
በተለይ ደግሞ እንደኛ በእርስበርስ ጦርነት ውስጥ ተዘፍቆና በገዛ ህዝቡ ላይ ጦርነት ማወጅን ልማድ አድርጎ እንዳለ አገዛዝ ፣ ሽንፈትህን አምነህ ስትቀበል ትናንት የተጓዝክበትን የተሳሳተ መንገድ ቆም ብለህ ለመገምገም እድል ታገኛለህ ፣ አላስፈላጊ ሀገራዊ ውድመትና መስዋዕትነትን ታስቀራለህ ፣ ከዚህ አዘቅትና ምስቅልቅል ውስጥ የከተተህን ስህተት ተመልሰህ ለመዳሰስ እድል ታገኛለህ ፣ አዲስ የመውጫና የሀሳብ መንገድ ለመፍጠር አጋጣሚዎች ይፈጠሩልሃል።
አገዛዙ 10 ቀን አቅዶት የጀመረው ዘመቻ 3ተኛ አመቱ ላይ ደርሶ እንኳ በተመሳሳይ መንገድና እልህ እየተጓዘ እጅግ ከፍተኛ ውድመትና እልቂት እያስተናገደ የመቀጠሉ ምስጢርም ይኸው ነው! ሽንፈትን አምኖ ለመቀበል የመቸገር ግትርነት! ''እኔ ብቻ ልክ'' የሚል ከንቱ መታበይ! ራስን አልሚ ሌላውን አጥፊና አውዳሚ አድርጎ የማሰብ የአስተውህሎት መዛነፍ..!
ተከታዩ ሀሳብ ሰሞኑን በሰሜን ወሎ አካባቢ ሰንብቶ ወደከተማ የገባ የመከላከያ አመራር ባረፈበት ሆቴል ''በውሃ ዙሪያ ጨዋታ'' ላይ አብረውት ለነበሩ ሰዎች ሲያወራ ከነበረውና ከደረሰን አስተያየት መካከል የተቀነጨበ ነው።
<< ...ከሁለት አመት በላይ ያዋጉን በራሳቸው የውጊያ እቅድ ነው። እዚህ ከተማ ድረሱ ተብለን ስንሄድ መንገድ ላይ ያስቀሩናል። እንደምንም አልፈን ከተባለው ቦታ ስንደርስ ደግሞ እነሱ ትተውን ይሄዳሉ። ለረዥም ጊዜ ያለውጊያ ተቀምጠን ጦሩ ተሰላችቶና ሞራሉ ተነክቶ ወደሌላ ቀጠና ለመሄድ ጉዞ ስንጀምር ደግሞ ወጣ ከማለታችን በመንገድ ይገጥሙናል። ባሰብነው ትተው ባላሰብነው ይመጡብናል። ሲፈልጉ ለቁጥር የሚታክት ግንባር ከፍተው ጦሩን ከወዲያ ወዲህ ያመናትሉታል። መቼ እንደሚመጡም ሆነ እንደሚወጡ ፣ በየት ግንባር እንደሚዋጉና እንደማይዋጉ ወስነው የሚጋብዙን እነሱ ናቸው! ነገሩ እንደሚወራው አይደለም። ከባድ ነው...>> ሲል ነበር ግምገማውን የገለፀው።
ከነባራዊ ሁኔታውና ህዝቡ በየእለቱ በአይኑ ከሚያየው ተጨባጭ እውነታ በመነሳት ይህ የአብዛኛው የበታች አዛዦችና የጦሩ አስተያየት ጭምር መሆኑን መገመት አያዳግትም።
'' ኃላቀር መሳሪያ የታጠቁ አስር ጃውሶች ፣ ሽፍቶች ፣ በአስር ቀን እናጠፋቸዋለን!'' ከሚለው ንግግር አንስቶ በየመድረኩ '' ቆመው መዋጋት እንዳይችሉ አድርገናቸዋል ፣ ደምስሰናቸዋል ፣ በትነናቸዋል ፣ እያፀዳን ነው ፣ ለቀማ ላይ ነን ፣ ...'' የሚሉ ተመሳሳይ ድስኩሮችን እየሰማን ዛሬ ላይ ደርሰናል። በተቃራኒው እውነታውን ደግሞ ህዝብ ያውቀዋል።
ጠብመንጃ ያነሳውን ሃይል ኮዝ እንደሌለው ፣ ፖለቲካዊ ጥያቄና አላማ እንዳላነገበ ፣ የህዝብ ጥያቄዎችን ለማስመለስ እንደማይታገል አድርጎ ለማቅረብ የሚደረገው ተራ ፕሮፓጋንዳም የአገዛዙን ገመና ከማጋለጥ ብሎም ነገሮችን ከማወሳሰብ የዘለለ አንዳች ፋይዳ የለውም።
ይህን ለአስር ቀን የታቀደን ሀይል በየእለቱ በሁለንተናዊ አቅሙ እያጎለበተና ግዙፍ ሀይል እየገነባ አመታትን ወደፊት እንዲጓዝ ያደረገው ጠንካራ ኮዝና ህዝባዊ መሠረት ስላለው መሆኑን አለመረዳት ደግሞ በርግጥም አይተ ጌታቸው ረዳ እንዳሉት የፖለቲካ ድንክነት ነው!
በነገራችን ላይ ለአንድ ፀረ-አገዛዝ አቋም ይዞ ጫካ ለገባ ታጣቂ ቡድን ፥ እንኳን በአንድ ቀን ሁለት እዝ እየደመሰሰ ፣ በየእለቱ አጃኢብ የሚያሰኝ ወታደራዊ ድል እየተቀዳጀ ፣ ራሱን በሁለንተናዊ መልኩ እያፈረጠመ መቀጠሉ ይቅርና መኖሩ/existence ብቻ እንደ ድል የሚወሰድ ሲሆን ለአገዛዝ ደግሞ የታጣቂ ቡድኑ መኖሩ ብቻ ሊጂቲሜሲውን እያሳጣው ፣ የነበረው መንግስታዊ መታመን እየተሸረሸረ ፣ ሀይሉና መዋቅሩ እየፈራረሰ እንዲሄድ ስለሚያደርገው እንደሽንፈት ይቆጠራል። በርግጥም ሽንፈት ነው!
በመሆኑም ፦ የሚበጀው ከተለመደው ተራ የፖለቲካና የፕሮፓጋንዳ አካሄድ ራስን አቅቦ እውነታን አምኖ መቀበል ነው። በመቀጠልም ትውልድ እየገበሩ ፣ ሀገር እያወደሙና በደም እየታጠቡ ከመጓዝ ፣ ለችግሮቹና ለህዝባዊ ጥያቄዎቹ እውቅና ሰጥቶ ያለአንዳች ቅድመ ሁኔታ ለድርድርና ለፖለቲካዊ መፍትሔ ራስን አዘጋጅቶ ወደተግባር መግባት ነው!
''በለው ፍለጠው ፣ ደምሳሹ ፣ ፀሀዩ መንግስቴ'' ከሚሉት ገደል ከታች የሚዲያ ሚሊሾቹ ውጪ የማይሰማው አገዛዝ ስርአታዊ መዋቅሩን ለማትረፍ በእጅጉ ያረፈደና እድሎቹን ያመከነ ቢሆንም ቅሉ ፣ ሀገርና የቀጣዩ ትውልድ ተስፋ የሚያተርፍበትን እድል የሚጠቀምበት ጊዜው ግን አሁን ነው!
አለበለዚያ ግን እመነኝ! አሜሪካን በአፍጋኒስታን ያሳለፈችውን ሁለት አስርት አመታት ያህል አይደለም በእጥፉ ብትዋጋ እንኳ ወታደራዊ ድልን ፈፅሞ ልትቀዳጅ አትችልም!
ይኸው ነው!
©ዘርይሁን ገሠሠ
ማህበረሰቡ ይኸንን አሸባሪ እና ወራሪ የብልፅግና ስርዓት እስኪወገድ ድረስ በፅኑ እንታገለዋለን ብሏል‼️
ሻለቃ አንሙት ያዛቸው ብርጌድ በአግታ ቀበሌ ሰፊ ህዝባዊ መድረክ ውይይት ተካሄደ።
በዛሬው እለት በቀን ጥቅምት 02/2018 ዓ.ም የማህበረሰብ ችግሮችን በመለየት በፋኖ አደረጃጀቶች እና አሰራር ዙሪያ እንዲሁም በህዝባዊ አስተዳደር መዋቅሮች ላይ ያለውን በመገምገም ህዝባዊ አደረጃጀቶችን በማጠናከር መዋቅሮችን በመፈተሽ ያለፉ አፈፃፀሞችን በመገም ቀጣይነት ያለው አሰራር በመዘርጋት የማብቃት ስራ በክፍለ ጦሩ የአደረጃጀት ዘርፍ እና የፓለቲካ ዘርፍ አመራሮች በጥልቀት የማወያየት ስራ የተሰራ ሲሆን በቀጣይ ስራወቻችን ላይ በመግባባት በማንኛውም ተግባር ህዝቡ ከጎናችን እንደሚሆኑ የመግባባት ስራ ተሰርቷል።
ፋኖ ሐብታሙ የሱፍ የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴድሮስ ዕዝ 1ኛ ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት
02/ዐ2/2018 ዓ.ም
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነዉ ዕዝ ኃ/ማርያም ማሞ ክፍለጦር በአገዛዙ ጥምር ጦር ላይ ድል ተቀዳጀ።
ከጧቱ ጀመሮ እስካሁን ድረስ ዉጊያዉ የቀጠለ ሲሆን የኃይለ ማርያም ማሞ ክፍለጦር በሸዋ ቡልጋ ሀገረማርያም ከተማ ወጣ ብላ በምትገኘው ነፋስ አምባ ከፍተኛ ትንቅንቅ እያደረገ ይገኛል።
የአጋዚ ኮማንዶ፣የሚሊሺያ እና የአድማ ብተና አባላት ላይ በተወሰደ የደፈጣ ጥቃት በደርዘን የሚቆጠር የጠላት ሀይል ተደምስሷል።በአዉደዉጊያ ሁለት አንቡላንስ የጥምር ጦሩ ሙት እና ቁስለኛ ይዞ ወደ ሀገረ ማሪያም ከተማ ሆስፒታል ይዞ መግባቱ ተረጋግጧል።
ዉጊያዉ አድማሱን አስፍቶ የቀጠለ ሲሆን የሃይለማርያም ማሞ ክፍለጦር በጠላት ላይ ከፍተኛ ድል አስመዝግቧል።በሸዋ ቡልጋ የገበዉ የአገዛዙ ሰራዊት አብዛኛው ሙትና ቁስለኛ መሆኑን ተከትሎ ጠላት ከቡልጋ ሀገረማሪያም ከተማ እና ከዙኖ መናገሻ ደብረብርሀን ከተማ በርካታ ሰራዊት ይዞ ቢገባም የሃይለማርያም ማሞ ልጆች የመጣዉን ጠላት በሚገባ እያናገሩት ይገኛሉ።
የአብይ አህመድ ሰራዊት የመዋጋት ሞራል የለውም።
ሰራዊቱ በግዳጅ እንዲሰለጥን ተደርጎ በግዳጅ እንዲዋጋ እየተደረገ ነው። ምንም የሚዋጋበት ምክንያት የለውም ። እንዲያውም የገዛ ቤተሰቡ በአሰቃቂ ሁኔታ በከባድ መሳሪያ እና ምክንያት እየፈለጉ የጥይት አረር ሲያነዳቸው ባይኑ እያየ መውጫ መንገዱ ጠፍቶበት አንገቱን ደፍቶ እያለቀሰ ይገኛል። ጥቂት የሚባሉት በስውር የሰለጠኑ ከመከላከያ ጋር በመቀላቀል ሕዝባችንን ጅምላ ጭፍጨፋ እየፈፀሙበት ይገኛሉ።። አብይ አህመድ ኢተር ሀሞይ ቡድን አሰልጥኖ የመከላከያ ልብስ አልብሶ ወደ አማራ ክልል እያስገባ ይገኛል።
በሕዝባቸው መጨፍጨፍና መደፈር የተቆረቆሩት እየለቀቁ ወደፋኖ በየቀኑ እየተቀላቀሉ ይገኛል። ዘር ጨፍጫፊው የመከላከያ ልብስ የለበሰው ኢንተር ሀሞይ ቡድንም በደረሰበት ምት አንገቱን ደፍቶ እያለቀሰ ይገኛል።
ባሰቡት መንገድ ያልሄደላቸው እኒህ አረመኔ ሰራዊቶች በየግንባሩ እየተሸነፉ እና የመዋጋት ሞራላቸውም እየላሸቀ ይገኛል። አብዛኛው መከላከያም በየአቅጣጫው ተበትኗል። በተቃራኒው በየቀኑ ኮማንዶ እያስመረቀ የሚገኘውፋኖ በሚገርም የድል ግስጋሴ የሚገኝ መሆኑ የአደባባይ ሚስጢር ነው።
በመሆኑም ሕዝብን ጨፎጭፎ መጨረስ አይቻልም። ሕዝብንም ያሸነፈ አንባገነን መሪ በዓለም ላይ አልታየም ። ከማለቃችሁና ከመደምሰሳችሁ በፊት በየትኛውም ቀጠና ያላችሁ የአብይ አህመድ የግል ጠባቂ መከላከያዎች ሆይ እጅ ትሰጡ ዘንድ ጥሪየን አቀርባለሁ።
አዲስ ትውልድ ፣አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!
ጥቅምት 02/2018ዓ.ም
©እስቲበል ዓለሙ
Repost from Amhara Revolution
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ምክትል ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ ድረስ ሞላ የትግሉን አሁናዉ ሁኔታ በማስመልከት ያስተላለፈዉ መልዕክት!!!!!!
አብይ አህመድ በአራቱም ማዕዘን ጦሩን አዝምቷል እንደ አመጣጡ ጀግኖች ስራ ላይ ናቸው።
ድሎች አሉን አጠናክርን እንመለሳለን እኛ ጋ አማራ ነፃ ሳይወጣ በአራቱም ማዕዘን አዲስ አበባን ጨምረን መተኛት የለም!!
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ትግላችን የአማራ ትግል ሾተላዮችንም በአስተማማኝ ሁኔታ ማምከን ጭምር ነው‼️ በ አረፋይኔ ተጎድ Arefyne T Sraye
**
ባለን አጭር የትግል ተሞክሮና ውስን ንባብ እንደተገነዘብነው እንደገባንም፧ ከትናንት እስከ ዛሬ የአማራን ትግል ስምረት የሚያከሽፉ ኹለት ሾተላዮች አሉ።እነሱም:-
፩| የ ተቋም ግንባታ ክሽፈት
፪|መሪ የመውለድ /ራሱን ዝግጁ አድርጎ የተገኜን መሪ ጠብቆ ለተገቢው ደረጃ የማድረስ ሾተለይ ናቸው።
አማራ ከተቃጣበት አደጋ ራሱን ለማዳን እና የሚወዳትን ሀገሩን እየጠሏት ከሚመሯት አፍራሾቿ እጅ ለመታደግ ትግል ማድረግ ከጀመረ ዋል አደር ብሏል።በትግል ሂደቱ ውስጥም ከመዐህድ እስከ አዴሃን፣ከቤተ አምሓራ እስከ አብን ከአስራት እስከ..... የተለያዩ የትግል ተቋማትና ድርጅቶችን ለመመስረት (በብዙ ዋጋ )ብርቱ ሙከራ ሲደረግ ቆይቷል። ተቋማቱን ማጽትና ማስቀጠል ላይ ግን ተደጋጋሚ ክሽፈት እያጋጠመ በተመሳሳይ አዙሪት ውስጥ ለመቆየት ግድ ሆኖ ቆይቷል።
እንደተጠቀሰው ሁለተኛው የአማራ ትግል ሾተላይ(መጨንገፍ) መሪ መውለድ አለመቻል እና በአንዳች አጋጣሚ የተገኙትን ደግሞ ጠብቆና ተንከባክቦ የሚሪነት ሚናቸውን እንዲወጡ ማድረግ አለመቻል ነው።
በተለይ በዚህ ረገድ ከባዱ ነገር መሪ መውለድ አለመቻሉ ብቻ አይደለም። በታሪክ አጋጣሚ በዘመን አንድ ጊዜ ብልጭ ያሉ የትውልድ አብሪ ክዋከብትን ጠብቆ ደግፎና አጎልምሶ ህዝብን ወደ አንዳች ምዕራፍ መርተው እንዲያሻግሩ ከማብቃት ይልቅ፣ የድመት ፖለቲካ በወለደው ልጅን የመብላት ክፉ በሽታ ተለክፎ ብቅ ያሉ መሪዎችን ማጥፋት የተቆየበት የታሪክ ርግማን ነው።
[ከአስማረ ዳኜ እስከ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ፣ከሳሙኤል አወቀ እሰከ ከጎቤ መልኬ ..እስከ ነብዩ ጀኔራል አሳምነው ጽጌ፣ ከአስቻለው ደሴ እስከ ሻምበል መማር ጌትነት ፣ ከነ አዲሱ ቢተው አስከ ሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ .....] ጆሮ ነፍጎ፣ ለጠላት አሳልፎ በመስጠትና አዋክቦ ማጥፋት የተፈጸመባቸው መሪዎችን መጥቀስ ከበቂ በላይ ነው።
~ ~
ዛሬም ከጠላት በላይ እየታገልን ያለነው እነዚህን የአማራ ትግል ሾተላዮች ለማምከን ነው። ትግሉ ከዚህ አዙሪትና መጥፎ የታሪክ ድግግሞሽ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በአስተማማኝ ሁኔታ ለመውጣት ጭምር ነው።
ለዚህም ነው ተቋምና ተቋማዊነትን ማንበር እንዲሁም መሪ ጥበቃን አውራ ተግባራቶቻችን አድርገን የምንለው፤ የትግላችን ግብ /ስኬት በነዚህ አልፎ የሚሆን ስለሆነ!
የሦስት ትውልድን ምጥና ህልም ተሸክሞ የሚቃትተው የኛ ትውልድ ግን በእውነት ሾተላዩን ያመክናል፤አዎ ለድል የታጨው እና የታሪክ ሙሽራ የሆነው አዲሱ ትውልድ ሁሉንም ያሳካል !!!!!
አማራነት ያሸንፋል !
ጥቅምት 02/2018 ዓ.ም
የአፋብሀ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ እዝ የ6ኛ ክ/ጦር ፖለቲካ መምሪያ ሀላፊ
አረፋይኔ ተጎድ Arefyne T Sraye
[ ከሰም ያደርጋል ክስም ]
"ከሰም ያደርጋል ክስም" የተባለለት ግዙፉ ክ/ጦር በቀጣይ ወደ ኮር ማደግ አለበት ከሚሉ ቀዳሚ ሰዎች አንዱ ነኝ!!
እውነት ለመናገር በአማራ ፋኖ ትግል ውስጥ አሉ ከተባሉት ጠንካራ ክ/ጦሮች አንዱ ነው።
ከሰም ክ/ጦር እንደ ድርጅት የዘመነ፣የህዝብ አደረጃጄቶች በሁሉም ቀበሌዎች እና በሚንቀሳቀስባቸው ቀጠናዎች ሁሉ ሲቪል አስተዳደር ያዋቀረ፣የሰለጠነ፣የክ/ጦር ስታፍ ያለው፣የስራ ስምሪቱን ድርጅታዊ መዋቅሩ በጠቅላላው ችግር ፈቺ የሆነ ፣አመራሩንና አባሉን በተደጋጋሚ የሚያሰለጥን፣ዘመናዊ የፋይናንስ ስርዓትን የሚከተል፣ከሰም ክ/ጦር በተቆጣጠራቸው ሁሉም ቀበሌዎች ባንዳን የሚከታተል የማህበረሰብ መረጃ ፍሰት ያለበት እንድሁም በመልካም አስተዳደር እና ተያያዥ ጉዳዮች ጭምር እጅግ ፍትሃዊ የሆነ ስራ የሚሰራበት ፣አማራ የሆነ ሁሉ በማንነቱ በእምነቱ ተከብሮ የሚታገልበት ክ/ጦር ነው።
ከሰም ክ/ጦር ብዙ የተግባር አማራዎች የተሰበሰቡበት፣ሰፊ ሰብአዊ ሃብት ያለው በሰራዊት ቁጥር ከፍ ያለ፣ከጠላት በቅርብ ርቀት የሚገኝ እንዲሁም የትግላችን መደማደሚያ ቦታዎችን ሸፍኖ የሚታገል ክ/ጦር መሆኑ ከሌሎች የአፋብኃ አደረጃጀቶች የተለየ ያደርገዋል።
ስለሆነም እኔም እንደ ታጋይ በከሰም ክ/ጦር ውስጥ ሆኘ በቅንነት ስታገል እና ሳታግል በመቆየቴ ኩራት ይሰማኛል!!
ስትራቴጅካዊ የመታገያ ቀጠና ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ሁሉም የአፋብኃ አመራር እና ሰራዊት የቀጠናውን አስፈላጊነት በደንብ አስበው እና ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩበት ስል በዚሁ አጋጣሚ ለመግለፅ እወዳለሁ!!
ከሰም ክ/ጦርም እስከ አሁኑ ይዞት የነበረውን አስተዳደራዊ ልምድ በማሳደግ እና ተጨማሪ አቅም በመፍጠር የአማራው ኩራት ለመሆን የጀመራችሁት አጠቃላይ ለውጥ እና ጠንካራ ዝግጁነት በእጅጉ የሚያስደንቅ ነው።
በተግባር አማራዎች እና የድርጊት አመራር እና ሰራዊት የተገነባው ከሰም ክ/ጦር በአፋብኃ አሳምነው ዕዝ ስር ሆኖ ለቀጣይ ግዳጅ አስተማማኝ ቁመና ላይ በመገኘታችሁ ኮርተናል!!
ከሰም ክ/ጦር በአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ውስጥ ከሚገኙት ጠንካራ ኮሮች ውስጥ ተመድቦ እንደምናየው አልጠራጠርም!!
አይበገሬዎቹ የአሳምነው ልጆች በቀጣዩ ተልዕኳችሁ አስደማሚ ተጋድሎ እንደምታደርጉ አልጠራጠርም!!
ከሰሞች በርቱ!!💪
እኔም እንደ ታጋይ አማራም እንደ ህዝብ ይኮራባችሗል!!
ምስሉ፦ የከሰም ክ/ጦር እና የድርጅት አመራሮች በክትትል ስራዎች ወቅት የተነሳነው ነው!!
እንበርታ አማራ💪
[አርበኛ አሸናፊ ገናን ]
#የጥንቃቄ_መልዕክት‼️
በሀብሩ ወረዳ በምትገኘዉ በመርሳ ከተማ መሸጎ የሚገኘዉ የመከላከያ ሀይል ኒኒ በር ያለዉን የወገን ሀይል ለማስለቀቅ ሲል በቀን 2/2/2018 ዓ/ም ከወልደያና መርሳ ተነስተዉ ወደ ደሴና አድስ አበባ ሲጓዝ የነበረን ህዝብ ከመኪና አዉርደዉ በግር አሰልፈዉ ሲያስመሯቸዉ ተይተዋል ጥንቃቄ ይደረግ ሲሉ የንስረ አማራ ምነጮች ገልፀዋል‼️
02/ዐ2/2018 ዓ.ም
[ አሳምነው ዕዝ ]
የአማራይቱ ልጅ አሳምነው እዝ በቀኝ በግራ የተፈተነው
ኢንጂነር ደሳሣለኝ ሲያስብ ሸዋ የሚመራው አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው እዝ ይችላል !💪
ይሄ የፋኖ ኃይል ከአየር ኃይል ልዩ ኮማንዶ ዩኒት እስከ special ኮማንዶና መከላከያ ፣ ከአማራ ሚሊሻ፣ፖሊስና አድማ በትን እስከ ኬሚሴ የልዩ ዞኑ ሚሊሻ ፣ፖሊስ ከኦሮሚያ ልዩ ኃይል እስከ ሸኔ ሀይል ጋር እየተፋለመና ከወገን በኩልም በተቃራኒው የተሰለፉ ወንድሞቹ ጋር ብዙ ፈተናወችን እያለፈ አሁን ካለበት ጠንካራ ቁመና ላይ የደረሰ አስተማማኝ የአማራ መከታ ኃይል ነው።
ይሄ የአፋብኃ ደ/አማራ ቀጠና አሳምነው እዝ የሚንቀሳቀስባቸው ቀጠናወች ለወደፊት ለሚደረጉ ወሳኝ ፍልሚያወች ለወገን ሃይል ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላቸው ሲሆን ለዚህ ከሚያግዙ ወሳኝ ስትራቴጅክ ቦታወች አንዷ የሆነችውን ግሸራቤል ከተማን በነበልባል ክንዱ ከወራሪው ቡድን ነፃ አድርጓል💪
አሳምነው ዕዝ ይችላል ስልህ💪
