uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Kanalga Telegram’da o‘tish

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Ko'proq ko'rsatish
4 416
Obunachilar
+1224 soatlar
+287 kun
+1 15930 kun
Postlar arxiv
🔊ሕዝባዊ የምክክር መድረክ በስናን አባጅሜ ብርጌድ🔊 የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክ/ጦር የስናን አባጂሜ ብርጌድ በሚያስተዳድራቸው ቀበሌዎች ተከታታይነ
+1
🔊ሕዝባዊ የምክክር መድረክ በስናን አባጅሜ ብርጌድ🔊 የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክ/ጦር የስናን አባጂሜ ብርጌድ በሚያስተዳድራቸው ቀበሌዎች ተከታታይነት ያለው ህዝባዊ ውይይት እያደረገ ይገኛል። ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክ/ጦር የስናን አባጂሜ ብርጌድ በሚያስተዳድራቸው ቀበሌዎች ተከታታይነት ያላቸው ህዝባዊ ውይይቶችን በማድረግ ማሕበረሰባዊ ተግባቦቶችን እያጎለበተ ይገኛል። በሁሉም የትግል ዘርፎች የጠላትን አከርካሪ በመስበር የሕልውና ትግሉ ወደፊት እንዲራመድና አሁን ከደረሰበት ልዕልና እንዲደርስ አስተዋጽኦ በማበርከቱ ረገድ የአንበሳውን ድርሻ እየተወጣ የሚገኘው የደጋው መብረቅ ስናን አባጅሜ ብርጌድ የትግሉ ባለቤት ከሆነው ማሕበረሰብ ጋርም ጠንካራ የሆኑ ግንኙነቶችን በማድረግ ማሕበረሰባዊ ተግባቦቶችን እያጎለበተ ይገኛል። በትናንትናው ዕለትም በወለቄ፣በጉድያሜ እና ታች ጫቢ ቀበሌዎች የሚገኙ ማሕበረሰቦችን በመሰብሰብ ሰፊ ማሕበረሰባዊ ውይይቶችን አካሂዷል። በውይይቶችም * በመልካም አስተዳደር ጉዳዮች፣ * የአማራ ሕዝብ የሕልውና ትግልን አሁናዊ ቁመናን በመለከተ የግንዛቤ ፈጠራና የስርጸት ስራ * የማሕበሰቡና የፋኖ የእርስ በእርስ ትስስር ምን መምሰል እንዳለበትና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል። ማሕበረሰቡም እስካሁን እያበረከተ ካለው ሁለንተናዊ ድጋፍ በላቀ ሁኔታ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል። ድል ለአማራ ፋኖ! ክብር ለሰማዕታቱ! አዲስ ትውልድ፣አዲስ ተስፋ፣አዲስ አስተሳሰብ" ፋኖ ዘመን ባሳዝነው ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ 6ኛ ክፍለ ጦር

#ፋኖ_ዝግጁ❓‼️ በለሊት ከበባ ፈፅሞ ጥቃት ለመክፈት የተዘጋጄ የአገዛዙ ወንበር ጠባቂ ኃይል አለ ዝግጁ እንሁን‼️ ከለሊቱ 5:37 02/ዐ2/2018 ዓ.ም ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎     

ግፈኛው እና ዘረኛው የዐቢይ አህመድ አገዛዝ የጅምላ ፍጅት እየፈፀመ በቀጠለበት አማራ ክልል እንዲህ ዓይነት አሳዛኝ ዜናዎችን መስመት የተለመደ ሆኗል። በደሴ ከተማ በግፍ የተገደለችው ሌዛ ራያ ቆቦ ተ
ግፈኛው እና ዘረኛው የዐቢይ አህመድ አገዛዝ የጅምላ ፍጅት እየፈፀመ በቀጠለበት አማራ ክልል እንዲህ ዓይነት አሳዛኝ ዜናዎችን መስመት የተለመደ ሆኗል። በደሴ ከተማ በግፍ የተገደለችው ሌዛ ራያ ቆቦ ተወልዳ ያደገች እህታችንን ስትሆን ከሰሞኑ በምሽት አስገድደው ከደፈሩ በኋላ ገድለው ጥለዋት እንደሄዱ ተገልጧል። መፍትሄው ፀረ አማራውን አገዛዝ ከማስወገድ ነው።  

ስለራሳችን ውይይቶች፤ ንግግሮችና ምክክሮች አድርገናል ቢቡኝ ወረዳ።               02/02/2018 ዓ.ም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምዕ/አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 2ኛ ተፈራ ዳምጤ ክ/ጦር ቢቡኝ መዝገበ ዋለልኝ ብርጌድ የአማራን ትግል ከውልደት እስከ እድገት በድርብርብ ድል እንዲፀዳ ህዝባችን የአምበሳውን  ድርሻውን እንደሚወስድ እናምናለን። ህዝባችን ዘርፈብዙ ችግር ደርሶበት ችግሩን በሰላምዊ መንገድ ጠይቆ ከአገዛዙ ሹማምንቶች የተንሸዋረረ ምላሽ በመነሳትና ችግሩን ከመፍታት የመጥፊያ የመፈናቀያና የመታገቻ የመንግስት ስልታዊ አሰራሮች ዘመነው አድገው በአደባባይ መሰራት ሲጀምሩ የአማራ ህዝብ በህዝባዊ እንቢተኝነት በሁሉም የአማራ ግዛቶች በአንድ ጀንበር ጀምሮ 2ት ዓመታትን ተዋግቶ ሰራዊት መስርቶ በገፍ ትጥቅ ታጥቆ ድርጅት መስርቶ እዚህ ደርሷል።        ድርጅታዊ ሰንሰለታዊ የመርህና የስርዓት መዋቅር ለሁሉም የደጀን ህዝባችን ደርሶ ከህዝብ ጋር በየጊዜው በመገናኘት በአጋርነትና በስልታዊ ተግባቦት በቀጣይ ሊደረጉ ስለሚችሉ ጉዳዮች ሁሉ ወገንን ያገናዘበና የጠላትን ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ አሰራርን በቅጡ ግንዛቤ በማስጨበጥ በተጨባጭ ስራ ተሰርቷል። የቢቡኝ መዝገበ ዋለልኝ ብርጌድ ዛሬ በ5 ቀጠናዎች ስለራሳችን ምክክር፤ ንግግርና ውይይት አድርጓል።   የአማራነትን የትናንት ግርማና ንግስና ብሎም የሃገር በጎ አበርክቶ እንደ ጥላቻ ተቆጥሮበት የነገዳውያን የተንሸዋረረ የሴራ አረዳድና "ወርቅ ላበደረ ጠጠር"  እንደሆነበት ፤ነገዳውያን የፖለቲካቸው ርዕት አማራ ጠል ሆኖ የትግላችንን መነሻ ለህዝባችን በተጨባጭ አስረድተናል። ፋኖ አዲሱ ነገሰ የመዝገበ ዋለልኝ ህዝብ ግንኙነት

ዛሬ ማለትም በቀን 02/02/2018 ዓ.ም የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ሀዲስ አለማየሁ 7ኛ ክ/ጦር አዋበል ወረዳ መብረቁ ብርጌድ ጣባ የጎደና ቀበሌ አዋበል ወረዳ የብልጽግና ካድሬዎች
ዛሬ ማለትም በቀን 02/02/2018 ዓ.ም የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ሀዲስ አለማየሁ 7ኛ ክ/ጦር አዋበል  ወረዳ መብረቁ ብርጌድ  ጣባ የጎደና ቀበሌ አዋበል ወረዳ የብልጽግና ካድሬዎች ህዝብን በማስገደድ ሰንበቴ እና ወራሀዊ ፅጌን ሊያከብር የመጣውን ህዝብ በመሰብሰብ ሊአዎያይ  ቢሞክርም የአዋበል ወረዳ መብረቁ ብርጌድ አናብስቶች ድንገት ፈጥነው በመድረስ ሊካሂደው የነበረውን ስብሰባ ብትንትኑ እንዲወጣ፣ እዲቋረጥና ለቆ እንዲፈረጥጥ አድርገውታል።ሊይዘው ሊጨብጠው የአጠው የአብይ ወንበር አስጠባቂ ህዝብ አልቀበለው ሲል በኃይል በማስገደድ የበዓላት ቀንን በመጠበቅ ስብሰባዎችን ማስኬድ ቢሞክርም የአዋባል አናብስቶች መሄጃ፣ መቀመጫ አሳጥተውት ውለዋል።    ህልዉናችን በተባበረ ክንዳች        ድልለአማራ ህዝብ         ድል ለአማራ ፍኖ !!! ፋኖ ወንድምነህ ሰውነት  የአዋበል ወረዳ መብረቁ ብርጌድ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ።

ከህዝባችን ጋር!!! የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና  ቴወድሮስ እዝ ፫ኛ ጎጃም አገዉ ምድር ክ/ጦር  ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ በሚያስተዳድራቸዉ የፋ/ለ/ወ ቀበሌዎች ዉስጥ ከሚገኘዉ  ማህበረሰባችን ጋር የሚደርጋቸዉ አቢዎታዊ  ዉይይቶች ዛሬም ቀጥለዉ ዉለዋል። የዛሬዉ የጥቅምት 2/2018 ዓ/ም አቢወቱን ያማከለ ህዝባዊ ዉይይት  በዋናነት ያተኮረዉ  ከዚህ በፊት በአቢዎቱ  የተሰሩ ህዝባዊ አደረጃጀቶችን የስራ ክንዉን ከህዝብ ጋር ሁኖ በመገምገም ለቀጣይ የስራ ስምሪት እና አቅጣጫ ማስቀመጥን ታሳቢ በማድረግ ሲሆን ዉይይቱ  ለነገ ትግላችን የሚሆን  ወሳኝ ጉዳዮች ላይ የጋራ በሆነ ስምምነት ወሳኝ የሆኑ ዉሳኔዎችን በማሳረፍ ደስ በሚል ሁኔታ ተጠናቋል። አዲስ ትዉልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ!!! ጥቅምት 2/2018 ዓ/ም ፋኖ ተሻገር አደመ የ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ ህ/ግንኙነት

ጓዶቻቸው በአማራ ፋኖ የተሰነበቱባቸው የአገዛዙ ስልጣን አስጠባቂ ወጣቶች አሁን ላይ ያሉበት ሁኔታ😰 እኛም በሰላም እጅ ስጡ እና ወደ እናት፣አባቶቻሁ በክብር እንሸኛችሁ ብለናል…እንቢ አሻፈረኝ ካላችሁ ግን እንደናተ ንፁሀን እናት፣አባ እና እህት፣ወንሞሞቻችሁን በግፍ በአሰቃቂ ሁኔታ በመግደል ሳይሆን በእውነት፣ስለ እውነት ታግለን ከዚህ በከፋ ሁኔታ ቅስማችሁን💪🏽 በመስበር ገና ደም፣እናስለቅሳችሁአለን!😭😭

ይህ ነው የሰው መከራ መሰረታዊ ምክንያት፡፡ ከራሱ በተቃራኒ የተከፋፈለ ሰው ገሀነብ ውስጥ እንደሆነ ነው የሚቀረው፤ ገነት የምትወለደው ሰው ከራሱ በተቃርኖ ካልተከፋፈለ ብቻ ነው፡፡ የተከፋፈለ ሰው ማለት መከረኛ ማለት ሲሆን ውህድ የሆነ ሰው ማለት የተባረከ ሰው ማለት ነው፡፡ እስካሁን የሰው ልጅ ብትንትኑ የወጣ ሆኗል፡፡ ምክንያቱም ብዙ ጊዜ ተፈጥሯዊ ሰብዓችሁን እንድትኮንኑ፣ እንድታስወግዱ፣ እንድትክዱ ተነግሯችኋል፡፡ እናም እነዚሀ ተፈጥሯዊ ነገሮችን ለማስወገድ፣ ለመካድ በመሞከር ልታጠፏቸው አይቻላችሁም:: እነዚህ ተፈጥሯዊ ነገሮች ከስር ብቻ ነው የሚጓዙት፣ ከያልነቃው አዕምሯችሁ ውስጥ ነው የሚሰሩት፤ እናም የእውነት በጣም አደገኞች ናቸው፡፡ ሰው ተፈጥሯዊ እና ምሉዕ ነው፡፡ እናም እግዝሀብሄር ለሰው የሰጠው ሁሉም ነገር ጥቅም ላይ መዋል አለበት፡፡ አንዳች ነገር ሊካድ አይገባም፡፡ የሰው ልጅ ኦርኬስትራ መሆን ይችላል፤ የሚፈለገው ብቸኛ ነገር በራሳችሁ ውስጥ ሰላማዊ ህብራዊነት የመፍጠር ጥበብን መለማመድ ብቻ ነው፡፡ ዴቭ ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎     

እጅግ ያሳዝናል ! 😭 ይህ ወጣት ልጅ ልገንዘበው አቦ ይባላል ። ተወልዶ ያደገው በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን አሰኮ ወረዳ፡ ጨፋ ቁዮ ቀበሌ ነው ። ይህ ወጣት በግል ስራ እየታተር ይተዳደር ነበር ።
እጅግ ያሳዝናል !  😭 ይህ ወጣት ልጅ ልገንዘበው አቦ ይባላል ። ተወልዶ ያደገው በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን አሰኮ ወረዳ፡ ጨፋ ቁዮ ቀበሌ ነው ። ይህ ወጣት በግል ስራ እየታተር ይተዳደር ነበር ። ከሰሞኑ ታዲያ በቀን 28/01/2018 ዓ.ም ለስራ ጉዳይ በሚንቀሳቀስበት ወቅት በመርቲ ወረዳ፡ ቢጮ በትምባል ልዩ ቦታ አማራ ስለሆነ ብቻ በኦነግ ሸኔ ታግቶ በአሰቃቂ ሁኔታ መገደሉ ተሰምቷል ። - የአገዛዙ መንግሥት ስለ ፋኖ በየሚዲያው ኡ...ኡ...ኡ... ሲል እየዋለ፤ ስለ ሸኔው ግን አንዳች አይተነፍስም ። እናም የአንድ ዓላማ እጆች ተባብረው አማራን እና ኦርቶዶክስን ማጥፋት ምግባራቸው ከሆነ ሰነባብቷል ።

"አማራውን እርስ በእርሱ ደም አቃብተነዋል" ጥሬ ስጋ እየቀለብን አሰልጥነን ያስቀመጥነው ሰራዊት አለን (የኦሮሚያ ልዩ ሀይል) ፈተን እንለቅበታለን። ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ ሚሊሻ ሆኖ ከፋኖ ቤተሰብ ያል
"አማራውን እርስ በእርሱ ደም አቃብተነዋል" ጥሬ ስጋ እየቀለብን አሰልጥነን ያስቀመጥነው ሰራዊት አለን (የኦሮሚያ ልዩ ሀይል) ፈተን እንለቅበታለን። ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ ሚሊሻ ሆኖ ከፋኖ ቤተሰብ ያልገደለ የለም በተመሳሳይ ፋኖ ሆኖ ከሚሊሻ ቤተሰብ ያልገደለ የለም ። በአማራ ባህል ደግሞ ደም ሳይመልሱ መቅረት እንደነውር የሚቆጠር ነገር አለ ፣ ስለዚህ አሁን ላይ ዕርስበርስ ለግድያ የሚፈላለጉ ደመኞች ሆነዋል፥ ፋኖን አጥፋልን ብለን የምንለምነው ሚሊሻ አይኖረንም ለራሱ ሲል የራሱን ህይወት ለማትረፍ ሲል ያለምንም ክፍያ ፋኖን ያሳድድልናል።በእንደዚህ አይነት መንገድ እጃችንላይ ያለውን ገንዘብ ለሚሊሻ ከመበተን ድነናል፣ ገንዘቡን ለገዳ ልዩ ኮማንዶ ማሰልጠኛ እና መሳሪያ መግዣ ይውላል። አማራ ከዚህ በሗላ ከነሙሉ ክብሩ በአባገዳ ልጆች ፊት የሚቆምበት ዘመን አብቅቷል ማንም አባከና የሚለው ሰው አይኖርም። ቀደም ብየ እንደነገርኳችሁ አማራ ከዚህ በኋላ እስከምፅዓት ድረስ ምንም አይነት የፖለቲካ ወሳኔ ሰጭነት ሚና እንዳይኖረው አድርገን ሰርተናል አንዳንዶች ይሄን ስንል መታበይ ይመስላቸዋል ነገር ግን ፖለቲካውን የሰራነው ሰዎች ስለምናውቀው ነው።  ከእንግዲህ ኦሮሞ ማድረግ ያለበት ስትበድለው ከነበረችው ሚኒሊክ ሰራሽ ሐገር ቁጭ ብሎ ካሳ መቀበል ብቻ ነው። ከኦሮሞ ጋር ሰላም ፈጥሬ እኖራለሁ የሚል አካል ካለ እሱን እንቀበላለን ነገር ግን አካሔዱ የሚሆነው ኦሮሞ በሚወስንለት ማነኛውም ህግና ድንጋጌ ሊመራ እና ሊተዳደር አምኖ ከተቀበለ ብቻ ይሆናል። ይሄን ካልተቀበለ ጥሬ ስጋ እየቀለብን አሰልጥነን ያስቀመጥነው ሰራዊት አለን (የኦሮሚያ ልዩ ሀይል)ፈተን እንለቅበታለን ማለት ነው። -ሽመልስ አብዲሳ ❗የኦሮሚያ ገዳ ልዩ ኮማንዶ የምርቃት ስነስርዓት ላይ የተናገሩት።

የአማራ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር በዘመቻ ኮማንዶ ደምሰው ከተማው ከፍተኛ የጦር ሜዳ ድል አስመዘገበ:: በምዕራብ ወሎ ግንባር መሀል ሳይንት ወረዳ ውስጥ ከትናንት ማለትም መስከረም 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ዛሬ እኩለ ቀን ድረስ በተደረገው ትንቅንቅ የንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ሰራዊት የመሀል ሳይንት ወረዳ መቀመጫ የሆነችው ደንሣ ከተማ ውስጥ መግባቱ ተርጋግጧል:: ከኮሩ ሰራዊት መካከል የአማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለ ጦር፣ የመብረቅ ክፍለ ጦር እና የኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለ ጦር የተወሰኑ አሃዶች ተውጣጥተው በሰሩት ኦፕሬሽን እስካሁን በደረሰን መረጃ መሰረት ከ30 በላይ ጠላት የተደመሰሰ ሲሆን 1 የአድማ ብተና ሻለቃ መሪ እና 1 ሻምበል መሪ እንዲሁም 3 የወረዳ አመራሮችም አብረው እስከወዳኛው ተሸኝተዋል:: የተደመሰሰው ጠላት ቁጥር ሊጨምር እንደሚችልም ይገመታል:: በኦፕሬሽኑ 11 የጠላት ምርኮኛ እንደተያዘም ነው ለማረጋገጥ የተቻለው:: በምኒልክ ዕዝ ም/ዘመቻ መሪ ኮሎኔል ፈንታው መኩዬ፣ በዕዙ ም/ወታደራዊ አዛዥ ሻለቃ ሀብታሙ ደምሴ እና በንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር አዛዥ በአርበኛ አብነው ታደሰ እንዲሁም በዕዙ ወታደራዊ አማካሪ በሻለቃ ክንዱ ሰውነት የተመራው የደንሣው ኦፕሬሽን የጠላት 4 ከባድ ምሽጎች የተሰበሩበት መሆኑም ታውቋል:: በከተማይቱ ዳር ማለትም በጎራደ ሽነት፣ በዙሀ፣ በጎጃም በር እና በሙያ እና ቴክኒክ ጠላት ያዘጋጃቸው ምሽጎች ሙሉ በሙሉ ተሰብረዋል:: ጠላት ሲጠቀምባቸው የነበሩ ቁሳቁሶች እና ሌሎች ንብረቶች በኮሩ ሰራዊት እጅ ገብተው ወደ ፋኖ የጦር ሰፈር የተወሰዱ ሲሆን በኮሎኔል መብሬ የተመራው የጠላት ኃይል ከእስከዛሬው በበለጠ አኳኃን ከባድ ሰብአዊ ኪሳራ ጭምር እንደደረሰበት ነው የውስጥ ወታደራዊ ምንጮች የገለፁት:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ጥቅምት 2 ቀን 2018 ዓ.ም

አገዛዙ ሊረዳው ያልቻለው ጉዳይ! ነጮቹ ''Accepting defeat is a beginning of victory/ሽንፈትን አምኖ መቀበል የድል ጅማሮ ነው!'' ይላሉ። አሜሪካዊው ሊዮን ብሎደር  ''When Accepting Defeat Is Winning'' በሚል መጣጥፉ ላይ '' ..እየተዋጋህ ወደፊት ለመቀጠል የሚያስችል አቅሙና ጥንካሬው ባይሟጠጥብህ እንኳ የተጓዝክበትን የሽንፈት መንገድ እየደገምክ መቀጠልህን ከተረዳህና አላስፈላጊ ዋጋ መክፈል መሆኑን ከተገነዘብክ በጊዜ ሽንፈትህን አምኖ መቀበል ከአሸናፊነት የማይተናነስ ውጤት አለው። ሁኔታው እንግዳ ቢመስልም ፣ ራስን በማግለል እፎይታን የሚያቀዳጅ ብሎም የተሻለ መፍትሔ እንዲመጣ በር የሚከፍት ውሳኔ ነው!'' ሲል የሚገልፀውም ይህንኑ ነው። በተለይ ደግሞ እንደኛ በእርስበርስ ጦርነት ውስጥ ተዘፍቆና በገዛ ህዝቡ ላይ ጦርነት ማወጅን ልማድ አድርጎ እንዳለ አገዛዝ ፣ ሽንፈትህን አምነህ ስትቀበል ትናንት የተጓዝክበትን የተሳሳተ መንገድ ቆም ብለህ ለመገምገም እድል ታገኛለህ ፣ አላስፈላጊ ሀገራዊ ውድመትና መስዋዕትነትን ታስቀራለህ ፣ ከዚህ አዘቅትና ምስቅልቅል ውስጥ የከተተህን ስህተት ተመልሰህ ለመዳሰስ እድል ታገኛለህ ፣ አዲስ የመውጫና የሀሳብ መንገድ ለመፍጠር አጋጣሚዎች ይፈጠሩልሃል። አገዛዙ 10 ቀን አቅዶት የጀመረው ዘመቻ 3ተኛ አመቱ ላይ ደርሶ እንኳ በተመሳሳይ መንገድና እልህ እየተጓዘ እጅግ ከፍተኛ ውድመትና እልቂት እያስተናገደ የመቀጠሉ ምስጢርም ይኸው ነው! ሽንፈትን አምኖ ለመቀበል የመቸገር ግትርነት! ''እኔ ብቻ ልክ'' የሚል ከንቱ መታበይ! ራስን አልሚ ሌላውን አጥፊና አውዳሚ አድርጎ የማሰብ የአስተውህሎት መዛነፍ..! ተከታዩ ሀሳብ ሰሞኑን በሰሜን ወሎ አካባቢ ሰንብቶ ወደከተማ የገባ የመከላከያ አመራር ባረፈበት ሆቴል ''በውሃ ዙሪያ ጨዋታ'' ላይ አብረውት ለነበሩ ሰዎች ሲያወራ ከነበረውና ከደረሰን አስተያየት መካከል የተቀነጨበ ነው። << ...ከሁለት አመት በላይ ያዋጉን በራሳቸው የውጊያ እቅድ ነው። እዚህ ከተማ ድረሱ ተብለን ስንሄድ መንገድ ላይ ያስቀሩናል። እንደምንም አልፈን ከተባለው ቦታ ስንደርስ ደግሞ እነሱ ትተውን ይሄዳሉ። ለረዥም ጊዜ ያለውጊያ ተቀምጠን ጦሩ ተሰላችቶና ሞራሉ ተነክቶ ወደሌላ ቀጠና ለመሄድ ጉዞ ስንጀምር ደግሞ ወጣ ከማለታችን በመንገድ ይገጥሙናል። ባሰብነው ትተው ባላሰብነው ይመጡብናል። ሲፈልጉ ለቁጥር የሚታክት ግንባር ከፍተው ጦሩን ከወዲያ ወዲህ ያመናትሉታል። መቼ እንደሚመጡም ሆነ እንደሚወጡ ፣ በየት ግንባር እንደሚዋጉና እንደማይዋጉ ወስነው የሚጋብዙን እነሱ ናቸው! ነገሩ እንደሚወራው አይደለም። ከባድ ነው...>> ሲል ነበር ግምገማውን የገለፀው። ከነባራዊ ሁኔታውና ህዝቡ በየእለቱ በአይኑ ከሚያየው ተጨባጭ እውነታ በመነሳት ይህ የአብዛኛው የበታች አዛዦችና የጦሩ አስተያየት ጭምር መሆኑን መገመት አያዳግትም። '' ኃላቀር መሳሪያ የታጠቁ አስር ጃውሶች ፣ ሽፍቶች ፣ በአስር ቀን እናጠፋቸዋለን!'' ከሚለው ንግግር አንስቶ በየመድረኩ '' ቆመው መዋጋት እንዳይችሉ አድርገናቸዋል ፣ ደምስሰናቸዋል ፣ በትነናቸዋል ፣ እያፀዳን ነው ፣ ለቀማ ላይ ነን ፣ ...'' የሚሉ ተመሳሳይ ድስኩሮችን እየሰማን ዛሬ ላይ ደርሰናል። በተቃራኒው እውነታውን ደግሞ ህዝብ ያውቀዋል። ጠብመንጃ ያነሳውን ሃይል ኮዝ እንደሌለው ፣ ፖለቲካዊ ጥያቄና አላማ እንዳላነገበ ፣ የህዝብ ጥያቄዎችን ለማስመለስ እንደማይታገል አድርጎ ለማቅረብ የሚደረገው ተራ ፕሮፓጋንዳም የአገዛዙን ገመና ከማጋለጥ ብሎም ነገሮችን ከማወሳሰብ የዘለለ አንዳች ፋይዳ የለውም። ይህን ለአስር ቀን የታቀደን ሀይል በየእለቱ በሁለንተናዊ አቅሙ እያጎለበተና ግዙፍ ሀይል እየገነባ አመታትን ወደፊት እንዲጓዝ ያደረገው ጠንካራ ኮዝና ህዝባዊ መሠረት ስላለው መሆኑን አለመረዳት ደግሞ በርግጥም አይተ ጌታቸው ረዳ እንዳሉት የፖለቲካ ድንክነት ነው! በነገራችን ላይ ለአንድ ፀረ-አገዛዝ አቋም ይዞ ጫካ ለገባ ታጣቂ ቡድን ፥ እንኳን በአንድ ቀን ሁለት እዝ እየደመሰሰ ፣ በየእለቱ አጃኢብ የሚያሰኝ ወታደራዊ ድል እየተቀዳጀ ፣ ራሱን በሁለንተናዊ መልኩ እያፈረጠመ መቀጠሉ ይቅርና መኖሩ/existence ብቻ እንደ ድል የሚወሰድ ሲሆን ለአገዛዝ ደግሞ የታጣቂ ቡድኑ መኖሩ ብቻ ሊጂቲሜሲውን እያሳጣው ፣ የነበረው መንግስታዊ መታመን እየተሸረሸረ ፣ ሀይሉና መዋቅሩ እየፈራረሰ እንዲሄድ ስለሚያደርገው እንደሽንፈት ይቆጠራል። በርግጥም ሽንፈት ነው! በመሆኑም ፦ የሚበጀው  ከተለመደው ተራ የፖለቲካና የፕሮፓጋንዳ አካሄድ ራስን አቅቦ እውነታን አምኖ መቀበል ነው። በመቀጠልም ትውልድ እየገበሩ ፣ ሀገር እያወደሙና በደም እየታጠቡ ከመጓዝ ፣ ለችግሮቹና ለህዝባዊ ጥያቄዎቹ እውቅና ሰጥቶ ያለአንዳች ቅድመ ሁኔታ ለድርድርና ለፖለቲካዊ መፍትሔ ራስን አዘጋጅቶ ወደተግባር መግባት ነው! ''በለው ፍለጠው ፣ ደምሳሹ ፣ ፀሀዩ መንግስቴ'' ከሚሉት ገደል ከታች የሚዲያ ሚሊሾቹ ውጪ የማይሰማው አገዛዝ ስርአታዊ መዋቅሩን ለማትረፍ በእጅጉ ያረፈደና እድሎቹን ያመከነ ቢሆንም ቅሉ ፣ ሀገርና የቀጣዩ ትውልድ ተስፋ የሚያተርፍበትን እድል የሚጠቀምበት ጊዜው ግን አሁን ነው! አለበለዚያ ግን እመነኝ! አሜሪካን በአፍጋኒስታን ያሳለፈችውን ሁለት አስርት አመታት ያህል አይደለም  በእጥፉ ብትዋጋ እንኳ ወታደራዊ ድልን ፈፅሞ ልትቀዳጅ አትችልም! ይኸው ነው! ©ዘርይሁን ገሠሠ

ማህበረሰቡ ይኸንን አሸባሪ እና ወራሪ የብልፅግና ስርዓት እስኪወገድ ድረስ በፅኑ እንታገለዋለን ብሏል‼️ ሻለቃ አንሙት ያዛቸው ብርጌድ በአግታ ቀበሌ ሰፊ ህዝባዊ መድረክ ውይይት ተካሄደ። በዛሬው እለ
ማህበረሰቡ ይኸንን አሸባሪ እና ወራሪ የብልፅግና ስርዓት እስኪወገድ ድረስ በፅኑ እንታገለዋለን ብሏል‼️ ሻለቃ አንሙት ያዛቸው ብርጌድ በአግታ ቀበሌ ሰፊ ህዝባዊ መድረክ ውይይት ተካሄደ። በዛሬው እለት በቀን ጥቅምት 02/2018 ዓ.ም የማህበረሰብ ችግሮችን በመለየት በፋኖ አደረጃጀቶች እና አሰራር ዙሪያ እንዲሁም በህዝባዊ አስተዳደር መዋቅሮች ላይ ያለውን በመገምገም ህዝባዊ አደረጃጀቶችን በማጠናከር መዋቅሮችን በመፈተሽ ያለፉ አፈፃፀሞችን በመገም ቀጣይነት ያለው አሰራር  በመዘርጋት የማብቃት ስራ በክፍለ ጦሩ የአደረጃጀት ዘርፍ እና የፓለቲካ ዘርፍ አመራሮች በጥልቀት የማወያየት ስራ የተሰራ ሲሆን በቀጣይ ስራወቻችን ላይ በመግባባት በማንኛውም ተግባር ህዝቡ ከጎናችን እንደሚሆኑ የመግባባት ስራ ተሰርቷል።  ፋኖ ሐብታሙ የሱፍ የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴድሮስ ዕዝ 1ኛ ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት 02/ዐ2/2018 ዓ.ም

የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነዉ ዕዝ ኃ/ማርያም ማሞ ክፍለጦር በአገዛዙ ጥምር ጦር ላይ ድል ተቀዳጀ። ከጧቱ ጀመሮ እስካሁን ድረስ ዉጊያዉ የቀጠለ ሲሆን የኃይለ ማርያም ማሞ ክፍለጦር በሸዋ ቡልጋ ሀገረማርያም ከተማ ወጣ ብላ በምትገኘው ነፋስ አምባ ከፍተኛ ትንቅንቅ እያደረገ ይገኛል። የአጋዚ ኮማንዶ፣የሚሊሺያ እና የአድማ ብተና አባላት ላይ በተወሰደ የደፈጣ ጥቃት በደርዘን የሚቆጠር የጠላት ሀይል ተደምስሷል።በአዉደዉጊያ ሁለት አንቡላንስ የጥምር ጦሩ ሙት እና ቁስለኛ ይዞ ወደ ሀገረ ማሪያም ከተማ ሆስፒታል ይዞ መግባቱ ተረጋግጧል። ዉጊያዉ አድማሱን አስፍቶ የቀጠለ ሲሆን የሃይለማርያም ማሞ ክፍለጦር በጠላት ላይ ከፍተኛ ድል አስመዝግቧል።በሸዋ ቡልጋ የገበዉ የአገዛዙ ሰራዊት አብዛኛው ሙትና ቁስለኛ መሆኑን ተከትሎ ጠላት ከቡልጋ ሀገረማሪያም ከተማ እና ከዙኖ መናገሻ ደብረብርሀን ከተማ በርካታ ሰራዊት ይዞ ቢገባም የሃይለማርያም ማሞ ልጆች የመጣዉን ጠላት በሚገባ እያናገሩት ይገኛሉ።

የአብይ አህመድ ሰራዊት የመዋጋት ሞራል የለውም። ሰራዊቱ በግዳጅ እንዲሰለጥን ተደርጎ በግዳጅ እንዲዋጋ  እየተደረገ ነው።  ምንም የሚዋጋበት ምክንያት የለውም ። እንዲያውም የገዛ ቤተሰቡ በአሰቃቂ ሁኔታ በከባድ መሳሪያ እና ምክንያት እየፈለጉ የጥይት አረር ሲያነዳቸው ባይኑ እያየ መውጫ መንገዱ ጠፍቶበት አንገቱን ደፍቶ እያለቀሰ ይገኛል። ጥቂት የሚባሉት በስውር የሰለጠኑ ከመከላከያ ጋር በመቀላቀል ሕዝባችንን ጅምላ ጭፍጨፋ እየፈፀሙበት ይገኛሉ።።  አብይ አህመድ ኢተር ሀሞይ ቡድን አሰልጥኖ የመከላከያ  ልብስ አልብሶ ወደ አማራ ክልል እያስገባ ይገኛል። በሕዝባቸው መጨፍጨፍና መደፈር የተቆረቆሩት እየለቀቁ ወደፋኖ በየቀኑ እየተቀላቀሉ ይገኛል። ዘር ጨፍጫፊው የመከላከያ  ልብስ የለበሰው ኢንተር ሀሞይ ቡድንም በደረሰበት ምት አንገቱን ደፍቶ እያለቀሰ ይገኛል። ባሰቡት መንገድ ያልሄደላቸው እኒህ አረመኔ ሰራዊቶች  በየግንባሩ እየተሸነፉ እና የመዋጋት  ሞራላቸውም  እየላሸቀ ይገኛል። አብዛኛው መከላከያም በየአቅጣጫው ተበትኗል።  በተቃራኒው በየቀኑ ኮማንዶ እያስመረቀ የሚገኘውፋኖ በሚገርም የድል ግስጋሴ የሚገኝ መሆኑ የአደባባይ ሚስጢር ነው። በመሆኑም  ሕዝብን ጨፎጭፎ መጨረስ አይቻልም። ሕዝብንም ያሸነፈ አንባገነን መሪ በዓለም ላይ አልታየም ። ከማለቃችሁና ከመደምሰሳችሁ በፊት በየትኛውም ቀጠና ያላችሁ የአብይ አህመድ  የግል ጠባቂ መከላከያዎች ሆይ እጅ ትሰጡ ዘንድ ጥሪየን አቀርባለሁ። አዲስ ትውልድ ፣አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ! ጥቅምት 02/2018ዓ.ም ©እስቲበል ዓለሙ

Repost from Amhara Revolution
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ምክትል ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ ድረስ ሞላ የትግሉን አሁናዉ ሁኔታ በማስመልከት ያስተላለፈዉ መልዕክት!!!!!!