cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Ashara Media - አሻራ ሚዲያ

ስልክ፥ +251984190114 / +251993111700

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
47 836
المشتركون
+2224 ساعات
+1347 أيام
+10530 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

አርበኛ ተፈሪ መኮነን! ከ2008 ዓ/ም በፊት የአሚኮ ፕሮሞሽን ሀላፊ፣ የህዝባዊ ግንባሩ መስራች፣ የንስር ሚዲያም መስራች ፣በባህርዳር ከተማ ወጣቱን ማንቃት ጉልህ ሚና የተጫወተ ድንቅ አርበኛ ነበረ። ይህ አርበኛ በኮሎኔል ፈንታው ሙሀቤ የሚመራው የወሎ ዕዝ እና በዋርካው ምሬ ወዳጆ የሚመራው የምስራቅ አማራ ፋኖ ወደ አንድ እንዲመጣ የተቋቋመውን ኮሚቴ በመምራትና ሂደቱ እንዲፋጠን ወሳኝ ሚና የተጫወተ ነው። በተመሳሳይ ሻለቃ መከታው ማሞ የሚመራውን የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛትን እና በአርበኛ አሰግድ የሚመራውን የአማራ ፋኖ በሸዋ ወደ አንድ እንዲመጡ ለማድረግ እየሰራ ካለው ኮሚቴ አባል በመሆን ስራዎችን እየሰራ ይገኝ ነበር። አገዛዙ ከወራቶች በፊት በደብረ ኤልያስ ገዳም የሰነዘረውን ጥቃት ለመመከት ከጓዶቹ ጋር ተሰልፎ በርካታ ገድሎችን ፈፅሟል። አርበኛ ተፈሪ አገዛዙ በጥላቻ ተነሳስቶ በአማራነታቸው ብቻ ገሚሶችን በማሰር፡ መያዝ ያልቻላቸውን ደግሞ በሌሉበት በሽብር ወንጀል ከከሰሳቸው ውስጥ አንዱ ናቸው። ይህ ኩሩ ጀግና በአማራ ትግል ሂደት ውስጥ የሚስተዋሉ ውስብስብ ችግሮችንና እንቅፋኖችን በመበጣጠስ በጎጃም፣ በሸዋ፣ በወሎና በጎንደር ያሉ ፋኖዎች ወደ አንድ መጥተው የአማራ ፋኖ እንዲቋቋም ትልቅ ጥረት እያደረገ ባለበት ሰሞኑን በሰሜን ወሎ ዞን ጉባላፍቶ ወረዳ ልዩ ስሙ ሸዋት በተባለ አከባቢ ላይ አገዛዙ በፈፀመው የድሮን ጥቃት በክብር ተሰውቷል። ©ጋዜጠኛ ሙሉጌታ አምበርብር
إظهار الكل...
😭 77👍 39😢 6 2
ባህር ዳር ባለፀጋ፣ ደፋር፣ በክብሩ የማይደራደር ሰው አጣች። ተፈሪ መኮንን ይባላል። የአሚኮ ፕሮሞሽን ሀላፊ ነበር። አንድ ለአምስት አልሰበሰብም በማለቱ ከደረጃ ዝቅ ሲል  በክብሬ እና በነፃነቴ ብሎ በ2008 ስራ ለቀቀ።  ከዚያም በባህርዳር ወጣቱን ማንቃት፣ ማደራጀት ጀመረ። የአብን ዋና አንቀሳቃሽ ሞተር፣ የንስር ሚዲያም መስራች፣ የህዝባዊ ግንባር መስራች፣ በሗላም ሁሉም የአማራ  ፋኖዎችን ወደ አንድ ሊያመጣ ወሎ በሄደበት ቤተክርስቲያን ላይ በድሮን ተመቶ መስዋዕት ሆኗል። ትግሉ በእንቁ ወንድሞቻችን መስዋዕትነት ይቀጥላል።
إظهار الكل...
🙏 81👍 49😢 25😭 10 5 3
የአማራ ፋኖ በጎጃም ም/ሰብሳቢና ዋና ወታደራዊ አዛዥ ሻለቃ ዝናቡ ልንገርህ በወቅታዊ ጉዳይ ከሮሃ ሚዲያ ጋዜጠኛ መዓዛ መሀመድ ጋር ያደረገው ቆይታ
إظهار الكل...
👍 102 12🔥 5
“ጎጃም ውስጥ 10 ክፍለጦሮች ካለው የአማራ ፋኖ በጎጃም ውጭ ሌላ ወታደራዊ አደረጃጀት አላውቅም” ሻለቃ ዝናቡ ልንገረው ~የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል እና የወታደራዊ መምሪያ ኃላፊ ለሮሀ ሚዲያ ከተናገረው
إظهار الكل...
107👍 48🔥 6🤬 3
በፈረንሳይ ፓሪስ የርዳታ ማሰባሰብ ፕሮግራም ይዘጋጃል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የአማራ ማህበር በፈረንሳይ ሀብታሙ አያሌውን የጋበዘው ቢሆንም ሀብታሙ ፋኖን በሚከፋፍል በያዘው አቋም የሀብታሙን ግብዣ እንደሰረዙት አዘጋጆች አስታውቀዋል።
إظهار الكل...
👍 107👏 16🔥 3😢 3
ሰበር ዜና - ያልታወቁ ኃይሎች! በአጠቃላይ 14 የባህርዳር ከተማ አመራሮች በአንድ መኪና እየሄዱ እያለ ባልታወቁ ኃይሎች መያዛቸው ታውቋል። ተምሮ ከህዝብ ይወግናል በሚል ከትንሽ እስከ ትልቅ ላለው የብአዴን አመራር በተለያየ ጊዜ እድል ቢሰጥም፣ ነገር ግን መዘባነኑ የበዛ ሆኖ በመታየቱ ባልታወቁ ኃይሎች እጅ የገባ በሙሉ መጨረሻው ግልፅ ይመስላል። ፑቲን በአንድ ወቅት እንዲህ እንዳለ ይነገራል - "ምህረት የፈጣሪ ስራ ነው፤ የእኔ ስራ እኩይ ፍጥረታትን ወደ እሱ (ወደ ፈጣሪ) መላክ ነው"። Bw
إظهار الكل...
👍 381 57🔥 27😢 24😎 19
መስመራዊ መኮንኖች በብዛት እንዲወስዱ ተደርጓል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በሰሜኑ ጦርነት የተሰው የአማራ እና የደቡብ ተወላጅ የሆኑ ከፍተኛ የመከላከያ የጦር መኮንኖችን ጨምሮ በርካቶች ቤተሰቦቻቸው ከመከላከያ ካምፕ ጭምር ተባርረው በየመንገዱ በልመና ላይ የተሰማሩ እንዳሉ ይታወቃል። "የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን" ዋና ሥራ አሥፈፃሚ ብርጋዲየር ጄኔራል ደረጀ መገርሳ የአማራ እና የደቡብ ተወላጅ የሆኑ በሰሜኑ ጦርነት ሲያዋጉ ህይወታቸው ያለፈ የጦር መኮንን ቤተሰቦች ያቀረቡትን 'የቤት ይሰጠን' ተማፅኖ ውድቅ በማድረግ ኦሮሙማዊ ተልዕኮውን  ስለመወጣቱ፣ በሌላ በኩል ደግሞ የመከላከያ ሚኒስትሩ አብረሃም በላይ፥ የወያኔ የጦር አዋጊዎች የመኖሪያ ቤት አፓርታማው እንዲሰጣቸው የማስተባበሩን ሚና እንደተወጣ ለኢትዮ 251 ሚዲያ የደረሳት መረጃ ያሳያል።  አሁን በአማራ ክልል በአማራ ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ዓላማ ያለው ጦርነት ተከፍቶ በውጊያ ላይ ያሉ የሰራዊቱ አባላት ለምን ዓላማ እንደሚዋጉ እንኳ አያውቁትም፤ ዓላማውን የሚያውቁት የፋሽስታዊ ስርዓቱ አርክቴክቶች ናቸው። በመሆኑም በህይወት ያላችሁ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ሞታችሁ የአንድ ግለሰብ ወንበር ከማስጠበቅ እንደማይዘል አውቃችሁ፣ የውሻ ሞት ከምትሞቱ ከዚህ ትምህርት ልትወስዱ ይገባል፤ ዓላማውን በማታውቁት ጦርነት ውስጥ ገብታችሁ ስትሞቱ ቤተሰባችሁን ዘወር ብሎ የሚመለከት የለም። ይህ ትምህርት የአማራና የደቡብ ተወላጅ ለሆናችሁ የሰራዊቱ አባላት በይበልጥ ደግሞ መስመራዊ መኮንኖች የቀረበ ጥሪ ነው። ©️ ኢትዮ 251 ሚዲያ
إظهار الكل...
👍 146 17😢 12
አስቸኳይ የጥንቃቄ መልዕክት!..‼️‼️ አሁን ምሽት 12:40 አካባቢ ከቢሾፍቱ በኩል ወደ አዲስ አበባ ከ 6-8 ቅጥቅጥ የቀድሞው የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ዩኒፎርም የለበሱ ተጭነው ፍተሻው ጋር ቀደም ብለው ቆመዋል። ምን አልባት ከተማውን ሲመሽ ለማለፍና ወደአማራ ክልል የሚያመራ ይመስላል። በሁለቱም መውጫ መንገዶች ክትትልና ማጣራት ይደረግበት። ሼር ለማድረግ አድርሱ !
إظهار الكل...
👍 127 18
🔥የኦነግ ብልፅግና መሪ ከባህርዳር ፈረጠጠ…‼️ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የባሕር ዳሩን ፕሮግራም አቋርጠው ወደ መጡበት መመለሳቸው ተሰምቷል። የአማራ ክልል መዲና በሆነችው ባሕር ዳር ከተማ ቀበሌ 11 ዙሪያ የተገነባው የዓባይ ድልድይ ምርቃ ሥነ ሥርዓት ላይ ከነባለቤታቸውና ከሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ጋር የታደሙት በአማራ ህዝብ ላይ ጦርነት ያወጁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ፡ ፕሮግራሙ ከሚካሄድበት አከባቢ በቅርብ ርቀት ላይ ፋኖ ተደጋጋሚ የሆነ የቦምብ ጥቃት በመፈፀሙ የምረቃ ሥነ ሥርዓቱን አቋርጠው በመጡበት ሄሊኮፍተር ወደ አዲስ አበባ መመለሳቸውን የአማራ ድምፅ ሚድያ የባሕር ዳር ከተማ ቅርንጫፍ ዘጋቢዎች ለማረጋገጥ ችለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሰሞኑ የምስራቅ ወለጋ ዋና መቀመጫ በሆነችው ነቀምቴ ከተማ ሄደው በሰላም መመለሳቸው የሚታወቅ ሲሆን ነገር ግን በዛሬው ዕለት የአማራ ክልል ርዕሰ መዲና ባሕር ዳር እንደ ምስራቅ ወለጋዋ ነቀምቴ ከተማ ሳትሆንላቸው ቀርታለች ነው የተባለው። የዓባይ ድልድይ ምረቃ ሥነ ሥርዓት በሚካሄድበት ቀበሌ 11 ዙሪያ ፋኖ ተደጋጋሚ የሆነ የቦምብ ጥቃት የፈፀመ ሲሆን በዚህም ጠቅላይ ሚኒስትሩና ባለቤታቸው ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እንዲሁም ሌሎች የፌደራልና የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት ተደናግጠው በሁለት ሄሊኮፍተር ተሳፍረው በአፋጣኝ የሰሜን ምዕራብ ዕዝ መቀመጫ ወደ ሆነው መኮድ ካምፕ የሄዱ ቢሆንም፡ ነገር ግን በካምፑ ዙሪያም ተመሣሣይ የሆነ የቦምብ ጥቃት በመፈፀሙ በድጋሚ ሄሊኮፍተሮቻቸውን አስነስተው ወደ አዲስ አበባ መብረራቸውን ነው የአማራ ድምፅ ሚድያ የባሕር ዳር ከተማ ወኪሎች ያረጋገጡት። ባለስልጣናቱ ተደናግጠው የድልድዩን ምረቃ ሥነ ሥርዓት ሳያጠናቅቁ ወደ መኮድ ካምፕ በሚበሩበት ወቅት፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከነ ባለቤታቸው ተሳፍረውበት የነበረው ሄሊኮፍተር በከፍታ ላይ የበረረ ሲሆን ነገር ግን በቅርቡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተደርገው የተሾሙት አቶ ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ ሌሎች ባለስልጣናትን የያዘችው ሁለተኛዋ ሄሊኮፍተር ዝቅ ብላ መብረሯን ዘጋቢዎቻችን ለመመልከት ችለዋል። በከተማዋ ሆምላንድን ጨምሮ ባለስልጣናቱ ተሰባስበው ይገኙባቸዋል በተባሉ በተለያዩ ትላልቅ ሆቴሎች ላይ ከለሊት ጀምሮ  የቦምብ ጥቃት ሲፈፀም ማደሩም ነው የታወቀው። በዚህም እስካሁን የታወቁ አንድ የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራርን ጨምሮ ከሚኒሊክ ክ/ከተማ በቁጥር ሦስት አመራሮች፣ ከፋሲሎ ክ/ከተማ ሁለት፣ ከቴዎድሮስ ክ/ከተማ አንድ አመራር ቆስለው ወደ ፈለገ ህይወት ሆስፒታል መወሰዳቸውንም ነው የአማራ ድምፅ ሚድያ የባሕር ዳር ወኪሎች ያረጋገጡት። ከዚህ በተጨማሪ፡ የድልድዩ ምረቃ ስነ ስርዓት በተጀመረ በደቂቃዎች ውስጥ በቁጥር ከአምስት በላይ የሚሆኑ ሪፐብሊካን ጋርዶች ከነመሣሪያቸው የተሰወሩ ሲሆን፡ እነሱን ፍለጋ መነሻቸውን ከመኮድ ካምፕ ያደረጉ በርካታ ወታደሮች በከተማዋ መሰማራታቸው ታውቋል። © አማራ ድምፅ
إظهار الكل...
👍 173 16🔥 8🤯 2🤬 1
አሳዛኝ እልቂት በድሮን ጥቃት በርካታ ንፁሃን ተጨፈጨፉ ..‼️‼️ በሸዋ ይፋት ቀጠና በቀወት ወረዳ የለን ቀበሌ ጉሎ  ትምህርት ቤት ላይ ዛሬ ግንቦት 4/2016 ዓ.ም ሁለት ጊዜ በተከታታይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት በርካታ ንፁሃን ተገድለዋል። ከተገደሉት ውስጥ የትምህርት ቤቱ ሰራተኞች የሆኑ 4 መምህራን ይገኙበታል። ከ27 በላይ ንፁሃን ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል። እግራቸውን እና እጃቸውን በድሮን ጥቃት ያጡት ወገኖች ህክምና ተቋም መድረስ ባለመቻላቸው ብዙ ደም ፈሷቸው ሕይወታቸው እያለፈ ነው ሲሉ ምንጮች ገልፀዋል። ባለፉት 11 ወራት በዐማራ "ክልል" ከ90 ጊዜ በላይ የድሮን ጥቃት ተፈጽሞ 512 በላይ ንፁሃን መጨፍጨፋቸውን   ምንጮች አስተውሰዋል። ግንቦት 4/2016 ዓ.ም @በለጠ ካሳ
إظهار الكل...
👍 59😢 23😭 6 5🥰 4 2