ፍኖተ ወንጌል ሰንበት ት/ቤት
الذهاب إلى القناة على Telegram
በአሰላ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ካቴድራል ፍኖተ ወንጌል ሰንበት ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው። የቴሌግራም ቻናል:- @Finote_Wongel የቴሌግራም ግሩፕ:- @FinoteWongel27 የቲክቶክ ገፅ:- https://www.tiktok.com/@finotewongel27 Youtube:- https://www.youtube.com/@Finote_Wongel ©ፍኖተ ወንጌል ሰንበት ት/ቤት
إظهار المزيد671
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+27 أيام
+530 أيام
جاري تحميل البيانات...
القنوات المماثلة
سحابة العلامات
لا توجد بيانات
هل تواجه مشاكل؟ يرجى تحديث الصفحة أو الاتصال بمدير الدعم الخاص بنا.
الإشارات الواردة والصادرة
---
---
---
---
---
---
جذب المشتركين
أكتوبر '26أكتوبر '26
أكتوبر '260
في 0 قنوات
سبتمبر '26
+18
في 0 قنوات
Get PRO
أغسطس '26
+16
في 0 قنوات
Get PRO
يوليو '26
+17
في 0 قنوات
Get PRO
يونيو '26
+9
في 0 قنوات
Get PRO
مايو '26
+13
في 0 قنوات
Get PRO
أبريل '26
+11
في 0 قنوات
Get PRO
مارس '26
+7
في 1 قنوات
Get PRO
فبراير '26
+25
في 0 قنوات
Get PRO
يناير '26
+39
في 0 قنوات
Get PRO
ديسمبر '25
+23
في 1 قنوات
Get PRO
نوفمبر '25
+19
في 0 قنوات
Get PRO
أكتوبر '25
+15
في 0 قنوات
Get PRO
سبتمبر '25
+17
في 0 قنوات
Get PRO
أغسطس '25
+10
في 0 قنوات
Get PRO
يوليو '25
+11
في 0 قنوات
Get PRO
يونيو '25
+23
في 0 قنوات
Get PRO
مايو '25
+7
في 0 قنوات
Get PRO
أبريل '25
+18
في 1 قنوات
Get PRO
مارس '25
+13
في 0 قنوات
Get PRO
فبراير '25
+14
في 0 قنوات
Get PRO
يناير '25
+53
في 1 قنوات
Get PRO
ديسمبر '24
+29
في 0 قنوات
Get PRO
نوفمبر '24
+35
في 0 قنوات
Get PRO
أكتوبر '24
+29
في 0 قنوات
Get PRO
سبتمبر '24
+20
في 1 قنوات
Get PRO
أغسطس '24
+27
في 0 قنوات
Get PRO
يوليو '24
+71
في 0 قنوات
Get PRO
يونيو '24
+76
في 0 قنوات
Get PRO
مايو '24
+61
في 0 قنوات
Get PRO
أبريل '24
+129
في 0 قنوات
Get PRO
مارس '24
+37
في 1 قنوات
Get PRO
فبراير '24
+21
في 0 قنوات
Get PRO
يناير '24
+277
في 0 قنوات
| التاريخ | نمو المشتركين | الإشارات | القنوات | |
| 03 أكتوبر | 0 | |||
| 02 أكتوبر | 0 | |||
| 01 أكتوبر | 0 |
منشورات القناة
ደስ ብሎናል ደስ ይበላችሁ፣ ለቅኖች ምስጋና ይገባልና እነሆ ልናመሰግናችሁ በቃን።
የምስራች ከሁሉ አስቀድሞ ሁሉን ላደረገ፣ ሲሰጥ የማይሰስት፣ ሰጥቶ የማይነጥፍበት፣ ሁሉ በርሱ : ለእርሱ የሆነለት ጌታችን መድኃኒታችን አምላካችን ቅዱስ እግዚአብሔር ስላደረገልን መልካም ነገር ሁሉ ስሙ ለዘለዓለሙ የተመሰገነ ይሁንልን!!!
ከሐምሌ 19/2018 ዓ/ም ጀምሮ በአሰላ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ካቴድራል ፍኖተ ወንጌል ሰንበት ትምህርት ሚዲያ እና በሌሎች ልዩ ልዩ የሚዲያ አጋሮች እንዲሁም በቅን እህት በወንድሞቻችን የግል ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሰንበት ትምህርት ቤታችን አገልጋይ የሆነችው እህታችን ዘማሪት ሰርክዓዲስ ኃይለመስቀል (ሐና ኃይለመስቀል) በመተንፈሻ አካሏ በደረሰባት የጤና እክል ምክንያት ጥቁር አንበሳ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ባደረገችው ምርመራ የልብ ቀዶ ጥገና ማድረግ እንዳለባት ስለተነገራት ህክምናውን ለመፈጸም ደግሞ 1,300,000.00 (አንድ ሚሊየን ሶስት መቶ ሺህ ብር) መጠየቋን ጠቅሰን መላው ኢትዮጵያውያን ለእህታችን ማሳከሚያ የሚሆን እጅ እንድትዘረጉልን ጠይቀን እናንተም ደግ ኢትዮጵያዊያን ከጉለታችሁም ላይ ቢሆን የምትችሉትን ሁሉ እንዳደረጋችሁልን ይታወቃል። ለዚህም ላቅ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን። መድኃኔዓለም ከክፉ ነገር ሁሉ እንዲጠብቃችሁ ጸሎታችን ነው።
ስለሆነም እግዚአብሔር አምላካችን የእናንተን ጸሎት ሰምቶ ያደረጋችሁትን መልካም ምኞት ሁሉ ተቀብሎ እህታችን ሙሉ በሙሉ የቀዶ ጥገና ህክምናዋን ጨርሳ ከህመሟም አገግማ በሰላም ወደቤቷ ገብታለች። በዚህ በጎ ተግባር ላይ ከእህታችን ጎን የቆማችሁ፣ ህመሟን ህመማችሁ፣ ችግሯን ችግራችሁ፣ ድካሟን ድካማችሁ አድርጋችሁ ልክ እንደራሳችሁ የለፋችሁላትና ከፈጣሪ ቀጥሎ እድሜና ጤናዋን የጨመራችሁላት፣ በንፁህ ልብ የፀለያችሁ፣ ከሌላችሁ ላይ ለረዳችሁ፣ ደውላችሁ ላፅናናችሁ፣ በምህረት ህሊና ላሰባችሁ የቅን ልብ ባለቤቶች እንዲሁም ገንዘብ በማሰባሰብ የተረባረባችሁ አጋር የሰንበት ት/ቤት አገልጋዮችና ደጋግ የተዋህዶ ልጆች ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው ።
የአሰላ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ካቴድራል ፍኖተ ወንጌል ሰንበት ትምህርት ቤት!
✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨
የቴሌግራም ቻናል:- T.me/Finote_Wongel
| 2 | 👥👥👥👥👥🌟🌟🌟👥👥👥👥👥
#ጉባዔ_ኒቅያ፦
በ፫፻፳፭ ዓ.ም አርዮስ የሚባል መናፍቅ የእግዚአብሔር ወልድን የባሕርይ አምላክነት አልቀበልም በሚል ክህደት እርሱ ተሰናክሎ ለሌሎችም መሰናክል ኾነ፡፡ ኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንት አርዮስ ክህደቱን እንዲተው ቢመክሩትም ሊመለስ አልቻለም፡፡ ይህ የአርዮስ ክህደትም በሊቃውንቱ መካከል መለያየትን ፈጥሯል፡፡ ጊዜው ታላቁ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ "አብያተ ጣዖታት ይትአጸዋ አብያተ ክርስቲያናት ይትረኀዋ፤ የጣዖታት ቤቶች ይዘጉ! አብያተ ክርስቲያናት ይከፈቱ!" የሚል ዐዋጅ የነገረበት ወቅት ነበርና ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ በአርዮስ ክህደት ምክንያት በኒቅያ የሃይማኖት ጉባኤ እንዲካሔድ በየአገሩ ላሉ ሊቃውንት መልእክት አስተላለፈ፡፡
በዚህም መሠረት ከሚያዝያ ፳፩ ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም ፳፩ ቀን ድረስ ፳፫፻፵፰ (ሁለት ሺሕ ሦስት መቶ ዐርባ ስምንት) ሊቃውንት በኒቅያ ተሰበሰቡ፡፡ ኒቅያ ለዚህ ጉባኤ የተመረጠችበት ምክንያትም ጳጳሱን ከማኅበረ ካህናቱ፤ ንጉሡን ከሠራዊቱ ጋር አጠቃላ ለመያዝ የምትችል ሰፊና ምቹ ቦታ ከመኾኗ ባሻገር ለኹሉም አማካይ ሥፍራ ስለ ነበረች ነው፡፡ በጉባኤው ከተሰበሰቡ ሊቃውንት መካከልም እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት ሙታንን ያስነሡ፣ ለምጽ ያነጹ፣ አንካሳ ያረቱ፣ የዕውራንን ዓይን ያበሩ ድውያንን የፈወሱ፣ ሌላም ልዩ ልዩ ተአምር ያደረጉ፤ እንደዚሁም ስለ ርትዕት ሃይማኖታቸው በመጋደል ዓይናቸው የፈረጠ፣ እጃቸው የተቈረጠ ይገኙበታል፡፡
ሊቃውንቱ ሱባዔ ይዘው በጸሎት ከቆዩ በኋላ ኅዳር ፱ ቀን በንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ሊቀ መንበርነት፣ በእለእስክንድሮስ አፈ ጉባኤነት ጉባኤው ተጀመረ፡፡ ንጉሡ ሊቃውንቱን "ስማችሁን፣ አገራችሁንና ሃይማኖታችሁን ጽፋችሁ ስጡኝ" ባላቸው ጊዜም ከ፳፫፻፵፰ቱ (2348) መካከል ፫፻፲፰ (318) ሊቃውንት ሃይማኖታቸውን ሲገልጹ እንደ አንድ ልብ መካሪ፣ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ኾነው "ዘዕሩይ ምስለ አብ በመለኮቱ፤ ወልድ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በመለኮት፣ በሥልጣን፣ በፈቃድ፣ በህልውና አንድ ነው" ብለው ጽፈው ሰጡት፡፡ ንጉሡም "ሃይማኖት እንደ ፫፻፲፰ቱ ሊቃውንት ይኹን" ብሎ ዐዋጅ አስነግሯል፡፡ እነዚህ ሊቃውንት በኦሪት ዘፍጥረት የተጠቀሱት ፫፻፲፰ቱ የአብርሃም ብላቴኖች ምሳሌዎች ናቸው /ዘፍ.፲፬፥፲፬/፡፡
፫፻፲፰ቱ ሊቃውንት በጉባኤው አርዮስን አውግዘው በመለየት "ነአምን በአሐዱ አምላክ፤ በአንድ አምላክ እናምናለን" የሚለውን የሃይማኖት ጸሎት (የሃይማኖት መሠረት) እና ሌሎችንም የሃይማኖት ውሳኔዎችን ደንግገዋል፡፡ ሊቃውንቱ ጉባኤውን ያካሔዱት ኅዳር ፱ ቀን ይኹን እንጂ በአንድነት የተሰባሰቡት መስከረም ፳፩ ቀን ስለ ነበረ ይህ ዕለት "ብዙኃን_ማርያም" እየተባለ ይጠራል፡፡ ብዙ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ለሃይማኖታዊ ጉባኤ የተሳባሰቡበት ዕለት ነውና፡፡
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✨✨✨✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ዕፀ_መስቀል፦
በሌላ በኩል መስከረም ፳፩ ቀን የጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በአምባሰል ተራራ በግሸን ደብረ ከርቤ የገባበትና በዓሉ የከበረበት ዕለት ነው፡፡ ታሪኩም በአጭሩ የሚከተለው ነው፤
ዐፄ ዳዊት መንፈሳዊና ደግ ንጉሥ ነበሩ፡፡ በዘመናቸው በኢትዮጵያ ቸነፈር ተከሥቶ ሕዝቡ ስለ ተሰቃየባቸው እጅግ አዘኑ፤ በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ቢያመለክቱም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላኩ ባሕታዊ መጥተው "የጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን መስቀል አስመጥተህ በአገርህ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አሠርተህ ብታስቀምጥ ረሃቡ፣ ቸነፈሩ ኹሉ ይታገሥልሃል" አሏቸው፡፡ ዐፄ ዳዊትም ከብዙ ገጸ በረከት (ስጦታ) ጋር "የጌታችንን መስቀል ላኩልኝ" የሚል መልእክት አስይዘው መልእክተኞችን ወደ ኢየሩሳሌም ሰደዱ፡፡ መልእክተኞቹም በታዘዙት መሠረት መስቀሉን ይዘው መምጣታቸውን ዐፄ ዳዊት ሲሰሙ "ክተት ሠራዊት ምታ ነጋሪት" ብለው መስቀሉን ለመቀበል ጉዞ ጀመሩ፡፡
ዐፄ ዳዊት ስናር (ሱዳን) ደርሰው ከመልእክተኞቹ ጋር ተገናኝተው መስቀሉን በክብር አጅበው ወደ መካከል ኢትዮጵያ ለማስገባት ሲነሡም ከበቅሏቸው ወድቀው ጥቅምት ፱ ቀን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፤ በዚህም ሠራዊታቸው ተደናግጠው የጌታችንን መስቀል እዚያው ትተው የዐፄ ዳዊትን አስከሬን ይዘው ተመለሱ፡፡ መስቀሉ በስናር ከቆየ በኋላ የዐፄ ዳዊት ልጅ ዘርዐ ያዕቆብ ሲነግሡ ወደ መሃል ኢትዮጵያ አምጥተው ቤተ ክርስቲያን አሠርተው ለማስቀመጥ ቢያስቡም ምቹ ቦታ ግን ሊያገኙ አልቻሉም ነበር፡፡ ንጉሡና ሠራዊታቸው ምቹ ቦታ ሲፈልጉ መስቀሉን በኤረር ተራራ፣ በደብረ ብርሃን፣ በመናገሻ ማርያም ዓምባ፣ በእንጦጦ ጋራ ብዙ ጊዜ አስቀምጠውት ቆይተዋል፡፡
መስቀሉ በእንጦጦ ጋራ ሳለ እግዚአብሔር አምላክ "አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል፤ መስቀሌን በመስቀለኛ ተራራ ላይ አስቀምጥ" የሚል ቃል ለንጉሡ በራእይ ነገራቸው፡፡ መስቀሉን ወደ ወሎ ሀገረ ስብከት እንዲወስዱትም አዘዛቸው፡፡ ንጉሡና ሠራዊታቸው በእግዚአብሔር መሪነት መስቀሉን ይዘው ወሎ ሲደርሱም ጌታችን ወደ አምባሰል እያመለከተ "አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል፤ መስቀሌን በመስቀለኛ ተራራ ላይ አስቀምጥ" ይላቸው ነበር፤ ንጉሡ መስቀሉን ይዘው ወደ ቦታው ሲያመሩ መስቀለኛው
የግሸን ተራራን አገኙ፤ በዚያም ቤተ ክርስቲያን አሠርተው በ፲፬፻፵፮ (1446) ዓ.ም የጌታችንን መስቀል በክብር አስቀምጠውታል፡፡
ከዚህ በኋላ ንጉሡ "መካከሏ ገነት፤ ዳሯ እሳት ይኹን! የበረረ ወፍ፣ የሠገረ ቆቅ አይታደንባት! በድንገት ሰው የገደለ፣ ቋንጃ የቈረጠ ወንጀለኛ አይያዝባት!" ብለው ዐዋጅ ነግረዋል፡፡ የእመቤታችን ጽላትም አብሮ በግሸን ደብረ ከርቤ እንዲቀመጥ አድርገዋል፡፡ ስለዚህም መስከረም ፳፩ ቀን በየዓመቱ በቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ይከበራል፡፡ ኀጢአታቸውን ለካህን ተናዘው፣ ንስሐ ገብተው በዚህ ዕለት ወደ ግሸን ደብረ ከርቤ በመሔድ የሚጸልዩና የሚማጸኑ ምእመናን ኹሉ እስከ ሰባት ትውልድ ድረስ የምሕረት ቃል ኪዳን እንደሚያገኙም ጤፉት በተባለችው መጽሐፍ ተጠቅሷል፡፡ ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሊቃውንት በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
🖋🖋🖋🖋🖋🖋🖋🖋🖋🖋🖋
ምንጭ፦ ከማኅበረ ቅዱሳን ጽረ ገጽ የተወሰደ። | 180 |
| 3 | ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
ብዙኃን_ማርያም፦
በቤተ ክርስቲያናችን ከሚዘከሩ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ክብረ በዓላት መካከል #መስከረም_፳፩ ቀን የሚውለው በዓል 🌼🌼"ብዙኃን ማርያም"🌼🌼 በመባል ይታወቃል፡፡ በዓሉ በሁለት ዐበይት ምክንያቶች ይከበራል፤ የመጀመሪያው ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ ውሳኔ ለማዘጋጀት ለጉባኤ ኒቅያ ከሩቅም ከቅርብም የተሰባበሰቡት ቀን፤ ሁለተኛው ደግሞ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ዕፀ መስቀል በግሸን ደብረ ከርቤ የተቀመጠበት ዕለት መኾኑ ነው፡፡ ሁለቱንም ታሪኮች ከዚህ ቀጥለን እንመለከታቸዋለን፤ | 150 |
| 4 | "በምድር ላይ የሰው ሕይወት ብርቱ ሰልፍ አይደለምን?
አገልጋይ ጥላ እንደሚመኝ፥እንዲሁ ዕጣዬ የከንቱ ወራት ሆነብኝ፥በተኛሁ ጊዜ። መቼ እነሣለሁ? እላለሁ።ሥጋዬ ትልና ጓል ለብሶአል፤ዘመኔ ከሸማኔ መወርወርያ ይልቅ ይቸኵላል፥ ሕይወቴ እስትንፋስ እንደ ሆነ አስብ፤የሚያየኝ ሰው ዓይን ከእንግዲህ ወዲህ አያየኝም፤ ደመና ተበትኖ እንደሚጠፋ፥ ወደ ቤቱ ዳግመኛ አይመለስም፥ስለዚህም አፌን አልከለክልም፤ ጠባቂ ታስነሣብኝ ዘንድ፥ እኔም። አልጋዬ ያጽናናኛል፥ አንተ በሕልም ታስፈራራኛለህ፥ነፍሴም ከአጥንቴ ይልቅ ሕይወቴን ናቅኋት፤ ለዘላለም ልኖር አልወድድም።ሰው ምንድር ነው ታከብረው ዘንድ፥ማለዳ ማለዳስ ትጐበኘው ዘንድ፥የማትተወኝ እስከ መቼ ነው?ሰውን የምትጠብቅ ሆይ፥ በድዬስ እንደ ሆነ ምን ላድርግልህ?ስለ ምን መተላለፌን ይቅር አትልም?"
መጽሐፈ ኢዮብ 7 | 139 |
| 5 | لا يوجد نص... | 271 |
| 6 | እንኳን ደስ አላችሁ🙏
ዘማሪት ሃና(ሰርክአዲስ) ሃ/መስቀል የቀዶ ጥገና ህክምናዋን ጨርሳ ወደ አሰላ ተመልሳለች። በገንዘባችሁ እና በጸሎታችሁ ላገዛችሁን በሙሉ መድኃኔዓለም ፍጻሜአችሁን ያሳምረው።
ስለ ሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን🙏
✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨
የቴሌግራም ቻናል:- T.me/Finote_Wongel | 246 |
| 7 | ፎቶ ;- መስቀል ደመራ አሰላ
16/1/2019 ዓ.ም | 304 |
| 8 | ፎቶ ;- መስቀል ደመራ አሰላ
16/1/2019 ዓ.ም | 335 |
| 9 | ፎቶ ;- መስቀል ደመራ አሰላ
16/1/2019 ዓ.ም | 340 |
| 10 | ፎቶ ;- መስቀል ደመራ አሰላ
16/1/2019 ዓ.ም | 319 |
| 11 | ፎቶ ;- መስቀል ደመራ አሰላ
16/1/2019 ዓ.ም | 323 |
| 12 | ፎቶ ;- መስቀል ደመራ አሰላ
16/1/2019 ዓ.ም | 278 |
| 13 | ፎቶ:- መስቀል ደመራ በአሰላ
16/1/2019 ዓ.ም | 259 |
| 14 | ፎቶ:- መስቀል ደመራ በአሰላ
16/1/2019 ዓ.ም | 264 |
| 15 | ፎቶ:- መስቀል በአሰላ
16/1/2019 ዓ.ም | 258 |
| 16 | Oduu Gamachisaa
Barnoota Afurraa Barbaadan
Hundaaf | 243 |
| 17 | አስደሳች ዜና
ለመንፈሳዊ ትምህረት ፈላጊዎች
በሙሉ! | 237 |
| 18 | የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ማርቶማ ማቴዎስ 3ተኛ ለሐዋርያዊ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ።
በሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ማርቶማ ማቴዎስ ፫ኛ የተመራው ልዑክ ለሐዋርያዊ ጉብኝት አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል
በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል ።
ቅዱስነታቸው በሐዋርያዊ ጉብኝታቸው በአለም ቅርስነት የተመዘገበውን የመስቀል ደመራ በዓልን በመስቀል አደባባይ ተገኝተው ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ጋር በጋራ እንደሚባርኩ እና መስከረም 17 በቦሌ መድኃኔዓለም ካቴድራል ተገኝተው ሥርአተ ቅዳሴውን እንደሚመሩ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።
📷 EOTC Broadcasting Service Agency | 340 |
| 19 | የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ።
የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ማርቶማ ማቴዎስ ፫ኛ (Baselios Marthoma Mathews III) ከመስከረም ፲፬-፲፰ ቀን ፳፻፲፱ ዓ.ም በኢትዮጵያ ሐዋርያዊ ጉብኝት ያደርጋሉ።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ማርቶማ ማቴዎስ ፫ኛ በ፳፻፲፱ ዓ.ም ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል በመስቀል አደባባይ ተገኝተው ቃለ ምዕዳን እና ቡራኬ የሚሰጡ ሲሆን በቦሌ ደብረ ሣሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል ሥርዓተ ቅዳሴ እንደሚያከናውኑ የተያዘው መርሐ ግብር ያስረዳል።
ዘገባው የEOTC TV ነው። | 343 |
| 20 | "ክርስቶስን መከተል ማለት መስቀሉን ተሸክሞ መጓዝ ነው፤ መስቀሉ ደግሞ የራስን ፈቃድ ለእግዚአብሔር ፈቃድ ማስገዛት ነው።"
አባ መቃርስ
✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨
የቴሌግራም ቻናል:- T.me/Finote_Wongel | 333 |
