ፍኖተ መጻሕፍት 📚FinoteBooks1623 ➮አድራሻ አዲስ አበባ ፒያሳ ገነተ ፅጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ማኅበረ በኩር ሰንበቴ ፊት ለፊት ለበለጠ መረጃ ፦በ0913083816 ይደውሉ።
الذهاب إلى القناة على Telegram
📚ፍኖተ መጻሕፍት @finoteBooks1623 ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን። [ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?] ይደውሉልን!📞፦0913083816 t.me/FinoteBooks1623
إظهار المزيد3 303
المشتركون
-224 ساعات
-107 أيام
-3830 أيام
أرشيف المشاركات
"መናፍቃንን እንደ መዶሻ የቀጠቀጣቸው ፣ እንደ ሰም ያቀለጣቸው ፣ እንደ እሳት ያቃጠላቸው ፣ እንደ ገለባ ያበጠራቸው።" መጽሐፍ በድጋሚ ለ17 ተኛ ጊዜ ታተመ።
"መድሎተ ጽድቅ ቅጽ ፩" ይህን መጽሐፍ በግዮን መጻሕፍት መደብር ዘወትር በልዩ ቅናሽ ታገኙታላችሁ።
ለበለጠ መረጃ
0912198891
0913083816
"መናፍቃንን እንደ መዶሻ የቀጠቀጣቸው ፣ እንደ ሰም ያቀለጣቸው ፣ እንደ እሳት ያቃጠላቸው ፣ እንደ ገለባ ያበጠራቸው።" መጽሐፍ በድጋሚ ለ17 ተኛ ጊዜ ታተመ።
"መድሎተ ጽድቅ ቅጽ ፩" ይህን መጽሐፍ በግዮን መጻሕፍት መደብር ዘወትር በልዩ ቅናሽ ታገኙታላችሁ።
ለበለጠ መረጃ
0912198881
0913083816
"መናፍቃንን እንደ መዶሻ የቀጠቀጣቸው ፣ እንደ ሰም ያቀለጣቸው ፣ እንደ እሳት ያቃጠላቸው ፣ እንደ ገለባ ያበጠራቸው።" መጽሐፍ በድጋሚ ለ17 ተኛ ጊዜ ታተመ።
"መድሎተ ጽድቅ ቅጽ ፩" ይህን መጽሐፍ በግዮን መጻሕፍት መደብር ዘወትር በልዩ ቅናሽ ታገኙታላችሁ።
ለበለጠ መረጃ
0912198881
0913083816
ቃና ዘገሊላ መጽሐፍ ለ11ኛ ጊዜ ታተመ።
"የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ሁለትን የመጀመሪያ አንቀጽ መነሻ ያደረገችውና በሰርግ ቤቱ ስም ቃና ዘገሊላ በማለት የተሰየመ ይህ መጽሐፍ፥ እንደ ሰርግ ቤቱ ስድስት ጋኖች በስድስት ምዕራፎች የተከፈለ ነው። ሁለት ወይም ሦስት እንስራ ይይዝ እንደነበሩት እንደ ቃና ጋኖችም እነዚህ ምዕራፎች እያንዳንዳቸው ሦስት ወይም አራት የንዑስ ርዕስ እንስራን የያዙ ናቸው፡፡ ...
"ይህ መጽሐፍ በስድስቱ ጋኖች /ምዕራፎች/ ውስጥ በቤተ ክርስቲያናችን ሊቃውንት ትርጓሜ መነሻነት በሰርግ ቤቱ ውስጥ ጥቂት እንድንቆይ ለማድረግ ይተጋል፡፡ .….
"እንኪያስ እኛም በኄኖክ መሪነት በቃና ዘገሊላ ሰርግ ቤት ውስጥ እንድንመላለስ፣ ከጌታችንና ከሐዋርያቱ ጋር ወደ ሰርግ ቤቱ እንድንገባ፣ ወደ ጓዳ ዘልቀን የወይኑን ማለቅ አስበን እንድንጨነቅ፣ እመቤታችን ስታማልድ ልጇም ሲማለድ እንድናይ፣ ከአገልጋዮቹ ጋር ውኃ ልንቀዳ ወንዝ እንድንወርድ፣ አብረን ውኃውን እስከአፉ ሞልተን ጌታችን የሚያደርገውን እንድንመለከት፣ ከታዳሚዎች ጋር ወይን የሆነውን ውኃ ቀምሰን እንድናደንቅ፣ መልካሙ የወይን ጠጅ ምነው እስካሁን ቆየ? ብለን ከአሳዳሪው ጋር አብረን እንድንቆጭ፣ ከዚያም ከሐዋርያቱ ጋር በስሙ አምነን ከሰርግ ቤቱ እንድንወጣ፣ ከምድራዊው ሰርግ ቤት ወጥተንም ወደ የቤታችን ሳንገባ ወደ ሌላ ሰማያዊ ሰርግ እንድንታደም ይህን ግሩም መጽሐፍ እናንብብ፡፡...
____
በግዮን መጻሕፍት መደብር ነባር እና አዳዲስ መጽሐፎቶችን ዘወትር በልዩ ቅናሽ ታገኛላችሁ።
ለበለጠ መረጃ በ0912198891/0913083816 ይደውሉ።
Repost from ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
ወዳጄ ሆይ
የትዕቢት መርዝ ተጠራቅሞ አብጦብሃልን? እንኪያስ ወደ #ቅዱስ_ሥጋዉና_ክቡር_ደሙ ቅረብ፤ ስለ ወዳጆቹ ሲል አርአያ ገብርን የነሣ ትሑቱ ጌታም ትሕትናን ያስተምርሃል፡፡
የስግብግብነት ትኩሳት አስቸግሮሃልን? ወደ #ቅዱስ_ሥጋዉና_ክቡር_ደሙ ቅረብ፤ ደግነትንም ትማራለህ፡፡
የምቀኝነት ብርድ አስቸግሮሃልን? እንኪያስ ወደ #ሰማያዊው_መዓድ ቅረብ፤ ምህረት ማድረግንም ገንዘብ ታደርጋለህ፡፡
ትዕግሥትን የማጣት እከክ ይዞሃልን? እንኪያስ ወደ #ቅዱስ_ሥጋዉና_ክቡር_ደሙ ቅረብ፤ ራስን መግዛትንም ገንዘብ ታደርጋለህ፡፡ በመንፈሳዊ ሕይወትህ ልል ዘሊል ብትሆን ይህን #መንፈሳዊ_መዓድ ተመገብና ብርቱ ትሆናለህ፡፡
ቆሽሸሃልን? እንኪያስ ወደዚሁ መብልና መጠጥ ቅረብ ብዬ እመክርሃለሁ፤ ንጽሕናንም ገንዘብ ታደርጋለህ፡፡”
#ቅዱስ_ቄርሎስ_ዘእስክንድርያ
የትቤ ተዋሕዶ ይዘቶች
ጸሐፊ፦ መ/ር መዝገበ ቃል ገብረ ሕይወት
የገጽ ብዛት፦ 200
ትቤ ተዋሕዶ ፲፮ የሚያህሉ የተዋሕዶ ዓይነቶችን እንደ ዐቢይ ጉዳይ በመያዝ በሌሎች ንኡሳን አርእስቶችና ዝርዝር ይዘቶች ተዋቅሮ የቀረበ መጽሐፍ ነው፡፡ ዐቢይ ይዘቱና የአሳቡ ማእከል ስለ ተዋሕዶ ሆኖ መዘርዝር ነጥቦችን ሳናካትት ዐበይት ይዘቶቹ የሚከተሉት የተዋሕዶ ዓይነቶች ናቸው፦
፩. የህልውና ተዋሕዶ (ያለ አካላት መጠፋፋት የሦስቱ አካላት የአንዱ በአንዱ መኖር)
፪. የፈቃድ ተዋሕዶ (ሦስቱ አካላት በአንድ ልብ አስበው የሚፈቅዱት አንድ ፈቃድ)
፫. የፍቅር ተዋሕዶ (አንዱ አካል አንዱን አካል የሚወድበት ፍቅረ ባሕረይ፣ ፍቅረ ተዋሕዶ፣ ፍቅረ ህልውና)
፬. የሕይወት ተዋሕዶ (የመላእክት በመንፈስ ቅዱስ ሕይወትነት መኖር)
፭. የዐራቱ ባሕርያት ተዋሕዶ (በፍጥረት አካል ውስጥና በየሚኖሩበት ዓለም ጸንቶና ተስማምቶ መኖር)
፮. የሰው ተዋሕዶ ፩ኛ የሥጋ አካል የሆኑት የ፬ቱ ባሕርያት ተዋሕዶ ፪ኛ የነፍስና የሥጋ ተዋሕዶ ፫ኛ ሥጋዊ ተዋሕዶ (ከልደት እስከ ሞት ከፍጥረት ጋር ያለን መስተጋብር) ፬ኛ የመንፈሳዊ ሕይወት የጸጋ ተዋሕዶ
፯. ፍቅረ እግዚአብሔር የኅድረት ተዋሕዶ
፰. ፍቅረ ቢጽ የፍቅር ተዋሕዶ
፱. የጋብቻ ተዋሕዶ (የሴትና የወንድ)
፲. መንፈሰ ረድኤት ተዋሕዶ (የነቢያት፣ የኦሪት ጻድቃን)
፲፩. የቃልና የትስብእት ተዋሕዶ (ነገረ ሥጋዌ)
፲፪. የጸጋ ተዋሕዶ (በመዓርጋተ ቅድስና የሚገኝ)
እኒህ ከላይ ከ፩ እስከ ፲፪ የዘረዘርናቸውና በሰው ተዋሕዶ እስከ ነጥብ ፬ የዘረዘርናቸውን በድምሩ ፲፮ የተዋሕዶ ዓይነቶችን በጥልቀት ይተነትናል፡፡ ጠጠር ያለ ስለሆነ ደጋግመን ማንበብ መልካም ነው፡፡
በግዮን መጻሕፍት መደብር ነባር እና አዳዲስ መጽሐፎችን ያገኛሉ።
#ዜና-ድጋሚ-ኅትመት
ዘመናችን ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን እጅጉን ፈተና ላይ የወደቀበት, የቤተ ክርስቲያን ሥርዐቷ ባለቤት ያጣበት ጊዜ መሆኑን መናገር ለቀባሪ የማርዳት ያህል ነው፡፡ ነገሩ ሲከፋ ደግሞ የቤተ ጉባኤና የቤተ ክርስቲያንን የሥርዐት መጻሕፍት ጠቅሶ ማስተማር የሚያሳፍር : የሚመስልበት ደረጃ ላይ ደርስናል። "ጸሐፊ" እና "ሰባኪ" የሚል ስም ተሸክመው ፍትሐ ነገሥትን የመሰሉ የሥርዐት መጻሕፍትን ለመጥቀስ እንኳ ፍላጎት የሌላቸው "አገልጋዮች" እጅግ ብዙ ናቸው፡፡ ይህ ደግሞ ምእመናንን (በተለይም በከተሞችና በውጭ ሀገራት የሚኖሩትን) ለእግዚአብሔር ሥርዐት ግዴለሽ እንዲሆኑ አድርጓል። በውጤቱም ክርስትና ከተግባር ቅድስና ይልቅ ስብከትና ጽሑፍ ብቻ እንዲሆን አስገድዷል። ስለዚህም እንደዚህ ያሉ የሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት በእጅጉ ያስፈልጉናል። ይህ መጽሐፍ ኹሉንም የቤተ ክርስቲያኗን ሥርዐቶች ለማካተት ይዘቱ፤ መጠኑ ባይፈቅድም ወሳኝ የሚባሉትን ነጥቦች በጥያቄና መልስ እያሰናሰለ ይዟል፡፡ ትኩረቱን ደግሞ በተለይ የዘመናችን የሥርዐት ክፍተት የሚታይባቸው የቅዳሴ፤ የቤተ ክርስቲያን ዙሪያና መሰል ጉዳዮች ላይ አድርጓል። ጸሐፊው፦ መምህር አብርሃም ከልጅነታቸው ተምረው በዜማ፤ በቅኔና በመጻሕፍተ ትርጓሜ የበሰለ አእምሮ ከጥሩ ብዕር ጋር ያላቸው ናቸውና ለዚህ የመጀመሪያ የጽሑፍ ሥራቸው መርቀናቸዋል። ቀጥሎም መሰል መጻሕፍትን ከመንፈስ ቅዱስ እርዳታ የተነሣ ከትበው ያበረክቱልናል የሚል ተስፋ አለን፡፡
ዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ
በግዮን መጻሕፍት ዘወትር በልዩ ቅናሽ ታገኙታላችሁ።
አዲስ መጽሐፍ በገቢያ ላይ
ወደ ገላትያ ሰዎች
የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሐተታ
እኛ ዘንድ ከዘወትር ልዩ ቅናሽ ጋር ያገኙታል።
#ዜና-ድጋሚ-ኅትመት
አሐቲ ድንግል ለ3 ግዜ ታትሞ ወቷል
በግዮን መጻሕፍት መደብር ዘወትር በልዩ ቅናሽ ታገኙታላችሁ።
#ዜና-ድጋሚ-ኅትመት
አሐቲ ድንግል ለ3 ግዜ ታትሞ ወቷል በግዮን መጻሕፍት መደብር ዘወትር በልዩ ቅናሽ ታገኙታላችሁ።
#ዜና-ድጋሚ-ኅትመት
አሐቲ ድንግል ለ3 ግዜ ታትሞ ወቷል በግዮን መጻሕፍት መደብር ዘወትር በልዩ ቅናሽ ታገኙታላችሁ።
#ዜና-ድጋሚ-ኅትመት
አሐቲ ድንግል ለ3 ግዜ ታትሞ ወቷል
በግዮን መጻሕፍት መደብር ዘወትር በልዩ ቅናሽ ታገኙታላችሁ።
#ዜና_መጽሐፍ
"ከኖኅ ጥፋት ውኃ በስተጀርባ" የተሰኘው የዲ/ን ዶ/ር አብነት ተስፋ መጽሐፍ ታተመ።
መጽሐፉ፥ በሰባት ምዕራፍ እና በ480 ገጾች የቀረበ ሲሆን፥ በኦሪት ዘፍጥረት ምእራፍ 6-9 ላይ ባለው በአንድ ወቅት ዓለም በመላው በመቅሰፍት ጎርፍ ስለ ጠፋበት በኖኅ ዘመን ስለ ተፈጠረው ታሪክ የሚያትት ነው። ምንም እንኳን ታሪኩ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አራት ምዕራፎችን የሸፈነ ቢሆንም፥ በአስተውሎት ከተመለከትነው ግን እጅግ ሰፊ ሐሳቦችን ያረገዘ ነው። በተለይ ከዘመናዊ ትምህርት አንጻር ሊታዩ ፣ ሊመረመሩ ፣ ሊተረጎሙ የሚገባቸው ግሩማን ሐሳቦች አሉበት። ስለዚህም ለእነዚህ ሐሳቦች ሐተታ ለመስጠት መጽሐፉ ''ከኖኅ ጥፋት ውኃ በስተጀርባ'' የሥነ ምሕንድስና (Engineering) ፣ የህክምና ጥበብ ፣ የሥነ ምድር ሳይንስ (Geology) ፣ ሥነ ምድራዊ ፊዚክስ (Geophysics) ፣ የእንስሳት ሥነ ምደባ (Animal Taxonomy) , . . . . . በሮች ያንኳኳል። በተጨማሪ በነገረ አበው ውስጥ ዘልቆ የአባቶችን ድንቅ ትንታኔ ያስቃኛል። ለምግባር እና ለትሩፋት የሚሆኑ ድንቅ የምክር ቋጠሯቸውን ከየመጻፎቻቸው እየፈታ ያቋድሳል። በታሪኩ ውስጥ የተገለጡ ዐበይት ሃይማኖታዊ ጉዳዮችን (ነገረ ክርስቶስ ፣ ምሥጢረ ጥምቀት ፣ ነገረ መንፈስ ቅዱስ ፣ . . .) ይዳስሳል። ከሁሉም ዓይነት ሊቋደሱበት የሚገባ ቡፌ ሆኖ በ480 ገጽ እና በ650 ብር የሽፋን ዋጋ ተሰናድቶ ለአንባቢያን ቀርቦአል።
በግዮን መጻሕፍት መደብር ታገኙታላችሁ።
#ዜና_መጽሐፍ
"ከኖኅ ጥፋት ውኃ በስተጀርባ" የተሰኘው የዲ/ን ዶ/ር አብነት ተስፋ መጽሐፍ ታተመ።
መጽሐፉ፥ በሰባት ምዕራፍ እና በ480 ገጾች የቀረበ ሲሆን፥ በኦሪት ዘፍጥረት ምእራፍ 6-9 ላይ ባለው በአንድ ወቅት ዓለም በመላው በመቅሰፍት ጎርፍ ስለ ጠፋበት በኖኅ ዘመን ስለ ተፈጠረው ታሪክ የሚያትት ነው። ምንም እንኳን ታሪኩ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አራት ምዕራፎችን የሸፈነ ቢሆንም፥ በአስተውሎት ከተመለከትነው ግን እጅግ ሰፊ ሐሳቦችን ያረገዘ ነው። በተለይ ከዘመናዊ ትምህርት አንጻር ሊታዩ ፣ ሊመረመሩ ፣ ሊተረጎሙ የሚገባቸው ግሩማን ሐሳቦች አሉበት። ስለዚህም ለእነዚህ ሐሳቦች ሐተታ ለመስጠት መጽሐፉ ''ከኖኅ ጥፋት ውኃ በስተጀርባ'' የሥነ ምሕንድስና (Engineering) ፣ የህክምና ጥበብ ፣ የሥነ ምድር ሳይንስ (Geology) ፣ ሥነ ምድራዊ ፊዚክስ (Geophysics) ፣ የእንስሳት ሥነ ምደባ (Animal Taxonomy) , . . . . . በሮች ያንኳኳል። በተጨማሪ በነገረ አበው ውስጥ ዘልቆ የአባቶችን ድንቅ ትንታኔ ያስቃኛል። ለምግባር እና ለትሩፋት የሚሆኑ ድንቅ የምክር ቋጠሯቸውን ከየመጻፎቻቸው እየፈታ ያቋድሳል። በታሪኩ ውስጥ የተገለጡ ዐበይት ሃይማኖታዊ ጉዳዮችን (ነገረ ክርስቶስ ፣ ምሥጢረ ጥምቀት ፣ ነገረ መንፈስ ቅዱስ ፣ . . .) ይዳስሳል። ከሁሉም ዓይነት ሊቋደሱበት የሚገባ ቡፌ ሆኖ በ480 ገጽ እና በ650 ብር የሽፋን ዋጋ ተሰናድቶ ለአንባቢያን ቀርቦአል።
በግዮን መጻሕፍት መደብር ታገኙታላችሁ
Repost from ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
ኅዳር ጽዮን
"ጽዮን" ማለት "ጸወን አምባ፣ መጠጊያ" ማለት ነው:: ጽዮን የሚለው ስም በቁሙ ለቅዱስ ዳዊት ተራራና ለኪዳኑ ጽላት ሲያገለግል በትንቢታዊ ምሥጢሩ ግን ለድንግል ማርያም፣ ለቤተ ክርስቲያንና ለዘለዓለማዊት ርስት ያገለግላል፡፡
ኅዳር ፳፩ ቀን በታቦተ ጽዮን የተፈጸሙ ታላላቅ ተአምራት የሚታሰቡበት ቀን ነው፡፡ በዚህ ቀን ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የታቦተ ጽዮንን ተአምራት እግዚአብሔር ቃል ቅድስት ድንግል ማርያምን ታቦቱ አድርጎ ከፈጸማቸው ታላላቅ የድኅነት ሥራዎች ጋር በማነጻጸር እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በነገረ ድኅነት ውስጥ ያላትን ድርሻ በስፋት ታስተምራለች፡፡
ነቢዩ ሙሴ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ጸልዮና ጹሞ ዐሥርቱ ቃላት የተጻፈበትን ጽላት ከእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑን ታቦት ‹ታቦተ ጽዮንን› እንደተቀበለ መጽሐፍ ቅዱስ ይገልጻል፡፡
ታቦተ ጽዮን ከማይነቅዝ እንጨት የተቀረጸችበት ምክንያት የእመቤታችን ድንግል ማርያምን ንጽሕና ለማመልከት ነው፡፡ በውስጥም በውጪም በጥሩ ወርቅ የተለበጠች መሆኗ ደግሞ የእመቤታችን ድንግል ማርያም ቅድስናዋንና በሁለት ወገን ድንግል የመሆኗ ምሳሌ ነው፡፡
ንጉሥ ዳዊት የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ከአቢዳራ ቤት ወደ ጽዮን ከተማ ባስመጣበት ወቅት በታቦቷ ፊት በሙሉ ኃይሉ በደስታ እየዘለለ ለእግዚአብሔር በዝማሬ ምስጋና አቅርቧል፡፡ ‹‹ለንጉሥ ዳዊትም “እግዚአብሔር የአቢዳራ ቤት የነበረውን ሁሉ ስለ እግዚአብሔር ታቦት ባረከ” ብለው ነገሩት፡፡
ዳዊትም ሄዶ የእግዚአብሔርን ታቦት ከአቢዳራ ቤት ወደ ራሱ ከተማ በደስታ አመጣት፡፡ ከእርሱም ጋር የእግዚአብሔርን ታቦት የተሸከሙ ሰባት መሰንቆ የሚመቱ መዘምራን ነበሩ፤ በሬዎችንና በጎችን ይሠዉ ነበር፡፡ ዳዊትም በእግዚአብሔር ፊት በገና ይደረድር ነበር›› እንዲል፤ ነቢዩ ዳዊት በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት የተቀኘው ለሰው ልጆች ሁሉ የመዳናችን ምክንያት የሆነችውን ቅድስት ድንግል ማርያምንና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሲያመስገን ነው፡፡ (፪ሳሙ.፮፥፲፪-፲፬)
ታቦተ ጽዮን እስራኤል የዮርዳኖስን ባሕር ለመሻገር በተቸገሩ ጊዜ ነቢዩ ኢያሱ እግዚአብሔር አምላክ በነገረው መሠረት ካህናቱ የቃል ኪዳኑን ታቦት ይዘው በሕዝቡ ፊት ወደ ዮርዳኖስ እንዲሄዱ ነገራቸው፤ እነርሱም እንደታዘዙት አደረጉ፤ ታቦቱን የተሸከሙት የካህናቱ እግሮች በውኃው ዳር ሲጠልቁ ከላይ የሚወርደው ውኃ ቆመ፤ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት የተሸከሙ ካህናት በዮርዳኖስ መካከል በደረቅ መሬት ጸንተው ቆመው ነበር፤ ሕዝቡም ሁሉ ዮርዳኖስን ፈጽመው እስኪሻገሩ ድረስ እስራኤል ሁሉ በደረቅ መሬት ተሻገሩ፡፡ (ኢያ. ፫፥፩-፲፯)
እስራኤላውያን በመካከላቸው የቃል ኪዳኑ ታቦት በያዙ ቁጥር በጦርነታቸው ሁል ጊዜ ያሸንፉ ነበሩ፡፡ ነገር ግን ልዑል እግዚአብሔር ሕዝበ እስራኤል ስለበደሉት እንዲሁም የኤሊ ልጆች አፍኒንና ፊንሐስ በደላቸውና ክፋታቸው ስለበዛ ታቦተ ጽዮን ተማርካ ወደ ፍልስጥኤም ሄደች፡፡ በዚያ በአሕዛብ ምድርም ልዩ ልዩ ተአምራትን እያደረገች ፍልስጥኤማውያንን ስለአስጨነቀቻቸው የፍልስጥኤማውያን አለቆች የቃልኪዳኑን ታቦት ልዩ ልዩ ገጸ በረከቶችን አስይዘው ወደመጣችበት በሠረገላ አድርገው በክብር ሸኝተዋታል፡፡ (፩ኛ.ሳሙ. ፭፥፩-፲፭)
ሀገራችን ኢትዮጵያም በንግሥተ ሳባ አማካኝነት ለታቦተ ጽዮን መቀመጫ እንድትሆን የእግዚአብሔር ፈቃዱ ሆኗል፡፡ ይህም እንዲህ ነበር፤ ንግሥተ ሳባ የንጉሥ ሰሎሞንን ጥበብ ለማድነቅ ምድረ እስራኤል ድረስ መጓዟን ተከትሎ ከንጉሡ ቀዳማዊ ምኒልክን ፀነሰች፡፡
ቀዳማዊ ምኒልክ ከአደገ በኋላ አባቱን ሊጠይቅ ሂዶ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለስ አብረውት አንድ ሺህ ሁለት መቶ እስራኤላውያን የበኩር ልጆች፣ ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት በአዛርያስ የሚመሩ ሌዋውያን ካህናትም አብረውት ለጉዞ ተነሡ፡፡ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍትንና ሌሎች በርካታ ቁሳቁሶችን ይዘውም ነበር።
ነገር ግን ታቦተ ጽዮንን አዛርያስና ካህናቱ ተማክረው ቀዳማዊ ምኒልክ እንኳን ሳይሰማ በምሥጢር ይዘዋት ሊመጡ ተስማሙ፡፡ ዕቅዳቸውን ለማሳካት በታቦተ ጽዮን አምሳያ ሌላ ታቦት አዘጋጅተው ለመሄድ በሚነሡበት ዕለት ሌሊትም ወደ ቤተ መቅደስ ይዘውት ሄዱ፡፡
ከቤተ መቅደስ ሲደርሱም የእግዚአብሔር ፈቃድ ነበርና የቤተ መቅደሱ በር ተከፍቶ እና ውስጡም በብርሃን ተሞልቶ ታቦተ ጽዮንም ከመንበሯ በመነሣት ከፍ ብላ አገኟት። በዚህም የአምላክን ፈቃድ ተረድተውና እግዚአብሔርን እያመሰገኑ በፍጥነት ይዘዋት ወጡ፡፡ በአምሳያዋ የሠሩትንም ቅርፅ በመንበሩ ላይ አስቀምጠው ሄዱ።
የንጉሡ ወታደሮች በፍጥነት ቢጓዙም ቀዳማዊ ምኒልክ እና አዛርያስ ታቦተ ጽዮንን ይዘው ሲጓዙ እጅግ ፍጣን ስለበር ሊደርሱባቸው አልቻሉም። መጽሐፈ ክብረ ነገሥት ይህንን ሲጠቅስ ‹‹ከመሬት አንድ ክንድ ያህል ከፍ ብለው ይሄዱ ነበር›› በማለት ይገልጸዋል። ባሕረ ኤርትራን ከተሻገሩና ግብፅ ከደረሱ በኋላ ዕረፍትን ባደረጉ ጊዜ አዛርያስ ለቀዳማዊ ምኒልክ ታቦተ ጽዮንን ይዘዋት እንደመጡ ነገረው፡፡
አያይዞም ‹‹አንተም ብትሻ ታቦቷንም ወደ ሀገሯ ልመልሳት ብትል አትችልም፤ አባትህ ሰሎሞንም ሊወስዳት ቢመጣ አይሆንለትም›› አለው። ከቦታ ቦታ ይዣት እንቀሳቀሳለው ቢልም ያለ ፈቃዷ ምንም እንደማያደርግና ሁሉ ነገር በአምላክ መልካም ፈቃድ እንደሚፈጸም ነገረው። ቀዳማዊው ምኒልክም ይህን ሲሰማ ተደሰተ፤ ሕዝቡና ሠራዊቱ በሙሉ ልዑል እግዚአብሔርን አመሰገኑ፤ ከግብፅ ምድር ወጥተው እስከ ኢትዮጵያ በታላቅ እልልታና ሆታ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ መጡ።
ኅዳር ፳፩ ቀን አክሱም በደረሱ ጊዜም እናቱ ንግሥተ ሳባ ተቀበለችው፤ ደስታና እልልታውን ተመልክታ ያገኙት ነገር እንዳለ ብትጠይቀው ታቦተ ጽዮንን እንዳመጧት ነገራት፡፡ የእርሷም ደስታ እጥፍ ድርብ ሆነ። ታቦቷንም በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን አስቀመጡአት፡፡
ከዚያም ዘመን ጀምሮ በየዓመቱ ኅዳር ፳፩ ቀን ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩም በታቦተ ጽዮን የተፈጸሙ ታላላቅ ተአምራትን በማሰብ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ታከብራለች፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
ምንጭ፤
ክብረ ነገሥት ተርጓሚ ሥርግው ገላው (1994 ዓ.ም)
መዝገበ ታሪክ ቊጥር 1 (መምህር ኅሩይ ኤርምያስ)
#ዜና_ድጋሚ_ኅትመት
ዘአወፈየኒ አወፈይኩከ-፦
የሰጠኝን ሰጠሁህ"
ውድ ኦርቶዶክሳውያን በብዙ ፈተና ውስጥ ሁኘ ባለችኝ ትንሽ ጊዜ በትንሿ መረዳቴ ይሄንንን መጽሐፍ፦"ከመዝ ነአምን" በሚል ርዕስ
ለማበርከት ሞክሬያለሁ።
ኦርቶዶክሳዊነትን ለማስረዳት በተቻለኝ መጠን የደከምሁበት ቢሆንም ከአጠገቤ መጻሕፍትን ባለማግኘቴ ግን እንደ ሚገባ ጽፌዋለሁ ብየ አላስብም።
ስለሆነም ርቱዓን ኦርቶዶክሳውያን የጠመመውን አቃንታችሁ፣የጎደለውን ሞልታችሁ፣የገደፍሁትን አርትታችሁ እንድታነቡት እማፀናለሁ።ግድፈተ ቃለ ካለም ግድፈቱ የእኔ ብቻ ነው እንጂ የቤተ ክርስቲያኗ አይደለም።
ከመጀመሪያው ጀምሮ አንብበን ከጨረስን በኋላ ቆም ብለን ወደ ኋላ ብናስበው ለአባቶች
ትምህርት መግቢያ የሚሆነንን የኦርቶዶክሳዊነት መነሻ ትምህርት እናገኝበታለን ብየ ተስፋ አደርጋለሁ።
የእኔ ደስታየ አንብበን ወደ ላይ ወደ አባቶቻችን ሐዋርያት በኅሊና ደርሰን ለልቡናችን
ድጋፍ የሚሆን ኦርቶዶክሳዊ መረዳትን ካገኘንበት ነው።
ስለሁሉም ነገር አሁን በመንፈሳዊ ተጋድሎ ላለው ትውልድ እና ከእኔ በኋላ ለሚነሣው
ትውልድ ኦርቶዶክሳዊ ሐሳቤን በጽሑፍ እንዳስተላልፍ የረዳኝን እግዚአብሔርን
አመሰግነዋለሁ።
“ጸልዩ ለነ ከመ ይሩጽ ቃለ እግዚአብሔር” ፪ ተሰ ፫፥፩
መምህር ገብረ መድኅን እንየው
በግዮን መጻሕፍት መደብር የተለያዩ
መጻሕፍቶችን ዘወትር በልዩ ታገኛላችሁ
መጽሐፍ ቅዱስ፣ ድርሳናት ፣ ገድላት፣
መዝሙረ ዳዊት፣ መዝገበ ጸሎት፣
በአጠቃላይ የታሪክና መንፈሳዊ
ነባር ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍቶችን ያገኛሉ
አድራሻ ፦መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ማህበረ በኵር ሰንበቴ ፊት ለፊት
ለበለጠ መረጃ በ0913083816 ይደውሉ።
Repost from ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
ምጽዋት
* ምጽዋት በመጽሀፍ ቅዱስ ትምህርት
* ምጽዋት በአበው ትምህርት
++++++++~~++++++
ከጥምቀት በኋላ የሚሠሩ ኃጢአቶችን ማስወገጃና ማጠቢያ መንገድ ማግኘት መቻል ምን ያህል ታላቅ ነገር መሆኑን ልብ በል! ምጽዋት መስጠት ምን ያህል ታላቅ ዋጋ እንዳለው አስተውል፡፡ እርሱ ምጽዋት ስጡ ባይለን ኖሮ፣ 'ገንዘብ መስጠትና ከሚመጣው ክፉ ነገር በምጽዋት አማካይነት መዳን የሚቻል ቢሆን ኖሮ እንዴት ጥሩ ነበር' የሚሉ ስንት ሰዎች በኖሩ ነበር! ነገር ግን አሁን እግዚአብሔር ለእኛ ካለው ቸርነት የተነሣ በምጽዋት አማካይነት ከሚመጣው ክፉ ነገር መዳን የምንችልበትን ዕድል ስለ ሰጠንና ይህን የሚቻል ስላደረገልን እንደገና ብዙዎች ተመልሰው ግድ የለሾች ሆነው ይታያሉ፡፡ አይ፣ እኔ ምጽዋት እሰጣለሁ እኮ ትል ይሆናል፡፡ ይህ ምንድን ነው? ሆኖም ግን መቀነቷን ፈትታ ሁለት ሣንቲሞችን እንደ ሰጠችው ሴት ያህል አልሰጠህም፡፡ ኧረ የእርሷን ግማሽ ያህል፣ እርሷ ከሰጠችው ጥቂቱን ያህል እንኳ አልሰጠህም፡፡ ካለህ ገንዘብ ብዙውን ክፍል ጥቅም በሌለው ነገር ላይ ታባክነዋለህና፡፡ በመጠጥ፣ በመባልዕት ቅጥ ባጣ አባካኝነት እያዋልክ ራስሀን ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም እንደ አንተ እንዲያባክኑና ገንዘባቸውን በማይጠቅማቸውና ተገቢ ባልሆነ ነገር ላይ እንዲያጠፉት ፈተና ትሆንባቸዋለህና፡፡ በዚህም ቅጣትህ እጥፍ ድርብ ይሆንብሃል፤ የራስህ ጥፋት አንሶህ ሌሎችንም ወደ ጥፋት መርተሃቸዋልና፣ የኃጢአት ምክንያት ሆነሀባቸዋልና፡፡ (ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ፣ ትርጓሜ ወንጌለ ማቴዎስ፣ ክፍለ ትምህርት 67፣ ቁ. 5)
#መድሎተ_ጽድቅ
#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
የዚህ መጽሐፍ ጸሐፊ አቡነ አትናስዮስ እስክንድር ይህን መጽሐፋቸውን ወደ አማርኛ እንድተረጉመው ፣ ‹መንፈሳዊነት› የሚል ርእስ ያላቸው ብዙ መጻሕፍት በመኖራቸው የመጽሐፉን ርእስ በቀጥታ ተግባራዊ መንፈሳዊነት (Practical Sprituality) ብሎ በመተርጎም _ ፈንታ ተግባራዊ ክርስትና (Practical Christianity) ብዬ እንድተረጕመው በመፍቀድ፣ ፎቶአቸውንና የመጽሐፉን አዲስ ኅትም በመላክ ቀና ትብብር ስላደረጉልኝ አመሰግናቸዋለሁ፡፡ በዚህ የአማርኛ ትርጕም ላይ ለኢትዮጵያውያን ምእመናን ልጆቻቸው መልእክት እንዲጽፉ ስጠይቃቸውም‹‹እኔ ካህን ሆኜ ሳለ በኢትዮጵያ ላሉ እኅቶቼ እና ወንድሞቼ መጻፍን እንደ ድፍረት እቆጥረዋለሁ፡፡ በእኔ ፈቃድ የታተመ መሆኑ ከገለጽህ ይበቃል፡፡›› ብለዋል፡፡ ይህም ሌላ ተግባራዊ ክርስትና ስለሆነ በፈቃዳቸው ይህንን አሳብም አካትቼዋለሁ፡፡
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
በግዮን መጻሕፍት መደብር ታገኙታላችሁ።
“ኃጢአቷን የቀበረችው ማርያም” መጽሐፍ በድጋሚ ታተመ
-በመ/ር ሥሙር አላምረው የተዘጋጀው “ኃጢአቷን የቀበረችው ማርያም” የተሰኘ መጽሐፍ ጌታን ሽቶ ስለቀቡት ማርያም ኀጥእት ብዙ ኃጢአቷን ቀብራ ብዙ ጸጋ ስላገኘችውና ማርያም እኀተ አልዓዛር ልዩነት ያስረዳል፡፡ መምህሩ “ከዚኽ በኋላ ጌታችንን ሽቱ የቀቡት ሴቶች እንዴት ሥስት ናቸው ተባለ የጋራ የቤት ሥራ ይኾነናል እንጅ አንዲት ሴት ብቻ ቀባችው ብለን የጨለማ ገልማጭ አንኾንም” ይሉናል፡፡
የመጽሐፉ አላማዎች
1) በእኅተ አልአዛር ማርያም ስም ማርያም ኃጥእት ተሠውራ እንዳትቀር ማድረግ
2)ስለ ባለሽቱ ሴቶች የግብጽ ቤ/ንና ሌሎች ተቋማት ምን አይነት ትምህርት እንዳላቸው ማሳየት
3)የተለያዩ የሊቃውንት ትርጓሜ ስለ ኃጢአተኛዋ ማርያም ምን እንደሚሉ ማስረዳት
4) የማርያም ኀጥእትን ገድል መሠረት በማድረግ የንስሐ ለቅሶዋን፣ ያጋጠማትን ፈተና እንዲሁም ገድሉ ያሉበትን የስምና የታሪክ ቅደም ተከተል ዝንፈትን መጠቆም፡፡
5)መጽሐፈ ስንክሳር የካቲት 6 የእኅተ አልዓዛር መታሰቢያ እንዳልሆነና የማርያም ዘሀገረ ናይን መታሰቢያ እንደሆነ ማስረዳት
መጽሐፉን እኛ ዘንድ ያገኙታል።
متاح الآن! بحث تيليغرام 2025 — أهم رؤى العام 
