Assaye Derbie
الذهاب إلى القناة على Telegram
إظهار المزيد
📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام Assaye Derbie
تُعد قناة Assaye Derbie (@asayede) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 14 346 مشتركاً، محتلاً المرتبة 2 649 في فئة المدوّنات والمرتبة 2 354 في منطقة Ethiopia.
📊 مؤشرات الجمهور والحراك
منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 14 346 مشتركاً.
بحسب آخر البيانات بتاريخ 24 يونيو, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار -112، وفي آخر 24 ساعة بمقدار -7، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.
- حالة التحقق: غير موثّقة
- معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 39.43%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 12.21% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
- وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 5 656 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 1 752 مشاهدة.
- التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 33.
📝 الوصف وسياسة المحتوى
وصف القناة غير متوفر.
بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 25 يونيو, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة المدوّنات.
14 346
المشتركون
-724 ساعات
-387 أيام
-11230 أيام
أرشيف المشاركات
14 343
መድረክ ላይ በወጣ ቁጥር ለአማራ ያለውን ጥላቻ መደበቅ የሚሳነውና "የአማራ ሸኔ" የሚል ታርጋ ሲለጥፍ የተሰማው ሰውዬ ከህው*ሓት ጋር ተቧድኖ አማራ ክልልን የሚወርበት ቀን ሩቅ አይሆንም።
14 343
በገጠሩ አካባቢ የሚኖረው ማሕበረሰብ በችግሮቹ ዙሪያ መምከርና የመፍትሔ ሐሳቦችን መቀመር ሲፈልግ ከጠራራ ጸሐይ የሚታደግ ጠለስ ወይንም ጥላ (ታዛ) ያለው ስፍራ ፈልጎ እንዲሰበሰብ ሁሉ ጠለስ ቲዩብም የተለያዩ ሒሶችን እና መወድሶችን የያዙ፣ የአገራችንን ፖለቲካዊ፣ ኦኮኖሚያዊና ማሕበራዊ ጉዳዮችን በኪናዊ መንገድ የሚያዋዙ፣ በእውነታና በሐቅ ባላዎች ላይ የተመረኮዙ፣ እንዲሁም ሰናይ ክንውኖችን ሲያወድሱ፣ እኩይ ድርጊቶችን የሚያሔሱ ዝግጅቶች የሚቀርቡበት ፕሮግራም ነው፡፡ ስለሆነም ጠለስ ቲዩብን Subscribe በማድረግ ጠለሳችንን ያደምቁልን ዘንድ በአክብሮት እጠይቃለሁ፡፡
14 343
ቁንጣን በሚያስደስተው ሆድ ፈንታ የወገን ጥቃት የሚንገበግበው ልብ ይዘው የተፈጠሩ 'ጀግና ልጆቹ' ትግል በጀመሩ ማግስት ከጉያው እየታደኑ ወደ ወሕኒ እና ወደ መቃብር ሲወርዱ፣ አድፍጦ የሚመለከት ማሕበረሰብ፣ በመከራው ወቅት የሚያወርደው እንባና ደም ክንፍ ያለው መልዓክ እስኪያወርድለት ድረስ የሕልውና አደጋውን ጸጋው አድርጎ መቅበዝበዝ ግዴታው ነው።
አሳዬ ደርቤ
14 343
የአፋልጉኝ ማስታወቂያ
የብልጽግና አካሄድና ፖለቲካ ቀድሞ የገባው ይህ ሐቀኛ ፖለቲከኛ ከጨዋታ ሜዳው ላይ ከተሰወረ ወራቶች ተቆጠሩ።
እናም እገታውን የፈጸመው መንፈስ እስክንድርን ለቅቆ የጃንጥራርን ደብዛ እንዲያጠፋልን እንጠይቃለን።
14 343
በልተው የማይጠግቡ፣ ቀምተውና ዘርፈው የማይረኩ፣ ገድለውና አውድመው የማያበቁ፣ ጠይቀው የማያባሩ... አረመኔዎች ሥልጣን ከያዙ በኋላ ከኢትዮጵያ ሰማይ ስር እረፍት ማድረግ እርም ሆነ።
14 343
በመልካም ወጣት ሥም የድሃ ቤት ከማፍረስ አልፎ በሃይማኖት ግጭት የወጣቶችን ደም ለማፋሰስ ቆርጦ የተነሳ እኩይ ሰው!ለነገሩ እነ ሙዓዘ ጥበባትን ያፈራች ቤተክርስቲያን ከዚህ የተሻለ እጣ ሊኖራት አይችልም።
14 343
ከአንድ ወር በፊት ከመስከረም አበራ ጋር ቡና እየጠጣሁ "ሞት እና ስደት ለተፈረደበት ወገንሽ ጠበቃ ሆነሽ የምታደርጊው ሙግት እስራት አምጥቶ ከሕጻን ልጅሽ እንዳይነጥልሽ..." በማለት ስጋቴን ስገልጽላት መስኪ የሰጠችኝ መልስ ... 👇
"አድጎ መራመድ ሲጀምር፥ እናት አገር የማይኖረው፣ የዜግነት ክብር እና የነፃነት አየር የሚጠማው ሕፃን ልጅ ከመኝታ ቤቴ ውስጥ ታቅፌ ጡት እያጠባሁ የወደፊት እጣ-ፈንታውን እና ባርነቱን ከማሰላሰል ይልቅ ፥ ለወለደኝ ወገንም ሆነ ለወለድኩት ሕጻን እኩልነት እና ነጻነት የማደርገው ትግል ሥጋት የፈጠረባቸው ቡከኖች የሚበይኑትን እስራትና ቅጣት ተቀብዬ ያለ እናት እና ያለ ጡት ያድግ ዘንድ የፈረዱበትን ልጄን ማሰብ የተሻለ ምቾት ይፈጥርብኛል" የሚል ነበረ።
አከብርሻለሁ ውዷ እኅቴ!!
14 343
የታፋኙ ማስታወሻ😆
▬▬▬▬▬▬
ልፋቴ በሞት እስኪጠናቀቅ ድረስ ላለፉት ሃያ ቀናት የመድሃኒት ማዘዣ አንጠልጥዬ ሆስፒታል ለሆስፒታል ስንከራተት ነበር። በዚህም የተነሳ፥ ይሄ እንኩቶ ሥርዓት የሚፈጽመውን የሕፃን ጨዋታ የምቃወምበት በቂ ጊዜ አላገኘሁም ነበር።
እንዲያም ሆኖ ታዲያ ኦነግ መራሹ ሥርዓት "አሳዬ ደርቤ የአዲስ አበባ ተማሪዎችን አመጽ ሲያቀነባብር ነበር" በማለት ከእነ ስንታየሁ ቸኮል፣ መስከረም አበራ፣ መዓዛ መሐመድ፣ ዶክተር ቴዎድሮስና ዘሪሁን ገሰሰ ጋር የእስር ማዘዣ እንዳወጣብኝ ሰማሁ።
እናም መረጃው እውነት ሆኖ ይሄ እንኩቶ ፓርቲ ሙሥና እና የዜጎች ደም ባጨቀየው መዳፉ ለሁለተኛ ጊዜ ሳያፍነኝ በፊት ጀግኖቹን እያስበላ ቂጣውን ለሚያላምጠው ከንቱ ፍጥረት "የታሠሩ ልሳኖችህን ማስፈታት ቢሳንህ እንኳን እስር ቤት ሄደህ ጠይቃቸው" ማለት እሻለሁ።
በተረፈ በሕይወት እስካለሁ ድረስ ይሄንን አስነዋሪ ሥርዓት መታገሌን አጠናክሬ የምቀጥል መሆኔን እገልጻለሁ።
ዝንታለም አማራ!!
14 343
የእኅቴ ኀዘን ላይ ብሆንም፤ የኦሮሞ አመራሮች፣ ፖለቲከኞች እና አክቲቪስቶች በሚፈጽሙት አገር የማተራመስ መርሐ ግብር አማራዎችን እና የአዲስ አበባ ልጆችን ማሰር ልክ አይደለም እላለሁ።
የአዳነች አቤቤ ካቢኔ ከሕፃናት ጋር በሚያደርገው ግብግብ እነ መስከረም አበራን እና ናትናኤል ያለምዘውድን እያፈኑ ከእስር ቤት መጎድጎድ እጅግ አስነዋሪ ወንጀል ነው እላለሁ።
14 343
የሆነ ነገር በጻፍኩ ቁጥር "እባክህ እነዚህ አረመኔዎች እንዳይገድሉህ..." እያለች የምትጨቀጭቀኝን ታላቅ እኅቴን አፈር አለበስኳት።
ነፍስሽን ይማረው እኅታለም!!
14 343
የዘር ማጥፋት ቅስቀሳ ማድረግ የተፈቀደለት ውርንጭላ...!!
የሚገርመው ነገር ለሚዲያዎች እውቅና ለመስጠት አንድ ዓመት የሚፈጅበት የመገናኛ ብዙሐን ባለሥልጣን፤ ይህ ጥጃ ጥላቻውን ለሚያዝረበርብበት ሚዲያ እውቅና የሰጠው በአንድ ሳምንት ውስጥ መሆኑ ነው።
14 343
ከትናንት ወዲያ ማታ ገጀራ የያዙ ወጣቶችን እና ልዩ ሃይሎችን የጫነ 30 መኪና ወደ አንገር ጉትን መጠጋት ጀምሮ ነበር። የእናንተ ጩኸትና እሪታ ግን በዚህ የጥፋት ኃይል ፈንታ መከላከያን ማስገባት ችሏል።👏
14 343
ሕዝቡ ይሄን ሥርዓት ማሽቀንጠር አለበት" የሚል ትዕዛዝ ከማስተላለፍህ በፊት የብልጽግና አባል ተብለው ወርሐዊ ክፍያ ከሚከፍሉትና ፓርቲውን ከተሸከሙት 4 ሚሊዮን አማራዎች መሀከል አንዱ አለመሆንህን አረጋግጥ!
14 343
በንጹሐን እንባ የተለኮሰው የሳቅህ እድሜ ሲገመት ለአረመኔዎች አሳልፈህ ከሰጠኸው ሕዝብ የለቅሶ ዘመን አይረዝምም።
እናም...
በብዙዎች ሳግ የብቻህን ሳቅ እንደፈጠርክ ሁሉ፤ እንደ በረከት ስምዖን ለብቻህ የምታዝንበት ረዥም የትካዜ ወቅት ከፊትህ አለ።
በመሆኑም የእንባህ ዘመን ከመድረሱ በፊት የጎዳና ተዳዳሪውን ፓርቲ ማሕተም ለባለቤቱ አስረክበህ መሐረብ ግዛ።
متاح الآن! بحث تيليغرام 2025 — أهم رؤى العام 
