ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

NGCS PARENTS GRADE 9-12

الذهاب إلى القناة على Telegram
2 771
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
+230 أيام
أرشيف المشاركات
ጥቅምት 25/2019 ለልደታ ማርያም ልጃገረዶች ት/ቤት ወላጆች/አሳዳጊዎች በሙሉ ከ1ኛ - 12ኛ ክፍል ለሚማሩ ተማሪዎች የት/ቤቱ መታወቂያ ጥራቱን በጠበቀና ዘመናዊ በሆነ ሁኔታ እየተዘጋጀላቸው ይገኛል፡፡ ስለሆነም የአንድ ተማሪ የመታወቂያ ዋጋ 200 ብር ሁለት መቶ ብር በመሆኑ ወላጆች ለልጆቻችሁ እንድትልኩ እናሳስባለን፡፡ ት/ቤቱ

ጥቅምት 25/2019 ለ11ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪ ወላጆች በሙሉ በ2018ዓም ለተማሪዎች በተሰጠ የተጠናከረ ቱቶሪያል ሁሉም ተማሪዎች 100% በማምጣት ያለፉ መሆናቸውን መነሻ በማድረግ ፤በአዲስ አበባ ት/ቢሮ ውጤት ማላቅ ስትራቴጂ ውጤታማ ለማድረግ በ2019ዓም ለ11ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከወላጆች ጋር ስምምነት ባደረግነው መሰረት በዋና ዋና የትምህርት አይነቶች ማጠናከሪያ ከጀመርን እነሆ ሶስት ሳምንት አስቆጥረናል፡፡ በመሆኑም ክፍያ ለመምህራን ለመፈፀም ያመቸን ዘንድ የሩብ ዐመት ክፍያችሁን እስከ 30/2/2019ዓም ድረስ ገቢ እንድታደርጉ ስንል በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡ ት/ቤቱ

photo content

ቀን:- ረቡዕ ጥቅምት 24/2019 ዓ.ም በ 2018ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠቃለያ ፈተና ለወሰዳችሁ ተማሪዎች የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋናውን የውጤት ሰርቲፊኬታችሁን አትሞ ስለላከልን መጥታችሁ እንድትወስዱ ። ከዚህም በተጨማሪ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ቅሬታ መቀበያ የጊዜ ገደብን አስመልክቶ ለ ሁሉም 2018 ዓ.ም 12ኛ ክፍል አስፈታኝ ትምህርት ቤቶችና ተማሪዎች በሙሉ ያስተላለፈውን መመሪያ ከዚህ በታች አስቀምጠንላችኋል። ስለዚህ የስም፣የፎቶ፣ ፆታ ወዘተ ቅሬታ ያለባችሁ ተማሪዎች መመሪያው ባስቀመጠው አቅጣጫ እና ጊዜ ገደብ ማቅረብ እንዳለባችሁ እያሳሰብን በጊዜ ገደቡ ሳትመጡ በሌላ ጊዜ ዘግይታችሁ ለምታመጡት ማንኛውም ጥያቄ ትምህርት ቤቱ የማይቀበል መሆኑን እንድታውቁትና ለሚመጣው ችግር ሀላፊነቱ ሙሉ በሙሉ የናንተ መሆኑን አበክረን እንገልፃለን።

ጥቅምት 20/2019 ለልደታ ማርያም ልጃገረዶች ት/ቤት ወላጆች/አሳዳጊዎች በሙሉ ከ1ኛ - 12ኛ ክፍል ለሚማሩ ተማሪዎች የት/ቤቱ መታወቂያ ጥራቱን በጠበቀና ዘመናዊ በሆነ ሁኔታ እየተዘጋጀላቸው ይገኛል፡፡ ስለሆነም የአንድ ተማሪ የመታወቂያ ዋጋ ሁለት መቶ ብር በመሆኑ ወላጆች ለልጆቻችሁ እንድትልኩ እናሳስባለን፡፡ ት/ቤቱ

ጥቅምት 20/2019 ለልደታ ማርያም ልጃገረዶች ት/ቤት ወላጆች/አሳዳጊዎች በሙሉ ከ1ኛ - 12ኛ ክፍል ለሚማሩ ተማሪዎች የት/ቤቱ መታወቂያ ጥራቱን በጠበቀና ዘመናዊ በሆነ ሁኔታ እየተዘጋጀላቸው ይገኛል፡፡ ስለሆነም የአንድ ተማሪ የመታወቂያ ዋጋ ሁለት መቶ /200 ብር በመሆኑ ወላጆች ለልጆቻችሁ እንድትልኩ እናሳስባለን፡፡ ት/ቤቱ

19/2/2019 ለ2019 ወደ ልደታ ማርያም ልጃገረዶች ት/ቤት የገባችሁ የ4ኛ ፣ 5ኛ እና 7ኛ አዲስ ተማሪዎች ቅዳሜ ለስብሰባ ስትመጡ መሙላት ያለባችሁ ፎርም ስላለ ከናንተ የሚጠበቀው 1. የአባት ፎቶ ጉርድ 2. የእናት ፎቶ ጉርድ 3. የተማሪዋን ፎቶ ጉርድ 4. ፋይዳ መታወቂያ የተማሪዋ በተጨማሪም ያላሟላችሁትን ዶኪሜንት ካለ ይዛችሁ እንድትመጡ ስንል በትህትና እናሳውቃለን ፡፡

19/2/2019 ለ2019 ወደ ልደታ ማርያም ልጃገረዶች ት/ቤት የገባችሁ የ4ኛ ፣ 5ኛ እና 7ኛ አዲስ ተማሪዎች ቅዳሜ ለስብሰባ ስትመጡ መሙላት ያለባችሁ ፎርም ስላለ ከናንተ የሚጠበቀው  የአባት ፎቶ ጉርድ  የእናት ፎቶ ጉርድ  የተማሪዋን ፎቶ ጉርድ  ፋይዳ መታወቂያ የተማሪዋ በተጨማሪም ያላሟላችሁትን ዶኪሜንት ካለ ይዛችሁ እንድትመጡ ስንል በትህትና እናሳውቃለን ፡፡

Nativity Girls' Catholic School
Nativity Girls' Catholic School

18/2/2019 ውድ ወላጆችና አሳዳጊዎች፣ ከ ልደታ ማርያም ካቶሊክ ትምህርት ቤት ሰላምታ ይድረሳችሁ! የ4ኛ፣ 5ኛ እና 7ኛ ክፍል ተማሪዎች ወላጆችና አሳዳጊዎች በልዩ የወላጅነት ሴሚናር ላይ እንድትሳተፉ በደስታ እንጋብዛችኋለን። የዚህ ሴሚናር ዓላማ በወላጆችና በልጆቻቸው መካከል ያለውን ግንኙነት ማጠናከር ነው። ሴሚናሩ ልጆቻችንን በተሻለ ሁኔታ መረዳት፣ ባህሪያቸውን በአግባቡ መምራት፣ ስሜታዊና ትምህርታዊ እድገታቸውን መደገፍ እንዲሁም ኃላፊነት የሚሰማቸውና በራሳቸው የሚተማመኑ ግለሰቦች ሆነው እንዲያድጉ ስለሚያስችሉ ጉዳዮች ያተኩራል። በተጨማሪም ውጤታማ የወላጅነት አስተዳደግ ዘዴዎችን እና የልጆቻችንን ስኬት ለመደገፍ ከትምህርት ቤቱ ጋር በትብብር መሥራት ስለሚቻልባቸው መንገዶች ጠቃሚ ግንዛቤ ይሰጣል። • ቀን፦ 21/2/2019 • ሰዓት፦ ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ • ተሳታፊዎች፦ የ4ኛ፣ 5ኛ እና 7ኛ ክፍል ተማሪዎች ወላጆችና አሳዳጊዎች • ቦታ፦ ልደታ ማርያም ካቶሊክ ትምህርት ቤት የስብሰባ አዳራሽ ለሁልጊዜው ትብብራችሁና ድጋፋችሁ ከልብ እናመሰግናለን። በሴሚናሩ ላይ በመገኘት ለልጆቻችን የተሻለ እድገትና ስኬት በጋራ እንድንሠራ እንጋብዛችኋለን። ከአክብሮት ጋር፣ የትምህርት ቤቱ ዳይሬክተረስ ሲስተር ሜሪ ሺና (Sr. M. Sheena)

ልደታ ማርያም የልጃገረዶች ት/ቤት 9/2/2019
ውድ የ9ኛ–12ኛ ክፍል ተማሪዎች፣ ነገ በሚካሄደው የፎቶ ፕሮግራም ላይ ሁሉም ተማሪዎች መገኘት እንዳለባቸው እናሳውቃለን። ስለዚህ ሁሉም ተማሪዎች በትክክለኛው የትምህርት ቤት ዩኒፎርም በንጹህና በሥርዓት ተዘጋጅታችሁ መምጣት አለባችሁ።
የሁሉም ተማሪዎች መገኘት ግዴታ ነው።

ሰኞ ጥቅምት 2/2019 ዓ.ም ለዘንድሮ 2019ዓ.ም የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠቃለያ ፈተና (ማትሪክ) ለምትወስዱ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ * በትራንስሪፕታችሁ እና በጂፒኤ ሰነዶቻችሁ ላይ የሚያርፉ በቅርብ ጊዜ በትምህርት ቤቱ ዩኒፎርም የተነሳችኋቸው ሁለት ባለቀለም ጉርድ ፎቶግራፎች ከነገ ጀምሮ ለቢሮ ገቢ እንድታደርጉ እናሳስባለን። * የፋይዳ መታወቂያ ካርዳችሁን ፎቶ ኮፒ እስከ አሁን ያላመጣችሁ በቶሎ እንድታመጡ * ለአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ተሰብስቦ በጥቅል ገቢ የሚደረገውን የመመዝገቢያ(150.00ብር) እና ለ 6 ትምህርቶች መፈተኛ 6*100 (600 ብር) በድምሩ 750.00 ብር ከነገ ጀምሮ ስለምንሰበስብ ይዛችሁ መምጣት እንዳትረሱ። * ትራንስክሪፕት ከቀድሞ ትምህርት ቤቶቻችሁ እንዲሁም የ ሚኒስትሪ ውጤት ሰርቲፊኬት እስከ አሁን ያላመጣችሁ እንድታመጡ እናሳስባለን። ትምህርት ቤቱ

ቀን:-ዓርብ መስከረም 29/2019ዓ.ም ለዘንድሮ 2019 ዓ.ም የ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠቃለያ ፈተና (ማትሪክ) ተፈታኝ ልጅ ላላችሁ ወላጆች እንዲሁም አሳዳጊዎች በሙሉ ። የግል ተማሪዎች እንደሁልጊዜው ሁሉ የመፈተኛ ማኑዋሉ ባስቀመጠው መሠረት ለመመዝገቢያ 150.00(አንድ መቶ ሃምሳ ብር) ለፈተናዎቹ በየትምህርት ዓይነቱ ( የተፈጥሮ ሳይንስ እንዲሁም የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የሚወስዷቸው ስድስት የትምህርት ዓይነቶች ስለሆኑ) ለአንድ ትምህርት 100.00 (አንድ መቶ ብር) በድምሩ 750.00(ሰባት መቶ ሃምሳ ብር የሚከፈል መሆኑን እየገለፅን እያንዳንዱ አስፈታኝ የግል ትምህርት ቤት ከተፈታኝ ተማሪዎች የሚሰበስበውን ብር ለአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በአካውንታቸው ገቢ በማድረግ ተፈታኝ ተማሪዎቹን በኦንላይን ማስመዝገብ ስላለበት ነገሮችን ከወዲሁ ዝግጁ አድርገን ለመጠበቅ ይረዳን ዘንድ ከመጪው ሰኞ ጥቅምት 2/2019 ዓ.ም ጀምሮ 750.00 ብሩን ስለምንሰበስብ በልጆቻችሁ በኩል እንድትልኩልን ስንል በተጨማሪም እስከአሁን የፋይዳ መታወቂያ ካርድ ኮፒውን የ 8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ውጤት ሰርቲፊኬት እንዲሁም ከቀድሞ ትምህርት ቤታችሁ ትራንስክሪፕት ያላመጣችሁ ተማሪዎች በአስቸኳይ እንድታመጡ እናሳስባለን ። ትምህርት ቤቱ

28/9/2019 ለ 6ኛ ፣ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ወላጆች /አሳዳጊዎች ፡፡ ቅዳሜ መስከረም 30/1/2019 ከጠዋቱ 2 : 00 እስከ 3 : 00 ሰዓት በተማሪዎች ትምህርት ዙሪያ እና የተማሪዎች አገር አቀፍ ክልላዊ ፈተና የሚደረግ ወይይት እንዲገኙ እያሳሰብን ሁሉም ወላጅ በስብሰባው ላይ ተገኝቶ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደር ጥሪ እናደርጋለን በስብሰባው ካልተገኙ በተገኙት ተሰብሳቢ ውሳኔ የሚጠቃለል መሆኑ እናሳስባለን ፡፡ ት/ቤቱ

28/9/2019 ለ 6ኛ ፣ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ወላጆች /አሳዳጊዎች ፡፡ ቅዳሜ መስከረም 30/1/2019 ከጠዋቱ 2 30 እስከ 3 00 ሰዓት በተማሪዎች ትምህርት ዙሪያ እና የተማሪዎች አገር አቀፍ ክልላዊ ፈተና የሚደረግ ወይይት እንዲገኙ እያሳሰብን ሁሉም ወላጅ በስብሰባው ላይ ተገኝቶ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደር ጥሪ እናደርጋለን በስብሰባው ካልተገኙ በተገኙት ተሰብሳቢ ውሳኔ የሚጠቃለል መሆኑ እናሳስባለን ፡፡ ት/ቤቱ

ቀን:-እሁድ መስከረም 24/2019 ዓ.ም የዘንድሮን 2019 ዓ.ም 6ኛ እና 8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና(ሚኒስትሪ) ተፈታኝ ልጅ ላላችሁ ወላጆች እንዲሁም አሳዳጊዎች በሙሉ ነገ ሰኞ መስከረም 25/2019 ዓ.ም በአድሚሽን ካርዳቸው ላይ የሚውል ፎቶግራፍ ማስነሻና ማሳተሚያ የሚሆን 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በየክፍላቸው አየሄድን ስለምንሰበስብ በልጆቻችሁ በኩል እንድትልኩልን በአክብሮት እናሳስባለን ። የትምህርት ቤቱን መታወቂያ ካርድ እስከአሁን ያላወጣችሁላቸው ከሆነ ከቢሮ እንድታወጡ እናሳስባለን ። ትምህርት ቤቱ

ቀን ሐሙስ መስከረም 21/2019 ዓ.ም በዘንድሮ 2019 ዓ.ም የ 8ኛ እና 6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና (ሚኒስትሪ) ተፈታኝ ልጅ ላላችሁ ወላጆች እንዲሁም አሳዳጊዎች በሙሉ ልጆቻችሁ ወደ ሚኒስትሪ መፈተኛ ጣቢያቸው የሚገቡበት አድሚሽን ካርድ ላይ የሚቀመጠውን ፎቶግራፍ ማስነሻና አድሚሽን ካርድ ዝግጅት እና ህትመት ወጪ ላይ የሚውል በ ተፈታኝ ተማሪዎች ቁጥር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ሰኞ መስከረም 25/2019 ዓ.ም በየክፍላቸው እየሄድን ስለምንሰበስብ ከላይ የገለፅነውን የገንዘብ መጠን (ሁለት መቶ ብር) በልጆቻችሁ በኩል እንድትልኩልን እያሳሰብን ከዚሁ ጎን ለጎን እስከ አሁን ለልጆቻችሁ የትምህርት ቤቱን መታወቂያ ካርድ ያላወጣችሁ ወላጆች/አሳዳጊዎች ይህንን በቶሎ ከወዲሁ እንድታስፈፅሙ እናሳስባለን። ተፈታኝ ተማሪዎች በሙሉ በፈተና ቀናቶች የትምህርት ቤት መታወቂያ እና የፈተና ጣቢያ መግቢያ ካርድ ይዘው መንቀሳቀስ ስላለባቸው ነው። ትምህርት ቤቱ

photo content

photo content

photo content