ሰላም ካቶሊክ ቴሌቪዥን - PAX Catholic TV
الذهاب إلى القناة على Telegram
ሰላም ካቶሊክ ቲቪ Pax Catholic TV መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ባሉበት ሆነው ይከታተሉን ✅ YT – https://youtube.com/pax_ctv ✅ Fb – https://facebook.com/ethiocatholic.addis ✅ X – https://x.com/CatholicTVEthi2 ✅ Ig– https://instagram.com/pax_ctv Contact - 0978 15 8461
إظهار المزيد2 298
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+147 أيام
+1430 أيام
أرشيف المشاركات
🔴Live Now:
Pax Catholic TV: https://youtube.com/live/fNmMXMokWuc?feature=share
🔴 የማዕረገ ክህነት መስዋዕተ ቅዳሴ ቀጥታ ስርጭት ከኮንሶላታ ማርያም ቤተ - ጸሎት
የዲን. ታሪኩ ዘለቀ እና ዲን. ሶሪ ቡራዩ
በሰላም ካቶሊክ ቴሌቪዥን
በYouTube: Pax Catholic TV YouTube Channel
https://youtube.com/live/azwL4jzSxYc
በFacebook: ሰላም ካቶሊክ ቲቪ – Pax Catholic TV
እሑድ ነሐሴ 17/2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ ከ1፡30 ሰዓት ጀምሮ በቀጥታ!
መልካም ምኞትዎን አሁን በቀጥታ ስርጭቱ ስር በኮመንት ያጋሩ።
«ወትቀውም ንግሥት በየማንከ፣ በአልባሰ ወርቅ ዑፅፍት ወኁብርት ስምዒ ወለትየ ወርኢ ወአጽምኢ እዝነኪ»
( « በወርቅ ልብስ ተጎናጽፋ ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች » ) መዝሙር 45:9
የፍልሰታ ማርያም መስዋዕተ ቅዳሴ ቀጥታ ስርጭት ከቀበና ኪዳነ ምህረት ቁምስና
በሰላም ካቶሊክ ቴሌቪዥን
በYouTube: Pax Catholic TV YouTube Channel
https://youtube.com/live/XX6z_OXoeQw?feature=share
በFacebook: ሰላም ካቶሊክ ቲቪ – Pax Catholic TV
ቅዳሜ ነሐሴ 16/2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ ከ1፡30 ሰዓት ጀምሮ በቀጥታ!
ያልዎትን ማንኛውም አስተያየት በቀጥታ ስርጭቱ ስር በኮመንት ያጋሩ።
የፍልሰታ ማርያም ጾም ሱባዔ መዝጊያ ተካሔደ
ነሐሴ 15 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ አገረ ስብከት ቅዱስ ዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን ለ15 ቀናት የተካሄደው የፍልሰታ ማርያም ጾም ሱባዔ በትልቅ መንፈሳዊነት የአዲስ አበባ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነየሱስ ሱራፌል ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ተጠናቋል።
ብፁዕነታቸው ባሰሙት ቃለ እግዚአብሔርም በያኔዋ ፍልሰታ ማርያም በአሁኗ ጽዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን የተጀመረው የፍልሰታ ማርያም ጾም ሱባዔ ባለፉት 28 ዓመታት በፍልሰታ ለማርያም ዕድገት ማኅበር አስተባባሪነት በአዲስ አበባ አገረ ስብከት በርካታ ቁምስናዎች ሲካሔድ የነበረ መሆኑን አስታውሰዋል።
የቅዱስ ዮሴፍ ቁምስና ቆሞስ ክቡር አባ ብርሃኑ ለ2 ሳምንታት ሲካሔድ በቆየው የፍልሰታ ማርያም ጾም ሱባዔ ትብብር ላደረጉት ሁሉ ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የፍልሰታ ማርያም ዕድገት ማኅበር መሪ ካህን ክቡር አባ አስፋው ጌታቸው በበኩላቸው ለብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ ለሐዋሪያዊ አገልግሎታቸው እና አባታዊ መሪነታቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ክቡርነታቸው በተጨማሪም የፍልሰታ ማርያም ዕድገት ማኅበር ባለፉት በርካታ ዓመታት ለሰጡት የፍልሰታ ማርያም ጾም ሱባዔን ማስተባበር አገልግሎት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በቅዱስ ዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን የተካሔደው የ2018 ዓ.ም የፍልሰታ ማርያም ጾም መዝጊያ ከብፁዕነታቸው በተጨማሪ በርካታ ካህናት፣ ደናግል፣ ዘማሪያን፣ ምዕመናን እና ተጋባዥ እንግዳዎች በመገኘት በዝማሬ፣ በጸሎት እና በመንፈሳዊ ድምቀት ተከብሯል።
ከዓመት ዓመት በተለያዩ ቁምስናዎች እየተካሔደ የቆየው የፍልሰታ ማርያም ጾም ሱባዔ በቀጣዩ የ2019 ዓ.ም የሚካሔድበት ቁምስና የልደታ ማርያም ካቴድራል እንደሆነ ይፋ በማድረግ ተጠናቋል።
🔴 የፍልሰታ ማርያም ሱባኤ መዝጊያ መስዋዕተ ቅዳሴ ቀጥታ ስርጭት ከቅዱስ ዮሴፍ ቁምስና
በሰላም ካቶሊክ ቴሌቪዥን
▶️ በYouTube: Pax Catholic TV YouTube Channel
https://www.youtube.com/live/L5k-nmQnmFA?si=kOvak17dy8n4OxrI
📱 በFacebook: ሰላም ካቶሊክ ቲቪ – Pax Catholic TV
🔴 ዐርብ ነሐሴ 15/2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ ከ5፡00 ሰዓት ጀምሮ በቀጥታ!
💬 ያልዎትን ማንኛውም አስተያየት በቀጥታ ስርጭቱ ስር በኮመንት ያጋሩ።
ውድ የጣቢያችን ቤተሰብ ዘወትር ኀሙስ ምሽት 3፡00 ላይ ይተላለፍ የነበረው የቅዱስ ቁርባን ስግደት ቀጥታ ስርጭት ዛሬ ኀሙስ ነሐሴ/14/2018 ዓ.ም እንደማይኖር እናሳውቃለን።
በነገው ዕለት ከቅዱስ ዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን በሚኖረን የፍልሰታ ማርያም ሱባኤ መዝጊያ መስዋዕተ ቅዳሴ ቀጥታ ስርጭት ይጠብቁን! መልካም ጊዜ!
ከአክብሮት ጋር! ሰላም ካቶሊክ ቲሌቪዥን!
