ይሁኔ ወልዱ መታሰቢያ ደሴ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት Yihunie woldu metasebiya Dessie Special Boarding School
الذهاب إلى القناة على Telegram
በአማራ ክልል የመጀመሪያው ስለሆነው ደሴ ልዩ አዳሪ ትምሀርት ቤት ወቅታዊ መረጃ እንዲሁም አዳዲስ ፈጠራዎች ፣ ለተማሪዎችና ለመምህራን አጋዥ መፅሀፎች፣ ጥያቄዎች፣ ማስታወቂያዎች እዚህ ቻናል ላይ ያገኛሉ።
إظهار المزيد4 468
المشتركون
+1224 ساعات
+907 أيام
+44730 أيام
أرشيف المشاركات
⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️
👇👇👇👇👇👇
ቀን: 8/01/2019 ዓ.ም
🔷የክልላችን ት/ቢሮ ባለሙያዎችና የአብክመ ት/ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ ደምስ እንድሪስ በት/ቤታችን በመገኘት የክረምት ቅድመ ዝግጅት ስራንና አጠቃላይ
የት/ቤቱን የስራ እንቅስቃሴ የተመለከተ ግምገማና ምልከታን አከናውነዋል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
በምልከታውና በውይይቱ የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች
👉 በክረምት በት/ቤቱ በየዘርፉ የተሰሩ ስራዎችን በማየት አስተያየታቸውንና ወደፊትም መደረግ ያለበትን ሁኔታዎች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል።
👉 ለነባርና አድስ ገቢ የት/ቤታችን ተማሪዎች አቀባበልን በተመለከተም የጋራ አቅጣጫ በውይይቱ ተቀምጧል።
👉የማጠናከሪያ ትም/ት አሰጣጥን አጠናክሮ በመቀጠል የተማሪዎችን ውጤታማነት ማስቀጠል እንደሚገባ ውይይት ተደርጓል።
👉የ12ኛ ክፍል የብሄራዊ ፈተና ውጤትን በመገምገም ከዚህ የተሻለ ውጤት እንድመዘገብ ለቀጣይ መሰራት ስላለባቸው ነጥቦች ዙሪያ ውይይት ተከናውኗልደ
👉የቦርድ አባላት ተሳትፎንና እያደረጉ ያሉትን ሁሉን አቀፍ ድጋፍና ትብብር ተጠናክሮ እንድቀጥል አቅጣጫ ተቀምጧል።
👉የጓሮ አትክልት ልማትና የአረንጓደ ልማት ስራዎች ከዚህ በበለጠ መልኩ እንድሰፉ የጋራ ተደርጓል።
👉የአጋር አካላት ተሳትፎን ለማሳደግ በልዩ ሁኔታ መሰራት እንዳለበትም በውይይቱ ተነስቷል
👉ተቋሙ ያሉበትን እጥረቶች ተቋቁሞ ለውጤት መብቃቱ የትምህርት ቤቱ መምህራን እና ሰራተኞች ያደረጉት ያላሰለሰ ጥረትና የጋራ ውጤት በመሆኑ ወደፊትም ተጠናክሮ እንድቀጥል
👉ክልሉ በቀጣይ የተጠናከረ ድጋፍ እና እገዛ ለት/ቤቱ እንደሚያደርግ
👉ክልሉ በአዳሪ ት/ቤቶች መምህራንና ሰራተኞች የሚነሱ የጥቅማ ጥቅም ጥያቄዎችን በጥናት ላይ የተመሰረተ ምላሽ ለመስጠት እየሰራ መሆኑን
👉የክልሉ ት/ቢሮ እያደረገ ያለውን ድጋፍ በማጠናከር ት/ቤቱ ምቹ ሳቢና ማራኪ እንድሁም ስታንዳርዱን የጠበቀ ለማድረግ መከናወን ያለባቸውን ስራዎች በዝርዝር ውይይት ተደርጓል ።
👉በአጠቃላይ የአድሱ አመት የስራ ዕቅድ ከባለፈው አመት በተሻለ መልኩ የስራ አፈፃፀም እንድመዘገብ በትኩረት መሰራት እንዳለበት መግባባት ላይ ተደርሷል።
⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️
🍒 በመጨረሻም
👉በክልሉ ት/ቢሮ ሱፐርቪዥን ቡድን በት/ቤታችን ተገኝቶ ስላደረገልን ድጋፊና ስለሰጡን ገንቢ አስተያየት ከልብ እናመሰግናለን።።
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
የት/ቤቱ አስተዳደር
Repost from N/a
ማስታወቂያ
የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የዩኒቨርሲቲ ምደባን ይመለከታል
በትምህርት ሚኒስቴር በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን ወደ መንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የመመደብ ሂደትን አጠናቋል።
ምደባው ፍትሐዊነትን፣ ግልጽነትን፣ እኩል ዕድልን እና ሚዛናዊ ስርጭትን በሚያረጋግጥ መልኩ፣ የተማሪዎችን ውጤትና ምርጫ፣ የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ አቅም እንዲሁም ሌሎች የምደባ መስፈርቶችን ታሳቢ በማድረግ ተከናውኗል።
1. የምደባው ዋና መስፈርቶች
1.1. የተማሪዎች አጠቃላይ ውጤት እና የዩኒቨርሲቲ ምርጫ
የተማሪዎች አጠቃላይ የብሔራዊ ፈተና ውጤት የምደባው ዋና የቅደም ተከተል መስፈርት ሆኖ ተወስዷል። በዚህም መሠረት ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በምርጫቸው መሠረት የመመደብ ቅድሚያ እንዲያገኙ የተደረገ ሲሆን በተቻለ መጠን ከመረጧቸው የመጀመሪያ ሦስት ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ተደርጓል።
1.2. የዩኒቨርስቲዎች የተማሪ ቅበላ አቅም
የእያንዳንዱ ዩኒቨርስቲ የተማሪ ቅበላ አቅም በምደባው ሂደት ታሳቢ ተደርጓል። በመሆኑም የተማሪው ውጤትና ምርጫ ከዩኒቨርስቲዎች የቅበላ አቅም ጋር በማጣጣም ምደባው ተከናውኗል።
1.3. የክልል፣ የዞን፣ የወረዳ እና የትምህርት ቤት ስርጭት
በዩኒቨርሲቲዎቻችን ህብረ ብሄራዊነትን የሚያጸና እና የተማሪዎችን ሚዛናዊ ስርጭት ለማረጋገጥ፦
• 70 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ከተማሩበት ክልል ወይም ዞን ውጭ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ፤
• 30 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ደግሞ በተማሩበት ክልል ወይም ዞን ውስጥ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ተደርጓል። በተጨማሪም የዞን፣ የወረዳ እና የትምህርት ቤት ስርጭት በምደባው ሂደት ታሳቢ ተደርጓል።
1.4. የፆታ ሚዛን
በዩኒቨርሲቲዎች የሴትና የወንድ ተማሪዎች ስብጥር ሚዛናዊ እንዲሆን በምደባው ሂደት ታሳቢ ተደርጓል።
2. ልዩ ምደባ
2.1. ማየት እና መስማት የተሳናቸው ተማሪዎች
ማየት እና መስማት የተሳናቸው ተማሪዎች አስፈላጊውን የትምህርትና የድጋፍ አገልግሎት ሊያገኙ በሚችሉባቸው ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ተደርጓል።
2.2. 500 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች
በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ600 ነጥብ 500 እና ከዚያ በላይ አጠቃላይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች፣ ላስመዘገቡት የላቀ የአካዳሚክ ውጤት ልዩ ታሳቢነት በመስጠት፣ በመጀመሪያ ምርጫቸው ተመድበዋል።
ይህ ልዩ የምደባ አሠራር ተማሪዎቹ በብሔራዊ ፈተናው ላስመዘገቡት የላቀ ውጤት ዕውቅና ለመስጠት እና ከፍተኛ አፈጻጸምን ለማበረታታት የተደረገ ነው።
3. የምደባ ውጤትን ስለመመልከት
ተማሪዎች የተመደቡበትን ዩኒቨርስቲ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የኦንላይን ሥርዓት በመጠቀም ማየት ይችላሉ።
የተመደቡበትን ዩኒቨርስቲ ለማየት ማስፈንጠሪያ፦ https://student.ethernet.edu.et/view-placement
4. ቅሬታ ስለማቅረብ
በምደባው ቅሬታ ያላቸው ተማሪዎች ቅሬታቸውን ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የኦንላይን ሥርዓት ብቻ ይህ ምደባ ይፋ ከሆነበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን መረጃና ማስረጃ በማያያዝ እንዲያቀርቡ እናሳስባለን።
የቅሬታ ማቅረቢያ ማስፈንጠሪያ፦ https://student.ethernet.edu.et/complaints
• በአካል ወደ ትምህርት ሚኒስቴር በመምጣት የሚቀርብ የምደባ ቅሬታ የማይስተናገድ መሆኑን ተማሪዎችና ወላጆች እንዲገነዘቡ እናሳውቃለን።
5. ማሳሰቢያ
ቅሬታ በሚቀርብበት ወቅት የሐሰት መረጃ፣ የተሳሳተ ማስረጃ ወይም የተጭበረበረ ሰነድ ማቅረብ በፍጹም የተከለከለ ነው። በቅሬታ ሂደት የሚቀርቡ መረጃዎችና ሰነዶች ትክክለኛነት የሚረጋገጥ ሲሆን፣ የሐሰት መረጃ ወይም ሰነድ አቅርበው የተገኙ ተማሪዎች ምደባቸው ሊሰረዝ ይችላል።
በመሆኑም ሁሉም ተማሪዎች ቅሬታቸውን በእውነተኛና በተረጋገጠ መረጃ ላይ ብቻ በመመሥረት በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ እንዲያቀርቡ እናሳስባለን።
የትምህርት ሚኒስቴር በ2018 ዓ.ም ወደ መንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ እያለ፣ በቀጣዩ የከፍተኛ ትምህርት ጉዟችሁ ስኬታማ እንድትሆኑ መልካም ምኞቱን ይገልጻል።
የትምህርት ሚኒስቴር
Repost from Ministry of Education Ethiopia
ማስታወቂያ
በ2018 ዓ.ም. የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ሰርተፊኬት ፈተና ወስዳችሁ በመደበኛው የትምህርት መርሃ ግብር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ላስመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፤
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና የትምህርት መስክ ምርጫ ማጠናቀቂያ ቀን እስከ መስከረም 5 ቀን የተራዘመ መሆኑን እንገልጻለን።
ስለሆነም በተለያዩ ምክንያቶች እስካሁን ምርጫችሁን ያላስገባችሁ ተማሪዎች በ https://student.ethernet.edu.et ድህረ ገጽ በመግባት የራሳችሁን ፋይዳ (የመለያ ቁጥር) በመጠቀም ምርጫችሁን እንድታጠናቅቁ እናሳውቃለን።
🌼 መልካም አዲስ ዓመት 2019! 🌼
የይሁኔ ወልዱ መታሰቢያ ደሴ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት
እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም በጤና አደረሳችሁ ‼️
ለትምህርት ቤታችን ማህበረሰብ፣ ለመምህራን፣ ለተማሪዎች፣ ለሰራተኞች እና ለወላጆች በሙሉ መጪው 2019 ዓ.ም የፍቅር፣ የጤና፣ የሰላም እና የስኬት ዓመት እንዲሆንላችሁ ከልብ እንመኛለን!
🌻 መልካም አዲስ ዓመት! 🌻
💐💐🇪🇹🇪🇹💐💐
ቀን 30/12/2018
👉የክልላችን የአዳሪ ት/ቤት
መግቢያ ፈተና ነገ 01/13/2018 ዓ.ም በደሴ ከተማ አስተዳደርና በደ/ወሎ ዞን ትም/መምሪያ የተመዘገባችሁና ምልመላውን ያለፋችሁ ተማሪዎች ወደ ክልሉ ወደሚገኙ አዳሪ ት/ቤቶች ለመግባት የሚሰጠው የመግቢያ ፈተና በሆጤ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የሚሰጥ ሲሆን ከጧቱ 1:30 ት/ቤቱ ቅጥር ግቢ ተፈታኞች በሙሉ ቀድማችሁ እንድትገኙ በማለት እናሳውቃለን‼️
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
ከክልሉ አንደኛ
ተማሪ ሙባረክ መሐመድ በአማራ ክልል በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር ዓቀፍ ፈተና ከ600 ጥያቄ 587 በመመለስ ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገቡት መካከል መኾን ችሏል ።
የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በታች አርማጭሆ ወረዳ ሳንጃ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተምሯል። ቀጥሎም ከ9ኛ ክፍል ጀምሮ በይሁኔ ወልዱ መታሰቢያ ደሴ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ሲከታተል ቆይቷል።
በተለይም ከ10ኛ ክፍል ጀምሮ በትምህርት ቤቱ ከፍተኛውን ውጤት እያስመዘገበ የአንደኛ ደረጃን እየያዘ ቀጥሎ በ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና የላቀ ውጤት አምጥቷል።
ለዚህ ስኬታማነቱ በክፍል ውስጥ መምህራን የሚያስተምሩትን ትምህርት በንቃት በመከታተል፤ በክፍል ውስጥ የተማረውን በየቀኑ መከለስ እና አብዛኛውን ጊዜውን በንባብ ማሳለፉ መኾኑን ገልጿል።
በተለይም ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉትን የትምህርት አይነቶች ጭምር እያጠና ለፈተና መዘጋጀቱ ለ12ኛ ክፍል ውጤቱ አንዳገዘው የትጋት መንገዱን አስረድቷል።
#አሚኮ #Education #AmharaRegion #TopScorers
Repost from N/a
ማስታወቂያ
የ2018 ዓ.ም. የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በመደበኛው የትምህርት መርሃ ግብር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ላስመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፡-
Ø የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና የትምህርት መስክ ምርጫችሁን ከነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ከታች የተቀመጠውን ማስፈንጠሪያ (Link) በመጠቀም ምርጫችሁን ት/ቤት መሄድ ሳይጠበቅባችሁ ባላችሁበት ቦታ እራሳችሁ በመሙላት እንድታሳውቁ እንገልጻለን።
Ø ማስፈንጠሪያ (Link) https://student.ethernet.edu.et/
ማሳሰቢያ፡-
v የህክምና፣ የአካል ጉዳተኝነት፣ ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው መንትያዎች እና ከ6 ወር በታች ህፃን የሚያጠቡ እናቶች አስፈላጊውን ሕጋዊ ማስረጃ ማያያዝ ይኖርባችኋል።
የትምህርት ሚኒስቴር
ቀን- 27-12-2018
የፈተና ቀን የተቀየረ መሆኑን ስለማሳወቅ:
ለክልል አዳሪ ትምህርት ቤቶች የሚወዳደሩ ተማሪዎች የፈተና ቀን በ 01/13/2018 ዓ.ም (የፊታችን እሁድ) መሆኑን እያሳወቅን አስፈላጊው ዝግጅት ይደረግ፡፡
ቀን-22-12-2018 ዓ.ም
ሰላም ለሁላችሁም፡፡
ለክልል አዳሪ ትምህርት ቤቶች በመስፈርቱ መሰረት የተመዘገቡ ተማሪዎች የጹህፍ ፈተና የሚሰጠው በ30/12/2018 ዓ.ም ነው፡፡ ፈተና የሚሰጥባቸው የትምህርት አይነቶች ሒሳብ እና እንግሊዝኛ ሲሆኑ ፈተናው የሚጀምረው 3፡00 ላይ ነው፡፡ በየደረጀው መረጃው እንዲደርስ ይደረግ፡፡መረጃው መድረሱም ክትትል መደረግ አለበት፡፡
አጠቃላይ ሂደቱን እና የፈተና መስጫ ቦታዎችን በተመለከተ ከዞን እና ከተማ አስተዳደሮች የሥርዓተ ትምህርት ቡድን መሪዎች ጋር በዙም የጋራ የምናደርግ ይሆናል፡፡
587 ያመጣው የኮከቡ ተማሪ ሙባረክ የስኬት መንገድ🎉🎉
ተማሪ ሙባረክ መሐመድ የይሁኔ ወልዱ መታሰቢያ ደሴ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪ ነው። በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር ዓቀፍ ፈተና ከ600 ጥያቄ 587 በመመለስ ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገቡት መካከል መኾን ችሏል ።🌟
✨ የተማሪው የቀደመ ታሪክ !
ተማሪ ሙባረክ እንደተናገረው የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በታች አርማጭሆ ወረዳ ሳንጃ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተምሯል። ቀጥሎም ከ9ኛ ክፍል ጀምሮ በይሁኔ ወልዱ መታሰቢያ ደሴ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ሲከታተል ቆይቷል።
🥇በተለይም ከ10ኛ ክፍል ጀምሮ በትምህርት ቤቱ ከፍተኛውን ውጤት እያስመዘገበ የአንደኛ ደረጃን እየያዘ ቀጥሎ በ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና የላቀ ውጤት አምጥቷል።
✨ የስኬታማነቱ ሚስጥር💡
ለዚህ ስኬታማነቱ በክፍል ውስጥ መምህራን የሚያስተምሩትን ትምህርት በንቃት በመከታተል፤ በክፍል ውስጥ የተማረውን በየቀኑ መከለስ እና አብዛኛውን ጊዜውን በንባብ ማሳለፉ መኾኑን ገልጿል።
በተለይም ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉትን የትምህርት አይነቶች ጭምር እያጠና ለፈተና መዘጋጀቱ ለ12ኛ ክፍል ውጤቱ አንዳገዘው የትጋት መንገዱን አስረድቷል።
📖"ለጥናት ስልት የተፈጥሮ መንገድን እከተላለሁ" የሚለው ተማሪ ሙባረክ "ቀን በደንብ ሙሉ ጊዜዬን ለንባብ አውላለሁ፤ ማታ ደግሞ በቂ እንቅልፍ አገኛለሁ ይህም ለተሻለ መረዳት ያግዛል" ብሏል። በዚህም ለስኬት መብቃቱን ነው የገለጸው።
✨ የትምህርት ቤቱ እና የመምህራን ድጋፍ
ለተማሪ ሙባረክ ስኬት የትምህርት ቤቱ መምህራን ከፍተኛ ድርሻ እንዳላቸው ተናግሯል። "ውጤቱ የእኔ ብቻ ሳይኾን የመምህራን ጭምር ነው ምክንያቱም በእያንዳንዷ የትምህርት ሂደት የመምህራን ሚና ከፍተኛ ነው"ብሏል።
የትምህርት ቤቱ ርእሰ መምህር ሳሊም አሕመድ ፤ ሙባረክ መልካም ስነ ምግባር ያለው፣ ትጉህ እና ታታሪ እንደኾነ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። የጥናት መርሐ ግብር በሚመቸው መንገድ ራሱ አዘጋጅቶ የሚመራ፣ በእርስ በርስ መረዳዳት ግንባር ቀደም፣ በትምህርት ቤቱ አርዓያ የኾነ እና ትልቅ ርዕይ ያለው ተማሪ ነው ብለዋል።
🎉 የወላጅ ድጋፍ እና ደስታ !
የተማሪ ሙባረክ ወላጅ አባት ሙሐመድ አየነው ልጃቸው ከበፊት ጀምሮ በጥሩ ሥነ ምግባር ያደገ መኾኑን አንስተዋል። ለትምህርቱ ልዩ ፍቅር ስላለው ውጤታማ እንዲኾንም እንደወላጅ የሚችሉትን ሁሉ ድጋፍ ማድረጋቸውን ጠቁመዋል።
አኹን ላይ ከፍተኛ ውጤት ማምጣት በመቻሉም ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸዋል።
💡 የተማሪው የወደፊት ርዕይ
ተማሪ ሙባረክ ለወደፊት በሜካኒካል ኢንጅነሪንግ ዘርፍ ማጥናት እንደሚፈልግ ተናግሯል። ከልጅነቱ ጀምሮ የምወደው ዘርፍ በመኾኑ በኢንጅነሪንግ ዘርፎች መፍትሔ በሚያመጡ የቴክኖሎጂ ሥራዎች ላይ የራሱን አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚፈልግ ሀሳቡን አጋርቶናል።
#አሚኮ #Education #AmharaRegion #TopScorers
#ባሕር_ዳር #ነሐሴ_22_2018_ዓ_ም
✍️ዘጋቢ:- አሰፋ ልጥገበው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
