የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU
الذهاب إلى القناة على Telegram
إظهار المزيد
📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU
تُعد قناة የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU (@eotcgssu21) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 14 356 مشتركاً، محتلاً المرتبة 6 146 في فئة الدين والقيم الروحية والمرتبة 2 357 في منطقة Ethiopia.
📊 مؤشرات الجمهور والحراك
منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 14 356 مشتركاً.
بحسب آخر البيانات بتاريخ 23 يونيو, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار 507، وفي آخر 24 ساعة بمقدار 14، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.
- حالة التحقق: غير موثّقة
- معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 25.68%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 13.08% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
- وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 3 681 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 1 875 مشاهدة.
- التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 28.
📝 الوصف وسياسة المحتوى
وصف القناة غير متوفر.
بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 24 يونيو, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة الدين والقيم الروحية.
14 356
المشتركون
+1424 ساعات
+1027 أيام
+50730 أيام
أرشيف المشاركات
በቅዱስ ሲኖዶስ ጸድቆ ወደ ትግበራ ስለገባው ወጥ የሰንበት ት/ቤቶች ሥርዓተ ትምህርትና መዋቅር የመመሪያ አቅጣጫ እንዲሁም የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ ግብር ተካሔደ ።
(የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት) ነሐሴ 20 /12/2016 ዓ.ም
በቅዱስ ሲኖዶስ ጸድቆ ወደ ትግበራ ስለገባው ወጥ የሰንበት ት/ቤቶች ሥርዓተ ትምህርትና መዋቅር የመመሪያ አቅጣጫ እንዲሁም የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ ግብር የዐዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ፤ ሀገር አቀፍየሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ተ/ም/ሰብሳቢ ዲ/ን ስንታየሁ ምስጋናው፤ የዐዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ተ/ም/ሰብሳቢ ላዕከ ኄራን መንክር ግርማ ና የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት ዛሬ ነሐሴ 20 በዐዲስ አበባ ሀገረ ስብከት መሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሒዷል።
የግንዛቤ ማስጨበጫው የተሠጠው በአ.አ ውስጥ ለሚገኙ አቢያተ ክርስቲያናትና ገዳማት አስተዳዳሪ ፣ ጸሐፊ ፣ የሰበካ ጉባኤ ም/ሊቀ መናብርት ፣ የስብከተ ወንጌል ሓላፊዎችና ለሰንበት ት/ቤት ሰብሳቢዎች ነው። በመርሐ ግብሩም የዐዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ተ/ም/ሰብሳቢ ላዕከ ኄራን መንክር ግርማ ከመንበረ ፖትርያሪክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ቤቶች አንድነት እስከ አጥቢያ ሰንበት ት/ቤት ድረስ ያለውን መዋቅር ፤ የሰንበት ት/ቤቶች ጠቅላላ ጉባኤ በበዓለ ጰራቅሊጦስ እንደሚካሔድ በዚያ የሚተላለፉ መመሪያዎች ተግባራዊ እንደሚሆኑ፤ የሰንበት ት/ቤቶች የውስጥ ደንብ በሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጸድቆ ወደታች እንደሚወርድ እንዲሁም የሰንበት ት/ቤቶች የምርጫ ጊዜ በተመሣሣይ ወቅት እንደሚሆን ለተሣታፊዎች ገለፃ አድርገዋል። በመቀጠልም የሀገር አቀፍ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ተ/ም/ሰብሳቢ ዲ/ን ስንታየሁ ምስጋናው ስለ ሥርዓተ ት/ት ገለፃ ሲያደርጉ ሥርዓተ ትምህርቱ የዕድሜ ደረጃቸውን ያማከለ እንደሆነና ከ1ኛ-12ኛ ክፍል በ6 ክፍላተ ትምህርትና 1 አጋዥ ክፍለ ትምህርት የተከፋፈለና እንደሆነ አስረድተዋል። ከ1ኛ-4ኛ ክፍል ያሉት 23 መጽሐፍት በ4 ጥራዝ በ13ኛው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ማስመረቁ ይታወሳል። በቀጣይም የቀሩትን መጻሕፍት ለማሳተም ዕቅድ መያዙን እንዲሁም ከሊቃውንት ጉባኤ ጋር የአርትዖ ሥራ እየተደረገባቸው እንደሆነ አስረድተዋል። አያይዘውም የመማሪያ ቦታ ፣ መምህራን ና መጽሐፍቱ ለሥርዓተ ትምህርቱ ትግበራ ጉልህ ድርሻ እንዳላቸውና ይሄንን ማሟላት የሁሉም ባለ ድርሻ አካላት ተግባር ሊሆን እንደሚገባ ገልጸዎል።
በመጨረሻም የዐዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስቅዱስ" ሰንበት ት/ቤት የቤተ ክርስቲያን ናትና የሰንበት ት/ቤት ዓባላትም ቤተክርስቲያኒቱን በሓላፊነት መምራትና መቆጣጠር ይገባቸዋል ፤ የሰበካ ጉባኤ ዓባላትም ከሰ/ት/ቤቶች ጋር በመመካከር መሥራት ይኖርባቸዋል።" ብለዋል አያይዘውም " የአጥቢያው ሰበካ ጉባኤ ከ1-4 ኛ ክፍል ያሉትን መጽሐፍት ከየአንዳንዱ ስድስት ስድስት መጽሐፍት ለሰንበት ት/ቤቶቹ እንዲገዙ" መመሪያ አስተላልፈዋል። ከተሣታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችም መልስ ተሰጥቶባቸው ጉባኤው ተጠናቋል።
(የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት)
የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!
👉 Youtube
👉 Facebook
👉 Telegram
👉 Tiktok
+6
የ12ኛ ክፍል ምዘና በጉራጌ ሀገረ ስብከት ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅና ልዩ ልዩ የመምሪያ ኃላፊዎች በተገኙበት በይፋ ተሰጠ።
(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) ነሐሴ 19/12/2016 ዓ.ም
በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሰንበት ትምህርት ቤቶች እየተሰጠ በሚገኘው ሥርዓተ ትምህርት መሠረት 12ኛ ክፍል የደረሱ አጥቢያዎች ዛሬ ነሐሴ 19 የማጠቃለያ ፈተና በመውሰድ ላይ ይገኛሉ።
ከነዚህም ተፈታኝ አጥቢያዎች መካከል በጉራጌ ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኘው የወልቂጤ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ተስፋ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት አንዱ ነው።
በፈተና ጣቢያው በመገኘት አባታዊ መልእክትና ቡራኬ የሰጡት የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ሰንበት ትምህርት ቤቱ በሥርዓተ ትምህርት ትግበራ እያሳየ ያለውን እምርታ አድንቀው ከትምህርቱ ጋር ምዘና መኖሩ ተማሪዎች ምን ያህል ከመምህሮቻቸው የሚያገኙትን ትምህርት ማወቃቸውን ያሳያል ብለዋል። በመጨረሻም እግዚአብሔር ምስጢሩን ይገልጥ ዘንድ ፀሎትን አድርገው በይፋ የፈተና መርሐ ግብሩን አስጀምረዋል።
(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)
የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!
👉 Youtube
👉 Facebook
👉 Telegram
👉 Tiktok
متاح الآن! بحث تيليغرام 2025 — أهم رؤى العام 
