የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU
الذهاب إلى القناة على Telegram
إظهار المزيد
📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU
تُعد قناة የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU (@eotcgssu21) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 14 322 مشتركاً، محتلاً المرتبة 6 154 في فئة الدين والقيم الروحية والمرتبة 2 360 في منطقة Ethiopia.
📊 مؤشرات الجمهور والحراك
منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 14 322 مشتركاً.
بحسب آخر البيانات بتاريخ 22 يونيو, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار 507، وفي آخر 24 ساعة بمقدار 11، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.
- حالة التحقق: غير موثّقة
- معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 49.23%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 13.09% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
- وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 0 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 1 875 مشاهدة.
- التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 0.
📝 الوصف وسياسة المحتوى
وصف القناة غير متوفر.
بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 23 يونيو, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة الدين والقيم الروحية.
14 322
المشتركون
+1124 ساعات
+1077 أيام
+50730 أيام
أرشيف المشاركات
+5
የመስቀል ደመራ በዓል በሻሸመኔ የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ በተገኙበት ተከብሯል።
+2
የ2017 ዓ.ም የመስቀል በዓል ቅድመ ዝግጅት ማጠቃለያ
በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት የደሴ ከተማ ሰንበት ትምህርት ቤቶች
+5
የ2017 ዓ.ም የመስቀል በዓል ቅድመ ዝግጅት ማጠቃለያ
በጅማና ማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት ሰንበት ትምህርት ቤቶች
+3
የመስቀል በዓል ቅድመ ዝግጅት በየአኅጉረ ስብከቱ በዛሬው እለት ተጠናቀቀ።
(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) መስከረም 15/1/2016
የ2017 ዓ.ም የመስቀል በዓል በደማቅ ሁኔታ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱንና ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ ተከብሮ ይውል ዘንድ በየአኅጉረ ስብከቱ የሚገኙ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ቅድመ ዝግጅታቸውን በዛሬው እለት መጨረሳቸውን ተነገረ።
የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የደባርቅ ከተማ የመስቀል በዓልን ባመረና በደመቀ ሃይማኖታዊ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ ለማክበር ስምንቱ የከተማ አድባራት መዝሙር በጋራ ሲያጠኑ ቆይተው በዛሬው እለት መፈጸማቸውንና ገልፀዋል።
የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ።
(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)
👉 Youtube
👉 Facebook
👉 Telegram
👉 Tiktok
ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የመስቀል ደመራ በዓል ፍፁም መንፈሳዊ በሆነ መልኩ ተከብሮ መዋል ይችል ዘንድ ሁሉም ባለድርሻ አካል የሚጠበቅበትን ሁሉ እንዲያደርግ ጥሪ አቀረቡ።
***
መስከረም ፲፬ ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም
""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
**
ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የባህር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓልን በማስመ
ልከት የእንኳን አደረሳችሁና የቅድመ ጥንቃቄ መልዕክት አስተላለፉ።
ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በዚሁ መልዕክታቸው ለመላው
ሕዝበ ክርስቲያን እንኳን ለ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ ካሉ በኋላ በዓሉ በድምቀት፣ባማረና በሰመረ መልኩ ተከብሮ መዋል ይችል ዘንድ ሕዝበ ክርስቲያኑ በንቃትና በሕብረት በመሆን ከጸጥታ አካላትና ቤተክርስቲያኒቱ ለዚሁ ዓላማ ካቋቋመቻቸው የኮሚቴ አባላት ጭምር በመተባበር እንዲሰራ አደራ ብለዋል።
የመንግሥት የጸጥታ ተቋማት በዓሉ ያለ አንዳች የጸጥታ ችግር ተከብሮ መዋል እንዲችል ከጠቅላይ ቤተክህነት ዐቢይ ኮሚቴ ጋር በጥምረት እየሰራ እንደሚገኝ የጠቀሱት ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በበዓሉ ወቅት ለሚደረግ ፍተሻ ፍፁም ክርስቲያናዊ ትብብር እንዲያደርግ አደራ ብለዋል።የጸጥታ አስከባሪዎችም ጨዋነት በተሞላና ክብርን በሚገልጽ አግባብ የፍተሻ ሥርዓቱን እንዲያከናውኑ አሳስበዋል።
ሕዝበ ክርስቲያኑ ከበዓላችን መንፈሳዊ ሥርዓት ውጪ የሆኑ መልዕክቶች፣ አለባበሶች እንዲሁም የቤተክርስቲያኒቱ መገለጫ ከሆኑ ዓርማዎች ውጭ መያዝ አይገባውም ያሉት ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በዓሉ ሃይማኖታዊና መንፈሳዊ እንደመሆኑ መጠን ቤተክርስቲያኒቱን ከማይገልጹ ሆታዎችና ጭፈራዎች እንዲርቅ በአጠቃላይ የመስቀል ደመራ በሚከበርባቸው ቦታዎች ሁሉ ያልተፈቀዱ ነገሮችን ይዞ መገኘት ፍጹም መንፈሳዊ የሆነውን በዓላችንን የሚያደበዝዘው ስለሆነ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል ብለዋል።
አያይዘውም ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጀ ወጣት የሰንበት ትምህርት ቤት ልጆቻችን ከሚያቀርቡት መንፈሳዊ ትርኢትና ዝማሬ ጎን ለጎን አካባቢያቸውን በመቆጣጠር በዓላችንን በሰላም እንዳናከብር የሚያደርጉ ሁኔታዎች እንዳይፈጠሩ በጥንቃቄ መጠበቅ ይኖርባቸዋል ብለዋል።
በሌላ መልኩም የሌሎች እምነት ተከታዮችም በነበረውና በኖረው የመከባበርና የመደማመጥ የአብሮነት ስሜት በዓሉ በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን እንዲወጡ የአደራ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
የበዓሉ ዝግጅት በየደረጃው በተቋቋሙት የበዓል አዘጋጅ ኮሚቴዎች ጥረት በጥሩ ሁኔታ በማጠናቀቅ ላይ መሆኑን የገለፁት ብፁዕነታቸው ከንጉሰ ነገስት አጼ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግስት ወዲህ ተደርጎ በማያውቅ ሁኔታ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሦስተኛ ጊዜ የመስቀል ደመራ በዓልን በድምቀት ማክበር የሚያስችል የስቴጅ፣የድምጽ ማጉያና የክብር እንግዶች ማስተናገጃ ቦታዎችን በማዘጋጀት የሚያደርገውን ተሳትፎ ያደነቁት ብፁዕ አቡነ አብርሃም የከተማ አስተዳደሩ እያደረገ ላለው ከፍተኛ አስተዋጽኦ በራሳቸውና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስ
ቲያን ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በመጨረሻም በዓሉን ስናከብር ፍቅር ሰላምንና አንድነትን እንዲሁም መግባባትን መርህ ባደረገ አግባብ መሆን አለበት ያሉት ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በዓሉ ሥጋዊ ፈቃዶቻችንን የምንፈጽምበት ሳይሆን ንስሐ ያልገቡ ንስሐ የሚገቡበት የተጣሉ የሚታረቁበት የተለያዩ አንድ የሚሆኑበት የተራራቁ የሚቀራረቡበት ፍፁም የደስታና የሰላም በዓል ሆኖ እንዲከበር ማድረግ ይኖርብናል በማለት መልዕክታቸውን አጠናቀዋል።
የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን የህዝብ ግንኙነት መምሪያ
+2
ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል ተገኝተው ከምዕራብ ክፍለ ከተማ ገዳማትና አድባራት ተዋጣጥተው ለመስቀል ደመራ በዓል በዝግጅት ላይ ለሚገኙት የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት መልእክትና አባታዊ ቡራኬ አስተላለፉ።
(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) መስከረም 14/01/2016 ዓ.ም
በመልእክታቸውም ወጣት የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት እግዚአብሔር ለአገልግሎት ጠርቶ ስላከበራችሁ ክብርና ምስጋና ለእርሱ ይሁን እንኳን ደስ አላችሁ ብለው ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤት ልጆቿ ተከብራ በልዩ ጣዕመ ዜማ ታጀባ በማንኛውም ክብረ በዓል ላይ እግዚአብሔር ሲመሰገን ማየት እጅግ ደስ ያሰኛልና በዓሉ የሰላም በዓል የድኅነት በዓል እንደመሆኑ ለሰላም ትልቅ ትኩረት በመስጠት ከሚመለከታቸው ክፍሎችም ጋር በጋራ በመስራት ሁላችን ዐይን እና ጆሮ ሆነን በስማችን ክፉ ሥራን በመስራት የቤተክርስቲያንን ስም የሚያጠለሽ እንዳይኖር እየዘመርንም ተግቶ ሥራ መሥራት ይገባል ብለዋል። የአደባባይ በዓል በመሆኑም የሚመጣውም ሁሉ የሚማርበት እንዲሆን የአደራ መልእክታቸውንም አክለዋል።
የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!
(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)
👉 Youtube
👉 Facebook
👉 Telegram
👉 Tiktok
متاح الآن! بحث تيليغرام 2025 — أهم رؤى العام 
