uz
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

Kanalga Telegram’da o‘tish

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Ko'proq ko'rsatish
3 613
Obunachilar
+6624 soatlar
+5877 kun
+1 04130 kun
Postlar arxiv
በ201ኛ ኮር 54ኛ ክ/ጦር ጥምር ሀይሉ ጋር የግዳጅ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ‼️ ~~~~~~~~~~~~~~~~~ መጋቢት 06/2818 ዓ.ም የ54ኛ ክፍለ ጦር ጥምር ሀይል እንደ ንስር በአዲስ መልኩ ታ
+8
በ201ኛ ኮር 54ኛ ክ/ጦር ጥምር ሀይሉ ጋር የግዳጅ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ‼️ ~~~~~~~~~~~~~~~~~ መጋቢት 06/2818 ዓ.ም የ54ኛ ክፍለ ጦር ጥምር ሀይል እንደ ንስር በአዲስ መልኩ ታድሶ እየመጣ ነው።ጦሩ በፊት ከነበረው በትጥቅም በስንቅም ራሱን በማጎልበት በቂ የሆነ የቅደመ ዝግጅት ስራዎችን በመስራት በተሻለ ቁመና ላይ የሚገኝ ሲሆን ከግዳጅ መልስ ችግር ፈች የሆኑ ውይይቶቾን ማካሄድ ተችሏል። በውይይቱ የኮር አመራሮች በወቅታዊ ጉዳዮች እና የሚዲያ በቀጣይ መሰራት ያለባቸውን አቅጣጫወች አመላክተዋል። በተያያዘ በህልውና ትግሉ አልፋና ኦሜጋ ከሆነው ማህበረሰባችን ጋር ስለሚኖሩ ሁለተናዊ መስተጋብር በልዩ ሁኔታ ትኩረት በመስጠት ትግላችን ማስቀጠል እንዳለብን የጋራ መግባባት ስራ ተሰርቷል። አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ የአፋብን ቴድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

በሰሜን ወሎ ሀብሩ ወርዳ ቁጥር 32 በኮለቦና በመርኮታ ሊካሄድ የነበረው የፋሽስቱ ብልፅግና ስብሰባ ተበተነ። አፋብን ምኒልክ ዕዝ 101ኛ ኮር በ35ኛ ክፍለ ጦር በሰሜን ወሎ ሀብሩ ወረዳ በኮለቦ ለስብሰባ ከመረሳ በፋሽስቱ እግረኛ ሰራዊት ታጅቦ የመጠዋን የወራዳ ካድሬ በተከፈተበት ተኩስ ያሰበውን አላማ ሳያሳካ ፈርጥጦ እንድመለስ ተደረጓል። ለምርጫ ቅስቀሳና የባህር በር እናስመልሳለን ወጣቶችን ወደ ስልጠና ግቡ የሚል የውሸት ድስኩር ለመደስኮር አላማ አንግቦ ህዝቡን ለመዋሸት አስቦ የነበረ ቢሆንም ሳያገኝ አይበገሬወቹ 35ኛ ክፍለ ጦር ብትትኑ እንዲወጣ አድርገውታል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ምኒልክ ዕዝ 101ኛ ኮር 35ኛ ክፍለ ጦር ቃል አቀባይ መጋቢት 6/2018 ዓ ም

ዘጠኝ ኮማንዶዎች ከአመራሮቻቸው ጋር ሆነው የፋሽስቱ አብይ አህመድን ሰራዊት ከድተው የፋኖን ትግል ተቀላቀሉ! የአየር ወለድ ኮማንዶ ዕዝ አካል ከሆነችው 105ኛ ክፍለ ጦር በመክዳት 9 ሆነው በምዕራብ ወሎ ግንባር ወግድ ወረዳ ውስጥ የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር መብረቅ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል:: መብረቅ ክፍለ ጦርን ከተቀላቀሉት እነዚህ ኮማንዶዎች መካከል የ105ኛ ክፍለ ጦር የሰው ሐብት ኃላፊ እና መረጃ መሃንዲስ ባለሙያው እንድሁም አንድ የሻንበል መሪ የተካተቱ መሆናቸው ታውቋል:: የመብረቅ ክፍለ ጦርን ክንድ መቋቋም ያቃተው ጠላት እየተፍረከረከ ሲሆን በየጊዜው እየከዳ ወደ ወገን እየመጣ ነው:: የፋኖን የማድረግ አቅም መጠናከርን እና ውስጣዊ አንድነትን ተከትሎ የጠላት ኃይል ተስፋ በመቁረጡ የተነሱ በየዕለቱ እየከዳ መሆኑ ይታወቃል:: አሁንም ከጠላት ጋር ሆናችሁ የአማራ ህዝብን እየወጋችሁ ያላችሁ የመከላከያ፣ አድማ ብተና፣ ፓሊስ እና ሚሊሻ አባላት ዛሬ ነገ ሳትሉ ወደ ወገናችሁ ትቀላቀሉ ዘንድ የምናስታውሳችሁ የትኛውም ኃይል ህዝብን አሸንፎ እንደማያውቅ በማረጋገጥ ጭምር ነው:: ስለዚህ ከተሸናፊው አገዛዝ ጎን ቆማችሁ አላስፈላጊ ዋጋ ከምትከፍሉ ከወድሁ ወደ ወገን እንድትቀላቀሉ የምንላችሁ ህይወታችሁን ማትረፍ ለምትፈልጉት ሁሉ ነው:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ መጋቢት 6 ቀን 2018 ዓ.ም

♦️ ተክለ ሃይማኖት ብርጌድ በጠላት ኃይል ላይ ጥቃት ፈጸመች። ዛሬ 06/2018 ዓ.ም የአፋብን በላይ እዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር አካል የሆነው ንስር በለሳ ክ/ጦር ተክለ ሃይማኖት ብርጌድ በምስራ
+4
♦️ ተክለ ሃይማኖት ብርጌድ በጠላት ኃይል ላይ ጥቃት ፈጸመች። ዛሬ 06/2018 ዓ.ም የአፋብን በላይ እዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር አካል የሆነው ንስር በለሳ ክ/ጦር ተክለ ሃይማኖት ብርጌድ በምስራቅ በለሳ ዳንጎራ ከተባለው ቦታ ላይ ስርዓቱ ጥምር ኃይል ብሎ በሚጠራው ጡት ቆራጭ ቡድን ላይ ጥቃት ፈጽመዋል። በጥቃቱ ቁጥሩ በእውን የማይታወቅ የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛ ከመደረጉም በላይ አስከሬኑንና ቁስለኛውን ትቶም እንዲፈረጥጥ ተደርጓል። ብልጽግና ቀጣይ የግንቦት ስርዓታዊ ምርጫን በተሳካ ሁኔታ ለማካሄድ ተገዶ በፋኖ ጠንካራ ክንድ ተመትቶ የለቀቃቸውን ከተሞች መልሶ ለመቆጣጠር በመላው አማራ አካባቢዎች ያለ የሌለ ኃይሉን አሟጦ በአየር ኃይልና በድሮን በመታገዝ ውጊያዎችን እያደረገ መሆኑ የሚተወቅ ነው። ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን። አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አብነት ሞላ የካቲት 06/2018 ዓ.ም

የአገዛዙን ሻለቃ መሪ በመደምሰስ ብሬን ተማረከ‼️ የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ዳግማዊ ቴውድሮስ /አምስተኛ/ኮር የጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር አሀድ የሆነችው ይታየሁ ብርጌድ አባላት በትናንትናው እለት ከዳባት ወደ ገደብየ ሲንቀሳቀስ በነበረን የአገዛዙ ሀይል ዳራ ላይ አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቷል ። የይታየሁ ብርጌድ መሪ አርበኛ አስንቆ መኳንት በመራው አፕሬሽን የአገዛዙን ሻለቃ መሪን ጨምሮ 15 የጠላት ሀይል ሲደመሰስ ከ12 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ከቀላል እስከ  ከባድ ቁስል አስተናግደው ወደ ሆስፒታል ገብተዋል። የአርበኛ አስንቆ መኳንት ወታደራዊ ጥበብና እውቀት በታየበት አውደ ውጊያ  ይታየሁ ብርጌድ  1 ብሬን ፣ 5 ክላሽንኮቭ ፣ 10 ቦንብ እንዲሁም በርካታ ተተኳሾች ከአስታጥቄው ብርሃኑ ጁላ ገቢ አድርጋለች ። አገዛዙ ከገደብየና ዳባት ከተሞች ሀይል ሰባስቦ መልሶ ለማጥቃት ቢሞክርም የራስ አሞራው ሶስተኛ ኮር ሸጋው ውበት ብርጌድ እንዲሁም ሌሎች የጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር አባላት  መከላከል ተችሏል። አንድነት ሀይልም መዳህኒትም ነው !!!! ©አርበኛ ታድሎ ደሴ (ካስትሮ ) የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ህ/ግን /ኃላፊ መጋቢት 6/2018 ዓ/ም

ሶስት የፌዴራል ፖሊስ ሰራዊት አባላት ሙሉ ትጥቃቸውን በመያዝ የፋኖን ትግል ተቀላቀሉ! መጋቢት 5 ቀን 2018 ዓ.ም በሰሜን መምሪያ 3ኛ ሬጅመንት 2ኛ ሻንበል ስር ሲያገለግሉ የነበሩ ሶስት የፌዴራል ፖሊስ የሰራዊቱ አባላት፤ የአገዛዙን የጥፋት መንገድ በመቃወም ሙሉ ትጥቃቸውን ይዘው የምኒልክ ዕዝ 101ኛ ኮር 15ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል። የክፍለ ጦሩ አመራሮችም አቀባበል አድርገውላቸዋል:: የፋሽስቱን አገዛዝ በመቃወም ፋኖን የተቀላቀሉት የፌደራል ፖሊስ አባላት የሰሜን ወሎ ዞን መቀመጫ ከሆነችው ወልድያ ከተማ ጀነቶ በር ተመድበው የነበሩ ሲሆን ከዛ ተነስተው ስሪንቃ ከተማ እንደገቡ ገልፀዋል:: ቁልፍ መረጃዎችና የሰራዊቱ ወቅታዊ ገፅታ ​ከቀድሞ የሰራዊት አባላቱ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው:- 💠 በፌዴራል ፖሊስ ተቋሙ ውስጥ ከፍተኛ መከፋፈልና ተስፋ መቁረጥ ሰፍኗል። 💠​የውስጥ መፈራረስ:- ሰራዊቱ እርስ በርስ ከመጋጨት ባለፈ የመዋጋት አቅሙና ሞራሉ ክፉኛ ተዳክሟል። 💠"ከግማሽ በላይ የሚሆነው የፌዴራል ፖሊስ የሰራዊት አባል በየጊዜው እየቀነሰ ነው" ሲሉ ገልጸዋል። 💠​የመሪዎች ስጋት:- የሻለቃ አመራሮች ሰራዊቱ ጥሎ እንዳይጠፋ በመስጋት ዲሽቃና ከባድ መሳሪያዎችን የኦሮሞ ተወላጅ እየተመረጠ እንደሚያስታጥቁ አባላቱ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። 💠​የጅምላ መነሳሳት:- የጊዜ ጉዳይ እንጂ ቀሪው የሰራዊት አባልም የህዝቡን መከራ በመመልከት ወደ ፋኖ መቀላቀሉ እንደማይቀር አመልክተዋል። የቤተክርስቲያንና የምእመናን ሰለባ መሆን የሰራዊት አባላት ፍልሰት የመጣው አገዛዙ ፊቱን ወደ ሃይማኖት ተቋማት ባዞረበት አስከፊ ወቅት ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቤተክርስቲያንና በምእመናን ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ በሰራዊቱ ዘንድ አጀንዳ መሆኑንም ገልፀዋል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ​ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! ​የምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 101ኛ ኮር 15ኛ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት አርበኛ አሰፋ መለስ መጋቢት 6/2018 ዓ.ም

ስርዓቱ ፋኖን ማስታጠቁን ቀጥሎበታል ። በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ አንዱ ማርኮ አንደኛው ከድቶ ሁለት ሁለት ክላሽ በመያዝ ወደ አ.ፋ.ብ.ን ቴወድሮስ ዕዝ 109 ኮር እና 102ኛ ኮር ደርሰዋል ። የመጀመሪያው ባለታሪክ ፋኖ አማኑ አራጋው ሲሆን ተወልዶ ያደገው ደንበጫ ሲሆን የ109ኛ ኮሩ የ99ኛ ክፍለ ጦር አባሉ ለድርጅታዊ ስራ በተላከበት 'ፓራ ኮማንዶ ' የሚባሉ በደፈጣ አላሳልፍህ ሲሉት ሁለቱን እርምጃ በመውሰድ ከራሱ መሣሪያ በተጨማሪ ሁለት ክላሽ ማርኮ ቀብረር ብሎ ወደ ቀጠናው በመግባት ሁለት መሣሪያ ያልታጠቁ ጓዶቹን ማስታጠቅ ችሏል ። ሁለተኛው ባለታሪክ ደግሞ ባዘዘው አደመ ይባላል ባህርዳር ከተማ አስተዳደር ዙሪያ አማራ የሁኑ አድማ ብተናዎችን ቀን ቀን እንዳይከዱ በማለት መሣሪያ እያወረዱ እስቶር ውስጥ ይቆልፉባቸዎል ። ይሄ የአማራ ተወለጅ ታዲያ ስርዓቱ ለአማራ ምንም ክብር እንደሌለው በመረዳት የተቋለፈውን እስቶር ሰብሮ ሁለት ክላሽ በመያዝ የቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛን ኮርን 22ኛ ክፍለ ጦርን የተቀላቀለ ሲሆን የተቀበሉት ፋኖዎችም አንዱን መሣሪያ እራሱ ይዞ እንዲታገል በመፍቀድ አንዱን መሣሪያ ጀሌ ፋኖ እንዲታጠቅ ሁኗል። በተያያዘ ዜናም እንደሻው ይታይህ የተባለ አንድ የአድማ ብተና አባል የ105ኛ ኮርን የ55ኛ ክፍለ ጦርን የአቤ ጉበኛ ሻለቃን የተቀላቀለ መሆኑን ከቦታው መረጃ ደርሶናል ። ስርዓቱ ፋኖን ማስታጠቁን ቀጥሎበታል ። አዲስ ትውልድ ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣ አዲስ ተስፋ !

ውጤታማ የሆነ የከተማ አፕሬሽን ዘመቻ መሪው አጃቢወችን በመያዝ ብቻ ድቦ ዙሪያ 7 የጠላት ሀይል እስከወዲያኛው ተሰናበቱ ➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾ መጋቢት 06/2018 ዓ.ም የ74ኛ ክ/ጦር መች ሀይል ዘመቻ መምሪያ የሆነው አበበ መስፍን የምሊሻ እና ፖሊስ ስብስብ ድቦ ዙሪያ ልዩ ቦታው ቤትጠባቂ አቦ አመታዊ ክብረ በኣል ለመታደም የሄደውን ማህበረሰብ በተለይ ወጣቶችን ክብረ በዓሉን ለማስተጎጎል አስቦ የተንቀሳቀሰው ገዳይ ቡድን ከሆኑት ምኒሻ አድማበትን እና ፖሊስ መሃከል መጋቢት 5 ከቀኑ በ7:00 ሰዓት አጃቢወቹን መቆጣጠሪያ ገዥ ቦታ በመስያዝ ሰርጎ በመግባት መብረቃዊ ጥቃት ፈፅመዋል። በኦፕሬሽኑም 3 ሚሊሻ 1) ባሳዝን አባተ 2) ዘገየ ምትኩ 3) አንድ ለጊዜው ስሙ ያልታወ ሚሊሻ ላይመለሱ ሲሸኛቸው ሁለት ሚሊሻ እና አንድ ፓሊስ ቁስለኛ ሲሆኑ 1.ሀብቴ ተፈራ 2.ገብሬ አሸብርና 3ኛ አንድ ለጊዜው ስሙ ያልታወቀ ፖሊስ በፅኑ በማቁሰል በጀግንነት ግዳጁ ፈፅሞ በኩራት ተመልሷል። በተደረገው መብረቃዊ ጥቃት በቀጠናው ያሉ የስርአቱ ተላላኪዎች እና ተቋሙ ውስጥ ትልቅ አለመተማመን እርስበርስ እንዲታኩሱ ማድረግ ችሏል በዚህም 1.ታዘብ 2.ስመኘው እና ሌላ ስሙ ያልታወቀ ምኒሻ እርስበርስ የተረሻሸኑ ሲሆን ፈለገብርሃን ከተማ ላይም በ1የመከላከያ ሰራዊት አባል ላይ በጀግናው የቀኘ አርበኞች በጩቤ እርምጃ በመውሰድ ክላሹን መማረክ ተችሏል። አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ አፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

ተኩላዊ ጉዞ ‼️ በአርሲ፣በሐረርጌ ፣በሰላሌ እና በአማራ በሃይማኖቱና በማንነቱ የሚጨፈጨፈውን መንጋቸውን ባላዬ እና ባልሰማ ንቀው ሳይጎበኙ ቀርቶም ሳያስቡት ሱዳን ድረስ በተኩላነት መጓዝ ሐዋርያዊ ተ
+2
ተኩላዊ ጉዞ ‼️ በአርሲ፣በሐረርጌ ፣በሰላሌ እና በአማራ በሃይማኖቱና በማንነቱ የሚጨፈጨፈውን መንጋቸውን ባላዬ እና ባልሰማ ንቀው   ሳይጎበኙ ቀርቶም ሳያስቡት ሱዳን ድረስ በተኩላነት መጓዝ ሐዋርያዊ ተልዕኮ ሳይሆን  የመዝናኛ የስጋ ድሎትን የመሻት ጉዞ ነው። በርቱ ተዝናኑ።ዛሬ ከዘረኛው አገዛዝ ፖለቲካውም ጋር ስለተጣበቃችሁ የሚጠይቃችሁ አካል ባይኖርም ከእግዚአብሔር ፍርድ ግን እንደማታመልጡ እወቁ። ክርስቶስ ለፍርድ ይመጣል ሁላችንም የዘራነውን እናጭዳለን። በምድር የሚጠይቃችሁም ክንድ እየፈረጠመ ለመሆኑ ምስክር አንጠራም።

በኤፍራታና ግድም ወረዳ፣ ፈረዶ ውሀ ቀበሌ በምትገኘው "ሌመን ጎጥ" የተባለች መንደር፣ የሰው ልጅ ህሊና ሊሸከመው የማይችለው አሰቃቂ የግፍ ተግባር ተፈጽሟል። ይህ ጥቃት የተፈጸመው በስልጣን ጥመኛው የአብይ አህመድ አስተዳደር "የወንበር አስጠባቂ" ተልእኮ በተሰጣቸው የብአዴን ቅጥረኛ ሚሊሻዎች ንፁሃን እየተገደሉ ይገኛሉ። ሰሞኑን በሸዋ ምድር "የአሳምነው አናብስቶች አንድነት እና የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) መዋቅራቸውን ወደ አንድ በማምጣት ያደረጉት ወታደራዊና ፖለቲካዊ ቅንጅት በቤተ-መንግስቱ ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤን ፈጥሯል። ይህን ተከትሎ ቅስሙ የተሰበረውና በቁጣ ያበደው የብአዴን ታጣቂ ኃይል በቀጥታ በንጹሃን ገበሬዎች ላይ አፈሙዙን አዙሯል። በዚህ አረመኔያዊ ድርጊት የሁለት ንጹሃን ህይወት በግፍ ተቀጥፏል፤ ሁለቱ ደግሞ ለሞት በሚያደርስ ከባድ ቁስለት ላይ ይገኛሉ። ማንነቱ ሳይጣራና ምንም ወንጀል ሳይኖረው በገዛ ቀያቸው በቅጥረኛ ሚሊሻዎች በጥይት በግፍ ተገድለዋል። የተገደሉት ስም ዝርዝር 1.​አደፍርስ ጉልቴ 2.ደምስ ማሞ በደረሰባቸው ጥቃት ሁኔታ ለህይወታቸው በከባድ ቁስለኛ ሰለባ ሆነው ይገኛሉ። የቆሰሉት ስም ዝርዝር ​3. መደለያ ታደሰ 4. ​ፈጠነ ደመላሽ የአብይ አህመድ አገዛዝ ቅጥርኛ ሚኒሻ በፈፀመው የንፁሃን ግድያ በኤፍራታ ግድም ወርዳ ሰማይ ላይ የምትታየው ፀሐይ ዛሬ ደም መስላለች። የፈረዶ ውሀ ጅረትም እንደወትሮው በደስታ አይፈስም በውስጡ የንጹሃንን እንባና ደም ቀላቅሎ በከባድ ሀዘን ተውጦ ይገኛል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!! የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግንኙነት ነው!!!!!! መጋቢት 05 /06/2018 ዓ.ም

በቃ ልመንን ነው።።።።።።።።።።።። በቃኝ ልመንን ነው ሰለቸኝ አለሙ፤ እኔ ተቀምጨ እነሱ እየደሙ እነሱ እያለሙ፤ ምንስ ሊጣፍጠኝ ይህ የቅንጦት ህልሙ ? ፣ አወ ልመንን ነው ልኑር እንደጀግና ልታከም
+1
በቃ ልመንን ነው።።።።።።።።።።።። በቃኝ ልመንን ነው ሰለቸኝ አለሙ፤ እኔ ተቀምጨ እነሱ እየደሙ እነሱ እያለሙ፤ ምንስ ሊጣፍጠኝ ይህ የቅንጦት ህልሙ ? ፣ አወ ልመንን ነው ልኑር እንደጀግና ልታከም ህመሜን፤ አማራነት ሞቶ:አማራነት ደምቶ እንደት ልየው ህልሜን፤ ፣ በፀሀይ ገርጥተው ፊታቸው ቢጠቁር፡ በርሀብ ተጎድተው ወዛቸው ቢጠፋ፣ በአማራነት ደምተው ልባቸው ቢከፋ አወ ልመንነው ከነሱው አድሬ ከነሱው ጋር ልልፋ፣ ፣ ሴት ነሽ አትበሉኝ ሴት እንደት አይመንን አርበነት የናት አሁን ብቻ አይደለን ፣ ትናንት የነበረ የትጌ ጣይቱ በኛ አልነበረም ወይ ? የተባልነው አንቱ ፤ ፣ ታዳ ልመጣ ነው በፀሀይ ጠይመህ ፊትህ የገረጣው ጀግንነትህ ኩራት ሆኖ የደመቀው ፋኖ ገዳም ልግባ ለቅዱስ ዓላማ ያሉትን ይበሉ ማንንም አልሰማ። መጣሁ የሴቷ አርበኛ !!

ከነበልባል ክፍለ ጦር የተሰጠ መግለጫ አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ነበልባል ክፍለ ጦር። መጋቢት 5/07/2018 ዓ ም የህዝብን መሰረታዊ ጥያቂዎችን ለመፍታት አቅም ያጣው የድኩማን ስብስብ የሆነው ብልፅግና ፓርቲ ይኸው ወደ ስልጣን ከመጣ የህዝብን ጥያቄ መሸሻና መደበቂያ ጦርነት በማረግ ይኸው ሀገሪቷን ከድጡ ወደ ማጡ እየከተታት ይገኛል።        ይህ ሀገር አፍራሽ የብልፅግና ስረዓት ከስር መሰረቱ ተገርስሶ ስረዓታዊ ለውጥ እስካልመጣ ድረስ በምርጫ ምንም አይነት ለውጥ ማምጣት እንደማይቻል ፋኖ ያምናል ይህንንም በማመን የብልፅግናን ገዢ ቡድን ከስር መሰረቱ መንቅሮ ለመጣል  በትጥቅ ትግል እየተፋለመ እና የስረዓቱን መዋቅር እያፈራረሰ የራሱን አደረጃጀት በተቆጣጠራቸው አካባቢ እየዘረጋ እንዲሁም  ከአጎራባች ክልሎችም ወንድማዊ ትስስር እየፈጠረ ይገኛል።       የብልፅግና ገዢ ቡድን የሀይል ሚዛኑን ባጣበትና አጣብቂኝ ውስጥ በገባበት ጊዜና ለመውደቅ በሚንገዳገድበት ሰዓት ሀገር ሰላም በማስመሰል ለምርጫ እየተዘጋጀ እንደሆ ሰምተናል።        ድሮም ከዕብድና ከዘመናችን ካሪጉላ ከሆነ ሰው የሚጠበቅ ሀቅ ሆኖ ሳለ አብራችሁ ለማበድና ዘመን ይቅር የማይለውን በደል በህዝባችን ላይ ለማውረድ የምትሯሯጡ የምርጫ ቦርድ አበል መተዳደሪያ ያደረጋችሁ ፓርቲዎች በሙሉ ለእናንተ  የሆነ ነገር ማስገንዘብ እንፈልጋለን።                ይኸውም   1ኛ ይህ ሁሉ በደል እና ግፍ በአማራ ህዝብ ላይ ሲፈፀም የት ነበራችሁ? 2ኛ ከአንዱ ክልል ወደ ሌላው ክልል እያዟዟረ ያላቋረጠ ጦርነት ሲያደርግ የት ነበራችሁ? 3ኛ የሀገሪቷን በጀት ሙሉ ጦርነት ላይ ሲያውል ምን እየሰራችሁ ነበር? 4ኛ ንቁ ተሳትፎ ያላቸውን የአማራ ወጣቶችንና ፓለቲከኞችን ሳይለቅ እንዴት ተወዳዳሪ ሆናችሁ ቀረባችሁ?        መልሱን ለእናንተው እንተወውና በእኛ በኩል ያለውን እውነታ ለህዝባችን ማሳወቅ እንወዳለን       ይኸውም በ2018 ዓ ም የሚካሄደው ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ  ለሀገሪቷም ሆነ ለህዝቦቿ የማይጠቅም ሆኖ ስላገኘነው በእኛ በኩል ተቀባይነት የሌለውና በዚህ ምርጫ ላይ የምትወዳደሩ ፓርቲዎችም ሆናችሁ ግለሰቦች ወይም አስመራጭ ኮሚቴ አባሎች ከብልፅግናው ገዢ ቡድን ለይተን የማናያችሁ መሆኑን በመረዳት እራሳችሁን ቆጥባችሁ እንድትገኙ እናሳስባለን።    ይህን ተላልፎ የተገኘ ማንኛውም ፓርቲ እና በውሎ አበልም ይሁን በሌላ ጥቅማጥቅም የምርጫው ስራ አስፈፃሚ የሆነ ሁሉ በሚወሰድበት እርምጃ ሀላፊነቱን እራሱ እንደሚወስድ እናሳውቃለን    ድል ለአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ክብርና ሞገስ ለትግሉ ሰማዕታት ነበልባል ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል

#የሰማዕታት_ዘመቻ_ተደረገ‼️ መጋቢት 05/2018 ዓ.ም አፋብን ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር ከፍተኛ ድል ተቀዳጀ። ዘመቻ ሰማዕታት በሚል አፍላ የወጣትነት እድሜያቸውን ለአማራ ህዝብ ነፃነትና ህልውና የሰጡ ለትግሉ ታምነው ከጠላት ጋር ፊት ለፊት ተጋፍጠው በጀግንነት በተሰው ሰማዕታት ስም በአርበኛ ሻለቃ ሀብቴ ተሾመ  በአርበኛ ኮማንዶ ደስታው  መላክ እና በአርበኛ ብርቁ ደሴ ስም የተሰየመ ልዩ ዘመቻ ተደረገ።  በ102ኛ ኮር ውስጥ በሚገኙ ክ/ጦሮች ከፍተኛ ቅንጅት በተደረገው በዚህ ታሪካዊ ግዳጅ በብራቃት ከተማ መሽጎ በነበረ የብልፅግና ስብስብ ላይ ከፍተኛ የሰውና የቁስ ኪሳራ ማድረስ ተችሏል። በዚህ ከፍተኛ ትንቅንቅ ጠላት በቆፈረው ምሽግ ለመመከት ቢሞክርም ለወሬ ነጋሪ ሳይተርፍ በተደበቀበት ምሽግ #ተደምስሷል።  በዚህም መላክ መለሰ የተባለ የሚሊሻ ጠርናፊ እና በብልፅግና የታጠቅ ቀበሌ አስተዳዳሪ ሆኖ የተሾመ እና ሌሎች 40 በላይ የሚሊሻና መከላከያ አባላት ተደምስሰዋል። ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ደግሞ ከባድ እና ቀላል ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል።    በተጨማሪም 5 የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎችን ጨምሮ ሌሎች ወታደራዊ ቁሳቁሶችን ማግኘት ተችሏል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ገርጨጭ ከተማ ላይ የመሸገው የስርአቱ ወንበር ጠባቂ ከበባ ተደርጎበት ሲጨነቅ መዋሉን ማረጋገጥ ተችሏል። 11ኛ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ክፍል! 05/ዐ7/2018 ዓ.ም