uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling 👈

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

Kanalga Telegram’da o‘tish

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Ko'proq ko'rsatish
4 039
Obunachilar
+22224 soatlar
+3937 kun
+1 35930 kun
Postlar arxiv
የጠላት እንቅስቃሴ መረጃ !! የጠላት ኃይል መነሻው ከአዲስ አበባ ጦር ሀይሎች በማድረግ 25 ተሳቢ ደጀን እየገቡ ሬሽን እና የህክምና ቁሳቁስ ፣የመድፍ እና የሞርተር ተተኳሽ የጫኑ 2 ኦራል ሀይል የ
የጠላት እንቅስቃሴ መረጃ !! የጠላት ኃይል መነሻው ከአዲስ አበባ ጦር ሀይሎች በማድረግ 25 ተሳቢ ደጀን እየገቡ ሬሽን እና የህክምና ቁሳቁስ ፣የመድፍ እና የሞርተር ተተኳሽ የጫኑ 2 ኦራል ሀይል የጫነ፣10 ባለስጣን የያዙ ኮብራዎች 5 ብሬን የጠመዱ ፓትሮሎች ፣እና 4መድፍ በመያዝ ደጀን ከተማ ገብቷል።

አሁን ከመሸ 1:00 ጀምሮ በመላው ሽዋ ድሮኖች አሰሳ እየተደረገ ነው። እንደሚታወቀው አረመኔው አብይ አህመድ ብዙህ ኃይል ሸዋ እንዳስገባ የሚታወቅ ሀቅ ነው የተወሰኑ የሽዋ ቦታዎች ኔትወርክ ሰለጠፋ
አሁን ከመሸ 1:00 ጀምሮ በመላው ሽዋ ድሮኖች አሰሳ እየተደረገ ነው። እንደሚታወቀው አረመኔው አብይ አህመድ ብዙህ ኃይል ሸዋ እንዳስገባ የሚታወቅ ሀቅ ነው የተወሰኑ የሽዋ ቦታዎች ኔትወርክ ሰለጠፋ ለመላው ፋኖ መረጃው እንዲደርስና አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲደርግ። መረጃውን ለመላው ህዝባችን ሸር አድርጉ። አፋብን የመኖር ነፃነት ድርጅታዊ ቤታች የቴሌግራም ገፃችን👉 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

ሰበር ሰበር ዜና !!! ነቀርሳ ነፍሰ በላ ተሸኘ !!! ሰዉየዉ #አሸናፊ ይባላል፣ በጃዊ እና ፓዊ ቀጠናዎች እየተንቀሳቀሰ #በብልፅግና ድጋፍ እና ሽፋን ሰጭነት በማህበረሰቡ ላይ ከፍተኛ ግፍ እና በደ
ሰበር ሰበር ዜና !!! ነቀርሳ ነፍሰ በላ ተሸኘ !!! ሰዉየዉ #አሸናፊ         ይባላል፣ በጃዊ እና ፓዊ ቀጠናዎች እየተንቀሳቀሰ #በብልፅግና ድጋፍ እና ሽፋን ሰጭነት በማህበረሰቡ ላይ ከፍተኛ ግፍ እና በደል ሲፈፅም የነበረ፣ ህዝቡን የደም እንባ ሲያስለቅስ የኖረ አረመኔ የመንግስት ተላላኪ ቅጥረኛ በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 66ኛ ክ/ጦር በእሳት ነበልባሏ 3ኛ ሻለቃ እርምጃ ተወስዶበታል። በ2016 ዓ.ም ሚያዚያ ወር ላይ ወርቅ ሜዳ ከፋኖ ከድቶ ወደ ብልፅግና የገባ ሲሆን አንድ ሴት ገድሎ እንደገና ወጥቶ የመንግስት መረጃ በመሆን ከመከላከያ በቅርብ እርቀት ሆኖ ህዝቡን ሲዘርፍ የነበረዉ  ሌባ አሸናፊ በዛሬዉ እለት እስከ ወዲያኛው ተሸኝቷል። የያዘዉ #ስናይፐርም በፋኖ እጅ ገብቷል። ህዝቡም የደስታ ስሜቱን አንፀባርቆ ለጀግናው ፋኖ ያለዉን ክብር የበለጠ ያሳየበት እና ድጋፍ ያደረገበት ድንቅ ተዓምር ነበር። አዲስ ትዉልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!!! ©ያእቆብ ጌታሁን

የአረመኔው አራዊት - ሰራዊት አውዳሚ ሰራዊት የሲቪሊያንን ቤት አቃጠለ !!! 29/05/2018 ዓ.ም ➯አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 11ኛ ክፍለጦር ቀጠና የአረመኔው ሰራዊት በተደጋጋሚ ጊዜ ንፁሀንን ያነጣጠረ ጥቃት እየፈፀመ ይገኛል ። የፋኖ ደጋፊ በሚል ስበብ በህዝባችን ላይ ግድያ የጅምላ ግድያና ሀብት ንብረት የማውደም ተግባራትን ለተከታታይ እየፈፀመ ባለበት በዚህ ወቅትም በዛሬው ዕለት በቀን 29/05/2018 ዓ,ም በይልማና ዴንሳ ወረዳ ጎሸየ ቀበሌ ነዋሪ እና የጎሽዬ ሀና ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ የሆቱት ቄስ ሀይማኖት ገበይን ቤት ከቀኑ 6:00 ሠዓት አቃጥሎታል ። በእሳት ቃጠሎው የወደመ ሀብት ንብረትም 1,ሙሉ የቤት እቃ 2,የቤተ ክርስቲያን ንዋየ ቅዱሳትና ከ100ሽ ብር በላይ የቤተክርስቲያኒቱን ጥሬ ገንዘብ ከተቀመጠበት ካዝና በመስበር 3,ከ100 ኩንታል በላይ እህል 4,ሁለት(2) ክበድ የሆኑ የፈረጅ ላምና አንድ የፈረንጅ በሬ በድምሩ 700,000ብር የሚያወጣ ንብረት ላይ ዘረፋ በመፈፀም በአካባቢው ማህበረሰብ ላይ ከፍተኛ ሽብር እየፈፀመ ይገኛል። ይህ አረመኒያዊ ሥርዓት በጅምላ በመግደል ያልቀለበሰው የህልውና ትግላችን ሀብት ንብረት በማውደም እንደማይገታ እራሱም ያቀዋል ። ስርዓቱ ከውልደቱ ይዞት የተፈጠረ ፀረ ሰው ተግባሩን ይዞ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከአማራ ህዝብ ብሎም ከኢትዮጵያ ህዝብ ትክሻ ወርዶ ይቀበር ዘንድ እንበርታ ። ክፋት ለማንም!በጎነት ለሁሉም! አዲስ ትውልድ!አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

በአውደ ውጊያ በፋኖ የተሸነፈው ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ ወግዲ ወረዳ ከ35 በላይ ንፁሃኖችን በከባድ መሳሪያ ጨፈጨፈ:: በጀኔራል አድማሱ አለሙ እና በጀኔራል ዘውዱ ሰጥአርጌ የሚመራው 11ኛ ዕዝ እና ቀጠናው ላይ የተሰማራው ሪፐብሊካን ጋርድ ደቡብ ወሎ ዞን ወግዲ ወረዳ ከንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር መብረቅ ክፍለ ጦር ከባድ ተጋድሎ ገጥሟቸው ለጊዜው በስም ያልታወቁ ከፍተኛ የብልፅግና መከላከያ አመራሮችን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠር ሰራዊቱ ያለቀበትና በመቶዎች የቆሰለበት ሲሆን አስከሬንና ቁስለኛውን በሄሊኮፕተር ወደ ኮምቦልቻ እና አዲስ አበባ ሲያመላልስ ከርሟል:: ከዚህ ጋር ተያይዞም ዛሬ ጥር 29/2018 ዓ.ም አራተኛ ቀኑን በያዘው ከባድ ውጊያ የአገዛዙ ብልፅግና መከላከያ ሰራዊት ከባድ መሳሪያ በማስወንጨፍ በርካታ ንፁሃን የጨፈጨፈ ሲሆን ወግዲ ወረዳ ጎረንጅ 016 ቀበሌ ብቻ ስድስት የአንድ ቤተሰብ አባላት በግፍና በአሰቃቂ ሁኔታ ሞተዋል:: በተመሳሳይ በዚሁ በጎረንጅ 014 ቀበሌ አንድ መኖሪያ ቤት ላይ ባረፈ ከባድ መሳሪያ አባት ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ እናትና ልጅ ከባድ ቁስለኛ ሆነዋል:: የምኒልክ ዕዝ ከፍተኛ አመራር የሆነው አርበኛ ሻለቃ ሃብታሙ ደምሴ ቤተሰቦች መኖሪያ የሆነች መንደር ላይ ብቻ ከ54 ጊዜ በላይ ከባድ መሳሪያ አስወንጭፎ ከባድ ውድመት አድርሷል:: ፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ወግዲ ወረዳ በግፍ የጨፈጨፋቸው ጦር መሳሪያ ያልታጠቁ አማራዎች ስም ዝርዝር፦ •የተሰው ጦር መሳሪያ ያልታጠቁ አማራዎች 1.አለሙ ጌታሁን 2.አህመድ ደረሰ 3.አታላይ መንገሻ 4.አቡሽ አሸብር 5.አረቡ ሙህዬ 6.አየሉ ቡሽራ 7.አብርሃም አሸብር ናቸዉ። •ቀላልና ከባድ ቁስለኛ የሆኑ ጦር መሳሪያ ያልታጠቁ አማራዎች 1.አህመድ ሻረዉ 2.ሰይድ አህመድ 3.አሊ ሻረዉ 4.ሙስጠፋ አህመድ 5.የሱፍ ብርቁ 6.ሁሴን ረምረም 7.ደሴ እንድሬ 8.አሸብር ጌታሁን 9.አስካል ፈለቀ 10.ሙሃመድ አህመድ 11.መካ ሙሃመድ 12.አረጋሽ ካሳዉ 13.ጦይባ አደም 14.ሙሃመድ ሰይድ 15.አህመድ አሸብር 16.አሚናት አለሙ 17.ተጓዴ ሃምዛ 18.እንድሪስ አለሙ 19.ሙሃመድ ደረሰ 20.ሙሃመድ አብዱ 21.አደም ሙህዬ 22.የሱፍ ጌታሁን 23.ኢዘድን የሱፍ 24.ከሪማ ሰይድ 25.ይማም አሸብር 26.ነኢማ አህመድ 27.አህመድ አረቡ 28.ፋኢዛ ሰይድ በግፍ ከተጨፈጨፉት ጦር መሳሪያ ያልታጠቁ አማራዎች በተጨማሪ ከአርባ በላይ ቤቶች በፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ሰራዊት ከባድ መሳሪያ ተቃጥለዋል:: *የተንቀሳቃሽ ምስል እና ምስል ማስረጃዎች እንደደረሰን የምናጋራ ይሆናል:: ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ጥር 29/2018 ዓ.ም

ሸዋ አካባቢ መረጃ❗️ ኦሄዴድ/ብልፅግና  ከዚህ ቀደም  በሸዋ ቀጠና :- 1: የሪፐብሊካን ጋርድ 2 ክፍለጦሮች 2: የአየር ወለድ እና ኮማንዶ  6 ክፍለጦሮች 3:- የባህር ኃይል ኮማንዶ 1 ክፍለጦር 4:- የ6ኛ ዕዝ አካል የሆኑ  እግረኛ ሁለት ክፍለጦሮች በለሚ እና በጅሩ በኩል። እንዲሁም ከአድማ ብተና እና ሚሊሻ አሰማርቶ የነበረ ቢሆንም ከባለፈው ሰኞ ጀምሮ  በቀጠናው የስልክ ኔትወርክ በማጥፋት :- ~>  ናዝሬት ይገኝ የነበረውን የደቡብ ዕዝ አንድ ኮር ከ3ኛ መካናይዝድ ጋር በማቀናጀት በአፋር ዞሮ በከሚሴ በኩል ወደ ሸዋ ቆላማ ቦታዎች ~> የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ፅንፈኛ ታጣቂዎችን ጨምሮ የብሄረሰብ ዞኑን ሚሊሻዎች ወደ ራሳ፣ ቀወት፣ኤፍራታ ግድም እና ማጀቴ አካባቢ ሰምሪት ሰጥቶ እያንቀሳቀሰ ይገኛል።   ይሄ ተስፋ የቆረጠ ቡድን የአፋብን ከፍተኛ አመራሮች ላይ ያነጣጠረ ፍላጎት ቢኖረውም፤ ፅንፈኛ የብሄረሰቡ ታጣቂዎችን በመጠቀም  ህዝብን ለማጎሳቆል ጨምሮ ድርብርብ ዓላማ ያለው በመሆኑ የአፋብን ሠራዊት እና ህዝቡ  ተገቢው ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርበታል!

በ7ኛው ዙር ምርጫ ተሳትፎየን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ ለተከበራችሁ የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች፣ ለመላው የአማራ ሕዝብ እና ለኢትዮጵያውያን ወገኖቼ በሙሉ፦ ባለፉት ዓመታት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ በኩሩው የባሕር ዳር ከተማ ሕዝብ ተመርጨ፣ እናንተን ወክዬ፣ ለሕዝባችን ሀቀኛ ድምፅ በመሆን ለማገልገል በመቻሌ ታላቅ ክብርና ኩራት ይሰማኛል። በዚህ ጉዞዬ ላሳያችሁኝ ያልተቆጠበ ድጋፍ፣ ፍቅር፣ አክብሮት እና ጽኑ እምነት ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። በአሁኑ ወቅት ለ7ኛው ዙር ሀገር አቀፍ ምርጫ የእጩ ተወዳዳሪዎች ምዝገባ እየተከናወነ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በመራጮቼ፣ ደጋፊዎቼ እና በሚዲያዎች ዘንድ በዕጩነት መመዝገብ አለመመዝገቤን በተደጋጋሚ ስጠየቅ ቆይቻለሁ። አንዳንድ ፓርቲዎችም ባሕር ዳርም ሆነ አዲስ አበባ በፈለግሁበት ቦታ በእጩነት እንድቀርብ እድሉን ሰጥተውኝ ነበር። በግልም የመወዳደርን አማራጭ በጥልቀት አስቤበታለሁ። ሆኖም ግን በመጪው 7ኛው ዙር ምርጫ ራሴን በዕጩነት ላለማቅረብ መወሰኔን ለሕዝቤ ይፋ ማድረግ እፈልጋለሁ። ለዚህ ውሳኔ ያበቃኝ ዋነኛው ምክንያት በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ካለው ተጨባጭ ነባራዊ  ሁኔታ ጋር የተያያዘ ነው። ነፃ፣ ሰላማዊና ፍትሐዊ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችል ምቹ መደላድል አለመኖሩ እና በፖርላማ ውስጥ ተጨማሪ 5 ዓመታትን በመቆየቴ ለህዝቤ የሚያበረክተው የረባ ጥቅም የሌለው መሆኑንም ተረድቻለሁ። ስለዚህ የ6ኛው ዙር ፓርላማ እስኪጠናቀቅ ድረስ ባሉት ጥቂት ወራት የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደራሴነት ስራየን ቀጥየ ሰኔ መጨረሻ ላይ የዚህን ዙር የአገልግሎት ዘመኔን የማጠናቅቅ ሲሆን፤ ወደፊት ሀገሬን እና ህዝቤን እንዴት ለማገለግል እንደምፈልግ የማሳውቅ ይሆናል። እስከ አሁኗ ሰዓት ድረስ በጽናት አብራችሁኝ ለቆማችሁ ቤተሰቦቼ፣ ጓደኞቼ፣ ውድ የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች፣ ለአማራ ሕዝብና ለመላው ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ ምስጋናዬ የላቀ ነው። እግዚአብሔር ይባርካችሁ፣ ህዝባችንን እና ሀገራችንም ይጠብቅልን! ደሳለኝ ጫኔ ዳኜው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል

አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ግዙፉ ላስታ አሳምነዉ ኮር እሸት ክፍለ ጦር ከአዉደ ዉጊያ ጎን ለጎን ጥልቅ ተሐድሶ አደረገ!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)  ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ በግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ስር የሚገኘው እሸት ክፍለ ጦር ለተከታታይ ሶሰት ቀናት በጥልቀት ከገመገመ በኋላ ሁሉን አቀፍ ተሐድሶ ካደረገ በኃላ የአመራር ሪፎርም ስራ ሰርቷል ። በተሐድሶው ላይ የተገኙት የምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ም/ወታደራዊ አዛዥ እና የላስታ አሳምነዉ ኮር ሰብሳቢ  አርበኛ ወንድሙ ማሩ ፣የላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ስትራቴጅክ ጉዳዮች ኃላፊ አርበኛ ተመቸ ቢራራ እና ሌሎች የኮር አመራሮች ተገኝተዉ ለሰራዊቱ አቅም ግንባታና ማበረታቻ የሰጡ ሲሆን ሰራዊቱም የነበሩባቸውን ጥቃቅን ክፍተቶች እንደሞሉበት ታውቋል። እሸት ክፍለ ጦር ወቅቱን የዋጄ በግዳጅ አፈፃፀም የላቀ ሰራዊት እየገነባ ያለ ክፍለ ጦር ሲሆን ከተራ ተዋጊ አባል እስከ ክፍለ ጦር መሪ ቅልቅልና አዲስ አደረጃጀት በመስራት ለቀጣይ ግዳጅ በወትሮ ዝግጁነታቸው እንደሚገኙ አስታውቀዋል። በመጨረሻም የተመደቡት  አመራሮች  ይህን የተጣለብነን አደራ በአግባቡ ተወጥተን የአማራን ህዝብ የተደቀነበትን የህልዉና አደጋና ዘርፈ ቡዙ ችግሮች አላቀን አማራ በማንነቱ እማይሸማቀቅበት እና ሁሉን አካታች ይምትሆን ሀገረ መንግስት እንደምንገነባ ቃል እንገነባለን ሲሉ ቃለ መሃላ ፈፅመዋል። በዚህ ጥልቅ ተሐድሶ የክፍለ ጦሩ አመራሮች እንደሚከተለዉ ተዘርዝረዋል። 1.የክ/ጦር አዛዥ..... መቶ አለቃ በሪሁን ደምሌ 2. የክ/ም/አዛዥ ..... አርበኛ ፍቃድ አበባዉ 3. የክ/ጦር ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ.......አርበኛ ደሰላ ወንዴ 4. የክ/ጦር ወታደራዊ  አስተዳደር ኃላፊ.........10 አለቃ  አንደበት ወንድምነዉ 5. ዘመቻ ኃላፊ.............አርበኛ ኮስትር አሸነፍ 6 .  ሕ/ግንኙነት ኃላፊ......... መቶ አለቃ ደስታዉ አንባዉ 7. ፋይናስ አርበኛ ዮሐንስ አዱኛዉ (ጆን) 8.  የሰዉ ሃይል አርበኛ ቡግሳ ተስፋ 9.  ስልጠና ክፍል ኃላፊ ......አርበኛ ጌትነት አለምነዉ 10.  ሎጀስቲክ  ኃላፊ.......አርበኛ እያያዉ ደረሰ 11. ህግ ክፍል  ኃላፊ.........አርበኛ ጌታሁን ወዳይ 12.  ጤና መምሪያ ኃላፊ......አርበኛ አበበ ሞላ 13. መረጃና ደህንነት         .............. አርበኛ XXXX የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ(አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ደረበ መኮንን!! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ጥር 29/2018 ዓ.ም

ከመከላከል በቅፅበት ወደ ማጥቃት የተቀየረው የኃይሉ ከበደ ክፍለ ጦር ፋኖዎች በድል የታጀበ አስደናቂ ተጋድሎ! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር አካል የሆነው ጄኔራል ኃይሉ ከበዴ ክፍለ ጦር ፋኖዎች በወሰዱት አፀፋዊ ምላሽ የአገዛዙ ብልፅግና ሰራዊት በተወሰደበት መብረቃዊ ጥቃት ከበባ ውስጥ አስገብቼ አፍናለሁ ብሎ የተንቀሳቀሰው የጠላት ኃይል ራሱን ለመከላከል ተገዶ ሲደቆስ ውሏል። የአገዛዙ ብልፅግና ሰራዊት መነሻውን ከዋግ ኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ጋዝጊብላ ወረዳ ላልኪው ከተማ በማድረግ ወደ ዘውማርያም ቀበሌ በሦስት አቅጣጫ የተንቀሳቀሰ ሲሆን አካባቢው ኔትወርክ የሌለው በመሆኑ የክፍለ ጦሩን አመራሮችና ሜካናይዝድ አፍናለሁ ብሎ ጥር 27 ለ28/2018 ዓ/ም ሌሊት 8:00 ሰዓት ላይ ከቦታው በመድረስ ጠላት በድሽቃ፣ሞርተርና ብሬን የታገዘ ተኩስ የከፈተ ሲሆን እስከ ጥር 28/2018  ዓ/ም ቀን 6:00 ሰዓት ድረስ በተደረገው ከፍተኛ ትንቅንቅ አካባቢያቸውን ጠንቅቀው የሚያውቁት ፋኖዎቹ በመጣበት ሦስት አቅጣጫ የገባውን ኃይል በሦስት አቅጣጫ በመቁረጥ ጠላት እርስ በእርሱ እንዲመታታና ከፋኖዎች ጥይት የተረፈው ኃይል ራሱን እየተከላከለ ወደ መጣበት ተመልሷል። በተደረገው ከባድ ትንቅንቅ 23 የጠላት ኃይል ሲደመሰስ ከ30 በላይ ቁስለኛውን ይዞ ተመልሷል፤ ዘጠኝ ክላሽንኮፍ፣540 የክላሽ ተተኳሽ፣16 የእጅ ቦምብ፣ሰባት የደረትና አምስት የወገብ ትጥቅ ተማርኳል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር  ህዝብ  ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ መምህር ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ጥር 29/2018 ዓ/ም

ሰበር የድል ዜና!!! የአገዛዙ ወንበር አስጠባቂ ጥምር ሰራዊት በቋራ ምድር ተደመሰሰ! የመይሳው ካሳ 2ኛ ኮር 4ኛ ቀኑን ያስቆጠረ እልህ አስጨራሽ አውደ ውጊያዎችን በቀጠናው እየተፋለመ ከፍተኛ ድል እያስመዘገበ ይገኛል። በትናንትናው እለት ጥር 28/2018 ከሌሊቱ 8:00 ስአት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12:00 ስአት ቋራ ወረዳ አባድግሱ ከምትባል ቦታ የተሰራው ጀብድ በአገዛዙ ግብስብስ ሀይል ላይ ከፍተኛ ሽንፈትን እንዲያስተናግድ አድርጓል። በመይሳው ካሳ 2ኛ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ ማንዴላ እያዩና በኮሩ ከፍተኛ አመራሮች የተመራው ይህ አውደ ውጊያ ጠላትን ከበባ ውስጥ በማስገባት ክፉኛ ሲርበተበት ውሎ ያመሸ ሲሆን የፋኖ ሰራዊት አሰላለፍ: አድዋ ክ/ጦ ከጀርባ በስተምዕራብ ፣ የኮሩ ተወርዋሪ ከፊታውራሪ ገበየሁ ክ/ጦ ከተውጣጡ ሰራዊቶች ጋር በመሆን በቀኝ በኩል ፣ ኦሜድላ ክ/ጦ ነብሮ ብርጌድ በግራ በኩል እና ካራማራ ክ/ጦ አሳምነው ብርጌድ ከጠላት ፊት ለፊት ሆነው የተሰለፉ ሲሆን ፤ ይህ የፋኖ አሰላለፍ ያስደነገጠው የአገዛዙ የብርሀኑ ጁላ ደም መጣጭ ሰራዊት በጭንቀት መውጫ መግቢያ ሲያጣ በአንድ በኩል ከፊት ለፊት ለመውጣት ሙከራ ቢያደርግም የበረሀው ፈርጦች የአሳምነው ልጆች ወይ ፍንክች በማለት ትንቅንቁን አፏፉመውት የጠላት ሀይል ነብስ ውጭ ነብስ ግቢ ሆኖበት አዳሩን በእሳት አለንጋ ሲለበለብ አድሮ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሙትና ቁስለኛውን ይዞ ያልቻለውን በየቦታው እያዝረከረከ በየቦታው የድረሱልኝ ጥሪውን እየቀባጠረ ወደ መጣበት ወደ ፋርሽዋ ሊመለስ ችሏል። በዚህ አውደ ውጊያ የአገዛዙ ከፍተኛ አመራሮች 50 አለቃ ማዕረግ ያለው እስከ ወዲያኛው የተሸኘ ሲሆን በየቦታው ያዝረከረከውን አስክሬን የፋኖ ሰራዊት የአካባቢውን ማህበረሰብ በማስተባበር ሊቀብር ችሏል። በዚህ ልዩ ኦፕሬሽን የተገኘ ድል: ሙት = 36 ቁስለኛ = 45 የተማረከ የነፍስ ወከፍ መሳሪያ = 12 1የዲሽቃ አፈሙዝ ተተኳሽ = 650 የክላሽ በዚህ አንድ ሳምንት ከአገዛዙ ጥምር ሰራዊት ጋር በሚደረገው እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ አገዛዙ ከሽንፈት የማያድነውን የኔት ወርክ መዝጋት ዘመቻ እንደ አንድ አማራጭ በማድረጉ በግንኙነት ማነስ ከህዝብ ጀሮ ያላደረስናቸው አውደ ውጊያዎች የሚከተሉት ናቸው: 1.ጥር 26_27/2018 የአድዋ ክ/ጦ በጋዝጌ ቀጠና ሮብ ገበያ እና ኤረፍት በተደረገው የሁለት ቀን አውደ ውጊያ የአገዛዙ የመከላከያ ሰራዊት ተብየው እና ጋሻአጃግሬው ሚኒሻ ክፉኛ ሽንፈትን አስተናግዷል። በዚህ አውደ ውጊያ የአገዛዙ ጥምር ሰራዊት መነሻውን ሰሜን አቸፈር ሊበን ተነስቶ ወደ ጋዝጌ ቀጠና አርሶአደሩን ትጥቅ ለማስፈታት እና ሁለንተናዊ ጀኖሳይድ ለመፈፀም አስቦ ቢንቀሳቀስም የመይሳው ካሳ ፪ኛ ኮር አድዋ ክ/ጦ በተደረገው እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ ከፍተኛ ኪሳራን ከማስተናገዱ ባሻገር ከበባ ውስጥ ገብቶ እጅ መስጠት ሲጀምር በሁለት አቅጣጫ ከጃዊ ጃይማላ እና ከአለፋ ሻሁራ ተጨማሪ ሀይል ደርሶ ሊያስለቅቀው ችሏል። በሁለት ቀን አውደ ውጊያ የተገኘ ድል: ከ20በላይ የታሰሩ ንፁሀን አርሶአደር መሳሪያ አላችሁ አስረክቡ በማለት በግፍ የታሰሩትን ማስፈታት ተችሏል። ከዚህ በተጨማሪ የአገዛዙ ሰራዊት ሙት እና ቁስለኛ እንደሚከተለው ይሆናል። ሙት = 30 ቁስለኛ =ከ38 በላይ 5 ምርኮኛ ሰራዊት የነፍስ ወከፍ መሳሪያ = 10 ከ3000በላይ ተተኳሽ የአንድ ሬጅመንት ሙሉ የእጅ ስልክ 2.ስቦ በመምታት ኦፕሬሽን ከአድዋ ክ/ጦ ፣ ከፊውታራሪ ገበየሁ ክ/ጦ እና ከኮሩ ተወርዋሪ በተውጣጡ የፋኖ ሀይሎች የአገዛዙ ሰራዊት ከአባድግሱ ወደ ባርባስ ወደ ምትባል ገዥ ቦታ ለኩሶ ወደ ኃላ በመውጣት የሙት ወረዳ ላይ/ባርባስ ጥር 26/2018 ከቀኑ 9:00 ስአት ጀምሮ ለ2ስአት ያህል በተደረገው አውደ ወጊያ የጠላት ሀይል ኩምሽሽ ብሎ ሙት እና ቁስለኛ በመሆን እንደ ገና ወደ ኃላ አባድግሱ ወደ ምትባል ቦታ ሊመለስ ችሏል። በዚህ አውደውጊያ የተገኘ ድል: ሙት = 5 ቁስለኛ = 12 3.በአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ ነጋዴ ባህር ከተማ አቸራበር በፊታውራሪ ገበየሁ ክ/ጦ ታጠቅ ብርጌድ 2ኛ ሻለቃ ቃኝ በሆነችው ሻንበል1 አንድ አስደማሚ ኦፕሬሽን ተደርጓል። ለአገዛዙ ሰራዊት አጋር የሆነው ሆድ አደር ሚኒሻ መነሻውን ከጭልጋ ወረዳ ወደ ነጋዴ ባህር ሲንቀሳቀስ ቀድመው መረጃን በማፈንፈን የሻለቃዋ ቃኝ በፍጥነት ደፈጣ በመያዝ በሚኒሻው ላይ መብረቃዊ ጥቃት በማድረስ ከቦታው መሰወር ችላለች። በዚህ ልዩ ኦፕሬሽን የተገኘ ድል: ሙት = 5 ቁስለኛ = 8 5 የነፍስ ወከፍ መሳሪያ እስከ መሉ ትጥቁ ይህ በእንዲህ እንዳለ ፈርጣጩ የአብይ ወንበር አስጠባቂ ጥምር ሰራዊት በማፊያ አመራሮች እየተመራ ፋኖን እናፅዳ እያለ እራሱ እየፀዳ የሀገሪቱን ወጣት በስሜት በሀገር መከላከያ ስም እየነገደ አማራ ላይ የተሰጠውን የአውሬውን ተልእኮ ለመፈፀም ቢሞክርም ከመጥፋት ግን አላዳነውም፤ የሀገሪቱን እንቁ ሀብት እያግበሰበሰ የወጣቱን ደም እየለገሰ በስልጣን መቆየት እንደማይቻል ክንደ ብርቱው የፋኖ ሰራዊት የሚያስመዘግበው ውጤት ማሳያ ነው። ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ መይሳው ካሳ ፪ኛ ኮር   ጥር 29/2018

ታጋይ ይሞታል ትግል ግን ይቀጥላል!! በደቡብ አማራ ቀጠና ​በመርሐቤቴ ወረዳ፣ በየይድመቆ መርከዥ ቀበሌ፣ ልዩ ስሙ ሞሐርባ በተባለ ስፍራ፤ የአንድ ጀግና ታሪክ በደም ተጻፈ። አርበኛ (ጎንደሬው አልታዩ) የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ፣ የደቡብ አማራ ቀጠና፣ አሳምነው ዕዝ፣ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ ኮር፣ ናደው ክፍለጦር ስልጠናና ክህሎት መምሪያ እንደ እሱ ብዙህ ጀግኖችን ያፈራ አዋጊ ተዋጊ የመከላከያ ተመላሽ ኮማንዶ የነበረው አርበኛ ጎንደሬው አልታዩ አጥሌ በሚባል የዛው አካባቢ ተወላጅ ባንዳ ሚኒሻ ተመርቶ ከመጣው የአረመኔው አብይ አህመድ መከላከያ ሰራዊት ኃይል ጋር ገጥሞ የጀግንነት ጥግ ምን እንደሆነ ለዓለም አሳይቶ በትናንትናው ዕለት በክብር ተሰውቷል። ​ ​ለአላማው በቁርጠኝነት እና በጀግንነት ሰማዕትነትን የተቀበለው ይህ አንበሳ፣ "እኔ ልሙት አንቺ ግን ሰንበቺ ፤ አለሁልሽ ሀገሬ አንቺ አትሙቺ" የሚለውን ቃለ መሀላ በልቡ ሰንቆ በእሳት ሊፈተን ገባ። ለምን እንደሚዋጋ የማያውቀውን፣ ግራ የተጋባውንና የሕዝብን ብሶት የማይረዳውን የገዥውን ሥርዓት ሠራዊት ፊት ለፊት ተጋፈጠው። ​"እኔ ወድቄ አንቺ ግን ሰንብቺ፣ አለሁ ሀገሬ አንቺ አትሙቺ፤ አንቺ ሙቺልኝ እኔ ጎሽዬ፣ ወጥቶ የለም ወይ ሰንደቅሽን ብዬ" ​ብሎ በሞቱ ቆርጦ ከወጣው ከዚህ ረመጥ ፋኖ ጋር የገጠመው ጠላት፣ የእሳቱን ወላፈን መቋቋም አልቻለም። ​ወትሮም ወርቅ በእሳት ተፈትኖ ያልፋልና፣ ይህ ልበ ሙሉ ጀግና ለአንድ ሰዓት ያህል ብቻውን ሆኖ እሳት በሚተፋው አፈሙዝ ጠላትን አርበደበደ። 6 ጠላትን ጥሎ፣ ከ5 በላይ አቁስሎ ታሪኩን በወርቅ ብዕር ጻፈ። በመጨረሻም ጠላት በእጁ እንዳይነካው፣ በገዛ ጥይቱ ክብሩን ጠብቆ በጎማ ምድር የሰማዕትነትን አክሊል ደፋ። ​የፈሪዎች ክፋት​ ገደልን እንዳይሉ ሞተው አገኟቸው፣ ማረክን እንዳይሉ ሰው የለ በእጃቸው" እንዲሉ፤ ጀግናው ካለፈ በኋላ እንኳን አስክሬኑ ያስፈራቸው ፈሪዎች፣ የተለመደውን የጭካኔ ተግባር በሬሳው ላይ ፈጽመው ውርደት በተሞላበት ቆራርጠው ጣሉት። ​ታሪክ እሱንና መሰል የቁርጥ ቀን ልጆችን መቼም አትረሳም፤ በትውልድ ዘንድ ስማቸው እየታወሰ ለዘላለም ይኖራሉ። በጀግኖች ደም የሕዝባችን ነፃነት እውን ይሆናል! ​ክብር ለሕዝብ ነፃነት ለተሰዋው ሰማዕታት! ​ድል ለአማራ ሕዝብ!!!!

መንፈሶች ነን!! የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን ከምሽቱ 4:45 በአምበር ከተማ በፈፀመው ኦፕሬሽን መርጌታ ጌታነህ ያየህ እና ፈንታ አበነህ የተባሉ ባንዳዎችን አፍነው በማውጣት አስደናቂ ጀብድ ፈፅመዋል። ጥር 29/2018 ዓ.ም =================================== መንፈሶች የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን ከምሽቱ 4:45 በአምበር ከተማ በወሰደው አስደናቂ ኦፕሬሽን ፈንታ አበነህ የተባለውን የሚኒሻ ብሬን ተኳሽ እና የጠለት የመረጃና ደህንነት አባል በመሆን የአረመኔውን ሰራዊት ከፊት በመሰለፍ መንገድ በመምራትና በርካታ ንፁሐንን እየጠቆመ ሲያሳስር ሲያስረሽን የነበረውን መርጌታ ጌታነህ ያየህን በቁጥጥር ስር በማዋል ከባዱን ተልዕኮ በብቃት ተወጠዋል። የአረመኔው ሰራዊት የሚመካባቸውን አገልጋዮችን በማናጠል ተደጋጋሚ ጥቃት የፈፀመው የኮሩ አዳኝ ቡድን ከአፍታ ቆይታ በኋላ በደብረ ማርቆስ ከተማ ከሌሊቱ 5:10 በወንቃ ትምህርት ቤት በመሸጉት ሚኒሻዎች ላይ በፈፀመው የቦንብ ጥቃት 2 (ሁለት) ቀንደኛ ሚኒሻዎች ሲገደሉ 4(አራት ) ከባድ ቁስለኞች ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸው ተረጋግጧል። በቀጠናው አዲስ ክስተት የሆነው 206ኛ ኮር በሞት አይፈሬ ነበልባል ተዋጊዎችና በጀብደኛ የሰራዊት አባላቱ አኩሪ ድል እያስመዘገበ ሲሆን ከትናት በስተያ በአድማ ብተናና የፖሊስ አሰልጣኝ የሆነውን ፻ አለቃ በየነ ጌትነትን በመግደል በደብረ ማርቆስ ከተማ በመሸገው የአረመኔው ሰራዊትና ካድሪ ላይ ከፍተኛ ሽብር መልቁም የሚታወስ ነው። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

አስቸኳይ የጥንቃቄ መልዕክት ለመላው የፋኖ አመራሮች!" ​"ከብልፅግና የደህንነት መሥሪያ ቤት (ከቁጥር 604) ለፋኖ አመራሮች ስልክ እየተደወለ ይገኛል። በመሆኑም ማንኛውም የአመራር አካል ከዚህ ቁጥር የሚመጣን ጥሪ በፍጹም እንዳያነሳ እና አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ እናሳስባለን። ይህ መረጃ ለሁሉም አመራሮች እንዲደርስ በከፍተኛ ፍጥነት 'ሼር' (Share) በማድረግ ተባበሩ።" ​ ​ይህ መልዕክት ለምን አስፈላጊ እንደሆነና ሊከተሉ የሚችሉ አደጋዎችን በሦስት ዋና ነጥቦች ማየት ይቻላል፡ ​1. የደህንነትና የመረጃ ጥበቃ ​የደህንነት መሥሪያ ቤቶች አጭር ቁጥሮችን (እንደ 604) ተጠቅመው የሚደውሉት መረጃ ለመሰብሰብ ወይም የአንድን ግለሰብ ማንነት ለማረጋገጥ ሊሆን ይችላል። ስልኩ በሚነሳበት ጊዜ ተደዋዩ ያለበትን ትክክለኛ ቦታ (Location) በቴክኖሎጂ ለመለየት ስለሚያመች፣ ጥሪውን አለማንሳት ለደህንነት ሲባል ተመራጭ ነው። ​2. የስነ-ልቦና ጫና (Psychological Tactics) ​እንዲህ ያሉ ጥሪዎች በአመራሮች መካከል ጥርጣሬን ለመፍጠር፣ ግራ ለማጋባት ወይም "ድርድር እንጀምር" በሚል ሽፋን መረጃ ለማውጣት ሊደረጉ ይችላሉ። ጥሪውን ባለመቀበል የጠላትን የመረጃ ምንጭ መዝጋት ይቻላል። ​3. የመረጃው ተደራሽነት (Urgency) ​"ሼር በፍጥነት ካልተሰራጨ፣ አንድ ወይም ሁለት አመራሮች ባለማወቅ ጥሪውን አንስተው ለአደጋ ሊጋለጡ ስለሚችሉ ነው። በመሆኑም መረጃውን በየደረጃው ላሉ የአደረጃጀት መዋቅሮች ማድረስ አስፈላጊ ነው። ​በተጨማሪም ለጥንቃቄ ያህል፦ አመራሮች የዲጂታል ደህንነታቸውን ለመጠበቅ ስልካቸውን በየጊዜው "Airplane Mode" ላይ ማድረግ ወይም ኢንተርኔት በማይጠቀሙበት ሰዓት መዝጋት ይመከራል። ❤Dawit fano አፋብን የመኖር ነፃነት ድርጅታዊ ቤታች የቴሌግራም ገፃችን👉 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk