ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Открыть в Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Больше3 954
Подписчики
+22224 часа
+3937 дней
+1 35930 дней
Архив постов
ጀነራሎች እና የክ/ጦር አዛዦች የተሰው የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ደሞዝ ለ6 ወራት ይቀበላሉ።
206ኛ ኮር ጥር 28/2018 ዓ.ም
===================================
አለሙ አንዳርጌ ይባላል የምዕራብ ዕዝ 401ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር ፋይናስ ቡድን ኃላፊ ሲሆን ከአረመኔው ሰራዊት በመክዳት 206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር ተቀላቅሏል። ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ የመከላከያ ሰራዊት በከፈታቸው የእርስበርስ ጦርነቶች ሁሉ የተሳተፈው አለሙ አንዳርጌ ለአምስት አመታት በቀጠለው ውጊያ የመከላከያ ሰራዊት የራሱን ህዝብ ከመጨፍጨፍ ባለፈ አንዳችም ለውጥ እንዳላመጣ ይናገራል።
በተለያዩ ከተሞች በተለይም ከኦሮሚያና ደቡብ ታፍሰው ወደ ጦርነት የሚማገዱ ታዳጊዎችን ሞት ተመልክቻለው የሚለው ነባሩ ወታደር ከማሰልጠኛ ወጠው ወደ ግንባር የተሰለፉ ምልምል ወታደሮች እልቂት በመከላከያ ሰራዊት ታሪክ እጅ አስከፊ እንደሆነም መስክሯል።
በአለፉት 3 አመታት ከአማራ ህዝብ ጋር በተደረገው ውጊያ የሰራዊቱ ሞትና ፍለስት ከቁጥጥር ውጭ በመሆኑ ጀነራሎችና የክ/ጦር አዛዦች የተሰው የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ደሞዝ ለ6 ወራት በማንቀሳቀስ ለራሳቸው ጥቅም እንደሚያውሉ ባደረግነው የፋይናስ ምርመራ ውጤት ማረጋገጡን ተናግሯል።
የምዕራብ ዕዝ 401ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር ፋይናስ ቡድን ኃላፊ በመሆን ለሶስት አመታት ያገለገለው አለሙ አንዳርጌ በንፁሃን ፍጅትና ሰቆቃ መካከል የሚደረገውን ጦርነት እንደ ትልቅ ካምፓኒ የሚጠቀሙት የጦር መኮንኖችና ጀነራሎች በጦር መሳሪያ እና በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ንግድ እንደበለጸጉ ገልጿል።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
በስቦ መምታት የውጊያ ታክቲክ የጠላት ብልፅግና ወታደርን ወሽመጥ በመቁረጥ ውጤታማ ድል ተመዘገበ!
በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 1 ባለሽርጡ ክፍለጦር ላይ ጥቅታ ለማድረስ ከጉቢሳ ወደ ኮለቦ፣ ከጭሰ አባሊማ ወደ ሲልኮ፣ከጊራና ወደ ጉባ ፣ከመርሳ ወደ ሀብሩና ፋጂ የተንቀሳቀሰው የጠላትን ሀይል በቀን 26/05/2018 ከኮለቦና ሩጋ ያለውን የጠላት ሀይል ስቦ በማስገባት መነዮ ቀሊና ላይ ምሽት 1:30 ላይ የጠላትን ሀይል ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ታላቅ ድል ተጎናፀፈ።
የባለሽርጡ ክፍለጦርን ሊያጠቃና የክፍለጦሩን ነባር ይዞታዎች ሊወር የመጣው የአብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት በአምስት አቅጣጫ ለማፈን ቢሞክርም የጠላትን የጥፋት እቅድ ቅዠት በማድረግ 50 ሙትና 78 ቁስለኛ በማድረግ ከትላንት ከጥዋቱ 12:30 እስከ ዛሬ 27/05/2018 ዓ.ም በቆየ አውደ ውጊያ የጠላትን ከበባ ያለምንም መስዋዕትነት በአርበኛ እንድሪስ ጉደሌና በሌሎች በሳል የክፍለጦሩ ወታደራዊ ጠበብቶች በመስበር በጥላት ላይ ከፍተኛ ስብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ ማድረስ ተችሏል።
በዚህ አውደ ውጊያ የተበሳጨው የጠላት ሀይል በደቡብ ወሎ ዞን ተወለደሬ ወረዳ ሲልኮ እየተባለ በሚጠራው ቦታ 450 የሚደርሱ ወጣቶችን፣ አርሶ አደሮችን እና የቀን ሰራተኛዎችን በማፈን ስልጠና ሰልጥናችሁ አገራችሁን ትጠብቃላችሁ በሚል ሰበብ ወደ ማጓሪያ ቀጠና አስገብቶ ፋኖን ማረኩ በሚል የሀሰት ዶክመንተሪ ዝግጂት ላይ ይገኛል።
በተያያዘም በሀይል ላፈናቸው ንፁሀን በየቤቱ እየገባ የግል ታጣቂ ግለሰቦችን መሳሪያ ለማስወረድ ድንገተኛ ፍተሻና ድብደባ እያካሄደ ይገኛል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበር ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምኒልክ ዕዝ
ጥር 28/2018 ዓ.ም
#የድል_ዜና‼️
አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ነበልባል ክፍለ ጦረ በባንዳ ላይ ድል ተቀዳጀ !!
ጥር 28/2018 ዓ.ም አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ነበልባል ክፍለ ጦር ጥላት ላይ ብሎም የፈረጃቸውን የከተማ ውስጥ አውደልዳይ ሆድ አደር ባንዳ ሚሊሻዎችን ማፅዳቱን አጠናክሮ ቀጥሎበታል ።
ይህም በከተማ ውስጥ ህዝብን ሲያስርና ሲረሽን ፥ ሴቶችን በጅምላ ሲያስደፍርና የፈለገውን ሲያደርግ እንዲሁም ንብረት ሲዘርፍና ሲያዘርፍ፤ በከተማው ላይ ከመጣ ከሄደው የብልፅግና ሰራዊት ጋር በማበር በህዝብ ላይ የመከራ ዶፍ ሲያወርድ በነበረው በሚሊሻው አቶ አስታጥቄና በግበረ አበሮቹ ላይ የለመደውን ህዝብን ለማደናገርና አለቃነቱን ለማሳወቅ ታጅቦ አረርቲ ሸዋገነት ኬላ ሲንቀሳቀሱ በተደረገ የቦንብ ጥቃት
1ኛ. ሶስት ሚሊሻ ፣ሚሊሻው አቶ አስታጥቄ እና አጃቢዎቹ በፋኖ ተደምስሰዋል
። አጃቢዎቹ፦
- አሰፋ ጥላሁን እና
- ተስፋ የተባሉ ሚሊሻዎች እንዲሁም አንድ ለጊዜው ስሙ ያልታወቀ የአስታጥቄ አጃቢ ሚሊሻዎች እስከ ወዲያኛው የተሸኙ እና የተደመሰሱ ናቸው ።
2ኛ. አንድ ለጊዜው ስሙ ያልታወቀ የፖሊስ አባል የተደመሰሰ ።
3ኛ. ሁለት ፻ አለቃ የነበሩ የመከላከያ ሰራዊት አባሎች አብረው የተደመሰሱ ሲሆን፤
የባንዳዎች ቁንጮ የሆነው ሚሊሻው አቶ #አስታጥቄ በደረሰበት የቦንብ ጥቃት ሆዱ እንደ አሪዎስ ተዘርግፎ በሆስፒታል በማጣር ላይ እንደሚገኝ የውስጥ አዋቂዎች መረጃውን አድርሰውናል ።
ይህ ግዳጅ እስካሁን ከተደረጉት የተለየ እና አስደናቂ ጀብድ የተሰራበት ሲሆን ለተቀሩትም ከነበልባል ክፍለ ጦር አናብስት ፋኖዎች ማምለጥ እንደማይችሉ ማስተማሪያ ጭምር ነው ሲሉ የነበልባል ክፍለ ጦር አመራሮች ገልፀዋል፤ ሲል አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር የነበልባል ክ/ጦር ሪፖርተራችን አርበኛ እንግዳ መረጃውን አድርሶናል ።
© ዘገባው፦ አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር አርበኛ ጋዜጠኛ አበባየሁ ሰይፈ ።
አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ህ/ግንኙነት መምሪያ‼️
28/ዐ5/2018 ዓ.ም
የሁሉም ጥያቄ መልስና መፍትሔ ያለው 4 ኪሎ ብቻና ብቻ ነው ሌላው ወሬ ማብዛት ነው።
ራያም በለው፣ወልቃይትም በለው፣መተከልም በለው፣ደራም በለው አዲስ አበባ በረራም በለው የወለጋ ጉዳይም በለው የሁሉም ጥያቄዎች ሊመለሱ የሚችሉት ስልጣነ መንበሩን ስትቆጣጠር ነው ከዛ ውጭ እየተከባለለ እየተከባለለ ሌላ ክፍለ ዘመን ከመጨመርና ስቃይን ከማራዘም ውጭ የሚመጣ መፍትሔ የለም።
የብልፅጥና መንግስት ወልቃይትን ጭፍር አድርጎ እስከ ዛሬ የያዘው ለአማራ አስቦ ሳይሆን ለራሱ ፖለቲካ መስሪያ አስቦ ነው ምክንያቱም የወልቃይት ጉዳይ የብዙ ሀገራት ፖለቲካ እጅ ያለበት ግዛት በመሆኑ ከእነዚህም እራሱ ብልፅግና አለበት፣የአማራ ብልፀግና ሉሌው ከለበት፣የትግራይ እጅ አለበት፣የኤርትራ እጅ ከለበት፣የሱዳን እጅ አለበት፣የግብፅ እጅ አለበት እንዲሁም የምራባዊያን እጅ አለበት ዋናው ተዋናይ የአሜሪካ እጅ አለበት ተመልከቱ እንግድህ የዚህ ሁሉ ብቻ ላይሆን ይችላል ሌላም እኛ የማናቀው ሀይልም ይኖርበታል ስለዚህ መንግትስም ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ ጨፍሮ የያዘው የራሱ የብልፅግና አስፈላጊና እስትራቴጅክ ቦታ ሁኖበት ነው።
ስለዚህ የአማራ ጉዳይ በአራት ኪሎ ተጨፍሮ የተያዘ እንጅ ከዛ ከዚህ በሚሰነዘረው ጥያቄና ጦርነት ሊፈታ አይችልም ሊመለስና ዘላቂ መፍትሔ ሊመጣ የሚችለው መሰሪዎና ህዝብ ጨፍጫፊው ሀገር አፍራሹ ብልፅግና እስከወዳኛው ሰመገረሰስ ብቻና ብቻ ነው የዛኔ ነው እንግድህ የሀገሪቱ ህገ መንግስት የምትሉት ጥያቄ የሚነሳበትና ሊሻሻልም ጭራሹን መቀየርም የሚቻለው።
ስለዚህ ከላይ ከታች የሚቦኩ ነገሮች ለአማራ መፍትሔ የሚሆኑ አይደሉም ፋኖ ራሱን ችሎ አሁን የራሱን ድራፍት ሰርቷል በሰራው መሰረት ይታገላል ትግሉንም ዳር ደበር ያደርሳል የዛኔ ነው እንግድህ ኢትዮጵያ ሰላሟን ልታገኝ የምትችለው።
#ሰበር_መረጃ‼️
ወደ ኮንቦልቻ ሆስፒታል ብቻ የገባ ቁስለኛ ወታደር አሃዛዊ ቁጥር 53 መድረሱ ታውቋል።
ይህ የቁስለኛ ብዛት ከኮምቦልቻ ከተማ ሁለት የጦር ሄሊኮፍተሮች የቆሰሉ አመራሮችንና መስመራዊ አዋጊዎችን ጭነው ወደ አዲስ አበባ ከወሰዱት ውጭ ነው።
ዛሬ ጥር 28/2018 ዓ/ም እኩለቀን 6:40 ላይ ኮምቦልቻ ከተማ ያረፉት ሁለት የጦር ሄሊኮፍተሮች፡ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦችና መስመራዊ አዋጊዎችን ጨምሮ ከ47 በላይ ቁስለኛ ወታደሮችን ወደ አዲስ አበባ ጭነው መውሰዳቸውን የአይን እማኞች ለመረብ ሚዲያ ተናግረዋል።
የወግዲ ወረዳ ሆስፒታልና ጤና ጣቢያዎች ማስተናገድ ከሚችሉት በላይ በቁስለኛ ወታደሮች ተጨናንቀዋል።
ፋኖ በአከባቢው ከባድ የሆነ የሽምቅ ጥቃት እየፈፀመ በመሆኑ በወግዲ የሚገኙ ቁስለኛ ወታደሮችን ወደ ደሴና ኮምቦልቻ ወስዶ ለማሳከም አዳጋች ሁኔታ ፈጥሯል።
በዚህም ምክኒያት፡ ወግዲ ጫቃታ ላይ አንዲት የጦር ሄሊኮፍተር ካረፈች በኋላ በውጊያ የቆሰለ አንድ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥን ጨምሮ ሌሎች ቁስለኛ መስመራዊ አዋጊዎችንና አባሎችን ጭና በጋስጫና ደገር አቆራርጣ ወደ ሸዋ አዲስ አበባ መብረሯን ከሰዓታት በፊት ጣቢያችን መረብ ሚዲያ የአይን እማኞችን ዋቢ አድርጎ መዘገቡ አይዘነጋም።
ትናንት አመሻሹን ከፍተኛ ቁጥር ባለውና የከባድ መሣሪያ ሽፋን እንዲሁም የድሮን ክትትል በሚደረግለት ሠራዊት የታጀበ በመቶዎች የሚቆጠር ቁስለኛ ወታደር ወደ ደሴና ኮምቦልቻ ተወስዷል።
በተመሣሣይ ዛሬ ማለዳም እንዲሁ በርካታ ቁስለኛ ወታደር ወደ ደሴና ኮምቦልቻ የተወሰደ ሲሆን፡ በደሴ ከተማ ከ74 በላይ ወታደሮች ሕክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ የመረብ ሚዲያ ወታደራዊ ምንጮች ገልፀዋል።
በኮምቦልቻ ከተማም በተመሣሣይ፡ ዛሬ ማርፈጃውን ከተወሰዱ ቁስለኞች ጋር በድምሩ 53 ወታደሮች ሕክምና እየተደረገላቸው ሲሆን፡ ከዚህ በተጨማሪ እኩለቀን ላይ ሁለት የጦር ሄሊኮፍተሮች ከ47 በላይ ቁስለኞችን ጭነው ወደ አዲስ አበባ መብረራቸውን ጣቢያችን ያነጋገራቸው የአይን እማኞች ገልፀዋል።
በሁለቱ ሄሊኮፍተሮች ተጭነ ከተወሰዱት ቁስለኞች መካከል የሰሜን ምስራቅ ዕዝና የ11ኛ ዕዝ እንዲሁም በአየር ወለድ ኮማንዶ መምሪያ ከፍተኛ አዛዦች እንደሚገኙበት ተጠቁሟል
28/ዐ5/2018 ዓ.ም
+1
ታላቅ የቅንደሻ ዜና በደብረማርቆስ ከተማ
በ24ኛ ክ/ጦር ልዩ የከተማ ኦፕሬሽን የአገዛዙ ዋና ቀኝ እጅ እስከመጨረሻው ተሸኝቷል
ጥር 27/2018 ዓ.ም
በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር ወታደራዊ አመራር ሰጭነት ጥር 26/ለ27 /2018 ዓ.ም ወደ ምስ/ጎጃም ዞን ደብረማርቆስ ከተማ ልዩ የከተማ ኦፕሬሽን ፈፃሚዎችን አስርጎ በማስገባት የአገዛዙ ገረድ ቀኝ ዕጅ ራሱን የሰላም አስከባሪ ኮማንድ ፖስት ብሎ በመሰየም በዞኑ የአድማ ብተና የሚሊሻና የህዝባዊ ፖሊስ አሰልጣኝ የነበረውን# መቶ_አለቃ_በየነ_ጌትነት የተባለውን ጠብደል ባንዳ ደብረማርቆስ ከተማ በተለምዶ አባብዙነህ ጉርድ ተብሎ ከሚጠራው ቦታ ቤት ለቤት ሲያውደለድል በ24ኛ ክ/ጦር ቆንጆዎች እርምጃ ተወስዶበታል!!
አዲስ ትውልድ አዲስ ተስፋ አዲስ አስተሳሰብ
የአፋብን ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
+1
የአገዛዙ ወታደሮች ከኦሮሚያ ክልል ለ8 ቀናት በመጓዝ ፋኖን ተቀላቀሉ
ጥር 28/2018 ዓ.ም
አገዛዙ ህዝብን እየዘረፈና እያሰቃዬ መሆኑን የተረዱት ናትናኤል ማስተዋል ፦ ሀይማኖት ሞላ እና ደረጀ መኳንንት የተባሉ የአገዛዙ ወታደሮች በዛሬው ዕለት ከኦሮሚያ ክልል ፍቸ ከሚገኘው 6ኛ ዕዝ 52ኛ ክ/ጦር 2ኛ ሬጅመንት 3ኛ ሻንበል የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦርን ከነ ሙሉ ትጥቃቸው እንድሁም በርካታ ጥይት ካዘናና ቦምቦችን በመያዝ ተቀላቅለዋል ።
በአዋባል ወረዳ 34ኛ ክ/ጦርን የተቀላቀሉት ወታደሮቹ አገዛዙ አማራ ላይ እያደረሰ ያለውን ዘርፈ ብዙ ጥቃት መረዳታቸውን እና እስካሁን በተሳሳተ መንገድ የቆዩ መሆናቸውን ገልፀው ከፋኖ ጎን ተሰልፈው ለመታገል ከኦሮሚያ ክልል ለ8 ቀናት በፈታኝ ሂደት ተጉዘው 34ኛ ክ/ጦርን መቀላቀላቸውን ገልፀዋል።
አድስ ትውልድ ! አድስ አስተሳሰብ ! አድስ ተስፋ !
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206 ኮር ህዝብ ግንኙነት
#የቅድመ_ጥንቃቄ_መልዕክት❗️
የአማራ ፋኖ አንድነት ብስራት ያስጨነቀው የብልፅግናው አገዛዝ በእጁ ላይ የሚገኙትን ሁሉንም ካርዶች አቃጥሎ በመጨረስ፣ ተጨማሪ አዲስ ስምሪት ለማድረግ አቅዷል። በመሆኑም:-
#1ኛ. ጠላት ፋኖ በሚያስተዳድራቸው በበርካታ ቦታዎት የኔትወርክና የኢንተርኔት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ አቋርጧል።
#2ኛ. የፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ ከኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን ተጨማሪ የገዳዩን አራዊት ሰራዊት ተባባሪ አካላት በማወያየት ወደ ሸዋ ለማዝመት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል።
#3ኛ. ከወሎ ቤተ አምሓራ ጠላት ከላላ እና ደገርን እያፀዳሁ ወደ ሸዋ እገባለሁ በማለት ከ2ቀን በፊት የቅዠት ዘመቻ መጀመሩ ይታወቃል፣ ለዚሕም ያመቸው ዘንድ በበርካታ ቀጠናዎች የኔትወርክ አገልግሎት ሙሉ በሙሉ እያቋረጠ ሲሆን "የዘመቻ ስያሜ የማያልቅበት ብልፅግና" ተጨማሪ የሞት ሽረት አድስ ዘመቻ ሊያደርግ እንዳቀደ የውስጥ መረጃዎች ያሳያሉ፣ በመሆኑም ውድ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የአፄ አምደ ፂዮን ኮር እና የክፍለጦር አባላተ እና አመራሮች በሙሉ የተለመደውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ወቅታዊ የጠላትን እንቅስቃሴ በሚገባ በመረዳት አስፈላጊወን ሁለ ገብ ጥንቃቄ በማድረግ የምርኮኛውን ሰራዊት ለማስተናገድ ከምታርጉት ከፍተኛ ዝግጅት ጎን ለጎን ከጠላት ከድተው በገፍ ፋኖን እየተቀላቀሉ ለሚገኙ የአገዛዙ ሰራዊት አባላት ከበቂ እንክብካቤ ጋር ከፍተኛ ጥንቃቄ በተሞላበት አያያዝ ታደርጉላቸው ዘንድ ኮሩ ወቅታዊ የጥንቃቄ መልዕክቱን ማስተላለፍ ይወዳል።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የአፄ አምደ ፂዮን ኮር መረጃና ደህንነት ክፍል
ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ምክትል መሪ አርበኛ ኢሳያስ ደመቀ የተላላፍ አስቸኳይ የጥንቃቄ መልክት!!
እንደሚታወቀው የአብይ አህመድ አገዛዝ ስልጣን ከያዘበት ማግስት ጀምሮ በአማራ ህዘብ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል አውጆ እየሰራ መሆኑ የሚታወቅ የምድር ሃቅ ነው።ሁኖም የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች ፍኖዎች እራሳቸውንና ህዝባቸውን ከዚህ ጥፋት ቡድን ለመከላከልና ነፃ ለመውጣት ለሶስት አመት ያህል ከአባቶቻችው በወረሱት ጀግንነት በእየተራራና ሸንተሩ በገባበት ገብተው እንዳይወጣ በማድረግ እየመከቱትና እየተፋለሙት አንድዬ ነፍሳቸውን እየሰጡ ይገኛሉ። ይሁን እንጅ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ፋኖዎችን ክንድ መቆቋም ያቃተው ተስፋ የቆረጠው የአረመኔው አብይ አህመድ አገዛዝ አዲስ እቅድ በመድፍ በሶስት አቅጣጫዎች ታንክ፣መድፍ እና ዙ-23 በማሰለፍ ወደ ሸዋ እያስገባ በመሆኑም ከአዲስ አበባ አቅጣጫ፦ በጫጫ በኩል ወደ መሀል ሸዋ፣ በአፋር ክልል በኩል፤በአንኮበርና በአልዩ አምባ እንዲሁም የምስራቅ ዕዝ የአብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ ኃይል በመላው ሸዋ ሁለት የጥፋት አላማ ይዞ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች ጀመሯል።
1. ለስልጠና" በሚል ስም ወጣቱን በጅምላ ለማፈስና ለጦርነት ማገዶነት ለማድርግ
2. የመከላከያ ሰራዊት የአማራ አድማ መከላከል፣ ፖሊስ እና ሚኒሻ አባላትን በማሰለፍ በከባድ መሳሪያ በመካናይዝድና አየር ሃይል በታገዘ የአማራን ህዝብ ለመጨፍጨፍ ተሰማርቷል የአየር ኃይሉ ታርጌት የሚያደርግባቸው የፋኖ ከፍተኛ አመራሮች፤ የፋኖ ሰራዊት ክምችት እና የመካናይዝድ መሳሪያዎች ያተኮረ ነው።
ይህ የጠላት እንቅስቃሴ የአማራን ወጣት ለማያባራ ጦርነት የሚዳርግ በመሆኑ፣ የአማራ ተወላጆች የመከላከያ ሠራዊት አባላት እና በአድማ መከላከል፣ፖሊስ ፣ሚኒሻ ከብልፅግና አረመኔው ሰራዊት ኃይል ጋር ተሰልፋችሁ በአማራ ወንድሞቻችሁና እህቶቻችሁ ላይ የሚዘመትበትን የጥፋት ዕቅድ ተፈጻሚ ከማድረግ እና ከታሪካዊ ተጠያቂነት እራሳችሁን እንድትቆጥቡ እናሳስባለን። የሕዝብን ደህንነት ለማስከበርና ከጥፋት ለመዳን፣ ከሕዝብ ጎን በመቆም ወደ ፋኖ እንድትቀላቀሉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
.በመላው ሸዋ ደቡብ አማራ ቀጠና የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት አቋርጦ በመላው ህዝባችን ላይ አረመኔያዊ የዘር ማጥፋት እንቅስቃሴዎች የጀመረ ሲሆን ። በቀጠናው የምትገኙ ፋኖዎች የመረጃ መረባችሁን በመዘርጋት የጠላትን ኃይል አከርካሪውን በመምታት አራሳችሁ ከአየር ኃይል ጥቃት በመከላከል የቀድሞ አባቶቻችሁን የድል ባለቤት እንድትሆኑ ስል መልክቴን አስተላፋለሁ።
በመጨረሻም መላው የሸዋ ወጣትና ሕዝብ አካባቢውን ነቅቶ እንዲጠብቅ፣ ከአረመኔው አብይ አህመድ ኃይል አፈሳ ራሱን እንዲከላከልና ወደ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የነፃነት ትግሉ እንድትቀላቀሉ ጥሪ እናቀርባልን።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!,ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ ምክትል መሪ አረበኛ ኢሳያስ ደመቀ
ጥረ 28/05/2018 ዓ.ም
እኛ ራስ በቅ ፖለቲካ የምናራምድ ህልውናችንን በክንዳችን የምናረጋግጥ አማራዎች ነን። እንደ አማችዝም የቁጭት ፖለቲካ አናራምድም። የመንደር ተንበርካኪዎች ሁነን ለመጣ ለሄደው ጫማ አንልስም ፤ እርስታችንን ለማስመለስ ከጠላት ብልፅግና ጋር ተሰልፈን አንማፀንም።
አርበኛ ዘመነ ካሴ በመተከል ቀጠና ካደራጀው ሠራዊት ጋር ያደረገው ንግግር 💪💪
ሰበር..በፋኖ የተመታው ወታደራዊ አዛዥ በሄሊኮፍተር ተጭኖ ወደ አዲስ አበባ ተወሰደ!
በምስራቅ ዐምሓራ ቀጠና ምዕራብ ወረዳዎች ሁለተኛ ቀኑን ባስቆጠረው ተጋድሎ ማዕረጉ በውል ያልታወቀ አንድ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ በፋኖ ስናይፐር ተመትቶ በሞትና በሕይወት መካከል ይገኛል።
ወታደራዊ አዛዡ ወደ ደሴ ተወስዶ እንዳይታከም የቀጠናው ዙሪያ ገባ በፋኖ ክርችም ተደርጎ በመዘጋቱ፡ የአዛዡን ሕይወት ለማትረፍ ዛሬ ጥር 28/2018 ዓ/ም ረፋድ 5:00 ሰዓት ገደማ በወግዲ ወረዳ ጫቀታ ላይ አንድ የጦር ሄሊኮፍተር ማረፉን የአይን እማኞች ለመረብ ሚዲያ ገልፀዋል።
የጦር ሄሊኮፍተሯ ቁስለኛውን ወታደራዊ አዛዥ ከጫነች በኋላ ካረፈችበት ጫቃታ በመነሳት፡ በጋስጫና በደገር አቆራርጣ ወደ ሸዋ አዲስ አበባ አቅጠጫ መብረሯንም መረብ ሚዲያ ያነጋገራቸው የአይን እማኞች አክለው ገልፀዋል።
አዛዡ ውጊያውን ሲመሩ ከነበሩ ዋና ዋና ወታደራዊ አዛዦች መካከል አንዱ እንደነበር የገለፁት ምንጮቻችን፡ የደረሰበት ጉዳት ከባድ ከመሆኑ የተነሳ ሕይወቱ ላይተርፍ ይችላል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
ዘውዱ ሰጣርጌ እና ብርጋዲየር ጄነራል ሞሲሳ እንዲሁም አንድ በአየር ወለድ ኮማንዶ ዕዝ የአንድ ኮር አዛዥ የሆነ የሌፍትናንት ጄነራል ማዕረግ ያለው ወታደራዊ አዛዥ፡ በሁለት ድሮን፣ በሦስት አየር መቃዎሚያና በሁለት ጄነራል መድፍ፣ በ10 ሞርተርና ቢኤም 107 እንዲሁም በ23 ዶሽቃ መሣሪያ ታግዘው ውጊያውን በዋናነት ሲመሩ እንደነበር መረብ ሚዲያ በትናንቱ ዜና እወጃው መዘገቡ ይታወቃል።
ከአየር ኃይሉ ጀምሮ በከባባድ መሣሪያዎች ታግዞ በሦስት ጄነራሎች እየተመራ ወደ ውጊያ የገባው ከ60 በላይ ተሽከርካሪ ሙሉ የአገዛዙ ኃይል፡ ከወደ ፋኖ የገጠመውን ጠንካራ የሆነ የፀረ መከላከልና የመልሶ ማጥቃት እርምጃን መቋቋም አቅቶት፡ ለሰዓታት ቆሞ መዋጋት በማይችልበት ሁኔታ ተሽመድምዶ እየፈረጠጠ ይገኛል።
(ምስል ከማህደር)
+1
1000 ወታደር አሰልፈው በለው ሲሉ የነበሩት ጀነራል በቀለ ዱጋሳ እና ሌሎች አራት የጦር መኮንኖች መገናኛ ሬዲዮናቸው በጀግኖቹ የአፋብን የጦር ጠበብቶች ተጠልፎ በአልሞ ተኳሾቹ እርምጃ ሲወሰድባቸው መሪዎቻቸው መገደላቸውን የሰሙት የጠላት ሀይሎች ሲደናበሩ ዙሪያውን የከበበው ድል ቁርሳቸው የሆነው የምንሊክ እዝ ሰራዊቶች 619 አንድ ሁለት ተብሎ የተቆጠረ የብልጽግናን ሰራዊት ላይመለስ ሲደመስሱት 24 ተማርኳል ሌሎቹም ተከበዋል በማይክራፎን እጅ ስጡ እየተባለ ነው። የተከበቡትን ለመታደግ ተጨማሪ ጦር ቢልክም ነገሩ ያልተዋጠላቸው የስርአቱ የጦር አመራሮች ወደኋላ ተመልሰዋል።
ብልፅግና የተራ ወታደሩን ክሬሳ ላሞራ በትኖ የአመራሮቹን እሬሳ ሰብስቦ ፈርጥጧል።
ድል ለአፋብን ሰራዊት ድል ለአማራ ህዝብት]
1000 ወታደር አሰልፈው በለው ሲሉ የነበሩት ጀነራል በቀለ ዱጋሳ እና ሌሎች አራት የጦር መኮንኖች መገናኛ ሬዲዮናቸው በጀግኖቹ የአፋብን የጦር ጠበብቶች ተጠልፎ በአልሞ ተኳሾቹ እርምጃ ሲወሰድባቸው መሪዎቻቸው መገደላቸውን የሰሙት የጠላት ሀይሎች ሲደናበሩ ዙሪያውን የከበበው ድል ቁርሳቸው የሆነው የምንሊክ እዝ ሰራዊቶች 619 አንድ ሁለት ተብሎ የተቆጠረ የብልጽግናን ሰራዊት ላይመለስ ሲደመስሱት 24 ተማርኳል ሌሎቹም ተከበዋል በማይክራፎን እጅ ስጡ እየተባለ ነው። የተከበቡትን ለመታደግ ተጨማሪ ጦር ቢልክም ነገሩ ያልተዋጠላቸው የስርአቱ የጦር አመራሮች ወደኋላ ተመልሰዋል።
ብልፅግና የተራ ወታደሩን ክሬሳ ላሞራ በትኖ የአመራሮቹን እሬሳ ሰብስቦ ፈርጥጧል።
ድል ለአፋብን ሰራዊት ድል ለአማራ ህዝብት
+1
ኤርትራ ነው ሲሉት ከጎንደር ብቅ ይላል፤ ሱዳን ነው ሲሉት ከቤኒሻንጉል ብቅ ይላል፤ ትግራይ ነው ሲሉት ከወሎ ብቅ ይላል። ይህ ሰው መንፈስ ሆነባቸው እኮ አቦ ይቻላል!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር አርበኛ ዘመነ ካሴ በተሳተፉበት ውይይት ለዓመታት በታጣቂወች ታግተው የነበሩ ሴቶችን ማስለቀቅ ተችሏል።
በመተከል ቀጠና በለተያዬ ጊዜ በነበሩ አገዛዙ በፈጠራቸው ግጭቶች ምክንያት በርካታ አማራወች ሲፈናቀሉ፣ ሲጨፈጨፉ እና ሲታገቱ የቆዩ መሆኑ ይታወቃል። ሊቀመንበሩ በቀጠናው ካሉ ታጣቂወች ጋር ባደረጉት ውይይት በባለፉት ዓመታት በተከታታይ በተከሰቱ በእነዚህ ግጭቶች አጋጣሚ እስከ አራት ዓመታት ድረስ ታግተው የቆዩ አስር ያህክል ሴት ወጣቶችን ለማስለቀቅ ተችሏል።
በቀጠናው ከሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ኃይሎች ኃይሎች ጋር ቀናትን የወሰደ ውይይት ያደረጉት አርበኛ ዘመነ ካሴ እህቶቻችንን ከታገቱበት ቦታ ተረክበው ወደ መኖሪያ አካባቢያቸው ሸኝተዋቸዋል።
በእለቱም አርበኛ ዘመነ ካሴ ተከታዩን መልዕክት አስተላፈዋል።
"እኛ አማራዎች ሰው ከሚፈጥረው የፖለቲካ ክፋትና ፀረ አማራ ርእዮት ጋር እንጅ ከሰው ልጆች ጋር ፀብ የለንም።ሰው ክቡር ነው። ርእዮታችን የሚቀዳውም ከዚህ የአስተሳሰብ ባህር ነው።እና ማንም ህዝብ ወገናችን ነው። (በዚህ ጉዳይ የጉምዝ ህዝብም)። ስለዚህ በመተከል በጉምዝና የአማራ ህዝብ መካከል፥ በሽናሻና የአማራ ህዝብ መካከል፥ በቤኒሻንጉልና የአማራ ህዝብ መካከል መገዳደልን ሊዘራ የሚሞክረውን የረጅም ጊዜ የጠላት አስተሳሰብ እየነቀልነው በቦታው ፍቅርንና አብሮነትን እየተከልን ነው።በዚህም የተነሳ ከድርጅቶች ጋር ጥሩ መቀራረብ ፈጥረናል።
በመሆኑም በተለያዬ ጊዜ በተነሱ ግጭቶች ምክንያት በጉምዝ ሃይሎች ከስራ ቦታቸው እየተያዙ እስከ አራት አመታት ታግተው የቆዩ አስር የአማራ ልጆችን ማስመለስ ችለናል። በዚህ ወቅት እህቶቻችን ተረክበን ወደ ቤተሰቦቻቸው እየላክን እንገኛለን።ይቀጥላል።"
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የተለያዬ ማንነት ካላቸው ኃይሎች ጋር የሚያደርገውን የአጋርነት እና የትብብር ስራ አጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን በዚህ ረገድ ድርጅታችን በኢትዮጵያ ህልውና፣ በህዝቦች አብሮነት፣ እና በአገዛዙ የጋራ ጠላትነት ላይ የተመሰረቱ ተጨባጭ ስራወችን አጠናክሮ የሚሰራ ይሆናል።
የአማራ ህዝብ የሰላም፣ የአንድነት፣ የአብሮነት እሴቶችን በሚያጎለብት መንገድ በሁሉም ማዕዘናት ለሚኖረው ህዝባችን ደህንነት አስፈላጊዉን ሁሉ ማድረጋችን ይቀጥላል።
