ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Kanalga Telegram’da o‘tish
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Ko'proq ko'rsatish4 039
Obunachilar
+22224 soatlar
+3937 kun
+1 35930 kun
Postlar arxiv
ሌላ የትም ቦታ የማያገኟቸውን የፋኖ አውደ ውጊያ መረጃዎች ይዞ በየዕለቱ ይቀርባል፣ በ30% ቅናሽ አሁኑኑ 1800 የደረሱትን ተከታታዮች ሰብስታክ ላይ ይቀላቀሉ። ሊንክ
ፋኖ ከወልድያ በቅርብ ርቀት በወሰደው የስቦ መምታት የጦር ታክቲክ በርካታ የአገዛዙ ወታደሮችን ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ድል ተቀዳጀ!
የፋኖ አባላቱ የአገዛዙ ወታደሮችን ከወልድያ ከተማ ጃርሣ መድኃኒአለም ተብሎ ወደ ሚጠራው የከተማዋ አከባቢ ስበው ካስገቡ በኋላ 360° በመክበብ እንዳይወጡና እንዳይሸሹ በማድረግ ዶግ አመድ አድርገዋቸዋል።
በአፋብን ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ ዐምሓራ ኮር1 አሳምነው ክ/ጦር ስር ከ4ኛ እና ከ5ኛ ሬጅመንት የተወጣጡ ጥቂት የፋኖ ኃይሎች ትናንት ጥር 27/2018 ዓ/ም የስቦ መምታት የውጊያ ታክቲክ ተጠቅመው በወሰዱት ብርቱ እርምጃ የጠላት ኃይልን አከርካሪ በመስበር ድል መቀዳጀታቸውን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።
በአሳምነው ስም የሚጠሩትና በአሳምነው ስም እየፎከሩ የጠላት ምሽግን የሚንዱት የፋኖ አባላቱ፡ ጠላትን በተደጋጋሚ ጊዜ በመቱበት ወልድያ ከተማ ዙሪያ ዛሬም የፋሽስቱ ሰራዊትን በአፈሙዝ እሳት ገርፈው ቀብረውታል።
የጠላት ኃይል ከየጁገነት ወልድያ መነሻውን አድርጎ በከተማዋ ዙሪያ ጃርሳ መድኃኒአለም ተብላ ወደምትጠራው አከባቢ ያቀና ሲሆን፡ የፋኖ አባላቱም መንገድ ከፍተው አሳልፈውታል።
የአገዛዙ ወታደሮች ጃርሳ ከደረሱ በኋላ የተተናኮሳቸው ኃይል ባለመኖሩ ድንጋጤና ጥርጣሬ ተጋብቶባቸው በአስቸኳይ አከባቢውን ለቀው ወደ ወልድያ ለመፈርጠጥ ሲሞክሩ፡ የፋኖ አባላቱ "መግባት እንጂ መውጣት የለም" በሚል የጥቃት ዶፍ አውርደውባቸዋል።
በዚህም በርካታ የአገዛዙ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ የተደረጉ ሲሆን፡ ከወልድያ መቻሬ ተጠምዶ ሲሰጣቸው በነበረው የከባድ መሣሪያ ሽፋን ተጠቅመው ሙትና ቁስለኛቸውን ተሸክመው ወደ ወልድያ ከተማ ፈርጥጠዋል።
የጠላት ብልፅግና ወታደራዊ ኃይል ወልድያ ዙሪያን ጨምሮ በምስራቅ ዐምሓራ ቀጠና በፋኖ በሚወሰድበት ጠንካራ እርምጃ፡ ለሰዓታት ቆሞ መዋጋት በማይችልበት ሁኔታ ተሽመድምዶ ከባድ የሆነ የሰብአዊና ቁሣዊ እንዲሁም ሞራላቂ ኪሳራን እየተከናነበ ይገኛል።
በሸዋ ደራ የተፈፀመ የግፍ ግፍ
ጥር 26 ቀን በደራ ወረዳ "ካራ ኦሮጎ" በተባለ ስፍራ በኦነግ-ሸኔ ታጣቂዎች የጭካኔ ጥግ የታየበት ግፍ ተፈፅሟል። ታጣቂዎቹ ንጹሃንን እያፈሱ ወደ እገታ ስፍራ ሲነዱ፣ አንዲት የ6ወር ጨቅላ ህፃን የታቀፈች ውብዬ ተፈራ ይተባለች እናትን ለይተው አቁመዋታል። ታጣቂዎቹም ጨቅላውን ሕፃን ከእናቱ እቅፍ ቀምተው ማንም በሌለበት ምድረ በዳ ጣሉት ልጇን ጥሎ መሄድ ያላስቻላት እናት ግን በእናት አንጀቷ እየተንስፈስፈች ልጄን እያለች እየጮኸች ተማጸነች ግፈኞች ግን ጩኸቷን ችላ ብለው ልጇን መሬት ላይ ጥለው እሷን በጉልበት ወደ ከእገታው ስፍራ መሳሪያ ደግነው ወደ በረሃው ነዷት።
በኋላም ወደ ጫካው በረሃ እየገፉ ሲሄዱ፣ እናቲቱ በሐዘንና በድካም በመዛሏና እነሱ ከሚጓዙበት ፍጥነት ጋር መሄድ ባለመቻሏ፣ እንደማይጠቅም ዕቃ እሷንም እንደ ልጇ መንገድ ላይ ጥለዋት ሄደዋል። ይህች እናት በታአምር ከአውሬ ተርፋ በስዎች እርዳታ ጉንደ መስቀል ገባች፣ የ6 ወር ጨቅላ ልጇ ግን መሬት ላይ ተጥሎ ቀረ እናትም የሐዘን ሲቃ እያሰማች የቁም ሞት ሞተች።
ይህ ሁሉ ድርጊት በሚፈፀምበት ወቅት የመንግስት የፀጥታ ኃይል በቅርብ ርቀት እያለ ምንም ዓይነት እርምጃ አለመውሰዱ ታጣቂዎቹ በነፃነት እንዲጨ*ፈጭፉ ፈቃድ እንደተሰጣቸው ማረጋገጫ ነው።
የአማራ ፋኖ አውደ ውጊያዎች ለመከታተል ከታች ያለውን ሊንክ ይወዳጁ!!
@abcdefghijklmnopqrstuvwxyz071167
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምስረታን አስመልክቶ የተዘጋጀው የውይይት መድረክ በበርካታ ሚዲያወች ለህዝብ እንዲደርስ ሆኗል።
ስርጭቱን ላስተላለፋችሁ መድረኩን ላስተባበራችሁ፣ ዝግጅቱ እንዲሳካ በተለያዬ መንገድ እገዛ ላደረጋችሁ፣ በፕሮግራሙ ላይ በመገኘት ጥያቄወችን በማቅረብ ጭምር ለተሳተፋችሁ የሚዲያ ሰወች እና ጋዜጠኞች ምስጋና እናቀርባለን።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ
የአረመኔው አብይ አህመድ ኃይል በመርሐቤቴ የፋኖ አመራር ቤተሰቦች ላይ እገታና የንብረት ውድመት አደርስ!!
የአረመኔው አብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ ኃይል የአማራ ፋኖዎችን ብትር መቋቋም ሲያቅተው ደቡብ አማራ ቀጠና መርሓቤቴ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር በበፍቃዱ ክፍለ ጦር ምክትል አዛዥ አርበኛ በላቸው እሸቴ ቤተሰቦች ላይ ያነጣጠረ የግድያ፣ የአፈና እና የንብረት ማውደም ድርጊት እየፈፀመ ይገኛል።
በመሆኑም ድርጊቱ የተፈጸመው መርሐቤቴ አውራጃ፣ ደራ ወረዳ ልዩ ስሙ ሰረር ኩላ አካባቢ ጥቃቱ የተፈጸመ ሲሆን ከአርበኛ በላቸው እሸቴ ጋር ያላቸውን የሥጋ ዝምድና መሠረት በማድረግ ሲሆን፤ በወቅቱ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚከተሉት ግፎች ተፈፅመዋል። ይሁንና የአርበኛው የቅርብ ቤተሰቦች የሆኑት አቶ ተሰማ ካሰኝ (አጎቱ) እና ወይዘሮ ፀሃይ ታለማ (የታናሽ ወንድሙ ባለቤት) ታፍነው ወደ ጉንዶ መስቀል ተወስደዋል።
እንዲሁም የአርበኛው አባት የሆኑት የአቶ እሸቴ አቢ ሶስት የቁም ከብቶች የተገደሉ ሲሆን፣ የመኖሪያ ቤት በአገዛዙ ኃይሎች ቃጠሎ ደርሷል። በተጨማሪ፣ ከጉዳዩ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ቤቶችም በቃጠሎ እንዲወድሙ አድርጓል። ጥቃቱ የተፈፀማባቸው ግለሰቦች ከፖለቲካ እንቅስቃሴ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የሌላቸው ነገር ግን የፋኖ ቤተሰብ ናችሁ በሚል ምክንያት የአገዛዙ ወንበር አስጠባቂ ኃይል የአሳምነው አናብሶቶችን ፊት ለፊት ገጥሞ ማሸነፍ ሲያቅጠው በህዝባችን ላይ ግፍ እየፈፀመ ይገኛል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!,ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
አርበኛ አማረ ታዘዘ
ጥረ 28/05/2018 ዓ.ም
ጀነራሎች እና የክ/ጦር አዛዦች የተሰው የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ደሞዝ ለ6 ወራት ይቀበላሉ።
206ኛ ኮር ጥር 28/2018 ዓ.ም
===================================
አለሙ አንዳርጌ ይባላል የምዕራብ ዕዝ 401ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር ፋይናስ ቡድን ኃላፊ ሲሆን ከአረመኔው ሰራዊት በመክዳት 206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር ተቀላቅሏል። ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ የመከላከያ ሰራዊት በከፈታቸው የእርስበርስ ጦርነቶች ሁሉ የተሳተፈው አለሙ አንዳርጌ ለአምስት አመታት በቀጠለው ውጊያ የመከላከያ ሰራዊት የራሱን ህዝብ ከመጨፍጨፍ ባለፈ አንዳችም ለውጥ እንዳላመጣ ይናገራል።
በተለያዩ ከተሞች በተለይም ከኦሮሚያና ደቡብ ታፍሰው ወደ ጦርነት የሚማገዱ ታዳጊዎችን ሞት ተመልክቻለው የሚለው ነባሩ ወታደር ከማሰልጠኛ ወጠው ወደ ግንባር የተሰለፉ ምልምል ወታደሮች እልቂት በመከላከያ ሰራዊት ታሪክ እጅ አስከፊ እንደሆነም መስክሯል።
በአለፉት 3 አመታት ከአማራ ህዝብ ጋር በተደረገው ውጊያ የሰራዊቱ ሞትና ፍለስት ከቁጥጥር ውጭ በመሆኑ ጀነራሎችና የክ/ጦር አዛዦች የተሰው የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ደሞዝ ለ6 ወራት በማንቀሳቀስ ለራሳቸው ጥቅም እንደሚያውሉ ባደረግነው የፋይናስ ምርመራ ውጤት ማረጋገጡን ተናግሯል።
የምዕራብ ዕዝ 401ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር ፋይናስ ቡድን ኃላፊ በመሆን ለሶስት አመታት ያገለገለው አለሙ አንዳርጌ በንፁሃን ፍጅትና ሰቆቃ መካከል የሚደረገውን ጦርነት እንደ ትልቅ ካምፓኒ የሚጠቀሙት የጦር መኮንኖችና ጀነራሎች በጦር መሳሪያ እና በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ንግድ እንደበለጸጉ ገልጿል።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
በስቦ መምታት የውጊያ ታክቲክ የጠላት ብልፅግና ወታደርን ወሽመጥ በመቁረጥ ውጤታማ ድል ተመዘገበ!
በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 1 ባለሽርጡ ክፍለጦር ላይ ጥቅታ ለማድረስ ከጉቢሳ ወደ ኮለቦ፣ ከጭሰ አባሊማ ወደ ሲልኮ፣ከጊራና ወደ ጉባ ፣ከመርሳ ወደ ሀብሩና ፋጂ የተንቀሳቀሰው የጠላትን ሀይል በቀን 26/05/2018 ከኮለቦና ሩጋ ያለውን የጠላት ሀይል ስቦ በማስገባት መነዮ ቀሊና ላይ ምሽት 1:30 ላይ የጠላትን ሀይል ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ታላቅ ድል ተጎናፀፈ።
የባለሽርጡ ክፍለጦርን ሊያጠቃና የክፍለጦሩን ነባር ይዞታዎች ሊወር የመጣው የአብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት በአምስት አቅጣጫ ለማፈን ቢሞክርም የጠላትን የጥፋት እቅድ ቅዠት በማድረግ 50 ሙትና 78 ቁስለኛ በማድረግ ከትላንት ከጥዋቱ 12:30 እስከ ዛሬ 27/05/2018 ዓ.ም በቆየ አውደ ውጊያ የጠላትን ከበባ ያለምንም መስዋዕትነት በአርበኛ እንድሪስ ጉደሌና በሌሎች በሳል የክፍለጦሩ ወታደራዊ ጠበብቶች በመስበር በጥላት ላይ ከፍተኛ ስብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ ማድረስ ተችሏል።
በዚህ አውደ ውጊያ የተበሳጨው የጠላት ሀይል በደቡብ ወሎ ዞን ተወለደሬ ወረዳ ሲልኮ እየተባለ በሚጠራው ቦታ 450 የሚደርሱ ወጣቶችን፣ አርሶ አደሮችን እና የቀን ሰራተኛዎችን በማፈን ስልጠና ሰልጥናችሁ አገራችሁን ትጠብቃላችሁ በሚል ሰበብ ወደ ማጓሪያ ቀጠና አስገብቶ ፋኖን ማረኩ በሚል የሀሰት ዶክመንተሪ ዝግጂት ላይ ይገኛል።
በተያያዘም በሀይል ላፈናቸው ንፁሀን በየቤቱ እየገባ የግል ታጣቂ ግለሰቦችን መሳሪያ ለማስወረድ ድንገተኛ ፍተሻና ድብደባ እያካሄደ ይገኛል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበር ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምኒልክ ዕዝ
ጥር 28/2018 ዓ.ም
#የድል_ዜና‼️
አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ነበልባል ክፍለ ጦረ በባንዳ ላይ ድል ተቀዳጀ !!
ጥር 28/2018 ዓ.ም አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ነበልባል ክፍለ ጦር ጥላት ላይ ብሎም የፈረጃቸውን የከተማ ውስጥ አውደልዳይ ሆድ አደር ባንዳ ሚሊሻዎችን ማፅዳቱን አጠናክሮ ቀጥሎበታል ።
ይህም በከተማ ውስጥ ህዝብን ሲያስርና ሲረሽን ፥ ሴቶችን በጅምላ ሲያስደፍርና የፈለገውን ሲያደርግ እንዲሁም ንብረት ሲዘርፍና ሲያዘርፍ፤ በከተማው ላይ ከመጣ ከሄደው የብልፅግና ሰራዊት ጋር በማበር በህዝብ ላይ የመከራ ዶፍ ሲያወርድ በነበረው በሚሊሻው አቶ አስታጥቄና በግበረ አበሮቹ ላይ የለመደውን ህዝብን ለማደናገርና አለቃነቱን ለማሳወቅ ታጅቦ አረርቲ ሸዋገነት ኬላ ሲንቀሳቀሱ በተደረገ የቦንብ ጥቃት
1ኛ. ሶስት ሚሊሻ ፣ሚሊሻው አቶ አስታጥቄ እና አጃቢዎቹ በፋኖ ተደምስሰዋል
። አጃቢዎቹ፦
- አሰፋ ጥላሁን እና
- ተስፋ የተባሉ ሚሊሻዎች እንዲሁም አንድ ለጊዜው ስሙ ያልታወቀ የአስታጥቄ አጃቢ ሚሊሻዎች እስከ ወዲያኛው የተሸኙ እና የተደመሰሱ ናቸው ።
2ኛ. አንድ ለጊዜው ስሙ ያልታወቀ የፖሊስ አባል የተደመሰሰ ።
3ኛ. ሁለት ፻ አለቃ የነበሩ የመከላከያ ሰራዊት አባሎች አብረው የተደመሰሱ ሲሆን፤
የባንዳዎች ቁንጮ የሆነው ሚሊሻው አቶ #አስታጥቄ በደረሰበት የቦንብ ጥቃት ሆዱ እንደ አሪዎስ ተዘርግፎ በሆስፒታል በማጣር ላይ እንደሚገኝ የውስጥ አዋቂዎች መረጃውን አድርሰውናል ።
ይህ ግዳጅ እስካሁን ከተደረጉት የተለየ እና አስደናቂ ጀብድ የተሰራበት ሲሆን ለተቀሩትም ከነበልባል ክፍለ ጦር አናብስት ፋኖዎች ማምለጥ እንደማይችሉ ማስተማሪያ ጭምር ነው ሲሉ የነበልባል ክፍለ ጦር አመራሮች ገልፀዋል፤ ሲል አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር የነበልባል ክ/ጦር ሪፖርተራችን አርበኛ እንግዳ መረጃውን አድርሶናል ።
© ዘገባው፦ አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር አርበኛ ጋዜጠኛ አበባየሁ ሰይፈ ።
አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ህ/ግንኙነት መምሪያ‼️
28/ዐ5/2018 ዓ.ም
የሁሉም ጥያቄ መልስና መፍትሔ ያለው 4 ኪሎ ብቻና ብቻ ነው ሌላው ወሬ ማብዛት ነው።
ራያም በለው፣ወልቃይትም በለው፣መተከልም በለው፣ደራም በለው አዲስ አበባ በረራም በለው የወለጋ ጉዳይም በለው የሁሉም ጥያቄዎች ሊመለሱ የሚችሉት ስልጣነ መንበሩን ስትቆጣጠር ነው ከዛ ውጭ እየተከባለለ እየተከባለለ ሌላ ክፍለ ዘመን ከመጨመርና ስቃይን ከማራዘም ውጭ የሚመጣ መፍትሔ የለም።
የብልፅጥና መንግስት ወልቃይትን ጭፍር አድርጎ እስከ ዛሬ የያዘው ለአማራ አስቦ ሳይሆን ለራሱ ፖለቲካ መስሪያ አስቦ ነው ምክንያቱም የወልቃይት ጉዳይ የብዙ ሀገራት ፖለቲካ እጅ ያለበት ግዛት በመሆኑ ከእነዚህም እራሱ ብልፅግና አለበት፣የአማራ ብልፀግና ሉሌው ከለበት፣የትግራይ እጅ አለበት፣የኤርትራ እጅ ከለበት፣የሱዳን እጅ አለበት፣የግብፅ እጅ አለበት እንዲሁም የምራባዊያን እጅ አለበት ዋናው ተዋናይ የአሜሪካ እጅ አለበት ተመልከቱ እንግድህ የዚህ ሁሉ ብቻ ላይሆን ይችላል ሌላም እኛ የማናቀው ሀይልም ይኖርበታል ስለዚህ መንግትስም ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ ጨፍሮ የያዘው የራሱ የብልፅግና አስፈላጊና እስትራቴጅክ ቦታ ሁኖበት ነው።
ስለዚህ የአማራ ጉዳይ በአራት ኪሎ ተጨፍሮ የተያዘ እንጅ ከዛ ከዚህ በሚሰነዘረው ጥያቄና ጦርነት ሊፈታ አይችልም ሊመለስና ዘላቂ መፍትሔ ሊመጣ የሚችለው መሰሪዎና ህዝብ ጨፍጫፊው ሀገር አፍራሹ ብልፅግና እስከወዳኛው ሰመገረሰስ ብቻና ብቻ ነው የዛኔ ነው እንግድህ የሀገሪቱ ህገ መንግስት የምትሉት ጥያቄ የሚነሳበትና ሊሻሻልም ጭራሹን መቀየርም የሚቻለው።
ስለዚህ ከላይ ከታች የሚቦኩ ነገሮች ለአማራ መፍትሔ የሚሆኑ አይደሉም ፋኖ ራሱን ችሎ አሁን የራሱን ድራፍት ሰርቷል በሰራው መሰረት ይታገላል ትግሉንም ዳር ደበር ያደርሳል የዛኔ ነው እንግድህ ኢትዮጵያ ሰላሟን ልታገኝ የምትችለው።
#ሰበር_መረጃ‼️
ወደ ኮንቦልቻ ሆስፒታል ብቻ የገባ ቁስለኛ ወታደር አሃዛዊ ቁጥር 53 መድረሱ ታውቋል።
ይህ የቁስለኛ ብዛት ከኮምቦልቻ ከተማ ሁለት የጦር ሄሊኮፍተሮች የቆሰሉ አመራሮችንና መስመራዊ አዋጊዎችን ጭነው ወደ አዲስ አበባ ከወሰዱት ውጭ ነው።
ዛሬ ጥር 28/2018 ዓ/ም እኩለቀን 6:40 ላይ ኮምቦልቻ ከተማ ያረፉት ሁለት የጦር ሄሊኮፍተሮች፡ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦችና መስመራዊ አዋጊዎችን ጨምሮ ከ47 በላይ ቁስለኛ ወታደሮችን ወደ አዲስ አበባ ጭነው መውሰዳቸውን የአይን እማኞች ለመረብ ሚዲያ ተናግረዋል።
የወግዲ ወረዳ ሆስፒታልና ጤና ጣቢያዎች ማስተናገድ ከሚችሉት በላይ በቁስለኛ ወታደሮች ተጨናንቀዋል።
ፋኖ በአከባቢው ከባድ የሆነ የሽምቅ ጥቃት እየፈፀመ በመሆኑ በወግዲ የሚገኙ ቁስለኛ ወታደሮችን ወደ ደሴና ኮምቦልቻ ወስዶ ለማሳከም አዳጋች ሁኔታ ፈጥሯል።
በዚህም ምክኒያት፡ ወግዲ ጫቃታ ላይ አንዲት የጦር ሄሊኮፍተር ካረፈች በኋላ በውጊያ የቆሰለ አንድ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥን ጨምሮ ሌሎች ቁስለኛ መስመራዊ አዋጊዎችንና አባሎችን ጭና በጋስጫና ደገር አቆራርጣ ወደ ሸዋ አዲስ አበባ መብረሯን ከሰዓታት በፊት ጣቢያችን መረብ ሚዲያ የአይን እማኞችን ዋቢ አድርጎ መዘገቡ አይዘነጋም።
ትናንት አመሻሹን ከፍተኛ ቁጥር ባለውና የከባድ መሣሪያ ሽፋን እንዲሁም የድሮን ክትትል በሚደረግለት ሠራዊት የታጀበ በመቶዎች የሚቆጠር ቁስለኛ ወታደር ወደ ደሴና ኮምቦልቻ ተወስዷል።
በተመሣሣይ ዛሬ ማለዳም እንዲሁ በርካታ ቁስለኛ ወታደር ወደ ደሴና ኮምቦልቻ የተወሰደ ሲሆን፡ በደሴ ከተማ ከ74 በላይ ወታደሮች ሕክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ የመረብ ሚዲያ ወታደራዊ ምንጮች ገልፀዋል።
በኮምቦልቻ ከተማም በተመሣሣይ፡ ዛሬ ማርፈጃውን ከተወሰዱ ቁስለኞች ጋር በድምሩ 53 ወታደሮች ሕክምና እየተደረገላቸው ሲሆን፡ ከዚህ በተጨማሪ እኩለቀን ላይ ሁለት የጦር ሄሊኮፍተሮች ከ47 በላይ ቁስለኞችን ጭነው ወደ አዲስ አበባ መብረራቸውን ጣቢያችን ያነጋገራቸው የአይን እማኞች ገልፀዋል።
በሁለቱ ሄሊኮፍተሮች ተጭነ ከተወሰዱት ቁስለኞች መካከል የሰሜን ምስራቅ ዕዝና የ11ኛ ዕዝ እንዲሁም በአየር ወለድ ኮማንዶ መምሪያ ከፍተኛ አዛዦች እንደሚገኙበት ተጠቁሟል
28/ዐ5/2018 ዓ.ም
+1
ታላቅ የቅንደሻ ዜና በደብረማርቆስ ከተማ
በ24ኛ ክ/ጦር ልዩ የከተማ ኦፕሬሽን የአገዛዙ ዋና ቀኝ እጅ እስከመጨረሻው ተሸኝቷል
ጥር 27/2018 ዓ.ም
በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር ወታደራዊ አመራር ሰጭነት ጥር 26/ለ27 /2018 ዓ.ም ወደ ምስ/ጎጃም ዞን ደብረማርቆስ ከተማ ልዩ የከተማ ኦፕሬሽን ፈፃሚዎችን አስርጎ በማስገባት የአገዛዙ ገረድ ቀኝ ዕጅ ራሱን የሰላም አስከባሪ ኮማንድ ፖስት ብሎ በመሰየም በዞኑ የአድማ ብተና የሚሊሻና የህዝባዊ ፖሊስ አሰልጣኝ የነበረውን# መቶ_አለቃ_በየነ_ጌትነት የተባለውን ጠብደል ባንዳ ደብረማርቆስ ከተማ በተለምዶ አባብዙነህ ጉርድ ተብሎ ከሚጠራው ቦታ ቤት ለቤት ሲያውደለድል በ24ኛ ክ/ጦር ቆንጆዎች እርምጃ ተወስዶበታል!!
አዲስ ትውልድ አዲስ ተስፋ አዲስ አስተሳሰብ
የአፋብን ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
+1
የአገዛዙ ወታደሮች ከኦሮሚያ ክልል ለ8 ቀናት በመጓዝ ፋኖን ተቀላቀሉ
ጥር 28/2018 ዓ.ም
አገዛዙ ህዝብን እየዘረፈና እያሰቃዬ መሆኑን የተረዱት ናትናኤል ማስተዋል ፦ ሀይማኖት ሞላ እና ደረጀ መኳንንት የተባሉ የአገዛዙ ወታደሮች በዛሬው ዕለት ከኦሮሚያ ክልል ፍቸ ከሚገኘው 6ኛ ዕዝ 52ኛ ክ/ጦር 2ኛ ሬጅመንት 3ኛ ሻንበል የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦርን ከነ ሙሉ ትጥቃቸው እንድሁም በርካታ ጥይት ካዘናና ቦምቦችን በመያዝ ተቀላቅለዋል ።
በአዋባል ወረዳ 34ኛ ክ/ጦርን የተቀላቀሉት ወታደሮቹ አገዛዙ አማራ ላይ እያደረሰ ያለውን ዘርፈ ብዙ ጥቃት መረዳታቸውን እና እስካሁን በተሳሳተ መንገድ የቆዩ መሆናቸውን ገልፀው ከፋኖ ጎን ተሰልፈው ለመታገል ከኦሮሚያ ክልል ለ8 ቀናት በፈታኝ ሂደት ተጉዘው 34ኛ ክ/ጦርን መቀላቀላቸውን ገልፀዋል።
አድስ ትውልድ ! አድስ አስተሳሰብ ! አድስ ተስፋ !
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206 ኮር ህዝብ ግንኙነት
