uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling 👈

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Kanalga Telegram’da o‘tish

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Ko'proq ko'rsatish
4 133
Obunachilar
+224 soatlar
+4237 kun
+1 19130 kun
Postlar arxiv
ላስታ አሳምነዉ ኮር በአገዛዙ ሰራዊት ላይ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ በርካታ ድሎችን ተጎናፀፈ:: አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ግዙፉ ላስታ አሳምነዉ ኮር ክንፍ የሆኑት እሸት ክፍለ ጦር እና ነብሮ ተወርዋሪ ኮማንዶ ብርጌድ በጥምረት በመሆን ከላሊበላ ጋሻና-ከጋሸና ላሊበላ በሁለት አቅጣጫ እየተንቀሳቀሰ የነበረን የአገዛዙ ሰራዊት አይቀጡ ቅጣት ሲቀጡት ተፈራ ማሞ ክ/ጦር ደግሞ መነሻዉን አይና ከተማ አደርጎ ወደ ቅዱስ ሐርቤ እየተንቀሳቀሰ የነበረን ግትልትል ሰራዊት እንደ ቃሪያ ሲያራግፉት ዉለዋል። ምላሱ ብቻ የቀረዉ የብልፅግናዉ አገዛዝ በአፈ- ቀላጤዎቹ በኩል "ፋኖን ከምደረ ገፅ አጥፍቻለሁ" የሚል የዉሸት ፕሮፖጋንዳ ለገና በዓል ወደ ላሊበላ ከተማ ለሚመጡ እንግዶች ለማስረፅ የተለያዬ የክልል እና የዞን ሆድ አደር ካቢኒዎችን ይዞ በመምጣት ላይ እያለ በዛሬዉ ዕለት ማለትም በቀን 26/2018 ዓ.ም በእሸት ክፍለ ጦር እና በነብሮ ተወርዋሪ ኮማንዶ ብርጌድ ሲገርፍ ዉሎ ያሰበዉን ሳያሳካ ወደየመጣበት ተመልሷል። ወጊያዉም ከንጋቱ 11:00-6:00 የዋለ ሲሆን በዚህም ብዛት ያለዉ የነፍስ ወከፍ መሳርያዎች ሲማረኩ ከ30 በላይ የአገዛዙ ሰራዊት በእሸት ክ/ጦር እና በነብሮ ኮማንዶ ብርጌድ ሲደመሰሱ ከወደ ቅዱስ ሐርቤም በተፈራ ማሞ ክ/ጦር ሲገረፍ ዉሎ ሙትና ቁስለኛ ሁኖ ወደ አይና ከተማ ተመልሷል። ዉጊያን በበላይነት የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ም/ወታደራዊ አዛዥ እና የላስታ አሳመነዉ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ ወንድሙ ማሩ የመራዉ ሲሆን አርበኛዉም "በደመቀ ሁኔታ ታህሳስ 29 የሚከበረዉ የገና በዓል አገዛዙ ከሚያስበዉ በላይ እኛ እንዲከበርልን እንፈልጋለን ነገር ግን በዚህ በዓል የብልፅግና አፈቀላጤ ሰለ አማራ ትግልም ሆነ ሰለ አማራ ፋኖ የዉሸት ፕሮፖጋንዳ እሚያሰራጩ ከሆነ እኛ በአቅራቢያዉ እስካለን ድረስ እርምጃ እንወስዳለን ብሏል"። መረጃውን ያደረሰን የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን መምሪያ ጋዜጠኛ ፋኖ ደረበ መኮንን ነው:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ታህሳስ 26/2018 ዓ.ም

ፋኖ ሰላዮችን ለምን ይገድላል? ድሮን ሲዘንብብን፣ በጅምላ ስንቀበር፣ እኅቶቻችንና እናቶቻችን ሲደፈሩና ጡታቸው ሲቆረጥ፣ ተቋማት ሲወድሙ አላዘኑልንም ድምፅም አልሆኑንም። ሙሉ የሀገሪቱ ጦር ሲዘምትብን ማንም ምን አላለም። ተፈጥሯዊ መብታችንን ተጠቅመን ራሳችንን ስንከላከል ግን እንደ ሀገር አፍራሽ እንደ እምቢተኛ እንቆጠራለን። የጠላት ተልእኮ ተሸካሚን ስንቀጣ፣ ጥቁር አማራውን ለሆዱ ብቻ የሚያስበውን አማራ ስንቀጣ የቅጣት ዓይነት ይመርጡልናል ይባሱንም በደላቸውን ንጽሑህን አድርገው ይዘግቡታል። ሕዝባችን ዓለም ላይ ያልተደረገ ግፍ ሲፈጸምበት እንዳላዩ አልፈው እኛ መቅጣት ስንጀምር ስለ ሰብአዊነት ይሰብኩናል ይከሱናል። ምርኮኛ አቀማጥሎ የሚይዝ ፋኖ ሰብአዊነትን ተግብሮ የሚኖር እንጅ ያለ አግባብ አይገድልም አይዘርፍም። እንደ ጦርነት ሕግ ይገጥማል ያሸንፋል ይማርካል ይደመስሳል። ሰላይን ይቀጣል። አንዳንንዶች የፋኖ ደጋፊ ነን የሚሉና የሦስተኛ ረድፍ የብልጽግና ደጋፊዎች ሳይቀር መሃል ሠፋሪነታቸውን መደበቅ ተስኗቸው በፋኖ የትግልና የሕዝብ አስተዳደር ብሎም የፍርድ አሰጣጥ ዙሪያ የእናውቅላችኋለን ጨኸት ያሰማሉ። እነዚህ ፋኖም ብልጽግናም ካሸነፉ በሰላም እንኖራለን የሚሉ ወላዋዮችና በሕዝብ ላይ ቁማር የሚይዙ ናቸው። ሰሞኑን ስለሚወራው ጉዳይም አርበኛ አስረስ፡ "ስለላ ላይ ተሰማርተዋል" በማለት የሚከስሷቸውን ሴቶች "እንደ ተዋጊ ኃይል" እንደሚቆጥሯቸው ተናግረዋል። "በሕገ ደንባችን መሠረት ለጠላት ስለላ ሥራ ሲሠራ የተገኘ ማንኛውም ሰው ላይ የሞት ቅጣት እርምጃ እንደምንወስድ፣ ሌላም አካባቢ ተመሳሳይ እርምጃዎችን እንደምንወስድ ይታወቃል" ብሏል። በቁጥጥር ስር ያሉ ሰዎች ላይ ግድያን መፈጸም እንደ የጦር ወንጀል ድርጊት ሊቆጠር የሚችል ስለመሆኑ ከቢቢሲ ጥያቄ ቀረበለት የፋኖ አመራሩ አስረስ "በምርኮ የተያዘ ሰው፤ በተኩስ ልውውጥ መሃል በፈቃደኝነት እጁን የሰጠ ሰው ሲሆን ነው። ይሄኛው ግን በልዩ ሁኔታ የስለላ ሥራ ሲሠሩ ስለሆነ በቁጥጥር ስር ዋሉት፤ በሕገ ደንባችን መሠረት እንደ ምርኮኛ የሚያዙ አይደሉም" የሚል ምላሽ ሰጥቷል። ©ብላክ ላዬን ሚዲያ

‎ወ/ሮ አየሁ አበባየሁን  እና  ወ/ሮ አታላይ አንቴን  #የገደ*ለው የወይዘሮ አየሁን ባለቤት በ23/04/2018 ዓ/ም #ያቆሰለው #አረ*መኔ ሰራዊት በቀን 24/04/2018 ዓ/ም  ሙሉ ለሙሉ #ተደም*ስሷል ። ‎ለምልክት  ቀረ ቢባል እንኳ #በምርኮ የተመዘገቡ ናቸው። ‎ ‎በርካታ ክላሽ ስናይፐር  ብሬን ዲሽቃ  ሞርተር እና የተለያዩ ተተኳሾች #ተማርከዋል። ‎የአረመኔው ስርዓት አዋጊዎች ተደም*ስሰዋል፤ ቀሪዎቹም ተጨብጠዋል። ‎ #በዘመቻው የአፋብኃ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ  ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክፍለጦር እና የ109ኛ ኮር 99ኛ ክፍለጦር የፋኖ ሰራዊቶች #ተሳትፈውበታል። ‎ ‎ቁጥራዊ ምርኮኞችን መሳሪያ ተተኳሽ እና የተማረኩ #የአረ*መኔው ስርዓት አገልጋዮችን ከቆጠራ በኃላ እምናሳውቅ ይሆናል። ‎ ‎አዲስ ትውልድ  አድስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ፤ ‎ታህሳስ 26/2018 ዓ/ም Dejen M Endale ‎

የአብይ አህመድ አገዛዝ 17 ንፁሃንን በግፍ ጨ*ፈጨፈ! **// ታህሳስ 25/2018 ዓ.ም አዮ ጓጉሳ ወረዳ እሁዲት የመሸገው የአብይ አህመድ ቅጥረኛ ጨፍጨ*ፊ ፀረ አማራ ሠራዊት ከምሽቱ 11 ሠዓት አካባቢ የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 109 ኮር የ88ኛ ክ/ጦሯን ቃኝና ማህንዲስ ሻለቃን (6ኛ ሻለቃን) ለማፈን እንቅስቃሴ አድርጓል። መረጃው የደረሳት ሻለቃዋ ጠላትን በደፈጣ መምታት ችላ ከ8 በላይ አቁስላ ከ10 በላይ ቅጥረኛ ጨፍጫፊውን ወደ ማይመለስበት ሽኝታዋለች። ያልጠበቀው የምት ውርጅብኝ የገጠመው ይህ ፀረ አማራ ቡድን ወደ ኋላ ተመልሶ አዮ ቀበሌ በመግባት 16 ንፁሃን ወጣቶችን ከመዝናኛ ቦታ እና ከስራ ቦታቸው ሠብስቦ በግፍ እረሽኗል። ስርዓቱ ፋኖን ለማጥፍት የአማራ ህዝብ ማጥፍት እንደ ወታደራዊ ስልት እየተጠቀመ ያለ እና አማራን መዝረፍ፣ መግደል፣ ሐብት ንብረት ማውደም፣ ፆታ እና እድሜ ሳይለይ በቡድን መድፈርን እንደ ተጨማሪ የጦር ስልት አድርጎ እየተጠቀመ ያለ ከኢትዮጵያ ባህል ያፈነገጠ የባዕድ ተልዕኮ አንግቦ ሁለ ገብ ጦርነት የከፈተ አለማቀፉን የጦር ህግን የማይቀበል የጦር ወንጀለኛ የሆነ አሸባሪ ኃይል ነው። በግፍ ከተረሸኑት መሃከል:- 1. ዳዊት ቀናው 2. ተውስል ምሬ 3. ብርሃኑ አረጋ 4. ክንዱ ታደሰ 5. እንዳለ ተስፉ 6. ሽኩር ጋሻው 7. አህመድ ሁሴን 8. አውላቸው አለነ 9. ትግስቱ ጌታቸው 10. ቸኮለ አስራደ 11. ምንባለ ቢተው እና 6 የቀን ስራ የሚሰሩ ማንነታቸው ያልታወቁ ይገኙበታል። ይህ ግፈኛ ፀረ አማራ ቡድን አስከሬን አላስነሳም ያለ ሲሆን ወንድሞቻችሁ ናቸው የገደሉን እኛም እናንተን እንገላለን እያለ እንደረሸናቸው ማረጋገጥ ተችሏል። ቡድኑ ሌላ ተጨማሪ ከ10 በላይ ንፁሃን ወጣቶችን አግቶ ወደ እሁዲት ወስዷል። 👉ይህ አሸባሪ ስርዓት ታህሳስ 24/2018 ዓ.ም ሌሊት ከቡራፈር ቀበሌ 6 እና ከሻምብላ ቀበሌ 2 በድምሩ 10 አ/አደሮችን አግቶ መሰወሩ ይታወሳል። ለሞቱት ነፍሳቸውን ይማር! ለወዳጅ ቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እንመኛለን!! 109ኛ ኮር ህ/ግንኙነት ታህሳስ 26/2018 ዓ.ም

የፋና ቲቪ ሀሰተኛ ዘገባ ሲጋለጥ'' በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 75ተኛ አመት የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ የምሑራን ሚና ለሀገራዊ ብልፅግና በሚል መሪ ቃል ዐብይ አህመድን ጨምሮ ብዙ ሚኒስተሮች
የፋና ቲቪ ሀሰተኛ ዘገባ ሲጋለጥ'' በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 75ተኛ አመት የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ የምሑራን ሚና ለሀገራዊ ብልፅግና በሚል መሪ ቃል ዐብይ አህመድን ጨምሮ ብዙ ሚኒስተሮች እና ታዋቂ የፖለቲካ ካድሬዎች  የተሳተፉበት በፋሽስቱ አብይ አህመድ የተመራ ውይይት መደረጉ ይታወሳል። በዚህም የተነሳ ፋና ቴሌቪዥን ዐብይ አህመድ አሊ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቀድሞ ተማሪ እንደነበር እና በውይይቱም ጥናታዊ ፅሁፍ እንዳቀረበ አድርጎ የሰራው ዘገባ የተሳሳተ እና ከእውነት የራቀ ነው ተብሏል። አብይ አህመድ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቀድሞ ተማሪ እንደነበር የሚገልፅ ምንም አይነት መረጃ እና ማስረጃ በዩኒቨርስቲው እንደሌለ የተገኙ ምንጮች ጠቁመዋል። በተጨማሪም ፋና ቴሌቪዥን አብይ አለህመድ ጥናታዊ ፅሁፍ እንዳቀረበ አድርጎ የሰራውም ዘገባ ሀሳት መሆኑ ተረጋግጧል፤ በውይይት መድረኩ የቀረበው ፅሁፍ ጥናታዊ ሳይሆን እንደዚህ በቀደሙ የተለመደ ልብ ወለድ ቅርፅ ያለው እንደሆነ ተሳታፊዎች ገልፀዋል። በተጨማሪ የፋና ቲቪን ዘገባ ሀሰተኛ የሚደርገው ዐብይ አህመድ በራሳሱ አንደበት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 75ተኛ አመት ምስረታ በዓል እንደማንኛው ባለስልጣን በተዘጋጀው የውይይት መድረክ እንደተሳተፈ እና ፅሁፍ እንዳቀረበ በማህበራዊ ሚዲያዎቻቸው ማጋራታቸው የፋና ቲቪን ዘገባ በራሱ ውድቅ ያደርገዋል።

ሰበር ዜና! ምኒልክ ዕዝ ወልድያ ከተማ ዙሪያ ዙ23 በአር ፒ ጂ ያቃጠለበትንና ያወደመበትን ድል ተጎናፀፈ:: አፋብኃ ምኒልክ ዕዝ የሰሜን ወሎ ዞን ዋና መቀመጫ በሆነው ወልድያ ከተማ ዙሪያ ጥቁር ውሃ
+4
ሰበር ዜና! ምኒልክ ዕዝ ወልድያ ከተማ ዙሪያ ዙ23 በአር ፒ ጂ ያቃጠለበትንና ያወደመበትን ድል ተጎናፀፈ:: አፋብኃ ምኒልክ ዕዝ የሰሜን ወሎ ዞን ዋና መቀመጫ በሆነው ወልድያ ከተማ ዙሪያ ጥቁር ውሃ እስከ ሳንቃ ከተማ ከባድ ትንቅንቅና ተጋድሎ በማድረግ የፋሽስቱ አገዛዝ ዙ23 ልዩ ስሙ ዘንዶ ጅራት የተባለ ቦታ ላይ በአር ፒ ጂ በማቃጠልና በማውደም ብሎም የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሳሪያ በመማረክ ታላቅ ድል ተጎናፀፈ:: ምስራቅ አማራ ኮር 1 አሳምነው ክፍለ ጦር እና የዞብል አምባ ክፍለ ጦር ቃኝ ወልድያ ዙሪያ ከጥቁር ውሃ እስከ ሳንቃ ከተማ እና ላስታ አሳምነው ኮር ተከዜ ክፍለ ጦር ድልብና ሰከላ ቀጠና ላይ በመዝጋት ባጠቃላይ የተጠቀሱት አሃዶች በጥምረት ባደረጉት ከባድ ተጋድሎ ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል:: ባጠቃላይ አሳምነው ክፍለጦር የዞብል አምባ ክፍለጦር ቃኝን ጨምሮ ጥቁር ውሃ እስከ ሳንቃ ከተማ መግቢያ ድረስ ከፍተኛ አመራሮችን ጭምር የማረኩበትን በርካታ ድሎች ሲያስመዘግቡ ላስታ አሳምነው ኮር ተከዜ ክፍለ ጦር ድልብና ሰከላ ላይ በመዝጋትና ተጨማሪ የጠላት ሃይል እገዛ እንዳያደርግ በማድረግ የጠላትን ግንኙነት በማቋረጥ ለተገኘው ድል ጉልህ ሚና ተጫውተዋል:: ማስታወሻ፦ የተማረከ ጠላት እና ንብረት በዝርዝርና በማስረጃ ይዘን እንመጣለን! መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ታህሳስ 25/2018 ዓ.ም

#ሰበር_ቪዲዮ_ከወልድያ‼️ ከወልድያ በቅርብ ርቀት ዘንዶ ጅራት ተብሎ የሚጠራው ቦታ ላይ የአየር መቃዎሚያው ተጠምዶበት እስከነበረው ኦራል በቦምብ መጋየቱን የመረብ ሚዲያ የግንባር ዘጋቢዎች ለማረጋገጥ ችሏል። ደፈጣ ጥቃቱን ተከትሎ  ከባድ ግብግብ እየተደረገ ነው። ምኒልክ ዕዝ ከደቂቃዎች በኋላ ዝርዝር መረጃ ይሰጣል። ©መረብ ሚዲያ 25/ዐ4/2018 ዓ.ም

የአደረጃጀት ዜና(25/04/18 ዓ.ም)👇 ~~////////~~/////~~/// አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ አሰራሩን እያዘመነ ይገኛል። በቅርቡ ዓለማቀፋዊ መስፈርት ያሟላ ወታደራዊ አደረጃጅት በዕዝ፥በኮር፥በክ/ጦር እና በሬጅመንት በማደራጀት በየግንባሩ ድል እየተቀዳጀ ይገኛል። በዛሬዉ ዕለትም በቀድሞዉ የክ/ጦር አደረጃጅት የ1ኛ ክ/ጦር አካል የነበሩትን ባ/ዳር ብርጌድ፥ጣናዉ መብረቅ ብርጌድ፥አንሙት ያዛቸዉ ብርጌድ እና ኮ/ሎ ታደሰ ሙሉነህ ብርጌድን በማወሃድ የዕዝ፥ የኮር፥ የብርጌድ፣የሻለቃ እና የሻምበል አመራሮች በተገኙበት የአመራር እንዲሁም በከፊል የሰራዊት ፕወዛ በማደረግ 11ኛ እና 22ኛ ክ/ጦር በሚል ስያሜ ክጦሮችን በማደራጀት የቀጣይ የስራ አቅጣጫዎችን በመስጠት አጠናቋል። ትግላችን መሰረቱን አለት ላይ በማቆም ማገር እና ጣሪያዉን አዋቅሮ በመጨረስ የአማራ ህዝብን ከፈፅሞ ጥፋት እያደነ ለኢትዮጵያውያን ተስፋ በመሆን ወደፊት እየገሰገሰ ይገኛል። አዲስ ትዉልድ፣አዲስ አስተሳስብ ፣አዲስ ተስፋ!! ክፋት ለማንም፣በጎነት ለሁሉም!! Zewdalem Adugnaw የ102ኛ ኮር ሰብሳቢ!!

ትላንት በነበረው በስናን ወረዳ በጀግና ፋኖዎች የተማረኩ የፋሽሽቱ ስራት ወንበር ጠባቂ አራዊት ሰራዊቶች፦በቪዲዮ እሄን ይመስላል

ጨካኝ ያልሆነ የአማራ ትግል ውጤት ስለማያመጣ ገና ከዚህ የበለጠ ጨካኝ እና መራራ በመሆን  ስለ እንቅስቃሴ፣አቅም እና  ዕቅድ  ጠላት ምንም መረጃ የሌለው ዓይነ-ስውር  ማድረግ ከወታደራዊ እና ፖለቲካዊ እኔቅሰሰቃሴ አንፃር ስትራቴጅክ  ስለሆነ  መተግበር ግዴታ ነው። የውስጥ አቆርቋዥን እና የጠላት ተላላኪ ላይ አምርሮ እርምጃ የማይወስድ ትግል የአማራን ህዝብ ከፋፍሎ መጠቀም ለሚፈልጉ ጠላቶች ስጋጃ እንደማንጠፍ ስለሚቆጠር  ህዝቡን ወደ ባሰ  ባርነት እና መከፋፈል ስለሚፈጥር  የወደፊቱን ትልቅ አደጋ ለማስቀረት ሲባል ዙሪያ መለሱን ማፅዳት ግዴታ ነው። ኢህዴን እንኳን በወቅቱ በህውሃት ትዕዛዝ  ሽፍታ ምንጠራ እያለ የተገፉ አማራዎችን በየጫካው እያረደ "ብዓዴን" የሚባል ምናምንቴ ጎሳ (submissive clan)   ሲፈጥር ፤ መንጣሪዎችም  "የጀነራልነት" እድገት አግኝተውበት ነበር።  ዛሬ  "ለላኪዎችም" ሆነ  ለመላላክ ዝግጁ ለሆኑት  ቀላል ስላይደለ ትግሉን  ለአዲሱ ትውልድ መሪዎች መተው ጠቃሚ ነው ብለን እንመክራለን።  የአማራ ኢሊት የሚባል ወዝጋባ ራስ ወዳድ ስብሰብ በጠረጴዛ  ፖለቲካ ሽንፈት ስለተከናነበ ትግሉ ሌላ መልክ ይዞ የብረት ትግል እየመሩ ያሉ  መሪዎችን እና ታጋዮችን "በአጉል ትክክለኝነት"  መርህ አቃቂር በማውጣት ሰ'ብ'ዓዊ መ'ብት ምናምን እያለ ሲጃጃል እንደማየት አስፀያፊ ነገር የለም።  ጉዳዩ በጠረጴዛ ዙሪያ የነበረው ቀርቶ በአፈሙዝ ከሆነ በኋላ የጨዋታው ህግ በሙሉ በጦርነት ህግ ብቻ ነው የሚሆነው። ጠላትን በወገን ላይ የበላይነት እንዲቀዳጅ ድጋፍ የሚያደርግ ሆነ የሚተባበር በሙሉ ጠላት ተደርጎ እንደሚቆጠር እንኳን ግንዛቤ ከሌለው ጋር ስለ ትግል አስተያየት ሲሰጥ መስማት ያሰለቻል።  በጦርነቱ ላይ የሌሉ ሲቪያሊያንን ማጥቃት ወይም የልዩነት መሠረት በሆኑ ማንነቶችን ለይቶ ማጥቃት አይደለም የጦርነት ህግ  የዳበረው የአማራነት ስነ-ልቦናችን ፈፅሞ አይፈቅድልንም! ➔ ዋናው  እና ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት  ጉዳይ ወደ ዋናው ጠላት ማጥቃት ከመጀመር በፊት በዙሪያ ያለን የጠላት ተባባሪ ያለ ምህረት ማፅዳት ወይም neutralize ማድረግ ግዴታ ነው። ይሄ ሳይደረግ ጠላትን ለማጥቃት መሞከር በራስ ዕቅድ ራስን  በጠላት ቀለበት ሥር እንደማስገባት ስለሚቆጠርም ነው።     በቸልተኝነት ችግርን ለነገ በማሳደር  ወይም ውሳኔ ባለመወሰን መካከል ባለ ወላዋይነት ምክንያት በሠርጎ ገብ ምክንያት አንድም የሠራዊት አባል ላይ የሚደርስ ጉዳት ቀዳሚ ተጠያቂ የሚሆኑት መሪዎች መሆኑን ግን ልብ ይሏል! ©በዛብህ በላቸው

ሰበር ዜና ስርቆትና ዝርፊያ ምግባሩ ያደረገው የአገዛዙ አረመኔ ሰራዊት የህዝብን ባንክ ዘረፋ። የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ  ዕዝ  ሜደር ጀኔራል ውባተ አባተ  አንደኛ ኮር ጉና ክ/ጦር በሚንቀሳቀስበት ቀጠና ምግባሩ ስርቆትና ዝርፊያ የሆነው የአገዛዙ ጡት ቆራጭ አረመኔ ሰራዊት የአርሶ አደሩን ሀብትና ንብረት ፣ መሳሪያ እና ትጥቅ መዝረፍ ፣ መቀማት ፣  ማቃጠል  ስራ አድርጎ ይዞታል ። ባለፋት 24 ሰዓት በእስቴ ወረዳ መካነየሱስ ከተማ ከ90 በላይ  ንፁሀን ዜጎችን የፋኖ ቤተሰብ ናችሁ ፣ ከፋኖ ጋር ትሰራላችሁ በማለት አንድ ማደበሪያ መጋዘን ውስጥ በማጎር እየደበደበና እያሰቃየአቸው ሲሆን በተጨማሪም ፋርጣ ወረዳ አለም ሳጋ አካባቢ የነበሩ አርሶ አደሮችን ወደ ደብረታቦር ከተማ  እየደበደበ ውስዶ አስራቸዋል። እንዲሁም አንዳቤት ወረዳ  ጃራ ገዶ ከተማ የሚገኘውን  የህዝብ ሀብት የሆነውን አባይ ባንክ በሀይል 6,347,000(ስድስት ሚሊየን ሶስት መቶ አርባ ሰባት ሺ ) ብር እና የባንኩን መገልገያ ቁሳቁሶች የቻለውን በመጫን የቀረውን ሙሉ በሙሉ  በማውደም ወደ ወለሽ ከተማ ተመልሷል ። የአገዛዙ ቅልብ ሀይል ሰሞኑን  በሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ የቁርጥ ቀን  ልጆች የሚደርስበትን ምት መቋቋም ሲያቅተው  በሌሊት  በመንቀሳቀስ የበቀል ዱላውን  ንፁሀንን በመግደልና በማሰር እንዲሁም ሀብትና ንብረታቸውን በማውደም አማራ ላይ ያለውን ጥላቻና ሁለተናዊ ማጥፋት ዘመቻ እያሳየን በመሆኑ ማንኛውም ማህበረሰብ እራሱን እንዲከላከል እና ከፋኖ ጎን እንዲሰለፍ ጥሪ እናስተላልፋለን ። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !!!! አርበኛ መ/ር   ያሄድ  ደገፋው የጉና  ክ/ጦር ህ/ግን /ኃላፊ   ተህሳስ 25/2018 ዓ/ም

ድንቄም ባህር ኃይል ¡ የአብይ አህመድ ባህር ኃይል በጀግኖች የ102ኛ ኮር አባላት በብሬን ጥይት አናቱ ተበስቶ ከእነ ጀልባው ጣና ውስጥ ሰጥሟል ። ነገሩ እንዲህ ነው ። አብይ አህመድ እና ቄስ ሞገሴ ዳጋ እስጢፋኖስ ገዳምን ለመጎብኘት በተዘጋጁበት በዚህ ሰዓት ያን የቀይ ባህር ተንሳፋፊ ፣ ያንን የባህር ላይ ፋልኮን ሐይላቸውን ከባህርዳር ጊዮርጊስ በብዙ ጀልባዎች ጭነው ወደ ደቅ ደሴት እና ወደ ዳጋ እስጢፋኖስ ገዳማት ይልካሉ ። ይህንን መረጃ የሰሙት ጀግኖች የ102ኛ ኮር የ11ኛ ክፍለጦር አባላት ( የባህርዳር ልጆች ) ደቅ ደሴት ላይ የተወሰኑ የቡድን መሳሪያዎችን ብቻ በመያዝ ይጠብቋቸዋል ። ከዚያም በጀልባ እየተግተለተለ ወደ ደሴቱ ለአሰሳ የመጣውን የባህር ኃይል ኮማንዶ በብሬን ጥይት ግንባር ግንባሩን በማለት ይደመስሱታል ። በዚህ ውጊያ :- 1/ 2 ጀልባ ሙሉ የባህር ኃይል ኮማንዶ ብዛቱ በግምት ከ80 - 100 የሚደርስ ጣና ሐይቅ ውስጥ ሰጥሟል ። 2/ ከ15 - 20 የሚደርሱት ሙትና ቁስለኛ ሆነዋል ። በጣም አስገራሚው ነገር ከውጊያው በኋላ አንድ የቀድሞው የጣናው መብረቅ አባል " ያን ሁሉ ጥርጥር ክላሽ ይዘውት ሰመጡ " ማለቱ በአባላቱ ዘንድ የዕለቱ ፀፀት ተብሎ ተመዝግቧል ። ድል ለጀግናው ፋኖ ድል ለጀግናው አማራ አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ !!

ፋኖ በቆረጣ ገብቶ የጠላት ድሽቃን  ከማረከ በኋላ የተቀረፀ ምስል! በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር እና 109 ኛ ኮር የጠላትን አከርካሪ የሰበረ ተጋድሎ በማድረግ በድል ተንበሽብሸዋል።

"መንፈሶች ነን!! ሰሌዳ ቁጥር 20253 land cruiser መኪና ከደብረ ማርቆስ ከተማ ነጥቀናል" 206ኛ ኮር ታህሳስ 25/2018 ዓ.ም ===================================
+2
"መንፈሶች ነን!! ሰሌዳ ቁጥር 20253 land cruiser መኪና ከደብረ ማርቆስ ከተማ ነጥቀናል" 206ኛ ኮር ታህሳስ 25/2018 ዓ.ም =================================== በደብረ ማርቆስ ከተማ መሀል አስፓልት ላይ 6 ፖሊሶችን በአንድ ቦንብ አነጥፈን የሰውነታቸው ደም ተንጠፍጥፎ ሳይቆም ከንጉስ ተ/ኃይማኖት አደባባይ ስር  የምስራቅ ጎጃም ዞን ብልፅግና ፅ/ቤት ንብረት የሆነችውን ሰሌዳ ቁጥር 20253 land cruiser መኪና 206ኛ ኮር 14ኛ ክ/ጦር አፈፍ አድርጋ ወስዳታለች። እኛ መንፈሶች ነን አይደለም መኪና መንጠቅ የጠፋባችሁን የስልካችሁን pattern አስተካክለን እንሰጣችኋለን የቤታችሁን መግቢያ መውጫ መዋያና ማደሪያችሁ ላይ የምንጎማለለው እኛ ነን ።206ኛ ኮር የቀጠናውን ትግል ከፍ በማድረግ የሰራዊታችንን የማድረግ አቅም ከፍ በማሳደግ የጠላትን ቅስም እያነከተው ይገኛል። 14ኛ፣ 24ኛ፣ 34ኛ ክ/ጦሮች በመቀናጀት እየፈፀሙት ያለው ተግድሎ ያስመዘገቡት ድል ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል ። ሁለ ነገራችን ለትግሉ ሰጠነዋል ፍላጎታችን እና ህልማችንን ለአማራ ህዝብ ሲባል ሰውተናል ዛሬ ህዝብን ለማኩራት ለህዝባችን ነፃነት የምንሰሰተው ህይወት የለም። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳብ! አዲስ ተስፋ! የአፍብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

ገዳማቱ ላይ ተኩስ የከፈተው የአገዛዙ ሠራዊት ** የአረመናያዊ አገዛዙ ሠራዊት በገዳሙና በገዳማውያኑ ላይ ተኩስ ከፍቷል። ደቅ እና አካባቢውን ሲዘርፍና ሲያወድም የቆየው የአገዛዙ ሠራዊት ዛሬ ደግሞ
ገዳማቱ ላይ ተኩስ የከፈተው የአገዛዙ ሠራዊት ** የአረመናያዊ አገዛዙ ሠራዊት በገዳሙና በገዳማውያኑ ላይ ተኩስ ከፍቷል። ደቅ እና አካባቢውን ሲዘርፍና ሲያወድም የቆየው የአገዛዙ ሠራዊት ዛሬ ደግሞ ጣና ሐይቅ ላይ ወደሚገኘው ዳጋ እስጢፋኖስ ገዳም በመግባት ገዳማውያኑን እያዋከበ ይገኛል። የገዳሙ አባቶች "ቦታው የጸሎት ቦታ በመሆኑ የጦር መሣሪያ ይዞ መግባት አይቻልም" ቢሉም ሃይማኖታዊ ቦታዎችንና እሴቶችን ማውደም እና ማራከስ የየዕለት ግብሩ ያደረገው ጨፍጫፊው ሠራዊት ግን ወደ ገዳሙ ዘልቆ በመግባት ተኩስ ከፍቷል። መፍትሔው ማሸነፍ ብቻ ነው! አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ! አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የ102ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

"የአማራ ትንሳኤ በአንድነታችን እውን ይሆናል"!! ...የተፍረከረከው የጠላት ኃይል በተባበረ ክንዳችን ድባቅ ይመታል። አማራ እና አማራነት የኢትዮጲያ ምሰሶ ይሆናል።ይሄን ለማሳካት የሁላችንንም በጎ ተሳትፎ ይጠይቃል። አንድነት ስለጠየቅን ብቻ የሚሰጠን ሳይሆን በጥረታችን እና ለአንድነት የሚደረግ ተግባራዊ እንቅስቃሴም ይፈልጋል። አንድነትን መጠየቅ ራስ አርበኛ ዘመነ ካሴ ፣አርበኛ አስረስማረ ዳምጤ መሪዎቻችን እንደሆኑ ሁሉ ዋርካው ምሬ ወዳጆ፣ አርበኛ ሔኖክ አድሴ እና ሌሎች የሚኒልክ ዕዝ አመራሮች፣ አርበኛ ደሳለኝ ፣አርበኛ ባዩ አለባቸው እና ሌሎች የአሳምነው ዕዝ አመራሮች ፣አርበኛ ሀብቴ ወልዴ፣አርበኛ ሳሙኤል ባለድል እና ሌሎች የበላይ ዕዝ አመራሮች ፣አርበኛ ንጉሴ ዋለልኝ ፣ሻለቃ ክንዱ እና ሌሎች የቢዛሞ ዕዝ አመራሮችም መሪዎቻችን መሆናቸውን ከማመን ይጀምራል!! አማራ አንድ ድርጅት አንድ መሪ ያስፈልገዋል ስንል አርበኛ መከታው ማሞ፣ አርበኛ ደረጀ በላይ ፣አርበኛ ጌታ አስራደ እና ሌሎች የአፋኃድ መሪዎችንም አማራነታቸውን እና የድርጅታችን አካል እንደሚሆኑ አምኖ መቀበል ግድ ይላል። ያ ማለት ከፀረ አንድነት ተግባር መቆጠብ ማለት ነው። ይሄን ስናደርግ ቀሪው ሁለት(2)ቡድን ብቻ ይቀራል ማለት ነው።እነሱም:- ▶️ ልዩነታችንን የራሳችን ማጥፊያ መሳሪያ ያደረገው ብልፅግና እና የብልፅግና ሳይበር ሚሊሻ ▶️ የሰፈር ተንደባላዩ ተክለ ብአዴን እና አቅመቢስ ጎጠኛ። ማሳሰቢያ:- አማራ እና የአማራ ፋኖ ወደ አንድ እየመጣ በሄደ ቁጥር የብልፅግና የሳይበር ሚሊሻ እና ጎጠኛው ቡድን ድምበር የለሽ ግንኙነት ፈጥረው አዲስ የመነጣጠል ዘመቻዎች ይጀምራሉ። ሀሰተኛ ፌክ Fb አካውንት በመክፈት የመሪዎችን ስም ማጥፋት፣ የስልክ ቅጅዎችን አስመስሎ አየር ላይ ማዋል እና ህዝብን ውዥምብር ውስጥ የሚከቱ አጀንዳዎችን በተናበበ ሁኔታ ይለቃሉ። ይሄን ሁኔታ ቀድመን በመረዳት የጠላት እቅድ ተባባሪ ባለመሆን መተባበር ተገቢ ነው። አማራ ያሸንፋል !! በአራቱም ማዕዘን 24 ስዓት እየሰራን እንገኛለን ከታች ባለው ቴሌግራም ሊንክ ጆይን በማድርግ ይወዳጁን። https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk