ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
Kanalga Telegram’da o‘tish
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Ko'proq ko'rsatish4 133
Obunachilar
+224 soatlar
+4237 kun
+1 19130 kun
Postlar arxiv
https://www.facebook.com/share/p/1BoavNZJV6/ ይህ የወንድማችን የፊስ ቡክ አካውንት ስለ ለአስር ግዜ ስለተዘጋ ፎሎው አድርጉት
"ጎጃም መለኛ ነው ሀሞትን ያስተፋል
የማይበርደው ክንዱ እንደ እሳት ይፋጃል"
እነዚያ ማይክ የጨበጡ የጀነራሎች ክንድ ዛሬ ዝሏል
በመድፍና ታንክ ታጅበው የእድር ድንኳን ወጥረው ሲደነፉ የነበሩ የካድሬ ጉሮሮዎች ተከድነዋል! አበል ተከፍሏቸው ሚኒሽር አውርደው ጋቢ ለብሰው እየየ ሲሉ የነበሩ ሚኒሻዎችና የሚኒሻ ቤተሰቦች አቅም አጥሯቸው በጭንቀት ተውጠዋል።
አወ ጎጄ መለኛ ነው--- ዛሬ ላይ ያለውን ሳይሆን የነገን አበክሮ ያስባል ያሰላስላል።
አወ ጎጃም መለኛ ነው ----አይደነፋም አይፎክርም አይታብይም ጊዜን ጠብቆ ከአፈር ይቀላቅላል።
አወ ጎጃም ልባም ነው---የጀግና መፍለቂያ የእነአጅሬ ምድር የእሳት እረመጥ ነው።
ፎክሮ ጭንቅላት በሚበትን ጀግና የተሞላው ቴዎድሮስ ዕዝ ዛሬ በጎጃም ምድር የፈፀመው ገድል የቤተ መንግስቱን ትቢት ያስተነፈሰ ድል ተቀናጅቷል።
የዚህ አስደናቂ ጀብድ ባለቤት የሆነው 206ኛ ኮር በስሩ ባሉ ጠንካራ ክ/ጦሮች የጠላትን ሰራዊት በደም ሲያዘረው መዋሉ የአማራን ህዝብ ጮቤ አስረግጧል ።
የማይቋረጥ ተጋድሎ በድል ታጅቦ ይቀጥላል በዛሬው ድል ደስ የተሰኛችሁ ወገኖች እንኳን ደስ አላችሁ።
© Baye Desta per
+1
~~~~~~~~~~~~~~~|||
➔ በግራ እጅ የቀጠናውን ትግል ከውስጥ አቆርቋዥ መጠበቅ፣የጠላት ሠራጊዎችን ማፅዳት ፣ ወታደራዊ መዋቅርን በመከለስ ቀጠናውን ወደ ሚታወቅበት አጥቂነት ከፍታ መመልስ ችሏል።
➔ በቀኝ እጅ ዋናውን ጠላት ለመደምሰስ ወታደራዊ የውጊያ ዕቅዶችን ያወጣል። የቀጠናው ወታደራዊ ሥራዎችን በበላይነት እየመራ ትንታግ እና ቆራጥ የአዲሱ የአማራ ትውልድ የጦር መኮነኖችን አፍርቷል።
የአማራነት መር ትግል "ቀኝ ክንድ" ቢባል የተሻለ ነው። የአማራነት መር ትግል ከወሬ እና ድስኩር አልፎ ወደ ብረት መር ትግል ከተሻገረ በኋላ መንፈሰ ጠንካራ እና በሳል፣ ሁኔታ ለዋጭ ልበሙሉነት ባህሪያቶች ትግሉን ለሚመሩ ወታደራዊ አመራሮች ሊኖራቸው የሚገባ ነበር ተላብሷል ። እንደዚያ ሲሆን የአማራነት መር ትግል "ተሸካሚነት" ተንከባሎ ያልነካካው በራሱ ቅርፅ ላይ የሚቆም እና የአማራን ህዝብ ዕጣ ፋንታ በያኝ ይሆናል።
ቀጣይ ብዙ ገድሎችን ለማየት ዝግጁ መሆን ብቻ ነው!
አስቸኳይ መረጃ ‼️ሸር ይደረግ
ሰላም እንዴት ነህ 8 መኪና የመከላከያ ሀይል ምሽት ከማርቆስ ወቷል አንድ RBG እና አንድ ብሬን በፖትሮል ተጭኗል 8 ሲኖና fsr 2 ፖትሮል ዙ 23 አለ በነ እነራታ አድርጎ ወደ ሮቡ ገብያ ስናን ወጥቷል ሲሉ ለኢትዮ ፎረንሲክ ሚዲያ ምንጮች አድርሰዋል። ስናን አባጅሜዋች በሚገባ ሲገርፋቸው መዋላቸውን በቀን ዜናችን አጋርተናል የቀረውን ሀይል ለማትረፍ ተጨማሪ ሀይል ከደብረማርቆስ እያስጠጋ ነው።
ይህ በእንዲህ እያለ የ206 ኮር ተርቦት ደብረ-ማርቆስ ከተማ ዘልቀው በመግባት በጥላት ላይ የቦምብ በረዶ በማዝነብ ሁለት ፖሊሶች ወዲያውኑ ሲያሸልቡ ሌሎች 6 ፖሊሶች ከባድና ቀላል ቁስለኛ ሆነው ሆስፒታል መግባታቸውን ምጮች አክለው ገልጸዋል
ታህሳስ 24/2018 ዓም
ነበልባሉ ፎገራ ክፍለ ጦር ክርሥትያን ታደለ ብርጌድ!
የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት መነሻውን ከሊቦ ከምከሙ አዲሥ ዘመን አድርጎ በአምቦ ሜዳ፣ ቦረን መሥክና ርብ ካናልን በመጠቀም ወደ ፎገራዋ ወጠምብ ቀበሌ በመንቀሳቀስ የገበሬዎችን(አርሶ አደሮችን) የግል መሣሪያ ለመንጠቅ ገብቶ ነበር። ነገር ግን በነፍጠኛው ''ነበልባሉ ፎገራ'' ክፍለ ጦር አሃድ በሆኑት ''ክርሥትያን ታደለ'' ብርጌድ ከቀኑ 4:00 ጀምሮ እሥከ 11:00 ወጠምብ ቀበሌ ላይ ውጊያ ተከፍቶበታል። ወጠምብ ሚካኤል የጀመረው ውጊያ ወደ ሙርና፣ አማኑኤል፣ አውሥኮድ ካምፕ፣ ጎጃሞች ሚካኤል እና ጎንደር በር ተሥፋፍቶ ውሏል።
በዚህ ውጊያ 13 የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት(መከላከያ) ሲደመሰስ፣ 07 የሚሆኑት ደግሞ ከባድ ቁሥለኛ ሆነዋል። በጠላት ላይ ከፍተኛ የሆነ የሞራል፣ የቁሥና የአካል ኪሳራ ደርሶበታል።የአገዛዙ ቅጥረኛ የሆነው መከላከያ፥ የአማራ አርሶ አደሮችን የግል መሣሪያ የማሥወረድ ዕቅዱም ከሽፎ፣ ኪሳራውን ለመቀነሥ ከተለያዬ መዳረሻ ያሉ መከላከያዎችን የድረሱልኝ ተማጽኖ ሲያሰማም አምሽቷል።
የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት የሚፈጽመውን የግል ትጥቅ የማሥወረድ አቢያዊ ተልዕኮ መላው ዓምሐራ በአንድ እሥትንፋሥ ወግድ ማለት አለበት። አማራ የሆነ ሁሉ በዚህ የሕልውና ትግል መሣሪያውን አገልግሎት ላይ እንዲያውል የመጭውን ኦሮሙማ አውሬያዊ ድርጊት ለሕዝቡ ግንዛቤ መፍጠር የግድ ይላል። በሬህን ሸጠህ፣ እህልህን አቅንተህና መሬትህን ሸጠህ የገዛኸውን መሣሪያ ሊያሥወርድህ ለሚመጣ ነውረኛ የኦሮሙማ አገዛዝ ምላሽህ እምቢ መሆን አለበት።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን✊👊
አፋብኃ ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ ሜ/ጀ ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ሕ/ግ ክፍል ፋኖ ኃቅአለው ፀጋ አለባቸው
[ታሕሣሥ 24/2018ዓ.ም]
በ54ኛ ክ/ጦር ባሉ ሻለቃዎች በወትሮ ዝግጁነትና በወደፊት አቅጣጫዎች ላይ ምክክር ተደርጓል ።
➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠
ታህሳስ 23/2018 ዓ.ም
የሻለቃዎችን ወትሮ ዝግጁነት በመፈተሽ የ54ኛ ክ/ጦር የሻለቆችን የአደረጃጀት ስራዎች በመዋቅሩ ለአባሉ በዓላማቸው ላይ በስርፅት በመንገር ህዝባችን እና ድርጅታችን የመጠበቅ እና የማዳን ተግባር በመተባበር በአንድነት መስራት የጋራ ሀላፊነታችን መወጣት እንዳለብን አስተውሎት እንዲኖራቸው ተደርጓል።
ከአባሉ ጋር በጥልቀት በመወያየት ችግሮችን በጥልቀት በመለየት በመፍታት መግባባትና የትግሉን ዕድገት በተሻለ ግለት ማስቀጠል እንዲሁም በቀጠናው የተሻለ ከወትሮው በበለጠ በስነምግባር በማነፅ የወጣንለትን አላማ በማስገንዘብ በጥምረት ኦፕሬሽን መደረግ እንዳለበት የመግባባት ስራ ተስርቷል።
ታህሳስ 23/2018 ዓ.ም
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ
የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና
ቴወድሮ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
🔥#ልዩ_ኮማንዶዎች_ተመረቁ‼️
የደጋው መብረቅ ኮር ደጀን ክፍለ ጦር ለበርካታ ወራቶች ያሰለጠናቸውን ልዩ ኮማንዶ ፋኖዎች በደማቅ ሁኔታ አስመረቀ‼️
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር ደጀን ክፍለ ጦር ለሁለተኛ ዙር ለወራቶች ያሰለጠናቸውን በርካታ ልዩ ኮማንዶዎችን በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል::
ታህሳስ 24/2018 ዓ/ም ለወራቶች ሲሰለጥኑ የነበሩ ልዩ ኮማንዶ ፋኖዎች በደማቅ ስነ-ስርዓት ተመርቀዋል። በምርቃቱ ላይ የኮሩ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተው ተመራቂ ኮማንዶዎችን የእንኳን ደስ አላችሁ መልካም ምኞት ሲገልፁ፤ በሌላ መልኩ የአማራን ህዝብ በታማኝነት እንዲያገለግሉ ታሪካዊ ሃላፊነት የተሰጣቸዉ ሲሆን ከዚህ ጋር ተያይዞ ተመራቂዎቹ የተሰጣቸውን ሃላፊነት ባግባቡ ተሸክመው ህዝባቸውን ከገባበት ሁለንተናዊ የህልውና አደጋ እንደሚታደጉ ቃል ገብተዋል::
ስለሆነም በሰላሳ ክላሽ የተጀመረው የአማራ ፋኖ ትግል በአሁኑ ሰዓት ላይ ከእግረኛ ሰልጣኝ እስከ ልዩ ኮማንዶ ሰልጣኝ ብሎም ተመራቂ ፋኖዎችን የማብቃትና የማምረት እንቅስቃሴውን ለአማራ ህዝብ አኩሪና የማንነት ግዳጅም ጭምር ሲሆን ለፋሽስቱ ስርዓት ደግሞ የሞት ደብዳቤን ከመዳፉ ላይ የማስቀመጥ ያክል መሆኑን በተግባር የታየበት ወሳኝ ድል ነው::
ሰልጥነን እንዋጋለን እየተዋጋን እንሰለጥናለን!
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
©አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
24/ዐ4/2018 ዓ.ም
ባለሽርጡ ክፍለ ጦር የዛሬ ታህሳስ 24/2018 ዓ.ም ተጋድሎ በድል ታጅቦ ቀጥሎ የጠላት ሃይል ላይ ተጨማሪ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ በማድረስ ስድስት የነፍስ ወከፍ ክላሽ ማርከዋል::
የምስራቅ አማራ ኮር አንዱ ባለ ሽርጡ ክፍለ ጦር ዛሬ ታህሳስ 24/2018 ዓ.ም ንጋት ጀምሮ ሃብሩ ወረዳ ጊራና ዙሪያ ተጋድሎ በማድረግ በጠላት ላይ ከባድ ሰብዓዊ ኪሳራ በማድረስ አስር የነፍስ ወከፍ ክላሽ እና ወደ 5500 የሚጠጋ ተተኳሽና ሌሎች ወታደራዊ ቁሳቁሶች መማረኩን ይፋ ማድረጋችን የሚታወቅ ሲሆን አሁንም አመሻሽ ላይ የተረፈውን የጠላት ሃይል የማፅዳት ስራ ሰርተው ስድስት ተጨማሪ ክላሽ ማርከዋል::
በዚህም በዛሬው ከባድ ትንቅንቅና ተጋድሎ ጠላት ከባድ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ አስተናግዶ አሁን ላይ እርስ በርሱ እስከ መታኮስ ደርሶ ተጨማሪ ሰብዓዊና ስነልቦናዊ ጉዳት ማስተናገዱን ለማወቅ ችለናል:: ክስተቱ የግፈኞች ጀንበር መጥለቋን ግፈኞች መጨረሻቸው እርስ በርስ መበላላት ብሎም መላ ቅጥ የሌለው ሽንፈት መሆኑን በተግባር የገለጠና ያሳየ ነው::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ታህሳስ 24/2018 ዓ.ም
ሰበር የድል ዜና
በ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር ታላቅ ጀብድ ተፈፀመ
በቀን 24/04/2018 ዓ.ም አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የ206ኛ ኮር የ24ኛ ክ/ጦር ጮቄን በመቆጣጠር ፋኖን አጠፋለሁ ብሎ ከስናን ወረዳ ዋና ከተማ ረቡዕ ገበያ ተነስቶ ዳንጉሌ ቀበሌን ለመዉረር እንቅስቃሴ ባዳረገዉ ጡት ቆራጭ ሰራዊት ላይ ታላቅ ጀብዱ ስራ። በዚህ አስደናቂ ተጋድሎ የ24ኛ ክ/ጦር ቃኝና መሃንዲስ፣ ስናን አባጅሜ ሻለቃ፣ የቦቅላ አባይ ሻለቃና ደባይ ጮቄ ሻለቃ ከዚህ በተጨማሪም ጀግናው የስናን አባጅሜ የኋላ ደጀን አባት አርበኞች ጦር እንዲሁም በ206ኛ ኮር የ14ኛ ክ/ጦር አካል የሆነዉ ንጉስ ተክለ ኃይማኖት ሻለቃና የ109ኛ ኮር 99ኛ ክ/ጦር አካል የሆነዉ በላይ ዘለቀ ሻለቃ ተሳትፈዉበታል። በዚህ አዉደዉጊያ ከአንድ ሻለቃ በላይ የጠላት ሀይል ተደምስሶ ጥቂት ሀይል ብቻ እግሬ አዉጭኝ ብሎ ወደመጣበት ረቡዕ ገብያ ከተማ ገብቷል። በምርኮ መዓት የተንበሸበሸዉ በዚህ አዉደዉጊያ በርካታ የነፍስወከፍ፣ የቡድንና የመካናይዝድ መሳሪያ ተማርኳል። በተመሳሳይ ሻለቃ አመራሮችን ጨምሮ ቀንደኛ የሚባሉ የአረመኔዉ የብልፅግና አገልጋዮች ተደምስሰዋል። ከነዚህም መካከል ይህንን አረመኔ ሰራዊት እየመራ ሲንቀሳቀስ የነበረዉ አየልኝ የተባለዉ ፖሊስን ጨምሮ በርካታ የጠላት ሀይል ተደምስሷል።
በዚህ ታላቅ አውደ ውጊያ የተገኙ ድሎች
- 2ዲሽቃ:01ሞርተር 05 ብሬል 01 ስናይፐርና በጣም በርካታ የነፍስ ወከፍ ክላሽ መሳሪያ ተማርኳል
ትንቅንቁ አሁንም እንደቀጠለ ነዉ
ዝርዝር የአዉደጊያ መረጃዎችን በሰፊዉ ይዘን እንመለሳለን
ክብር ለጀግኖች የአማራ ፋኖ ሰማዕታት
አዲስ ትዉልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ
ኃይለማርያም ክበር ተመስገን
አፋብኃ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር ሚዲያ ክፍል
አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የ24ስዓት የተጋድሎ ውሎ
ታህሳስ 24/2018 ዓ.ም
_______፩
አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር ከሌሊቱ 11:30 ጀምሮ ከምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረማርቆስ ከተማ በ27ኪ.ሜ ርቀት ከምትገኘው ረቡዕ ገብያ ከተማ በመነሳት ወደ ዳንጉሌ ቀበሌ እንቀሳቀሳለሁ ባለ ጠላት ላይ ባደረገው ትንቅንቅ የሜጀር ጀነራል ብርሀኑ ጥላሁን ሰራዊት አመድ በማልበስ
1 ሞርተር
1 ዲሽቃ
4 ብሬን
ስናይፐርን ጨምሮ ለቁጥር የሚከብድ የነፍስ ወከፍ መሳሪያ ማርኳል።
ለስድስት ቀናት ተንኳቶ ከደብረ ማርቆስ ተነስቶ ወደ ጮቄ ተራራ ለመውጣት በተንቀሳቀሰው የአረመኔው ሰራዊት ላይ የተቀናጀ ውጊያ የከፈተው 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር ጠላትን በመረፍረፍ ታሪክ ሰርቷል።
የ206ኛ ኮር 14ኛ ክ/ጦር አሃዶች በዕሮቡ ገበያ በመግባት የጠላትን ኃይል በማዛባት ግዳጇን በብቃት ተወጣለች።
በተመሳሳይ በዚ አውጊያ 109ኛ ኮር 99ኛ ክፍለጦር ሽፋን በመስጠት ሲያግዝ ቆይቶ ቆረጣ በመግባት 1ዲሽቃ መማረክ ችሏል።
ከፍትኛ ቁርጠኝነትና ጀግንነት በታየበት በዚህ ውጊያም ከአንድ ሻለቃ በላይ የአረሠኔው ሰራዊትን መደምሰስ ተችሏል።
_______፪
ከተማ ውስጥ መሽገው ሕዝብ ሲሚያሰቃዩ የነበሩ አመራሮችን በመምታት መሳሪያቸውን በመያዝ ፋኖን ተቀላቀሉ።
ወጣት ዘላለም በለጠ ይባላል። ተወልዶ ያደገው ሰከላ ወረዳ አቻይታ ቀበሌ ሲሆን። የሚኖረው አዲስ አበባ ነበረ። ነገር ግን ጠላት አጉት የሚኖረውን የአጎቱን ልጅ ምላሱንና ብልቱን መቁረጡን ሲሰማ ከአዲስ አበባ ወደ ሰከላ ወረዳ ግሽ አባይ ከተማ በመመለስ ሻለቃ መሪውን በጩቤ ወግቶ ክላሹንና ሽጉጡን በመማረክ የአጎቱን ልጅ ገዳይ በመበቀል 44ኛ ክ/ጦርን ተቀላቅሏል።
በተመሳሳይ ይልማና ዴንሳ ወረዳ አዴት ከተማ ላይ ሻንበል በለጠ የተባለን የሚሊሻ ሀላፊ መሳሪያ እሳት የላሰው ጀግና ወጣት መሀል ከተማ ላይ በዱላ ማጅራቱን ብሎ ሰደፍ ክላሽ ማርኮ 102ኛ ኮር 11ኛ ክፍለጦር አንሙት ያዛቸው ሻለቃን ተቀላቅሏል።
ግፍ ሕዝብን የበለጠ እንዲታገል በማድረግ ትግልን የበለጠ ያፋጥናል ። ስለሆነም ግፍን ተፀይፈው ፋኖን የተቀላቀሉ ወንድሞችን እንኳን ደና መጣችሁ እንላለን።
አዲስ ትውልድ፣አዲስአስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !
አፋብኃ| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ታህሳስ 24/2018 ዓ.ም
የድል ዜና
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር በፍቃዱ በላይ ክፍለ ጦር የፍቃዱ አበበ ሻለቃና ትግስት ይርሳው ሻለቃ በትናንትናው ዕለት በወሰዱት የደፈጣ ውጊያ የአረመኔው አብይ አህመድ ጡት ቆራጭ ኃይል ሻለቃ የ15ኛ ክፍለጦር አየር ወለድ ኮማንዶ አዛዥ ኮሌኔል ጌትዬ እና እግርኛ እንዲሁም አጃቢዎች ላይ ሳላይሽ ከተማ ያለውን የጠላት ካንፕ ላይ ባደረገው ከበባ መቶ አለቃው እና ምክትል መቶ አለቃውን እንዲሁም 14 የአገዛዙ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት ተደምስሷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በትናትና ዕለት ማለትም በቀን 23/4/2018 ዓ.ም ከቂቃ ተነስቶ ወደ ጉንዶ መስቀል ዲሽቃ ጠምዶ በፓትሮል እንደፈለገው ሲሮጥ የነበረው የብርሃኑ ጁላ ኃይል የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር በፍቃዱ በላይ ክፍለ ጦር የፍቃዱ አበበ ትግስት ይርሳው ሻለቃ በወሰዱት የደፈጣ ውጊያ በመገን ሸዋ መርሓቤቴ አውራጃ የደራ አማራን ህዝብን ለማጥፋት የጥፋት ተልኮ ይዞ ህዝባችንን እያሰቃየ የነበርውን አርመኒያዊ የብልፅግና ኃይል ይዞት ሲንቀሳቀሱበት የነበረውን ተሽከርካሪና ድሻቃ ተኳሹና ምድብተኞ ጭምር ተደምሰዋል።
በመሆኑም በትናንትናው ዕለት እርምጃ የተወሰደበት የብልፅግና ወንበር አስጠባቂው አየር ወለድ ኮማንዶ ኃይል እግርኛ ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ ሆኖ ያመሸበት ድል ከመሆኑም አንፃር በአገዛዙ ቤት ሽብር ተፈጥሮ እየተጨነቀ መሆኑን መርጃዎች ያሳያሉ። በምድርም አይደለም በሰማይ መብርቅ ቢያዘንብ እኛ የአሳምነው ልጆች ይህንን አማራ ጠሉን ኃይል በገባበት ገብተን የህዝባችን ነፃነት በእጃችን የምናስገባበት ቀን ቅርብ ሲሆን ይህ የብልግና ኃይል የክንደ ነበልባሎችን የፋኖን በትር መቋቋም ሲያቅተው ከፋኖ ነፃ ያልወጡ ቀጠናዎች ላይ አረመኔያዊ ኃይል የሸዋ ደራ አማራ ህዝብን ሳልጨርስ እንቅልፍ አልተኛም ያለው የኦነግ ሸኔ ሰራዊትና ጡት ቆራጩ የሽመልስ አብዴሳ ልዩሀይል በህዝባችን ላይ እያደረሰ ያለው ግፍና ሰቆቃ ወደርተኛ የለውም። የማህበረሰባችን እህል የፉኖ ሬሽ ነው በማለት ይዘርፋል፥ በከባድ መሳሪያ የቀንድ ከብቶች ከነ እረኞቻቸው እየተጨፈጨፉ እያሰቃየ ስለሆነም ማህበረሰቡ ራሱን ከዚህ ጠላት ራሱን እንዲጠብቅና ለጥፋት ሰለባ እንዳይሆን ከወዲሁ መልዕክታችንን ማስተላለፍ እወዳለሁ።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
ታህሳስ 24/04/2018 ዓ.ም
