ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Kanalga Telegram’da o‘tish
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Ko'proq ko'rsatish3 606
Obunachilar
+6624 soatlar
+5877 kun
+1 04130 kun
Postlar arxiv
አያሌ ጠላት ረገፈ!!
የዘመናት ትውልድ የጀግንነት ምንጭና የማይቋረጥ የጀግንነት ጅረት አውራሹ የዓፄ ቴዎድሮስ ልጆች በጎንደር ጣቁሳና አለፋ ለሁለት ቀናት በተከታታይ ባደረጉት ጠንካራ ተጋድሎ ከፍተኛ ጠላት ረገፈ!!
በ4ቱም ማዕዘን ተግተልትሎ ለወረራ እና ለጥፋት ያቀናው የፋሽስቱ ዓባይ አህመድ ሰራዊት የአሞራ ሲሳይ ሁኖ ረግፏል።
የአፋብን በላይ ዕዝ መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር አድዋ ክ/ጦር፣ቋራ ኦሜድላ ክ/ጦር እና ካራ ማራ ክ/ጦሮች ከአፋብን ጎንደር ጠ/ግዛት ዕዝ በጌምድር ክ/ጦር ጣና ብርጌድ ጋር በመጣመር በብርሃኑ ጁላ ሰራዊት ላይ ከፍተኛ ድምሰሳ ፈፅመዋል።
ህልውናችን በአርበኝነታችን!!
ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ
ሰበር ዜና
የአብይ አህመድ እና የብርሀኑ ጁላ ልጆች ባሉበት አውደ ውጊያ በርካታ የብልፅግና ስልጣን አስጠባቂዎች የሆኑት ሲደመሰሱ! ቀሪዎቹ ደርዘን ሙሉ ቁስለኞች ጤና ጣቢያን የሲቃ ድምፃቸውን እያቋረሩ ይገኛሉ!!
አፋብን ሚኒሊክ እዝ 106ኛ ኮር 34ኛ ክፍለ መጋቢት 14/2018 ዓ/ም ከጋሸና ወደ እስታይሽ አቅጣጫ የጥፋት ፈረሱን ጉግስ ሲጋልብ በነበረ የፋሽስቱ ሰራዊት ላይ መራር ቅጣት የተወሰደ ሲሆን! በዚህም የአውደ ውጊያም የተገኙ ቱርፋቶች አንድ ማዕረጉ በወል ያልታወቀ የመከላከያ አመራር ወደማይቀረው ሲሸኝ፤
በ29ኙ ላይ የድምሰሳ እርምጃ የተወሰደ ሲሆን፤ ቀሪዎች ከ31 በላይ የጁላ ሰራዊት ከባድ ቁስለኛ ተደርገዋል። ጥምር ጦር እያሉ የሚያሞካሹት ሆድ አደር ሰራዊታቸው ጥምር አስከሬን ተደርጓል።
በዚህ አውደ ውጊያ የአቶ አብይ አህመድ ከዝናሽም ይሁን የደቀለው ልጅ የለም። እድሁም የብርሀኑ ጁላ የቁባት ልጅም በለሉበት ከየትም ተጋፈው የመጡ የስልጣን አስጠባቂዎች ላይ እየድርሻቸው ተለብልበው ገሚሱን አስከሬኑን ሳያነሱ ሌላውንም ቁስለኛ ጥለው እግሬ አውጭኝ የዘወትር ነፍስ አድን ፍርጠጣቸውን መርጠው ወደየመጡበት በሀዘን ኮፍያ ተከልለው ተመልሰዋል።
ከቀኑ 10:00 ሰዓት የተጀመረው አውደ ውጊያ እስከ አመሻሽ 1:30 ሰዓት የዘለቀ ሲሆን በርካቶች የስርዓቱ ወታደሮች ከጥርናፊያቸው ተበታትነው በፋኖዎች እየተለቀሙ ይገኛሉ። እስካሁን በቁጥር በውል ያልተረጋገጡ የመከላከያ ሰራዊትና የአድማበትን ሰራዊቶች አጋጣሚውን በመጠቀም ከጥርናፊ አምልጠው እራሳቸውን ከከንቱ ሞት እያዳኑ ይገኛሉ።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ #106ኛ ኮር ህ/ግ መምሪያ ሀላፊ!
መጋቢት 14/2018 ዓ.ም
+1
በግፍ ደም ማፋሰስ ስልጣን ለማራዘም የወሰነው
የዓብይ አገዛዝ ዛሬም በጎንደር ክፉኛ ተመቷል!!
በነ አባድፈን መሳፍንት ተስፉ፣በነ ደጃች አያሌው ብሩ ቀዬ ዳባት አረደጃን አካባቢ ሲክለፈለፍ የዘለቀው የምርኮኛው ብርሃኑ ጁላ ሰራዊት እንደተለመደው ከኮሶ የመረረ ሽንፈትን በጀግናው ሰራዊታችን ተጎንጭቷል።
በዝምተኛው መብረቅ ዘራይ አዝመራው ስም የተሰየመው በላይ ዕዝ ደጃዝማች 4ኛ ኮር ዘራይ ክ/ጦር ሸጋው ውበት ብርጌድ በተከታታይ ሳምንታት በሚወስዳቸው የተጠና ኦፕሬሽኖች በቀጠናው ጠላት እንደ ሰም ቀልጦ እንዲቀር እያደረገ ነው።
መጋቢት 14/2018 ዓ.ም ወደ ብርጌዱ ጠንካራ ይዞታዎች ተግተልትሎ የዘለቀው ግፈኛ ሰራዊትም በእሳት አለንጋ ተገርፎ መራር ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳትን አስተናግዷል።
*15 የተደመሰሰ
* 15 ቁስለኛ ሲሆን
* 25 ነፍስ ወከፍ የጦር መሳሪም ተማርኳል።
ከዳባት ከተማ ቅርብ ርቀት ቀርሃ ቀበሌ በተደረገው የአፈሙዝ ክርክር ሽንፈት የገጠመው ግፈኛ የዓብይ የታጣቂ ስብስብ ቀሪው ነብሴን አውጭኝ ብሎ ወደ መጣበት ዳባት ሸሽቷል።
አፋብን በላይ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ!
ስሜ አስር አለቃ ጌታሰው አዳነ ነው። በቀድሞ ዘመኔ ውስጥ በRepublican Guard ክፍል ውስጥ በታማኝነት እና በጥልቅ ዲሲፕሊን የተሞላ አገልግሎት አበረከትሁ። በትምህርቴም በBSc degree በነርሲንግ ተመርቄ፣ #ከ801 ተመራቂዎች መካከል አንደኛ በመውጣት ከፍተኛ ውጤት አሳይቻለሁ። በዚህ ስኬትም ምክንያት #በምርኮኛው #ከፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ መሆኔ የማይረሳ ክብር ነው።
በውትድርና ያሳለፍኩት ጊዜ በጥንካሬ፣ በትእዛዝ መከበር እና በሙያዊ ብቃት የተገነባ ነበር። ነገር ግን ጊዜ ሲቀጥል እውነታዎችን በዓይኔ ሲገለጡ ልቤ ዝም ብሎ ሊቆይ አልቻለም። በአገር ውስጥ የተፈጠረውን የፖለቲካ ሁኔታ፣ የሕዝብ መከራና የፍትህ እጥረት በቅርብ ስመለከት እኔ እንደ ሰው እና እንደ ሙያዊ ሰራተኛ ዝም ብሎ መቆየት አልቻልኩም።
በዚህ ምክንያት የብልፅግና/ኦህዴድ ስርዓትን በመቃወም የአማራ ህዝብ ነፃነት እንዲመጣ በማመን ወደ አማራ ፋኖ ተቀላቀልሁ። ወደዚህ ትግል ስገባ የነበረኝ ዋና እምነት አንድ ነበር—አንድም ታጋይ በሕክምና እጥረት መሞት የለበትም። ይህን እምነት በመሸከም በሙያዬ እውቀት እና በልምዴ ትግሉን ለማጠናከር ተጋለጥሁ።
ከዚህ በተጨማሪም ከትግል አጋሮቼ ጋር በመሆን የነበሩ አንዳንድ የሃሳብ ልዩነቶችን በግልጽ ውይይት በመፍታት ትግሉን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሻሻል እንደ ኃላፊነት ተመልክቻለሁ።
ነገር ግን ባለፉት ሶስት ዓመታት ያየሁት እና ያሳለፍኩት ሁኔታ እጅግ ከባድ ነው። በድሮን ጥቃት እና በተለያዩ ከባድ መሳሪያዎች የተፈጸመው የሕዝብ መከራ በቀጥታ ስመለከት ልቤ ተሰበረ። በእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ በውትድርና መቆየቴ ራሴን እንድጠይቅ አደረገኝ።
ስለዚህ ዛሬ በግልጽ ልብ እና በቅንነት ለአማራ ህዝብ #ይቅርታ እጠይቃለሁ። የተፈጸመው ጉዳት ቀላል አይደለም፤ ነገር ግን እውነትን መቀበል የመጀመሪያ እርምጃ ነው።
ቀሪውን ዘመኔን በሙሉ ታማኝነት፣ በቅንነት እና በሙያዊ ብቃት ለሰፊው የአማራ ህዝብ ለማገልገል ቃል እገባለሁ። ይህ ቃል ቃል ብቻ አይደለም—በተግባር የሚገለጥ ኃላፊነት ነው።
እንኳን ደህና መጣህ!!
+3
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ፣ የደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ፣ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር የሰባት ለሰባ በካራለጎማ ቀበሌ ከማህበረሰቡ ጋር ሰፊ ውይይት አካሔደ!!
ሆኖም የሰባት ለሰባ አዛዥ አርበኛ አረጋ ሙሉነህ እና የክፍለ ጦሩ ወታደራዊ አስተዳደር አርበኛ እንዳለ ሸዋዬ በተገኙበት የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ከተመሰረተ ጀምሮ ዛሬ የደረሰበት የፖለቲካና የወታደራዊ ቁመና፣ የአማራ ሕዝብ ለህልውናው የሚያደርገው ትግል የመጨረሻ ምዕራፍ ማሳያ መሆኑን ለማህበረሰቡ የድርጅቱን መርህና ዓላማ ለሕዝቡ ሰጠዋል።
ሕዝቡ የራሱን ልጆች የትግል ጉዞ በትኩረት ከአደመጠ በኃላ የሕዝቡ መኖርና ነፃነት የሚረጋገጠው በዚህ የጋራ ክንድ መሆኑን አፅንዖት ከመስጠትም በላይ እናንተ ልጆቻችን ናችሁ እስካሁን ያስመዘገባችሁት ድል ለኛ ኩራትና ተስፋ ነው።ፋኖ እስካሁን ባስመዘገበው ድል ያለውን ከፍተኛ እርካታም ነው። ልጆቻችን ለኛ የቁም ዋስትና ናቸሁ።
በመጨረሻም ማህበርሰቡም ከፋኖ ጎን ቆሞ እስከ ድል መጨረሻ ድረስ አብሮ እንደሚዘልቅ ቃል በካራለጎማ ቀበሌ የታየው ውይይት፣ በትግሉና በሕዝቡ መካከል ያለውን የማይበጠስ ሰንሰለት ይበልጥ አጥብቆታል በማለት ውይይት በሰላም ተጠናቋል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!
የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ አማረ ታዘዘ !!
መጋቢት 14/07/2018 ዓ.ም
አራት የአድማ ብተና አባላቶች አንድ ብሬን እና ሶስት ክላሽ በመያዝ የፋኖን ትግል ተቀላቀሉ::
ከብልፅግ ና አገዛዝ ጋር በመወገን ህዝባችን ላይ ዘር ማጥፋት አንፈፅምም በቃን ያሉ የ አድማ ብተና አባላቶች አንድ ብሬን እና ሶስት ክላሽ በመያዝ ወደ አፋብን ምኒልክ ዕዝ 106ኛ ኮር ተቀላቀሉ:: የኮሩ አመራሮችም አቀባበል አድርገውላቸዋል::
ከዚህ ጋር ተያይዞም የ106ኛ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ ሻለቃ ሃብቴ እባቡ በአቀባበል ፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው የእንኳን ወደ ህዝባችሁና ወንድሞቻችሁ ፋኖዎች ደህና መጣችሁ መልክትን አስተላልፈዋል።
የፋኖን የህልውና ትግል የተቀላቀሉ የ አድማ ብተና አባላቶች አማራን ህዝብ የህልውና አዳጋ ለመቀልበስ መጥተናል ሲሉ ተናግረዋል። አያይዘውም በአድማ ብተና ውስጥ ሙሉ ሰራዊቱ ወደ ፋኖ መቀላቀል ይፈልጋል። የአማራ ፋኖ አንድነት (አፋብን) ከተመሰረተ በኋላ ጠቅላላ ሰራዊቱ ወደ ፋኖ መቀላቀል ይፈልጋል ሲሉ መልክታቸውን አስተላልፈዋል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
መጋቢት 14/2018 ዓ.ም
ዋሲል ክፍለ ጦር ለወራት የሰለጠኑ ምልምል ፋኖዎችን አስመረቁ::
በአፋብን ምኒልክ ዕዝ ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር ስር የሚገኘው ዋሲል ክፍለጦር ከስድስት ወራት በላይ ሲያሰለጥናቸው የነበሩ የ6ኛ ዙር ሰልጣኞችን በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል።
በምረቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ የጃማ ቀጠና የሀገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶችን ጨምሮ የክፍለጦርና የሬጅመንት አመራሮች የተገኙ ሲሆን፡ የሃይማኖት አባቶቹና የሀገር ሽማግሌዎቹ "የአካባቢውን ሰላምና ደህንነት የሚያስከብርና የአማራን ሕልውና የሚታደግ እንዲሁም ፍትሕ ርትዕ የሚያሰፍን ብቁና ንቁ የፋኖ ኃይል መገንባቱ እንዳስደሰታቸው ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።
በተለይ የመስጂድ ኢማም የሆኑ ትላልቅ የሃይማኖት አባቶች፡ ዋሲል ክፍለ ጦር የአማራን ሕልውና ለመታደግ ወጣቱን ኃይል በማሰልጠንና በማደራጀት እየሰራ ያለውን ስራ አድንቀውና አመስግነው "ይህ ተከታታይ የማሰልጠንና የማብቃት ሂደት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት በማሳሰብ፡ ለሰራዊቱ ያላቸውን ድጋፍና አጋርነት በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።
ይህ ክፍለጦሩ በየቀኑ ከሚያደርገው ውጊያ ጎን ለጎን ያልተቋረጠ የስልጠና መርሃ ግብር በማካሄድ የጠላትን ቅስም የሚሰብር ብቁና እጅግ ጠንካራ ኃይል የመገንባት አቅሙን ያሳየበት ነው ተብሏል።
ሰልጥነን እንዋጋለን እየተዋጋን እንሰለጥናለን!
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
መጋቢት 14/2018 ዓ.ም
ክፍለጦሩ 3 ብልፅግና ያሰማራቸውን ዘራፊዎች በቁጥጥር ስር ያዋለ ሲሆን ለወረራ በመጣው የብልፅግናው የጫካ ክንፍ የሸኔ ዘራፊ ቡድን ላይ በወሰደው እርምጃ የቡድን መሳሪያ መማረኩን አስታወቀ።
አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ
መጋቢት 14/2018ዓ.ም
ሰራዊታችን ብልፅግና ያሰማራቸውን የህዝብ መከራ የሆኑ አረሞችን በመንቀል የትግላችንን ህዝባዊነት እያሰመሰከረ ይገኛል።
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ አምደ ፅዮን ኮር የራስ አበበ አረጋይ ክፍለጦር ከማህበረሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ለበርካታ ወራቶች ሹፌሮችን እና ባለሀብቶችን በማገት ከፍተኛ ገንዘብ በመጠየቅ ሲዘርፉ ከነበሩ የወንበዴዎች ግበረ-አበሮች ውስጥ ሶስቱን (3) ከነዘረፉት በርካታ ገንዘብ እና ከሁለት ታጋቾች ጋር የክፍለጦሩ ቃኝ እና ከሻለቆቹ የተወጣጡ ቃኝዎች ባደረጉት ልዩ ኦፕሬሽን በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ትላንትን መጋቢት 13 ቀን 2018ዓ.ም በእንሳሮ ወረዳ እና በሳያደብርና ዋዬ ወረዳ በዝርፊያ ስራ ላይ ተሰማርተው ነጋዴወችንና ሹፌሮችን ብሎም በአካባቢው የሚገኙትን ሀብታም ገበሬወችን በማገትና ዋሻ ውሰጥ በመሰወር ከፍተኛ የገንዘብ መጠን በመጠየቅና በማሰከፍል ለአንድ ዓመት ያክል ሲዘርፉ የቆዩና ከቡድኑ ዘጠኝ (9) አባላት ወስጥ ሶስት (3) አባላቱን ጀግናው የራስ አበበ አረጋይ የመንፈስ ልጆች የትግላችን ነቀርሳ፣የህዝባችን መከራ፣ የአገዛዙ የጫካ ስራ አስፈፃሚዎችን በቁጥጥር ስር አውለን ምርመራ ጀምረናል ሲል የራስ አበበ አረጋይ ክፍለጦር የህዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ ፋኖ ሽታው አሻግሬ ለኮሩ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ክፍል በላከው መረጃ አስታውቋል።
ክፍለጦሩ የዘራፊዎችን ስም ዝርዝር ይፋ ያደረገ ሲሆን፣
1ኛ. አይዳኝሁም አሰፋው
2ኛ. አይናለም ግዛው እና
3ኛ. ብሩክ አስፋው የተባሉትን የብልፅግና ተላላኪ ዘራፊዎችን በመግለፅ የታገቱ ግለሰቦችን ከፍተኛ ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ በማስለቀቅ በዘራፊዎች የተወሰደባቸውን 400,000ብር ሲያስመልስ ተበዳዮችም ለክፍለጦሩ ምስጋናቸውን ማቅረባቸውን አርበኛው በመልዕክቱ አስታውቋል። ።
ይሕ በእንዲሕ እንዳለ በዛሬው ዕለት በፊቸ ሰላሌ ወረዳ እንጓለላና ሸበል ፋጢ ቀበሌወች ላይ የስርዓቱ ሌላኛው ዘራፊ ቡድን የሆነው የኦሆዴድ ብልፅግናው የጫካው ክንፍ በመሆን ከአገዛዙ ጋር ተናቦ እየሰራ የሚገኘው እራሱን ኦነግ ሸኔ ብሎ የሚጠራው ዘራፊ ቡድን እንደለመደው የጥፋት አላማውን አንግቦ ህፃናትንና ሸማግሌዎችን ለመግደልና ዝርፊያ ለመፈፀም አቅዶ የመጣ ቢሆንም ነገር ግን አናብስቶቹ የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የራሰ አበበ አረጋይ ክፍለጦር የአርበኛ አሊ ሻለቃ እና የቀጠናው የሚገኘው የአርበኞች ጦር ሰራዊት ከበባ ውሰጥ በማሰገባት ሲቀጠቀጥ ያረፈደ ሲሆን የተረፈው እግሬ አውጭኝ ብሎ ሲፈረጥጥ ይዞት የመጣውን ከብልፅግና የተበረከተለትን አዲስ ብሬንና ከነ ሸንሸሉ ከያዘው ተተኳሽ ጋር ለጀግኖቹ የራስ አበበ አረጋይ ክፍለጦር አስረክቦ መፈርጠጡን ክፍለጦሩ በግንባር መረጃው አስታውቋል።
ክብርና ሞገስ ለትግሉ ሰማዕታት!!
ድል ለፋኖ!!
አንድነታችን አሸናፊነታችን!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የአፄ አምደ ፂዮን ኮር ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ክፍል
መጋቢት 14 /2018 ዓ.ም
+1
"ያ ቀበቶውን ሳይቀር እናስፈታዋለን ተብሎ ተፎክሮበትና ከምድር ጦር እስከ ሰማይ ጄትና ድሮን ተዘምቶበት የነበረው አማራ፡ ዛሬ ላይ ደርቦ ደራርቦ ማራኪ፣ መርጦ መራርጦ ማርኮ ታጣቂ ሆኗል።
አጃኢብ ነው!"
14/ዐ7/2018 ዓ.ም
ሰበር የድል ዜና!!!
የአገዛዙ ጥምር ሰራዊት ዙ-23 ተኳሽን ጨምሮ በፋኖ ብርቱ ክንድ እየተረፈረፈ ይገኛል።
የአገዛዙ ግሳንግስ ጥምር ሰራዊት ያለ የሌለ ሰራዊቱን በየአቅጣጫው ሰብስቦ መነሻውን ጎንደር በማድረግ ወደ ደልጊ ከተማ ከገባ በኃላ ትናንት መጋቢት 13/2018 ወደ አለፋ ወረዳ ሻሁራ ከተማ ለመግባት ሙሉ ቀኑን በእግሩ ሲማቅቅ ሲወጣ ሲወርድ የዋለ ሲሆን ተናዳፊዎቹ አፋብን በላይ ዘለቀ ዕዝ የመይሳው ካሳ (፪ኛ) ኮር ቋራ ኦሜድላ ክ/ር፣ ካራማራ ክ/ር እና አድዋ ክ/ር በጦር መሀንዲሶች በኮሩ ም/ሰብሳቢ አርበኛ ባበይ አንባየ፣ ወታደራዊ አዛዥ አርበኛ በሊሁን ጌታቸው ፣ ዘመቻ አርበኛ ጌታቸው አማረና በሁሉም የጦር ጠበብት የክ/ር ወታደራዊ አዛዦችና ዘመቻዎች እየተመራ እንዲሁም አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ በጌምድር ክ/ር ጣና ብርጌድ በአንድ በመጣመር የጠላትን ሰራዊት ስቦ ወደ ሙት ወረዳ ቀለበት ውስጥ በማስገባት ቀኑን ሙሉ በየሜዳው የከባድ መሳሪያ የጭንቀት ተኩስ ሲያደርግ የዋለ ሲሆን አድፍጦ የተሻለ አሰላለፍ ሲያመቻች የዋለው ነበልባሉ ፋኖ ከቀኑ 9:00 ስአትገደማ ጀምሮ እስከ ምሽቱ 1:00 ስአት አምቹሀ ከምትባል ቀበሌ በሁሉም አቅጣጫ በቀጥታ በተሰነዘረበት የማጥቃት ዘመቻ የአብይ ተስፋ ቆራጭ ሰራዊት ክፋኛ ሲረፈረፍ አምሽቷል። ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሙትና ቁስለኛ ከመሆኑ ባሻገር ሰፊ ቀጠና ሸፍኖ ሲንቀሳቀስ የነበረውን ወደ አንድ ተሰብስቦ ተራራ ላይ በመውጣት ከበባ ውስጥ የገባው የጠላት ሀይል ሙሉ ሌሊቱን የጭንቀት ተኩስ ሲተኩስ አድሯል። ስለሆነም በቀጣይ የዜና መሰናዶአችን አህዛዊ የድል ዜናዎችን አጠናክረን የምናቀርብ ይሆናል።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ (፪ኛ) ኮር የህ/ግ
መጋቢት 14/2018
+2
በሰርጅካል ኦፕሬሽን የጠላት ሻለቃ መሪ መሀል አስፓልት ማጋደም ተችሏል‼️
የ101ኛ ኮር 35ኛ ክፍለ ጦር አባላቶች ወርጌሳ እና መርጦ ከተማ ላይ ታላቅ ጀብድ ፈፀሙ::
101ኛ ኮር 35ኛ ክፍለ ጦር ውርጌሳ ከተማ ላይ ሰርገው በመግባት የጥላትን ሻለቃ መሪ በመደምሰስ መገናኛ ሬዲዮ እና የእጅ ስልክ አንስተው በመውጣት ታላቅ ጀብድ ፈፅመው ድል አስመዝግበዋል::
በተመሳሳይ 35ኛ ክፍለ ጦር መርጦ እየሱስ በመግባት አንድ ጓድ (ቲም) የጠላት ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ጀብድ ፈፅመው ድል ተጎናፅፈዋል::
ከዚህ ጋር ተያይዞም አገዛዙ የፋኖን ክንድ መቋቋም ሲያቅተው የበቀል አፈሙዙን ወደ ንፁሃን በማዞር ወልድያ ከተማ ልዩ ቦታው መቻሬ አቦየ ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ በመግባት አንድ የቆሎ ተማሪ በጥይት በመደብደብ ገድለው አስከሬኑን በጩቤ ቆራርጠው ወጥተዋል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
©አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
መጋቢት 13/2018 ዓ.ም
#እጅ_ስጡ‼️
13/ዐ7/2018 ዓ.ም
#የአደረጃጀት_ዜና‼️
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የልጅ ዕያሱ ኮር ከአፋብን በወረደው አቅጣጫ መሠረት የኮር እና የክፍለ ጦር የማደራጀት ግዳጁን በዛሬው ቀን በቀን 13/07/2018 ዓም አጠናቀቀ፡፡
በቀጠናችን በዚህም ሂደት ቀድሞ ክፍለ ጦሮችን ወደ ቁጥር በመቀየር ግምባር ቀደም የነበረው የልጅ እያሱ ኮር የቀደመ ታሪካዊ ስሙን ሪፎርም በማድረግ 345ኛ ኮር በመባል ተሰይሟል፡፡
ከዚህ ቀደም አራት ክፍለ ጦር የነበሩትን ወደ ሁለት በመቀየር ወደ 24ኛ እና 25ኛ ክፍለ ጦር የቀየረ መሆኑ ይታወቃል ::
በመሆኑ ከቀን 9/07/2018 ዓም ጀምሮ ከየጎፍ ክፍለ ጦር ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም አባሎች ጋር ጥልቅ ውይይት በማድረግ አራት የነበሩትን የክፍለ ጦር ሻለቅች ብዛት ወደ ሁለት በማውረድ የግምገማ እና የሪፎርም ስራውን በስኬት አጠናቆ በዛሬው ዕለት ማለትም በቀን 13/07/2018 ዓም ቀድሞ የጎፍ ክፍለ ጦር እየተባለ ሲጠራ የነበረው ክፍለ ጦር ወደ የ25ኛ ክ/ጦር መጠሪያውን የቀየረ መሆኑን ለህዝባችን እና ለድርጅታችን እንገልፃለን፡፡
በግምገማ እና በውይይቱ የኮር እና የክፍለ ጦሩ አመራር ለተከታታይ ቀናት ባደረጉት ስብሰባ የአመራር መተካካትና አጠቃላይ የትግል ጉዞ ግምገማ አድርገዋል።
በመሆኑም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅንቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 345ኛ ኮር የ25ኛ ክፍለጦር አዲስ የክፍለ ጦር የአመራር መዋቅር በማዋቀር ግምገማውን ተጠናቋል፡፡
በዚሁም መሠረት፦
1.ወታደራዊ አዛዥ...........አርበኛ ሁሴን አደም
2.ም/ወታደራዊ አዛዥ.......አርበኛ ቋራው ከተማ
3.ዘመቻ መሪ ..................አርበኛ እንድሬ ዳምጠው
4.ም/ዘመቻ.መሪ..............አርበኛ እሸቱ በላይ
5.የፖለቲካ መምሪያ...........አርበኛ መቶዓለቃ ሙሲባ(አያሌው)
6. አሰተዳር.........አርበኛ ገረመው አልታሰብ
6.1ምክትል አስተዳደር.....አርበኛ ሙሀመድ ሀምዛ
7.የሰው ሀይል አስተዳደር...አርበኛ ማሩ አስቻለው
8.ኦርድናንስ መምሪያ.........አርበኛ ሁሴን አቡዬ
10. ጤና መምሪያ፦👈
11.ስልጠና መምሪያ.........አርበኛ አግማስ
12.ሎጂስቲክ መምሪያ......አርበኛ ሁሴን ሰይድ
13. ም/ሎጂስቲክ.........አርበኛ ሞገስ ይማም
14.ፋይናንስ ሀላፊ..............አርበኛ ሙሀመድ ሁሴን
15.ሴቶች ጉዳይ፦👈
16.የህዝብ ግንኙነት............አርበኛ አበባው አበራ
18.የህግ ክፍል ሁለት ሰው
1ኛ አርበኛ ሁሴን ሰይድ
2ኛ መቶዓለቃ በቀለ ሁሴን
ግምገማውን የመሩት የ345ኛ ኮር ከፍተኛ አማራሮች፦
1 አርበኛ እንዳሻው ጌታሁን ም/ሰብሳቢና ወታደራዊ አዛዥ
2 አርበኛ ሲሳይ አየለ (ሳተናው) ም/ ሰብሳቢና የፖለቲካ ጉዳዮች ኀላፊ
3 አርበኛ ሞላ አባተ ም/ወታደራዊ አዛዥ
4 አርበኛ ጌታቸው ዘመቻ
5 አርበኛ እያሱ ፈንታው ህግ ክፍል
6 አርበኛ መላኩ መስፍን ም/ኦርድናንስ
7 አርበኛ ሱልጣን ይሱፍ ህዝብ ግኑኝነት
8 አርበኛ ዮሃንስ
9 አርበኛ ሙሉቀን አያልነህ የኮር አማካሪ በመሆን ሂደቱን በስኬት መርተው የተፈለገውን ውጤት በማምጣት ድርጅቱ እና ኮር የሠጣቸውን ግዳጅ የነበሩ መሰናክሎችን በፅናት ተሻግረው ለዚህ ቀን አብቅተውታል፡፡
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
©የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የ345ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት አርበኛ ሱልጣን የሱፍ
መጋቢት 13/07/2018 ዓ.ም
13/ዐ7/2018 ዓ.ም
+1
ሰበር የድል ዜና አቸፈር ሳንክራ 💪💪💪
5 ሁነው ገብተው ሁለት ጥቁር ክላሽ ማርከው ወጡ ።
ከሰሞኑ የቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 55ኛ ክፍለ ጦር ቢተወድድ አያሌው መኮነን ሻለቃ በተመረቁ ማግስት ሰርገው በመግባት ሁለት ጥቁር ክላሽ ማርከው ወጡ ።
ይሄ ኃይል በኮድ እና በዓላማ ብቻ ለሚያውቃቸው የከተማ የቀኜ ንቅናቄ አባላት ጋር መረጃ ይቀበላል ስራውንም በተግባር ይወጣል ።
ከተማ ውስጥ ከፋኖ እይታ ውጭ ነን በማለት ጠላትን በሐሳብ ፣ በገንዘብ እና በጉልበት የሚያግዙትን ራስ-ጠል አማሮችን በመከታተል እና አንቆ ከከተማ በማውጣት ድርጅታዊ ግዳጆችን በደስታ የሚወጡ ትዕዛዝ ጠባቂዎች ብቻ ናቸው ።
ከተመረቁ ጀምሮ ለዚህ ተግባር መረጃ እና ማስረጃን መሠረት አድርገው ስራ በመስራት ላይ ይገኛሉ ።
ይበልጣል የዉነቱ ጀግናዉ
