uk
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

Відкрити в Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Показати більше
3 613
Підписники
+1324 години
+4187 днів
+1 05630 днів
Архів дописів
በርካታ የወረዳው ማህበረሰብ የተገኘበት ህዝባዊ መድረክ ተካሔደ።   መጋቢት 16/2018ዓ.ም የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ አምደ ፅዮን ኮር በሚያስተዳድራቸው ቀጠናዎች በርካታ ህዝብ የታደመበት ህዝባዊ መድረኮች እየተደረጉ ይገኛሉ። በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ተጉለትና ቡልጋ አውራጃ  በባሶና ወረና ወረዳ ስር ከሚገኙ ከተለያዩ ቀበሌዎች ከተወጣጡ የማህበረሰብ ክፍል በአይዞሽ አሞራ ቀበሌ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል። በውይይቱም የአፄ አምደ ፅዮን ኮር የ7ለ70 ክፍለጦር፣ የንጉስ ሳህለ ስላሴ ክፍለጦር እና የዕዙ ፖለቲካ ዘርፍ አመራሮች መድረኩን የመሩ ሲሆን ከማህበረሰቡ ለተነሱ የአስተዳደራዊ ጥያቄዎች አመራሮቹ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል። በተደረገው ህዝባዊ መድረክ በክላስተሩ ያልተሟሉ አመራሮችን በህዝብ በመምረጥና የተሰየሙ መሆናቸውን የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ አምደ ፅዮን ኮር የ7ለ70 ክፍለጦር አስታውቋል። ክብርና ሞገስ ለትግሉ ሰማዕታት!!           ድል ለፋኖ!! አንድነታችን አሸናፊነታችን!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የአፄ አምደ ፂዮን ኮር ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ክፍል   መጋቢት 16 /2018 ዓ.ም

አፋብን ምኒልክ ዕዝ 106ኛ ኮር 34ኛ ክፍለ ጦር እና 22ኛ ክፍለ ጦሮች የጥላትን የጥፋት እንቅስቃሴ በማደናቀፍ ድል አስመዝግበዋል:: መጋቢት 14/2018 ዓ/ም ከጋሸና እና ከወልድያ በገፍ ሀይል በማስገባት ሶስት(03) ቢኤም ሁለት (02) ዙ23 ለቁጥር የሚያታክቱ እግረኛ እንዲሁም በድሽቃና በሞርተር ጭምር በመታገዝ ወደ መቄ፣ዋድላና እስታይሽ አቅጣጫ የጥፋት እንቅስቃሴውን ለማራመድ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ አመሻሽ 2:30 ሰዓት ድረስ የቋመጠ ቢሆንም፤በአይበገሬ ፋኖዎች ተለብልቦ ተመልሷል። እለተ መጋቢት 15/2018 ዓ.ም መራር ሽፈትን የተከናነበው የጥላት ብርሀኑ ጁላ ሰራዊት ለበቀል ተነሳስቶ የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን የሆነበት አገዛዙ  በሁለቱ ክፍለ ጦሮች ተናዳፊ ተርቦች ቅንድብ ቅንድቡን ሲባል ዉሎ አምሽቶም ወደየመጣበት ቁስለኛውን ተሸክሞ ወደመጣበት ተመልሷል። ሰርክ ተሸናፊነትን በሞራሉ፤አስከሬኑን እና ቁስለኛውን በትከሻው ተሸክሞ የሚመለሰው የብልፅግና ወበር አስጠባቂ ጥምር ሰራዊት ተብሎ የሚጠራው ሀይል ዛሬም የዘወትር የጥፋት እጆቹን ተሸንፎ ሲመለስ በሲቪሊያን አማራዎች ላይ ሰንዝሮ ጥፋት ፈፅሟል። በወ/ሮ ጥሩሴት ሰጠኝ እና በአቶ ሲሳይ አበራ የተባሉ ግለሰቦችን ከመኖሪያ ቤታቸው ድረስ ዘልቆ በመግባት እረሽኗቸዋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ #106ኛ ኮር ህ/ግ ሃላፊ መጋቢት 16/2018 ዓ.ም

🥇🥇🥇እጅህ ላይ ያለዉን ስልክ እንደጦር መሳሪያ ተጠቀመዉ!! ✅እጅህ ላይ ያለዉ ስልክ እኔ ከያዝሁት ክላሽ: ብሬንና ስናይፐር: ዲሽቃና ሞርተር ጋር ጠላት ላይ በሚያደርሰው ጉዳት እኩል እንደሆነ ያቃሉ!!! ✅እንግዲያውስ ከጠላት ጎን ለጎን ስትሄድ የጠላትን ሰልፍ ስነ-ልቦና እና የትጥቅ ሁኔታ በዉስጥ መስመር ሹክ በለን !! ✅ከተማ ተቀምጠህ ከሞቀ ቤትህ ሁነህ ስራህን እየሰራህ የጠላትን የቀን ተቀን እንቅስቃሴ በመከታተል አዘውትረው ምግብም ሆነ መጠጥ የሚጠቀሙበትን ቤት በመለየት በዉስጥ መስመር ሹክ ማለት!! ✅ጠላት ብዙ ጊዜዉን በጀማ ተሰባስቦ ጊዜ የሚያሳልፍበት እናም ስብሰባ የሚያካሂድበትን ድብቅ ቦታዎችን ተከታትሎ በመለየት በዉስጥ መስመር ሹክ ማለት እንዲሁም የከተማ ፖሊስ አድማና ሚሊሻ እዚሁ ከኛ ጋር አብረዉ የሚኖሩ ስለሆነ የመኖሪያ ቤት አድራሻቸዉን እናም የቤተሰባቸዉን ሁኔታ ከበቂ ማስረጃ ጋር የሚወጡና የሚገቡበትን ሰዓት መከታተል!! ✅እያንዳንዱን የጠላትን እርምጃና ሙሉ እንቅስቃሴ በአይነቁራኛ በመከታተል በሕዝባችን ላይ ሊያደርስ ያሰበውን ጭፍጨፋና ዘረፋ ክፉ እቅድ እንዲከችፍ ፈጥኖ እጅህ ላይ ባለዉ ስልክ መተኮስ !! ✅እቤትህ ቁጭ ብለህ የጣፈጠ ምግብህን እየበላህ የፋሽሽቱ ስረዓት በሕዝባችን ላይ ያደረሰዉን የሚያደርሰውን ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ቀዉስ በምስክርነት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ብሎም ለኢትዮጵያ ህዝቦች እጅህ ላይ ባለዉ ስልክ ማስረዳት መቻል!! ✅በዚህ ታሪካዊ ትግል ዉስጥ አማራዊ ግዴታችንን የምንወጣዉ በቻልነዉ አቅም ሲሆን እሱም ገንዘብ ያለዉ በገንዘቡ ጉልበት ያለዉ በጉልበቱ እዉቀት ያለዉ በእውቀቱ የበኩሉን አስተዋፅኦ ከአበረከት አማራን እንደአማራ ከጥፋት ለማዳን የድርሻውን እየተወጣ እንደሆነ እጅህ ላይ ባለዉ ስልክ ሕያው ምስክርነት ትሰጠዋለህ !! ✅እጅህ ላይ ባለዉ ስልክ የጠላትን የጥፋት ተልኮ ክፉ ስራዎች በማስረጃ አስደግፈህ በማጋለጥ ህዝባችን በቀላሉ እንዲረዳና ቀድሞ እንዲዘጋጅ ማድረግ አለብህ !! ✅እጅህ ላይ ያለዉ ስልክ ስልክ ብቻም ሳይሆን ድምፅ አልባ መሳሪያ መሆኑን አምነህ ተቀበልና አቀባብለህ ለመተኮስ ተዘጋጅ ዛሬ አማራዉን ከምድረ ገፅ አጠፋለሁ ብሎ ከእግረኛ እስከ ሙሉ መካናይዝድ ጦር የአማራን ምድር እንደ ዝንብ ወሮን እያለ እጅህን አጣጥፈህ ከምትቀመጥ ለነገ የሚሆን ታሪክህን ዛሬ ከትብ። ✅ የወገንን መልካም ስራዎች የጠላትን ክፉ ሀሳቦች አሰራጭ፣ክፉዎችን ለመገርሰስ አዎ ስልክዎትን እንደጦር መሳሪያ ተጠቅመው ይፋለሙ!! ህልውናችን በአርበኝነታችን ይፀናል!!

ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት የተባለው የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብስብ አገዛዙ ከምርጫ በፊት መወጣት ያለበትን ግዴታ በመጥቀስ የአማራ ክልልን ጨምሮ ጦርነት እየተካሄደባቸው ባሉት አካባቢዎች ይፋዊ የአደባባ
+1
ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት የተባለው የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብስብ አገዛዙ ከምርጫ በፊት መወጣት ያለበትን ግዴታ በመጥቀስ የአማራ ክልልን ጨምሮ ጦርነት እየተካሄደባቸው ባሉት አካባቢዎች ይፋዊ የአደባባይ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማቆሙን ያሳወቀበትን መግለጫ ተመልክተናል። ስብስቡ ከአንድ ሃላፊነት ከሚሰማው አካል ሊደረግ የሚገባውን ነገር ማድረጉን በበጎ የምንመለከተው ነው። ትብብሮች ከጠቀሳችኋቸው አካባቢዎች ብቻ ሳይሆን ከሁሉም አካባቢ አብይ አህመድ በምርጫ ስም ካዘጋጀው የደም ድግስ የመራቅ ተጨማሪ ኃላፊነት እንዳለባችሁም ይሰማናል። ዓላማውም ሆነ ውጤቱ በሚታወቅ እልቂትን ቅቡል ለማድረግ ከታሰበ ድግስ ውስጥ መሳተፍ ለህግ እና ለታሪክ ተጠያቂነት ይዳርግ እንደሆን እንጅ ለሀገር የሚያበረክተው ምንም ነገር የለም። በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ በምርጫ የሚፈታ ችግር የለም። የቀውሱን አገዛዝ ቁንጮ አብይ አህመድን ካልሞሸርን በሚል በምርጫ ለመሳተፍ የተሰለፋችሁ ሌሎች ፓርቲዎችም አገዛዙ የሚፈፅመውን ጭፍጨፋ በይፋ እየደገፋችሁ መሆኑን ተረድታችሁ ተመሳሳይ አቋም በመያዝ ከህዝብ ጎን እንድትቆሙ አደራ እንላለን።

ትግል ፍላጎት ሳይሆን ግዴታ ነው !!! የሀገራችን ኢትዮጵያ የፖለቲካ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ጉዳይ ስንመለከት እጅጉን አሳዛኝ ሁኔታ ላይ ነው ያለው ። ፖለቲካዊ ፦ ሃገር በጥበብ እጂ የምትመረው በመግደል በማፈናቀል በመዝረፍ ከተማን በማቀጠል እና ሰዎችን በማሰር የትም አይደረስም ። ብልፅግና ሀገር ማስተዳደር ሳይሆን እየሰራ ያለው ሃገሪቷን እያፈረሰ ነው ያለው ። ከኢኮኖሚያዊ ፦ አብይ ወደ ስልጣን ከመጣ ጀምሮ የንኑሮ ውድነት እዴት እደሆነ ማንም ሰው ይረደዋል ። ይህ ሰው ከመጣ ጀምሮ ስንቱ ምግብ መመገቡን አቁሟል ከስረው ተፈናቅሏል ፣ ስንቱ ቤተሰቡን አጥቶ መገድ ላይ ወቷል ፣ ነጋዴው ከቦታ ቦታ ተቀሳቅሶ መስራት አልቻለ ። የብልፅግናን የኢኮኖሚ ሁኔታ ለመተንተን ተነግሮ አያልቅም አብይ በሚዲያ ወጥቶ ጥሩ ነገር ከተናገረ ገልብጣችሁ ተረዱት ። ይህ ማለት ነዳጅ በኩበን አለ ለሌብነት ያመች ዘንድ አድርጎ የድለላ ስራ ሲሰራ ቆየ አስር ቦቲ ማደያ ገብቶ አንዱ በህጋዊ መገድ ይሸጥና ዘጠኙ ቦቲ አልቋል እየተባለ ተደብቆ በህገወጥ መገድ እየተሸጠ ሲዘርፉ ኖሩ ። ይሄ ድርጊት ሳያሳቸው ነዳጅ አወጣን ባለ ማግስት ዛሬ ነዳጅ የለም አንድ መኪና በተጓዘው ልክ በኪሎ ሜትር ታስቦ ነው የምሰጠው አለ በቀጥታ መኪናዎች ቁሙ ህዝብ በእግርህ ተቀሳቀስ ብሎ ትዛዝ ማውረድ ነው የቀረው በተዘዋዋሪ እያለ እደሆነ ሁሉም ሰው ይረዳል ። ከማህበራዊ አንፃር ፦ ህዝቡን በቤሄር ከፋፍሎ አንዱን የአንዱ ጠላት እደሆነ ሰው በዘሩ ብቻ ወንጀለኛ አድርጎ ፈርጆ እርስ በርስ እዳይተማመን አብሮ ተከባብሮ እና ተቻችሎ ለረዥም አመት የኖረን ህዝብ ቡጅሌ እያዋቀረ አፍጀው ። በአለማችን በ21 ክፍለ ዘመን የሚመረውን ህዝብ በዘር ላይ መሰረት አድርጎ የራሱን ህዝብ የገደለ ወይም የበላ ፖርቲ ብልፅግና ነው ። በአደባባይ መግስታት ሀይለኛ ከሆኑ አባገነን ይባላሉ ጥሩ መሪ ከሆኑ የህዝብ አባት ይባላሉ ብልፅግና ግን ሁለቱንም የማያሟላ ነው ። ምንስ ተባለ ብልፅግና 👉 ሰው በላ አረመኔ ነው። እና ብልፅግና .....? የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ምክትል ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አርበኛ ኤፍሬም ባዩ

የሰርጎ ማጥቃት በሰሜን አቸፈር ሊበን ከተማ አርበኛ አስፋው አንተነህ (የጠባው ) በሰሜን አቸፈር ወረዳ ዋና ከተማ ሊበን በመግባት ሁለት የአገዛዙን ስልጣን አስጠባቂ ራሳቸውን ጥምር ጦር እያሉ የሚጠ
+2
የሰርጎ ማጥቃት በሰሜን አቸፈር ሊበን ከተማ አርበኛ አስፋው አንተነህ (የጠባው ) በሰሜን አቸፈር ወረዳ ዋና ከተማ ሊበን በመግባት ሁለት የአገዛዙን ስልጣን አስጠባቂ ራሳቸውን ጥምር ጦር እያሉ የሚጠሩትን በመሸኘት ሁለት ክላሽንኮቭ መሳሪያ በመ,ማረክ በሰላም ወደ 55ተኛ ክ/ጦር ተቀላቅሏል ። በዚህ ኦፕሬሽን በቅርቡ በ55ተኛ ክ/ጦር ቢትወደድ አያሌው መኮንን ሻለቃ ያስመረቃቸው ልዩ የከተማ ሸማቂ ኮማንዶወች ተሳትፈዋል። አገዛዙ አንድም ለሊት በሰላም እንዳያ,ሳልፍ ጀግኖቹ ተማምለው ወደ ስራ ገብተዋል ። ምስጌ ዘድንግል 105ኛ ኮር የ55ኛ ክ/ጦር ህ/ግንኙነት

አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር የነበልባል ክ/ጦር አዲስ የፋኖ ሰራዊት አባላት በደማቅ ሁኔታ አስመረቀ ። መጋቢት 13/2018 ዓ.ም፡ ከሰም ፪ኛ ኮር ነበልባል ክ/ጦር ከሁለት ወር በላይ ያሰለጠናቸው ከፍተኛ ቁጥር ያለው የፋኖ ሰራዊት አባላት ማስመረቁን አስታወቀ ። ተመራቂ የፋኖ ሰራዊት አባላት፤ የክፍለጦሩ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ወደ ነበሩ የክፍለጦሩ አሃድ ከዛሬ ጀምሮ በይፋ መቀላቀላቸውን ተገልጿል ። የክፍለጦሩ ከፍተኛ አመራሮች በዚህ ዝግጅት ላይ በመታደም፤ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት እና ትግሉን በተመለከተ የተለያዩ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል ። በዚህ የምርቃት ፕሮግራም ላይ ከተገኙት ከፍተኛ አመራሮች መካከል አንዱ፤ ከሰም ፪ኛ ኮር የነበልባል ክ/ጦር፡ ወታደራዊ አስተዳደር የሆኑት አርበኛ ፲ አለቃ ስመኝ አለማየሁ ናቸው፤ አርበኛው በመድረክ ቆይታቸው ከአስተላለፉት መልዕክት መካከል፤ - በቅድሚያ ለተመራቂ የፋኖ ሰራዊት አባላት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ከአስተላለፉ በኋላ፤ "...በዛሬዋ ዕለት የክፍለጦሩ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት መመረቃችሁን በደስታ እናበስራለን ። አሁን እናንተ ሰልጣኞች ሳትሆኑ ወደ ነባሩ ሰራዊት ተቀላቅላችሁ ለአማራ ህዝብ ጋሻና መከታ ሆናችሁ በልበ - ቆራጥነት ከዛሬዋ ቀን ጀምሮ እንደምትታገሉ መሪዎቻችሁ በመድረክ ያረጋግጡላችኋል..." ሲሉ ተደምጠዋል ። አክለውም፤ "...ህዝባችን ለሰጠን አደራና ኃላፊነት አንዳች ሳታጓድሉና ከአቋማችሁ ሳትዋዥቁ በጋራ ሆነን በጽናት የምንታገል ይሆናል..." በማለት መልዕክታቸውን ለተመራቂ ሰራዊት አባላቱ አጋርተዋል ። ሌላው፤ በዚህ የምርቃት ስነ-ሥርዓት ላይ ከተገኙት አመራሮች መካከል፤ ከሰም ፪ኛ ኮር የነበልባል ክ/ጦር፡ ምክትል ጦር አዛዥ የሆኑት አርበኛ እምሽ በጋሻው ናቸው፤ "...ለቆምንለት ዓላማ መርህን ተከትለን፤ ህዝባችንን በአግባቡ ይዘን በአንድነት ጠላታችንን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማስወገድ አለብን ። እኛ የአማራ ልጆች ለያዝንው ዓላማ በጽናት ቆመን ፥ ሳንፍረከረክ በአንድነት ጠላታችንን እንታገላለን..." ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ። ሌላኛው፤ በዚህ ደማቅ የፋኖ ሰራዊት አባላት ፕሮግራም ላይ ከታደሙት አመራሮች መካከል፤ ከሰም ፪ኛ ኮር የነበልባል ክ/ጦር፡ ሎጀስቲክ ኃላፊ የሆኑት አርበኛ ደሴ ሞገሴ ናቸው፤ "...ይህ ስልጠና ብቻ ሳይሆን ከልብ የያዛችሁትን እውቀትና ኃይል ለተጨቆነው ለአማራ ህዝብ ይህን የሰለጠናችሁትና የደከማችሁበትን ፍሬ አፍርቶ እንደምናይ አንጠራጠርም ። እኛ የወጣንው ተበድለን ፥ ተገፍተን ነው ወደ ጫካ የገባንው ። የአማራ ህዝብ እንደ ሰው ፥ እንደ ብሔር የሚታይበት ጊዜ ላይ ስላልሆነ፤ ያለን አማራጭ እናንተን የመሰለ የአማራ ህዝብ እንቁ ልጆችን ይዘን ይህን አውሬ ስርዓት ነቅሎ መጣል ብቻ ነው መፍትሄው..." በማለት በቆይታቸው ተናግረዋል ። በመጨረሻም፤ የማጠቃላይ ንግግር እና የቃልኪዳን ዝግጅትን ያካሄዱት ደግሞ ከሰም ፪ኛ ኮር የነበልባል ክ/ጦር፡ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ የሆኑት አርበኛ ሞገስ ገበየሁ ናቸው፤ "...ዛሬ የእናንተ መመረቀ የአማራ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለው ግፍና በደል እንዴት አድርገን መመከት ላይ አበክረን መስራትና ትኩረት ማድረግ እንዳለብን ዋነኛው ጉዳይ ነው ። © አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ነበልባል ክፍለ ጦር ዜና ክፍል ። - አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ

📌አርበኛ ወንድሙ ማሩ፡ ከላስታ ምድር የበቀለው የምኒልክ ዕዝ የጦር ጥበበኛ የአማራ ፋኖ የህልውና ትግል በታሪክ ማህደር ደምቀው የሚጻፉ የቁርጥ ቀን ልጆችን እያፈራ ይገኛል። ከእነዚህም መካከል የምስራቅ አማራ ቀጠና የምኒልክ ዕዝ ምክትል ወታደራዊ አዛዥ አርበኛ ወንድሙ ማሩ፣ የጀግንነትና የብልህ መሪነት ተምሳሌት ሆነው ይጠቀሳሉ። ከጀግኖች ምድር ከላስታ የወጣው ይህ አርበኛ፣ በብዙዎች ዘንድ የጀነራል አሳምነው ጽጌ "የመንፈስ ልጅ" ተባሎ ይጠራል። ይህ መጠሪያውም ዝም ብሎ የተሰጠ ሳይሆን፣ እንደ ጀነራሉ ሁሉ ለህዝብ ማንነትና ክብር ያለውን ጽኑ አቋም፣ የማያወላውል ወታደራዊ ስነ-ምግባርና ለጠላት የማይበገር አንበሳ መሆኑን በተግባር ስላሳየ ነው። አርበኛ ወንድሙ ማሩ በውጊያ ሜዳ ላይ ያለው ጥበብና ስልታዊ መሪነት በጉልህ የታየው ንፋስ መውጫ ላይ በተደረገው ታላቅ ተጋድሎ ነው። በወቅቱ የነበረውን እጅግ አስቸጋሪ ወታደራዊ ሁኔታ ወደ ድል ለመቀየር የተጠቀመበት የጦር ጥበብ የሚደነቅ ነበር። ጠላት በሰንሰለታማ ተራራዎችና በከባድ መሳሪያ ታጅቦ በነበረበት በዚያ ፈታኝ ወቅት፣ አርበኛው ሰራዊቱን ያስተባበረበት መንገድና የሰጠው ወታደራዊ አመራር የጠላትን ስልት የበታተነ ነበር። በላስታ፣ በመቄት፣ በግዳን፣ በነፋስ መውጫ አጠቃላይ በወሎ ምድር የአርበኛ ወንድሙን የጦር ሜዳ ብልህነትና የአመራር ብቃት ለወዳጅም ለጠላትም ያስመሰከረ የታሪክ አሻራ ሆኖ ይኖራል። በምስራቅ አማራ ቀጠና የተመዘገቡት ድሎች ከሌሎቹ ጓዶች ጋር በመሆን የአርበኛው የቆራጥነት ውጤቶች ናቸው። የጠላት ሰራዊት በቁጥርም ሆነ በታጠቁ ዘመናዊ መሳሪያዎች የበላይነት ቢኖረውም፣ አርበኛ ወንድሙ ማሩ ግን በመንፈስ ጥንካሬና በህዝባዊ መሰረት ላይ የተገነባ የጦር ስልትን በመጠቀም ተአምራዊ ድሎችን አዝንቧል። ፋኖዎችን በማሰልጠን፣ በወታደራዊ ዲሲፕሊን በማነጽና በጋራ አላማ ዙሪያ በማስተባበር ረገድ ያለው ሚና፣ ለምኒልክ ዕዝ መጠናከር ዋነኛው ምሰሶ ሆኗል። ይህ የላስታ አንበሳ በውጊያ መሀል የሚያሳየው መረጋጋትና ፈጣን ውሳኔ የመስጠት ችሎታው፣ ከታላቁ ጀነራል አሳምነው ጽጌ የወረሰው መንፈሳዊ ጥንካሬ መገለጫ ነው። "አማራነትን ማንም አይሰጠንም፣ ማንም አይነጥቀንም" የሚለውን መርህ አንግቦ የሚዋጋው አርበኛ ወንድሙ ማሩ፣ ዛሬም በምስራቅ አማራ ጋራዎች ላይ የነጻነት ችቦ ሆኖ እየበራ ይገኛል። ታሪክ ለነጻነቱ የሚዋጋውን ጀግና ስም በወርቅ ቀለም እንደሚጽፍ ሁሉ፣ የአርበኛ ወንድሙ ማሩ የጀግንነት ተጋድሎም በአማራ ህዝብ ልብ ውስጥ ለዘላለም ታትሞ ይኖራል። ✍️ አርበኛ ደረበ መኮንን ደረሰ

🔥በሕዝቡ ላይ እየተፈፀመ ያለውን የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋን ለመከላከል ተፈጥሯዊ መብቱን ተጠቅሞ የተደራጀው የአማራ ፋኖ በወለጋ ዕዝ ባደረገው ውጊያ በርካታ የአገዛዙ ወታደሮችን በመደምሰስ አንድ ዶሽቃ መሣሪያን ጨምሮ አምስት ብሬንና ስናይፐር ማርኮ ታጠቀ‼️ የአማራ ፋኖ በወለጋ ዕዝ በምስራቅ ወለጋ ዞን በአንገር ጉቴ ከተማ ዙሪያ አሊ ቀበሌ ላይ ትናንት መጋቢት 14/2018 ዓ/ም ከንጋት ጀምሮ እስከ ምሽት ባደረገው ተጋድሎ የጠላት ኃይልን በመደምሰስና ከቡድን መሣሪያ ጀምሮ በርካታ ክላሽንኮቭ እንዲሁም ከ20 በላይ የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት አባላትን መማረኩን የዕዙ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ለመረብ ሚዲያ በላከው መረጃ አስታውቋል። ከዕዙ ስር ከሚገኙ ሬጅመንቶች የተወጣጡ የፋኖ አሃዶች በጋራ በመሆን ትናንት ከንጋት ጀምሮ እስከ ምሽት በወሰዱት የጨበጣ እርምጃ ነው የጠላት ኃይል ተፍረክርኮና ተሽመድምዶ ከባድ ኪሳራን የተከናነበው። በሕዝቡ ላይ እየተፈፀመ ያለውን ግልፅ ጭፍጨፋንና ወረራን ለመከላከል ተፈጥሯዊ መብቱን ተጠቅሞ የተደራጀው የአማራ ፋኖ በወለጋ ዕዝ፡ ባካሄደው በዚህ ተጋድሎ 1 ዶሽቃ መሣሪያ፣ 3 ብሬን መትረጊስ እና ሁለት ስናይፐር የቡድን መሣሪያዎችን ማርኮ ታጥቋል። በተጨማሪም በርካታ ክላሽንኮቭ መሣሪያ፣ 654 የብሬን ተተኳሽ፣ 304 የዶሽቃ ተተኳሽ፣ 27 የእጅ ቦምብ፣ 1 መገናኛ ራዲዮ፣ 39 የጥይት ካዝና፣ 18 የወገብና የደረት ትጥቅ እንዲሁም ሌሎች ወታደራዊ ቁሳቁሶችን ማርኮ መታጠቁን የአማራ ፋኖ በወለጋ ዕዝ በሕዝብ ግንኙነት መምሪያው በኩል ለመረብ ሚዲያ በላከው መረጃ አስታውቋል። በተያያዘ ዜና! የአገዛዙ ኃይል በዚኸው በምስራቅ ወለጋ ዞን ሲቡ ስሬ ወረዳ ትናንት መጋቢት 14/2018 ዓ/ም አመሻሽ ላይ በሞርታር የታገዘ ጥቃት ከፍቶ የነበረ ቢሆንም፡ ነገር ግን  ከወደፋኖ በተሰነዘረበት የመልሶ ማጥቃት እርምጃ ከባድ የሆነ ሰብአዊና ቁሣዊ እንዲሁም ሞራላዊ ኪሳራን ተከናንቦ አከባቢውን ለቆ መሸሹ ታውቋል። በወለጋ የሚገኘው አማራ፡ ካለፉት በርካታ ዓመታት ጀምሮ እየተፈፀመበት ያለውን የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋን ለማስቆም፡ እራሱን የመከላከል ተፈጥሯዊ መብቱን በመጠቀም የየትኛውንም ብሔር ጥቅምና መብት ባከበረ መልኩ ተደራጅቶ የሚወስደው የፀረ ማጥቃት እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መረብ ሚዲያ ከአማራ ፋኖ በወለጋ ዕዝ ለማረጋገጥ ችሏል። በወለጋ የሚንቀሳቀሱት የአማራ ፋኖ በወለጋ ዕዝ እና ቢዛሞ ዕዝ በቅርቡ ወጥ የሆነ አደረጃጀት ፈጥረውና አንድነታቸውን አብስረው በታላቁ የአማራ ሕዝብ አታጋይ ድርጅት በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ስር እንደሚታቀፉ ተነግሯል። 15/ዐ7/2018 ዓ.ም

የአማራ ተወላጅ የሆኑ ወታደራዊ አዛዦች በህቡዕ በተደራጀ ቡድን ተገደሉ! በኦሮሚያ ክልል ከተሰማራው የአገዛዙ ወታደራዊ ኃይል መካከል፡ በማዕከላዊ ዕዝ የአማራ ተወላጅ የሆኑ 10 የሬጅመንት አዛዦች፣ ሦስት ምክትል የሬጅመንት አዛዦች አምስት የሻምበል አዛዦች ሲገደሉ፡ ገዳዩ ቡድን በህቡዕ የተደራጀ በዛው በዕዙ ውስጥ የሚገኝና በዕዙ አዛዦች የሚመራ ነው ብለዋል ወታደራዊ ምንጮች። በሌተናል ጀኔራል ዘውዱ በላይ የሚመራው ማዕከላዊ ዕዝ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አከባቢዎች ተሰማርቶ ይገኛል። ዕዙ በክልሉ ስምሪት ከተሰጠው ቀን ጀምሮ በሚካሄዱ ውጊያዎች በርካታ ወታደሮቹ ያለቁበት ሲሆን፡ በርካቶችን ደግሞ የኦሮሚያ ክልል መንግስት አስገድቶበታል ተብሏል። በክልሉ ከማዕከላዊ ዕዝ በተጨማሪ ማዘዣውን ነቀምቴ ኩምሳ ሞሮዳ ቤተመንግስት ውስጥ ያደረገው በሜጀር ጄኔራል አማረ ባህታ የሚመራው ምዕራብ ዕዝም የሚገኝ ሲሆን፡ ከዕዙ አንድ ሦስተኛ የሚሆነው ኃይል ከነሙሉ ትጥቁ ከድቶ ወደ ኦሮሚያ ልዩ ኃይል መቀላቀሉን  ከወታደራዊ ምንጮቹ ለማረጋገጥ ችሏል። የማዕከላዊ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ዘውዱ በላይ ከሁሉም የዕዙ ክፍሎች ከተውጣጡ ታክቲካልና ኦፕሬሽናል አመራሮች ጋር የዕዙን ግዳጅ አፈፃፀም በተመለከተ ከየካቲት መጨረሻዎቹና መጋቢት መጀመሪያዎቹ ቀናት ጀምሮ ባሉት አሥር ተከታታይ ቀናት ግምገማ ማድረጋቸው ታውቋል። በግምገማው የዕዙ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ሜጀር ጀነራል አብድሮ ከድርን ጨምሮ የኮር አዛዥ ጀነራል መኮንኖችና ከከፍተኛ መኮንን እስከ ባለ ሌላ ማዕረግተኛ አዛዦች እንዲሁም በየደረጃው ያሉ የመካከለኛና የበታች አመራሮች የተገኙ ሲሆን፡ በግምገማ መድረኩ የቀረቡ ሪፖርቶች እጅግ አስደንጋጭ ናቸው ብለዋል ምንጮቻችን። በግምገማ መድረኩ ከቀረቡ ሪፖርቶች መካከል አንዱና ዋናው አስደንጋጭ ጉዳይ፡ የአማራ ተወላጅ የሆኑ መካከለኛና የበታች ወታደራዊ አዛዦች ያለ ምንም ውጊያ ተገድለው እየተገኙ መሆናቸውን የሚያመላክት ነው። በሪፖርቱ እንደተገለፀው 10 የሬጅመንት አዛዦችና ሦስት ምክትል የሬጅመንት አዛዦች እንዲሁም አምስት የሻምበል አዛዦች ያለምንም ውጊያ በሳንጃ ጭምር ተወግተው መገደላቸውንና በርካቶች ደግሞ ቆስለው በሕክምና ላይ እንደሚገኙ ተነግሯል። ገዳዩ ቡድን በህቡዕ የተደራጀ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፡ የዕዙ አዞዦች ግን ገዳዩ አካል ማን እንደሆነና በማን እንደሚመራ በግምገማ መድረኩ እንዳይታወቅ አድበስብሰውት አልፈዋል ነው ያሉት የመረጃ ምንጮቻችን። ከዚህ በተጨማሪ በዕዙ ውስጥ ከፍተኛ የሰራዊት መክዳት እንዳለ በግምገማ መድረኩ የተገለፀ ሲሆን፡ ሰራዊቱን እያስከዳ የሚገኘው አንዱና ዋናው የኦሮሚያ ክልል መንግስት መሆኑምንም  ምንጮች አክለው ገልፀዋል። በምዕራብ ዕዝ ስር የ67ኛ ክ/ጦር አዛዡ ኮሎኔል ገመቹ ዲባባ የምስራቅ ወለጋ ዞን ዋና መቀመጫ በሆነችው ነቀምቴ ከተማ ባረፈበት ደሣለኝ ሆቴል የካቲት 30/2017 ዓ/ም ለመጋቢት አጥቢያ ለሊት ሕይወቱ አልፎ መገኘቱን በወቅቱ የአይን እማኞችንና ወታደራዊ ምንጮቹን ዋቢ በማድረግ  መዘገቡ አይዘነጋም።

ምኒልክ ዕዝ 104ኛ ኮር 25ኛ ክፍለ ጦር ወረኢሉ ከተማ ዙሪያ የፋሽስቱን አገዛዝ የምርጫ እንቅስቃሴ በመግታት ድል አስመዘገቡ:: ፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና እድሜውን ለማራዘም በማሰብ ያሰበውን ምርጫ ፋኖ ምክንያታዊና ፍትሃዊ የሆነ ትግል እንደሚያደርግ የገለፀ ሲሆን የምኒልክ ዕዝ አሃዶች የተጠናና የተጠናከረ ተጋድሎ እያደረጉ ይገኛሉ:: የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 104ኮር 25ኛ ክፍለ ጦር ሞርተር ምድብተኞች የአማራን ህዝብ ስቃይና መከራ ለማራዘም እንዲሁም ፋሽስቱ አገዛዝ እድሜውን ለማራዘም የአማራን ህዝብ እየጨፈጨፈ ላለው ብልፅግና ቡድን በወረኢሉ ወረዳ ካቤ ከተማ ህዝብን በግዴታ ለመሰብሰብና የምርጫ ካርድ እንዲያወጡ ለማድረግ ሲሯሯጥ የተጠና የሞርተር ጥቃት በመፈፀም የቡድኑን ቅዥት በማክሸፍና ስራቸውን በአግባቡ በመወጣት ድል አስመዝግበዋል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ መጋቢት 15/2018 ዓ.ም

34ኛ ክ/ጦር የሚሰጠውን ማንኛውንም ግዳጅ ተቀብሎ መፈፀም በሚያችለው ሁሉን አቀፍ አቅም ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ። 206ኛ ኮር መጋቢት 14/2018 ዓ.ም ===============================-=--====== 206ኛ ኮር አደረጃጀቱን እና ወቅታዊ የክ/ጦሮችን እየፈተሸ ሲሆን ለተከታታይ አራት ቀናት በወሰደው ጥልቅ ግምገማ የ34ኛ ክ/ጦር ወቅታዊ የስራ ክንውን፣ ግዳጅ አፈፃፀምና የወትሮ ዝግጁነት ተፈትሿል። 34ኛ ክ/ጦር በመልሶ ማደራጀት ትግበራው የሰራዊት አባላቱን በማነቃነቅ ሻለቆችን በማጣመርና በማቀናጀት በደጀን (ጉብያ) በአምበር (ጃማ) በሉማሜ ከተማና የሰንበት ከተማ በፈፀመው አስደናቂ ጀብድ ድል መቀናጀቱ ተመላክቷል። በጃዊ በአደረገው እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ ያስመዘገበው ወታደራዊ ድል ክ/ጦሩ ድንበር አልባ ተፋላሚ መሆኑን ያስመሰከረበት እንደሆነ ተገልጿል። ህዝብን በማስተዳደር የማህበረሰቡን የፀጥታ ችግር እየቀረፈ ፈጣን የፍትህ አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን ከጥር ወር እስከ መጋቢት 1 ባሉ 60 ቀናት ብቻ 122 የፍታብሔር እና የወንጀል መዝገቦች ምርመራ በማድረግ ከ60 በላይ የሆኑ መዝገቦች ወሳኔ ተሰጦባቸዋል። ማዕከላዊነትን ጠብቆ የድርጅቱን ተልዕኮ እየፈፀመ የሚገኘው 34ኛ ክ/ጦር በ206ኛ ኮር ስር ካሉ ሌሎች ክ/ጦሮች ጋር ሲወዳደር በስራ አፈፃፀም ቀዳሚ የሆነ ሲሆን የተሻለ የስራ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የክ/ጦር አመራሮች እንዲሁ እውቅና ተሰጧል። በቀጣይ መስተካከል ያለባቸውን አብይ ጉዳዮች በመለየት የቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ የስራ ስምሪት በ206ኛ ኮር አመራሮች ተሰጦ ቀናትን የወሰደው የስራ ግምገማ በስኬት ተጠናቋል። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ ! የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት