ch
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

前往频道在 Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

显示更多
3 589
订阅者
+524 小时
+5667 天
+97730 天
帖子存档
ክፍለጦሩ 3 ብልፅግና ያሰማራቸውን ዘራፊዎች በቁጥጥር ስር ያዋለ ሲሆን ለወረራ በመጣው የብልፅግናው የጫካ ክንፍ የሸኔ ዘራፊ ቡድን ላይ በወሰደው እርምጃ የቡድን መሳሪያ መማረኩን አስታወቀ።    አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ       መጋቢት 14/2018ዓ.ም ሰራዊታችን ብልፅግና ያሰማራቸውን የህዝብ መከራ የሆኑ አረሞችን በመንቀል የትግላችንን ህዝባዊነት እያሰመሰከረ ይገኛል። የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ አምደ ፅዮን ኮር የራስ አበበ አረጋይ ክፍለጦር ከማህበረሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ለበርካታ ወራቶች ሹፌሮችን እና ባለሀብቶችን በማገት ከፍተኛ ገንዘብ በመጠየቅ ሲዘርፉ ከነበሩ የወንበዴዎች ግበረ-አበሮች ውስጥ ሶስቱን (3) ከነዘረፉት በርካታ ገንዘብ እና ከሁለት ታጋቾች ጋር የክፍለጦሩ ቃኝ እና ከሻለቆቹ የተወጣጡ ቃኝዎች ባደረጉት ልዩ ኦፕሬሽን በቁጥጥር ስር ውለዋል። ትላንትን መጋቢት 13 ቀን 2018ዓ.ም በእንሳሮ ወረዳ እና በሳያደብርና ዋዬ ወረዳ በዝርፊያ ስራ ላይ ተሰማርተው ነጋዴወችንና ሹፌሮችን ብሎም በአካባቢው የሚገኙትን ሀብታም ገበሬወችን በማገትና  ዋሻ ውሰጥ በመሰወር ከፍተኛ የገንዘብ መጠን በመጠየቅና በማሰከፍል ለአንድ ዓመት ያክል ሲዘርፉ የቆዩና ከቡድኑ ዘጠኝ (9) አባላት ወስጥ ሶስት (3) አባላቱን ጀግናው የራስ አበበ አረጋይ የመንፈስ ልጆች የትግላችን ነቀርሳ፣የህዝባችን መከራ፣ የአገዛዙ የጫካ ስራ አስፈፃሚዎችን በቁጥጥር ስር አውለን ምርመራ ጀምረናል ሲል የራስ አበበ አረጋይ ክፍለጦር የህዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ ፋኖ ሽታው አሻግሬ ለኮሩ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ክፍል በላከው መረጃ አስታውቋል። ክፍለጦሩ የዘራፊዎችን ስም ዝርዝር ይፋ ያደረገ ሲሆን፣ 1ኛ. አይዳኝሁም አሰፋው 2ኛ. አይናለም ግዛው እና 3ኛ. ብሩክ አስፋው  የተባሉትን የብልፅግና ተላላኪ ዘራፊዎችን በመግለፅ የታገቱ ግለሰቦችን ከፍተኛ ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ በማስለቀቅ በዘራፊዎች የተወሰደባቸውን 400,000ብር ሲያስመልስ ተበዳዮችም ለክፍለጦሩ ምስጋናቸውን ማቅረባቸውን አርበኛው በመልዕክቱ አስታውቋል። ። ይሕ በእንዲሕ እንዳለ በዛሬው ዕለት በፊቸ ሰላሌ ወረዳ እንጓለላና ሸበል ፋጢ ቀበሌወች ላይ የስርዓቱ ሌላኛው ዘራፊ ቡድን የሆነው የኦሆዴድ ብልፅግናው የጫካው ክንፍ በመሆን ከአገዛዙ ጋር ተናቦ እየሰራ የሚገኘው እራሱን ኦነግ ሸኔ ብሎ የሚጠራው ዘራፊ ቡድን እንደለመደው የጥፋት አላማውን አንግቦ ህፃናትንና ሸማግሌዎችን ለመግደልና ዝርፊያ ለመፈፀም አቅዶ የመጣ ቢሆንም ነገር ግን አናብስቶቹ የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የራሰ አበበ አረጋይ ክፍለጦር የአርበኛ አሊ ሻለቃ እና የቀጠናው የሚገኘው የአርበኞች ጦር ሰራዊት ከበባ ውሰጥ በማሰገባት ሲቀጠቀጥ ያረፈደ ሲሆን የተረፈው እግሬ አውጭኝ ብሎ ሲፈረጥጥ ይዞት የመጣውን ከብልፅግና የተበረከተለትን አዲስ ብሬንና ከነ ሸንሸሉ ከያዘው ተተኳሽ ጋር ለጀግኖቹ የራስ አበበ አረጋይ ክፍለጦር  አስረክቦ መፈርጠጡን ክፍለጦሩ በግንባር መረጃው አስታውቋል። ክብርና ሞገስ ለትግሉ ሰማዕታት!!           ድል ለፋኖ!! አንድነታችን አሸናፊነታችን!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የአፄ አምደ ፂዮን ኮር ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ክፍል   መጋቢት 14 /2018 ዓ.ም

"ያ ቀበቶውን ሳይቀር እናስፈታዋለን ተብሎ ተፎክሮበትና ከምድር ጦር እስከ ሰማይ ጄትና ድሮን ተዘምቶበት የነበረው አማራ፡ ዛሬ ላይ ደርቦ ደራርቦ ማራኪ፣ መርጦ መራርጦ ማርኮ ታጣቂ ሆኗል። አጃኢብ ነ
+1
"ያ ቀበቶውን ሳይቀር እናስፈታዋለን ተብሎ ተፎክሮበትና ከምድር ጦር እስከ ሰማይ ጄትና ድሮን ተዘምቶበት የነበረው አማራ፡ ዛሬ ላይ ደርቦ ደራርቦ ማራኪ፣ መርጦ መራርጦ ማርኮ ታጣቂ ሆኗል። አጃኢብ ነው!" 14/ዐ7/2018 ዓ.ም

ሰበር የድል ዜና!!! የአገዛዙ ጥምር ሰራዊት ዙ-23 ተኳሽን ጨምሮ በፋኖ ብርቱ ክንድ እየተረፈረፈ ይገኛል። የአገዛዙ ግሳንግስ ጥምር ሰራዊት ያለ የሌለ ሰራዊቱን በየአቅጣጫው ሰብስቦ መነሻውን ጎንደር በማድረግ ወደ ደልጊ ከተማ ከገባ በኃላ ትናንት መጋቢት 13/2018 ወደ አለፋ ወረዳ ሻሁራ ከተማ ለመግባት ሙሉ ቀኑን በእግሩ ሲማቅቅ ሲወጣ ሲወርድ የዋለ ሲሆን ተናዳፊዎቹ አፋብን በላይ ዘለቀ ዕዝ የመይሳው ካሳ (፪ኛ) ኮር ቋራ ኦሜድላ ክ/ር፣ ካራማራ ክ/ር እና አድዋ ክ/ር በጦር መሀንዲሶች በኮሩ ም/ሰብሳቢ አርበኛ ባበይ አንባየ፣ ወታደራዊ አዛዥ አርበኛ በሊሁን ጌታቸው ፣ ዘመቻ አርበኛ ጌታቸው አማረና በሁሉም የጦር ጠበብት የክ/ር ወታደራዊ አዛዦችና ዘመቻዎች እየተመራ እንዲሁም አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ በጌምድር ክ/ር ጣና ብርጌድ በአንድ በመጣመር የጠላትን ሰራዊት ስቦ ወደ ሙት ወረዳ ቀለበት ውስጥ በማስገባት ቀኑን ሙሉ በየሜዳው የከባድ መሳሪያ የጭንቀት ተኩስ ሲያደርግ የዋለ ሲሆን አድፍጦ የተሻለ አሰላለፍ ሲያመቻች የዋለው ነበልባሉ ፋኖ ከቀኑ 9:00 ስአትገደማ ጀምሮ እስከ ምሽቱ 1:00 ስአት አምቹሀ ከምትባል ቀበሌ በሁሉም አቅጣጫ በቀጥታ በተሰነዘረበት የማጥቃት ዘመቻ የአብይ ተስፋ ቆራጭ ሰራዊት ክፋኛ ሲረፈረፍ  አምሽቷል። ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሙትና ቁስለኛ ከመሆኑ ባሻገር ሰፊ ቀጠና ሸፍኖ ሲንቀሳቀስ የነበረውን ወደ አንድ ተሰብስቦ ተራራ ላይ በመውጣት ከበባ ውስጥ የገባው የጠላት ሀይል ሙሉ ሌሊቱን የጭንቀት ተኩስ ሲተኩስ አድሯል። ስለሆነም በቀጣይ የዜና መሰናዶአችን አህዛዊ የድል ዜናዎችን አጠናክረን የምናቀርብ ይሆናል። ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ መይሳው ካሳ (፪ኛ) ኮር የህ/ግ መጋቢት 14/2018

በሰርጅካል ኦፕሬሽን የጠላት ሻለቃ መሪ መሀል አስፓልት ማጋደም ተችሏል‼️ የ101ኛ ኮር 35ኛ ክፍለ ጦር አባላቶች ወርጌሳ እና መርጦ ከተማ ላይ ታላቅ ጀብድ ፈፀሙ:: 101ኛ ኮር 35ኛ ክፍለ ጦር
+2
በሰርጅካል ኦፕሬሽን የጠላት ሻለቃ መሪ መሀል አስፓልት ማጋደም ተችሏል‼️ የ101ኛ ኮር 35ኛ ክፍለ ጦር አባላቶች ወርጌሳ እና መርጦ ከተማ ላይ ታላቅ ጀብድ ፈፀሙ:: 101ኛ ኮር 35ኛ ክፍለ ጦር ውርጌሳ ከተማ ላይ ሰርገው በመግባት የጥላትን ሻለቃ መሪ በመደምሰስ መገናኛ ሬዲዮ እና የእጅ ስልክ አንስተው በመውጣት ታላቅ ጀብድ ፈፅመው ድል አስመዝግበዋል:: በተመሳሳይ 35ኛ ክፍለ ጦር መርጦ እየሱስ በመግባት አንድ ጓድ (ቲም) የጠላት ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ጀብድ ፈፅመው ድል ተጎናፅፈዋል:: ከዚህ ጋር ተያይዞም አገዛዙ የፋኖን ክንድ መቋቋም ሲያቅተው የበቀል አፈሙዙን ወደ ንፁሃን በማዞር ወልድያ ከተማ ልዩ ቦታው መቻሬ አቦየ ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ በመግባት አንድ የቆሎ ተማሪ በጥይት በመደብደብ ገድለው አስከሬኑን በጩቤ ቆራርጠው ወጥተዋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! ©አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ መጋቢት 13/2018 ዓ.ም #እጅ_ስጡ‼️ 13/ዐ7/2018 ዓ.ም

#የአደረጃጀት_ዜና‼️ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የልጅ ዕያሱ ኮር ከአፋብን በወረደው አቅጣጫ መሠረት የኮር እና የክፍለ ጦር የማደራጀት ግዳጁን በዛሬው ቀን በቀን 13/07/2018 ዓም አጠናቀቀ፡፡ በቀጠናችን በዚህም ሂደት ቀድሞ ክፍለ ጦሮችን ወደ ቁጥር በመቀየር ግምባር ቀደም የነበረው የልጅ እያሱ ኮር የቀደመ ታሪካዊ ስሙን ሪፎርም በማድረግ 345ኛ ኮር በመባል ተሰይሟል፡፡ ከዚህ ቀደም አራት ክፍለ ጦር የነበሩትን ወደ ሁለት በመቀየር ወደ 24ኛ እና 25ኛ ክፍለ ጦር የቀየረ መሆኑ ይታወቃል :: በመሆኑ ከቀን 9/07/2018 ዓም ጀምሮ ከየጎፍ ክፍለ ጦር ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም አባሎች ጋር ጥልቅ ውይይት በማድረግ አራት የነበሩትን የክፍለ ጦር ሻለቅች ብዛት ወደ ሁለት በማውረድ የግምገማ እና የሪፎርም ስራውን በስኬት አጠናቆ በዛሬው ዕለት ማለትም በቀን 13/07/2018 ዓም ቀድሞ  የጎፍ ክፍለ ጦር እየተባለ ሲጠራ የነበረው ክፍለ ጦር ወደ የ25ኛ ክ/ጦር መጠሪያውን የቀየረ መሆኑን ለህዝባችን እና ለድርጅታችን እንገልፃለን፡፡ በግምገማ እና በውይይቱ የኮር እና የክፍለ ጦሩ አመራር ለተከታታይ ቀናት ባደረጉት ስብሰባ የአመራር መተካካትና አጠቃላይ የትግል ጉዞ ግምገማ  አድርገዋል። በመሆኑም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅንቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 345ኛ ኮር የ25ኛ ክፍለጦር  አዲስ የክፍለ ጦር የአመራር መዋቅር በማዋቀር ግምገማውን ተጠናቋል፡፡ በዚሁም መሠረት፦ 1.ወታደራዊ አዛዥ...........አርበኛ ሁሴን አደም 2.ም/ወታደራዊ አዛዥ.......አርበኛ ቋራው ከተማ 3.ዘመቻ መሪ ..................አርበኛ እንድሬ ዳምጠው 4.ም/ዘመቻ.መሪ..............አርበኛ እሸቱ በላይ 5.የፖለቲካ መምሪያ...........አርበኛ መቶዓለቃ ሙሲባ(አያሌው) 6. አሰተዳር.........አርበኛ ገረመው አልታሰብ 6.1ምክትል አስተዳደር.....አርበኛ ሙሀመድ ሀምዛ 7.የሰው ሀይል አስተዳደር...አርበኛ ማሩ አስቻለው 8.ኦርድናንስ መምሪያ.........አርበኛ ሁሴን አቡዬ 10. ጤና መምሪያ፦👈 11.ስልጠና መምሪያ.........አርበኛ አግማስ 12.ሎጂስቲክ መምሪያ......አርበኛ ሁሴን ሰይድ 13. ም/ሎጂስቲክ.........አርበኛ ሞገስ ይማም 14.ፋይናንስ ሀላፊ..............አርበኛ ሙሀመድ ሁሴን 15.ሴቶች ጉዳይ፦👈 16.የህዝብ ግንኙነት............አርበኛ አበባው አበራ 18.የህግ ክፍል ሁለት ሰው       1ኛ አርበኛ ሁሴን ሰይድ        2ኛ መቶዓለቃ በቀለ ሁሴን ግምገማውን የመሩት የ345ኛ ኮር ከፍተኛ አማራሮች፦ 1 አርበኛ እንዳሻው ጌታሁን ም/ሰብሳቢና ወታደራዊ አዛዥ 2 አርበኛ ሲሳይ አየለ (ሳተናው) ም/ ሰብሳቢና የፖለቲካ ጉዳዮች ኀላፊ 3 አርበኛ ሞላ አባተ ም/ወታደራዊ አዛዥ 4 አርበኛ ጌታቸው ዘመቻ 5 አርበኛ እያሱ ፈንታው ህግ ክፍል 6 አርበኛ መላኩ መስፍን ም/ኦርድናንስ 7 አርበኛ ሱልጣን ይሱፍ ህዝብ ግኑኝነት 8 አርበኛ ዮሃንስ 9 አርበኛ ሙሉቀን አያልነህ የኮር አማካሪ በመሆን ሂደቱን በስኬት መርተው የተፈለገውን ውጤት በማምጣት ድርጅቱ እና ኮር የሠጣቸውን ግዳጅ የነበሩ መሰናክሎችን በፅናት ተሻግረው ለዚህ ቀን አብቅተውታል፡፡ መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! ©የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የ345ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት አርበኛ ሱልጣን የሱፍ መጋቢት 13/07/2018 ዓ.ም 13/ዐ7/2018 ዓ.ም

ሰበር የድል ዜና አቸፈር ሳንክራ 💪💪💪 5 ሁነው ገብተው ሁለት ጥቁር ክላሽ ማርከው ወጡ ። ከሰሞኑ የቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 55ኛ ክፍለ ጦር ቢተወድድ አያሌው መኮነን ሻለቃ በተመረቁ ማግስት
+1
ሰበር የድል ዜና አቸፈር ሳንክራ 💪💪💪 5 ሁነው ገብተው ሁለት ጥቁር ክላሽ ማርከው ወጡ ። ከሰሞኑ የቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 55ኛ ክፍለ ጦር ቢተወድድ አያሌው መኮነን ሻለቃ በተመረቁ ማግስት ሰርገው በመግባት ሁለት ጥቁር ክላሽ ማርከው ወጡ ። ይሄ ኃይል በኮድ እና በዓላማ ብቻ ለሚያውቃቸው የከተማ የቀኜ ንቅናቄ አባላት ጋር መረጃ ይቀበላል ስራውንም በተግባር ይወጣል ። ከተማ ውስጥ ከፋኖ እይታ ውጭ ነን በማለት ጠላትን በሐሳብ ፣ በገንዘብ እና በጉልበት የሚያግዙትን ራስ-ጠል አማሮችን በመከታተል እና አንቆ ከከተማ በማውጣት ድርጅታዊ ግዳጆችን በደስታ የሚወጡ ትዕዛዝ ጠባቂዎች ብቻ ናቸው ። ከተመረቁ ጀምሮ ለዚህ ተግባር መረጃ እና ማስረጃን መሠረት አድርገው ስራ በመስራት ላይ ይገኛሉ ። ይበልጣል የዉነቱ ጀግናዉ

ልዩ ኮማዶዎች በተመረቁ ማግስት ታሪክ ሰርተዋል‼️ መጋቢት 13/2018 ዓ/ም መጋቢት 11/2018 ዓ/ም የቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 55ኛ ክፍለ ጦር ቢተወድድ አያሌው መኮነን ሻለቃ ያስመረቃቸው የል
+1
ልዩ ኮማዶዎች በተመረቁ ማግስት ታሪክ ሰርተዋል‼️ መጋቢት 13/2018 ዓ/ም መጋቢት 11/2018 ዓ/ም የቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 55ኛ ክፍለ ጦር ቢተወድድ አያሌው መኮነን ሻለቃ ያስመረቃቸው የልዩ ዘመቻ ተመራቂ አባላት በተመረቁ ማግስት ሳንካራ ከተማ ሰርገው በመግባት ጠላትን በትኖ በመምታት ሁለት ጥቁር ክላሽ ማርከው ተመልሰዋል። ልዩ የኮማንዶ አባላት ልዩ ዘመቻ በአጭር ስአት በቀላል መስዋት፣በቀላል የሠው ሃይል የፈለጉትን የጠላት ሀይል መምታትና መማረክ የሚችሉ በመሆናቸው የመጀመሪያውን ግዳጃቸውን በስኪት አጠናቀው ተመልሰዋል። አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ‼️ አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ የ105ኛ ኮር ሕ/ግንኙነት

የተከበራችሁ የፍኖተ አማራ ሚዲያ ተከታታዮች እንዲሁም የቴሌግራም ፒጃችን ጆይን ያላደረጋችሁ በሙሉ እኛ ከግንባር ሁነን የአማራን የነፃነት ትግል አብርን ከወንድሞቻችን ጋር አሰየተዋደቅን እንገኛለን ሚ
+1
የተከበራችሁ የፍኖተ አማራ ሚዲያ ተከታታዮች እንዲሁም የቴሌግራም ፒጃችን ጆይን ያላደረጋችሁ በሙሉ እኛ ከግንባር ሁነን የአማራን የነፃነት ትግል አብርን ከወንድሞቻችን ጋር አሰየተዋደቅን እንገኛለን ሚዲያችን ተደራሽ እንዲሆን ይወዳጁን!! አፋብን💪 ፍኖተ አማራ ሚዲያ ከግንባር የቴሌግራም ገፃችንን ይወዳጁ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!! https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

የተከበራችሁ የፍኖተ አማራ ሚዲያ ተከታታዮች እንዲሁም የቴሌግራም ፒጃችን ጆይን ያላደረጋችሁ በሙሉ እኛ ከግንባር ሁነን የአማራን የነፃነት ትግል አብርን ከወንድሞቻችን ጋር አሰየተዋደቅን እንገኛለን ሚዲያችን ተደራሽ እንዲሆን ይወዳጁን!!

የብልፅግና ባለሥልጣናት በባህር ዳር ካህናትን ለማስገደድ ያደረጉት ሙከራ በዛቻና በተስፋ መቁረጥ ተጠናቀቀ! በተስፋ መቁረጥ ውስጥ የሚገኘው የብልፅግና ሥርዓት በባህር ዳር ከተማ የሚገኙ የቤተክርስቲያን አገልጋዮችንና የአስተዳደር ሠራተኞችን ለፖለቲካዊ ዓላማው መጠቀሚያ ለማድረግ የጠራው ስብሰባ፣ በካህናቱ ብርቱ ተቃውሞና በባለሥልጣናቱ መሸነፍ መጠናቀቁን የኢትዮ 251 ሚዲያ ምንጮች አረጋገጡ። ትላንት መጋቢት 12 ቀን 2018 ዓ.ም በከተማዋ በሚገኘው አቫንቲ ሆቴል የተካሄደው ይህ ስብሰባ፣ ካህናቱ በገዛ ፈቃዳቸው ሊገኙ ባለመቻላቸው ምክንያት በዛቻና በማስፈራራት እንዲካሄድ ተገዷል። የሥርዓቱ ካድሬዎች ቀደም ብለው በጠሩት ስብሰባ ላይ አገልጋዮች ባለመገኘታቸው የተቆጡት እነ ጎሹ እንዳላማው፣ የሀገረ ስብከቱን ሥራ አስኪያጅና ዋና ጸሐፊ በማስገደድ በስብሰባው ላይ ያልተገኘ አካል ላይ ጥብቅ አስተዳደራዊ እርምጃ ይወሰዳል የሚል የጽሁፍ መመሪያ እንዲወርድ አድርገዋል። በዚህም ምክንያት የሃይማኖት አባቶችና የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪዎች በስም ዝርዝር እየተጠሩና እየተፈተሹ በግዴታ ወደ ስብሰባው አዳራሽ እንዲገቡ ተደርጓል። በዕለቱ በሥርዓቱ ቀዳሚ ካድሬዎች የቀረቡት አጀንዳዎች ሙሉ በሙሉ ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው እንደነበሩ የኢትዮ 251  ሚዲያ የመረጃ ምንጮች ገልጸዋልዠ ባለሥልጣናቱ ካህናቱ "ጽንፈኛ" ያሉትን የፋኖ ኃይል እንዲያወግዙ፣ ከሕዝብ እንዲነጥሉና ከሥርዓቱ ጎን እንዲቆሙ በይፋ ጠይቀዋል። ከዚህም ባለፈ፣ ለባህርዳር ከተማ ምርጫ ክልል አቶ ተመስገን ጥሩነህ እና አቶ አረጋ ከበደ መቅረባቸውን በመግለጽ፣ ካህናቱ ራሳቸው እንዲመርጡና ምዕመናንም ለብልፅግና ድምፅ እንዲሰጡ እንዲቀሰቅሱ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል። ይሁን እንጂ ስብሰባው የባለሥልጣናቱን ግምት የሳተ ነበር። በዕለቱ ጥቂት ሆድ አደር ግለሰቦች ሥርዓቱን ለማሞገስና ድጋፍ ለመስጠት ሲሞክሩ፣ በአዳራሹ የነበሩ ካህናት በስላቅና በጫጫታ ንግግራቸውን ሲያቋርጧቸው እንደነበር የመረጃ ምንጫችን አክሎ ገልጿል። ካህናቱ የቀረበውን አጀንዳ ባለመቀበላቸውና ከሥርዓቱ ዓላማ በተቃራኒ የግልና የሕዝብ ብሶቶችን በማንሳታቸው ባለሥልጣናቱ ለከፍተኛ ቁጣና ተስፋ መቁረጥ ተዳርገዋል። በመጨረሻም የሥርዓቱ ካድሬዎች በካህናቱ ምላሽ በመናደድ፦ "ወደዳችሁም ጠላችሁም ብልፅግና ያሸንፋል፤ እኛም እስከመጨረሻው ለብልፅግና እንሞታለን፤ ዛሬ እዚህ የተቀመጥነው በዕውቀትና በክህሎት ተሽለን ሳይሆን ለብልፅግና ታማኝ በመሆናችን ነው፤ እናንተ ብትደግፉንም ባትደግፉንም እንደምንቀጥል እወቁ" በሚል የዛቻ ቃላት ስብሰባውን ለመዝጋት ተገደዋል ነው ያሉት የ251 ሚዲያ የመረጃ ምንጯች። የኢትዮ 251 ሚዲያ የመረጃ ምንጭ በቦታው ተገኝቶ እንደታዘበው፣ ይህ ክስተት አገዛዙ በሃይማኖት ተቋማት ውስጥ ያለውን ተቀባይነት ሙሉ በሙሉ ማክተሙንና በኃይል ብቻ ለመቀጠል እየሞከረ መሆኑን የሚያሳይ ትልቅ ማሳያ ሆኖ አልፏል ብሏል።

🔥ምኒልክ ዕዝ የ102ኛ ኮር 12ኛ ክፍለ ጦር ከሰባቱ ሻለቃ ለልዩ ተልዕኮ የተውጣጡ አዲስና ነባር ሰልጣኞችን በማዋሃድ በደማቅ ሁኔታ አስመረቀ‼️ የምረቃ ፕሮግራሙን የመክፈቻ ንግግር በአርበኛ ጌታቸው መልኩ የ102ኛ ኮር ወታደራዊ አዛዥ የተደረገ ሲሆን ለሰልጣኛት የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት ካስተላለፉ በኋላ ወታደራዊ አዛዡ አያይዘው እንደተናገሩት ከሆነ የአብይ አህመድን ጨፍጫፊ አገዛዝ በአጭር ጊዜ ለማስወገድ የተለያዩ ስልጠናዎች በሌሎች ክፍለ ጦሮች እንደሚቀጥሉ ጠንከር ያለ ሀሳብ አስተላልፈዋል። በተጨማሪም የ102ኛ ኮር የስልጠና መምሪያ ሀላፊ መቶ አለቃ ሲሳይ መንግስቴና የኩሩ ምክትል የስልጠና መምሪያ ሃላፊ ሻለቃ ቢሆን አከለ እንደተናገሩት ያለጦርነት መኖር ከማይፈልገው የአብይ አህመድ አገዛዝ  የአማራን ህዝብ በቀላሉ ነፃ ለማውጣት ከ12ኛ ክፍለ ጦር በሁሉም ሻለቃ የተወጣጡ አዲስና ነባር ሰልጣኞችን በማዋሃድ በተግባርና በንድፈ ሀሳብ የተደገፈ ስልጠና መስጠታቸውን ተናግረዋል። እንድሁም የ102ኛ ኮር አሰልጣኝ የሆኑት መቶ አለቃ ሉዑልሰገድ ፣ አስር አለቃ አለሙ መልኩ፣ ባሻ ሰማየ ተመቸ፣ አምሳ አለቃ የአብቃል ቢተው አንደተናገሩት  የሰራዊታችን የውጊያ ልምድ ሞራልና አጠቃላይ ስነ-ልቦና ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመምጣትና በጥሩ ቁመና ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል። በወቅቱም  አድስና ነባር ልዩ ሰልጣኞች ያለምንም አሰልጣኝ ድጋፍ በንድፈ ሀሳብ የተማሩትን ትምህርት ኢላማውን የጠበቀ የተግባር ልምምድ በማድረግ ለምረቃ ብቁ መሆናቸውን አስመስክረዋል። በመጨረሻም 102ኛ ኮር ዋና ሰብሳቢ ቀኝ አዝማች ረዳ ውበቱ ለሰልጣኞች የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት ካስተላለፉ በኋላ የ102ኛ ኮር ከፍተኛ አመራሮችና የ12ኛ  ክፍለጦር አመራሮች በተገኙበት ከ12ኛ ክፍለ ጦር የተወጣጡ አድስና ነባር ልዩ ሰልጣኞችን ለልዩ ግዳጅ ማስመረቅ መቻላችን የአማራን ህዝብ በሀይል ለማንበርከክ፣ ህገ-መንግስታዊና መዋቅራዊ በደል ለማስቀጠል  እንድሁም የዳር ተመልካች ለማድረግ የመጣውን የብልፅግና አገዛዝ በቀላሉ ለማስወገድ በኮራችን ለሚገኙ ክፍለጦሮች ስልጠናው ጥሩ ተሞክሮ መሆኑን በመግለጽ፣ለሰልጣኞች አድስ ዩኒፎርም በማልበስ መረሀ ግብሩ ተጠናቋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! ©የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የ102ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት መጋቢት 13/2018 ዓ.ም

ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር በደራ ምድር ባደረገው አውደ ውጊያ በጨዋታው ሕግ የተሸነፉና ከብልጽግና ሕይወት የተሰረዙ የአቢይ አሕመድ ብልጽግናዎች ዝርዝር፦ 1.የደራ ወረዳ ፖሊስ  ዋና አዛዥ ኢንስፔክተር👉  ታከለ እርቄ 2.የደራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ👉 አቶ እስቲበል ጓዴ 3. የደራ ወረዳ ብልፅግና ፅ/ቤት ኃላፊ 👉 አቶ ፈንታሁን  ድረሥ 4.የደራ ወረዳ ትምህርት ፅ/ቤት ኃላፊ 5.የሐሙሲት ክፍለ ከተማ ከተማ ከንቲባ👉 አቶ ተመስገን የሸዋስ 6. የደራ ወረዳ አድማ ብተና ሻለቃ ዋና አዛዥ 7.የአድማ ብተና ሻለቃ  ዋና ዘመቻ ኃላፊ 8.የአምበሳሜ ከተማ አሥተዳደር መዘጋጃ ኃላፊ 9.የደራ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ 10.የሐሙሲት ክፍለ ከተማ  ከተማ የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ኮማንደር ምሕረት ካሴ 11.የደራ ወረዳ ፖሊስ ሰው ኃይል አስተዳደር 12. የአርብ ገበያ ከተማ ፖሊሥ አዛዥ(የመከላከያ መንገድ መሪ የነበር፣ ሜ/ጀነራል ውባንተ አባተ የክብር መሥዋዕትነትን ሲቀበል መከላከያን መንገድ እየመራ የመጣ፣ የደራ ሕዝብ ቁጥር አንድ ጠላት) ረዳት ኢንሥፔክተር   ''ሰለሞን ምሥጋናው'' 13. ደራ ወረዳ ሚሊሺያ ኃላፊ👉👉ጋሻነው አበራ 14. ሐሙሲት ክፍለ ከተማ ወንጀል ምርመራ አሥተዳደር👉👉ዋና ሳጅን ነጋ ... ሌሎቹም ከፍተኛና መካከለኛ የብልፅግና አመራሮችና የአድማ ብተና(አማራ በታኝና መደበኛ ፖሊሥ ኃላፊዎቹ  ይገኙበታል። ማነህ ባለሳምንት----? የብአዴን ብልጽግና ቅዱሥ የለውምና ይህ ዕንቁ ዓምሐራዊ ርምጃ በእጅጉ ተጠናክሮ ይቀጥላል። 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 መልዕክት ለሆድ አደር አማራ ብልጽግናዎች፦ ዓምሐራን በዓምሐራ'' የሚለውን የአቢይ አሕመድ ፕሮጀክት ማስቀጠሉ ይበቃችሁ፣ ለአቢይ ሥልጣን ብላችኹ መሞቱ ይቅርባችኹ፣ ታሪካችኹን በቆሸሸ ቀለም  ከማጻፍ ተቆጠቡና ወደ ዓምሐራነት ተመለሱ❗ አማራ ያልሆንከው ብአዴን ብልጽግና በጊዜ ዓምሐራ ሁን❗ ውባንተነት አይበገሬነት ውባንተነት ዓምሐራነት ዓምሐራነት አሸናፊነት✊👊 የጎንደሩ ደራ ለጠላቱ እማይራራ ለወገኑ የሚያኮራ እርሱ ነው ዓምሐራ። ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን❗ ዝንተዓለም ዓምሐራ Forever AMHARA✊👊 ፩ ዓምሐራ✊ አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ህ/ግ ክፍል ቋሚ ምሥል፦ ከሐሙሲት ክፍለ ከተማ እሥከ ጎምባት በተደረገው ውጊያ የተደመሰሱ የዕቡይ አሕመድ አማራ ብልጽግናዎች መጋቢት 09/2018ዓ.ም ደራ/ጎንደር/ዓምሐራ/ኢትዮጵያ

ሰበር የአደረጃጀት ዜና ቀን 12/07/2018 🌿🌿🌿🌿=====🌿🌿🌿🌿 አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር ግዙፉ እትጌ ጣይቱ ክፍለ ጦር አደረጃጀት ሪፎርም  ሰርቷል። 🌿🌿🌿🌿====🌿🌿🌿🌿   የአማራነት መሰረት ለአማራነት መታመን ገብርየነት ከትግል ፊደላቸው አርበኛ አስቻለው ደሴ በመቀበል በኃላም በታማኙ አስተዋዩ እና የጽናት ተምሳሌቱ አርበኛ ተሾመ ስትመራ የቆየችው እትጌ ጣይቱ ክፍለ ጦር የመሪነት ችቦውን  በአማራነት ስነልቦና ተቀርጸው ላደጉት ወጣት ታጋዮች ; አታጋዮች እና መሪወች ዛሬ የጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ  ዘመቻ መሪ እና የ204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር ዋና አዛዥ አርበኛ ተሾመ አበባው በተገኙበት ሪፎርም አድርገናል። ➊ ዋና ወታደራዊ አዛዥ------  አርበኛ መልካም አበባው ➋ ምክትል ወታደራዊ አዛዥ---- አርበኛ አዛናው ታረቀኝ ➌ ፅ/ቤት -------መ/አለቃ ገዳም ካሳ ➍ ዘመቻ ኃላፊ ---------- አርበኛ ድግሴ አብራራው ➎ ም/ዘመቻ----------- አርበኛ ደስየ ገብሩ ➏ መረጃና ደህንነት ኃላፊ----------##### ➐ ወታደራዊ ምልመላና ስልጠና ኃላፊ ------አርበኛ አሽናፊ አበራ ➑ ምክትል  ምልመላና ስልጠና -----አርበኛ አብዩ ካሳው ➒  ወታደራዊ እቅድና ስትራቴጂ ኃላፊ----- አርበኛ አዲሴ ከበደ ❿አደረጃጀት ዘርፍ ኅላፊ -----------አርበኛ አረጋ ደሴ  ⓫ የሰው ሀይል ------- አርበኛ እርቂሁን አበራ ⓬ ፋይናንስና ንብረት ኃላፊ ----አርበኛ ቄሴ ስንታየሁ አደባባይ ⓭ ገንዘብ ያዥ ------- አርበኛ ክብሬ ጥጋብ ⓮ ፍይናንስ ፀሀፊ -----አርበኛ ሰፊው ደስታው ⓯  ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ----አርበኛ ቴዎድሮስ መስፍን ⓰ ም/ፓለቲካ ዘርፍ -----አርበኛ መልኬ ገነቱ ⓱ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ----አርበኝ ሙሉየ ደሴ ⓲ ሕዝብ አስተዳደር ኃላፊ------አርበኛ ሳለአምላክ እሽቴ ⓳ ቀጠናዊ ትስስር -----------አርበኛ አንጋው ሹመት ⓴ ህግ ጉዳይ   ኃላፊ----------አርበኛ አገኝ እጂጉ ➋➊  ዳንኤል አዲስ  ------------- ወታደራዊ አስተዳደር ሆኖ  ተደራጂቷ፡፡ ድል ለአማራ ፋኖ!!! ድል ለአማራ ህዝብ!!! አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል!