uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling 👈

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Kanalga Telegram’da o‘tish

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Ko'proq ko'rsatish
4 129
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
+4197 kun
+1 13230 kun
Postlar arxiv
የ201ኛ ኮር 54ኛ ክ/ጦር የተሳካ የአመራር ግምገማ አካሂዷል። ➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺ ጥር 04/2018 ዓ.ም የአማራ የትጥቅ ትግል በየጊዜው እያሳየ ባለው የአደረጃጀት እድገት በፋኖነት የትግል
+1
የ201ኛ ኮር 54ኛ ክ/ጦር የተሳካ የአመራር ግምገማ አካሂዷል። ➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺ ጥር 04/2018 ዓ.ም የአማራ የትጥቅ ትግል በየጊዜው እያሳየ ባለው የአደረጃጀት እድገት በፋኖነት የትግል አረዳድ ቅንነት ዋነኛ መሰረቱና ንግግር ፣ ምክክር ደግሞ የዕለት ከዕለት ስራው ነው። በዕለቱ ብዙ ሀሳቦችን በማንሳት የወደፊቱን የውጤት አቅጣጫወችን ድንቅ የተግባቦት መድረክ ተፈጥሯል። ይኸውም 1● በአዲሱ አደረጃጀት የስራ ስምሪት ያጋጠሙትን ተግዳሮትና የስራ ውጤት 2● የ5ቱንም ሻለቆች ቁመና ፍተሻና የክፍለጦሯን ተወርዋሪ ኃይል በሚናዋ እንድትገኝ የማድረግ ስራ 3● የኃብት አሰባሰብና ድጋፍን በተመለከተ ቀጠናዊ ሚዛናዊ ስራን መስራት 4● የክፍለ ጦሩ የጋራ አቋም ለቀጠናው አስፈላጊነት የሚሉና በወትሮ ዝግጁነት በድርጅት ሚዛን አስጠባቂነት የጋራ አስተውሎት ይዞ ስብሰባውን አጠናቋል። ጥር 04/2018 ዓ.ም አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!! የቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

የአማራ ህዝብ ትግል በግለሰቦች ላይ የተንጠለጠለ አይደለም!! ትግላችን የአማራን ህዝብ መሰረታዊ ጥያቄዎች በመመለስ በድል የሚቋጭ እንጅ ግለሰቦች በስናዳሪነት ከድተው ስለገቡ የሚለወጥ አንዳች ነገር የለም። የአማራ ህዝብ በየአዝማናቱ የገጠመውን ብሔራዊ አደጋ በመቀልበስ ረገድ ዘለግ ያሉ ዓመታትን የተሻገረ ቢሆንም ከቅርብ ጊዚያት ወድህ የጀመርነው የእኛ ዘመን ትውልድ አብዮት ደግሞ ከቀድሞዎች የአማራ ታጋዮች የተለየ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል!! አማራነትን ለመናኛ ጥቅም አናውለውም ሲባል በርካቶች የከፈሉትን ዋጋ በማሳነስ ከተነሳንለት ዓላማ በተፃራራው መቆምን በፅናት ስንታገለው ብቻ ነው። ትግላችን በጠላቶቻችን ላይ ፍፁም ጭካኔ እና የስነ ልቦና የበላይነትን በመያዝ የማያዳግም እርምጃ መውሰድን ይጠይቃል። ስለሆነም በአብዮታችን ውስጥ በሚያጋጥሙ ውስጣዊ እና ውጫዊ ተግዳሮቶች ሳናደናገጥ ለእውነተኛው አላማችን በፅናት ልንቆም ይገባል። ጠላት እየተሸነፈ እና እየወደቀ ባለበት ስዓት ወደ መታረጃ ቄራው መሄድ ነውረኝነት ነው። ትግላችንን እንደ ዓይን ብሌናችን ልንጠብቀው ይገባል!! አይበገሬው የአማራ ሰራዊት ያሸንፋል!! ዝንታለም አማራ ወይራው አማራ

ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ !!! ፕሮፌሰሩ ምን አሉ ??? የአማራ ጠላት ሆዳም አማራ ነው ። የፋኖም ጠላት ሆዳም ፋኖ ነው ። የአማራን ህዝብ ጥያቄ ይዘው ወደፋኖ የተቀላቀሉ እና በዚህ ትግል በማጓተት እና በውስጥ አድነት እዳይመጣ ስታተራምሱ የቆያችሁ ምስለኔዎች ወልዳችሁ አትሳሙ የሰራችሁት አይባረክላችሁ ። በዚሀ ትግል ላይ አስመምስላችሁ ስትናገሩ ቆይታችሁ ወጣቱ ለዚህ ትግል የተሰዉትን መርሳት ሂሊና ቢስነት ነው ። በወጣቱ ደም እደነገዳችሁ ፈጣሪ የጀግና ደም ፈሶ ስለማይቀር ነገም ብልፅግናንም ትከዱታላችሁ ምክንያቱም የከዳችሁት የአማራን ህዝብ ነው። የአማራ ትግል አንድ እዳይሆን አተራመሳችሁ እጅ የሰጣችሁት የምትመሩት ሰራዊት እና ህዝብ አንድ ካልሆናችሁ ብሎ ጫና ሲያሳድርባችሁ ነው ሸሽታችሁ የገባችሁት ። ይሄንን ትግል በእውነት የምትታገሉ እና የምትደግፍ ሲነቃባቸው ስለሆነ የገቡት ከምግዜውም በላይ እደብረት ጠንክረን ማሸነፍ አለብን ። እስካሁን ትግሉን ሲጎትቱ የነበሩ ሰዎች መሄዳቸው ጥሩ ነው ወደፊት እቅፋት የሚሆኑ ሰዎችን እየለየን እርምጃ መውሰድ ይጠበቅብናል ሲጠራ ትግሉ አይጓተትም በአጭር እቋጨዋለን ስለዚህ መጠከር ነው አማራ ያሸንፍል። የዚህ ትግል እቅፍቶች 1.የመግስት ተላላኪዎች ተቀጥረው ለማተራመስ የመጡ ይኖራሉ 2.ትግሉ ሳይገበው ቲክቶክ አይቶ የመጠው ሲጨቀው ይጠፋል 3. ስራ አቶ ግራ ሲገበው ይመጣ ይኖራል 4.በፍኖ ውስጥ ተደብቆ የግል ጠላቱን ለመበቀል የመጣ ይኖራል 5. በፋኖ ስም ተደራጅቶ ለመዝረፍ የወጣ ይኖራል በአጭሩ በዚህ ተመሳሳይ ሰዎች ይኖራሉ ትግሉ እያደገ ሲመጣ አሰራር ሲዘረጋ መርህ ሲኖርባቸው እየሸሸ ወደ መግስት ሲገቡ ትግሉ እየጠራ ነው። እውነተኛ ታጋይ ይቀጥላል ተላላኪው ሲሸሽ ትግሉ በአጭር ይቋጫል ። ስለፍኖ መጥፎ የሚያወሩ ሰዎችን ተከታተሉ ችግር ያለበትን መለየት አለብን ጥሩ ሰው እየመሰሉ መርዝ የሚረጩትን መከታተል አለብን ትግል ይቀጥላል ። ደጋፌዎች እና ለዚህ ትግል ሚዲያ የምትሰሩ እየተከታተላችሁ ለህዝቡ እውነታውን ማስረዳት አለባችሁ። ከልብ የምትታገሉ አመራሮች፣ ስራዊቶች እና ህዝባችን በንፁሀን ላይ የሚደርስ በደሎችን መከታተል እውቅና መፈጣጠር ይኖርብናል የመግስትን ተልኮ ተሸክመው ንፁሀንን እዳይበደልብን። ትግል ይቀጥላል ተላላኪዎች እጁን ይሰጣሉ !!! በተላላኪዎች ታሪክ ተፅፎ አያውቅም !!! ተኮለኛ እድሜው አጭር ነው !!! ኢቶጵያ በጀግኖች አጥንት እና ደም የተመሰረተች ሀገር ነች!!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ምክትል ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አርበኛ ኤፍሬም ባዩ

"አንበሳ ምን ቢርበው ሳር አይግጥም!!" የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ከፍተኛ አመራር የሆነው ሻለቃ ሀብታሙ ደምሴ በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ያስተላለፈው መልዕክት!! የአማራ ህዝብ ላይ የተደቀነው የህልውና አደጋን ተከትሎ ለህዝባችን የደህንነት ዋስትና ለመሆን ዱር ቤቴ ብለን ጠብመንጃ አንስተን ወደ ጫካ እና በርሃ የገባነው ህዝብን የማዳን አላማን አንግበን መሆኑ ይታወቃል። በበኩላችን የምንሞትለትን አላማ ጠንቅቀን ስለምንረዳ ይህን አላማ ለማሳካት የሚያስችል ፅናት ተላብሰን ትግላችንን ቀጥለናል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ቅርብ ወራጆች ደግሞ በየተራ ወደ ጠላት እየገቡ መሆናቸውን ታዝበናል። ትግል ያለ አላማ እና ፅናት እንደማይሰምር ሁሉ፤ አላማ ቢስ የሆኑ ልፍስፍሶች ወደ ጠላት ሲገቡ ልንረዳው የሚገባ ነገር ቢኖር የትግሉ ሜዳ እየፀዳ መምጣቱን ነው። በትግሉ ሜዳ ላይ በፅናት መቆየት የሚችሉት አላማ ያላቸው ብቻ መሆናቸውን ልንገነዘብ ይገባል። አላማ ከሌላቸው ብዙኃን ይልቅ አላማ ያላቸው ጥቂቶች ለድል ይበቃሉ። የአማራ ህዝብ አሁን ላይ እየሆነ ባለው ነገር ሳይደናገር እና ሳይደናገጥ በእኛ በልጆቹ ሙሉ እምነት እንድኖረው የምናሳስበው የፀና ህዝብ አሸናፊ እንደሚሆን ስለምናውቅ ጭምር ነው። የትግሉ ሂደት መሰናክል የበዛበት መሆኑን አምነን መሰናክሎችን ሁሉ በፅናት ለማለፍ ቆርጠን እንደ ህዝብ መነሳት ይገባናል። ይህ ሊሆን የሚችለው ደግሞ አማራዊ አንድነታችንን ማንበር ስንችል እና የጋራ መግባባት ላይ ስንደርስ ነው። ባቡሩ ሲጓዝ በየፌርማታው የሚወርዱ ተሳፋሪዎች እንደሚኖሩ ተገማች ነው። ይህን ትግል እንደ ባቡር ቆጥረነው በየፌርማታው የሚወርደው ተሳፋሪ ጉዳይ ሊያሳስበን እንደማይገባ ለማስታወስ እንወዳለን:: በጣም የሚገርመው ነገር ቢኖር ወደ ጠላት የሚገቡ አካላት ለክዳታቸው እንደ ሰበብ የሚቆጥሩት በዋናነት ጌቶቻቸው የሚሰጧቸውን አጀንዳ መሆኑ ነው። ስለዚህ እነሱ ከጅምሩ የጠላት እንጅ የእኛ አልነበሩም ማለት ነው። የጠላትን አጀንዳ ከጠብመንጃ ጋር ተሸክመው ላይ ታች ሲሉ የነበሩ ስለሆኑ እነሱ ቢመጡ ቢሄዱ ምንም ሊደንቀን ሊጨንቀንም አይገባም። ጥርሳችንን ነክሰን በመታገል የሚከፈለውን መስዋዕትነት እየከፈልን ለአማራ ህዝብ የደህንነት ዋስትናዎች ለመሆን እና ኢትዮጵያን ከመፍረስ ለመታደግ ቆርጠን የተነሳን በመሆናችን እስከመጨረሻዋ የድል ብስራት ከአላማችን ዝንፍ እንደማንል እያረጋገጥኩኝ "አንበሳ ምን ቢርበው ሳር አይግጥም!!" እንድሉ አበው እኛም ምንም አይነት አጀንዳ ቢወረወር ከጠላት ጎን ልንሰለፍ እንደማንችል እሙን ነው። ሻለቃ ሀብታሙ ደምሴ የአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ከፍተኛ አመራር መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ጥር 4 ቀን 2018 ዓ.ም

ኮ/ል ፋንታሁን ሙሀባ እጁን እንደሰጠ ተዘግቧል። አሕፋድም ኮሎኔሉ ከሃላፊነት መነሳቱን ገልፆል። ኮሎኔሉ በአቅማቸው ለአማራ ህዝብና ለአመኑበት አላማ ታግለዋል። እስካሁን ለከፈሉት መስዋዕትነትም ሊመሰ
ኮ/ል ፋንታሁን ሙሀባ እጁን እንደሰጠ ተዘግቧል። አሕፋድም ኮሎኔሉ ከሃላፊነት መነሳቱን ገልፆል። ኮሎኔሉ በአቅማቸው ለአማራ ህዝብና ለአመኑበት አላማ ታግለዋል። እስካሁን ለከፈሉት መስዋዕትነትም ሊመሰገኑ ይገባል። የኮሎኔሉ እጅ መስጠትም ወሎ በአንድ እዝ ስር እንዲገባ ስለሚያደርገው፣ ለፋኖ የሚጠቅም እንጅ የሚጎዳ አይሆንም። ለብልፅግና ግን ጉዳቱ ከፍተኛ ነው ምክንያቱም ፋኖዎችን ለመከፋፈል የሚጠቀምበትን መንገድ ሁሉ እያጠበበበት ይሄዳል። የፋኖ አንድነት በዚህ ሳምንት ውስጥ የሚበሰር ከሆነ፣ ከስልጣን ወይም ከሌሎች ህዝባዊ ካልሆኑ ግላዊ ፍላጎቶች ጋር በተያያዘ፣ ለቀው የሚወጡ ብዙ ሰዎች እንደሚኖሩ ይጠበቃል። ይህ በየትኛውም የድርጅት ጉዞ ላይ የሚያጋጥም በመሆኑ ሊገርም አይገባም። ትልቁ ነገር እንዲህ አይነት ሂደቶች መልካም ነገር ይዘው እንደሚመጡ ማመንና መስራት ነው። አፋሕድ ዛሬ ባወጣው መግለጫ የአማራ ፋኖ አንድነት እየተጠናቀቀ መሆኑን ገልፇል። የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝም እንዲሁ ትናንት ተስፋውን ገልፇል። ይህ ዜና ነው አማራውን እና ነፃነት ወዳዱን የኢትዮጵያ ህዝብ ሊያስፈነድቀው የሚገባው። © Fasil YeneAlem

የአማራ ህዝብ በዚህ ልክ ነው ሙሃቤ አጭበርብሮ ለብልፅግና ከአራት ያልበለጠ ኃይሉን ይዞ የገባው ለማነኛውም ያው የብልጽግና ውሸት ብዙ ነውና ሙሉ ጦሩን ይዞ ገባ እንዳይል ይህን አረመኔያዊ ሰውዬ ሲሸኝ የሚያሳይ ቭድዮ ሸር አድርጎናል

ኮሎኔል ፋንታሁን ሄደ መጣ ምንም የሚጠቅመው ነገር የለም በፈረሰ ተጭኖ ሲሄድ ነው ነገሩ ያለቀው ጡረተኛ ዛሬም ነገም ፋኖ ያሸንፋል እኛ ለክብሩ ብለን ነው እንጂ ድሮም ዝም ያልነው ሴረኛ መሆኑ ጠፍቶ
ኮሎኔል ፋንታሁን ሄደ መጣ ምንም የሚጠቅመው ነገር የለም በፈረሰ ተጭኖ ሲሄድ ነው ነገሩ ያለቀው ጡረተኛ ዛሬም ነገም ፋኖ ያሸንፋል እኛ ለክብሩ ብለን ነው እንጂ ድሮም ዝም ያልነው ሴረኛ መሆኑ ጠፍቶን አይደለም። አሸናፊዎቹ እኛው አማራዎች ነን!!

ከአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ም/ ወታደራዊ አዛዥ እና የግዙፉ ላስታ አሳምነዉ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ ወንድሙ ማሩ በወቅታዊ ጉዳይ የተሰጠ አጠር ያለ መግለጫ!!
ከአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ም/ ወታደራዊ አዛዥ እና የግዙፉ ላስታ አሳምነዉ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ ወንድሙ ማሩ በወቅታዊ ጉዳይ የተሰጠ አጠር ያለ መግለጫ!! ይህን የአማራ ፋኖ ትግል የጀመርንበት ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩንም ዋነኛ ምክንያታችን አማራ በመሆናችን ብቻ በወለጋ ፣ በነቀምት ፣በሻሸመኔ፣ በጉራፈርዳ ፣በመተከል እና በሌሎች አካባቢዎች በጃምላ ተጨፍጭፈናል በጅምላ ተገለናል ፣ በጅምላ ተፈናቅለናል በዚህም ምክንያት አማራ የመዳኛ መንገዱ ክንዱና ነፍጡ መሆኑን አዉቀን ዱር ቤቴ ካልን 3 እና 4 ዓመታትን አሳልፈናል። በዚህም ቆይታችን ዱላ ይዘን ወጥተን ከክላሽ እስከ እስከ ዲሽቃ ከዲሽቃ እስከ ሞርተር እና ሌሎች ካባድ መሳርያዎችን ታጥቀናል። ይህን ሁሉ መሳርያዎች ይዘን እየታገልን ባለንበት ወቅት በ አባታችን ብ/ጄኔራል አሳምነዉ ፅጌ ስም ሲነግድ የነበርዉ ኮረኔል ፈንታሁን ሙሃቤ በትላንትናዉ ዕለት ለዚህ ፋሽዝም ስርዓት እጅ ሰጠ የሚል ዜና ሰምተናል። ኮረኔል ፈንታሁን ለአገዛዙ እጅ ሰጠ አልሰጠ የአማራ ፋኖ ትግል አይቆምም ምክንያቱም ይህ ትግል ለግለሰቦች ስንል ሰላልወጣን። እኛ ግን የጀኔራል አሳምነዉ ልጆች የአባታችን የአደራ ቃል ተወጥተን የአማራን ትንሳኤ እናበስራለን። አሁንም በዚህ ትግል እሚነግድ ካለ መንገዱ ክፍት ነዉ እንክርዳዶቹ ከስንዴዉ እንድትለዩልን እንፈልጋለን። ይህን ትግል ስንጀምር ላንጨርስ አልጀመርነዉም አማራነት ያሸንፋል ድል ለፋኖ ድል ለአማራ!! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ም/ወታደራዊ አዛዥ እና የግዙፉ ላስታ አሳምነው ኮር ሰብሳቢ አርበኛ ወንድሙ ማሩ!! ጥር 4/2016 ዓ.ም

ተጠናክሮ በቀጠለው ተጋድሎ ዋግሹም ብርጌድ 46 የአገዛዙን ፖሊስና ሚሊሻ በመደምሰስና 58 የነፍስ ወከፍ መሳሪያ በመማረክ ታላቅ ድል ተጎናፀፉ‼️ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የላስታ ጄኔራል አሳምነዉ ፅጌ ኮር አካል የሆነው ዋግሹም ብርጌድ በዋግኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ድሃና ወረዳ 010 ቀበሌ አባም አቦ ቀጠና ጥር 03/2018 ዓ/ም ከጧቱ 12:00 ሰዓት እስከ ምሽት 1:00 ሰዓት ባደረጉት ከባድ ትንቅንቅ የብልፅግና ዙፋን አስጠባቂ የሆኑትን የድሃና ወረዳ ፖሊስና ሚሊሻ አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ታላቅ ጀብዱ ፈፅመዋል። መነሻውን ከድሃና ወረዳ አምደወርቅ ከተማ ወደ 010 ቀበሌ አባም አቦ ቀጠና በመንቀሳቀስ ዋግሹም ብርጌድ ፋኖዎችን አፍናለሁ በሚል የተንቀሳቀሰው የወረዳው ፖሊስና ሚሊሻ አባላት መረጃው ቀድሞ የደረሰው የብርጌዱ ወታደራዊ መረጃ ክፍል ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ሊያፍን የመጣውን የጠላት ኃይል በተቃራኒው ከበባ ውስጥ በማስገባት አንድም ኃይል ሳይቀር እንዲደመሰስ፣እንዲቆስልና እንዲማረክ ተደርጓል። በዚህ አውደ ውጊያ 46ቱ ሲደመሰስ፣29ኙን በማቁሰል ሁለት አመራሮችን ጨምሮ 24ቱ ሊማረኩ ችለዋል። በተያያዘም 32 ክላሽንኮፍና 16 የቃታ መሳሪያ በድምሩ 48 የነፍስ ወከፍ መሳሪያ፣2860 ተተኳሽ፣56 የወገብ ትጥቅ ተማርኳል። ከምርኮኞቹ መካከልም የድሃና ወረዳ ፖሊስ ምርመራ ሂደት ኃላፊ ኢንስፔክተር ሸጋ አያናውና የድሃና ወረዳ ሚሊሻ ፅህፈት ቤት ኃላፊ መቶ አለቃ ምስጋናው ይገኙበታል። ©አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ! 04/ዐ5/2018 ዓ.ም

"ዘመነነት" ግለሰብ ብቻ አይደለም ርዕዮት ዓለም ነው! ስንልህ አረፋ እየደፈቀህ እያጓራህ የጮኸው አጋንንት መንጋ በፅናት እና በትዕግስት ስትቀጠቀጥ ወደ አሳማነትህ እየገባህ ነው። አሁን ጥያቄው ጥን
"ዘመነነት"  ግለሰብ ብቻ አይደለም ርዕዮት ዓለም ነው! ስንልህ አረፋ እየደፈቀህ እያጓራህ የጮኸው አጋንንት መንጋ በፅናት እና በትዕግስት ስትቀጠቀጥ ወደ አሳማነትህ እየገባህ ነው። አሁን ጥያቄው ጥንብ አንሳው መቼ ነው የሚገባ የሚለው ነው።

ውድ የአማራ ፋኖ እንዲሁም የአማራ ህዝብ እንዴት ዋልህ አደርህ ? በያላችሁበት ሰላማችሁ ይብዛ እና አንድ መልዕክት ላስተላልፍ እፈልጋለሁ ! ጠላት የአማራ ፋኖን በትር እንደማይቋቋመው መቶ ፐርሰንት አረጋግጦ እነሱ ያዋጣናል ያሉትን ስትራቴጂ ላሳውቃችሁ እፈልጋለሁ ! እናም እኛ ደግሞ ምን አይነት ስትራተጂክ እንደምንጠቀም እና ይበልጥ ስኬታማ የሚያደርገንን በዝርዝር እመለስበታለሁ ። ✍️የጠላት ስትራቴጂ ምንድን ነው እየተጠቀመው ያለው ለሚለው ጥያቄ ? 1. ከበባ ውስጥ በማድረግ አለ የለም የሚባል ሀይል ተጠቅሞ ፋኖን ማዳከም 2.የአማራ ሆዳሞችን አስርጎ በማስገባት "እጀን በእጀ ቆረጥሁት " አይነት ስትራቴጂ 3. ፋኖን ሽህ ጊዜ ቢዋጉ በክላሽ፣ዲሽቃ፣ስናይፐር እና ብሬን ቁሞ መግጠም 154 ጠላት ለአንድ ፋኖ Ratio ሲሰራ መሆኑ ከአሁን በፊት በተደረጉት ውጊያዎች በተደረገ ጥናት በደጋ ዳሞት፣ስናን፣ቋሪት፣ደምበጫ እና መራዊ በትንሹ ሬሽዋቸው ይመጣል ! እናም ጠላት መጠቀም የሚፈልገው ድሮን ፣ ታንክ፣ ፔንፔ፣ ዙ-23 እና ጀነራል መድፍ ብቻ ነው! 4. ጠላት የህዝብ ተቀባይነት ለማግኘት እሁድ እሁድ ከቤተክርስቲያን እያስወጡ መሰብሰብ እና ፓለቲካ መጋት! 5.የሀይማኖት አባቶችን እንግልት ማብዛት ምክንያቱም አማራ ፈጣሪውን እንጂ ጠላቱን ስለማይፈራ እና እንደማይለቃቸው ስለሚያውቁ በሀይማኖት አባቶች በኩል ደካማ ጎኖችን መጠቀም 6. ፋኖዎችን በቅርብ ዘመድ ወዳጆቻቸው ይሄን እናደርግላችኋለን ብሉ መደለል እና ማስከዳት ......ስለዚህ ጠላትን ከእነሱ በላይ ምሁራን የሚበዛበት የአማራ ፋኖ ነው አንድነት ያስፈልጋል ከላይ የተጠቀሱት የጠላት መንገዶች መታጨድ አለባቸው ! እንዲሁም ለሸክም እማያስቸግሩ መሳሪያዎች ነገር ግን ጉልህ ሚና የሚጫወቱ መሳሪያዎች መግባት አለባቸው እንደ RBG እና ብሬን እና ስናይፐሮች ከመጠን በላይ ያስፈልጋሉ ።

"#አንበሳ_ምን_ቢርበው_ሳር_አይግጥም‼️" የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ከፍተኛ አመራር የሆነው ሻለቃ ሀብታሙ ደምሴ በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ያስተላለፈው መልዕክት!! የአማራ ህዝብ ላይ የተደቀነው የህልውና አደጋን ተከትሎ ለህዝባችን የደህንነት ዋስትና ለመሆን ዱር ቤቴ ብለን ጠብመንጃ አንስተን ወደ ጫካ እና በርሃ የገባነው ህዝብን የማዳን አላማን አንግበን መሆኑ ይታወቃል። በበኩላችን የምንሞትለትን አላማ ጠንቅቀን ስለምንረዳ ይህን አላማ ለማሳካት የሚያስችል ፅናት ተላብሰን ትግላችንን ቀጥለናል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ቅርብ ወራጆች ደግሞ በየተራ ወደ ጠላት እየገቡ መሆናቸውን ታዝበናል። ትግል ያለ አላማ እና ፅናት እንደማይሰምር ሁሉ፤ አላማ ቢስ የሆኑ ልፍስፍሶች ወደ ጠላት ሲገቡ ልንረዳው የሚገባ ነገር ቢኖር የትግሉ ሜዳ እየፀዳ መምጣቱን ነው። በትግሉ ሜዳ ላይ በፅናት መቆየት የሚችሉት አላማ ያላቸው ብቻ መሆናቸውን ልንገነዘብ ይገባል። አላማ ከሌላቸው ብዙኃን ይልቅ አላማ ያላቸው ጥቂቶች ለድል ይበቃሉ። የአማራ ህዝብ አሁን ላይ እየሆነ ባለው ነገር ሳይደናገር እና ሳይደናገጥ በእኛ በልጆቹ ሙሉ እምነት እንድኖረው የምናሳስበው የፀና ህዝብ አሸናፊ እንደሚሆን ስለምናውቅ ጭምር ነው። የትግሉ ሂደት መሰናክል የበዛበት መሆኑን አምነን መሰናክሎችን ሁሉ በፅናት ለማለፍ ቆርጠን እንደ ህዝብ መነሳት ይገባናል። ይህ ሊሆን የሚችለው ደግሞ አማራዊ አንድነታችንን ማንበር ስንችል እና የጋራ መግባባት ላይ ስንደርስ ነው። ባቡሩ ሲጓዝ በየፌርማታው የሚወርዱ ተሳፋሪዎች እንደሚኖሩ ተገማች ነው። ይህን ትግል እንደ ባቡር ቆጥረነው በየፌርማታው የሚወርደው ተሳፋሪ ጉዳይ ሊያሳስበን እንደማይገባ ለማስታወስ እንወዳለን:: በጣም የሚገርመው ነገር ቢኖር ወደ ጠላት የሚገቡ አካላት ለክዳታቸው እንደ ሰበብ የሚቆጥሩት በዋናነት ጌቶቻቸው የሚሰጧቸውን አጀንዳ መሆኑ ነው። ስለዚህ እነሱ ከጅምሩ የጠላት እንጅ የእኛ አልነበሩም ማለት ነው። የጠላትን አጀንዳ ከጠብመንጃ ጋር ተሸክመው ላይ ታች ሲሉ የነበሩ ስለሆኑ እነሱ ቢመጡ ቢሄዱ ምንም ሊደንቀን ሊጨንቀንም አይገባም። ጥርሳችንን ነክሰን በመታገል የሚከፈለውን መስዋዕትነት እየከፈልን ለአማራ ህዝብ የደህንነት ዋስትናዎች ለመሆን እና ኢትዮጵያን ከመፍረስ ለመታደግ ቆርጠን የተነሳን በመሆናችን እስከመጨረሻዋ የድል ብስራት ከአላማችን ዝንፍ እንደማንል እያረጋገጥኩኝ "አንበሳ ምን ቢርበው ሳር አይግጥም!!" እንድሉ አበው እኛም ምንም አይነት አጀንዳ ቢወረወር ከጠላት ጎን ልንሰለፍ እንደማንችል እሙን ነው። ሻለቃ ሀብታሙ ደምሴ የአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ከፍተኛ አመራር መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! ©አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ጥር 4 ቀን 2018 ዓ.ም 04/ዐ5/2018 ዓ.ም

በክልሉ የመረጃና ደህንነት የፀረ መረጃ ክትትል ሀላፊ ሲሆን ትውልዱ ደቡብ ጎንደር ደራ ወረዳ ሀሙሲት ነው። ታዋቂ የጎጃም ባለሀብቶችን ልትታሰሩ ነው በማለት እያስፈራራ ገንዘብ የሚዘርፍ ጸረ-ህዝብ የ
በክልሉ የመረጃና ደህንነት የፀረ መረጃ ክትትል ሀላፊ ሲሆን ትውልዱ ደቡብ ጎንደር ደራ ወረዳ ሀሙሲት ነው። ታዋቂ የጎጃም ባለሀብቶችን ልትታሰሩ ነው በማለት እያስፈራራ ገንዘብ የሚዘርፍ ጸረ-ህዝብ የሆነ ጎጠኛ መሆኑን ደርሰንበታል። እሄ ግለሰብ በስሙ ባህርዳር ከተማ ላይ ዘንዘልማ 250 ካሬ ፣ ዲያስፖራ 150 ካሬ ፣ በወንድሙ ስም መሸንቲ 200 ካሬ ፣ ቀበሌ 04 130 ሚሊዮን የተገዛ አክሲዮን ፣  ቀበሌ 11 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ ጀርባ 120 ሚሊዮን የተገዛ  ወዘተ ...... ሌሎችን በዝርዝር እንመለሳለን።

የሚፈራና የሚንቀጠቀጥ ቢኖር ተመልሶ ይሂድ፥ መሳ7:3 በዓለም ታሪክ ውስጥ እጅግ የሚሰቀጥጠው ክህደት በጠላት የሚፈጸመው ሳይሆን፣ አብሮ በበላ፣ አብሮ በጠጣና "እስከ መቃብር አብሬህ ነኝ" ባለ የቅርብ ወዳጅ የሚፈጸመው ነው። ሐዋርያው ጴጥሮስ በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ የጌታውን ጠላቶች በሰይፍ ሊከላከል የቆረጠ ቢመስልም፣ በመጨረሻው ስዓት  ግን "አላውቀውም!" በማለት ሦስት ጊዜ ክዶታል። ጴጥሮስ፤ የከዳው ጠላት ስለበረታ ሳይሆን፣ በውስጡ ያለው "የመሞት ፍርሃት" ስላሸነፈው ነው። ዛሬም በሕልውና ትግላችን ውስጥ ያሉ አንዳንድ ሰዎች፣ የጥቅም ፍርፋሪ ሲያሳያቸው፣ እንደ ጴጥሮስ "ትግሉን አላውቀውም! ሕዝቤን አላውቀውም!" እያሉ ወደ ጠላት ካምፕ ይኮበልላሉ። ጴጥሮስ፤ የከዳው ጌታው ሊሰቀል ጥቂት ሰዓታት ሲቀሩት ነበር። ዛሬም ከዳተኞች የሚከዱት የነፃነት ፀሐይ ልትወጣ፣ የአምባገነኑ ሥርዓት ምሰሶ ሊናጋ ጥቂት ሲቀረው ነው። በድል ዋዜማ ላይ የሚደረግ ክህደት ደግሞ የታሪክ ጠባሳው አይፋቅም። በመጽሐፍ ቅዱስ ዶሮ መጮኽ ጴጥሮስን ከእንቅልፉ የቀሰቀሰች፣ የክህደቱን ጥልቀት ያሳየች ድምፅ ነበረች። ለዛሬዎቹ ከዳተኞችም "የዶሮዋ ጩኸት" የሕዝብ እንባና የታሪክ ፍርድ ነው። አምባገነኑ አገዛዝ እጅ የሰጡትን ከዳተኞች "ወንድሞቻችን ተመለሱ" እያለ በቲቪ ቢያሳያቸውም፣ በውስጣቸው ግን የሕሊና ዶሮ ትጮህባቸዋለች። ጴጥሮስ ከከዳ በኋላ "ምርር ብሎ አለቀሰ" (ማቴ 26፡75)፤ ንስሐም ገባ። የዛሬዎቹ ከዳተኞች ግን ክህደታቸውን "ለሰላም ነው፣ ለሀገር ነው" በሚል የሐሰት ስብከት ለማስረዳት ይሞክራሉ። ጴጥሮስ ስህተቱን አምኖ ተመለሰ፤ እነዚህ ግን በወንድሞቻቸው ደም ላይ ለሚቆም የባርነት ሹመት ሰገዱ። ዶሮ ሳይጮህ (የድል አዋጅ ሳይነገር) ሕዝባችሁን የካዳችሁ ሆዳሞች ሆይ! የያዛችሁት የጥቅም ዲናር እጃችሁን ያቃጥለዋል። አምባገነኑ ሥርዓት ሲወድቅ፣ እናንተ መሸሸጊያ አታገኙም። ታሪክ እናንተን የሚዘክራችሁ በጀግንነት ሳይሆን፣ "ብርሃን ሲቃረብ ጨለማን በመረጡ" የሽንፈት ተምሳሌቶችነታችሁ ነው። በታሪክ ውስጥ የድል ዋዜማ ሁልጊዜም "የጀግኖች መፈተኛ" እና "የከዳተኞች መውጫ" ናት። ጌዲዮን፤ ምድያማውያንን ለመውጋት 32,000 ሰራዊት አሰባስቦ ነበር። ነገር ግን ድል ሊደረግ ጥቂት ሲቀረው እግዚአብሔር አንድ መመሪያ ሰጠው "የሚፈራና የሚንቀጠቀጥ ቢኖር ተመልሶ ይሂድ" (መሳፍንት 7)፤ ድል ሊገኝ ጥቂት እርምጃ ሲቀረው 22,000 ወታደሮች ትግሉን ጥለው ወደ ቤታቸው ሄዱ። የቀሩትም ቢሆኑ ተፈትነው መጨረሻ ላይ ለድል የበቁት 300 ቆራጦች ብቻ ነበሩ። የትግል ብዛት ለድል ዋስትና አይደለም። በድል ደጃፍ ላይ ፈሪዎችና ተጠራጣሪዎችሆድ መክዳታቸው ትግሉን አያዳክመውም፤ ይልቁንም ትግሉን ከቆሻሻ ያጠራዋል። ድል የሚመጣው በሺዎች በሚቆጠሩ " አደሮች" ሳይሆን፣ በማይበገሩ ጥቂት "ልበ ሙሉዎች" ነው። ኢትዮጵያ በፋሽስት ጣሊያን ተወራ በነበረበት ወቅት፣ አርበኛው በላይ ዘለቀ በዓባይ በረሃዎች ላይ ጽኑ ትግል ያደርግ ነበር። ጣሊያን ድል መመታቷ ሲቃረብና አርበኞቹ አዲስ አበባን ለመያዝ ሲዘጋጁ፣ ጣሊያን አንድ ዘዴ ተጠቀመች። በበላይ ዘለቀ ዙሪያ የነበሩ አንዳንድ "ጽናት አልባ" አርበኞችን በገንዘብና "ሹመት እንሰጣችኋለን" በሚል ተስፋ መለመላች። ድሉ ዋዜማ ላይ እያለ አንዳንዶቹ "ትግሉ ሰለቸን፣ ጣሊያን አታሸነፍም፣ ይልቅ ይቺን ሹመት እንቀበል" ብለው እጃቸውን ሰጡ። በላይ ዘለቀ ግን እስከ መጨረሻው ጸና። ዛሬ ታሪክ የበላይ ዘለቀን ስም በወርቅ ቀለም ሲጽፈው፣ በዋዜማው የከዱት ግን ስማቸው ከባንዳነት ተርታ ተፈርጆ ቀርቷል። ክህደት ለጊዜው "እረፍት" ቢመስልም፣ ለዘላለም ግን "እሳት" ነው። በአሜሪካ የነፃነት ጦርነት ወቅት ቤኔዲክት አርኖልድ እጅግ ጀግና ከሚባሉ ጄነራሎች አንዱ ነበር። ነገር ግን አሜሪካ ድል ልታደርግ ጥቂት ሲቀራት፣ በነበረው የሥልጣን ጥመኝነትና በገንዘብ ፍላጎት ምክንያት አገሩን ከድቶ ለብሪታንያ ወገነ። ብሪታንያ ጦርነቱን ተሸነፈች። አርኖልድም ወደ ብሪታንያ ሸሸ። ነገር ግን የከዳቸው ወገኖቹ ብቻ ሳይሆኑ፣ የሄደባቸው ብሪታንያውያንእንኳን "ከዳተኛን ማን ያምነዋል?" ብለው ናቁት። በብቸኝነትና በውርደት ሞተ። አምባገነን አገዛዞች እጃቸውን ለሚሰጡ ከዳተኞች "እንኳን መጣችሁ" ቢሏቸውም፣ በልባቸው ግን ይንቋቸዋል። የገዛ ወንድሙን የከዳ ሰው ለማንም ታማኝ ሊሆን እንደማይችል ጠላትም ያውቀዋል። ዶሮ ሳይጮኽ ጴጥሮስ ክዷል፤ ግን ንጋቱ አልቀረም። ጌዲዮን 22,000 ሰራዊት ዮሐንስና ግን ድሉ አልቀረም። በላይ ዘለቀ በባንዳዎች ተከቧል፤ ግን ነፃነቱ አልቀረም። ጴጥሮስ ቢክድም የክርስትና ጉዞ አልቆመም። ዮሐንስና ሌሎች ጽኑዓን ግን እስከ ቀራንዮ ድረስ ተከተሉት። ዛሬም፤ በመካከላችን ያሉት "ጴጥሮሶች" ቢከዱ፣ ትግሉ ከከባድ ሸክም እየቀለለ መሆኑን እወቁ። እኛ የምንሸከመው የነፃነት አክሊል ለከዳተኞች አይገባቸውም ነበርና ፈጣሪ ለይቷቸዋል። ጽናት አልባዎች ቢከዱ፣ ትግሉ አይቆምም። እንዲያውም ትግሉ ከ"ይሁዳዎች" እና ከ"ፈሪ ጴጥሮሶች" ጸድቶ ወደ መጨረሻው ድል ይሸጋገራል። እኛ፤ እስከ ቀራንዮ (እስከ መስዋዕትነት) የቆምን የነፃነት ሐዋርያት ነን።   ትዕግሥት ፣ፅናት፣ፍቅር ፣እምነት ፣እውነት።                             ፅና! ፋኖ እስቲበል ዓለሙ የአፋብኃ ቴወድሮስ እዝ ምክትል የህዝብ ግንኙነት መምሪያ ሀላፊ

#የአማራ_ትግል_እየጠራ_ነው‼️ #የዳውንቱ_ስምምነት_ተግባራዊነቱ_ቀጥሏል‼️ ከአመት በፊት አፋሕድ ዳውንት ላይ ከአፍሪካ ህብረት ፣ ከኢጋድ ፣ እና ከብልፅግና ሰዎች ውይይት ማድረጉን የአፋሕድ ሊቀመበር እስክንድር ነጋ መግለጫ መስጠቱ ይታወሳል። አፋሕድ ይህንን ትግል ለአመታት ሲረብሽ ከቆዬ በኋላ ተራ በተራ ወደ ላኪያቸው አገዛዝ እየገቡ የሚገኙ ሲሆን በዛሬው ዕለት 9:00 አካባቢ ዳውንት ላይ የአፋሕድ እና የአፋሕድ ወሎ ጠቅላይ ግዛት ከፍተኛ አመራሩ ኮሎኔል ፈንታው ሙሀቤ ወደ ፀረ አማራው ብልፅግና ገብቷል። ብልፅግና ኮሎኔሉን ለመውሰድ ሄሊኮፕተር በመላክ ከዳውንት ኩርባ ላይ እንዳሳረፈ ማረጋገጥ ችለናል። የሚገርመው ደግሞ ብልፅግና ቤታቸው ተገቡ በኋላ #ከኃላፊነት_አግደናል እኛን አይወክሉም እየተባለ የሚሰጠው የአፋሕድ መግለጫ አመት ያስቃል😂😂 #ማስታወሻ:- አፋሕድ የአማራን ህዝብ የመከራ ዘመን ለማራዘም በገንዘብና በተለያለ ጥቅማጥቅሞች የተታለሉና በአገዛዙ ተመልምለው የአማራን ህዝብ ትግል እንዲያከስሙ ተልኮ የተሰጣቸው ስብስቦች ድርጅት ነውና #በስህተት ፣ባለማወቅ እዚህ ድርጅት ላይ የገባችሁ መሪና ተዋጊዎች ህዝባችሁንና አፋብኃ ድርጅታችሁን ይቅርታ ጠይቃችሁ በመቀላቀል ራሳችሁንም አማራንም ታድኑ ዘንድ እናሳስባለን‼️ የአማራ ትግል ጥርት እያለ ነው፣ ተላላኪዎች እጅ የመስጠት ፍጥነታችሁ በመጨመር ለአማራ ውለታ ዋሉለት!! 04/ዐ5/2018 ዓ.ም

አፋብኃ - ብቸኛው የአማራ ፋኖ ድርጅት! ✊ ዝም ብለህ ድርጅትህን አፋብኃን አጠናክር ! መንጓተቱ ይብቃ !!
አፋብኃ - ብቸኛው የአማራ ፋኖ ድርጅት! ✊ ዝም ብለህ ድርጅትህን አፋብኃን አጠናክር ! መንጓተቱ ይብቃ !!