ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
Kanalga Telegram’da o‘tish
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Ko'proq ko'rsatish4 129
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
+4197 kun
+1 13230 kun
Postlar arxiv
የሚፈራና የሚንቀጠቀጥ ቢኖር ተመልሶ ይሂድ፥ መሳ7:3
በዓለም ታሪክ ውስጥ እጅግ የሚሰቀጥጠው ክህደት በጠላት የሚፈጸመው ሳይሆን፣ አብሮ በበላ፣ አብሮ በጠጣና "እስከ መቃብር አብሬህ ነኝ" ባለ የቅርብ ወዳጅ የሚፈጸመው ነው። ሐዋርያው ጴጥሮስ በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ የጌታውን ጠላቶች በሰይፍ ሊከላከል የቆረጠ ቢመስልም፣ በመጨረሻው ስዓት ግን "አላውቀውም!" በማለት ሦስት ጊዜ ክዶታል።
ጴጥሮስ፤ የከዳው ጠላት ስለበረታ ሳይሆን፣ በውስጡ ያለው "የመሞት ፍርሃት" ስላሸነፈው ነው። ዛሬም በሕልውና ትግላችን ውስጥ ያሉ አንዳንድ ሰዎች፣ የጥቅም ፍርፋሪ ሲያሳያቸው፣ እንደ ጴጥሮስ "ትግሉን አላውቀውም! ሕዝቤን አላውቀውም!" እያሉ ወደ ጠላት ካምፕ ይኮበልላሉ።
ጴጥሮስ፤ የከዳው ጌታው ሊሰቀል ጥቂት ሰዓታት ሲቀሩት ነበር። ዛሬም ከዳተኞች የሚከዱት የነፃነት ፀሐይ ልትወጣ፣ የአምባገነኑ ሥርዓት ምሰሶ ሊናጋ ጥቂት ሲቀረው ነው። በድል ዋዜማ ላይ የሚደረግ ክህደት ደግሞ የታሪክ ጠባሳው አይፋቅም። በመጽሐፍ ቅዱስ ዶሮ መጮኽ ጴጥሮስን ከእንቅልፉ የቀሰቀሰች፣ የክህደቱን ጥልቀት ያሳየች ድምፅ ነበረች። ለዛሬዎቹ ከዳተኞችም "የዶሮዋ ጩኸት" የሕዝብ እንባና የታሪክ ፍርድ ነው።
አምባገነኑ አገዛዝ እጅ የሰጡትን ከዳተኞች "ወንድሞቻችን ተመለሱ" እያለ በቲቪ ቢያሳያቸውም፣ በውስጣቸው ግን የሕሊና ዶሮ ትጮህባቸዋለች። ጴጥሮስ ከከዳ በኋላ "ምርር ብሎ አለቀሰ" (ማቴ 26፡75)፤ ንስሐም ገባ። የዛሬዎቹ ከዳተኞች ግን ክህደታቸውን "ለሰላም ነው፣ ለሀገር ነው" በሚል የሐሰት ስብከት ለማስረዳት ይሞክራሉ። ጴጥሮስ ስህተቱን አምኖ ተመለሰ፤ እነዚህ ግን በወንድሞቻቸው ደም ላይ ለሚቆም የባርነት ሹመት ሰገዱ።
ዶሮ ሳይጮህ (የድል አዋጅ ሳይነገር) ሕዝባችሁን የካዳችሁ ሆዳሞች ሆይ! የያዛችሁት የጥቅም ዲናር እጃችሁን ያቃጥለዋል። አምባገነኑ ሥርዓት ሲወድቅ፣ እናንተ መሸሸጊያ አታገኙም። ታሪክ እናንተን የሚዘክራችሁ በጀግንነት ሳይሆን፣ "ብርሃን ሲቃረብ ጨለማን በመረጡ" የሽንፈት ተምሳሌቶችነታችሁ ነው። በታሪክ ውስጥ የድል ዋዜማ ሁልጊዜም "የጀግኖች መፈተኛ" እና "የከዳተኞች መውጫ" ናት።
ጌዲዮን፤ ምድያማውያንን ለመውጋት 32,000 ሰራዊት አሰባስቦ ነበር። ነገር ግን ድል ሊደረግ ጥቂት ሲቀረው እግዚአብሔር አንድ መመሪያ ሰጠው "የሚፈራና የሚንቀጠቀጥ ቢኖር ተመልሶ ይሂድ" (መሳፍንት 7)፤ ድል ሊገኝ ጥቂት እርምጃ ሲቀረው 22,000 ወታደሮች ትግሉን ጥለው ወደ ቤታቸው ሄዱ። የቀሩትም ቢሆኑ ተፈትነው መጨረሻ ላይ ለድል የበቁት 300 ቆራጦች ብቻ ነበሩ።
የትግል ብዛት ለድል ዋስትና አይደለም። በድል ደጃፍ ላይ ፈሪዎችና ተጠራጣሪዎችሆድ መክዳታቸው ትግሉን አያዳክመውም፤ ይልቁንም ትግሉን ከቆሻሻ ያጠራዋል። ድል የሚመጣው በሺዎች በሚቆጠሩ " አደሮች" ሳይሆን፣ በማይበገሩ ጥቂት "ልበ ሙሉዎች" ነው።
ኢትዮጵያ በፋሽስት ጣሊያን ተወራ በነበረበት ወቅት፣ አርበኛው በላይ ዘለቀ በዓባይ በረሃዎች ላይ ጽኑ ትግል ያደርግ ነበር። ጣሊያን ድል መመታቷ ሲቃረብና አርበኞቹ አዲስ አበባን ለመያዝ ሲዘጋጁ፣ ጣሊያን አንድ ዘዴ ተጠቀመች። በበላይ ዘለቀ ዙሪያ የነበሩ አንዳንድ "ጽናት አልባ" አርበኞችን በገንዘብና "ሹመት እንሰጣችኋለን" በሚል ተስፋ መለመላች።
ድሉ ዋዜማ ላይ እያለ አንዳንዶቹ "ትግሉ ሰለቸን፣ ጣሊያን አታሸነፍም፣ ይልቅ ይቺን ሹመት እንቀበል" ብለው እጃቸውን ሰጡ። በላይ ዘለቀ ግን እስከ መጨረሻው ጸና። ዛሬ ታሪክ የበላይ ዘለቀን ስም በወርቅ ቀለም ሲጽፈው፣ በዋዜማው የከዱት ግን ስማቸው ከባንዳነት ተርታ ተፈርጆ ቀርቷል። ክህደት ለጊዜው "እረፍት" ቢመስልም፣ ለዘላለም ግን "እሳት" ነው።
በአሜሪካ የነፃነት ጦርነት ወቅት ቤኔዲክት አርኖልድ እጅግ ጀግና ከሚባሉ ጄነራሎች አንዱ ነበር። ነገር ግን አሜሪካ ድል ልታደርግ ጥቂት ሲቀራት፣ በነበረው የሥልጣን ጥመኝነትና በገንዘብ ፍላጎት ምክንያት አገሩን ከድቶ ለብሪታንያ ወገነ። ብሪታንያ ጦርነቱን ተሸነፈች። አርኖልድም ወደ ብሪታንያ ሸሸ። ነገር ግን የከዳቸው ወገኖቹ ብቻ ሳይሆኑ፣ የሄደባቸው ብሪታንያውያንእንኳን "ከዳተኛን ማን ያምነዋል?" ብለው ናቁት። በብቸኝነትና በውርደት ሞተ። አምባገነን አገዛዞች እጃቸውን ለሚሰጡ ከዳተኞች "እንኳን መጣችሁ" ቢሏቸውም፣ በልባቸው ግን ይንቋቸዋል። የገዛ ወንድሙን የከዳ ሰው ለማንም ታማኝ ሊሆን እንደማይችል ጠላትም ያውቀዋል።
ዶሮ ሳይጮኽ ጴጥሮስ ክዷል፤ ግን ንጋቱ አልቀረም። ጌዲዮን 22,000 ሰራዊት ዮሐንስና ግን ድሉ አልቀረም። በላይ ዘለቀ በባንዳዎች ተከቧል፤ ግን ነፃነቱ አልቀረም። ጴጥሮስ ቢክድም የክርስትና ጉዞ አልቆመም። ዮሐንስና ሌሎች ጽኑዓን ግን እስከ ቀራንዮ ድረስ ተከተሉት።
ዛሬም፤ በመካከላችን ያሉት "ጴጥሮሶች" ቢከዱ፣ ትግሉ ከከባድ ሸክም እየቀለለ መሆኑን እወቁ። እኛ የምንሸከመው የነፃነት አክሊል ለከዳተኞች አይገባቸውም ነበርና ፈጣሪ ለይቷቸዋል። ጽናት አልባዎች ቢከዱ፣ ትግሉ አይቆምም። እንዲያውም ትግሉ ከ"ይሁዳዎች" እና ከ"ፈሪ ጴጥሮሶች" ጸድቶ ወደ መጨረሻው ድል ይሸጋገራል። እኛ፤ እስከ ቀራንዮ (እስከ መስዋዕትነት) የቆምን የነፃነት ሐዋርያት ነን።
ትዕግሥት ፣ፅናት፣ፍቅር ፣እምነት ፣እውነት።
ፅና!
ፋኖ እስቲበል ዓለሙ
የአፋብኃ ቴወድሮስ እዝ ምክትል የህዝብ ግንኙነት መምሪያ ሀላፊ
#የአማራ_ትግል_እየጠራ_ነው‼️
#የዳውንቱ_ስምምነት_ተግባራዊነቱ_ቀጥሏል‼️
ከአመት በፊት አፋሕድ ዳውንት ላይ ከአፍሪካ ህብረት ፣ ከኢጋድ ፣ እና ከብልፅግና ሰዎች ውይይት ማድረጉን የአፋሕድ ሊቀመበር እስክንድር ነጋ መግለጫ መስጠቱ ይታወሳል። አፋሕድ ይህንን ትግል ለአመታት ሲረብሽ ከቆዬ በኋላ ተራ በተራ ወደ ላኪያቸው አገዛዝ እየገቡ የሚገኙ ሲሆን በዛሬው ዕለት 9:00 አካባቢ ዳውንት ላይ የአፋሕድ እና የአፋሕድ ወሎ ጠቅላይ ግዛት ከፍተኛ አመራሩ ኮሎኔል ፈንታው ሙሀቤ ወደ ፀረ አማራው ብልፅግና ገብቷል።
ብልፅግና ኮሎኔሉን ለመውሰድ ሄሊኮፕተር በመላክ ከዳውንት ኩርባ ላይ እንዳሳረፈ ማረጋገጥ ችለናል። የሚገርመው ደግሞ ብልፅግና ቤታቸው ተገቡ በኋላ #ከኃላፊነት_አግደናል እኛን አይወክሉም እየተባለ የሚሰጠው የአፋሕድ መግለጫ አመት ያስቃል😂😂
#ማስታወሻ:- አፋሕድ የአማራን ህዝብ የመከራ ዘመን ለማራዘም በገንዘብና በተለያለ ጥቅማጥቅሞች የተታለሉና በአገዛዙ ተመልምለው የአማራን ህዝብ ትግል እንዲያከስሙ ተልኮ የተሰጣቸው ስብስቦች ድርጅት ነውና #በስህተት ፣ባለማወቅ እዚህ ድርጅት ላይ የገባችሁ መሪና ተዋጊዎች ህዝባችሁንና አፋብኃ ድርጅታችሁን ይቅርታ ጠይቃችሁ በመቀላቀል ራሳችሁንም አማራንም ታድኑ ዘንድ እናሳስባለን‼️
የአማራ ትግል ጥርት እያለ ነው፣ ተላላኪዎች እጅ የመስጠት ፍጥነታችሁ በመጨመር ለአማራ ውለታ ዋሉለት!!
04/ዐ5/2018 ዓ.ም
አፋብኃ - ብቸኛው የአማራ ፋኖ ድርጅት! ✊
ዝም ብለህ ድርጅትህን አፋብኃን አጠናክር ! መንጓተቱ ይብቃ !!
አለን ለማለት ያክል ነው፤ አሸናፊዎች እንደምንሆንም ጥርጥር የለውም:: የአማራ ልጅ ፋኖ: ተኩሶ የማይስት: 1 ጥይት ለ 1 ጠላት፤ ዞር በል አንተ: ዋ!
የማድረግ አቅም ያለው እና ዲስፕሊንድ የሆነ ሰራዊት ለመፍጠር የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል:: በምዕራብ ወሎ ግንባር ያለው ሰራዊት እየሰለጠነ እና የአመራር ሪፎርም እያደረገ ሰንብቷል:: የፋይናንስ እና ሎጅስቲክስ አሰባሰብ ሂደቱም ተቀይሯል:: የእስካሁኑ ደረሰኝ አልባ አሰራር ቀርቶ በኮር ደረጃ በህጋዊ ደረሰኝ አማካኝነት ገቢ የሚሰበሰብበት ምዕራፍ ተከፍቷል:: የምኒልክ ዕዝ ፋይናንስ መምሪያ ባወጣው መመሪያ መሰረት የፋይናንስ አሰባሰብ ሂደት ላይ ማሻሻያ መደረጉ ለትግሉ ስኬት ወሳኝ ነው:: ሰራዊታችን ወታደራዊ እና ፓለቲካዊ አቅሙ እንድጎለብት የሚያስችል የአቅም ግንባታ ስልጠና መውሰዱም ሌላ blessing ነው::
የምናሸንፍበትን ቅዋ (ሀይል) መፍጠር ችለናል:: የነቃ ማህበረሰብ እና የበቃ ሰራዊት ከያዝን እናሸንፋለን::
እንደ ምኒልክ ዕዝ ብቻ ሳይሆን እንደ አፋብኃ ወጥ የሆነ አሰራር በመዘርጋት አንድ ሆነን ይህን የህልውና ትግል በድል ለመቋጨት መትጋት አለብን::
"ይመከራል እንጅ ጓድ አይከዳም" ሲሉ እንሰማ ነበር:: ያጠፋ እንኳን ቢኖር ይህ ጥፋት ነው፤ ሊስተካከል ይገባል ይባላል እንጅ እንደት ህዝብ እና ጓድ ተከድቶ ወደ ጠላት ይኮበለላል? ኮሎኔል ፈንታው ሙሀባ የአማራ ህዝብን እና ባለፉት 33 ወራት በጠላት እጅ እየተገደሉ ንፁሓንን ከድቶ ወደ ጠላት መግባቱን ተከትሎ እሱን ለመውሰድ ዳውንት ወረዳ ኩርባ ከተማ ገበያው አጠገብ ሄሊኮፕተር አርፏል::
በጣም ያሳፍራል:: እኔ ለእሱ አዘንኩኝ:: አይ ሰው!!
የተማረኩ የደቡብ ወሎ ዞን ሰላም አስከባሪዎች እና ፓራ ኮማንዶዎች ወደ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር የተሀድሶ ማዕከል ገቢ ተደረጉ‼️
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ወግድ እና ከላላ ወረዳ ውስጥ ባለፉት ቀናት በሰራው ኦፕሬሽን በርካታ ጠላት የተደመሰሰ ሲሆን መንገድ መሪዎቹ የሆኑት የደቡብ ወሎ ዞን ሰላም አስከባሪዎች እና ፓራ ኮማንዶዎች ተማርከዋል:: ፋኖን እናጠፋለን ብለው ከጠላት አብረው ሌት ተቀን ንፁሀን ወገኖቻችንን ሲገድሉ እና ሲያስገድሉ ከርመው በስተመጨረሻ እጃችን ላይ ወድቀዋል:: እነዚህ የደቡብ ወሎ ዞን ሰላም አስከባሪዎች እና ፓራ ኮማንዶዎች አሁን ላይ የተሀድሶ ስልጠና እየተሰጣቸው ሲሆን በስልጠናው መሀል አስተያየታቸውን የለገሱት በጥቅሉ የተናገሩት እስካሁን በሄዱበት መንገድ እና በፈፀሙት ድርጊት እጅጉን እንደተፀፀቱ ነው::
ምርኮኞቹ በንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር የተሀድሶ ማዕከል የሚሰጣቸውን ስልጠና እንዳጠናቀቁ ወደ ማህበረሰቡ ይመለሳሉ ተብሏል:: ፋሽስቱ አብይ አህመድ አማራን በአማራ ለማስመታት የሚያደርገው ጥረት አካል የሆነውን ፕሮጀክት ለማሳካት ደፋ ቀና የምትሉ የፀጥታ ኃይል አባላት በአስቸኳይ ከህዝባችሁ ጎን እንድትቆሙ ሲል ኮሩ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን ይህን ጥሪ ባለመቀበል ከጠላት ጎን የተሰለፉት ላይ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
©አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥር 4 ቀን 2018 ዓ.ም
04/ዐ5/2018 ዓ.ም
ሆዳቸው ሁለት ሔክታር መሬት የሚሸፍን ዘረጦ ዘረጦ ሰዎች ቁና ቁና እየተነፈሱ በአንቡላንሷ የተጋደመውን አጋሰስ እየገተቱ ድንገተኛ ክፍል ሲያስገቡት ነገሩ አልጣመኝም እና ተከትያቸው ብገባ ያ ! የህዝቡን ደም ለጌታው ለአብይ አህመድ ግብር መስዋት የሚያቀርበው ዋለ አባተ የምስራቅ ጎጃም ም/ አስተዳዳሪ ሰሞኑን በስናን ወረዳና በደብረ ማርቆስ ከተማ በተደረገው ገድል ከፍተኛ የጤና መታወክ ገጥሞት አልጋ ቁራኛ ከሆነ ቢሰነባብትም ከዘጠኝ ቀን በኋላ ግፊቱ የበለጠ በመጨመሩ ለህክምና ሆስፒታል እየገባ ኑሯል።
እኔ የእሱ መታመም አልደነቀኝም ይልቁንስ ዋለ አባተን ለማስታመም የመጡት አሽቃባጭ በንፁሀን ደም ልባቸው የደነደነው ሁለቱ ካድሬዎች ሁኔታ አሳፍሮኝ እንጂ።
አቶ ሙሉቀን ቢያድግልኝ በጎዛምን ወረዳ ገደማላ ቀበሌ ተወላጅ ሲሆን የምስራቅ ጎጃም ብልፅግና ፅ/ቤት አደረጃጀት ኃላፊ ነው በስዓቱ የዋለን ቂጥ በመደገፍ የደም ግፊቱን ለመቆጣጠር የማያደርገው ነገር አነበረም ። እኔን የገረመኝ ቂጥና ደም ግፊት ምን አገናኝቷቸው ሙሉቀን የዋለን ቂጥ ደጋፊ ሆነ የሚለው ነው።
ሌላኛው ደግሞ አቶ የሽዋስ አንዷለም ሲሆን የዋለን እግር በመደገፍ የሁለት እግር አውራ ጣቶች እያሳሳበ ሊያድነው ይጣደፋል። ይሔኛው የጤና መምሪያ ተብየው አቶ የሸዋስ ግፊትና አውራ ጣት ያላቸውን ግንኙነት ባይነግረንም ለአቶ ዋለ የተሻለ የህክምና ድጋፍ እንዲሰጥ ከብልፅግና የቦርድ አባላት የተሻለ ሁኖ ተገኝቶ የተመደበ ሰልኮፍ እግር ያዥ ሁኖ ነው ያመሸው።
እኔን እጅግ በጣም የደነቀኝ እናቶችን በተለየ ሁኔታ ያገለግላል ተብሎ በውድ የተገዛውን የአልትራ ሳውንድ ማሽን የዘረፉ እነዚህ ካድሬዎች ያውም የምስራቅ ጎጃም ጤና መምሪያ ኃላፊ ተብየው ሆስፒታሉ በማሽኑ መጥፋት በአንድ እግሩ ቁሞ እየተተራመሰ እሱ የጌታውን ቂጥ እንደደገፈ ስዓታት መንጎዳቸው ነው።
እናተ አጣሩ ቢሮ ቁጥር 4 ያለው እጅግ ዘመናዊ አልትራ ሳውንድ አልተዘረፈም ወይ? ትናትስ ዋለና ቂጥ ደጋፊዎቹ ሆስፒታል አልመጡም ወይ? በደብረ ማርቆስ ሆስፒታል ከ25,000,000 ብር በላይ ገንዘብ አልተዘረፈም ወይ? እስኪ ይሔን እናተ ጠይቁ እኔስ መንቆረር ተመችታኛለች የማልገባት ቦታ የለም። ይሔን ማሽን ከዘራፊዎች ጉሮሮ ነጥቄ ለህዝባችን ሳናስረክብ ሌቦችን ሳናፀዳ ከመንቆረሯ ማርቆስ ከንጉስ ተክለሃይማኖት አደባባይ ንቅንቅ አልልም።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ
አርበኛ ባየ ደስታ
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
መንቆረር ነኝ ! ( ከሶስት ዋና ዋና ካድሬዎች ጋር ሆስፒታል ተገናኘን) አጣሩ!
ጥር 4/ 2018 ዓ.ም
==================================
እግዚኦ ወላዲተ አምላክ ! እያልኩ ስደነቅ በዙሪያየ የነበረው ሰው ሁሉ ፊቱን አዙሮ አይኑን እያጉረጠረጠ ሲመለከተኝ ትንሽ ሀፍረት ይሰማኝ እንጂ በደብረ ማርቆስ ሆስፒታል የማየው ነገር አይኔ እስኪ ቀላ አፍጥጨ እንደቀረሁ ነው።
በቀደም ለታ ማርቆስን እያሰስኩ የሰበሰብኩት ጉድ አንጀቴን ቢያላውሰኝ ለክፉም ለደጉም የጤና መታዎኬን ልፈተሽ ብየ ደብረ ማርቆስ ሆስፒታል ብሔድ ህሙማኑ፣ ዶክተሮች ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች ቢሮ ቁጥር 4 ላይ ቁመው እየተንጫጩ ጠበቁኝ ።
ቢሮ ቁጥር 4 ቦግ ብሎ ተከፍቶ ሰራቶኞች በየተራ እየገቡ እየወጡ ይደነቃሉ ፣ እርስ በዕርስ መተማመን አቅቷቸው በጥርጣሬ ሲተያዩ ከመሀላቸው ጥልቅ ብየ የተፈጠረውን ማጣራት ስጀምር ወዲያውኑ በቢሮ ቁጥር 4 የነበረው --------
1ኛ. የማህፀን ፅንስና ሕመም መመርመሪያ
2ኛ. የሆድ እቃ መመርመሪያ ( የአንጀት መታጠፍ፣ ትርፍ አንጀት፣ የኩላሊት ኢንፌክሽን ፣ የልብ ምት እንቅስቃሴን) የሚመረምር እጀግ ዘመናዊ አልትራ ሳውንድ ማሽን ከሆስፒታሉ መሰረቁን አረጋገጥኩ።
እግዚኦ ወላዲተ አምላክ!! ማርቆስ የሚፈፀመው ወንጀልስ ለከት የለውም ከአልትራ ሳውንዱ ማሽን አጠገብ የተተከለው የ security camera በጥንቃቄ ከተወገደ በኋላ የቢሮ ቁጥር 4 በር ተገንጥሎ ነው ማሽኑ የተዘረፈው። ይህ ማሽን እጅግ በተሻሻለ ቴክኖሎጂ የበለፀገ ሲሆን ዋጋው 3,000,000 ሶስት ሚሊዮን ይደፍናል በቀላሉ መንቀሳቀስ የሚችል ሲሆን በፀና ለታመሙ ህሙማን በየ ክፍሉ እየተዘዋወረ አገልግሎት የሚሰጥ ምርጥ ማሽን ነው። (ማሽኑም ከስር በፎቶ ተያይዟል )
በዚህ ዝርፊያ የተሳተፉትን
1ኛ .ተሾመ ዋለ የደብረ ማርቆስ ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባና የሆስፒታሉ የቦርድ ሰብሳቢ
2ኛ. አቶ አንዷለም ገረመው የሆስፒታሉን ስራ አስኪያጅ አንገታቸው አንቄ እያፋጠጥኳቸው እያለ ከርቀት የሚሰማኝ የአምቡላንስ ልቅሶ እየቀረበኝ የሆስፒታሉን በር አልፎ ግቢ ውስጥ ሲሰማ ፣ዲሽቃ የጠመዱ ሶስት ፓትሮሎች ተከታትለው ሆስፒታሉ ውስጥ ተንደርድረው ገቡ።
ሆዳቸው ሁለት ሔክታር መሬት የሚሸፍን ዘረጦ ዘረጦ ሰዎች ቁና ቁና እየተነፈሱ በአንቡላንሷ የተጋደመውን አጋሰስ እየገተቱ ድንገተኛ ክፍል ሲያስገቡት ነገሩ አልጣመኝም እና ተከትያቸው ብገባ ያ ! የህዝቡን ደም ለጌታው ለአብይ አህመድ ግብር መስዋት የሚያቀርበው ዋለ አባተ የምስራቅ ጎጃም ም/ አስተዳዳሪ ሰሞኑን በስናን ወረዳና በደብረ ማርቆስ ከተማ በተደረገው ገድል ከፍተኛ የጤና መታወክ ገጥሞት አልጋ ቁራኛ ከሆነ ቢሰነባብትም ከዘጠኝ ቀን በኋላ ግፊቱ የበለጠ በመጨመሩ ለህክምና ሆስፒታል እየገባ ኑሯል።
እኔ የእሱ መታመም አልደነቀኝም ይልቁንስ ዋለ አባተን ለማስታመም የመጡት አሽቃባጭ በንፁሀን ደም ልባቸው የደነደነው ሁለቱ ካድሬዎች ሁኔታ አሳፍሮኝ እንጂ።
አቶ ሙሉቀን ቢያድግልኝ በጎዛምን ወረዳ ገደማላ ቀበሌ ተወላጅ ሲሆን የምስራቅ ጎጃም ብልፅግና ፅ/ቤት አደረጃጀት ኃላፊ ነው በስዓቱ የዋለን ቂጥ በመደገፍ የደም ግፊቱን ለመቆጣጠር የማያደርገው ነገር አነበረም ። እኔን የገረመኝ ቂጥና ደም ግፊት ምን አገናኝቷቸው ሙሉቀን የዋለን ቂጥ ደጋፊ ሆነ የሚለው ነው።
ሌላኛው ደግሞ አቶ የሽዋስ አንዷለም ሲሆን የዋለን እግር በመደገፍ የሁለት እግር አውራ ጣቶች እያሳሳበ ሊያድነው ይጣደፋል። ይሔኛው የጤና መምሪያ ተብየው አቶ የሸዋስ ግፊትና አውራ ጣት ያላቸውን ግንኙነት ባይነግረንም ለአቶ ዋለ የተሻለ የህክምና ድጋፍ እንዲሰጥ ከብልፅግና የቦርድ አባላት የተሻለ ሁኖ ተገኝቶ የተመደበ ሰልኮፍ እግር ያዥ ሁኖ ነው ያመሸው።
እኔን እጅግ በጣም የደነቀኝ እናቶችን በተለየ ሁኔታ ያገለግላል ተብሎ በውድ የተገዛውን የአልትራ ሳውንድ ማሽን የዘረፉ እነዚህ ካድሬዎች ያውም የምስራቅ ጎጃም ጤና መምሪያ ኃላፊ ተብየው ሆስፒታሉ በማሽኑ መጥፋት በአንድ እግሩ ቁሞ እየተተራመሰ እሱ የጌታውን ቂጥ እንደደገፈ ስዓታት መንጎዳቸው ነው።
እናተ አጣሩ ቢሮ ቁጥር 4 ያለው እጅግ ዘመናዊ አልትራ ሳውንድ አልተዘረፈም ወይ? ትናትስ ዋለና ቂጥ ደጋፊዎቹ ሆስፒታል አልመጡም ወይ? በደብረ ማርቆስ ሆስፒታል ከ25,000,000 ብር በላይ ገንዘብ አልተዘረፈም ወይ? እስኪ ይሔን እናተ ጠይቁ እኔስ መንቆረር ተመችታኛለች የማልገባት ቦታ የለም። ይሔን ማሽን ከዘራፊዎች ጉሮሮ ነጥቄ ለህዝባችን ሳናስረክብ ሌቦችን ሳናፀዳ ከመንቆረሯ ማርቆስ ከንጉስ ተክለሃይማኖት አደባባይ ንቅንቅ አልልም።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነትመንቆረር ነኝ ! ( ከሶስት ዋና ዋና ካድሬዎች ጋር ሆስፒታል ተገናኘን) አጣሩ!
ጥር 4/ 2018 ዓ.ም
==================================
እግዚኦ ወላዲተ አምላክ ! እያልኩ ስደነቅ በዙሪያየ የነበረው ሰው ሁሉ ፊቱን አዙሮ አይኑን እያጉረጠረጠ ሲመለከተኝ ትንሽ ሀፍረት ይሰማኝ እንጂ በደብረ ማርቆስ ሆስፒታል የማየው ነገር አይኔ እስኪ ቀላ አፍጥጨ እንደቀረሁ ነው።
በቀደም ለታ ማርቆስን እያሰስኩ የሰበሰብኩት ጉድ አንጀቴን ቢያላውሰኝ ለክፉም ለደጉም የጤና መታዎኬን ልፈተሽ ብየ ደብረ ማርቆስ ሆስፒታል ብሔድ ህሙማኑ፣ ዶክተሮች ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች ቢሮ ቁጥር 4 ላይ ቁመው እየተንጫጩ ጠበቁኝ ።
ቢሮ ቁጥር 4 ቦግ ብሎ ተከፍቶ ሰራቶኞች በየተራ እየገቡ እየወጡ ይደነቃሉ ፣ እርስ በዕርስ መተማመን አቅቷቸው በጥርጣሬ ሲተያዩ ከመሀላቸው ጥልቅ ብየ የተፈጠረውን ማጣራት ስጀምር ወዲያውኑ በቢሮ ቁጥር 4 የነበረው --------
1ኛ. የማህፀን ፅንስና ሕመም መመርመሪያ
2ኛ. የሆድ እቃ መመርመሪያ ( የአንጀት መታጠፍ፣ ትርፍ አንጀት፣ የኩላሊት ኢንፌክሽን ፣ የልብ ምት እንቅስቃሴን) የሚመረምር እጀግ ዘመናዊ አልትራ ሳውንድ ማሽን ከሆስፒታሉ መሰረቁን አረጋገጥኩ።
እግዚኦ ወላዲተ አምላክ!! ማርቆስ የሚፈፀመው ወንጀልስ ለከት የለውም ከአልትራ ሳውንዱ ማሽን አጠገብ የተተከለው የ security camera በጥንቃቄ ከተወገደ በኋላ የቢሮ ቁጥር 4 በር ተገንጥሎ ነው ማሽኑ የተዘረፈው። ይህ ማሽን እጅግ በተሻሻለ ቴክኖሎጂ የበለፀገ ሲሆን ዋጋው 3,000,000 ሶስት ሚሊዮን ይደፍናል በቀላሉ መንቀሳቀስ የሚችል ሲሆን በፀና ለታመሙ ህሙማን በየ ክፍሉ እየተዘዋወረ አገልግሎት የሚሰጥ ምርጥ ማሽን ነው። (ማሽኑም ከስር በፎቶ ተያይዟል )
በዚህ ዝርፊያ የተሳተፉትን
1ኛ .ተሾመ ዋለ የደብረ ማርቆስ ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባና የሆስፒታሉ የቦርድ ሰብሳቢ
2ኛ. አቶ አንዷለም ገረመው የሆስፒታሉን ስራ አስኪያጅ አንገታቸው አንቄ እያፋጠጥኳቸው እያለ ከርቀት የሚሰማኝ የአምቡላንስ ልቅሶ እየቀረበኝ የሆስፒታሉን በር አልፎ ግቢ ውስጥ ሲሰማ ፣ዲሽቃ የጠመዱ ሶስት ፓትሮሎች ተከታትለው ሆስፒታሉ ውስጥ ተንደርድረው ገቡ።
ዋግሹም ብርጌድ በሆድ አድር ሚኒሻ እና ፖሊስ ላይ የማያዳግም እርምጃ በመዉሰድ ድል ተጎናፀፈ!!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ላስታ አሳምነዉ ኮር ዋግሹም ብርጌድ አማራነታቸዉን በምስር ወጥ በሸጡ ፖሊስ እና ሚኒሻ ላይ የማያዳግም እርምጃ ወሰደ።
መነሻዉን ዋግህምራ ዞን ድሃና ወረዳ አምደ ወርቅ አድርጎ ዋግሹም ብርጌድን አፍናለሁ ብሎ ቢመጣም ጀግኖቹ የሃይሉ ከበደ ልጆች አባም አቦ ተብሎ ከሚጠራዉ ቦታ ላይ ሲቀጠቅጡት ዉለዋል።
ዉጊያዉም ዛሬ ማለትም ጥር 3/2018 ዓ.ም ከ ጧቱ 2:00 - 8:30 የፈጀ ሲሆን በዚህም 20 ሚኒሻ እና ፖሊስ እስከወዲያኛዉ ሲሸኝ 15 የሚሆኑ ባንዳዎችን ምርኮ ማድረግ የተቻለ ሲሆን 37 የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎች ተማርከዋል።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ደረበ መኮንን!!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
"በደብረ ማርቆስ ከተማ 670 መምህራን ታፈኑ"
ጥር 3/ 2018 ዓ.ም
===================================
206ኛ ኮር በመማማር ማስተማር ሒደቱ ከመምሕራን ጋር ለመዋያየት ባደረገው ጥሪ መሰረት ከደብረ ማርቆስ ከተማ ተነስተው ወደ ስብሰባ ሲሔዱ የነበሩ 670 መምህራን እና ዕርሰ መምህራን በአረመኔው ሰራዊት ታፍነዋል።
ከ25 በላይ መኪና በማዘጋጀት ከ206ኛ ኮር አመራሮች ጋር ለመወያየት ያቀኑት 670 መምህራን ከህዳር ወር ጀምሮ የሁለት ወር ደሞዝ በአምባገነኑ ስርዓት ተነጥቀዋል። ትግሉን በማጠልሸት ተጠምዶ የነበረው የምስራቅ ጎጃም ካድሬ ዛሬ ከጠዋት ጀምሮ ኬላ ዘርግቶ መምህራንን በማጎር የተጠመደ ሲሆን ከ74 በላይ መምህራን በከፍተኛ ድብደባ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተረጋግጧል።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ጭና የጠላት መቀበሪያ ሁና ቀጥላለች!!
ዛሬ ጥር 03/2018 ዓ.ም በዳባት ወረዳ ጭና ቀበሌ የአረመኔው ዓብይ አህመድ ራሱን ጥምር ጦር ሃይል ብሎ የሚጠራው ሰራዊት የንፁሃን ወገኖቻችን ለመዝረፍ በተሰማራበት አፋብኃ በላይ ዕዝ የራስ አሞራው 3ኛ ኮር የደጃች አያሌው ብሩ ክ/ጦር የተሳካ ጥቃት ሰንዝሮበታል።
ከ13 በላይ የጥምር ወራሪው ሀይል ዓባላት እሰከ ወዲያኛው ሲሸኙ ቁጥሩ ያልታወቀ ቁስለኛ ሁኗል።
ከፊሎቹ በዳባት መድሃኒያለም ሲቀበሩ ቀሪዎቹ ወደ ደባርቅ ከተማ ተወስደዋል።
አፋብኃ በላይ ዕዝ
ጥር 03/2018 ዓ.ም
ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ
በአፋብኃ በላይ ዕዝ ቴዎድሮስ ኮር
ጥር 01/2018 ዓ/ም በበለሳ ግንባር ጣይመን ከተማ ላይ ባደረገው ተጋድሎ...የማረካቸው የአገዛዙ ወታደሮች!
የቴሌግራም ገፃችን👉
ምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ መምሪያ ለወራቶች የሰለጠኑ ልዩ ኮማንዶ ፋኖዎችን አስመረቀ::
ምኒልክ ዕዝ የልዩ ዘመቻ መምሪያ አሃድ ከሆኑት መካከል ለወራት የሰለጠኑ ልዩ ኮማንዶ ፋኖዎች የዕዝ የኮርና የክፍለጦሩ አመራሮች በተገኙበትና መልክት ባስተላለፉበት ሁኔታ ተመርቀዋል::
ከፍተኛ የዕዙ አመራሮችም የተጀመረውን የፖለቲካ ትጥቅ ትግል ከግብ ለማድረስና የአማራን ህዝብ ህልውና ለማረጋገጥ ብሎም ቀጣይነት ያለው ነፃነት ለመጎናፀፍና የሃገራችን ባለቤት ለመሆን በፅናትና ቁርጠኝነት መታገል ብቻኛ አማራጭ መሆኑን ለተመራቂዎች አስገንዝበዋል::
ልዩ ኮማንዶ ፋኖዎችን ያስመረቁት በልዩ ዘመቻ መምሪያው ስር የሆነው አሃድ ወታደራዊ አዛዥና ምክትል ወታደራዊ አዛዥ የሆኑት አርበኞችም ለተመራቂዎች መልክታቸውን አስተላልፈዋል::
የልዩ ዘመቻ ሰልጣኝ ተመራቂዎች ዛሬ የተመረቃችሁ ምኒልክ ዕዝ የልዩ ዘመቻ እንደስማችሁ ልዩ ሰልጣኝ ተመራቂዎች ለበርካታ ወራት ፀሀዩን:ብርዱን:ቁሩን በርካታ ውጣውረዱ ሳይበግራችሁ ባልተመቻቸ ሁኔታ ተቋቁማችሁ ለዚህች ልዩ ቀን በመብቃታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ እያልኩ የናንተ ስልጠና ለየት የሚያደርገው ያኔ በጣት በምንቆጠረበት ጊዜ ሳይሆን አሁን በሺዎች ብሎም በሚልዮኖች በትጥቅም ይሁን በሰው ኃይል አቅማችን እንዲሁም የማድረግ አቅማችን ትልቅ የስኬት ጫፍ ላይ ባለንበት ጊዜ መቀላቀላችሁ በተጨማሪም የዚህን አንባገነን ስርዓት ግፍ በደል እና ሰቆቃ አድራሽነት ማንም ሳይጎተጉታችሁ እያንዳንዳችሁ ቤት አንኳኩቶ የገባ በመሆኑ ያለማንም ቀስቃሽ በቃኝ አሻፈረኝ ብላችሁ ይህን ትልቅ የትጥቅ ትግል የተቀላቀላችሁ መሆኑ ከምንጊዜውም በላቀ ሁኔታ ለየት ያደርገዋል።
እንሰባሰባለን እንደራጃለን እንሰለጥናለን እንታጠቃለን ተዋግተን ይህን አንባገነን ፀረ_አማራ ስርዓት ከትክሻችን ላይ አሽቀንጥረን እንጥላለን።
የአማራ ተጋድሎ አካሄድ እና መስመር⚡:-
👉 የተጋድሏችን
መነሻ:-የአማራ ህልውና አደጋ ነው።
መዳረሻው:- አደጋውን ቀልብሶ ህዝቡን ከባርነት አውጥቶ ከሁሉም ኢትዮጵያዊያን ጋር በመተባበር የሃገሪቱን በትረ ስልጣን መልሶ መቆጣጠር ነው::
👉የተጋድሎው ርዮት አማራ ብሔርተኝነት ነው!
👉የተጋድሎው አካሄድ የትጥቅ ትግል ነው!
👉የአማራ ብሔርተኝነት የህልውናችን ዘላለማዊ ዋስትናም ነው!
👉የአማራ ብሎም ኢትዮጵያ ህልውና በሀገር መስራቹ በታላቁ አማራና በተባባሪ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ትብብር ዳግም ይፀናል።እናሸንፋለን!
በመቀጠልም የዚህ ስርዓት አካሄድና የህዝባችን ግፍና ሰቆቃ ለኛ ብቻ ሳይሆን እንደአማራ አማራን ለማጥፋት እየተሄደበት ያለው እርቀት መላው ዓለም እየተረዳው ያለ ሀቅ ነው ።እሄ ሆኖ ሳለ እስካሁኗ ሰዓት ድረስ ያልገባችሁ በተለያየ የፀጥታ ዘርፍ በመከላከያ :በፌደራል :ፖሊስ :በአድማ ብተናና ብሎም ሚኒሻ ውስጥ ሆናችሁ ስርዓቱን እያገለገላችሁ ያላችሁ ትውልደ አማራውያን በሙሉ በቃኝ በማለት የትጥቅ ትግሉን በመቀላቀል ህዝባችሁን ከባርነት ቀንበር ነፃ ታወጡት ዘንድ ታላቅ የተጋድሎ ጥሪየን አስተላልፋለሁ።
በመጨረሻም አማራ በወርቃማ ልጆቹ መስዋትነት አራሱን ነፃ ያወጣል እናሸንፋለን።መ/አለቃ ግርማው አብየ
የምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ የክፍለ ጦር አዛዥ
ምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ ተመራቂዎች እንኳን ለዚች ቀን በሰላም አደረሳችሁ
ከዚህ በመቀጠል ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ እንኳን ለዚች ቀን በሰላም አደረሳችሁ!
ተመራቂወች የአማራ ህዝብ የተቃጣበት የማንነት ተኮር ጥቃት ከመገደል ወደ መከላከል ከመከላከል ወደ ሺምቅ ከሺምቅ ወደ ማጥቃት ገብተናል።
ሰለዚህ የአማራ ህዝብ መዳኛው መሰልጠን መታጠቅ እንዲሁም በአድነት ቁመን የአማራን ህዝብ የታወጀበትን ዘር ማጥፋት በአድነት በመተባበር ወደፊት እንሄዳለን::
አንድነት ሃይል ነው በአንድነታችን የማንሻገረው ወንዝ የማንወጣው ተራራ የማንወርደው ቁልቁለት የለም:: እኛ አማራዎች ጀምረን ያልጨረስነው ትግል የለም:: ምክንያቱም የአባቶቻችን ልጆች ነን የአማራን ህዝብ ለማዳን እስካሁን መሰዋትነት እየከፈሉ የመጡ ጎዶቻችነን ትግል የማስቀጠል ግዴታችንን እደምንወጣ አልጠራጠርም:: አማራ ያሸንፋል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አርበኛ አሻግሬ ሙሉ /ቦምበኛው/
ሰልጥነን እንዋጋለን እየተዋጋን እንሰለጥናለን!
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥር 3/2018 ዓ.ም
አሁን ዉስጣችንን እያጠራን ነዉ!!
***
በድርጅታችን ውስጥ ትክክል መስለው ትክክል ያልነበሩ መስየዋች ወደ ሰለጠኑበት ካምፓስ አየተመለሱ ነው።
የውስጥ ባንዳዋች የታሪክ ጠላት የወለደው ስርአት አስፈፃሚ የነጻነት ታጋዯችን ለማፈረስ ስልጠና አሰልጥኖ በውስጥ አስርጎ በማስገባት ተልኮ የሰጣቸው ትክክል መስለው ትክክል ያልነበሩ ፀረ ፋኖዋች አላማቸው ስላልተሳካ ወደ ግንዳችው እየተመሙ ይገኛሉ።
እነዚህ እኩይ ተግባር አንግበው ሲቀሳቀሱ የነበሩ አካላት በዋናነት ሁለት ተልእኮ ነበራቸው።
እነሱም:-
1ኛዉ ዓላማቸዉ:-
➤ሰራዊቱ በሃላፊው እንዳይመራ ማድረግ
➤ሰራዊቱ ከአላማው ወጭ ወደ ገንዘብ ፍላጎት እንዲገባ ማድረግ
➤በሰራዊቱ ውስጥ ብሔርተኝነት መፍጠር
➤ማህበረሰቡን ማንገላታትና ከሰራዊቱ መነጠል
➤በውጊያ ወይም ግዳጅ ሰአት ሽብር መፍጠር
➤ትግሉ የግል እንደሆነ ፕሮፖጋንዳ መንዛት ሲሆን
2ኛው አላማቸው ደግሞ:-
➤ጉዳዮ ሲነቃባቸው የነፃነት ታጋይ የነበሩ በመምሰል እና ትግሉ አላማ እንደሌለው በማስመሰል ህዝብን ተስፋ ለማስቆረጥ ፕሮፖጋንዳ በመንዛት በምህረት መልክ ወደ አሰልጣኛቸው መመለስ ነው።
ስለሆነም እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት ተግባር አላማቸው ታወቆ እርምጃ ሲወሰድባቸውና ሲታደኑ ከየተደበቁበት ጉድጓድ በመዉጣት እየበረሩ ጠፍተዋል። ከተማ ውስጥም በመሰግሰግ ለጠላት የተለያየ የሃሰት ማስረጃ በመስጠት ማህረሰባችን ለእስራትና ለእንግልት እየዳረጉት ይገኛሉ።
ይህ ደግም ሁለተኛ በደል መሆኑን ማህበረሰቡ እንዲረዳ ስንል እያሳሰብን በሚቀጥለው ቀን ሙሉ ስማቸውን ከሰሩት ጥፋት ጋር ውሳኔውን ጨምረን ይፋ የምናደርግ መሆኑን እናሳዉቃለን።
የአ.ፋ.ብ.ሃ ሰሜን አማራ ቀጠና
በላይ ዘለቀ ዕዝ
4ኛ ደጃዝማች ኮር ሰብሳቢ
አርበኛ አንዳርግ ጫቅሉ
