ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك 👈

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

الذهاب إلى القناة على Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

إظهار المزيد
4 132
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+4577 أيام
+1 19430 أيام
أرشيف المشاركات
206ኛ ኮር ተቀናጅቶ ስራ ከጀመረበት ቀን አንስቶ በስቦ ማስከዳት 52 ክላሽ አግኝቷል። ታህሳስ 2018 ዓ.ም =================================== የጋራ አመራርነትን መርህ አድርጎ በርካታ ተግባራትን እየከወነ የሚገኘው 206ኛ ኮር መዋቅራዊ አሰራርን በማዘመን፣ ከክ/ጦሮች እና ሻለቆች ጋር አስተማማኝ የሆነ የዕዝ ሰንሰለቱን በጠበቀ መልኩ ያለው ተዋረዳዊ ግንኙነት እና በአመራሩና በሰራዊቱ መካከል ያለው መተማመን ኮሩ በሚንቀሳቀስበት ቀጠና የነበሩ ውዝፍ ችግሮችን በመፍታት በአስደናቂ ድል እየተምዘገዘገ ይገኛል። በሰራዊታችንና በአመራሩ ጥብቅ ዲስፒልን የታገዘው 206ኛ ኮር በተለየ መልኩ ጎልቶ እየታየ ሲሆን በተለያዩ ከተሞች ባደረገው ተጋድሎ የጠላትን ኃይል ቅስሙን እየሰበረ ይገኛል። ከጠላት ወይንም ከጠላት ቃል አቀባዮች ቃላት የማይዋሰው 206ኛ ኮር ለጠላት ካድሬዎች አጀንዳ በማቀበልና አጀንዳ በመቀማት የፕሮፓጋንዳ እና የሚዲያ ብልጫን አስመዝግቧል። ጓዳዊነት ወንድማማችነትና ድርጅታዊ ሰልፍን ያለማመንታት በሚከተሉ አመራሮች የተዋቀረው 206ኛ ኮር ዛሬ ከጠላት ሰራዊት 50ኛ 52ኛ እና 53ኛ ክላሽ ሲቀበል ከ7 ጀሌዎች ጋር 206ኛ ኮር በ3ቱም ክ/ጦር 59 የአረመኔው ሰራዊት አባላትን ተቀብሏል። ተመስገን ተስፋው፣ ሙረታ ሐሰን፣ ታዱ ሐምዛ የሚባሉ መሰረታዊ ወታደሮች ከ6ኛ ዕዝ 206ኛ ኮር 32ኛ ክ/ጦር 5ኛ ሬጅመንት ከደብረ ኤልያስ ከተማ በመውጣት 206ኛ ኮር 14ኛ ክ/ጦርን ተቀላቅለዋል። ድርጅታዊነት ይቅደም ! ጓዳዊነት ለትግላችን አንድነት! አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ! የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

🔥ዛሬ ጥር 5 የኢትዮጵያ ደመላሽ ጀግናው ደጅ አዝማች አባኮስትር በላይ ዘለቀ ላቀው እና ወንድሙ አርበኛ እጅጉ ዘለቀ ያረፈቡት 81ኛ ዓመት መታሰቢያ ነው‼️ ============================== ጀግናው አርበኛ ደጃዝማች በላይ ዘለቀ (አባ ኮስትር) እና ወንድማቸው እጅጉ ዘለቀ የተሰቀሉት (የተገደሉት) ከዛሬ 81 ዓመታት በፊት (ጥር 5 ቀን 1937 ዓ.ም) ነበር፡፡ በላይ ዘለቀ ከአባታቸው ባሻ ዘለቀ ላቀው እና ከእናታቸው ወ/ሮ ጣይቱ አስኔ በ1904 ዓ.ም ተወለዱ። አባታቸው ባሻ ዘለቀ ላቀው የልጅ ኢያሱ ሚካኤል አንጋች (ባለሟል) ነበሩ፡፡ በላይ ገና ልጅ ሳሉ አባታቸው በሰው እጅ በመገደላቸው ምክንያት በእናታቸው እንክብካቤ ያለአባት አደጉ። እድሜያቸው እየጨመረ ሲመጣም የአባታቸው ገዳይ ማን እንደሆነ በማወቅ ለመበቀል ገዳዩን ማፈላለግ ጀመሩ። ለምጨን ተሻግረው የአባታቸውን ደም ለመበቀል ሲጠባበቁ ፋሺስት ኢጣሊያ ኢትዮጵያን ወረረች፡፡ በላይም ሀገርን የወረረውን የኢጣሊያን ጦር ለመውጋት ቆርጠው ተነሱ።  ብዙ ተከታዮችን በማፍራትም ወደ አርበኝነት ገቡ፡፡ ጀግናው አርበኛ ከፋሺሽት ኢጣሊያ ጋር ባደሩጓቸው ተደጋጋሚ ውጊያዎች ታላላቅ ድሎችን አስመዘግበው በርካታ የኢጣሊያና የባንዳ ወታደሮችን በመማረክና በመግደል እንዲሁም የጠላት ጦር ካምፖችን በማቃጠል ታላላቅ ጀብዶችን ፈፀሙ፡፡ የፋሺስት ኢጣሊያ ወራሪ ጦር በበላይ ዘለቀና በሌሎች ጀግና ኢትዮጵያውያን ታላቅ ተጋድሎ ድል ሆኖ ከምድረ ኢትዮጵያ ከተባረረ በኋላ ንጉሰ ነገሥት አፄ ኃይለ ሥላሴ ከእንግሊዝ ወደ ኢትዮጵያ በሱዳን በኩል ሲገቡ በላይ ዘለቀ የጎጃምን ብዙ ጦር አሰልፈው ንጉሡን በታላቅ ድምቀት በመቀበል ታማኝነታቸውን አሳዩ፡፡ ንጉሡ ወደ መናገሻ ከተማቸው አዲስ አበባ ደርሰው ለአርበኞች ስልጣንና ሹመት ሲሰጡ ከበላይ ዘለቀ ያነሰ ድሎችን ያስመዘገቡ ሁሉ ለከፍተኛ ሹመትና ማዕረግ ሲታደሉ በላይ ዘለቀ ግን እጅግ ከሚገባቸው በታች የ‹‹ደጃዝማች››ነት ማዕረግና የብቸና ገዢ ብቻ  እንዲሆኑ ተሾሙ፡፡ ጀግናው አርበኛ ተበሳጩ፡፡ በዚህም ምክንያት ከበላይ አካል (ከአዲስ አበባ) የሚመጣን ትዕዛዝ አልቀበልም በማለታቸው ከማዕከላዊው መንግሥት ባለስልጣናትና ከመንግሥት ታማኞች ጋር በተደጋጋሚ ግጭት ውስጥ ገቡ፡፡  ወንድማቸው እጅጉ ዘለቀን፣ አያሌዉ መሸሻን እና ሽፈራዉ ገርባዉን አስከትለው ሶማ በረሃ ገቡ፡፡ በዚያም ሳሉ ከጎጃም፣ ከጎንደርና ከወሎ ከተዉጣጣዉ የመንግሥት ጦር ጋር ለሶስት ወራት ያክል ሲዋጉ ቆይተው በሚያዚያ ወር 1936 ዓ.ም እጃቸውን ለመንግሥት ሰጡ፡፡ በላይ እና እጅጉ ዘለቀም አዲስ አበባ ተወስደው ታሰሩ፡፡ አዲስ አበባ ለተወሰኑ ወራት ያህል በእስር ከቆዩ በኋላ ግን በላይና እጅጉ ከእስር ቤት አምልጠዉ ወደ ጎጃም ሲያመሩ በድጋሚ ተያዙ። በመጨረሻም ወንድማማቾቹ በላይ ዘለቀና እጅጉ ዘለቀ ጉዳያቸው በልዩ ፍርድ ቤት ታይቶ ታህሳስ 23 ቀን 1937 ዓ.ም የሞት ፍርድ ተፈረደባቸዉ፡፡ ጥር 4 ቀን 1937 ዓ.ም በገነተ ልዑል ቤተ መንግስት ዙፋን ችሎት ፊት ቀርበውም የሞት ፍርዱ ፀናባቸው፡፡ በውሳኔው መሰረትም ቅዳሜ ዕለት ጥር 5 ቀን 1937 ዓ.ም ጀግናዉ አርበኛ ደጃዝማች በላይ ዘለቀና ወንድሙ እጅጉ ዘለቀ በአደባባይ ተሰቀሉ፡፡ ደጃዝማች በላይ ዘለቀ የሻሽወርቅ፣ ባሕሩ፣ መላኩ፣ ጎሹ፣ የሺእመቤት እና የሮምነሽ የተባሉ ስድስት ልጆችን አፍርተዋል፡፡ ደጃዝማች በላይ ዘለቀ የጠላት ጦር በተለይ ጐጃም ውስጥ መቆሚያ እና መቀመጫ እንዳይኖረው በማድረግ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ውለታ ያበረከቱ ጀግና ናቸው። መቼም ኢትዮጵያ ጀግኖቿን የማክበርና የመንከባከብ ነገር ብዙም አይሆንላትም እንጂ ጀግናው በላይ ዘለቀ ይህ ዓይነቱ የሞት ፍርድ የሚገባቸው ሰው አልነበሩም! የኢትዮጵያ ሕዝብ በጀግናው ሰው ስቅላት ምክንያት የደረሰበትን ሐዘንና ቁጭት ለመረዳት በተለያዩ ወቅቶች የተፃፉ መፃሕፍትን መመልከትና የተዘፈኑ ዘፈኖችን ማዳመጥ በቂ ነው፡፡ ምንጭ: አምደጽዮን ሰርጸድንግል ተጨማሪ: ለበላይ ከተገጠሙ ግጥሞች በጥቂቱ ================================ እስቲ በስምሽ ብዬ ልጀምር ሰላምታ አባ ኮስትር በላይ የሃይማኖት ጌታ ። እስቲ በስምም ብዬ ልጀምር ታምር አባ ኮስትር በላይ የጦር ምንስትር ። እስቲ በስምም ብዬ ልጀምር ምስጋና ኮስትርን የሚያህል ምን ወንድ ተገኘና ። እንደ ቀትር እሳት የሚፋጀው ፊቱ አባ ኮስትር በላይ ለምጨን ላይ ነው ቤቱ ። ጎጃም ዓይኑን ታሞ ሲደነባበር የለምጨኑ አንበሳ ይመራው ጀመር ። የወንዶችን ሱሪ ደርበህ ታጥቀህ አባ ኮስትር በላይ ምን ይሆን ሥራህ? የፊላው አንበሳ መጣ አሉ እያገሳ ። የፊላው ንጉሥ ገባ አሉ ማርቆሥ ። በላይ ዘለቀ ላቀው ቅዱስ ጊዮርጊስ የላከው ። ባንዲራው የዘለቀ ልጅ ጣሊያንን ደምሳሽ የኢትዮጵያ ደም መላሽ ። ታርበኞቹ ሁሉ ይበልጣል ኮስትር ሺ ብረት ማራኪ ባንድ ናስማስር ። አባ ኮስትር በላይ እባክህ ተቆጣ አንተም ራስ ተባል እኛም ጎጃም እንውጣ። እነማይ፣ በረንታ፣ ጥለትግን፣ ወድሚትም አዋበል፣ ማርቆስም፣ ወዮልሽ! ወዮልሽ! "ሞተ" "ሞተ" ስትይ በላይ ዘለቀሽ። ፈረንጅ ምድር ለቆ ቢሄድ በሰማይ ደመናውን አልፎ ዘለቀ በላይ። "አለቅን" አለ ፈረንጅ በሬዲዮኑ ኮስትር እንዴት አርገህ ወጣህባቸው ይሆን?   ጣሊያን ፍየል ሁኖ ቅጠል ቅጠል ሲያይ ነብር መስሎ አረደው በላይ። የጣሊያኖች ሱሪ ረጅም ነወይ? በግድ አስወልቆ ታጠቀው በላይ። አባ ኮስትር በላይ ወጣቱ ጎልማሳ አካላብሮት መጣ እሬሳ በሬሳ። አባ ኮስትር በላይ ያርበኛው ባለቤት ሃር አላበቀለም ነጩን የወቃበት። አባ ኮስትር በላይ አላወቀበትም ጉዞምነቱን አደባልቆ ወቃው ነጩን ጥቁሩን። የሶማ ጎራዴ ሰገባው ነጭ ነው የኮስትር ጎራዴ ሰገባው ነጭ ነው የሚበላው ሥጋ የሚጠጣው ደም ነው። እንዲን ሠራሁበት በቀኝ በግራ እጄ ሮም ላይ ተሰማ ጎጃም ተወልጄ። 23. ይህ ሁሉ መላ ነው፣ ይህ ሁሉ መላ ነው ያባ ኮስትር ታማኝ ውበቱ ትርፌ ነው። የአባ ኮስትር አሽከር እስጢፋኖስ ገብሬ ሰው እየበረረ ይገድላል እንደ አዉሬ። አንተ ቁመህ ተኩስ እኒያ ይሩጡ የአባ ኮስትር አሽከር ገብሬ ባለቁርጡ። እነዚህ ታጠቁ አልበኑን እንደ ድጉ የአባ ኮስትር ታናሽ አባ ቀስት እጅጉ። የአባ ኮስትር አሽከር ደልነሣ አባ ይባስ ቆርጦ ቆርጦ ጣለው የጣሊያንን ምላስ። እስቲ ላንሳው በግጥም አርጌ የአባ ኮስትር አሽከር አጋፋሪ መንጌ። የኮስትርን ሱሪ ሰፊ አበላሽቶበት መንግሻ ጀምበሬ ጉልበቱን አየበት። ወንዱ አባ ኮስትርን ጉልበቱ በላው ቢቆም አይለቅም የሚል ሰው ገደለው። ለምጨን አገራችን ሽምብራ ተዘርቶ ዓባይ አገራችን ሽምብራ ተዘርቶ ነቀሉት በጨርቃው መከርከሩ ቀርቶ። ሞፈርን ቀንበርን ጎጃም ቆርጦልኝ "ማቀፊያው ሸዋ ነው" ብሎ ሰደደኝ። አበባው በላይ ወጣቱ በላይ ሄደህ ቀረህ ወይ? በቅሎ ላጣው በቅሎ የሚሰጠውን በልጅግ ላጣው በልጅግ የሚሰጠውን ቸኮዝ ላሻው ቸኮዝ የሚሰጠውን አሻገረው በቀለት በላይ ዘለቀን። የደቦጭ ጌታ፣ የገምባው ጌታ "ተሰቅሎ አደረ" አሉ የጥምቀት'ለት ማታ። ተሰቀለ ቢሉኝ ዝናር ነው ብየ ተሰቀለ ቢሉኝ ናስማስር ነው ብየ ለካስ አንገቱ ነው መከራውን ያየ። እጅጉ ባይቆስል ሸፈራው ባይሞት ማን ይደፍረው ነበር የበላይ ግዛት?

በላይ ዕዝ መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር ተወርዋሪዎችን አስመረቀ!! በመይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የኮሩ ተወርዋሪ ልዩ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ስልጠና የወሰዱ አባላት ተመረቁ። ጥር 5/2018 ከመይሳው ካሳ 2ኛ ኮ
+2
በላይ ዕዝ መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር ተወርዋሪዎችን አስመረቀ!! በመይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የኮሩ ተወርዋሪ ልዩ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ስልጠና የወሰዱ አባላት ተመረቁ። ጥር 5/2018 ከመይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የሰራዊት አባላት ውስጥ ለመጀመሪያ ዙር በልዩ ስልጠና የተመለመሉ እና  በአግባቡ ለወራት የሰለጠኑ የቆየውን ሁሉን አቀፍ ስልጠና  በማጠናቀቅ በዛሬው እለት የኮሩ አመራር ባሉበት የምረቃ ስነ ስርዓቱ ተከናውኗ። ኅልውናችን በተባበረ ክንዳች!!! አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ

የምኒልክ ዕዝን ክንድ መቋቋም ያቃተው ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ ከተግባር ይልቅ "ውሸት"ን ትልቅ የአውደ ውጊያ ግንባር ካደረገው አመታቶች የተቆጠሩ ሲሆን ዛሬም አጠናክሮ ቀጥሎበት በምታዩት መልኩ በ
የምኒልክ ዕዝን ክንድ መቋቋም ያቃተው ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ ከተግባር ይልቅ "ውሸት"ን ትልቅ የአውደ ውጊያ ግንባር ካደረገው አመታቶች የተቆጠሩ ሲሆን ዛሬም አጠናክሮ ቀጥሎበት በምታዩት መልኩ በአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ስም የሃሰት መግለጫ እያወጣ ይገኛል:: እኛም እንላለን እናንተም በውሸታችሁ ቀጥሉ እኛም በሐቀኛ ተግባራችን! በያዝናቸው አመርቂ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ድሎቻችን ታጅበን ለመጨረሻው ግብ ድልና ነፃነታችን እየታገልን እንገኛለን:: ግፈኞች ሆይ ጦራችሁም ወሬያችሁም አይፈታንም:: አላማችንን ላፍታም ቢሆን አያደናቅፈውም! መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! ©አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ጥር 5/2018 ዓ.ም 05/ዐ5/2018 ዓ.ም

ሁለት የአገዛዙ ሰራዊቶች ፋኖን ተቀላቀሉ ጥር 05/2018 ዓ.ም ➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺ 1 አደም ፈረደ.. 25ኛክ/ጦር 6ኛ ሬጅመንት 2 ላምነው መከታ ....25ክ/ጦር 6ኛ ሬጅመንት ሰ
+1
ሁለት የአገዛዙ ሰራዊቶች ፋኖን ተቀላቀሉ ጥር 05/2018 ዓ.ም ➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺ 1 አደም ፈረደ.. 25ኛክ/ጦር 6ኛ ሬጅመንት 2 ላምነው መከታ ....25ክ/ጦር 6ኛ ሬጅመንት ሰዴ ወረዳ ከመሸገው ሀይል በመውጣት ከእነ ሙሉ ትጥቃቸው ወደ 201ኛ ኮር 54ኛ ክፍለ ጦር ፋኖን የተቀላቀሉ ሲሆን በፋኖ አመራሮች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!! አፋብኃ ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

ከእያንዳንዱ ሚዲያዎች በስተጀርባ ረጃጅም የሴራ ፖለቲካ እጆች እንዳሉ ስንቶቻችን እናውቅ ይሆን...? አሁን ላይ የአማራ ፋኖን ትግል ደጋፊ፣ዘጋቢና አጋዥ መስለው የተቋቋሙ ሚዲያዎች መስራቾቻቸውን፣የቦርድ አባሎቻቸውንና ስራ አስኪያጆቻቸውን ታውቋቸው ይሁን? በዋናነት የሳተላይትና ዩ ቱብ ቤዝድ (satellite&youtube based) ሚዲያዎች፣አልፎ አልፎ ከማኀበራዊ ትስስር አውታሮች ደግሞ ፌስቡክና ቲክታክ (facebook& tiktok) ላይ ውለው የሚያድሩትን ግለሰቦችና ቡድኖች ከጀርባ ያላቸውን ፍላጎት የአማራ ህዝብ ይረዳው ይሆን? በተለይ በአማራ ህዝብ የሕልውና ትግል ስም የሳተላይትና ዩቱብ ሚዲያ ከፍተው እርስ በእርስ ሲያጋድሉ የሚውሉትን የሚዲያ ባለቤቶች፣የቦርድ አባላት፣ዋናና ምክትል ስራ አስኪያጆች ማንነት፣ምንነት፣ፖለቲካዊ ፍላጎት፣የት አገራት እንደሚኖሩ፣የቤተሰብ ሁናቴ፣የግል ስራ፣ሐይማኖት፣ለአገዛዙ ያላቸው አጠቃላይ ሁኔታ፣የፋኖን ትግል የሚያዩበት መነፀር፣ የግል ስብዕናቸውና የጀርባ ታሪካቸው ወዘተ... ይታዎቅ ይሁን?? አይመስለኝም። ምድር ላይ የሚታገሉ ሃቀኛ የፋኖ አመራሮችን፣ፋኖዎችን፣ ትግሉን የሚያግዙ አካላትን፣ተቋማትን፣ድርጅቶችንና በአጠቃላይ የትግሉ አስኳል የሆኑ አካላትን መሬት ላይ በስመ ፋኖ አገዛዙ ካሰማሯቸው የይስሙላ ታጣቂዎችና የፋኖ አመራሮች "ነን" ባዮች ጋራ ተናበው እንዴት እንደሚያጠቁ ተገልጦላችሁ ይሆን?? ከአንድ ዓመት ተኩል ቀደም ብሎ በቀድሞ አጠራሩ የ "አማራ ፋኖ በጎጃም" (አፋጎ) ከእኔ ጋራ ግጭት ውስጥ እንዲገባ፣ አስቀድመው፣ በእኔ ላይ ከፍተኛ የጥላቻ ቅስቀሳ፣በሬ ወለድ ስም ማጥፋት(defamation)፣ የስብዕና ግድያ (character assassination)፣መልካም ስምና ዝናዬን (Good name and reputation) በማጥፋት በገዛ ጦራችን ከበባ እንዲፈፀምብን ከፍ ሲል ደግሞ የህይወት መሰዋዕትነት በማስከፈል ጎጃም ላይ ታሪካዊ ስህተት እንዲሰራ ሲቀሰቀሱ የነበሩ ሚዲያዎችና ቧልተኞቻቸው ዛሬ ላይ የት እንዳሉ ታውቁ ይሆን?እነ ማ እንደሆኑ ልብ ብላችሁ ይሆን? ያኔ በእኛ ላይ ከውስጥም ከውጭም ሲዘምቱ የነበሩት ራሳቸውን ፍፁም የትግሉ አራማጅ፣ተቆርቋሪ፣አዳኝ፣መሪና አለኝታ አስመስለው ነበረ። በአንፃሩ እኛን ደግሞ የትግሉ ስጋቶች አድርገው በመቀስቀስ እንድንወገር ሲያቧልቱ ነበረ። በጣም አስቂኙ ጉዳይ ግን እነዚህ በውስጥም በውጭም በሚዲያ፣ በጋዜጠኛ፣በቃል አቀባይና በፖለቲከኛ ስም በእኛ ላይ በሀሰት ሲዘምቱ የነበሩት አገዛዙን በዋናነት የብአዴንን መዋቅር አንገት ለአንገት ተናንቀን ካፈረስነው በኋላ እጃቸውን እየጎተትን ከባርነትም ከፍራቻም ነፃ ያወጣናቸው አንጊዎች መሆናቸው ነው።ዛሬ ደግሞ መፅናት አቅቷቸው እየተንጠባጠቡ ወትሮም ከባርነት ተጎትተው ወደ ወጡበት ስፍራ እየተመለሱ ነው።  በዚህ አጋጣሚ እጅግ በጣም ጥቂት በሐቅ የሚታገሉና የሚያታግሉ ሚዲያዎችና በለሙያዎቻቸውን አልዘነጋንም። ለማንኛውም እኛ ሐቀኞች ከነ ሐቃችን እስከ ቀራኒዮ የሕልውና አደጋ ውስጥ ለገባው ህዝባችን ያለማዎላዎል ፀንተን እንታገላለን። በጋዜጠኛ፣በፋኖ፣በአርበኛ፣በካፒቴን ..ወዘተ...ስሞች እየዘለሉ ለአገዛዙ ቢገብሩ እንዳይደንቃችሁ። የፀኑ፣የሚፀኑና የሚያፀኑ ዝም ያሉ ጀግና ታጋይ ልጆች ስላሏችሁ። በቀጣይ የሚዲያና የጋዜጠኛ ሚና በትግሉ ምን መሆን አለበት? ምንድን ነውስ? ዛሬ ላይ እዚህም አዛም የምናያቸው ጋዜጠኞች ወይስ ደላሎች የሚሉትን እናነሳለን። እንፅና!!! ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው - የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የሚድያ እና ዝግጅት መምሪያ ኃላፊ

2ት የ25ኛ ክ/ጦር የአገዛዙ ሰራዊቶች ፋኖን ተቀላቀሉ ◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌ ስቦ ማስከዳት:➔ 201ኛ ኮር 54ኛ ክ/ጦርን ተቀላቀሉ። የአገዛዙ 2ት የመከላከያ አባሎች ሰዴ ከመሸገው ከ25ኛ ክ/ጦር ከ
+1
2ት የ25ኛ ክ/ጦር የአገዛዙ ሰራዊቶች ፋኖን ተቀላቀሉ ◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌ ስቦ ማስከዳት:➔ 201ኛ ኮር 54ኛ ክ/ጦርን ተቀላቀሉ። የአገዛዙ 2ት የመከላከያ አባሎች ሰዴ ከመሸገው ከ25ኛ ክ/ጦር ከ6ኛ ሬጅመንት ከእነ ሙሉ ትጥቃቸው ወደ ፋኖ ጥር 04/2018 ዓ.ም ተቀላቅለዋል። በፋኖ ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው መከላከያዎቹ በአማራነታቸው በአገዛዙ ይደርስባቸው የነበረውን መገፋት እና እናንተ ግልገል ፋኖዎች ናችሁ እየተባልን ቆይተናል ዛሬ ከፋኖዎች ጋር በመቀላቀላችን ተደስተናል፤  በማለት ተናግረዋል። በእውቀት ፈረደና ላመነው መከታው የሚባሉ ጠብደል መከላከያዎች ወደ እኛ ተቀላቅለዋል። አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ!! ፋኖ አዲሱ ነገሰ አፋብኃ ቴወድሮስ ዕዝ ምዕ/አማራ ቀጠና 201ኛ ኮር 54ኛ ክ/ጦር ህ/ግንኙነት

ፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ዛሬ ጥር 5/2018 ዓ.ም ደቡብ ወሎ ዞን ውጫሌ ከተማ ደረሳዎችን ጨምሮ ወጣቶችን በሃይል እያፈሰ ወደ ጦር ማሰልጠኛ እያጋዘ የሚያሳይ ቪዲዮ ነው::

ሰበር ዜና ከ5 በላይ አጎራባች የወረዳ ህዝብ በሚሳተፍበት የወልድያ ከተማ ታላቅ የገበያ ቀን የአገዛዙ ሃይል የከባድ መሳሪያ ድብደባ እየፈፀመ ነው:: በዛሬው እለተ ማክሰኞ በወልድያ ከተማ የገበያ ቀን ቢሆንም ከኢንዱስትሪ መንደር/ማር ማቀነባበሪያው ከማለዳው ጀምሮ ከባድ መሳሪያ በመተኮስ ከጉባላፍቶ እና ራያ ቆቦ ወረዳ የውርድንብር ድብደባ እየፈፀመ ነው:: የፈሪ ነገር ሆኖበት የፋኖን ጦር ፊትለፊት መጋፈጥ ሲያቅተው በሩቁ በሚያስወነጭፈው የከባድ መሳሪያ ቅንቡላ ንፁሃን ላይ ሰባዊና ቁሳዊ ጉዳት እያደረሰ ነው:: ዝርዝር መረጃ ከእዙ እንደደረሰን የምናደርሳችሁ ይሆናል::

እውቅ የፖለቲካ እስረኞች ጉዳያቸው ፖለቲካዊ መፍትሄ አግኝቶ ከእስር እንዲፈቱ ፍላጎት መኖሩ ተሰማ (መሠረት ሚድያ)- ከሰሞኑ አንዳንድ የማህበራዊ ትስስር ገፆች አሁን ላይ በእስር ላይ የሚገኙ ፖለቲከኞችን፣ ጋዜጠኞችን እና ምሁራንን ጨምሮ ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች በመንግስት ምህረት ተደርጎላቸው ሊፈቱ እንደሆነ የሚገልፁ መረጃዎች ሲያሰራጩ ነበር። ይህን ተከትሎ መረጃውን የሚያጠናክር ወይም ሐሰትነቱን የሚገልፅ ማብራርያ ከመንግስት በኩል ባይሰጥም እነዚህ የፖለቲካ እስረኞች ጉዳያቸው ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲፈታ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ፍላጎት እንዳለው ሚድያችን የደረሰው መረጃ ይጠቁማል። የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አቶ ብርሀኑ አዴሎ ታኅሣሥ 11 ቀን 2018 ዓ.ም. በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ቂሊንጦ የጊዜ ቀጠሮ ማረፊያ ማእከል ተገኝተው ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት አቶ ዮሐንስ ቧያሌውን፣ አቶ ክርስቲያን ታደለን፣ ዶ/ር ወንደሰን አሰፋን፣ ዶ/ር ጫኔ ከበደን ፣ ዶ/ር ካሳ ተሻገርን፣ ዶ/ር ሲሳይ አውግቸውን እና ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይን አስጠርተው ማነጋገራቸው ታውቋል። የሚድያችን ምንጮች እንዳረጋገጡት በዚህ ወቅት አቶ ብርሀኑ ከአማራ ክልል ግጭት ጋር በተገናኘ ተጠርጥረው በሕግ ጥላ ስር የሚገኙ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች፣ ማህበረሰብ አንቂዎች እና የሲቪል ማህበራት መሪዎች ጉዳያቸው የፖለቲካ መፍትሄ  እንዲያገኝ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ፍላጎት አለው ማለታቸው ታውቋል። በ1997 ዓ.ም ከተካሄደው አገር አቀፍ  ምርጫ ጋር በተገናኘ ሁከትና ብጥብጥ ፈጥረዋል በሚል ተጠርጥረው የታሰሩ የቀድሞው ፖለቲከኞች ክሳቸው የተቋረጠው በፖለቲካ ውሳኔ መሆኑን ኮሚሽነሩ አስታውሰው አሁንም በሽብር ተጠርጥረው በእስር ላይ ያሉ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች እና ማህበረሰብ አንቂዎች ክሳቸው በፖለቲካዊ ውሳኔ እንዲቋረጥ ኮሚሽኑ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተነጋገረ ነው ብለው ምንጮች ገልፀዋል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በጉብኝቱ ዙርያ በፌስቡክ ገፁ መረጃ ያጋራ ቢሆንም ሚድያችን በሰማው የፖለቲካ ውሳኔ አስፈላጊነት ዙርያ ያለው ግን የለም። "በማእከሉ የተጠርጣሪዎች የሰብአዊ መብቶች አያያዝን አስመልክቶ በታዩ መልካም ለውጦች እና ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ ከተጠርጣሪዎች ተወካዮች፣ ከማእከሉ እና ከፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ተደርጓል" ያለው ኮሚሽኑ ተጠርጣሪዎች በማእከሉ ስለሚኖራቸው ቆይታ እና ስለሚያገኟቸው አገልግሎቶች በቂ ማብራሪያ የሚሰጣቸው መሆኑ አንዱ አበረታች ጉዳይ መሆኑን አንስቷል። ይሁንና ማእከሉ መያዝ ከሚችለው የተጠርጣሪዎች ቁጥር በላይ የያዘ በመሆኑ ከፍተኛ መጨናነቅ መፈጠሩ፣ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ተጠርጣሪዎች ከሌሎች ተለይተው አለመያዛቸው፣ መዝጊያ የሌላቸው መጸዳጃ እና መታጠቢያ ቤቶችን ጨምሮ የተወሰኑ የውሃ ቧንቧዎች አገልግሎት ያቆሙ መሆናቸው መሻሻል የሚገባቸው ጉዳይ መሆናቸው በጉብኝቱ ወቅት ተነስቷል። ሚድያችን የፖለቲካ እስረኞቹን ለመፍታት በመንግስት በኩል ፍላጎት እንዳለ ለማወቅ ጉዳዩ ይመለከታቸዋል ለተባሉት ለፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ በላይሁን ይርጋ ተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርብም ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል። -መሠረት ሚድያ-

የፋኖ መዋቅር ጠንካራ የማይነቀነቅ እደአለት የጠነከረ ሆኗል በየጊዜው ፋኖ የሚታጠቃቸው የቡድን መሳሪያዎች ብቻ እየሆኑ መጥተዋ !! አማራ ሁሌም አሸናፊ የሚሆንበትን መንገድ መርጧል እሱም ፈርጣማ ጡን
+2
የፋኖ መዋቅር ጠንካራ የማይነቀነቅ እደአለት የጠነከረ ሆኗል በየጊዜው ፋኖ የሚታጠቃቸው የቡድን መሳሪያዎች ብቻ እየሆኑ መጥተዋ !! አማራ ሁሌም አሸናፊ የሚሆንበትን መንገድ መርጧል እሱም ፈርጣማ ጡንቻወቹ ከነፍጡ ጋር ብቻ ነው።

የ201ኛ ኮር 54ኛ ክ/ጦር የተሳካ የአመራር ግምገማ አካሂዷል። ➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺ ጥር 04/2018 ዓ.ም የአማራ የትጥቅ ትግል በየጊዜው እያሳየ ባለው የአደረጃጀት እድገት በፋኖነት የትግል
+1
የ201ኛ ኮር 54ኛ ክ/ጦር የተሳካ የአመራር ግምገማ አካሂዷል። ➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺ ጥር 04/2018 ዓ.ም የአማራ የትጥቅ ትግል በየጊዜው እያሳየ ባለው የአደረጃጀት እድገት በፋኖነት የትግል አረዳድ ቅንነት ዋነኛ መሰረቱና ንግግር ፣ ምክክር ደግሞ የዕለት ከዕለት ስራው ነው። በዕለቱ ብዙ ሀሳቦችን በማንሳት የወደፊቱን የውጤት አቅጣጫወችን ድንቅ የተግባቦት መድረክ ተፈጥሯል። ይኸውም 1● በአዲሱ አደረጃጀት የስራ ስምሪት ያጋጠሙትን ተግዳሮትና የስራ ውጤት 2● የ5ቱንም ሻለቆች ቁመና ፍተሻና የክፍለጦሯን ተወርዋሪ ኃይል በሚናዋ እንድትገኝ የማድረግ ስራ 3● የኃብት አሰባሰብና ድጋፍን በተመለከተ ቀጠናዊ ሚዛናዊ ስራን መስራት 4● የክፍለ ጦሩ የጋራ አቋም ለቀጠናው አስፈላጊነት የሚሉና በወትሮ ዝግጁነት በድርጅት ሚዛን አስጠባቂነት የጋራ አስተውሎት ይዞ ስብሰባውን አጠናቋል። ጥር 04/2018 ዓ.ም አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!! የቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

የአማራ ህዝብ ትግል በግለሰቦች ላይ የተንጠለጠለ አይደለም!! ትግላችን የአማራን ህዝብ መሰረታዊ ጥያቄዎች በመመለስ በድል የሚቋጭ እንጅ ግለሰቦች በስናዳሪነት ከድተው ስለገቡ የሚለወጥ አንዳች ነገር የለም። የአማራ ህዝብ በየአዝማናቱ የገጠመውን ብሔራዊ አደጋ በመቀልበስ ረገድ ዘለግ ያሉ ዓመታትን የተሻገረ ቢሆንም ከቅርብ ጊዚያት ወድህ የጀመርነው የእኛ ዘመን ትውልድ አብዮት ደግሞ ከቀድሞዎች የአማራ ታጋዮች የተለየ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል!! አማራነትን ለመናኛ ጥቅም አናውለውም ሲባል በርካቶች የከፈሉትን ዋጋ በማሳነስ ከተነሳንለት ዓላማ በተፃራራው መቆምን በፅናት ስንታገለው ብቻ ነው። ትግላችን በጠላቶቻችን ላይ ፍፁም ጭካኔ እና የስነ ልቦና የበላይነትን በመያዝ የማያዳግም እርምጃ መውሰድን ይጠይቃል። ስለሆነም በአብዮታችን ውስጥ በሚያጋጥሙ ውስጣዊ እና ውጫዊ ተግዳሮቶች ሳናደናገጥ ለእውነተኛው አላማችን በፅናት ልንቆም ይገባል። ጠላት እየተሸነፈ እና እየወደቀ ባለበት ስዓት ወደ መታረጃ ቄራው መሄድ ነውረኝነት ነው። ትግላችንን እንደ ዓይን ብሌናችን ልንጠብቀው ይገባል!! አይበገሬው የአማራ ሰራዊት ያሸንፋል!! ዝንታለም አማራ ወይራው አማራ

ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ !!! ፕሮፌሰሩ ምን አሉ ??? የአማራ ጠላት ሆዳም አማራ ነው ። የፋኖም ጠላት ሆዳም ፋኖ ነው ። የአማራን ህዝብ ጥያቄ ይዘው ወደፋኖ የተቀላቀሉ እና በዚህ ትግል በማጓተት እና በውስጥ አድነት እዳይመጣ ስታተራምሱ የቆያችሁ ምስለኔዎች ወልዳችሁ አትሳሙ የሰራችሁት አይባረክላችሁ ። በዚሀ ትግል ላይ አስመምስላችሁ ስትናገሩ ቆይታችሁ ወጣቱ ለዚህ ትግል የተሰዉትን መርሳት ሂሊና ቢስነት ነው ። በወጣቱ ደም እደነገዳችሁ ፈጣሪ የጀግና ደም ፈሶ ስለማይቀር ነገም ብልፅግናንም ትከዱታላችሁ ምክንያቱም የከዳችሁት የአማራን ህዝብ ነው። የአማራ ትግል አንድ እዳይሆን አተራመሳችሁ እጅ የሰጣችሁት የምትመሩት ሰራዊት እና ህዝብ አንድ ካልሆናችሁ ብሎ ጫና ሲያሳድርባችሁ ነው ሸሽታችሁ የገባችሁት ። ይሄንን ትግል በእውነት የምትታገሉ እና የምትደግፍ ሲነቃባቸው ስለሆነ የገቡት ከምግዜውም በላይ እደብረት ጠንክረን ማሸነፍ አለብን ። እስካሁን ትግሉን ሲጎትቱ የነበሩ ሰዎች መሄዳቸው ጥሩ ነው ወደፊት እቅፋት የሚሆኑ ሰዎችን እየለየን እርምጃ መውሰድ ይጠበቅብናል ሲጠራ ትግሉ አይጓተትም በአጭር እቋጨዋለን ስለዚህ መጠከር ነው አማራ ያሸንፍል። የዚህ ትግል እቅፍቶች 1.የመግስት ተላላኪዎች ተቀጥረው ለማተራመስ የመጡ ይኖራሉ 2.ትግሉ ሳይገበው ቲክቶክ አይቶ የመጠው ሲጨቀው ይጠፋል 3. ስራ አቶ ግራ ሲገበው ይመጣ ይኖራል 4.በፍኖ ውስጥ ተደብቆ የግል ጠላቱን ለመበቀል የመጣ ይኖራል 5. በፋኖ ስም ተደራጅቶ ለመዝረፍ የወጣ ይኖራል በአጭሩ በዚህ ተመሳሳይ ሰዎች ይኖራሉ ትግሉ እያደገ ሲመጣ አሰራር ሲዘረጋ መርህ ሲኖርባቸው እየሸሸ ወደ መግስት ሲገቡ ትግሉ እየጠራ ነው። እውነተኛ ታጋይ ይቀጥላል ተላላኪው ሲሸሽ ትግሉ በአጭር ይቋጫል ። ስለፍኖ መጥፎ የሚያወሩ ሰዎችን ተከታተሉ ችግር ያለበትን መለየት አለብን ጥሩ ሰው እየመሰሉ መርዝ የሚረጩትን መከታተል አለብን ትግል ይቀጥላል ። ደጋፌዎች እና ለዚህ ትግል ሚዲያ የምትሰሩ እየተከታተላችሁ ለህዝቡ እውነታውን ማስረዳት አለባችሁ። ከልብ የምትታገሉ አመራሮች፣ ስራዊቶች እና ህዝባችን በንፁሀን ላይ የሚደርስ በደሎችን መከታተል እውቅና መፈጣጠር ይኖርብናል የመግስትን ተልኮ ተሸክመው ንፁሀንን እዳይበደልብን። ትግል ይቀጥላል ተላላኪዎች እጁን ይሰጣሉ !!! በተላላኪዎች ታሪክ ተፅፎ አያውቅም !!! ተኮለኛ እድሜው አጭር ነው !!! ኢቶጵያ በጀግኖች አጥንት እና ደም የተመሰረተች ሀገር ነች!!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ምክትል ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አርበኛ ኤፍሬም ባዩ