uz
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

Kanalga Telegram’da o‘tish

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Ko'proq ko'rsatish
3 589
Obunachilar
+524 soatlar
+5667 kun
+97730 kun
Postlar arxiv
በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የሚመራዉ የአማራ ፋኖ በወለጋ ትላንት መጋቢት 14 ቀን/2018 ዓ.ም ወራሪዉን ኃይል ሲደቁሰው ውሏል። የጠላት ማዕከላዊ ዕዝ፣ 101ኛ ሕዳሴ ኮር፣ 33ኛ አባይ ሻለቃን ያ
+1
በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የሚመራዉ የአማራ ፋኖ በወለጋ ትላንት መጋቢት 14 ቀን/2018 ዓ.ም ወራሪዉን ኃይል ሲደቁሰው ውሏል። የጠላት ማዕከላዊ ዕዝ፣ 101ኛ ሕዳሴ ኮር፣ 33ኛ አባይ ሻለቃን ያስተናገደው የፋኖ ሰራዊት ድል ተጎናፅፏል። በወለጋ ጊዳ አያና እና ጉደያ ቢላ ወረዳወች በተደረገው በዚህ ውጊያ ዘረ ፈጁ የብልፅግና ሰራዊት ተደምስ*ሷል። 1 (አንድ) ዲሽቃ፣ 3 (ሶስት) ስናይፐር፣ 3 (ሶስት) ብሬን እና 21 (ሃያ አንድ)/የመከላከያ አባላት ከበርካታ ተተኳሽ፣ ክላሽ ንኮቭ እና ሌሎች ወታደራዊ ቁሳቁሶች ጋር መማረካቸው ተረጋግጧል። ይቀጥላል...

ሶስት የፋሽስቱ በልፅግና አገዛዝ ሰራዊት አባላቶች የፋኖን ትግል ተቀላቀሉ! የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት 11ኛ ዕዝ 203ኛ ኮር 83ኛ ክፍለ ጦር ሶስት አባላቶች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ብልፅግናን በመክዳ
+3
ሶስት የፋሽስቱ በልፅግና አገዛዝ ሰራዊት አባላቶች የፋኖን ትግል ተቀላቀሉ! የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት 11ኛ ዕዝ 203ኛ ኮር 83ኛ ክፍለ ጦር ሶስት አባላቶች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ብልፅግናን በመክዳት የፋኖን ትግል ተቀላቀሉ! አላማ ቢስ በሆነ ጦርነት ወገናችንን መውጋታችን ፀፅቶናል ያሉት የሰራዊቱ አባላቶች ምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻን የተቀላቀሉ ሲሆን አመራሮችም አቀባበል አድርገውላቸዋል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ መጋቢት 15/2018 ዓ.ም

የአደረጃጀት ዜና! በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምኒልክ ዕዝ ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር አደረጃጀት በመስራት የኮርና የክፍለ ጦር ስያሜ ሰጠ:: በአፋብን ምኒልክ ዕዝ የመልሶ ማደራጀት እና የመ
የአደረጃጀት ዜና! በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምኒልክ ዕዝ ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር አደረጃጀት በመስራት የኮርና የክፍለ ጦር ስያሜ ሰጠ:: በአፋብን ምኒልክ ዕዝ የመልሶ ማደራጀት እና የመዋቅር ማሻሻል ተግባራት መካከል አንዱ የሆነው የኮር አደረጃጀት እና የክፍለ ጦር መልሶ ማደራጀት ብሎም ስያሜ መስጠት ይገኝበታል። ስለሆነም ከዚህ በፊት የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምኒልክ ዕዝ ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር ይባል የነበረው በአሁኑ አደረጃጀት 105ኛ ኮር በሚል መጠሪያ የተሰየመ ሲሆን በስሩ የሚገኙ ክፍለ ጦሮችንም እንደሚከተለው ሰይሟል:: •45ኛ ክፍለ ጦር (መብረቅ ክፍለ ጦር) •71ኛ ክፍለ ጦር (አርበኛ አደም አሊ አባ ናደው ክፍለ ጦር) •47ኛ ክፍለ ጦር (አማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለ ጦር) •29ኛ ክፍለ ጦር (ኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለ ጦር) •33ኛ ክፍለ ጦር (ዋሲል ክፍለ ጦር) በሚል ክፍለ ጦሮችን ሰይሞ ለትግል እንዲያመች በማድረግ አደረጃጀቱን አዘምኗል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ መጋቢት 15/2018 ዓ.ም 👇

አስደሳች ዜና‼️ አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር የነበልባል ክ/ጦር አዲስ የፋኖ ሰራዊት አባላት በደማቅ ሁኔታ አስመረቀ ። መጋቢት 13/2018 ዓ.ም፡ ከሰም ፪ኛ ኮር ነበልባል ክ/ጦር ከሁለት ወር በላይ ያሰለጠናቸው ከፍተኛ ቁጥር ያለው የፋኖ ሰራዊት አባላት ማስመረቁን አስታወቀ ። ተመራቂ የፋኖ ሰራዊት አባላት፤ የክፍለጦሩ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ወደ ነበሩ የክፍለጦሩ አሃድ ከዛሬ ጀምሮ በይፋ መቀላቀላቸውን ተገልጿል ። የክፍለጦሩ ከፍተኛ አመራሮች በዚህ ዝግጅት ላይ በመታደም፤ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት እና ትግሉን በተመለከተ የተለያዩ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል ። በዚህ የምርቃት ፕሮግራም ላይ ከተገኙት ከፍተኛ አመራሮች መካከል አንዱ፤ ከሰም ፪ኛ ኮር የነበልባል ክ/ጦር፡ ወታደራዊ አስተዳደር የሆኑት አርበኛ ፲ አለቃ ስመኝ አለማየሁ ናቸው፤ አርበኛው በመድረክ ቆይታቸው ከአስተላለፉት መልዕክት መካከል፤ - በቅድሚያ ለተመራቂ የፋኖ ሰራዊት አባላት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ከአስተላለፉ በኋላ፤ "...በዛሬዋ ዕለት የክፍለጦሩ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት መመረቃችሁን በደስታ እናበስራለን ። አሁን እናንተ ሰልጣኞች ሳትሆኑ ወደ ነባሩ ሰራዊት ተቀላቅላችሁ ለአማራ ህዝብ ጋሻና መከታ ሆናችሁ በልበ - ቆራጥነት ከዛሬዋ ቀን ጀምሮ እንደምትታገሉ መሪዎቻችሁ በመድረክ ያረጋግጡላችኋል..." ሲሉ ተደምጠዋል ። አክለውም፤ "...ህዝባችን ለሰጠን አደራና ኃላፊነት አንዳች ሳታጓድሉና ከአቋማችሁ ሳትዋዥቁ በጋራ ሆነን በጽናት የምንታገል ይሆናል..." በማለት መልዕክታቸውን ለተመራቂ ሰራዊት አባላቱ አጋርተዋል ። ሌላው፤ በዚህ የምርቃት ስነ-ሥርዓት ላይ ከተገኙት አመራሮች መካከል፤ ከሰም ፪ኛ ኮር የነበልባል ክ/ጦር፡ ምክትል ጦር አዛዥ የሆኑት አርበኛ እምሽ በጋሻው ናቸው፤ "...ለቆምንለት ዓላማ መርህን ተከትለን፤ ህዝባችንን በአግባቡ ይዘን በአንድነት ጠላታችንን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማስወገድ አለብን ። እኛ የአማራ ልጆች ለያዝንው ዓላማ በጽናት ቆመን ፥ ሳንፍረከረክ በአንድነት ጠላታችንን እንታገላለን..." ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ። ሌላኛው፤ በዚህ ደማቅ የፋኖ ሰራዊት አባላት ፕሮግራም ላይ ከታደሙት አመራሮች መካከል፤ ከሰም ፪ኛ ኮር የነበልባል ክ/ጦር፡ ሎጀስቲክ ኃላፊ የሆኑት አርበኛ ደሴ ሞገሴ ናቸው፤ "...ይህ ስልጠና ብቻ ሳይሆን ከልብ የያዛችሁትን እውቀትና ኃይል ለተጨቆነው ለአማራ ህዝብ ይህን የሰለጠናችሁትና የደከማችሁበትን ፍሬ አፍርቶ እንደምናይ አንጠራጠርም ። እኛ የወጣንው ተበድለን ፥ ተገፍተን ነው ወደ ጫካ የገባንው ። የአማራ ህዝብ እንደ ሰው ፥ እንደ ብሔር የሚታይበት ጊዜ ላይ ስላልሆነ፤ ያለን አማራጭ እናንተን የመሰለ የአማራ ህዝብ እንቁ ልጆችን ይዘን ይህን አውሬ ስርዓት ነቅሎ መጣል ብቻ ነው መፍትሄው..." በማለት በቆይታቸው ተናግረዋል ። በመጨረሻም፤ የማጠቃላይ ንግግር እና የቃልኪዳን ዝግጅትን ያካሄዱት ደግሞ ከሰም ፪ኛ ኮር የነበልባል ክ/ጦር፡ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ የሆኑት አርበኛ ሞገስ ገበየሁ ናቸው፤ "...ዛሬ የእናንተ መመረቀ የአማራ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለው ግፍና በደል እንዴት አድርገን መመከት ላይ አበክረን መስራትና ትኩረት ማድረግ እንዳለብን ዋነኛው ጉዳይ ነው..." በማለት ፕሮግራሙን አጠቃለዋል፤ ሲል የነበልባል ክ/ጦር ሪፖርተራችን መረጃውን ከምባር አድርሶናል ። © አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ሚዲያ ክፍል ኃላፊ፡ አርበኛ ጋዜጠኛ አበባየሁ ሰይፈ ። - አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ህ/ግንኙነት መምሪያ ።

አያሌ ጠላት ረገፈ!! የዘመናት ትውልድ የጀግንነት ምንጭና የማይቋረጥ የጀግንነት ጅረት አውራሹ የዓፄ ቴዎድሮስ ልጆች በጎንደር ጣቁሳና አለፋ ለሁለት ቀናት በተከታታይ ባደረጉት ጠንካራ ተጋድሎ ከፍተኛ ጠላት ረገፈ!! በ4ቱም ማዕዘን ተግተልትሎ ለወረራ እና ለጥፋት ያቀናው የፋሽስቱ ዓባይ አህመድ ሰራዊት የአሞራ ሲሳይ ሁኖ ረግፏል። የአፋብን በላይ ዕዝ መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር አድዋ ክ/ጦር፣ቋራ ኦሜድላ ክ/ጦር እና ካራ ማራ ክ/ጦሮች ከአፋብን ጎንደር ጠ/ግዛት ዕዝ በጌምድር ክ/ጦር ጣና ብርጌድ ጋር በመጣመር በብርሃኑ ጁላ ሰራዊት ላይ ከፍተኛ ድምሰሳ ፈፅመዋል። ህልውናችን በአርበኝነታችን!! ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ

ሰበር ዜና የአብይ አህመድ እና የብርሀኑ ጁላ ልጆች ባሉበት አውደ ውጊያ በርካታ የብልፅግና ስልጣን አስጠባቂዎች የሆኑት  ሲደመሰሱ! ቀሪዎቹ ደርዘን ሙሉ ቁስለኞች ጤና ጣቢያን  የሲቃ ድምፃቸውን እያቋረሩ ይገኛሉ!! አፋብን ሚኒሊክ እዝ 106ኛ ኮር 34ኛ ክፍለ  መጋቢት 14/2018 ዓ/ም ከጋሸና ወደ እስታይሽ አቅጣጫ የጥፋት ፈረሱን ጉግስ ሲጋልብ በነበረ የፋሽስቱ ሰራዊት ላይ መራር ቅጣት የተወሰደ ሲሆን! በዚህም የአውደ ውጊያም የተገኙ ቱርፋቶች አንድ ማዕረጉ በወል ያልታወቀ የመከላከያ አመራር ወደማይቀረው ሲሸኝ፤ በ29ኙ ላይ የድምሰሳ እርምጃ የተወሰደ ሲሆን፤ ቀሪዎች ከ31 በላይ የጁላ ሰራዊት ከባድ ቁስለኛ ተደርገዋል። ጥምር ጦር እያሉ የሚያሞካሹት ሆድ አደር ሰራዊታቸው ጥምር አስከሬን ተደርጓል። በዚህ አውደ ውጊያ የአቶ አብይ አህመድ ከዝናሽም ይሁን የደቀለው  ልጅ የለም። እድሁም የብርሀኑ ጁላ የቁባት ልጅም  በለሉበት ከየትም ተጋፈው የመጡ የስልጣን  አስጠባቂዎች ላይ እየድርሻቸው ተለብልበው ገሚሱን አስከሬኑን ሳያነሱ ሌላውንም ቁስለኛ ጥለው እግሬ አውጭኝ የዘወትር ነፍስ አድን ፍርጠጣቸውን መርጠው ወደየመጡበት በሀዘን ኮፍያ ተከልለው ተመልሰዋል። ከቀኑ 10:00 ሰዓት የተጀመረው አውደ ውጊያ እስከ አመሻሽ 1:30 ሰዓት የዘለቀ ሲሆን በርካቶች የስርዓቱ ወታደሮች ከጥርናፊያቸው ተበታትነው በፋኖዎች እየተለቀሙ ይገኛሉ። እስካሁን በቁጥር በውል ያልተረጋገጡ የመከላከያ ሰራዊትና የአድማበትን ሰራዊቶች አጋጣሚውን በመጠቀም ከጥርናፊ አምልጠው እራሳቸውን ከከንቱ ሞት እያዳኑ ይገኛሉ። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ #106ኛ ኮር ህ/ግ መምሪያ ሀላፊ! መጋቢት 14/2018 ዓ.ም

በግፍ ደም ማፋሰስ ስልጣን ለማራዘም የወሰነው የዓብይ አገዛዝ ዛሬም በጎንደር ክፉኛ ተመቷል!! በነ አባድፈን መሳፍንት ተስፉ፣በነ ደጃች አያሌው ብሩ ቀዬ ዳባት አረደጃን አካባቢ ሲክለፈለፍ የዘለቀው
+1
በግፍ ደም ማፋሰስ ስልጣን ለማራዘም የወሰነው የዓብይ አገዛዝ ዛሬም በጎንደር ክፉኛ ተመቷል!! በነ አባድፈን መሳፍንት ተስፉ፣በነ ደጃች አያሌው ብሩ ቀዬ ዳባት አረደጃን አካባቢ ሲክለፈለፍ የዘለቀው የምርኮኛው ብርሃኑ ጁላ ሰራዊት እንደተለመደው ከኮሶ የመረረ ሽንፈትን በጀግናው ሰራዊታችን ተጎንጭቷል። በዝምተኛው መብረቅ ዘራይ አዝመራው ስም የተሰየመው በላይ ዕዝ ደጃዝማች 4ኛ ኮር ዘራይ ክ/ጦር ሸጋው ውበት ብርጌድ በተከታታይ ሳምንታት በሚወስዳቸው የተጠና ኦፕሬሽኖች በቀጠናው ጠላት እንደ ሰም ቀልጦ እንዲቀር እያደረገ ነው። መጋቢት 14/2018 ዓ.ም ወደ ብርጌዱ ጠንካራ ይዞታዎች ተግተልትሎ የዘለቀው ግፈኛ ሰራዊትም በእሳት አለንጋ ተገርፎ መራር ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳትን አስተናግዷል። *15 የተደመሰሰ * 15 ቁስለኛ ሲሆን * 25 ነፍስ ወከፍ የጦር መሳሪም ተማርኳል። ከዳባት ከተማ ቅርብ ርቀት ቀርሃ ቀበሌ በተደረገው የአፈሙዝ ክርክር ሽንፈት የገጠመው ግፈኛ የዓብይ የታጣቂ ስብስብ ቀሪው ነብሴን አውጭኝ ብሎ ወደ መጣበት ዳባት ሸሽቷል። አፋብን በላይ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ!

ስሜ አስር አለቃ ጌታሰው አዳነ ነው። በቀድሞ ዘመኔ ውስጥ በRepublican Guard ክፍል ውስጥ በታማኝነት እና በጥልቅ ዲሲፕሊን የተሞላ አገልግሎት አበረከትሁ። በትምህርቴም በBSc degree በነርሲንግ ተመርቄ፣ #ከ801 ተመራቂዎች መካከል አንደኛ በመውጣት ከፍተኛ ውጤት አሳይቻለሁ። በዚህ ስኬትም ምክንያት #በምርኮኛው #ከፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ መሆኔ የማይረሳ ክብር ነው።     በውትድርና ያሳለፍኩት ጊዜ በጥንካሬ፣ በትእዛዝ መከበር እና በሙያዊ ብቃት የተገነባ ነበር። ነገር ግን ጊዜ ሲቀጥል እውነታዎችን በዓይኔ ሲገለጡ ልቤ ዝም ብሎ ሊቆይ አልቻለም። በአገር ውስጥ የተፈጠረውን የፖለቲካ ሁኔታ፣ የሕዝብ መከራና የፍትህ እጥረት በቅርብ ስመለከት እኔ እንደ ሰው እና እንደ ሙያዊ ሰራተኛ ዝም ብሎ መቆየት አልቻልኩም። በዚህ ምክንያት የብልፅግና/ኦህዴድ ስርዓትን በመቃወም የአማራ ህዝብ ነፃነት እንዲመጣ በማመን ወደ አማራ ፋኖ ተቀላቀልሁ። ወደዚህ ትግል ስገባ የነበረኝ ዋና እምነት አንድ ነበር—አንድም ታጋይ በሕክምና እጥረት መሞት የለበትም። ይህን እምነት በመሸከም በሙያዬ እውቀት እና በልምዴ ትግሉን ለማጠናከር ተጋለጥሁ።    ከዚህ በተጨማሪም ከትግል አጋሮቼ ጋር በመሆን የነበሩ አንዳንድ የሃሳብ ልዩነቶችን በግልጽ ውይይት በመፍታት ትግሉን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሻሻል እንደ ኃላፊነት ተመልክቻለሁ።       ነገር ግን ባለፉት ሶስት ዓመታት ያየሁት እና ያሳለፍኩት ሁኔታ እጅግ ከባድ ነው። በድሮን ጥቃት እና በተለያዩ ከባድ መሳሪያዎች የተፈጸመው የሕዝብ መከራ በቀጥታ ስመለከት ልቤ ተሰበረ። በእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ በውትድርና መቆየቴ ራሴን እንድጠይቅ አደረገኝ።   ስለዚህ ዛሬ በግልጽ ልብ እና በቅንነት ለአማራ ህዝብ #ይቅርታ እጠይቃለሁ። የተፈጸመው ጉዳት ቀላል አይደለም፤ ነገር ግን እውነትን መቀበል የመጀመሪያ እርምጃ ነው። ቀሪውን ዘመኔን በሙሉ ታማኝነት፣ በቅንነት እና በሙያዊ ብቃት ለሰፊው የአማራ ህዝብ ለማገልገል ቃል እገባለሁ። ይህ ቃል ቃል ብቻ አይደለም—በተግባር የሚገለጥ ኃላፊነት ነው።        እንኳን ደህና መጣህ!!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ፣ የደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ፣ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር የሰባት ለሰባ በካራለጎማ ቀበሌ ከማህበረሰቡ ጋር ሰፊ ውይይት አካሔደ!! ​ ሆኖም ​የሰባት ለሰባ አዛዥ
+3
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ፣ የደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ፣ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር የሰባት ለሰባ በካራለጎማ ቀበሌ ከማህበረሰቡ ጋር ሰፊ ውይይት አካሔደ!! ​ ሆኖም ​የሰባት ለሰባ አዛዥ አርበኛ አረጋ ሙሉነህ እና የክፍለ ጦሩ ወታደራዊ አስተዳደር አርበኛ እንዳለ ሸዋዬ በተገኙበት የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ከተመሰረተ ጀምሮ ዛሬ የደረሰበት የፖለቲካና የወታደራዊ ቁመና፣ የአማራ ሕዝብ ለህልውናው የሚያደርገው ትግል የመጨረሻ ምዕራፍ ማሳያ መሆኑን ለማህበረሰቡ የድርጅቱን መርህና ዓላማ ለሕዝቡ ሰጠዋል። ሕዝቡ የራሱን ልጆች የትግል ጉዞ በትኩረት ከአደመጠ በኃላ የሕዝቡ መኖርና ነፃነት የሚረጋገጠው በዚህ የጋራ ክንድ መሆኑን አፅንዖት ከመስጠትም በላይ እናንተ ልጆቻችን ናችሁ እስካሁን ያስመዘገባችሁት ድል ለኛ ኩራትና ተስፋ ነው።ፋኖ እስካሁን ባስመዘገበው ድል ያለውን ከፍተኛ እርካታም ነው። ልጆቻችን ለኛ የቁም ዋስትና ናቸሁ። በመጨረሻም ማህበርሰቡም ከፋኖ ጎን ቆሞ እስከ ድል መጨረሻ ድረስ አብሮ እንደሚዘልቅ ቃል በካራለጎማ ቀበሌ የታየው ውይይት፣ በትግሉና በሕዝቡ መካከል ያለውን የማይበጠስ ሰንሰለት ይበልጥ አጥብቆታል በማለት ውይይት በሰላም ተጠናቋል። ​ መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!! የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ አማረ ታዘዘ !! መጋቢት 14/07/2018 ዓ.ም

አራት የአድማ ብተና አባላቶች አንድ ብሬን እና ሶስት ክላሽ በመያዝ የፋኖን ትግል ተቀላቀሉ:: ከብልፅግ ና አገዛዝ ጋር በመወገን ህዝባችን ላይ ዘር ማጥፋት አንፈፅምም በቃን ያሉ የ አድማ ብተና አባ
አራት የአድማ ብተና አባላቶች አንድ ብሬን እና ሶስት ክላሽ በመያዝ የፋኖን ትግል ተቀላቀሉ:: ከብልፅግ ና አገዛዝ ጋር በመወገን ህዝባችን ላይ ዘር ማጥፋት አንፈፅምም በቃን ያሉ የ አድማ ብተና አባላቶች አንድ ብሬን እና ሶስት ክላሽ በመያዝ ወደ አፋብን ምኒልክ ዕዝ 106ኛ ኮር ተቀላቀሉ:: የኮሩ አመራሮችም አቀባበል አድርገውላቸዋል:: ከዚህ ጋር ተያይዞም የ106ኛ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ ሻለቃ ሃብቴ እባቡ በአቀባበል ፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው የእንኳን ወደ ህዝባችሁና ወንድሞቻችሁ ፋኖዎች ደህና መጣችሁ መልክትን አስተላልፈዋል። የፋኖን የህልውና ትግል የተቀላቀሉ የ አድማ ብተና አባላቶች አማራን ህዝብ የህልውና አዳጋ ለመቀልበስ መጥተናል ሲሉ ተናግረዋል። አያይዘውም በአድማ ብተና ውስጥ ሙሉ ሰራዊቱ ወደ ፋኖ መቀላቀል ይፈልጋል። የአማራ ፋኖ አንድነት (አፋብን) ከተመሰረተ በኋላ ጠቅላላ ሰራዊቱ ወደ ፋኖ መቀላቀል ይፈልጋል ሲሉ መልክታቸውን አስተላልፈዋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ መጋቢት 14/2018 ዓ.ም

ዋሲል ክፍለ ጦር ለወራት የሰለጠኑ ምልምል ፋኖዎችን አስመረቁ:: በአፋብን ምኒልክ ዕዝ ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር ስር የሚገኘው ዋሲል ክፍለጦር ከስድስት ወራት በላይ ሲያሰለጥናቸው የነበሩ የ6ኛ ዙር ሰልጣኞችን በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል። በምረቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ የጃማ ቀጠና የሀገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶችን ጨምሮ የክፍለጦርና የሬጅመንት አመራሮች የተገኙ ሲሆን፡ የሃይማኖት አባቶቹና የሀገር ሽማግሌዎቹ "የአካባቢውን ሰላምና ደህንነት የሚያስከብርና የአማራን ሕልውና የሚታደግ እንዲሁም ፍትሕ ርትዕ የሚያሰፍን ብቁና ንቁ የፋኖ ኃይል መገንባቱ እንዳስደሰታቸው ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። በተለይ የመስጂድ ኢማም የሆኑ ትላልቅ የሃይማኖት አባቶች፡ ዋሲል ክፍለ ጦር የአማራን ሕልውና ለመታደግ ወጣቱን ኃይል በማሰልጠንና በማደራጀት እየሰራ ያለውን ስራ አድንቀውና አመስግነው "ይህ ተከታታይ የማሰልጠንና የማብቃት ሂደት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት በማሳሰብ፡ ለሰራዊቱ  ያላቸውን ድጋፍና አጋርነት በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል። ይህ ክፍለጦሩ በየቀኑ ከሚያደርገው ውጊያ ጎን ለጎን ያልተቋረጠ የስልጠና መርሃ ግብር በማካሄድ የጠላትን ቅስም የሚሰብር ብቁና እጅግ ጠንካራ ኃይል የመገንባት አቅሙን ያሳየበት ነው ተብሏል። ሰልጥነን እንዋጋለን እየተዋጋን እንሰለጥናለን! መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ መጋቢት 14/2018 ዓ.ም

ክፍለጦሩ 3 ብልፅግና ያሰማራቸውን ዘራፊዎች በቁጥጥር ስር ያዋለ ሲሆን ለወረራ በመጣው የብልፅግናው የጫካ ክንፍ የሸኔ ዘራፊ ቡድን ላይ በወሰደው እርምጃ የቡድን መሳሪያ መማረኩን አስታወቀ።    አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ       መጋቢት 14/2018ዓ.ም ሰራዊታችን ብልፅግና ያሰማራቸውን የህዝብ መከራ የሆኑ አረሞችን በመንቀል የትግላችንን ህዝባዊነት እያሰመሰከረ ይገኛል። የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ አምደ ፅዮን ኮር የራስ አበበ አረጋይ ክፍለጦር ከማህበረሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ለበርካታ ወራቶች ሹፌሮችን እና ባለሀብቶችን በማገት ከፍተኛ ገንዘብ በመጠየቅ ሲዘርፉ ከነበሩ የወንበዴዎች ግበረ-አበሮች ውስጥ ሶስቱን (3) ከነዘረፉት በርካታ ገንዘብ እና ከሁለት ታጋቾች ጋር የክፍለጦሩ ቃኝ እና ከሻለቆቹ የተወጣጡ ቃኝዎች ባደረጉት ልዩ ኦፕሬሽን በቁጥጥር ስር ውለዋል። ትላንትን መጋቢት 13 ቀን 2018ዓ.ም በእንሳሮ ወረዳ እና በሳያደብርና ዋዬ ወረዳ በዝርፊያ ስራ ላይ ተሰማርተው ነጋዴወችንና ሹፌሮችን ብሎም በአካባቢው የሚገኙትን ሀብታም ገበሬወችን በማገትና  ዋሻ ውሰጥ በመሰወር ከፍተኛ የገንዘብ መጠን በመጠየቅና በማሰከፍል ለአንድ ዓመት ያክል ሲዘርፉ የቆዩና ከቡድኑ ዘጠኝ (9) አባላት ወስጥ ሶስት (3) አባላቱን ጀግናው የራስ አበበ አረጋይ የመንፈስ ልጆች የትግላችን ነቀርሳ፣የህዝባችን መከራ፣ የአገዛዙ የጫካ ስራ አስፈፃሚዎችን በቁጥጥር ስር አውለን ምርመራ ጀምረናል ሲል የራስ አበበ አረጋይ ክፍለጦር የህዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ ፋኖ ሽታው አሻግሬ ለኮሩ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ክፍል በላከው መረጃ አስታውቋል። ክፍለጦሩ የዘራፊዎችን ስም ዝርዝር ይፋ ያደረገ ሲሆን፣ 1ኛ. አይዳኝሁም አሰፋው 2ኛ. አይናለም ግዛው እና 3ኛ. ብሩክ አስፋው  የተባሉትን የብልፅግና ተላላኪ ዘራፊዎችን በመግለፅ የታገቱ ግለሰቦችን ከፍተኛ ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ በማስለቀቅ በዘራፊዎች የተወሰደባቸውን 400,000ብር ሲያስመልስ ተበዳዮችም ለክፍለጦሩ ምስጋናቸውን ማቅረባቸውን አርበኛው በመልዕክቱ አስታውቋል። ። ይሕ በእንዲሕ እንዳለ በዛሬው ዕለት በፊቸ ሰላሌ ወረዳ እንጓለላና ሸበል ፋጢ ቀበሌወች ላይ የስርዓቱ ሌላኛው ዘራፊ ቡድን የሆነው የኦሆዴድ ብልፅግናው የጫካው ክንፍ በመሆን ከአገዛዙ ጋር ተናቦ እየሰራ የሚገኘው እራሱን ኦነግ ሸኔ ብሎ የሚጠራው ዘራፊ ቡድን እንደለመደው የጥፋት አላማውን አንግቦ ህፃናትንና ሸማግሌዎችን ለመግደልና ዝርፊያ ለመፈፀም አቅዶ የመጣ ቢሆንም ነገር ግን አናብስቶቹ የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የራሰ አበበ አረጋይ ክፍለጦር የአርበኛ አሊ ሻለቃ እና የቀጠናው የሚገኘው የአርበኞች ጦር ሰራዊት ከበባ ውሰጥ በማሰገባት ሲቀጠቀጥ ያረፈደ ሲሆን የተረፈው እግሬ አውጭኝ ብሎ ሲፈረጥጥ ይዞት የመጣውን ከብልፅግና የተበረከተለትን አዲስ ብሬንና ከነ ሸንሸሉ ከያዘው ተተኳሽ ጋር ለጀግኖቹ የራስ አበበ አረጋይ ክፍለጦር  አስረክቦ መፈርጠጡን ክፍለጦሩ በግንባር መረጃው አስታውቋል። ክብርና ሞገስ ለትግሉ ሰማዕታት!!           ድል ለፋኖ!! አንድነታችን አሸናፊነታችን!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የአፄ አምደ ፂዮን ኮር ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ክፍል   መጋቢት 14 /2018 ዓ.ም

"ያ ቀበቶውን ሳይቀር እናስፈታዋለን ተብሎ ተፎክሮበትና ከምድር ጦር እስከ ሰማይ ጄትና ድሮን ተዘምቶበት የነበረው አማራ፡ ዛሬ ላይ ደርቦ ደራርቦ ማራኪ፣ መርጦ መራርጦ ማርኮ ታጣቂ ሆኗል። አጃኢብ ነ
+1
"ያ ቀበቶውን ሳይቀር እናስፈታዋለን ተብሎ ተፎክሮበትና ከምድር ጦር እስከ ሰማይ ጄትና ድሮን ተዘምቶበት የነበረው አማራ፡ ዛሬ ላይ ደርቦ ደራርቦ ማራኪ፣ መርጦ መራርጦ ማርኮ ታጣቂ ሆኗል። አጃኢብ ነው!" 14/ዐ7/2018 ዓ.ም

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea - Telegram kanali @httpsuykzrgfszrnjnjfk statistikasi va tahlili