በናያስ | Benaiah
Kanalga Telegram’da o‘tish
526
Obunachilar
-124 soatlar
-17 kun
+830 kun
Postlar arxiv
የእግዚአብሔር ቃል በልባችን ይኑር
መንፈሳዊ ጦርነት በእምነት ልናረገው የሚገባ ጦርነት ነው፡፡ ጠላት ሁል ጊዜ ስለእግዚያብሄር ያለንን ትክክለኛ የሆነ አመለካከት ሊሸረሽር ይፈልጋል፤ እሱ ብቻ ሳይሆን ከእግዚያብሄር የተሻለ ነገር እንዳለ እንድናስብ በማድረግ ከእውነት መንገድ ሊያወጣን ይጥራል፡፡ ይህን የጠላትን ውሸት ልንቃወመው የምንችልበት ብቸኛው መንገድ እውነት ሲሆን፡ ያም እውነት የእግዚያብሄር ቃል ነው፡፡ በኤፌሶን 6፡17 ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ የእግዚያብሄርን ቃል እንደ መንፈስ ሰይፍ እንድንጠቀመው ይነግረናል፡፡ ይህም ሰይፍ ከጠላት ጋር ባለን ውጊያ እንደማጥቂያም፣ እንደመከላከያም ልንጠቀመው እንችላለን።
ሰይፍን በሚገባ ለመጠቀም አጠቃቀሙን ማወቅ እንደሚያስፈልገን ሁሉ የጠላትንም ፈተና በተገቢው መንገድ ለመመከት የእግዚያብሄርን ቃል እንዴት መጠቀም እንዳለብን ልናቅ ይገባናል፡፡ ይህንን ደግሞ ከክርስቶስ በደንብ እንማራለን፡፡ ኢየሱስ በማቴዎስ 4 ላይ በገጠመው የጠላት ፈተና፡ በልቡ ከታተመው የእግዚአብሔር ቃል በማውጣት “ተብሎ ተፅፏል” በሚል ሁሉንም ሙከራ ሲመክተው እንመለከታለን። የእግዚያብሄርን ቃል በመረዳት በህይወታችን ስንተገብረው የሰይጣንን ፈተና በድል እናልፋለን፡፡ ከሁሉ በላይ ግን ያ ህያው የሆነው የእግዚያብሄር ቃል በእኛ ልብ ውስጥ መታተም አለበት፡፡
ይህም ዘወትር መጽሐፍ ቅዱስን የማጥናት አስፈላጊነት ወደሚለው ሃሳብ ይወስደናል። ጠላት ልክ ኢየሱስ አርባ ቀንና ሌሊት ጾሞ በስጋ እጅግ በደከመው ሰዓት ሊፈትነው እንደቀረበ፡ እኛም በድካማችን ሰዓት ለፈተና ይበልጥ ተጋላጭ ነን። ስለዚህም የእግዚያብሄርን ቃል ሁል ግዜ በማጥናትና በማሰላሰል በልቦቻችን ጽላት መቅረጽ አለብን። በዚህም በድካማችንም ሰዓት ቢሆን በውስጣችን ከሰረጸው ህያው የሆነው የእግዚያብሄር ቃል በማውጣት፡ “ተብሎ ተጽፏል” እያልን የጠላትን ፈተና እናሸንፋለን።
ስለዚህ ርዕስ በጥልቀት ከኛ ጋር ይረዱ።
Instagram | Facebook | Threads
LinkedIn | Twitter | Website
#የጥሞናፅሁፍ #የመንፈስሰይፍ #የእግዚአብሔርዕቃጦር
@Benaiah_Amharic
