515
订阅者
无数据24 小时
无数据7 天
-930 天
帖子存档
አዲስ ዓመት፤ አዲስ ጅምር
አዲስ ዓመት ስንል የቁጥር መለወጥ ብቻ አመልካች አይደለም ይልቁንስ ከፈጣሪ ጋር በአዲስ መንፈስ ለመጓዝ የተሰጠ ድንቅ ዕድል እንጂ። በኢሳይያስ 43:19 ላይ "እነሆ፥ አዲስ ነገርን አደርጋለሁ" ተብሎ እንደተጻፈው፣ ያለፉትን ውድቀቶች፣ ስህተቶችና ተስፋ መቁረጦችን ወደኋላ ጥለን በሙሉ እምነት ወደፊት ልንራመድ ይገባል። ብዙ ጊዜ አዲስ ዓመትን የምንጀምረው "አምላክ የእድል በሬን ይክፈትልኝ" በሚል የውጭ ለውጥ ጥያቄ ነው፤ ነገር ግን እውነተኛው አዲስ ነገር የሚጀምረው በሮች ሲከፈቱ ሳይሆን፣ በእነዚያ የተዘጉ በሮች ፊት ቆመን እንክዋን ፈጣሪ የውስጥ ማንነታችንን፣ ትዕግስታችንን እና ባህሪያችንን እንዴት እንደቀረጸው ስንረዳ ነው።
ስለዚህ አምላካችንን አካባቢዎቻችንን ብቻ እንዲለውጥልን ሳይሆን ልባችንን እንዲያድስ፣ እምነታችንን እንዲያጠነክር፣ ውሳኔዎቻችንን እንዲመራና ለእርሱ ክብር የተፈጠርንበትን ዓላማ እንድንኖር እንጠይቀው። ባለፈው ዓመት ያቀድናቸው ሕልሞቻችን ሳይሳኩ ቢቀሩም አንፍራ፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር አዲሱን መልካም ታሪካችንን የሚጀምረው ባልተሳኩት ሕልሞቻችን ላይ አዲስ ተስፋ በመስጠት ነው። በዚህ አዲስ ዓመት እምነታችን የጠለቀ፣ ጸሎታችን የበረታ፣ ታዛዥነታችን የላቀ፣ ልባችንም ወደ አምላክ እጅግ የቀረበ ይሁን፤ ምንም እንክዋን አዲስ ዓመት አዲስ ጅምር ቢሆንም አምላካችን ግን ያው የማይለወጥ ታማኝ አምላካችን ነው።
#Devotional #Graphics #NewYears #SpecialTheme
@Benaiah_Org
