uz
Feedback
Ethiopian Business Network

Ethiopian Business Network

Kanalga Telegram’da o‘tish

የኢትዮጵያ ብቸኛ የስራ ፈጠራ መድረክ! ማንኛውንም ፕሮጀክት፣ ሃሳብ ለህዝብ በማድረስ አዳዲስ ድርጅቶችን ለማቋቋም የነፃ እገዛ እናደርጋለን! ያነጋግሩን!

Ko'proq ko'rsatish
4 355
Obunachilar
-224 soatlar
-147 kun
-5730 kun
Postlar arxiv
ከኤርትራ እና ከግብፅ ጋር የተጣመረቸው ሱዳን ወደ ኢትዮጲያ ድንበር ሮኬቶችን እያስጠጋች ነው በአልቡርሃን የሚመራው የሱዳን ጦር በመተማ በኩል ሮኬቶችን ጭና አቅጣጫውን ወደ ኢትዮጵያ አድርጋ ማስጠጋቷ
ከኤርትራ እና ከግብፅ ጋር የተጣመረቸው ሱዳን ወደ ኢትዮጲያ ድንበር ሮኬቶችን እያስጠጋች ነው በአልቡርሃን የሚመራው የሱዳን ጦር በመተማ በኩል ሮኬቶችን ጭና አቅጣጫውን ወደ ኢትዮጵያ አድርጋ ማስጠጋቷን ከወታደራዋ ምንጮች የተገኘው መረጃ ያመላክታል። ኤርትራ በግልፅ ኢተዮጲያ ላይ ጦርነት አውጃ ባለችበት በዚህ ወቅት፣ ሱዳን የጦር መሳሪያ ወደ ኢትዮጲያ ማስጠጋቷ፣ ኢትዮጲያን በጋራ የማጥቃት እና ተረባርቦ ከአገር ወሰጥ ባንዶች ጋር የማፍረስ ህልም አካል ነው ተብሏል። https://t.me/addisreporter2

ሰበር ዜና‼️ የኤርትራ ጦር የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጦ መግባቱ ተሰማ። የአፋር ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አወል አርባ ከአልጀዚራ አረብኛው ክፍል ጋር ባደረጉት ቆይታ የኤርትራ ጦር ወደ አፋር ክልል መግ
ሰበር ዜና‼️ የኤርትራ ጦር የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጦ መግባቱ ተሰማ። የአፋር ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አወል አርባ ከአልጀዚራ አረብኛው ክፍል ጋር ባደረጉት ቆይታ የኤርትራ ጦር ወደ አፋር ክልል መግባቱንና በአፋር በኩል እየተደረገ ባለው ውጊያ ላይ እየተሳተፈ መሆኑን ይፋ አድርገዋል። የኤርትራ ጦር የኢትዮጵያን ድንበር መጣሱን በኢትዮጵያ በኩል በይፋ የተናገሩ ባለስልጣን ሲል አቶ አወልን የገለጻቸው አልጀዚራ ኢትዮጵያን፣ ኤርትራን እና ጅቡቲን የሚያዋስነውን ስፍራ የሻብያ ሰራዊት እንደገባ ጠቅሷል።

ብሔራዊ ባንክ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ወለድን አስቀድመው እንዳይከፍሉ አዘዘ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት በጻፈው ደብዳቤ በቅርቡ ባካሄደው የቁጥጥር ሥራ በአንዳንድ ተቋማት
ብሔራዊ ባንክ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ወለድን አስቀድመው እንዳይከፍሉ አዘዘ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት በጻፈው ደብዳቤ በቅርቡ ባካሄደው የቁጥጥር ሥራ በአንዳንድ ተቋማት የጊዜ ተቀማጭ ሒሳብ ላይ ወለድን አስቀድሞ የማስላትና የመክፈል ሂደት መኖሩን ማረጋገጡን ገልጿል። ተቋማቱ በመጀመሪያው ቀን ወለዱን አስልተው እንደሚከፍሉና ከዋናው ገንዘብ ጋር የማዳመር ሥራ እንደሚሰሩ ገልጾ ይህም የደንበኛን ሂሳብ ጊዜው ሳይደርስ ያለ ኢኮኖሚያዊ ምክንያት እንዲጨምር የሚያደርግ ነው ብሏል። ባንኩ ይህ አሠራር ገበያውን የሚያዛባ፣ ጤናማ ያልሆነ ውድድር የሚያባብስና የፋይናንስ ተቋማትን አሠራር የሚያዳክም መሆኑን አክሎ ገልጿል። በዚህ መሠረትም የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ወለድን አስቀድሞ አስልቶ ለተቀማጭ ገንዘብ ባለቤቶች መክፈል፤ እና ወለድን ከዋናው ገንዘብ ጋር ጊዜው ከመድረሱ በፊት ማዋሃድ በአስቸኳይ እንዲያቆሙ አስጠንቅቋል። ===========

የበጎ ፈቃደኞች ጥሪ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የቱሪዝም ሚኒስቴር ምድረ ቀደምት ኢትዮጵያ | Ethiopia: Land of Origins ! የበጎ ፈቃደኞች ጥሪ – የቱሪዝም እና ኬተሪንግ አገልግሎት አስቸኳይ ጥሪ ❗️ ለCPHIA 2026፣ ለ40ኛው መደበኛ የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ እና ለCOP32 የቱሪዝም ሚኒስቴር የበጎ ፈቃድ ካዴቶች የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በቱሪዝም ሚኒስቴር አማካኝነት በቅርቡ የሚካሄዱ ሶስት ታላላቅ ዓለም አቀፍ መድረኮችን በተሳካ ሁኔታ ለመደገፍ ዝግጅት ላይ ይገኛል። የሚካሄዱ ዓለም አቀፍ መድረኮች ፦ • የአፍሪካ የህዝብ ጤና ዓለም አቀፍ ጉባኤ (CPHIA 2026)፦ 23–27 ኖቬምበር 2026 • 40ኛው መደበኛ የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ፦ 8–15 ፌብሩወሪ 2027 • 32ኛው የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP32)፦ ኖቬምበር 2027 ኢትዮጵያ በእነዚህ ታላላቅ ዓለም አቀፍ መድረኮች ወቅት የቱሪዝምና የኬተሪንግ አገልግሎቶችን ለማጠናከር የቱሪዝም ሚኒስቴር ብቁ ኢትዮጵያዊያን የቱሪዝም፣ኬተሪንግ እና መስተንግዶ የበጎ ፈቃድ ካዴቶች እንዲሆኑ ይጋብዛል። የሚመረጡ በጎ ፈቃደኞች ዓለም አቀፍ እንግዶችን በመቀበል ፣ ኢትዮጵያን የመነሻዎች ምድር (Land of Origins) በማስተዋወቅ፣ የቱሪዝም መረጃ በመስጠት፣ የኬተሪንግ፣ የመስተንግዶ አገልግሎቶችን በመደገፍ እና ጎብኚዎች ደህንነታቸው የተጠበቀ፣ የማይረሳ እና ዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው ተሞክሮ እንዲያገኙ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ። ሁሉም አመልካቾች ከምደባ በፊት የማጣራት፣ የምርጫ፣ የስልጠና እና የምደባ ሂደት ያልፋሉ። 1. የሥራ ሚናዎች እና ኃላፊነቶች የሚመረጡ የቱሪዝም የበጎ ፈቃድ ካዴቶች ልዩ ስልጠና ተቀብለው በሚከተሉት መስኮች ሊመደቡ ይችላሉ፦ • በአየር ማረፊያዎች፣ ሆቴሎች እና የጉባኤ ማዕከላት ዓለም አቀፍ ልዑካንንና ጎብኚዎችን መቀበል እና መርዳት። • የቱሪዝም መረጃ፣ የመዳረሻ ምክር እና የአቅጣጫ መመሪያ መስጠት። • የካተሪንግና የምግብ ጥራት ቁጥጥር አገልግሎት • የኢትዮጵያን ብሔራዊ መለያ ምድረ ቀደምት ኢትዮጵያ (Land of Origins) እና ባህላዊና ተፈጥሯዊ ቅርሶቿን ማስተዋወቅ። • በተመደቡ የሆቴል ክላስተሮች የእንግዳ ግንኙነትና የመስተንግዶ አገልግሎት መደገፍ። • የጎብኚ መረጃ ማዕከላት፣ የአክሬዲቴሽን ዴስኮች እና የቱሪዝም ድጋፍ ማዕከላትን ማገዝ። • የባህል ፕሮግራሞች፣ የከተማ ጉብኝቶች፣ ኤግዚቢሽኖች እና የቱሪዝም ፕሮሞሽን ተግባራትን መደገፍ። • ከቱሪዝም ሚኒስቴር፣ ሆቴሎች፣ የጉዞ ኦፕሬተሮች እና የዝግጅት አስተዳደር ቡድኖች ጋር መተባበር። • በሁሉም ዝግጅቶች የኢትዮጵያን እንግዳ ተቀባይነት፣ ሙያዊነት እና የላቀ የአገልግሎት ጥራት ማሳየት። • እንዲሁም የሚከናወኑ ዓለም አቀፍ ኹነቶችን የመደገፍ ተግባራትን 2. የመመዝገቢያ መስፈርቶች (እነዚህ መስፈርቶች በዓለም አቀፍ የበጎ ፈቃድ መመዘኛዎች እና በUNFCCC የበጎ ፈቃድ ማዕቀፍ መሠረት ተዘጋጅተዋል።) * ዜግነት፦ የኢትዮጵያ ዜጋ መሆን አለበት። * የቋንቋ ችሎታ፦ * የእንግሊዝኛ ቋንቋ ብቃት ግዴታ ነው። * ከUN ኦፊሴላዊ ቋንቋዎች (አረብኛ፣ ቻይንኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ ሩሲያኛ ወይም ስፓኒሽ) አንዱን ወይም ከዚያ በላይ ማወቅ ተጨማሪ ጥቅም ነው። * የኢትዮጵያ አካባቢ ቋንቋዎችን ማወቅ ተጨማሪ ጥቅም ነው። ትምህርት ፦ * እውቅና ባለው ዩኒቨርሲቲ፣ ኮሌጅ ወይም TVET ተማሪ ወይም ተመራቂ መሆን አለበት። * በቱሪዝም፣ በመስተንግዶ፣ በሆቴል አስተዳደር፣ በቋንቋ ፣ በኮሙኒኬሽን፣ በማርኬቲንግ፣ በታሪክ፣ በቅርስ፣ በጂኦግራፊ ወይም ተዛማጅ ዘርፎች የሚማሩ ወይም የተመረቁ እንዲያመለክቱ ይበረታታሉ። • የቀድሞ ልምድ፦ * የቀድሞ ሙያዊ ልምድ አያስፈልግም። * በቱሪዝም፣ በመስተንግዶ፣ በጉባኤዎች፣ በፌስቲቫሎች ወይም በማህበረሰብ ዝግጅቶች የበጎ ፈቃድ ወይም የደንበኛ አገልግሎት ልምድ መኖሩ ተጨማሪ ጥቅም ነው። 3. አመልካቾች የሚከተሉትን ለማከናወን ፈቃደኛ መሆን አለባቸው ፦ • ሁሉንም ግዴታ ያለባቸውን ስልጠናዎች እና የልምምድ መርሃ ግብሮች መሳተፍ። • በተመደበት የዝግጅት ጊዜ ሙሉ ጊዜ ተገኝቶ ማገልገል። • ቅድመ ዝግጅት ኦሪየንቴሽን እና ከዝግጅት በኋላ የግምገማ ሂደቶች መሳተፍ። • በተለዋዋጭ ፈረቃ፣ የሳምንት መጨረሻና የምሽት ሰዓት ጨምሮ መስራት። • በአየር ማረፊያዎች፣ ሆቴሎች፣ የቱሪስት መስህቦች፣ የጉባኤ ማዕከላት እና የጎብኚ አገልግሎት ማዕከላት መመደብን መቀበል። • የቡድን ስራ፣ ተለዋዋጭነት፣ የባህል ስሜት እና የስሜት ብልህነት ማሳየት። • የደህንነት፣ የአደጋ ምላሽ እና የኦፕሬሽን መመሪያዎችን መከተል። • ያለ የገንዘብ ክፍያ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መስጠት። 4. ሙያዊ ሥነ-ምግባር ፦ የቱሪዝም የበጎ ፈቃድ እጩዎች የሚከተሉትን ማሳየት ይጠበቅባቸዋል፦ • ሙያዊነት እና ሰዓት አክባሪነት • ታማኝነት እና ሥነ-ምግባራዊ ባህሪ • የላቀ የደንበኛ አገልግሎት እና እንግዳ ተቀባይነት • ለባህል ልዩነት እና ለአካታችነት ክብር • የእንግዶችን እና ጎብኚዎችን መረጃን በሚስጥር እና በኃላፊነት መያዝ • የኢትዮጵያን የቱሪዝም ገፅታ እና ብሔራዊ እሴቶች በአዎንታዊ መንገድ መወከል 5. የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ጥቅሞች በተሳካ ሁኔታ የሚያጠናቅቁ በጎ ፈቃደኞች የሚከተለውን ያገኛሉ፦ • የአገልግሎት ምስክር ወረቀት፦ የተመደበውን ተግባር በተሳካ ሁኔታ ላጠናቀቁ በጎ ፈቃደኞች በቱሪዝም ሚኒስቴር የተሰጠ ኦፊሴላዊ የአገልግሎት ምስክር ወረቀት ይሰጣቸዋል። የኢትዮጵያ ቱሪዝም ሚኒስቴር ምዝገባ ቦታ፡- አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ቦሌ ጃፓን ዳይመንድ ሆቴል አጠገብ በአካል እና በኦንላይን መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የቡርኪናፋሶው ፕሬዝዳት ኢብራሂም ትራውሬ ለሀገራቸውን ተዋግተው ለተሰው ወይም ለተጎዱ ወታደር ቤተሰቦች የነፃ ማህበራዊ አገልግሎት ማለትም የጤና፣የትምህርት እና የትራንስፖርት አገልግሎቶችን በነፃ ተጠ
የቡርኪናፋሶው ፕሬዝዳት ኢብራሂም ትራውሬ ለሀገራቸውን ተዋግተው ለተሰው ወይም ለተጎዱ ወታደር ቤተሰቦች የነፃ ማህበራዊ አገልግሎት ማለትም የጤና፣የትምህርት እና የትራንስፖርት አገልግሎቶችን በነፃ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚፈቅድ ህግ አጸደቁ።

አሜሪካ በህወሓት ላይ ከፍተኛ ቁጣዋን ገለጸች‼️ ተጨማሪ ኃይለኛ ማዕቀቦችን እንደምትጥልም ዝታለች! በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ጄ. ማሲንጋ ዛሬ ባወጡት እጅግ ጠንካራ መግለጫ የህወሓት አ
አሜሪካ በህወሓት ላይ ከፍተኛ ቁጣዋን ገለጸች‼️ ተጨማሪ ኃይለኛ ማዕቀቦችን እንደምትጥልም ዝታለች! በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ጄ. ማሲንጋ ዛሬ ባወጡት እጅግ ጠንካራ መግለጫ የህወሓት አመራሮች የጀመሩትን አዲስ እና መጠነ ሰፊ ጥቃት አጥብቀው ኮንነዋል። አምባሳደሩ የቡድኑን እርምጃ "ማሸነፍ የማይቻልበት እና ለህዝብ ምንም የማይፈይድ አደገኛ ውሳኔ" ሲሉ አጣጥለውታል። በቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ አደራዳሪነት በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር የተጀመረውን የሰላም ውይይት ወደ ጎን በመተው ህወሓት ዳግም ወደ ጦርነት ማምራቱ አሜሪካን ክፉኛ አሳዝኗል። ይህንኑ ተከትሎም ሌሎች ታጣቂ ቡድኖች ከዚህ እብደት እና የጥፋት ጦርነት እራሳቸውን እንዲያርቁ እና ከስህተቱ እንዲማሩ አምባሳደሩ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ አስተላልፈዋል። በ2026 ዓመት መጀመሪያ ላይ በህወሓት አመራሮች ላይ ማዕቀብ መጣሏን ያስታወሰችው አሜሪካ፣ ኢትዮጵያን ወደ ተሳሳተ አዘቅት በሚገፉ ተጨማሪ አመራሮች ላይም ኃይለኛ ማዕቀብ ለመጣል የሚያስችል ሙሉ አቅምና መሳሪያ እንዳላት አስጠንቅቃለች። ምንም እንኳን አሜሪካ ይህን የቅጣት በትር ለማሳረፍ ዝግጁ መሆኗን ብታሳውቅም፣ አሁንም ቢሆን ከጥፋቱ ለመመለስ ትክክለኛው መንገድ ምክንያታዊ የሆነ የፖለቲካ ውይይት ማድረግ ብቻ መሆኑን አምባሳደር ማሲንጋ በአፅንዖት አሳስበዋል።

ሰበር ዜና ጀነራል ምግበይ ታገዱ! የህወሃት ሴንትራል ኮማንድ በምዕራብ ግንባር ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ ጀነራል ምግበ ኃይሌ ላይ የእገዳ ውሳኔ ማሳለፉ ተሰማ። የህወሃት ቁልፍ ወታደራዊ አዛዥ በመባል
ሰበር ዜና ጀነራል ምግበይ ታገዱ! የህወሃት ሴንትራል ኮማንድ በምዕራብ ግንባር ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ ጀነራል ምግበ ኃይሌ ላይ የእገዳ ውሳኔ ማሳለፉ ተሰማ። የህወሃት ቁልፍ ወታደራዊ አዛዥ በመባል የሚታወቁት ጀነራል ምግበ ኃይሌ ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ እና ከኃላፊነት ተገልለው እንዲቆዩ በትግራይ ሴንትራል ኮማንድ ውሳኔ የተላለፈባቸው መሆኑን የመረጃ ምንጮችን ጠቅሶ አውራምባ ታይምስ ዘግቧል። ጀነራል ምግበ ኃይሌ በምዕራብ ግንባር አዛዥነት በሽሬ ቀጠና፣ በሱዳን እና በኢትዮጵያ ድንበር፣ በሸረሪ፣ በሰሞኑ በጸሊሞይ እና ደደቢት፣ እንዲሁም ቀደም ሲል በሽራሮ ግንባር የሚገኙ የህወሓት ታጣቂዎችን በበላይነት ሲመሩ የቆዩ ናቸው። ጀነራሉ ከኃላፊነት እንዲባረሩ የተደረገው በእነዚህ ግንባሮች በተፈጸሙ ጥቃቶችና በደረሰባቸው ከፍተኛ ወታደራዊ ኪሳራ ምክንያት ባለፈው ሳምንት ጀምሮ ሲካሄድ በቆየው ከፍተኛ ግምገማ እንደሆነ ተገልጿል። ጀነራል ምግበ ኃይሌ ከተነሱ በኋላ የምዕራብ ግንባር አዛዥነት ቦታን በጊዜያዊነት የአርሚ 42 አዛዥ የነበሩት ጀነራል አብርሃ ተስፋዬ (አብርሃ ዲንኮል) እንዲረከቡት ተደርጓል። በሌላ በኩል፣ የቀድሞው የትግራይ ክልል ፖሊስ አዛዥ ጀነራል ገብረ አድሃና (ጀነራል ገብረ ድላ) ከትግራይ አምልጠው አዲስ አበባ መግባታቸው ታውቋል። ይህንን ተከተሎም ህወሓት በትግራይ ውስጥ የሚገኙና አሁን በዘመቻ ላይ የማይሳተፉ ወታደራዊ አዛዦች እንዲሁም የፖሊስ መኮንኖች በጥብቅ ክትትል እንዲደረግባቸው አዲስ መመሪያ ማስተላፉ ተጠቅሷል።

የህወሃት ታጣቂዎች በድሮን ጥቃት ምክንያት የጦር መሳሪያዎችን በጋማ ከብቶች ማንቀሳቀስ መጀመራቸው ተገለጸ‼ የህወሃት ታጣቂዎች ተተኳሾችን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለማንቀሳቀስ የጋማ ከብቶችን እየተ
+1
የህወሃት ታጣቂዎች በድሮን ጥቃት ምክንያት የጦር መሳሪያዎችን በጋማ ከብቶች ማንቀሳቀስ መጀመራቸው ተገለጸ‼ የህወሃት ታጣቂዎች ተተኳሾችን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለማንቀሳቀስ የጋማ ከብቶችን እየተጠቀሙ ይገኛሉ። ከላይ የማታየው ምስል በሰቆጣ አቅጣጫ ተተኳሽ ከሰሞኑ በራያ አካባቢዎች የጋሪ ፈረሶችን ጭምር ሲወስዱ ነበር ተብሏል። እዚህ በምስሉ የሚታዩት ራሱን የትግራይ ሰላም ሰራዊት ብሎ በሚጠራ ኃይል ዛሬ ማለዳ ከህውሃት ታጣቂዎች ላይ የተወሰዱ መሆኑም ተነግሯል።

❤️አስቸኮይ የሚሸጥ ቅናሽ ባለ 2 መኝታ ኮንዶሚንየም❤️ በኮዬ 2 ኮንደሚንየም ሳይት ላይ የሚገኝ 👉ፕሮጀክት - 16 🎷ስፋት_ 88ካሜ 🎷ባለ _ 2 መኝታ ቤት 🎷ይዞታ _ የእጣ 👉7ኛ - ወለል
+5
❤️አስቸኮይ የሚሸጥ ቅናሽ ባለ 2 መኝታ ኮንዶሚንየም❤️ በኮዬ 2 ኮንደሚንየም ሳይት ላይ የሚገኝ 👉ፕሮጀክት - 16 🎷ስፋት_ 88ካሜ 🎷ባለ _ 2 መኝታ ቤት 🎷ይዞታ _ የእጣ 👉7ኛ - ወለል 🎷 ዋጋ - 5,200,000 🎷ኮምሽን 2% የሚሸጥ ወይም የሚከራይ ቤት መኪና መጋዘን ወይም ቦታ ከሎት ይደውሉልን ወይም ይፃፉልን። ☎️ 0913565998 ☎️ 0991213676 https://t.me/Addislembosa

በጀሞ1 ለሽያጭ የቀረበ ባለ2 መኝታ 🧣64ካሬ 🔹4ኛ ፍሎር 🔹አስፓልት ጊቢ 🔹ጥግ ላይ የራሱ ቨረንዳ ያለው 🔹ሙሉ ሴራሚክ የተሰራ 🔹ዘመናዊ ቁምሳጥን 🔹ኪችን ካቢኔት አለው 🔹ምርጥ ቦታ ላይ
+9
በጀሞ1 ለሽያጭ የቀረበ ባለ2 መኝታ 🧣64ካሬ 🔹4ኛ ፍሎር 🔹አስፓልት ጊቢ 🔹ጥግ ላይ የራሱ ቨረንዳ ያለው 🔹ሙሉ ሴራሚክ የተሰራ 🔹ዘመናዊ ቁምሳጥን 🔹ኪችን ካቢኔት አለው 🔹ምርጥ ቦታ ላይ የሚገኝ 🔹ካርታ ይዟል 👉👉..የመሸጫ ዋጋ 6 ሚሊየን ብር ⏰⏰ማየት ሲፈልጉ ቀድመው ቀጠሮ ያሲዙን ☎️... +251944742424 +251920039447 ✅ ሲገዙ 2% ኮሚሽን ይከፍሉናል 🗑🗑🗑🗑🗑🗑🗑🗑🗑🗑🗑🗑🗑🗑🗑 🕰🕰🕰🕰🕰🕰🕰🕰🕰🕰🕰🕰🕰🕰🕰 https://t.me/Addislembosa

የአገልግሎት ክፍያ ማሻሻያ‼️ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወረዳ ደረጃ ለነዋሪዎች አገልግሎት የሚጠይቀው የአገልግሎት ክፍያዎች ላይ ጭማሪ ተደርጓል። አዲስ ዲጂታል መታወቂያ ለመስጠት እና ዲጂታል
የአገልግሎት ክፍያ ማሻሻያ‼️ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወረዳ ደረጃ ለነዋሪዎች አገልግሎት የሚጠይቀው የአገልግሎት ክፍያዎች ላይ ጭማሪ ተደርጓል። አዲስ ዲጂታል መታወቂያ ለመስጠት እና ዲጂታል መታወቂያ በወቅቱ ለማደስ 300 ብር፣የእድሳት ጊዜ ያለፈበት መታወቂያ ለማደስ እና በተለያየ ምክንያት የተበላሸ ዲጂታል መታወቂያ ለመቀየር 600 ብር፣ያላገባ አገልግሎት 400 ብር፣ለትውልደ ኢትዮጵያን ያላገባ አገልግሎት ለማግኘት 800 ብር ይከፍላሉ።

በአዲስ አበባ የመንግሥት ሠራተኞች የማኅበር ቤት ግንባታ መነሻ ዋጋ በካሬ ሜትር ወደ 50 ሺህ ብር ከፍ አለ❗❗ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራት የሚገነቡ መኖሪያ ቤቶች
በአዲስ አበባ የመንግሥት ሠራተኞች የማኅበር ቤት ግንባታ መነሻ ዋጋ በካሬ ሜትር ወደ 50 ሺህ ብር ከፍ አለ❗❗ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራት የሚገነቡ መኖሪያ ቤቶች መነሻ የግንባታ ዋጋ በካሬ ሜትር ከነበረበት 35 ሺህ ብር ወደ 50 ሺህ ብር ከፍ እንዲል አድርጓል። የዋጋ ጭማሪውን መሸከም ባለመቻላቸው ከማኅበሩ ለመውጣትና የተከፈለውን ገንዘብ ለመመለስ የጠየቁ መምህራን ደግሞ "ገንዘቡ አይመለስላችሁም" መባላቸው ቅሬታን ፈጥሯል። የከተማ አስተዳደሩ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ምክትል ሀላፊ ዶ/ር መኮንን ጥበቡ ቸኮል ለኅብረት ሥራ ኮሚሽን በጻፉት ደብዳቤ መሠረት፣ በታህሳስ ወር 2017 ዓ.ም በካሬ ሜትር 35 ሺህ ብር የነበረው የመነሻ ግንባታ ዋጋ በመስከረም ወር 2018 ዓ.ም በተደረገ ክለሳ ወደ 50 ሺህ ብር ከፍ እንዲል ተወሰኗል። በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በተጠናው ወቅታዊ ጥናት መሠረት ደግሞ አንዳንዶቹ የግንባታ ተመኖች በካሬ ሜትር እስከ 82 ሺህ ብር ይደርሳሉ። አስተዳደሩ ለመምህራን እና ለጤና ባለሙያዎች መሬት በነፃ በማቅረብ 25 በመቶ ቅድመ ክፍያ በሠራተኞች እንዲሸፈን እና ቀሪው 75 በመቶ በባንክ ብድር እንዲመቻች ባደረገው መርሃ-ግብር፣ 6 ሺህ 194 መምህራን በ57 ማኅበራት ተደራጅተው መሬት ተረክበው ነበር። ሆኖም መምህራኑ የመጀመሪያውን የ25 በመቶ ቅድመ ክፍያ የከፈሉት ከወርሃዊ ደመወዛቸው በተጨማሪ በብድር እና በቤተሰብ ድጋፍ እንደነበር ገልጸው፣ አዲሱ ጭማሪ ከገቢያቸው አንጻር ሊሸከሙት የማይችሉት መሆኑን አስረድተዋል። በዚህም ምክንያት ጭማሪውን መክፈል ባለመቻላቸው "ገንዘባችን ተመልሶልን ከማኅበሩ እንውጣ" ብለው የጠየቁ አባላት "ገንዘቡ አይመለስላችሁም" የሚል ምላሽ ስለተሰጣቸው ለከፍተኛ ስጋትና ቅሬታ ተዳርገዋል።

ፌደራል ፖሊስ ተረክቧል‼ ከ46.4 ሚሊዮን ብር በላይ በሚገመቱ ተሽከርካሪዎች የተፈጸመ ከባድ የማታለል ወንጀል ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር ዋለ‼ ከግል ተበዳይ ዮናስ ገብረመስቀል 12 የBYD Seagull
+3
ፌደራል ፖሊስ ተረክቧል‼ ከ46.4 ሚሊዮን ብር በላይ በሚገመቱ ተሽከርካሪዎች የተፈጸመ ከባድ የማታለል ወንጀል ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር ዋለ‼ ከግል ተበዳይ ዮናስ ገብረመስቀል 12 የBYD Seagull ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በውክልና ተረክቦ በመሸጥ፣ ገንዘቡን ሳይመልስ ከሀገር የተሰወረው ሰልማን መሀመድ የተባለው ግለሰብ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ። ዋና ዋና ነጥቦች፦ 📌ተጠርጣሪው በታይላንድ፣ ሲንጋፖር፣ ፊሊፒንስ እና ኢንዶኔዥያ ሲዘዋወር የቆየ ሲሆን፣ በወጣበት ዓለም አቀፍ የቀይ ማስታወቂያ (Red Notice) መሠረት በኢንዶኔዥያ ተይዟል። 📌 ተጠርጣሪው መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ተላልፎ ተሰጥቷል። 📌 ከዚህ ወንጀል በተጨማሪም ግለሰቡ በሌሎች ሁለት ከባድ የማታለል ወንጀሎች ተጠርጥሮ ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገበት ይገኛል። የፌደራል ፖሊስ ለኦፕሬሽኑ መሳካት አስተዋጽኦ ላደረጉት ለአዲስ አበባ ፖሊስ፣ ለኢንዶኔዥያ ፖሊስ እና ለኢንተርፖል ምስጋና አቅርቧል።

የኢትዮጵያ ፓስፖርት የዓለም አቀፍና አህጉራዊ ደረጃ ይፋ ሆነ‼ የኢትዮጵያ ፓስፖርት በዓለም አቀፍ ደረጃ 173ኛ፣ በአፍሪካ ደግሞ 49ኛ ደረጃን ይዟል።የፓስፖርቱ ቁልፍ መረጃዎች፡- 📌የኢትዮጵያ ፓስ
የኢትዮጵያ ፓስፖርት የዓለም አቀፍና አህጉራዊ ደረጃ ይፋ ሆነ‼ የኢትዮጵያ ፓስፖርት በዓለም አቀፍ ደረጃ 173ኛ፣ በአፍሪካ ደግሞ 49ኛ ደረጃን ይዟል።የፓስፖርቱ ቁልፍ መረጃዎች፡- 📌የኢትዮጵያ ፓስፖርት ባለቤቶች ወደ 51 ሀገራት (ከዓለም አቀፍ መዳረሻዎች 25%) ያለ ቅድመ ቪዛ መጓዝ ይችላሉ። 📌11 ሀገራት (ቤኒን፣ ጋምቢያ፣ ኬንያ፣ ሩዋንዳ እና ቶጎን ጨምሮ)። በሩዋንዳና ቶጎ ለ30 ቀናት፣ በሌሎቹ ለ90 ቀናት መቆየት ይቻላል። 📌በመድረሻ ቪዛ (Visa on Arrival)፡ 34 ሀገራት (20 የሚሆኑት በአፍሪካ እንደ ኮሞሮስና ሶማሊያ ያሉ)። 📌 በኢ-ቪዛ (e-Visa) / የኤሌክትሮኒክስ ፈቃድ፡ 4 ሀገራት። 📌ኢትዮጵያ የሌሎች ሀገራት ዜጎችን በማስተናገድ ረገድ ከ199 ሀገራት 24ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠች ሲሆን፣ የ146 ሀገራት ዜጎች ያለ ቅድመ ቪዛ ወደ ሀገሪቱ መግባት ይችላሉ።

AI የሰውን ልጅ ሊያጠፋ ይችላል‼️ ከፍተኛ አቅም ያለው ሰው ሰራሽ አስተውሎት (#AI) ከሰው ልጅ አቅም በላይ ከደረሰና በቂ ቁጥጥር ካልተደረገበት ለሰው ልጅ ህልውና ከባድ አደጋ ሊሆን እንደሚችል የAI ተመራማሪዎችና የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች እያስጠነቀቁ ነው። #በአሜሪካዊው የAI ኩባንያ Anthropic የሚሰሩ ተመራማሪዎች ኃይለኛ AI በዚህ አስር ዓመት ውስጥ ለሰው ልጅ ህልውና አደጋ ሊሆን እንደሚችል ገልጸዋል። ከኩባንያው የለቀቀው ጃኮብ ኮክሰን የተባለ ተመራማሪ፣ AI እስከ 2030 መጨረሻ ድረስ የሰው ልጅን ሙሉ በሙሉ ሊያጠፋ/ሊገድል የሚችልበት #እድል እንዳለ ሲገልጽ፣ አንድ የአሁኑ የAnthropic ተመራማሪም የዚህ አደጋ ዕድል ከ10 በመቶ በላይ ሊሆን እንደሚችል ጠቅሷል። እንደ የAI ተመራማሪዎቹ ገለጻ፣ እጅግ የላቀ AI ከሰው ልጅ ጥቅም ጋር ተጣጥሞ እንዲሰራ የሚያረጋግጥ በቂ #የደህንነት ዕቅድ አሁን የለም። ይህ ስጋት #በብሪታንያ ፓርላማም ተነስቷል። የቀድሞ የመከላከያ ሚኒስትር ዴዝ ብራውን እና የኮምፒውተር ሳይንስ ተመራማሪው ፕሮፌሰር ስቱዋርት ራሰል፣ እጅግ የላቀ AI ከኑክሌር መሣሪያዎች ጋር ተመጣጣኝ ወይም ከዚያ የሚበልጥ ለሰው ልጅ ስጋት ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። ሆኖም ሁሉም ባለሙያዎች በዚህ ላይ አይስማሙም። የAI እና ማኅበረሰብ ባለሙያ ፕሮፌሰር ኬት ዴቭሊን እንደሚሉት፣ " AI የሰው ልጅን #ሊያጠፋ ይችላል " የሚለው ትንበያ የተረጋገጠ እውነታ ሳይሆን የአደጋ ግምት ነው። በአሁኑ ወቅት እጅግ የላቀ " ሱፐር ኢንተሊጀንት " AI እንደሌለን እና መቼ እንደሚኖርም በትክክል መተንበይ እንደማይቻል ገልጸዋል። ባለሙያዎች ግን AI የሚያስከትለው አደጋ የሰውን ልጅ ሙሉ በሙሉ መጥፋት #ብቻ እንዳልሆነ ያስረዳሉ። #የAI ስርዓቶች ለጎጂ ዓላማዎች መጠቀም፣ ሳይበር ጥቃት ማድረስ ወይም በሰው ስህተት አደገኛ ስርዓቶችን መቆጣጠር ከሚጠቀሱት አደጋዎች መካከል ናቸው። በተጨማሪም የሐሰት መረጃ መስፋፋት፣ ሰው የሚሰራባቸውን ቦታዎች መተካት ፣ የግል መረጃ ደህንነት ስጋት እና AI ለማስኬድ የሚያስፈልገው ከፍተኛ ኃይል አሁኑ ወቅት እየታዩ ያሉ ችግሮችና ስጋቶች መሆናቸው ተጠቁሟል። አሁን ላይ " AI የሰው ልጅን ያጠፋል ወይ ? " ከሚለው ጥያቄ ባሻገር፣ እጅግ ኃይለኛ AI ከተፈጠረ በኋላ በሰው ልጅ ጥቅም ላይ እንዲውል ምን ዓይነት ቁጥጥር፣ ሕግና የደህንነት ሥርዓት መዘርጋት አለበት ? የሚለው አሳሳቢ ጉዳይ ነው። ዘጋርዲያን

የሚከራይ ትምህርት ቤት አያት አከባቢ 2,000 ካሬ ስፋት 20 መማሪያ ክፍሎች 5 ቢሮዎች 1 አዳራሽ ዋጋ/በወር : 900,000 ብር 0920862433/ 0988108854
+4
የሚከራይ ትምህርት ቤት አያት አከባቢ 2,000 ካሬ ስፋት 20 መማሪያ ክፍሎች 5 ቢሮዎች 1 አዳራሽ            ዋጋ/በወር : 900,000 ብር 0920862433/ 0988108854

የደመወዝ ወለል ተስፋ አለው‼️ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲወሰን አሁንም የውትወታ ሥራዬን አላቆምኩም ሲል የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ተናገረ። በኢትዮጵያ ያለው የኑሮ ውድነት በተለይ በቋሚ ደመወዝ ኑሯቸውን ለሚገፉ ተቀጣሪ ሠራተኞች ላይ እየፈጠረ ያለው ጫና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምጣቱን ኮንፌዴሬሽኑ ተናግሯል። የኑሮ ውድነቱ የሚያድግበት ፍጥነት ሠራተኛው ከሚያገኘው ቋሚ ገቢ ጋር ሊመጣጠን ባለመቻሉ ደመወዝተኛው በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንዲያልፍ እያስገደደው ነው ተብሏል። በዚህም ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲወሰንና የግብር ቅናሽ እንዲደረግ ኢሠማኮ የተለያዩ ሥራዎችን ሲሰራ መቆየቱን የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ አሰታውሰዋል። የአሰሪና ሠራተኛ አዋጁ ሲሻሻል ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲወሰን የተደረገው የውትወታ ሥራ መሳካቱን ተናግረው ይሁንና ተግባራዊ እንዲሆን አሁንም እየጠየቅን ነው ሲሉ ያብራራሉ። ሌላኛው በተደጋጋሚ ከሚጠየቁት መካከል የሥራ ግብር እንዲቀነስ የሚለው ይገኝበታል። በዚህም በኩል ኢሠማኮ የተለያዩ ሥራዎችን እንደሰራ ያነሱት ፕሬዝዳንቱ ግብር እንዲቀነስ ከማይፈልጉት መካከል አንዱ IMF ነው ሲሉ ተናግረዋል። ይሁን እና የIMF ኢትዮጵያ ተወካይም ሆነ ዋና የIMF ዳይሬክተርን አግኝተን ለምን ግብር እንዲቀነስ እና ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል መወሰን እንዳለበት ለማስረዳት ሞክረናል ያሉት አቶ ካሳሁን በመጨረሻ መስማማት ላይ መድረሳቸውን ለሸገር ሬዲዬ አስረድተዋል:: አሁን ተስፋ ሰጭ ነገሮች እንዳሉት አክለዋል።