Construction Solution- @Consite Media[የግንባታ ሥራ ተቋራጮች]🏗
Kanalga Telegram’da o‘tish
Addis Ababa, Ethiopia Con-Site is a Comprehensive Construction Filed Works and Materials Reference Catalogue for Architects, Engineers, Consultants and Customer service. t.me/ConsitesolutionBot ☜|]Comments Construction Solution Official Service
Ko'proq ko'rsatish3 585
Obunachilar
-124 soatlar
-57 kunlar
+5330 kunlar
Postlar arxiv
+6
♦️ያዶን ♦️
የኮንስትራክሽን ዕቃ አቅራቢ ድርጅት
▪️◽️◽️▪️◽️◽️▪️
አስተማማኝ ጥራትና ጥንካሬ ያላቸውን የብረታ ብረት ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ እና ከአስተማማኝ አቅርቦት ጋር ይዞ መጥቷል፤
🔹 ከምንይዛቸው ብረታ ብረት ምርቶች መካከል፦
▪️◽️ቱቦ ላሬ፦ ክብ ቱቦ፣ RHS, SHS, CHS
በተፈለገው ውፍረት (thickness)
▪️◽️LTZ profiles
28/38/48 (በተፈለገው thickness, size)
▪️◽️ ላሜራ (Sheet Metal)
🔹ኦቨር ሳይዝ (Oversize)
🔹 ሸካራ (Cqeuerd)
🔹 ልሙጥ
🔹 2*1m
🔹 3*1m
በተፈለገው ውፍረት (thickness)
ካልሆነም በትዕዛዝ በተፈለገው ሳይዝ እንቆርጣለን፤
🔹 አንጉላሬ (Angle)
በተፈለገው ውፍረት (thickness)
🔹 ድፍን ብረቶች
ቶንዲኖ እና ኳድሮ (Round Bar and Squire Bars)
🔹 U channel and I section
🔹
ለማንኛውም የብረታ ብረት ምርቶች ይደውሉልን፤ 0916416641 0931246190 የቴሌግራም ግሩፖችንን ይቀላቀሉ t.me/yadonco
🚧 ኮንትራክተር ለመመዝገብ የሚያስፈልጉ ሂደቶች
1. የንግድ አይነትና የመደብ ደረጃ መምረጥ
በህንፃ፣ መንገድ፣ ውሃ ወይም ኤሌክትሮ-ሜካኒካል ደረጃ መመዝገብ እንደሚፈልጉ ይወስኑ። የመደብ ደረጃው በሰራተኞች፣ ተሞክሮ፣ መሳሪያና ፋይናንስ አቅም ይወሠናል።
2. የንግድ መመዝገብና ታክስ መለያ (TIN) ማውጣት
በንግድ መዝገብ ቢሮ የንግድ ፈቃድ እና የታክስ መለያ ቁጥር ያግኙ። ይህ ከECA ለመመዝገብ ከመጀመሪያ የሚፈለገው መሠረት ነው።
3. የአስፈላጊ ሰነዶችን ማዘጋጀት
ለአዲስ ኮንትራክተሮች የተከታታይ አዲቲድ ፋይናንስ ሪፖርት እና organization chart አያስፈልግም።
4. ግምገማ እና መደብ መመደብ (Evaluation & Grading)
ኢትዮጵያ ሥራ ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን (ECA) የተላኩትን ሰነዶች በእያንዳንዱ መደብ መስፈርቶች መሠረት ይገምጻል።
ይህ ግምገማ የሚያካትቱት፡
የቴክኒክ ሰራተኞች ብቃትና ልምድ፣
የሥራ ዘመን (ተሞክሮ)፣
የመሳሪያ አቅም፣
የፋይናንስ አቅም እና የኩባንያው ድርጅት ተደራሽነት ናቸው።
ባለሥልጣኑ ተጨማሪ መረጃ መጠየቅ፣ ቃለ መጠይቅ ወይም በቦታ ምርመራ ሊያደርግ ይችላል።
መስፈርቱን ካሟሉ የኮንትራክተር ደረጃ ይመድባችሁ እና የመመዝገብ ምስክር ወረቀት ይሰጣችሁ።
5. በECA መድረክ ላይ መመዝገብ
በመስመር ላይ ይመዝገቡ፡:
ECA መዝገብ መድረክ (registration.eca.et)
6. የክፍያ ክፍያና ፈቃድ መቀበል
ክፍያውን ካከፈሉ በኋላ የብቃት ምስክር ወረቀት ይወስዳሉ።
7. Etrade ላይ online በመግባት ንግድ ምዝገባ በማስገባት , የንግድ ፈቃዱን መውሰድ ::
8. በየመንግስት ጨረታ (e-GP) መመዝገብ
የመንግስት ፕሮጀክቶች ላይ ለመተካት በe-GP መድረክ https://egp.ppa.gov.et/
መመዝገብ ያስፈልጋል።
FDRE-Procurement-Manual-Final-2018-NBGMS-1221-3.pdf2.94 MB
▶️ ሰሞኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ ለሚያከናውናቸው አዳዲስ የጋራ የመኖሪያ ህንፃዎች ግንባታ ተሳታፊ የሚሆኑ ስራ ተቋራጮችን ለመመልመል የሚያስችለው ማስታወቂያ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል ፤
▶️ ለመሆኑ ይህንን በተመለከተ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ ተቋራጮች መመልመያና የስራ ስምሪት መመሪያ ቁጥር 180/2017 ምን ይላል ?
▶️ የንግዱ ማኅበረሰብ አባላት መመሪያውን ታገኙት ዘንድ አያይዘናል።
ሊንኩን ይከተሉ
Source: chamber of Commerce
አንድ ለጨረታ የገባ ዋጋ የተሰበረ ነው (abnormally/unusually low) የሚባለው መቼ ነው? የተሰበረ ዋጋ ሲያጋጥም ምን እናደርጋለን?
በአዲሱ የፌደራል የግዥ አፈፃፀም መመሪያ አፈፃፀም መመሪያ 1073/2017 አንቀፅ 123 መሠረት:
ለዕቃ ግዥ በተጫራቹ የቀረበው የጨረታ ዋጋ ከገበያ ዋጋ አንጻር ከ30% (ሰላሳ በመቶ) ያነሰ ሲሆን ፤ ለምክር እና ከምክር ውጭ የሆነ የአገልግሎት ግዥ በተጫራቹ የቀረበው ዋጋ ከገበያ ዋጋ ከ20% (ሃያ በመቶ) ያነሰ ሲሆን እና፤ (እዚህ ላይ በእንግሊዘኛ በተቀመጠው "also more than twenty percent (20%) lower than other bid prices." የሚል አካቷል)
🏗 ለግንባታ ግዥ በተጫራቹ የቀረበው የጨረታ ዋጋ ከምህንድስና ግምት ዋጋ ጋር በአንጻራዊነት ሲታይ የቀረበው ዋጋ ከ20% (ሃያ በመቶ) ያነሰ ሲሆን እንደተሰበረ የጨረታ ዋጋ ይቆጠራል፡፡
ይህ በሚያጋጥምበት ጊዜ ምን አይነት የማጣራት እና ግምገማ ሂደቶችን ማለፍ እንዳለበት የመመሪያው አንቀፅ 123 ዝርዝር ሃሳቦችን አካቷል።
ይህን ሂደት በተመለከተ በዓለም ባንክ የተዘጋጀው "Guide to the identification and treatment of Abnormally Low Bids and Proposals" የሚለው መመሪያ ጠቃሚ ማብራሪያ ይሰጣል።
https://t.me/cotm2022
አዲስ አሠራር!
የገቢዎች ሠራተኞች በካሜራ የታገዘ ዩኒፎርም ሊለብሱ ነው!
የግልፅነትና ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ወደ ሥራ አስገባ!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ከግብር ከፋዮች ጋር ግንኙነት የሚፈጥሩና ቁጥጥር የሚያደርጉ ሠራተኞች ላይ ትልቅ ለውጥ አመጣ።
ከዛሬ ረቡዕ፣ ኅዳር 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ግብር ከፋዮችን የመከታተልና የመቆጣጠር ኃላፊነት የተሰጣቸው የቢሮው ሠራተኞች ቪዲዮ ካሜራ የተገጠመበት ዩኒፎርም ለብሰው ወደ ሥራ ይሠማራሉ።
ስሙ የቦዲ ዎርን ካሜራ ፕሮጀክት (Body Worn Camera Project) ሲሆን ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ወጥቶበታል::
ከኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት (ኢንሳ) ጋር በመተባበር።
የተሰራው ይህ አዲስ የካሜራ ቴክኖሎጂ በርካታ ጠቀሜታዎች አሉት፡-
1. ቀረጻ:
የቁጥጥር ባለሙያዎች የሚያደርጉትን ሥራ በሙሉ በድምፅና በምሥል ይመዘግባሉ።
2. ቀጥታ ስርጭት:
የተቀረጸው መረጃ ወዲያውኑ ለዋናው መሥሪያ ቤትና ለቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች በቀጥታ ይላካል።
3. ክትትል (Location Tracking):
የቢሮው ባለሙያዎች በዋና መሥሪያ ቤት እና በቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ቁጥጥር የሚያደርጉ ሠራተኞች እያንዳንዱን እንቅስቃሴ እና የት አካባቢ እንደሚገኙ ይከታተላሉ።
4.ግልጽነት:
ከግብር ከፋዮች ጋር የሚደረጉ ንግግሮች በሙሉ ስለሚመዘገቡ ግልፅነትና ተጠያቂነትን ያረጋግጣል።
ይህ እርምጃ በግብር አስተዳደር ሥራዎች ላይ ያለውን ግልፅነትና ቅልጥፍና እንደሚያሳድግ ይጠበቃል።
©️Ethiopia Reporter 😁
ለዚህ መሰንጠቅ ዋናው ምክንያት ምንድን ነው?
- ይህ በአጥሩ ብሎከትና masonry ግድግዳ ላይ የሚታየው ዋናው ቀጥ ያለ ስንጥቅ (major vertical crack)፣ በድንጋይ መሰረቱ እና በላይኛው የሲሚንቶ ብሎክ ክፍል ውስጥ የሚያልፍ ሲሆን፣ ብዙውን ጊዜ የሚከሰተው በመሰረት ችግሮች ምክንያት በሚመጣ መዋቅራዊ ውድቀት ምልክት ነው።
ለዚህ ዓይነቱ ውድቀት /መሰንጠቅ/ ምክንያቶች ሊሆኑ የሚችሉ እነሆ፦
- የመሰረት መንቀጥቀጥ ወይም መውረድ (Foundation Movement or Settlement)
- ዋናው መንስኤ በግድግዳው መሰረት ላይ ያለው ልዩነት ያለው መውረድ (differential settlement) ነው። ይህ የሚሆነው የመሰረቱ አንድ ክፍል ከአጠገቡ ካለው ክፍል በላይ ሲሰምጥ ወይም ሲንሸራተት ነው።
ያልተስተካከለ የአፈር ጥንካሬ
- ከመሰረቱ በታች ያለው አፈር በግድግዳው ርዝመት ላይ የተለያየ የመሸከም አቅም ሊኖረው ይችላል። ለምሳሌ፣ አንዱ ክፍል ጠንካራ መሬት ላይ ሲያርፍ፣ የተሰነጠቀው ክፍል ደግሞ በላላ፣ በትክክል ባልተጨመቀ አፈር ላይ ወይም በጊዜ ሂደት በበሰበሰ አፈር ላይ ሊያርፍ ይችላል።
አፈር መታጠብ ወይም መሸርሸር
- የውሃ መግባት (ለምሳሌ ደካማ የፍሳሽ ማስወገጃ፣ የፈሰሰ ቧንቧ ወይም ከባድ የዝናብ ፍሰት) መሰረቱን የሚደግፈውን አፈር ሊያበላሽና ሊያጥበው ይችላል።
- ይህ ክፍተቶችን በመፍጠር ያ ክፍል እንዲሰምጥ ያደርጋል። በምስሉ ላይ የሚታየው የተንጣለለው መሬት የገፀ ምድር ውሃ ፍሰት ለችግሩ አስተዋፅዖ ሊኖረው እንደሚችል ይጠቁማል።
የግንባታ እና የንድፍ ጉድለቶች (Construction and Design Deficiencies)
- ግድግዳው የተገነባበት መንገድ ለመሰረት ችግሮች እንዲጋለጥ አድርጎት ሊሆን ይችላል።
በቂ ያልሆነ መሰረት
- መሰረቱ ራሱ ለአፈሩ ሁኔታ በጣም ጥልቀት የሌለው ወይም በቂ ማጠናከሪያ (ሪባር/ብረት) የሌለው ሊሆን ይችላል። በመሰረቱ ወይም በግድግዳው የኮንክሪት ምሰሶዎች ውስጥ በቂ የብረት ማጠናከሪያ አለመኖር፣ መሰረቱ በሰመጠበት አካባቢ ላይ ያለውን ጫና ለመሸከም አቅም ያሳጣዋል።
የመቆጣጠሪያ መጋጠሚያዎች እጥረት (Lack of Control Joints)
- ግድግዳው በጣም ረጅም ነው፣ እና ሁሉም የብሎከት እና የሲሚንቶ ቁሳቁሶች በሙቀት ለውጦች ይለጠጣሉ እንዲሁም ይኮማተራሉ። የቋሚ የመቆጣጠሪያ መጋጠሚያዎች (vertical control joints) አለመኖር ጭንቀትን ይፈጥራል፣ ይህም በተዳከመ ቦታ ላይ (በተለይ ከመሰረት መውረድ ጋር ሲደመር) ትኩረት አድርጎ ወደ ስንጥቅ ሊለወጥ ይችላል።
የስንጥቁ ቀጥ ያለ እና ያልተስተካከለ (በተለምዶ shear failure ተብሎ የሚጠራ) ባህሪው ከመሬት በታች ባለው እንቅስቃሴ ምክንያት ግድግዳው በአቀባዊ እየተገነጠለ መሆኑን ያሳያል።
በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጁ አዳዲስ መደበኛ የጨረታ ሰነዶች (Standard Bidding Documents)
📌 በግዥና ንብረት ባለስልጣን በኩል ከአዲሱ የግዥ መመሪያ አንፃር የተዘጋጁ ሶስት ለእቃ (Goods)፣ ግንባታ (Works) እና ለማዕቀፍ (Framework) ግዥዎች የሚያገለግሉ መደበኛ የጨረታ ሰነዶች (Standard Bidding Document) በአማርኛ ቋንቋ ተዘጋጅተው በድህረ ገጻቸው ይፋ ተደርገዋል። ሰነዶቹ ከላይ አያይዘንላችኋል👆👇
📌 በቀጣይ በእንግሊዘኛ ቋንቋም ሰነዶቹ ተዘጋጅተው እንደሚቀርቡ ይጠበቃል።
📢 Join: @procinsightet
📬 Contact: @Procinsight_bot
👵 Discussion: @procinsightet2
❇️ ለ7ኛው ዙር የ40/60 እና ለ1ኛው ዙር የካፒታል በጀት ንግድ ቤቶች ጨረታ አሸናፊዎች የወጣ የውል ጥሪ ማስታወቂያ
UPVC ጥንካሬን፣ የረጅም እድሜ አገልግሎትንና ውበትን ከመስጠት ባለፈ በተለያዩ ዲዛይኖች እና ቀለም መመረት እና መገጠም መቻሉ ተመራጭ ያደርገዋል።እንዲሁም በሚፈልጉት የቁልፍ አማራጮች ይዘንላቹ መጥተናል።
📍 Location: ጋዜቦ አደባባይ፣ ሙልሙል ዳቦ ቤት አጠገብ
📞 Call us: 0930099146,0930099145
DELINA uPVC & ALUMINUM
“The door is the face of a home; beauty begins there"💪
👉 INTERCON Construction Chemicals
● Concrete Admixtures
● Bonding Agents
● Waterproofings
● Wall Putty, Prime Coat
● Concrete Repair Mortar
● Floor hardener, Epoxy
● Grout, Self-level mortar
● Quartz paint, Contextra
● Tile Adhesive & Tile Joint Fillers
● Geotextiles and other construction chemicals and materials
☎️ Tel: 0961955555
🔹 Address 1: Signal road, around
Dinberwa Hospital
🔹 Addres 2: Wellosefer, Infront of
Dani Plaza
Standard_bid_document_for_Turn_key_projects__1764236443.pdf1.79 MB
የአማካሪ ማህበራት አገልግሎት የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 004/2018
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዲዛንና ግንባታ ስራዎች ፅ/ቤት በክፍለ ከተማው ሊያስገነባቸው የፈለገውን ስራ ልዩ አማካሪ አወዳድሮ በመዋዋል ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን፣ የሰው ሀይል በተጨማሪም የሚቀጥሉትን መስፈርቶች በሟሟላት የጨረታ ሰነዱን አንድ ብቻ መውሰድ ይችላሉ፡፡
UPVC ጥንካሬን፣ የረጅም እድሜ አገልግሎትንና ውበትን ከመስጠት ባለፈ በተለያዩ ዲዛይኖች እና ቀለም መመረት እና መገጠም መቻሉ ተመራጭ ያደርገዋል።እንዲሁም በሚፈልጉት የቁልፍ አማራጮች ይዘንላቹ መጥተናል።
📍 Location: ጋዜቦ አደባባይ፣ ሙልሙል ዳቦ ቤት አጠገብ
📞 Call us: 0930099146,0930099145
DELINA uPVC & ALUMINUM
“The door is the face of a home; beauty begins there"💪
👉የግዢ አይነቶች (Procurement Methods):-1) ክፍት ጨረታ (Open Competitive Bidding) ለሁሉም ተቸራሪ ክፍት የሆነ የግዢ ዘዴ ነው። የተሻለ ዋጋ እና ጥራት ለመያዝ በግልጽነት የሚያስችል። በመንግስት ውስጥ የተለመደው ዋና ዘዴ ነው። 2) የተወሰነ ጨረታ (Restricted Bidding) ተመረጡ አቅራቢዎችን ብቻ የሚጥራ ዘዴ ነው። የብቃት መስፈርት ከፍ ባለ ስራዎች ላይ ይውላል። 3) ከተወሰኑ አቅራቢዎች የጥያቄ ማቅረብ (Request for Quotations – RFQ) ዋጋ ቀላል ያለው እቃ/አገልግሎት ለመግዛት ከ3 ወይም ከዚያ በላይ አቅራቢዎች ዋጋ ይሰበስባል። ቀላል በሆነ ግዢ ላይ ይጠቀማል። 4) ቀጥታ ግዢ (Direct Procurement / Single-Source Procurement) ከአንድ አቅራቢ ብቻ ማግኘት ስለሚያስፈልግ የሚውል ሁኔታ። ይህ መርሀ ግብር ለሚከተሉት ተፈቃዶች ይሰጣል፦ ብቻውን የሚያቀርብ አቅራቢ ከሆነ አስቸጋሪ ወይም ድንገተኛ ሁኔታ በአስፈላጊ ምክንያት ጊዜ ሲጫን 5) የልዩ ሁኔታ ግዢ (Special Procurement / Exceptional Circumstances) ከተለመዱ ዘዴዎች ውጭ በተስፋቸው ልዩ ሁኔታዎች ላይ የሚውል። የሚፈቀድበት ሁኔታ በግዢ ባለስልጣን ፈቃድ ነው። 6) ማዕቀፍ ግዢ (Framework Agreement Procurement) የብዛት ተደጋጋሚ ግዢዎች ላይ የሚመጣ። አቅራቢው ከመንግሥት ጋር ረዥም ጊዜ የተጠናቀቀ ስምምነት ይያዛል። 7 ጋራ ግዢ (Joint Procurement) ብዙ መ/ቤቶች የጋራ እቅድ በመያዝ በአንድ ግዢ ሂደት ይገናኛሉ። የትርፍ ተመጣጣኝነት ይፈጥራል። 8 በኪራይ የሚፈጸም ግዢ (Lead Procurement) የመሳሪያ ወይም አቅርቦት በኪራይ በማድረግ የሚውል ዘዴ። በየወር ወይም በየአመት ክፍያ ይኖራል። 9) በፎርስ አካውንት (Force Account) መንግስት በራሱ ሀይል (ሰራተኞች፣ መሳሪያ፣ ተቋማት) ሥራ ሲፈጽም ይጠቀማል። ብዙ ጊዜ በመኖሪያ፣ መሰረታዊ ኢንፍራ ሥራዎች ላይ ይኖራል። 10) ተርንኪ / Turnkey Procurement አቅራቢው ዲዛይን፣ ሥራ፣ መተግበሪያ ሁሉ አንድ በማድረግ የሚያቀርብ ኮንትራት። “ቁልፍ ተስፋ” ይባላል፣ ስራው ሙሉ በሙሉ እስኪዘጋጀ ድረስ። 11) ኤሌክትሮኒክ የተቃራኒ ጨረታ (Electronic Reverse Auction) አቅራቢዎች በመድረክ ላይ በቀጥታ ዋጋ ይቀንሳሉ። ዝቅተኛ ዋጋ በተለይ ለመያዝ ይጠቅማል። 13) የቅድመ ብቃት ጨረታ (Prequalification) በማኅበረሰብ ላይ ትልቅ ወይም ውስብስብ ስራዎች ተወዳዳሪዎችን በመርጠት የሚደርስ።
👉የ ኮንስትራክሽን ውሎችን ለሌላ መልቀቅ(Assignment) ምን ማለት ነው?
- ውሎችን ለሌላ መልቀቅ (Assignment) ዋናው ተቋራጭ የግንባታ ውሉን ስራ በሙሉ እንዲፈጽምለት ለአንድ ሶስተኛ ወገን ለሆነ ሲያስተላልፍ ነው፡፡ (የፍ/ህ/ቁ 3201(1))
- ይሄውም ከንኡስ ተቋራጭነት ጋር ሁኔታውአንድ አይነት ሲሆን በዋናነት ልዩነቱ ዋናው ተቋራጭ ለሌላ ተቋራጭ(ለንኡስ ተቋራጩ) የሚያሰራው ሙሉውን የግንባታ ስራ ነው፡፡
- በዚህ ውል ውስጥ ሁለቱም ተዋዋይ ወገኖች ተቋራጮች ናቸው፡፡
ለምሳሌ "ሀ" የተባለ ተቋራጭ "ለ" ከተባለ አሰሪ ጋር የኮንስትራክሽን ውል ገባ እንበል፡፡የግንባታ ስራው ደግሞ ትምህርት ቤት ቢሆን እና ሁለት ብሎክ መማሪያ ህንጻ እና አንድ ሽንት ቤት ግንባታ ቢሆን እንበል፡፡
እንግዲህ ዋናው ተቋራጭ "ሀ" ከግንባታ ስራው ውስጥ አንዱን ብሎክ መማሪያ ክፍል "ሐ" ለተባለ ተቋራጭ በውል ሰጥቶ ቢያስገነባው በ "ሀ" እና "ሐ" መካከል የሚደረገው ውል የንኡስ ተቋራጭነት ውል ይባላል ማለት ነው፡፡
- በሌላ በኩል ምናልባት ዋናው ተቋራጭ "ሀ" ሁሉንም ግንባታ ማለትም ሁለት ብሎክ መማሪያ ህንጻ እና አንድ ሽንት ቤት "መ" ለተባለ ተቋራጭ በውል ሰጥቶ ቢያስገነባው በዋናው ተቋራጭ "ሀ" እና "መ" በተባለው ተቋራጭ መካከል የተደረገው ውል በንኡስ ተቋራጭነት ሳይሆን ውሎችን ለሌላ መልቀቅ(Assignment) በሚለው የህግ ክፍል የሚጠቃለል ይሆናል ማለት ነወ፡፡
- ጀኔራል ኮንዲሽኖች ንኡስ ተቋራጭነትን በምን ሁኔታ ያስቀምጡታል?
🚧ፒፒኤ 2011 ስለ ንኡስ ተቋራጭነት አስመልክቶ በክሎስ 14 ላይ አስቀምጧል፡፡
በዚህም የንኡስ ተቋራጭነት ውሉ በጽሁፍ መሆን እንዳለበት እና ይሄውም የቫሊዲቲ መስፈርት ስለመሆኑ ይገልጻል፡፡
ንኡስ ተቋራጮች በዋናው የኮንስትራክሽን ውል ላይ ያልታወቁ( Non nominated) የሆኑ እንደሆነ ዋናው ተቋራጭ ሌሎች ንኡስ ተቋራጮችን የግንባታ ስራ ለማሰራት የአሰሪውን የጽሁፍ ፈቃድ ማግኘት ይኖርበታል በሚል ያስቀምጣል፡፡
ንኡስ ተቋራጭነት ውሉም ከዋናው ውል ጋር የተጣጣመ እና በዋናው ውል ጭምር የሚገዛ እንደሚሆን ክሎስ 14.3 ላይ ተቀምጧል፡፡
ዋናው ተቋራጭ የአሰሪው መስሪያ ቤት ሳይፈቅድለት የንኡስ ተቋራጭነት ውል የገባ እንደሆነ አሰሪው ፎርማል ማስጠንቀቂያ መስጠት ሳያስፈልገው ውልን ማቋረጥ እንደሚችል ክሎስ 14.8 ያስቀምጣል፡፡
*ሌላው ንኡስ ተቋራጩ የግንባታ ስራ ለማከናወን ብቃት የሚያንሰው እንደሆነ አሰሪው መስሪያ ቤት ወይም መሀንዲሱ ዋናውን ተቋራጭ ሌላ ብቃት ያለው ንኡስ ተቋራጭ እንዲያመጣ ወይም ስራውን በራሱ እንዲያከናውን ሊጠይቀው እንደሚችል ክሎስ 14.9 ይገልጻል፡፡
🚧ፊዲክ ሬድ ቡክ 1999-በዚህ ጀኔራል ኮንዲሽን ክሎስ 4.4 ላይ ዋናው ተቋራጭ ሙሉውን የግንባታ ስራ ለንኡስ ተቋራጭ መስጠት እንደማይችል ተቀምጧል፡፡
እንዲሁም በስፔሻል ኮንዲሽን ላይ በሌላ ሁኔታ ካልተቀመጠ በስተቀር ንኡስ ተቋራጩ በዋናው የኮንስትራክሽን ውል ላይ ስሙ የተጠቀሰ በሆነ ጊዜ በንኡስ ተቋራጭነት ለማሰራት የመሀንዲሱን ፈቃድ መጠየቅ አይጠበቅበትም፡፡
ሆኖም የታሰበው ንኡስ ተቋራጭ አዲስ እና በዋናው ውል ስሙ ያልተጠቀሰ የሆነ እንደሆነ በቅድሚያ የመሀንዲሱን ፈቃድ ማግኘት አስፈላጊ ይሆናል፡፡
*ዋናው ተቋራጭ ለመሀንዲሱ በተለይ ንኡስ ተቋራጩ የሚሰራውን የግንባታ ስራ መጀመሪያ ቀን/ኮመንስመንት ዴት/ ተብሎ የታሰበውን ጊዜ ከ28 ቀን ባላነሰ ጊዜ ማስታወቅ ሲኖርበት ንኡስ ተቋራጩ በትክክል በሳይት ላይ ስራ የጀመረበትንም ቀን ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡
🚧Nominated subcontractors በሚመለከት በክሎስ 5.1 ላይ ትርጉም ተሰጥቶታል፡፡
*በዚህም መሰረት ኖምኔትድ ሰብ ኮንትራክተር የሚባለው በዋናው የኮንስትራክሽን ውል ላይ ኖምኔትድ ሰብ ኮንትራክተር መሆኑ የተገለጸ እንደሆነ ወይም ኢንጅኒየሩ ለተቋራጩ ንኡስ ተቋራጭ መርጦለት እንዲያሰራው ያዘዘው የሆነ እንደሆነ ነው፡፡
🚧ለኖምኔትድ ሰብ ኮንትራክተሩ ክፍያ የሚፈጸምለት በንኡስ ተቋራጭነት ውሉ አግባብ በመሀንዲሱ በሚሰጥ የክፍያ ሰርተፍኬት መሰረት ሲሆን ክፍያውን የሚፈጽመውም ዋናው ተቋራጭ ስለመሆኑ ክሎስ 5.3 ላይ ተቀምጧል፡፡
በ ጉባዔ አሰፋ
@consite🏗
Endi mavjud! Telegram Tadqiqoti 2025 — yilning asosiy insaytlari 
