Dejazmach Hailu Tesfaye Pre-primary , Primary & Middle School
Kanalga Telegram’da o‘tish
This channel will provide information to school community
Ko'proq ko'rsatish706
Obunachilar
-124 soatlar
-217 kun
-930 kun
Postlar arxiv
QAJEELFAMA_HAARAA_GUDDINA_BARSIISOTAA_ILAALCHISEE_QOPHAA E.pdf1.71 MB
1148_የአጠቃላይ_ትምህርት_መምህራን_የደረጃ_እድገት_አፈጻጸም_1.pdf3.32 KB
በአዲስ ከተማ ት/ፅ/ቤት ስር ለ1ኛ ደረጃ ት/ቤቶች፦ የብቃት ማረጋገጫ የወሰዳችሁ መምህራን እና ር/መምህራን (ከ2ኛ ደረጃ ውጪ) ውጤታችሁ ስለመጣ ትምህርት ምዘናና ስልጠና ቢሮ (ሰሜን ሆቴል፣ ዳኪ ህንፃ) በስራ ሰዓት በመሄድ እንድትወስዱ እናሳስባለን። የ2ኛ ደረጃ ውጤት ሲመጣ የምናሳውቅ ይሆናል።
የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ክፍያ ከ750 ወደ 2,000 ብር ከፍ አለ።
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ለሚሰጣቸው ልዩ ልዩ አገልግሎቶች የሚከፈል ክፍያን የሚያሻሽል አዲስ ደንብ ወጥቷል።
በዚህም ቀደም ሲል 750 ብር የነበረው የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና (Exit Exam) ክፍያ ወደ 2,000 ብር ከፍ ብሏል። ከዚህ ውስጥ 500 ብር የምዝገባ፣ 1,500 ብር ደግሞ የፈተና ክፍያ ሲሆን፣ ለውጭ ዜጎች 100 ዶላር ተወስኗል።
በተጨማሪም፦
👉 የድህረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT) ፦ ለኢትዮጵያውያን 3,500 ብር፤ 500 ብር የምዝገባና 3,000 ብር የፈተና ክፍያ። ለውጭ ዜጎች 100 ዶላር።
👉 የ12ኛ ክፍል ፈተና ምዝገባ ፦ ለኢትዮጵያውያን 950 ብር፤ ለውጭ ዜጎች 100 ዶላር።
👉 የሙያ ፈቃድና ብቃት ምዘና ፦ ለኢትዮጵያውያን 3,500 ብር፤ 1,000 ብር የምዝገባና 2,500 ብር የፈተና ክፍያ። ለውጭ ዜጎች 150 ዶላር።
👉 የትምህርት ማስረጃ ምትክ ሰርተፊኬት ፦ ለኢትዮጵያውያን 600 ብር ፤ ለውጭ ዜጎች 115 ዶላር።
👉 ምትክ ሰርተፊኬትና ማረጋገጫ ፦ ለኢትዮጵያውያን 900 ብር ፤ ለውጭ ዜጎች 170 ዶላር።
👉 የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጥ/ማጣራት ፦ ለኢትዮጵያውያን 400 ብር፤ ለውጭ ዜጎች 75 ዶላር።
👉 በስም ላይ የፊደል ግድፈት ለማስተካከል ፦ ለኢትዮጵያውያን 700 ብር፤ ለውጭ ዜጎች 130 ዶላር።
👉 ኦፊሴላዊ ትራንስክሪፕት መላክ ፦ ለኢትዮጵያውያን 750 ብር፤ ለውጭ ዜጎች 50 ዶላር።
የፈተና ውጤት መረጃን ለምርምር ለሚጠይቁ ተቋማት በአንድ ጥናት 10,000 ብር፣ ለውጭ ተቋማት 1,875 ዶላር ክፍያ ተወስኗል። ለግለሰቦች ደግሞ ለኢትዮጵያውያን 1,000 ብር፣ ለውጭ ዜጎች 190 ዶላር እንደሚከፈል ተገልጿል።
በተጨማሪም ያገለገሉ የምዘና መሳሪያዎችን ለመጠቀም ከጠቅላላ ወጪው 5 በመቶ፣ አዲስ የምዘና መሳሪያ ለማዘጋጀት ደግሞ 10 በመቶ ክፍያ እንደሚፈጸም ደንቡ ያስቀምጣል።
ደንቡ ለሌሎች የምዘናና የማረጋገጫ አገልግሎቶችም አዳዲስ የክፍያ ተመኖችን አካቷል።
የተሻሻለው ደንብ ቁጥር 593/2018 ሙሉ ይዘት ከላይ በተያያዘው ምስል ላይ ይገኛል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 17 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia
1148_የአጠቃላይ_ትምህርት_መምህራን_የደረጃ_እድገት_አፈጻጸም.pdf3.32 KB
ለትምህርት ቤቱ መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች በሙሉ
በነገው ዕለት በቀን 15/01/2019ዓ.ም በትምህርት ቤቱ አጠቀላይ የሠራተኞች ስብሰባ ስላለ ሁሉም የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ 8:00ሰዓት በትምህርት ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ እንድትገኙ ትምህርት ቤቱ በጥብቅ ያሳስባል ።በእለቱ መገኘት የሁሉም ስራተኞች ግደታ ነው
ቀልድ መስለው ነገር ግን ወንጀል የሆኑ ድርጊቶች!
****
1. የሰውን ፎቶ/ቪዲዮ መለጠፍ
ድርጊቱ፦ መንገድ ላይ ያዩትን ጠብ ወይም አስቂኝ ነገር ያለ ባለቤቱ ፈቃድ ቀርጾ ፌስቡክ ላይ መለጠፍ።
ውጤቱ፦ የግል ነፃነትን መጣስ ተብሎ ያስከስሳል።
2. የሀሰት ወሬ ማሰራጨት
ድርጊቱ፦ "እውነት ይመስላል" ብለው መረጃን ሳያረጋግጡ "Share" ማድረግ።
ውጤቱ፦ ሀ, በሀሰተኛና ጥላቻ ንግግርን የማሰራጨት ተጠያቂነት
ለ,የኮምፒውተር ወንጀል አዋጅን መጣስ እና የሰላም መታወክ ተጠያቂነት።
3. በኮሜንት መሳደብ
ድርጊቱ፦ በፖስት ስር ሰዎችን በብሄር፣ በሃይማኖት ወይም በግል ማንነታቸው መስደብ።
ውጤቱ፦ የጥላቻ ንግግር እና ስም ማጥፋት ወንጀል።
4. ያለፈቃድ ገንዘብ ማሰባሰብ
ድርጊቱ፦ "ለታመመ ሰው እርዳታ" በሚል የባንክ አካውንት እየለጠፉ በሶሻል ሚዲያ ገንዘብ መለመን።
ውጤቱ፦ ያለፈቃድ የገንዘብ ማሰባሰብ እና የማጭበርበር ጥርጣሬ።
5. የሰው ዲዛይን መስረቅ
ድርጊቱ፦ የሌላ ሰውን ሎጎ ወይም የፈጠራ ስራ "የእኔ ነው" ብሎ መጠቀም።
ውጤቱ፦ የቅጂ መብት (Copyright) ጥሰት ክስ።
6. የግል መልዕክትን ማጋራት (Screenshot)
ድርጊቱ፦ በ "Inbox" የተላከልዎትን ሚስጥራዊ መልዕክት ያለ ሰውየው ፈቃድ ለሰው እንዲታይ ፖስት ማድረግ።
ውጤቱ፦ የግል ሚስጥርን ማባከን (Privacy violation)።
ማሳሰቢያ፦ በኢንተርኔት የምንለጥፈው ነገር ሁሉ "ዲጂታል አሻራ" ስላለው በሕግ ፊት ማስረጃ ሆኖ ሊቀርብ ይችላል።
በዛሬው ቀን 5/01/2019 ዓ.ም አብዛኛው መምህራን የተሰጣቸውን ኃላፊነት በመውሰድ ተማሪዎችን ከማስተባበር ጀምሮ የተመደቡበትን ክፍለ ግዜያቸውን በአግባቡ አስተምሯል።ይሁን እና አሁንም ከጥፋት አባዜ የማይወጡ መምህራን
1ኛ በትምህርት ቤት ግብ ውስጥ እያሉ ክፍለ ጊዜ የባከኑ እና በሰዓቱ ክፍል ያልገቡ
2ኛ ሙሉ በሙሉ እስከአሁን ድረስ ለትምህርት ቤቱ ሪፖርት ያላደረጉ መምህራን መኖራቸውን / ያልመጡ /መምህራን መኖራቸውን ተረጋግጧል ።ስለሆነም በእነዚህ መምህራን ላይ መረጃዎችን በበቂ ሁኔታ ትምህርት ቤቱ እያደራጀ ስለሆነ በተለይም በ5/01/2018ዓ.ም በስራ ገብታችሁ የልተገኘችሁ መምህራን አሳማኝ ውይም ህጋዊ ማስረጃ ከለቀረበ በስተቀር ትምህርት ቤቱ አስተማሪ የእርምት እርምጃ ለመወሰድ የሚገደድ መሆኑን እያሳወቁ መምህራን ከመቼውም በበለጠ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ የትምህርት ቤቱ አስተዳደር አካላት ያሳስባል ።
