uz
Feedback
Eliyah Mahmoud

Eliyah Mahmoud

Kanalga Telegram’da o‘tish
6 029
Obunachilar
-424 soatlar
-157 kun
+54830 kun
Postlar arxiv
አወወ ከጉርፑ ጋር ተያይዞ የተፈጠረ ችግር ስለነበረ ለማስተካከል በሚል የዛሬውን ርዕሰ ጉዳይ ደጋግሜ ለጥፌዋለኹ።

፪) ሰው እንፍጠር ... ዘፍጥረት 1/26 .... "እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር" ከዚህ በፊት እዚህ ጥቅስ ላይ ቆመን አንድ ሐሳብ አውግተናል። የስላሴ አካላት በመለኮታዊ ማንነት አንድ ከኾኑ የመፍጠር ሐሳቡ ከኹሉም በኩል መነሳት ነበረበት፤ ኾኖም ግን ከአብ ብቻ መነሳቱ የወልድንና የመንፈስ ቅዱስን ዝቅተኛነት ያንጸባርቃል። ይሕ ደግሞ የሶስት አቻ አማልክት ስሪት የኾነውን -ስላሴን ገደል ይከተዋል ብለናል። አብ ብቻ አዳምን የመፍጠር ሐሳብ አነሳ ከተባለ ስላሴአውያን Partialism (Fractional Godhood) የሚባለውን የስላሴ አስተምህሮ እንዲቀበሉ ያስገድዳል። ከፊላዊነት (Partialism_ Fractional Godhood) ሶስት አካላት ተሰባስበው የጋራ አንድ አካል ፈጠሩ የሚል አስተምህሮ ነው። ይሕ ደግሞ እያንዳንዱ አካል 1/3 የስላሴን በትረ_ስልጣን ይቀራመታል እንደ ማለት ነው። በሌላ አባባል እያንዳንዱ የስላሴ አካል በራሱ ምሉዕ መለኮታዊ ኃልና ስልጣን የለውም ማለት ነው። ይሕንን "ንፍቅና" ለመሸሽ አንዳንድ ክርስቲያኖች አምላክ ራሱን በሶስት መልክ አስገኘ_አብ፣ወልድ፣መንፈስ ቅዱስ በማለት ለማስረዳት ይሞክራሉ። ይሕ ደግሞ "አገላለጥ" (Modalism / Sabellianism _One God in Different Roles) የሚባለውን የስላሴ አስተምህሮ ይወክላል። በአጭሩ አንድ አምላክ ራሱን በሶስት መልክ ገለጸ እንደ ማለት ነው። እዚህ ላይ ቆም ብለን ያ ራሱን በሶስት መልክ ያስገኘው አካል ማን ነው? ብለን እንጠይቃለን። አብ ነው ካሉ፣ አብ ከሶስቱ አካላት አንዱ እንጂ ራሱን በሶስት መልክ የገለጠው አካል አይደለም። ስለዚህ ራሱን በሶስት መልክ የገለጠው ማነው? ይሕ አስተምህሮ የኒቂያን ስላሴ በሚል ብዙዃኑ ክርስቲያን የሚያምንበትን ሶስት የተለያዩ ግን ደግሞ ዝንተ_ዓለማዊ የኾነ እኩል ስልጣን ካላቸው አካላት አስተምሕሮ ጋር ይጣረሳል። የኒቂያው "ስላሴ" ሶስት በግልጽ የሚለያዩ ግን በስልጣን እኩል የኾኑ በምግባር ደግሞ _ አብ የማይወለድ፣ወልድ ተወላጅ፣መንፈስ ቅዱስ ሰራጺ አካላትን ይሰብካል። ወደ መጽሐፉ ገብቶ ከኹሉም የስላሴ አስተምህሮ ዓይነቶች አንዱን እንኳ ለማግኘት የሞከረ ሳያገኘው ቀርቶ አምላክ አንድ እሱም ሰው ያልኾነና የማይሞት እንደኾነ ይረዳል። ኢየሱስን አምላክ ለማድረግ የሚታትሩ አካላት ይሕንን ጥቅስ በዋቢነት ሲጠቀሙ ይታያል፦ ማቴዎስ 28/18 "ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው። ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር #ተሰጠኝ#። " ተሰጠኝ የሚለው ኀይለ ቃል ኢየሱስ የኾነ ጊዜ ያልነበረውን አብ እንደሰጠው በግልጽ ያሳያል። ታዲያ ይሕ መሰጠት መለኮታዊ ኃይልንም ጭምር ካጠቃለለ፣አብ መለኮታዊ ኃይሉን ለወልድ እንዳካፈለ ወይም እንደሰጠ እንረዳና በእግረ መንገዳችን ደግሞ ሰጪ በላጭ ተቀባይ ደግሞ አናሳ እንደኾነ እንገነዘባለን። በዚህ ጥቅስ ብቻ ያሳለፍናቸው ኹሉም የስላሴ አስተምሕሮዎች ገደል ይገባሉ። ኢየሱስ ከአብ ስልጣን ኹሉ ከተሰጠው፣የስላሴ ሶስተኛው አካል መንፈስ ቅዱስስ ስልጣኑን ማን ሰጠው? .... ይቀጥላል https://t.me/E_M_ahmoud

H

H

What

፪) ሰው እንፍጠር ... ዘፍጥረት 1/26 .... "እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር" ከዚህ በፊት እዚህ ጥቅስ ላይ ቆመን አንድ ሐሳብ አውግተናል። የስላሴ አካላት በመለኮታዊ ማንነት አንድ ከኾኑ የመፍጠር ሐሳቡ ከኹሉም በኩል መነሳት ነበረበት፤ ኾኖም ግን ከአብ ብቻ መነሳቱ የወልድንና የመንፈስ ቅዱስን ዝቅተኛነት ያንጸባርቃል። ይሕ ደግሞ የሶስት አቻ አማልክት ስሪት የኾነውን -ስላሴን ገደል ይከተዋል ብለናል። አብ ብቻ አዳምን የመፍጠር ሐሳብ አነሳ ከተባለ ስላሴአውያን Partialism (Fractional Godhood) የሚባለውን የስላሴ አስተምህሮ እንዲቀበሉ ያስገድዳል። ከፊላዊነት (Partialism_ Fractional Godhood) ሶስት አካላት ተሰባስበው የጋራ አንድ አካል ፈጠሩ የሚል አስተምህሮ ነው። ይሕ ደግሞ እያንዳንዱ አካል 1/3 የስላሴን በትረ_ስልጣን ይቀራመታል እንደ ማለት ነው። በሌላ አባባል እያንዳንዱ የስላሴ አካል በራሱ ምሉዕ መለኮታዊ ኃልና ስልጣን የለውም ማለት ነው። ይሕንን "ንፍቅና" ለመሸሽ አንዳንድ ክርስቲያኖች አምላክ ራሱን በሶስት መልክ አስገኘ_አብ፣ወልድ፣መንፈስ ቅዱስ በማለት ለማስረዳት ይሞክራሉ። ይሕ ደግሞ "አገላለጥ" (Modalism / Sabellianism _One God in Different Roles) የሚባለውን የስላሴ አስተምህሮ ይወክላል። በአጭሩ አንድ አምላክ ራሱን በሶስት መልክ ገለጸ እንደ ማለት ነው። እዚህ ላይ ቆም ብለን ያ ራሱን በሶስት መልክ ያስገኘው አካል ማን ነው? ብለን እንጠይቃለን። አብ ነው ካሉ፣ አብ ከሶስቱ አካላት አንዱ እንጂ ራሱን በሶስት መልክ የገለጠው አካል አይደለም። ስለዚህ ራሱን በሶስት መልክ የገለጠው ማነው? ይሕ አስተምህሮ የኒቂያን ስላሴ በሚል ብዙዃኑ ክርስቲያን የሚያምንበትን ሶስት የተለያዩ ግን ደግሞ ዝንተ_ዓለማዊ የኾነ እኩል ስልጣን ካላቸው አካላት አስተምሕሮ ጋር ይጣረሳል። የኒቂያው "ስላሴ" ሶስት በግልጽ የሚለያዩ ግን በስልጣን እኩል የኾኑ በምግባር ደግሞ _ አብ የማይወለድ፣ወልድ ተወላጅ፣መንፈስ ቅዱስ ሰራጺ አካላትን ይሰብካል። ወደ መጽሐፉ ገብቶ ከኹሉም የስላሴ አስተምህሮ ዓይነቶች አንዱን እንኳ ለማግኘት የሞከረ ሳያገኘው ቀርቶ አምላክ አንድ እሱም ሰው ያልኾነና የማይሞት እንደኾነ ይረዳል። ኢየሱስን አምላክ ለማድረግ የሚታትሩ አካላት ይሕንን ጥቅስ በዋቢነት ሲጠቀሙ ይታያል፦ ማቴዎስ 28/18 "ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው። ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር #ተሰጠኝ#። " ተሰጠኝ የሚለው ኀይለ ቃል ኢየሱስ የኾነ ጊዜ ያልነበረውን አብ እንደሰጠው በግልጽ ያሳያል። ታዲያ ይሕ መሰጠት መለኮታዊ ኃይልንም ጭምር ካጠቃለለ፣አብ መለኮታዊ ኃይሉን ለወልድ እንዳካፈለ ወይም እንደሰጠ እንረዳና በእግረ መንገዳችን ደግሞ ሰጪ በላጭ ተቀባይ ደግሞ አናሳ እንደኾነ እንገነዘባለን። በዚህ ጥቅስ ብቻ ያሳለፍናቸው ኹሉም የስላሴ አስተምሕሮዎች ገደል ይገባሉ። ኢየሱስ ከአብ ስልጣን ኹሉ ከተሰጠው፣የስላሴ ሶስተኛው አካል መንፈስ ቅዱስስ ስልጣኑን ማን ሰጠው? .... ይቀጥላል

የአዲስ ሰማይ በጢስ ሲታጠን.. ... ዒሻ ሰግደን እየወጣን አንድ አስም ብጤ ያለበት ሰው ለመተንፈስ ሲቸገር አየኹ። ኹሌም መሰል ችግር ያለበት ሰው ሲሰቃይ ካየን እንደ መጀመሪያ እርዳታ ከጀርባው በኩል አንገቱንና ትከሻውን የሚያያይዘውን አካባቢ (Beauty bone areas) ደረቱን ጨምሮ ማሻሸት እጅግ ይጠቅማል። ለማንኛውም የሰውዬውን ኹኔታ እያሰላሰልኹ "በዚህ ልክ በበዓል ስም አየር ሲበከል ያየ አንድ የአካባቢ ጥበቃ (Environmental Science) ባለሙያ ምን ሊያስብ ይችል ይኾን? ብዬ ራሴን ጠየቅኹ። መቼም አመክንዮአዊ አምላክ ይሕንን የአየር ብከላና ደን ምንጠራ በበዓል ስም ፈጽሙ ብሎ ያዛል ብሎ አያምንም። ዛሬ ላይ ዓለም በካርበን ልቀት እየተወዛገበ ባለበት ተጨባጭ ደን እያቃጠሉ መዘመር አምላክን ያስደስታል ብሎ ማሰብ ወቅቱን ያላማከለ የድንጋይ ዘመን ሕሳቦ ብቻ ነው የሚኾነው። ለዚህ ደግሞ ከአተነፋፈስ ጋር ተያይዞ ችግር ያለባቸው ሰዎች በዚሕ እፍን_እምቅ ባለ አየር ውስጥ ምን ያሕል ሊቸገሩ እንደሚችሉ ያየ ኹሉ እማኝ መኾን ይችላል። ከዚህ ጋር ተያይዞ በጎረቤት ሐቅ ስም ተጠርቼአለኹና መገኘት አለብኝ በማለት ደመራው ዙሪያ የምትኮለኮሉ ሙስሊም ጎረቤቶች፣ ዐቅላችኹን የወሰደው ምንም ይኹን እሱ ይረገም!!! እናንት ግዑዛን ነገ በአረቄ "ከሚደምቀው" አጋፋሪያቸው ዘንድ ተጠርቼአለኹ ብላችኹ እንደምትጣዱ እጠረጥራለኹ። ሞጣ ላይ ከዐመታት በፊት የኾነው ኹሉ ለዚህ ወጋችን ታላቅ ምሳሌ ነው። በዕድሜ ከጠኑት በላይ ከዕውቀት መሃይምነትን የመረጡ ወጣቶች ከአውደ ምሕረታቸውም እየተገኙ "አልሓምዱሊላህ"እያሉ እያየን ነው። ዕውነት ዕውነት እሎታለኹ ወዳጄ በዚህ ልክ አላዋቂነትን መውደድ ከእንስሳት ዓለምም የለም። ምክንያቱም እንስሳትም ቢኾኑ ተፈጥሮአዊ ባሕሪያቸውን በመጠቀም የሚጠቅማቸውን ቅጠል ይቀነጥባሉ። መርዝማ የኾኑ እጽዋትንም ይሸሻሉ። ታዲያ ሰው ምን ያሕል ባላዋቂነት ፍቅር ቢከንፍ ነው ይሕንን ኹሉ የሚዳፈረው? ድፍረት ነው እንዳይባል፣ ሰው ምንም ያሕል የኻሊድ ቢን ወሊድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ዓይነት የብረት ልብ ቢኖረው በአያቃጥለኝም አጓጉል እብሪት እጁን ጎመራ ውስጥ አይነክርም። ወዳጄ እየኾነ ያለው ኹሉ ወላእና በራእ የተዘነጋበት፣በአጭሩ ኢስላም ያሰመረው መስመር ችላ የተባለበት እንደኾነ ልብ ይሏል። ነገ ሴቶቻችን ከነርሱ ቢጋቡ ምን አለ?ዋናው መቻቻላችን ነው የሚል በሌላ ጫማ ውስጥ የሚራመድ ትውልድ እንዳይመጣ ያሰጋል።።

...ሰው እንፍጠር ... የክርስቲያኑ አምላክ "ስላሴ" ከኾነ፣ስላሴን የሰሩት ሶስቱ አካላት እያንዳንዳቸው በተናጠል ምሉዕ አምላክ ሊባሉ አይችሉም። ኢየሱስ ብቻውን፣አብም ብቻውን፣መንፈስ ቅዱስም ብቻውን አምላክ ሊባል አይችልም። ይህ ማለት ደግሞ "ስላሴ" የሚባለው አምላክ በሶስት አካላት የጋራ ጥምረት የተሰራ ነው። ይህ ማለት አኹንም ሶስት እኩል መለኮታዊ ኃይል ያላቸው አካላት ተባብረው የጋራ ጥምር መለኮት ፈጠሩ ነው። ይሕ ሐሳብ ግን ከበርካታ ጥቅሶች ጋር ይጣረሳል፦ "እግዚአብሔርም አለ። ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤ ዘፍጥረት 1/26 "ስላሴ" እኩል ኃይል ያላቸው የሶስት አማልክት ጥምር ውጤት ከኾነ፣ያሳለፍነው ጥቅስ ላይ እየተናገረ ያለ እግዚአብሄር አብ ነው። ኢየሱስም መንፈስ ቅዱስም ዝም ብለዋል። ኾኖም ግን በትክክል ሶስቱም እኩል ስልጣን ካላቸው በአምሳላቸው ሰው የመፍጠር ሐሳብ ከኹሉም መነሳት ነበረበት። ያ ሳይኾን ግን ሐሳቡ ከአብ ብቻ መነሳቱ በመካከላቸው ቢያንስ የአሰላስሎ ክሕሎት ልዩነት እንዳለ ያሳያል። ይሕ ደግሞ ሶስት የተለያየ መለኮታዊ ኃይል ያላቸው በመንበረ_ስልጣን የሚለያዩ አማልክት ያደርጋቸዋል። ሌላው ጥቅሱን ስንፈታታ የምንረዳው ስላሴ የሚባለውን "አምላክ" ሶስት አማልክት ሲፈጥሩት የተፈጠረው ስላሴአዊ አምላክ በሰው አምሳያ ኾኖ መገኘቱ ነው። "አብን ማንም አላየውም፦ እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም፤ ለእርሱ ክብርና የዘላለም ኃይል ይሁን፤ አሜን" 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 6:16 መንፈስ ቅዱስም የማይታይ ነው። ብቸኛው የታየው አካል ወልድ ነው። ታዲያ አዳም የተፈጠረው በአምሳላቸው ነው ወይስ በወደፊቱ ወልድ አምሳል? በወልድ አምሳል ነው ከተባለ ኢየሱስስ ወደ ምድር ከመምጣቱ በፊት በሰው መልክና ቅርጽ አልነበረም። ነበር ከተባለ ደግሞ የወልድ አምሳልና ቅርጽ ብቻውን የስላሴን አንዱን ክፍል እንጂ ሙሉ ስላሴን አይወክልም። ታዲያ እንዴት "በአምሳላችን" ተባለ? ... በአላህ ፍቃድ ጉዳዩን እየፈታታን እናየዋለን!! https://t.me/E_M_ahmoud

Yes

فإن الكريم المحسن أشرح الناس صدراً، وأطيبهم نفساً، وأنعمهم قلباً، والبخيل الذي ليس فيه إحسان أضيق الناس صدراً، وأنكدهم عيشاً، وأعظمهم هماً وغماً...» ኢብኑል ቀዩም " ዛዱል መዓድ" በተሰኘ መጽሐፉ ኹለተኛው ቅጽ ላይ فصل: «في أسباب شرح الصدر، وحصولها على الكمال له صلى الله عليه وسلم በሚል ንዕስ ክፍል ስር ከላይ ያሰፈረኩትን ሐሳብ ያነሳል፦ "ለጋስና ቸር ሰው ልበ_ሰፊ ፣ ውስጥ እስራቱ ቀና የኾነ፣ ልቡም ከሁሉ በላይ የተመቸችና የተደሰተች ናት። ስሳታም ሰው ግን በተቃራኒው ከሰዎች ሁሉ ደረቱ የጠበበ፣ ኑሮው የተተረማመሰ፣ ጭንቀቱና ትካዜው እጅግ የተጋነነ ነው...» በማለት ኹለት ዓይነት ሰዎችን ያወዳድራል። ከሰዎች መካከል ያለቸውን በሰጡና ባገዙ ልክ እጅግ ደስተኛ የኾኑ ጥቂት አሉ። እነዚህ ሰዎች ከጊዜ ጀምሮ ዕውቀታቸውንና ገንዘባቸውን ለግሰው ተጨማሪ በኖረኝ ደግሜ ባደረግኹት የሚሉ ናቸው። ከሰዎች መካከል ደግሞ ስስታቸው ተከምሮ ከሰማይ ቀበሌ የደረሰ፣ለራሳቸው እንኳ እጅግ ንፉጎች፣ ትንሽ ባገኙ ቁጥር ከሰዎች እጅጉን የሚሸሹ ብዙ አሉ። እነዚህ ሰዎች ከሰዎች የሚያገኙት ትንሽ ጥቅም ካለ ከሰዎች ደጃፍ ጎዝጉዘው ቢለማመኑ አይሰቃቸውም። እነርሱ ዘንድ ንዋይ ማንዣበብ የጀመረ ጊዜ በሐምሌ ጸሐይ ልኬት ራሳቸውን ከአድማስ ባሻገር ቢሸሽጉ ይወዳሉ። ባላችኹ ዕውቀትና ጊዜ ሰዎችንና ዳዕዋውንም እያገዛችኹ ያላችኹ በሙሉ ሰላም በናንተ ላይ ይኹን!!! ጣቶቻቾኹ ነገ በጀነት "አልማዝ" የሚያሸበርቁ፥ እጆቻችኹ በጀነት አምባር የሚንቆጠቆጡ ያድርገው። https://t.me/E_M_ahmoud

አንድ የአይሁድ ራባይ የራሳቸውን "ቅዱስ" መጽሐፍ በራረዘና አሳትሞ ለራሳቸው ልሒቃን ሰጠቸው። አዲሱን እትም የተቀበሉት ራባዮችም ግለሰቡ የሰራውን ብረዛዎች ስላላወቁ እንደ አምላክ ቃል ተቀበሉት። አይሁዳዊው ራባይም ቀጠለና የክርስቲያኑን መጽሐፍ በነካ ዕጁ በራርዞ አሳተመና የክርስቲያን ቀሳውስት ሰጠቸው። ቀሳውስቱም የተፈጠረውን ባለማወቃቸው እንደ ፈጣሪ ቃል ተቀበሉት። ራባዩ ቀጠለና አንዳንድ የቁርኣን አያቶችን በረዝረዝ አድርጎ በአዲስ መልክ አሳተመና ወደ መስጂድ ይዞ ሄደ። እንደ ደረሰም የራሱን እትም "ቁርአን" መስጂድ ላገኛቸው ሐፊዞች በስጦታ መልክ አበረከተ። እዛው ሰውዬው ሩቅ ሳይሄድ ሐፊዞቹ የሰጣቸው መጽሐፍ የተበረዘ እንጂ ቁርአን እንዳልኾነ አስረግጠው ነግረው በፊቱ ወረወሩለት። በዝህች አጋጣሚ ብቻ ያ የአይሁዱ ራባይ ኢስላምን ተቀብሏል።  ŘĽŮŮ†Ů‘َا نَحْنُ نَزَّلْنَا الذِّكْرَ وَإِنَّا لَهُ لَحَافِظُونَ

ቢታሰብበት ... ከሰሞኑን በርካታ የቁርኣን መርከዞች ቁርኣን ያሳፈዟቸውን አሊያም ክረምት ላይ ሲያስተምሯቸው የቆዩትን ልጆች እያስመረቁ ይገኛሉ። ምርቃቱ መልካም ኾኖ ሳለ ግን በጥቅሉ መርከዞቻችን እጅግ የጥራት ጉድለት እንደሚያንሳቸውም ይገነዘቧል። የጥራት ክፍተቱን ተከትሎ የሚያሶመርቋቸው ሐፊዞች ላይ የሚነሱ ብዙ ማስተካከያዎችም (ملاحاظات) አሉ። አንድ ቁርኣን የተሸከመ ሰው ሊኖረው ከሚገባ ባሕሪ ጀምረን ቁርኣኑ በራሱ በትክክል አለመቀራቱን ስናይ በአንበሳ ጫማ ምርት ልኬት በዚህ ልክ በየዓመቱ ያልጥራት የሚመረቁ ልጆች የነገው ትውልድ ኡስታዞች ናቸውና አላህ (ሱብሓነሁ ወተዓላ) ያላለውን ነገር ተማሪዎቻቸውን እንደሚያስተምሩና ስሕተቱም ከትውልድ ትውልድ እየዘለለ ሊነባበር እንደሚችል ቀላል ልብ ይሏል!!! በዚህ አጋጣሚ በስርዓት አስተምረውና በጥሩ ተርቢያም ቀርጸው የሚያስመርቁ መርከዞች መኖራቸውን አንዘነጋም። ሌላውና እጅግ አሳሳቢው ጉዳይ የተመራቂ ልጆች ወላጆች ልክ እንደ ግዴታ ለኡስታዞች እየገዙ የሚሰጧቸው ስጦታዎች መብዛታቸው ነው። አንድ ጀለቢያ ለራሱ መቀየር እንኳ ያልቻለ ወላጅ በገንዘብ ሲያስተምሩ ለቆዩ ኡስታዞች በስጦታ ስም ሺህ ብሮችን አውጥቶ በብድር ጭምር ጀለቢያ እንዲገዛ አስገዳጅ ባህል ቀስ እያለ መፈጠሩን ስንቶች እንዳስተዋልን አላውቅም። ከጀለቢያው ባሻገር ኹሉንም የመርከዙ ኡስታዞች ሰብስበው ድል ባለ ድግስ ብፌ ማስነሳትም አሉ። ይሕንን ኹሉ ኖሮት ሳይቸገር አላህን ለማመስገን ምስኪኖችን ሳይከለክል የሚያበላ ሰው በትክክልም ለአላህ የሚገባ ሹክር ነውና አላህ (ሱብሓነሁ ወተዓላ) ይቀበለው። አካሄዱ ግን የቀን ውሎአቸውን እንኳ ማሸነፍ ያልቻሉ ወላጆችን ጭምር እጅግ እየፈተነና አላስፈላጊ ብድር ውስጥ እየከተተ በመኾኑ በየዓመቱ በነጻ ጀለቢያ እየሰበሰቡ ያሉ ኡስታዞቹ ጭምር "አይኾንም ተው !"ሊሉ ይገባል። https://t.me/E_M_ahmoud

ቁርአን ከመጽሐፍ ቅዱስ ወስዷልን.m4a9.07 MB

አዲስ እና ልዩ አጭር ኮርስ ከሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል | #1ኛ ዙር ስልጠና ​“ቁርአን ብቻ ይበቃናል” የሚሉ አካላት መነሻቸው ምንድን ነው? የሱና (ሀዲስ) አስፈላጊነትና በኢስላም ውስጥ ያለው ድርሻ
አዲስ እና ልዩ አጭር ኮርስ ከሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል | #1ኛ ዙር ስልጠና ​“ቁርአን ብቻ ይበቃናል” የሚሉ አካላት መነሻቸው ምንድን ነው? የሱና (ሀዲስ) አስፈላጊነትና በኢስላም ውስጥ ያለው ድርሻስ ምን ያህል ነው? ​እነዚህን እና ሌሎች ተያያዥ አንገብጋቢ ጥያቄዎችን በሰፊው የሚዳስሰውን 1ኛ ዙር የንፅፅር ትምህርት ኮርስ በማዕከላችን የቴሌግራም ቻናል ይዘንላችሁ ቀርበናል። • ​አዘጋጅ፦ ኢልያህ ማሕሙድ • ​የሚሰጥበት ቦታ፦ በሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል የቴሌግራም ቻናል ​ይህንን ወሳኝ ኮርስ ሙሉ በሙሉ ተከታትለው በመጨረሻም የሚዘጋጀውን ፈተና ለሚወስዱ እና ለሚያልፉ ተሳታፊዎች በሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል በኩል የምስክር ወረቀት ይሰጣል። ​እውቀትን ከትክክለኛው ምንጭ እንቅሰም! ትምህርቱን ለመጀመር የቴሌግራም ቻናላችንን አሁኑኑ ይቀላቀሉ፦ https://t.me/Hidayaic8212