uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀

💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀

Kanalga Telegram’da o‘tish

« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر» قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ ↓↓↓↓↓↓ @Ass_Selefyaa1bot @Ass_Selefyaa1bot

Ko'proq ko'rsatish

📈 Telegram kanali 💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀 analitikasi

💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀 (@https_asselefya1) Amxar til segmentidagi kanali faol ishtirokchi. Hozirda hamjamiyat 13 787 obunachidan iborat bo'lib, Din & Maʼnaviyat toifasida 6 303-o'rinni va Efiopiya mintaqasida 2 575-o'rinni egallagan.

📊 Auditoriya ko‘rsatkichlari va dinamika

невідомо sanasidan buyon loyiha tez o‘sib, 13 787 obunachiga ega bo‘ldi.

06 Noyabr, 2026 dagi oxirgi ma’lumotlarga ko‘ra kanal barqaror faollikka ega. Oxirgi 30 kunda obunachilar soni -183 ga, so‘nggi 24 soatda esa -6 ga o‘zgardi va umumiy qamrov yuqori darajada qolmoqda.

  • Tasdiqlash holati: Tasdiqlanmagan
  • Jalb etish (ER): Auditoriya o‘rtacha 25.02% darajada jalb etiladi. Nashrdan keyingi dastlabki 24 soatda kontent odatda umumiy obunachilar sonining 6.58% ini tashkil etuvchi reaksiyalarni to‘playdi.
  • Post qamrovi: Har bir post o‘rtacha 3 450 marta ko‘riladi; birinchi sutkada odatda 907 ta ko‘rish yig‘iladi.
  • Reaksiyalar va o‘zaro ta’sir: Auditoriya faol: har bir postga o‘rtacha 1 ta reaksiya keladi.

📝 Tavsif va kontent siyosati

Muallif resursni shaxsiy fikrni ifoda etish maydoni sifatida ta’riflaydi:
“« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر» قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ ↓↓↓↓↓↓ @Ass_Selefyaa1bot @Ass_Selefyaa1bot”

Yuqori yangilanish chastotasi (oxirgi ma’lumot 07 Noyabr, 2026 da olingan) sababli kanal doimo dolzarb va katta qamrovli bo‘lib qoladi. Analitika auditoriya kontent bilan faol hamkorlik qilishini, uni Din & Maʼnaviyat toifasidagi muhim ta’sir nuqtasiga aylantirishini ko‘rsatadi.

13 787
Obunachilar
-624 soatlar
-267 kun
-18330 kun
Postlar arxiv
ይሄን ኢንሻአላህ እጨርስላችኃለሁ

➾ሱመያህ ቢንት ኸይጥ ረዲየላሁ አንሃ ▰▱▰▱▰▱▰▱▰▱▰▱▰ ➩አቡ ጀህል የተጎዳ አካሏን በጣጠሰው ስጋዋ እዚህም እዛም ተከተፈ። በዚያ መልኩ ስቃይ ላይ ሆና ሞተች። አዎን ሱመያ ሞተች። ዲኗን ይዛ፣ አቋሟን ጠብቃ ወደ መጨረሻው አለም ሄደች። በእስልምና ታሪክ የመጀመሪያዋ ሰመአት ሆነች። አላህ ይዘንላት። ዛሬ እኛ እንደዋዛ የተመለከትነው እስልምና በዚህና በመሳሰሉት መልኩ ስቃይ ተከፍሎበታል። ከወንድም ከሴትም በርካቶች መስዋት ሆነውለት ነው ከእኛ ዘንድ የደረሰው። እኛ ግን ሌላው ቀርቶ ምንዳ በሚያስገኙልን ሸሪአዊ ድንጋጌዎች ላይ እንኳን መፅናት አቅቶናል። ሂጃብን አስተካክለሺ ልበሺ አለብስም በሚል ግብግብ ውስጥ ነን። ተኳኩለሺ አትወጭም እወጣለሁ በሚል ሰጣ ገባ ውስጥ ነን። ይህ ሁሉ እምነታችንን ደረጃና ጥልቀቱ ምን ያህል እንደሆነ አመልካች ነው። የያሲርና የሱመያን ቤተሰብ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸው። የእስልምና ሰማዕታት ታሪክ ሲወሳ መዝገቡ በቅድሚያ የሚጠራው ወንድን ሳይሆን ሴትን ነው። እስልምና ሱመያን የመጀመሪያዋ ሸሂድ ይላታል። አወን ሱመያ ሸሂድ ሆነች። በአላህ መንገድ ተሰዋች። ዲኗን እንደያዘች ዝንፍ ሳትል ተሰዋች። በርግጥም በቀደምት ሙስሊሞች ተጋድሎ ብዙ የምንማራቸው ቁም ነገሮች አሉ።
➩ምንኛ እድለኛ ናት በአላህ ጌታዋ የሚፈልግባትን አድርጋ ሞተች። ውዴታዋን የምኞቶች ሁሉ ጣሪያ አድርጋ ሞተች። በሀይማኖቷ ላይ ፀናች። ሀይማኖቷን ይዛ ሞተች። እስልምና ከወጣትም ሆነ ከጎልማሳ ከሴትም ሆነ ከወንድ ብዙ ጀግኖች አፍርቷል። እናት ሱመያ አንዷ ናት። የነ አማር እናት፣ የያሲር ባለቤት ያሰቃዮት ማሰቃየት ግድ አልሰጣትም።
የስቃይ ብዛት ከእምነቷ አልመለሳትም። አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላት። ከምርጥ ጀነቱም ያሳርፋት። ➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷ https://t.me/https_Asselefya1

አትሸወድ! አንድ አንድ ሰው ስታየው ሰው ይመስላል አጢነህ ስታየው ባዶ መሆኑን ትገነዘባለህ። =t.me/AbuSufiyan_Albenan
አትሸወድ! አንድ አንድ ሰው ስታየው ሰው ይመስላል አጢነህ ስታየው ባዶ መሆኑን ትገነዘባለህ። =t.me/AbuSufiyan_Albenan

የጧሊበል ዒልም መለያ.mp34.74 KB

القارئ_سعود_الشريم_لتجدن_أشد_الناس.mp36.28 MB

🌙🌟•تلاوة صباحية•💫⭐️ ﴿وَٱلَّذِينَ يُحَآجُّونَ فِى ٱللَّهِ مِنۢ بَعْدِ مَا ٱسْتُجِيبَ لَهُۥ حُجَّتُهُمْ دَاحِضَةٌ عِندَ رَبِّهِمْ وَعَلَيْهِمْ غَضَبٌ وَلَهُمْ عَذَابٌ شَدِيدٌ ۝﴾ 🎙قارئ : عبدالله الخلف «አንድ ነገር ደጋግመን ስንሰማው እንሰለቻለን የአሏህን ቃል ግን ይበልጥ እናፈቅረዋለን።» «አሏህ ቁርዓንን የልባችን መርጊያ የመንገዳችን ብርሃን ያድርግልን» ➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➴ https://t.me/https_Asselefya1 https://t.me/https_Asselefya1

ፈገግም አደረገኝ…«እሄ ገጣጣ ማጭድ¡» ~ብቻ…ስኬት ልፋትን፣ ቁርጠኝነትን፣ እና ሌሎችም ብዙ ነገሮችን የሚጠይቅ ጉዞ ነው። ይህ ጉዞ ሁልጊዜ ቀላል ላይሆን ይችላል፣ ነገር ግን በመጨረሻ ስኬት ማግኘት ሁሉንም የሚጠይቀውን ዋጋ አለው። እና ሐቢቢ ኢጃዛ ቤቱንም ትደርስበታለህ ጠንክረህ ስራ ሀሀ¡¡ =t.me/AbuSufiyan_Albenan

አፋልጉኝ! السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ከስር በፎቶ የምትመለከቷቸው አባት ስማቸው ጀማል አህመድ ይባላሉ። በመስከረም 23/2017 ከወራቤ ወደ ሻሸመኔ ጉዞ ጀምረው በመሀል ድምፃ
አፋልጉኝ! السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ከስር በፎቶ የምትመለከቷቸው አባት ስማቸው ጀማል አህመድ ይባላሉ። በመስከረም 23/2017 ከወራቤ ወደ ሻሸመኔ ጉዞ ጀምረው በመሀል ድምፃቸው ጠፍቷል። ስልክ ሳይዙ ሰለወጡ ከቤተሰቦቻቸው ጋር የሚገናኙበት መንገድ የላቸውም። ልጆቻቸው በከባድ ጭንቀት ውስጥ ይገኛሉ። ምናልባት ያገኛቸው ካለ 0916692699 በመደወል ይተባበሩን። ሼር አድርጉት።

تلاوة من سورو الكهف .m4a12.42 MB

➾ተዋት ትመርበት
ለሱናዋ ቆንጆ ለሒጃቧ ንግስት የተውሒድ አርበኛ ሰለፊይዋ እንስት እንቅፋት አትሁናት ኢልሟን ትቅሠምበት በተውሒድ ብርሃን ትደግ ትድመቅበት በንፁሕ ልቧላይ ኢማን ትትከልበት በአቂዳ ብትር ሽርክን ትግረፍበት ተው እንቅፋት አትሁን በሕይወት መስመሯ በቃ እሷ አትንካት ተዋት ትኑር ከእነክብሯ!!

✍️ነቢዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲ ይላሉ፦ ➾ሶስት ሴት ልጅ ያለው ሰው በትዕግስት መግቦ አጠጥቶ አልብሶ ያሳደገ ሰው የቂያማ ቀን ከእሳት ግርዶ ይሆኑለታል። 📚رواه ابن ماجه وأحمد و
✍️ነቢዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲ ይላሉ፦ ➾ሶስት ሴት ልጅ ያለው ሰው በትዕግስት መግቦ አጠጥቶ አልብሶ ያሳደገ ሰው የቂያማ ቀን ከእሳት ግርዶ ይሆኑለታል። 📚رواه ابن ماجه وأحمد وصححه الألباني ➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷ https://t.me/https_Asselefya1

➾ሱመያህ ቢንት ኸይጥ ረዲየላሁ አንሃ ➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬ ➩የመጀመሪያዋ ሰመዓት እሙ አማር ሱመያህ ቢንት ኸይጥ ረዲየላሁ አንሃ ትባላለች። ከእስልምና በፊት የአቡ ጀህል አገልጋይ ባሪያ ነበረች። አላህ ሱበሃነሁ ተአላ ነብዩን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን እስልምናን አሲዞ በላከ ጊዜ እሷ፣ባሏና፣ ልጇ ሰለሙ። ቤተሰቧ ደሃና የሚላስ የሚቀመስ የሌለው ችግርተኛ ቤተሰብ ነው። ሀብት የለው! ወገን የለው! ➾እስልምናን በተቀበሉ ወቅት አቡ ጀህል ይሄንን ቤተሰብ ይፈታተን ጀመር። ከያዙት እምነት እንዲመለሱ በመሻት ያለማቋረጥ የቅጣት ማአቱን ያወርድባቸው ነበር። በቃጠሎና በጥም ነፍሳቸውን እስኪስቱ ድረስ ያሰቃያቸዋል።በከባድ የበረሃ ሀሩር ላይ ያስራቸዋል። የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እነርሱ እየተቀጡ ባሉበት ሁኔታ በአካባቢው ያልፉ ነበር። ስቃያቸው በርትቶ ደማቸውም ሰውነታቸው ላይ ሲፈስ ያያሉ። በቅጣትና ግርፋት ብዛት የሰውነት ቆዳቸው ገርጥቶ ደግሞ ስቃያቸውን አባብሶታል። ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም የተከታዮቻቸውን ሁኔታ እያዩ ምንም ማድረግ ባለመቻላቸው በእጅጉ ያዝናሉ። በህመማቸው ይታመማሉ።  "የያሲር ቤተሰቦች ሆይ"! ታገሱ ቀጠሯችሁ ጀነት ነው። ከማለት ውጭ ምንም ማድረግ አልቻሉም።
➪መካ በዘመነ ጃህልያ እንድህ ነበረች። ሀብታሙ ደሃውን የሚቀጣበት። ጉልበት ያለው ደካማውን የሚሰብርባት ነበረች። በመካ የተከታዮቻቸውን ስቃይ ለመከላከል ጉልበት ያልነበራቸው ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም በዚች ቃል ውድ ሰሀቦቻቸውን ያፅናናሉ። ከተስፋዎች ሁሉ ምርት በሆነው የጀነት ተስፋ ሞራላቸውን ይገነባሉ። እነርሱም በርሳቸው ቃል ይበረታታሉ። እርሳቸውን ሲያዩ በተስፋ ይሞላሉ።ውስጣቸው በደስታ ይፍነከነካሉ።
➾ወዲያውኑ የዚህ ኡመት ፊርዓውን የተባለው የተረገመው አቡ ጀህል ብቅ ይላል።ሲያያቸው ንደቱ ይጨምራል። ቁጣውም ያይላል ቅጣቱንም ከፍ ያደርግባቸዋል።ሙሀመድና ጌታውን ስደቡ። የሁበልና የኡዛን ጣኦት ስም ከፍ አድርጉ። በማለት ያሰቃያቸዋል።ቅጣቱ ፅናትና ትዕግስት እንጂ አይጨምርላቸውም። እልሁ እየተባባሰው መጥፎው ሰው አቡ ጀህል አንካሴውን ያነሳል። ወዲያውኑ በቁጣ ጀግናዋን ሴት በሰው ልጂ ታሪክ ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ የጭካኔ አወጋግ ይወጋታል። ብልቷ ስር ነበር የወጋት ደሟ በከፍተኛ ሁኔታ ይፈሳል የእናትነት አጥንቷ ይሰባበራል። ትጮሃለች.........! ያ አላህህ ➩ልጇና ባለቤቷ ስቃይ ላይ ሆነው ከጎኗ ናቸው። ድርጊቱን በታሰሩበት ሆነው ከመመልከት ውጭ ምንም ሊያደርጉላት አልቻሉም። አቡ ጀህል ይሳደባል፣ ይራገማል፣ እርሷም ሞት አፋፍ ላይ ሆና ፅናቷን ታሳያለች። "አላሁ አክበር" ትላለች። ◉ ◉ ◉✍️ይቀጥላል ➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷ https://t.me/https_Asselefya1

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ፕሮግራማችን ሊጀመር ነው! ገባ ገባ በሉ! https://t.me/Sle_qelbachn1?livestream=

❞الواسطة بين الحق والخلق ❝ ❛አል ዋሲጠህ በይነል ሐቂ ወል ኸልቅ❜       【መግቢያ ከባለፈ የቀጠለ ❺】 «ዑመር ኢብኑ ዐብዲል ዐዚዝ እንድህ ይላሉ» ፦ እኛ  የምናስተካክለዉ  ጉዳይ ከአላህ ዉጭ ምንም አጋዥ የለዉም። ታላላቆች አልቀዉበታል። ህፃናቶች ሸብተዉበታል። ባለሀገሮች ተሰደዉበታል። እምነት ነዉ ብለዉ ያስቡታል እርሱ ግን ከአላህ ዘንድ እምነት አይደለም።  በዚህ ላይ አዲስ ነገር የለም፦ መልእክተኛዉ ﷺ እንድህ ሲሉ የእስልምናን እንግዲነት ተናግረዋል"እስልምና እንግዳ ሆኖ ጀመረ ፣እንደጀመረዉ ወደ እንግድነት ይመለሳል። ለእንግዶች ጡባ(በዱኒያ መልካም ኑሮ በአኼራ ያማረ መመለሻም) አላቸዉ። «ሙስሊም በቁጥር 145 ዘግበዉታል።» መልክተኛዉ ﷺእንዲህ ይላሉ፦ "ለእንግዶች ጡባ አላቸዉ። እነዚያ ሰዎች ሲበላሹ የሚያስተካክሉ ለሆኑት። (አቡ ዑመር አድዳኒ ሶሒሕ በሆነ ሰነድ ዘግበዉታል) መልእክተኛዉﷺጉረባእ ማለት ምን ማለት ነዉ ? ከተባሉ በኋላ እንዲህ አሉ፦ በመጥፎ ሰዎች ዉስጥ ያሉና ከሚታዘዛቸዉ ይልቅ የሚያምፃቸዉ የሚበዙ ጥሩ ሰዎች ናቸዉ አሉ። (ሐዲሱ ሶሒሕ ነዉ ኢማሙ አሕመድ ዘግበዉታል ሶሒሑል ጃሚዕ ቁጥር 3918 ይመልከቱ) «ይህች ቡዲን በማስተካከሉ ዘርፍ ላይ ሙስሊሞች ነቅተዉ ወደ ትክክለኛ እስልምና እስኪመለሱ ድረስ የተሀዲሶን መብራት በ ማብራት ጠንክራ መስራት አለባት። ተፃራሪ ለሆኑ አጥፊዎች አላህ ለአምሳያዎቻቸዉ ያለዉን እንላለን፦ 
« وَمَا لَنَاۤ أَلَّا نَتَوَكَّلَ عَلَى ٱللَّهِ وَقَدۡ هَدَىٰنَا سُبُلَنَاۚ وَلَنَصۡبِرَنَّ عَلَىٰ مَاۤ ءَاذَیۡتُمُونَاۚ وَعَلَى ٱللَّهِ فَلۡیَتَوَكَّلِ ٱلۡمُتَوَكِّلُونَ »
"መንገዳችንንም በእርግጥ የመራን ሲኾን በአላህ ላይ የማንመካ ለእኛ ምን አለን ? በማሰቃየታችሁም ላይ በእርግጥ እንታገሳለን። በአላህ ላይ ተመኪዎች ይመኩ።" (ኢብራሂም :12) «አሁን "አል ወሳኢጥ በይነል ሐቂ ወል ኸልቅ" በተሰኘችዉ ምርጥ መልእክታቸዉ አል ወሳኢጥን እንድያብራሯት  መድረኩን ለሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ እንተዉላቸዉ።  «ይች በወርቅ ብዕር ልትፃፍ ይገባል። ሙስሊሞችም በነብያትና በደጋግ ሰዎች ቀብር ዙሪያ መዞራቸዉን ትተዉ፤ በፍርሃትና በዉርደት በቆሻሻቸዉ መተባበስ ርቀዉ፣ ከእንቅልፋቸዉ ነቅተዉ፤ የሃይልን፣ የዲልን አድራጊነትን ምክንያት ይዘዉ በአጽንኦት እና በማስተንተን ላማሯት ይገባል። «መልካም ነገሮችን ሁሉ አስተማሪ በሆኑት ነብያችን ሙሐመድ ላይ የአላህ ሶላት ይዉረድ በቤተሰቦቻቸዉ እና በባልደረቦቻቸዉ ላይ ይስፈን።   የመጨረሻ ጸሎታችን ምስጋና ሁሉ ለአላማቱ ጌታ አላህ ይሁን ።(ሞሕሙድ መህዲ የቱሕፈቱል ዐሩስ ኪታብ ባለቤት) ✍️ኢንሻ አላህ ይቀጥላል......!   ​•┈┈•┈┈•⊰✿◇✿⊱•┈┈•┈┈• http://t.me/https_Asselefya1

➾የፅናት ተምሳሌት የሆነችውን የሱመያህ ቢንት ኸይጥን ታሪክ ባጭሩ ላስነብባችሁ??