cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

➜ ከዚህ ቻናል አንብባችሁ በተጠቀማችሁ ቁጥር፤ይህን ደካማ እና ስህተቱ ብዙ የሆነውን ወንድማችሁን በመልካም ዱዓችሁ አስታውሱት! || ✍ወንድማችሁ አቡ ሱፍያን―

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
18 409
Obunachilar
+18924 soatlar
+3277 kunlar
+61230 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Photo unavailableShow in Telegram
~አንዳንድ ሀጃዎቻችንን በመደበቅ ልናግዛቸው ይገባል።―ይህ ነብያዊ አስተምሕሮትም ነው― ምክንያቱም አይኖች አያዝኑላቸውም። ከተሳኩም በቅናተኞች እጅ የነገር ሙከራ ይደረግባቸዋል፣ ካልተሳኩም በወረኞች አንደበት ማላገጫ ይሆናሉ።  በዝምታ ሰርተን… ምናልባት ውጤቶች እንዲናገሩ ማድረግ ይሻላል። =t.me/AbuSufiyan_Albenan
Hammasini ko'rsatish...
~የስልክ ሱሰኛ የሆነች ሴት ወይም የስልክ ሱሰኛ የሆነ ወንድ ትዳሩ ላይ ችግር መፍጠሩ አይቀርም። | ስታገቡ የጫት ሱስ ብቻ አትመልከቱ¡ =t.me/AbuSufiyan_Albenan
Hammasini ko'rsatish...
የስልክ ሱስ በ ትዳር ላይ.mp32.96 MB
ዛሬ ከዓሱር ብኃላ በሰላም መስጁድ የሚሰጠው ደርስ አይኖረንም
Hammasini ko'rsatish...
~አንዳንድ ሰዎች ንግግርህ ደስ ስለሚላቸው በተለይ በስልክ ብዙ እንድታወራቸው ይፈልጋሉ ። ግና ብዙ ማውራት ብዙን ጊዜ ኸይር እንደሌለው እንድታውቁ ይሁን። ብዙ ባወራህ ቁጥር ንግግርህ ሀሳቡም ጣዕሙም እያለቀ ይሄዳል። በመጨረሻም ትስታለህ፣ትሳሳታለህ፣ ያልሆነ ነገር መቀባጠር ትጀምራለህ። ቀጥሎም ንግግርህ እንጨት እንጨት ማለት ሲጀምር ከወዲያ በኩል ምን እያልክ ነው? ምን ለማለት ፈልገህ ነው?… የሚል ግብግብ ይመጣል። አውራኝ እንጂ 40 ደቂቃ ብቻ እኮ ነው ያወራነው የሚሉትን እንዳትሰሟቸው። የስልክ ንግግራችሁን አሳጥሩ እሺ። «የንግግር ሁሉ ምርጡ አጠር ያለው እና ፍሬው ላይ ትኩረት ያደረገው ነው።» ብለዋል ረሱላችን! =t.me/AbuSufiyan_Albenan
Hammasini ko'rsatish...
ድንገት ያለምንም ምክንያት… ከልክ በላይ ከምትወዳቸው ነገሮች ጀርባ መሮጥ ታቆማለህ። … የምትፈልገው ብቸኛ ነገር…  ሰላም መሆንና የልብ መረጋጋት ይሆናል። =t.me/AbuSufiyan_Albenan
Hammasini ko'rsatish...
Repost from N/a
01:27
Video unavailableShow in Telegram
ማረኝ ጌታዬ ሆይ የአምና ከች አምና ክምሩ ወጅሌ......... በኡስታዝ ሙሀመድ ሲራጅ https://t.me/Altewhid1
Hammasini ko'rsatish...
9.40 MB
Photo unavailableShow in Telegram
«አትርገሙት… እርሱኮ አላህና መልዕከተኛውን ይወዳል።» ረሱል(ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም)በየጊዜው መጠጥ እየጠጣ የሚገረፍ ሰሓባቸውን አስመልክቶ የተናገሩት ቃል ነበር። ታውቃለህ? ጊዜ ያዳልጣል፣ ትናንትና ዛሬ አንድ ላትሆን ትችላለህ…ስሜትህ አሸንፎህ ኃጢያት ውስጥ ትዘፈቅ ይሆናል… ምናልባት ለመቁጠር የሚያዳግት ኃጢያት ውስጥ…ግን የአላህና የመልዕክተኛው ፍቅር ከውስጥህ አይለይ።መውደድህን ቀጥል። አንድ ቀን ፍቅር በተግባር ይገለጣል። ውዴታህ ስሜትህን ያሸንፋል! =t.me/AbuSufiyan_Albenan
Hammasini ko'rsatish...
~በነገራችን ላይ…የቤት ዋጋ እየቀነሰ ከሆነና እጃችሁ ላይ ብር ካለ ጨምራችሁ ግዙ።ቤት መሠረታዊ ፍላጎቶች ውስጥ ዋነኛው ስለሆነ ወርዶ አይቀርም።እየጨመረም ከሆነ አትንገብገቡ። የሀገራችን የግንባታ ሁኔታ ካየነው የሕዝብ ቁጥር እየጨመረ የመንግሥት የግንባታ ትኩረት የመዝናኛ ኢንደስትሪው ላይ ነው። ይልቅስ የአከራይ ተከራይ አዋጅና መመሪያ ላይ ነው እየሠራ ያለው።ግንባታ እየጨመረ ካልሄደ አዋጅ ብቻውን መፍትሔ አይሆንም።ከፍተኛ የሆነ የቤት ፍላጎት አለ። ብራችሁን መኪና ላይ የምታደርጉ እህቶችና ወንድሞችም ብርን መኪና ላይ ማዋል ጥሩ ቢሆንም ቴክኖሎጂ ስለሚያስረጀው ጥንቃቄ ይፈልጋል። ሕግ ይበዛዋል።በየቀኑ ማሻሻያ ይደረግበታል። ይህንን ባገናዘበ ሁኔታ መሆን ይኖርበታል። =t.me/AbuSufiyan_Albenan
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
~ነብዩ(ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) የጣት ቀለበታቸውን በትንሿ ጣት ላይ ነበር የሚያደርጉት። በቀኝ እጃቸው ጣት ላይ እንደሚያደርጉ 12 ሀዲሶች ተዘግበዋል። በግራ እጃቸው ስለመሆኑ የሚገልፁት ደግሞ 7 ሀዲሶች ናቸው።ስለዚህ በየትኛውም እጅ ጣት ላይ ማድረግ ይቻላል። የቀኙ ግን አመዛኝ ነው። =t.me/AbuSufiyan_Albenan
Hammasini ko'rsatish...
~በጣም መንገብገብ፣ በጣም ክፍት መሆን፣ በጣም ራስን መስጠት ብዙ ጊዜ በጣም  ያዋርዳል። ሁለተኛ ሰው ወይም አማራጭ የሚታይበት ሰው ያስደርጋል። ሁሉንም ነገር ሰጥቶ  አንድ ነገር እንዲሰጡት የሚለምን አይነት ሰው ያስደርጋል። ሰዎች ያልተዘጋጁበትና ያላሰቡት ዓይነት ቦታ  ስትመጣላቸው ይኮራሉ። በእጅ ያለወርቅ እንደመዳብ የሚሉትን ዓይነት እንዲሆኑ እናደርጋቸዋለን… በራሳችን እጅ።  አንዳንዴ  «አይመቸኝም»ያስፈልጋል። አንዳንዴ «ፈልገው ይደውሉ» ብሎ መተውም ያስፈልጋል። እንዳንዴ … ሲመስለኝ። =t.me/AbuSufiyan_Albenan
Hammasini ko'rsatish...
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.