💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
前往频道在 Telegram
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر» قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ ↓↓↓↓↓↓ @Ass_Selefyaa1bot @Ass_Selefyaa1bot
显示更多📈 Telegram 频道 💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀 的分析概览
频道 💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀 (@https_asselefya1) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 13 787 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 6 303,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 575 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 13 787 名订阅者。
根据 06 十一月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 -183,过去 24 小时变化为 -6,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 25.02%。内容发布后 24 小时内通常能获得 6.58% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 3 450 次浏览,首日通常累积 907 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 1。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله
ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ
↓↓↓↓↓↓
@Ass_Selefyaa1bot
@Ass_Selefyaa1bot”
凭借高频更新(最新数据采集于 07 十一月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。
13 787
订阅者
-624 小时
-267 天
-18330 天
帖子存档
➾ሱመያህ ቢንት ኸይጥ ረዲየላሁ አንሃ
▰▱▰▱▰▱▰▱▰▱▰▱▰
➩አቡ ጀህል የተጎዳ አካሏን በጣጠሰው ስጋዋ እዚህም እዛም ተከተፈ። በዚያ መልኩ ስቃይ ላይ ሆና ሞተች። አዎን ሱመያ ሞተች። ዲኗን ይዛ፣ አቋሟን ጠብቃ ወደ መጨረሻው አለም ሄደች። በእስልምና ታሪክ የመጀመሪያዋ ሰመአት ሆነች። አላህ ይዘንላት።
ዛሬ እኛ እንደዋዛ የተመለከትነው እስልምና በዚህና በመሳሰሉት መልኩ ስቃይ ተከፍሎበታል። ከወንድም ከሴትም በርካቶች መስዋት ሆነውለት ነው ከእኛ ዘንድ የደረሰው። እኛ ግን ሌላው ቀርቶ ምንዳ በሚያስገኙልን ሸሪአዊ ድንጋጌዎች ላይ እንኳን መፅናት አቅቶናል። ሂጃብን አስተካክለሺ ልበሺ አለብስም በሚል ግብግብ ውስጥ ነን። ተኳኩለሺ አትወጭም እወጣለሁ በሚል ሰጣ ገባ ውስጥ ነን። ይህ ሁሉ እምነታችንን ደረጃና ጥልቀቱ ምን ያህል እንደሆነ አመልካች ነው። የያሲርና የሱመያን ቤተሰብ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸው። የእስልምና ሰማዕታት ታሪክ ሲወሳ መዝገቡ በቅድሚያ የሚጠራው ወንድን ሳይሆን ሴትን ነው። እስልምና ሱመያን የመጀመሪያዋ ሸሂድ ይላታል። አወን ሱመያ ሸሂድ ሆነች። በአላህ መንገድ ተሰዋች። ዲኗን እንደያዘች ዝንፍ ሳትል ተሰዋች። በርግጥም በቀደምት ሙስሊሞች ተጋድሎ ብዙ የምንማራቸው ቁም ነገሮች አሉ።
➩ምንኛ እድለኛ ናት በአላህ ጌታዋ የሚፈልግባትን አድርጋ ሞተች። ውዴታዋን የምኞቶች ሁሉ ጣሪያ አድርጋ ሞተች። በሀይማኖቷ ላይ ፀናች። ሀይማኖቷን ይዛ ሞተች። እስልምና ከወጣትም ሆነ ከጎልማሳ ከሴትም ሆነ ከወንድ ብዙ ጀግኖች አፍርቷል። እናት ሱመያ አንዷ ናት። የነ አማር እናት፣ የያሲር ባለቤት ያሰቃዮት ማሰቃየት ግድ አልሰጣትም።የስቃይ ብዛት ከእምነቷ አልመለሳትም። አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላት። ከምርጥ ጀነቱም ያሳርፋት። ➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷ https://t.me/https_Asselefya1
Repost from 𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
አትሸወድ!
አንድ አንድ ሰው ስታየው ሰው ይመስላል አጢነህ ስታየው ባዶ መሆኑን ትገነዘባለህ።
=t.me/AbuSufiyan_Albenan
🌙🌟
•تلاوة صباحية•💫⭐️
﴿وَٱلَّذِينَ يُحَآجُّونَ فِى ٱللَّهِ مِنۢ بَعْدِ مَا ٱسْتُجِيبَ لَهُۥ حُجَّتُهُمْ دَاحِضَةٌ عِندَ رَبِّهِمْ وَعَلَيْهِمْ غَضَبٌ وَلَهُمْ عَذَابٌ شَدِيدٌ ﴾
🎙قارئ : عبدالله الخلف
«አንድ ነገር ደጋግመን ስንሰማው እንሰለቻለን የአሏህን ቃል ግን ይበልጥ እናፈቅረዋለን።»
«አሏህ ቁርዓንን የልባችን መርጊያ የመንገዳችን ብርሃን ያድርግልን»
➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➴
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1Repost from 𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
ፈገግም አደረገኝ…«እሄ ገጣጣ ማጭድ¡»
~ብቻ…ስኬት ልፋትን፣ ቁርጠኝነትን፣ እና ሌሎችም ብዙ ነገሮችን የሚጠይቅ ጉዞ ነው። ይህ ጉዞ ሁልጊዜ ቀላል ላይሆን ይችላል፣ ነገር ግን በመጨረሻ ስኬት ማግኘት ሁሉንም የሚጠይቀውን ዋጋ አለው። እና ሐቢቢ ኢጃዛ ቤቱንም ትደርስበታለህ ጠንክረህ ስራ ሀሀ¡¡
=t.me/AbuSufiyan_Albenan
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
አፋልጉኝ!
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
ከስር በፎቶ የምትመለከቷቸው አባት ስማቸው ጀማል አህመድ ይባላሉ።
በመስከረም 23/2017 ከወራቤ ወደ ሻሸመኔ ጉዞ ጀምረው በመሀል ድምፃቸው ጠፍቷል። ስልክ ሳይዙ ሰለወጡ ከቤተሰቦቻቸው ጋር የሚገናኙበት መንገድ የላቸውም። ልጆቻቸው በከባድ ጭንቀት ውስጥ ይገኛሉ። ምናልባት ያገኛቸው ካለ 0916692699 በመደወል ይተባበሩን።
ሼር አድርጉት።
➾ተዋት ትመርበትለሱናዋ ቆንጆ ለሒጃቧ ንግስት የተውሒድ አርበኛ ሰለፊይዋ እንስት እንቅፋት አትሁናት ኢልሟን ትቅሠምበት በተውሒድ ብርሃን ትደግ ትድመቅበት በንፁሕ ልቧላይ ኢማን ትትከልበት በአቂዳ ብትር ሽርክን ትግረፍበት ተው እንቅፋት አትሁን በሕይወት መስመሯ በቃ እሷ አትንካት ተዋት ትኑር ከእነክብሯ!!
✍️ነቢዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲ ይላሉ፦
➾ሶስት ሴት ልጅ ያለው ሰው በትዕግስት መግቦ አጠጥቶ አልብሶ ያሳደገ ሰው የቂያማ ቀን ከእሳት ግርዶ ይሆኑለታል።
📚رواه ابن ماجه وأحمد وصححه الألباني
➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
https://t.me/https_Asselefya1
➾ሱመያህ ቢንት ኸይጥ ረዲየላሁ አንሃ
➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬
➩የመጀመሪያዋ ሰመዓት እሙ አማር ሱመያህ ቢንት ኸይጥ ረዲየላሁ አንሃ ትባላለች። ከእስልምና በፊት የአቡ ጀህል አገልጋይ ባሪያ ነበረች። አላህ ሱበሃነሁ ተአላ ነብዩን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን እስልምናን አሲዞ በላከ ጊዜ እሷ፣ባሏና፣ ልጇ ሰለሙ። ቤተሰቧ ደሃና የሚላስ የሚቀመስ የሌለው ችግርተኛ ቤተሰብ ነው። ሀብት የለው! ወገን የለው!
➾እስልምናን በተቀበሉ ወቅት አቡ ጀህል ይሄንን ቤተሰብ ይፈታተን ጀመር። ከያዙት እምነት እንዲመለሱ በመሻት ያለማቋረጥ የቅጣት ማአቱን ያወርድባቸው ነበር። በቃጠሎና በጥም ነፍሳቸውን እስኪስቱ ድረስ ያሰቃያቸዋል።በከባድ የበረሃ ሀሩር ላይ ያስራቸዋል። የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እነርሱ እየተቀጡ ባሉበት ሁኔታ በአካባቢው ያልፉ ነበር። ስቃያቸው በርትቶ ደማቸውም ሰውነታቸው ላይ ሲፈስ ያያሉ። በቅጣትና ግርፋት ብዛት የሰውነት ቆዳቸው ገርጥቶ ደግሞ ስቃያቸውን አባብሶታል። ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም የተከታዮቻቸውን ሁኔታ እያዩ ምንም ማድረግ ባለመቻላቸው በእጅጉ ያዝናሉ። በህመማቸው ይታመማሉ። "የያሲር ቤተሰቦች ሆይ"! ታገሱ ቀጠሯችሁ ጀነት ነው። ከማለት ውጭ ምንም ማድረግ አልቻሉም።
➪መካ በዘመነ ጃህልያ እንድህ ነበረች። ሀብታሙ ደሃውን የሚቀጣበት። ጉልበት ያለው ደካማውን የሚሰብርባት ነበረች። በመካ የተከታዮቻቸውን ስቃይ ለመከላከል ጉልበት ያልነበራቸው ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም በዚች ቃል ውድ ሰሀቦቻቸውን ያፅናናሉ። ከተስፋዎች ሁሉ ምርት በሆነው የጀነት ተስፋ ሞራላቸውን ይገነባሉ። እነርሱም በርሳቸው ቃል ይበረታታሉ። እርሳቸውን ሲያዩ በተስፋ ይሞላሉ።ውስጣቸው በደስታ ይፍነከነካሉ።➾ወዲያውኑ የዚህ ኡመት ፊርዓውን የተባለው የተረገመው አቡ ጀህል ብቅ ይላል።ሲያያቸው ንደቱ ይጨምራል። ቁጣውም ያይላል ቅጣቱንም ከፍ ያደርግባቸዋል።ሙሀመድና ጌታውን ስደቡ። የሁበልና የኡዛን ጣኦት ስም ከፍ አድርጉ። በማለት ያሰቃያቸዋል።ቅጣቱ ፅናትና ትዕግስት እንጂ አይጨምርላቸውም። እልሁ እየተባባሰው መጥፎው ሰው አቡ ጀህል አንካሴውን ያነሳል። ወዲያውኑ በቁጣ ጀግናዋን ሴት በሰው ልጂ ታሪክ ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ የጭካኔ አወጋግ ይወጋታል። ብልቷ ስር ነበር የወጋት ደሟ በከፍተኛ ሁኔታ ይፈሳል የእናትነት አጥንቷ ይሰባበራል። ትጮሃለች.........! ያ አላህህ ➩ልጇና ባለቤቷ ስቃይ ላይ ሆነው ከጎኗ ናቸው። ድርጊቱን በታሰሩበት ሆነው ከመመልከት ውጭ ምንም ሊያደርጉላት አልቻሉም። አቡ ጀህል ይሳደባል፣ ይራገማል፣ እርሷም ሞት አፋፍ ላይ ሆና ፅናቷን ታሳያለች። "አላሁ አክበር" ትላለች። ◉ ◉ ◉✍️ይቀጥላል ➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷ https://t.me/https_Asselefya1
በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ፕሮግራማችን ሊጀመር ነው! ገባ ገባ በሉ!
https://t.me/Sle_qelbachn1?livestream=
❞الواسطة بين الحق والخلق ❝
❛አል ዋሲጠህ በይነል ሐቂ ወል ኸልቅ❜
【መግቢያ ከባለፈ የቀጠለ ❺】
«ዑመር ኢብኑ ዐብዲል ዐዚዝ እንድህ ይላሉ» ፦
እኛ የምናስተካክለዉ ጉዳይ ከአላህ ዉጭ ምንም አጋዥ የለዉም። ታላላቆች አልቀዉበታል። ህፃናቶች ሸብተዉበታል። ባለሀገሮች ተሰደዉበታል። እምነት ነዉ ብለዉ ያስቡታል እርሱ ግን ከአላህ ዘንድ እምነት አይደለም። በዚህ ላይ አዲስ ነገር የለም፦ መልእክተኛዉ ﷺ እንድህ ሲሉ የእስልምናን እንግዲነት ተናግረዋል"እስልምና እንግዳ ሆኖ ጀመረ ፣እንደጀመረዉ ወደ እንግድነት ይመለሳል። ለእንግዶች ጡባ(በዱኒያ መልካም ኑሮ በአኼራ ያማረ መመለሻም) አላቸዉ። «ሙስሊም በቁጥር 145 ዘግበዉታል።»
መልክተኛዉ ﷺእንዲህ ይላሉ፦ "ለእንግዶች ጡባ አላቸዉ። እነዚያ ሰዎች ሲበላሹ የሚያስተካክሉ ለሆኑት። (አቡ ዑመር አድዳኒ ሶሒሕ በሆነ ሰነድ ዘግበዉታል)
መልእክተኛዉﷺጉረባእ ማለት ምን ማለት ነዉ ? ከተባሉ በኋላ እንዲህ አሉ፦ በመጥፎ ሰዎች ዉስጥ ያሉና ከሚታዘዛቸዉ ይልቅ የሚያምፃቸዉ የሚበዙ ጥሩ ሰዎች ናቸዉ አሉ። (ሐዲሱ ሶሒሕ ነዉ ኢማሙ አሕመድ ዘግበዉታል ሶሒሑል ጃሚዕ ቁጥር 3918 ይመልከቱ)
«ይህች ቡዲን በማስተካከሉ ዘርፍ ላይ ሙስሊሞች ነቅተዉ ወደ ትክክለኛ እስልምና እስኪመለሱ ድረስ የተሀዲሶን መብራት በ ማብራት ጠንክራ መስራት አለባት። ተፃራሪ ለሆኑ አጥፊዎች አላህ ለአምሳያዎቻቸዉ ያለዉን እንላለን፦
« وَمَا لَنَاۤ أَلَّا نَتَوَكَّلَ عَلَى ٱللَّهِ وَقَدۡ هَدَىٰنَا سُبُلَنَاۚ وَلَنَصۡبِرَنَّ عَلَىٰ مَاۤ ءَاذَیۡتُمُونَاۚ وَعَلَى ٱللَّهِ فَلۡیَتَوَكَّلِ ٱلۡمُتَوَكِّلُونَ »"
መንገዳችንንም በእርግጥ የመራን ሲኾን በአላህ ላይ የማንመካ ለእኛ ምን አለን ? በማሰቃየታችሁም ላይ በእርግጥ እንታገሳለን። በአላህ ላይ ተመኪዎች ይመኩ።" (ኢብራሂም :12)
«አሁን "አል ወሳኢጥ በይነል ሐቂ ወል ኸልቅ" በተሰኘችዉ ምርጥ መልእክታቸዉ አል ወሳኢጥን እንድያብራሯት መድረኩን ለሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ እንተዉላቸዉ።
«ይች በወርቅ ብዕር ልትፃፍ ይገባል። ሙስሊሞችም በነብያትና በደጋግ ሰዎች ቀብር ዙሪያ መዞራቸዉን ትተዉ፤ በፍርሃትና በዉርደት በቆሻሻቸዉ መተባበስ ርቀዉ፣ ከእንቅልፋቸዉ ነቅተዉ፤ የሃይልን፣ የዲልን አድራጊነትን ምክንያት ይዘዉ በአጽንኦት እና በማስተንተን ላማሯት ይገባል።
«መልካም ነገሮችን ሁሉ አስተማሪ በሆኑት ነብያችን ሙሐመድ ላይ የአላህ ሶላት ይዉረድ በቤተሰቦቻቸዉ እና በባልደረቦቻቸዉ ላይ ይስፈን። የመጨረሻ ጸሎታችን ምስጋና ሁሉ ለአላማቱ ጌታ አላህ ይሁን ።(ሞሕሙድ መህዲ የቱሕፈቱል ዐሩስ ኪታብ ባለቤት)
✍️ኢንሻ አላህ ይቀጥላል......!
•┈┈•┈┈•⊰✿◇✿⊱•┈┈•┈┈•
http://t.me/https_Asselefya1❞الواسطة بين الحق والخلق ❝

http://t.me/https_Asselefya1