Cecilia School Alamura Branch
Kanalga Telegram’da o‘tish
3 758
Obunachilar
-224 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kun
+5330 kun
Postlar arxiv
ጥቅምት 27 ቀን 2019 ዓ.ም
የቅዳሜ ጥናትን የተመለከተ መረጃ
ለ6ኛ፣7ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች እና ወላጆች:-
✅ነገ ቅዳሜ ጥቅምት 29 ቀን 2019 ዓ.ም የሚሰጠው የቅዳሜ ጥናት መርሃግብር 2:00 ላይ ተጀምሮ 5:45 ላይ ይጠናቀቃል‼️
#ሰሲሊያትምህርትቤትአላሙራካምፓስ
#CARPEDIEMSEIZETHEDAY
ጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ.ም
ለት/ቤታች ወላጆች በመሉ
የ2019 ዓ.ም የአንደኛ መንፈቀ-ዓመት አጋማሽ ፈተና (First Semester Mid Exam) የሚሰጠው ከህዳር 07-11 ቀን 2019 ዓ.ም ባለው ጊዜ ስለሆነ ተማሪዎች በቂ ቅድመ ዝግጅት ያደርጉ ዘንድ ወላጆች በቤት ውስጥ ከምንጊዜውም በተለየ ሁኔታ በቂ ድጋፍና ክትትል እንድታደርጉ እናሳስባለን‼️
#ሰሲሊያትምህርትቤትአላሙራካምፓስ
#CARPEDIEMSEIZETHEDAY
ጥቅምት 25 ቀን 2019 ዓ.ም
🏦ለትምህርት ቤታችን ወላጆች በሙሉ:-
የህዳር ወር የት/ቤት ወርሃዊ ክፍያ የመክፈያ ጊዜ ከጥቅምት 25 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ መሆኑን እየገለፅን የትምህርት ቤት ክፍያ በወቅቱ በመክፈል አላስፈላጊ የቅጣት ወጪ እንዲያስቀሩ እያሳሰብን ወርሃዊ ክፍያዎችን በወቅቱ በመፈጸም ለትምህርት ቤታችን ሥራዎች መሳካት ለምታደርጉት ትብብርና ኃላፊነት የተሞላበት አስተዋጽኦ ከወዲሁ ልናመሰግን እንወዳለን‼️
#ሰሲሊያትምህርትቤትአላሙራካምፓስ
#CARPEDIEMSEIZETHEDAY
#School_Pay_System
+4
🍎 Learning Through Fun at Cecilia School! 🌟
Today, our Lower Kindergarten (LKG) students took part in an exciting and educational activity during the morning assembly. They enthusiastically identified different kinds of fruits, demonstrating their growing knowledge, confidence, and speaking skills.
At Cecilia School, we believe that learning goes beyond the classroom. Through fun and interactive activities, we nurture curiosity, creativity, and confidence in our young learners.
Small steps today, great minds tomorrow! 🌱
#ሰሲሊያትምህርትቤትአላሙራካምፓስ
#CARPEDIEMSEIZETHEDAY
ጥቅምት 24 ቀን 2019 ዓ.ም
ውጤታማ የማጥናት ክህሎትን እንዴት እናዳብር?
ውድ የትምህርት ቤታችን ተማሪዎች!
ትምህርት መማር ብቻ ሳይሆን በተማርነው ነገር ላይ ጥሩ ግንዛቤ መፍጠርና ለረጅም ጊዜ በአእምሯችን ማቆየትም ነው።
ለዚህም የተሻለ የማጥናት ልምድና ክህሎት ማዳበር ያስፈልጋል።
እነሆ ውጤታማ ተማሪ ለመሆን የሚረዱ 10 ጠቃሚ ምክሮች፦
1. የጥናት ጊዜህን አቅድ። 🕒
2. ጸጥ ያለ ቦታ ምረጥ። 🤫
3. በክፍል ውስጥ በንቃት ተሳተፍ። 🙋
4. ያልገባህን ነገር ጠይቅ። ❓
5. በየቀኑ ያጠናኸውን ድገም። 🔄
6. ማስታወሻ ያዝ። ✍️
7. በተግባር ላይ አውል። የሒሳብ ልምምዶችን ሥራ፣ ጥያቄዎችን መልስ፣ የተማርከውንም በራስህ ቃላት ግለጽ።
8. ስልክና ሌሎች አዘናጊ ነገሮችን ተቆጣጠር። 📵
9. በቂ እንቅልፍና እረፍት ውሰድ። 😴
10. በራስህ እመን። 🌟
በትዕግሥትና በተከታታይ ጥረት ስኬትን ማሳካት ይቻላል። ከስህተትህ ተማር፤ ተስፋ አትቁረጥ!
🌟 “ስኬታማ ተማሪ የሚሆነው ብዙ ሰዓት በማጥናት ብቻ ሳይሆን፣ በትክክለኛ ዘዴና በተከታታይ ጥረት በመማር ነው።
#ሰሲሊያትምህርትቤትአላሙራካምፓስ
#CARPEDIEMSEIZETHEDAY
#Tips
+3
ጥቅምት 23 ቀን 2019ዓ.ም
ወርሃዊ ፈተና
ዛሬ ሰኞ ጥቅምት 23 ቀን 2019 ዓ.ም ከ5ኛ-8ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች የአመቱ የሁለተኛ ዙር ወርሃዊ ፈተና በወጣላቸው የፈተና ፕሮግራም መሰረት ከመማር ማስተማር ጎን ለጎን የዕለቱ ፈተና መሰጠት ጀምሯል‼️
ወርሃዊ ፈተናው እስከ ዕለተ አርብ ጥቅምት 27 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ እያስታወስን ውድ ወላጆች በቤት ውስጥ ከምንጊዜውም በተለየ ሁኔታ እንድታግዟቸው ጥርያችንን እናስተላልፋለን።
#ሰሲሊያትምህርትቤትአላሙራካምፓስ
#CARPEDIEMSEIZETHEDAY
#Monthly_Test
ጥቅምት 22 ቀን 2019 ዓ.ም
ወርሃዊ ፈተናን የተመለከተ መረጃ
✅ ከነገ ሰኞ ጥቅምት 23 ጀምሮ እስከ 27 ቀን 2019 ዓ.ም ባለው ሣምንት ከ5-8ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች በወጣው የፈተና ፕሮግራም መሠረት የመንፈቀ ዓመቱ የሁለተኛ ዙር ወርሃዊ ፈተና እንደሚሰጥ በድጋሚ እያስታወስን የጥቅምት ወር የት/ቤት ወርሃዊ ክፍያ እና የጥናት ክፍያዎችን ያልከፈለ ተማሪ ወርሃዊ ፈተና ላይ የማናስቀምጥ(የማይፈተን) መሆኑን ከወዲሁ እየገለፅን ክፍያዎችን ያላጠናቀቃችሁ ወላጆች ያለባችሁን ክፍያ ታጠናቅቁ ዘንድ እናሳስባለን‼️
#ሰሲሊያትምህርትቤትአላሙራካምፓስ
#CARPEDIEMSEIZETHEDAY
#Monthly_Test
ጥቅምት 20 ቀን 2019 ዓ.ም
የቅዳሜ ጥናትን የተመለከተ መረጃ
ለ6ኛ፣7ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች እና ወላጆች:-
✅ነገ ቅዳሜ ጥቅምት 21 ቀን 2019 ዓ.ም የሚሰጠው የቅዳሜ ጥናት መርሃግብር 2:00 ላይ ተጀምሮ 6:25 ላይ ይጠናቀቃል‼️
#ሰሲሊያትምህርትቤትአላሙራካምፓስ
#CARPEDIEMSEIZETHEDAY
ጥቅምት 19 ቀን 2019 ዓ.ም
የነገ አርብ አጫጭር መረጃዎች
✅ነገ አርብ ጥቅምት 20 ቀን 2019 ዓ.ም የት/ቤቱ ማኔጅመንት እና መምህራን ከ7:30 ጀምሮ ውይይት ስለሚኖራቸው:-
✅ከ1ኛ-8ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች የጥናት መርሃ-ግብር ለነገ ብቻ የማይኖር መሆኑን እያሳወቅን
✅ከ6-8ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች ለዚህ ሳምንት ብቻ አርብ ከሰዓት ያላጠኗቸውን ክ/ጊዜዎች ጨምሮ ቅዳሜ ከ2:00-6:25 ድረስ የሚያጠኑ መሆኑን እንገልፃለን!
#ሰሲሊያትምህርትቤትአላሙራካምፓስ
#CARPEDIEMSEIZETHEDAY
ጥቅምት 19 ቀን 2019 ዓ.ም
የሁለተኛ ዙር ወርሃዊ ፈተናን የተመለከተ መረጃ
የተስተካከለ የፈተና ፕሮግራም
✅ ከፊታችን ሰኞ ጥቅምት 23 ጀምሮ እስከ 27 ቀን 2019 ዓ.ም ባለው ሣምንት ከ5-8ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች በወጣው የፈተና ፕሮግራም መሠረት የመንፈቀ ዓመቱ የሁለተኛ ዙር ወርሃዊ ፈተና ስለሚሰጥ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ታደርጉ ዘንድ ከወዲሁ እናሳስባለን።
⚠️ማሣሰቢያ
✅ፈተናው የሚሰጠዉ ከትምህርቱ ጎን ለጎን ስለሆነ ትምህርት ለመሉ ቀን እንደሚሰጥ እና የትምህርት ቁሳቁስ አሟልተው መገኘት እንደሚኖርባቸው እንገልፃለን‼️
✅የጥቅምት ወር የት/ቤት ክፍያ ያልከፈለ ተማሪ ወርሃዊ ፈተና ላይ የማናስቀምጥ(የማይፈተን) መሆኑን ከወዲሁ እናሳስባለን‼️
#ሰሲሊያትምህርትቤትአላሙራካምፓስ
#CARPEDIEMSEIZETHEDAY
#Monthly_Test
+4
ጥቅምት 18 ቀን 2019 ዓ.ም
Learning Through Jumbled Words! 🌟📚
🔠 በዛሬው የሰንደቅ ዓላማ ሥነ-ሥርዓት (Flag Ceremony) ላይ ተማሪዎቻችን ስለ Jumbled Words (የተደበላለቁ ፊደላትን በማስተካከል ትክክለኛ ቃላትን ማውጣት)
አስደሳችና ትምህርታዊ ውድድር አቅርበዋል።
✨ ይህ ተግባር ተማሪዎች የእንግሊዝኛ ቃላትን በትክክል እንዲጽፉ፣ የቃላት እውቀታቸውን እንዲያሳድጉ፣ የማሰብ ችሎታቸውን እንዲያጎለብቱ እና በራስ መተማመን በመድረክ ላይ እንዲቀርቡ የሚያግዝ ተግባር ነው።
💡 “Jumbled Words today, Brilliant Minds tomorrow!” 🧠✨
👏 በዚህ የተማሪዎችን እውቀት፣ ፈጠራ እና ተሳትፎ በሚያበረታታ መርሃ ግብር ለተሳተፉ ተማሪዎችና ለመርሃ ግብሩ አዘጋጆችን እጅግ አድርገን እናመሰግናለን‼️
#ሰሲሊያትምህርትቤትአላሙራካምፓስ
#CARPEDIEMSEIZETHEDAY
#JumbledWords
ጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ.ም
የሁለተኛ ዙር ወርሃዊ ፈተናን የተመለከተ መረጃ
✅ ከፊታችን ሰኞ ጥቅምት 23 ጀምሮ እስከ 27 ቀን 2019 ዓ.ም ባለው ሣምንት ከ5-8ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች በወጣው የፈተና ፕሮግራም መሠረት የመንፈቀ ዓመቱ የሁለተኛ ዙር ወርሃዊ ፈተና ስለሚሰጥ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ታደርጉ ዘንድ ከወዲሁ እናሳስባለን።
⚠️ማሣሰቢያ
✅ፈተናው የሚሰጠዉ ከትምህርቱ ጎን ለጎን ስለሆነ ትምህርት ለመሉ ቀን እንደሚሰጥ እና የትምህርት ቁሳቁስ አሟልተው መገኘት እንደሚኖርባቸው እንገልፃለን‼️
#ሰሲሊያትምህርትቤትአላሙራካምፓስ
#CARPEDIEMSEIZETHEDAY
#Monthly_Test
+4
ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ.ም
🌞 ጤናማ አካል፣ ብሩህ አእምሮ፣ የተሻለ ትምህርት! 💚
ዛሬ ጠዋት ተማሪዎቻችን በጋራ በመሆን የጠዋት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አከናውነዋል።
ይህ ተግባር ተማሪዎች ቀናቸውን በደስታ፣ በጉልበትና በንቃት እንዲጀምሩ ከማገዙም በላይ ለአካላዊና አእምሯዊ ጤንነታቸው ከፍተኛ ጥቅም አለው።
🏃♂️ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ዋና ዋና ጥቅሞች
☑ ለአካላዊ ጤንነት፦ የጡንቻና የአጥንት ጥንካሬን ያጎለብታል፣ የሰውነት ቅንጅትንና ቅልጥፍናን ያሻሽላል።
☑ ለአእምሮ ንቃት፦ የትኩረት ችሎታን ያግዛል፣ ተማሪዎችም በትምህርት ላይ በንቃት እንዲሳተፉ ይረዳል።
☑ ለሥነ ልቦናዊ ደህንነት፦ ውጥረትን ለመቀነስ፣ ደስታን ለመጨመርና በራስ መተማመንን ለማዳበር ይረዳል።
☑ ለማህበራዊ ክህሎት፦ ተማሪዎች በጋራ እንዲሠሩ፣ እንዲተባበሩ፣ ሥርዓትን እንዲጠብቁና የቡድን መንፈስን እንዲያዳብሩ ያግዛል።
☑ ለትምህርት ዝግጁነት፦ ጠዋት የሚደረግ እንቅስቃሴ ተማሪዎች ቀናቸውን በንቃትና በተሻለ የትምህርት ዝግጁነት እንዲጀምሩ ይረዳል።
🌟 ትምህርት ማለት የመጽሐፍ እውቀትን ብቻ ማስጨበጥ ሳይሆን ጤናማ፣ ብቁ፣ በራሳቸው የሚተማመኑና በማህበረሰብ ውስጥ በኃላፊነት የሚሳተፉ ተማሪዎችን ማፍራት ነው።
ስለዚህ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የተማሪዎቻችንን ሁለንተናዊ እድገት ከሚያግዙ አስፈላጊ ተግባራት አንዱ ነው።
#ሰሲሊያትምህርትቤትአላሙራካምፓስ
#CARPEDIEMSEIZETHEDAY
ጥቅምት 13 ቀን 2019 ዓ.ም
የቅዳሜ ጥናትን የተመለከተ መረጃ
ለ6ኛ፣7ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች
✅ነገ ጥቅምት 14 ቀን 2019 ዓ.ም የሚሰጠው የቅዳሜ ጥናት መርሀግብር 2:00 ላይ ተጀምሮ 5:45 ላይ ይጠናቀቃል‼️
🚨ማሳሰቢያ
የጥናት ፕሮግራሙ ላይ የማይገኝ ተማሪ ሰኞ ለመደበኛው ትምህርት ወደ ክፍል የማናስገባ መሆኑን ከወዲሁ ልናሳስብ እንወዳለን‼️‼️
#ሰሲሊያትምህርትቤትአላሙራካምፓስ
#CARPEDIEMSEIZETHEDAY
+5
ጥቅምት 12 ቀን 2019 ዓ.ም
የማለዳ የጋራ ስፖርት እንቅስቃሴ 💚💙
🌞 ዛሬ ጠዋት የአፀደ ሕፃናት ተማሪዎች በደስታና በጉጉት Morning Mass Sport ላይ ተሳትፈዋል። 🏃♂️
🤸♀️ይህ የጋራ የስፖርት እንቅስቃሴ የሕፃናትን አካላዊ ጤና ለማጠናከር፣ የእንቅስቃሴ ችሎታቸውን ለማዳበር፣ በራስ መተማመንን ለመገንባትና የቡድን መንፈስን ለማጎልበት ወሳኝ ሚና አለው። 🌟
💚ጤናማ አካል፣ ብሩህ አእምሮና የተሻለ ነገን አብረን እንፍጠር!
#ሰሲሊያትምህርትቤትአላሙራካምፓስ
#CARPEDIEMSEIZETHEDAY
#Morningmasssport
+5
ጥቅምት 11 ቀን 2019 ዓ.ም
📚 የፊደላት ልየታና የቃላት አመሰራረት በስልፍ መርሃ ግብር! ✨
✅የአፀደ ሕፃናት ተማሪዎቻችን ፊደላትን በመለየትና ፊደላትን በማጣመር ቃላትን የመመስረት ችሎታቸውን በስልፍ መርሃ ግብር ላይ በደስታ አቅርበዋል። 📖
ይህ ተግባር የልጆቻችንን የቋንቋ ክህሎት፣ የማንበብ ዝግጁነት፣ የቃላት ዕውቀትና በራስ የመተማመን ችሎታ ለማዳበር የሚያግዝ ጠቃሚ የትምህርት ተግባር ነው። 🌟
እያንዳንዱ ሕፃን በመማር፣ በመለማመድና በራስ በመተማመን ወደ ስኬት እንዲያድግ እንሠራለን! 💚📚
ሰሲሊያ ትምህርት ቤት — የዛሬ ትንንሽ ተማሪዎች፣ የነገ ታላላቅ ተስፋዎች! 🌱
#ሰሲሊያትምህርትቤትአላሙራካምፓስ
#CARPEDIEMSEIZETHEDAY
+4
ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም
📚🏆 የሰንደቅ ዓላማ ልዩ ፕሮግራም – Spelling Bee Competition 🇪🇹
ዛሬ በት/ቤታችን የሰንደቅ ዓላማ መርሃ ግብር ላይ ተማሪዎቻችን በእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታቸውን፣ በትክክለኛ ፊደል አጻጻፍ ብቃታቸውን እና በራስ መተማመናቸውን ያሳዩበት አስደሳች የSpelling Bee Competition ውድድር ተካሂዷል። 🐝📖
ይህ ውድድር ተማሪዎቻችን የቋንቋ እውቀታቸውን እንዲያዳብሩ፣ የውድድር መንፈሳቸውን እንዲያጎለብቱ እና ለተሻለ ውጤት እንዲተጉ የሚያበረታታ ጠቃሚ ተግባር ነው።
በእውቀት የበለጸገ፣ በብቃት የተደራጀ እና በስኬት የሚያብብ ትውልድ ለማፍራት ቁርጠኛ ነን!
#ሰሲሊያትምህርትቤትአላሙራካምፓስ
#CARPEDIEMSEIZETHEDAY
#SpellingBee
ጥቅምት 07/2019 ዓ.ም
🚨በድጋሚ እናስታውሶ
ለትምህርት ቤታችን ወላጆች በሙሉ:-
✅የጥቅምት ወር የት/ቤት ወርሃዊ ክፍያ ያለቅጣት የሚከፈልበት የመጨረሻ ቀን ዛሬ ጥቅምት 07 ቀን 2019 ዓ.ም መሆኑን አውቀዋል?
ታዲያ ውድ የት/ቤታችን ወላጆች የትምህርት ቤት ክፍያ ዛሬውኑ በመክፈል አላስፈላጊ የቅጣት ወጪ ያስቀሩ እንላለን።
#Birhan_School_Pay_System
#ሰሲሊያትምህርትቤትአላሙራካምፓስ
#CARPEDIEMSEIZETHEDAY
⚠️ማሣሰቢያ
ይህ የጥናት መርሃግብር ተማሪዎችን ለሚኒስትሪ ፈተና የምናዘጋጅበት ቁልፍ ተግባር በመሆኑ ጥናቱ ላይ በጊዜ እንድትገኙ በጥብቅ እየገለፅን የጥናት መርሃግብሩ ላይ የማይገኝ ተማሪ ላይ ት/ቤቱ አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ በጥብቅ እናሳስባለን‼️
+3
ጥቅምት 05 ቀን 2019 ዓ.ም
🌞 የጠዋት እንቅስቃሴ 🤸♀️🏃♂️
ዛሬ ጠዋት የአፀደ ሕፃናት ተማሪዎች የጠዋት የአካል ብቃት እንቅስቃሴን በደስታ አከናውነዋል።
ይህ እንቅስቃሴ የሕፃናትን አካላዊ እድገት፣ ቅልጥፍና፣ ትብብርና የትምህርት ዝግጁነት ለማጎልበት የሚያግዝ ከመሆኑም በላይ ቀናቸውን በንቃት እንዲጀምሩ ያስችላቸዋል።
ጤናማ አካል፣ ንቁ አዕምሮና ደስተኛ ተማሪዎችን እናበረታታለን!🥳
#ሰሲሊያትምህርትቤትአላሙራካምፓስ
#CARPEDIEMSEIZETHEDAY
