Cecilia School Alamura Branch
Открыть в Telegram
3 736
Подписчики
+524 часа
+317 дней
+12430 дней
Архив постов
ጥቅምት 07/2019 ዓ.ም
🚨በድጋሚ እናስታውሶ
ለትምህርት ቤታችን ወላጆች በሙሉ:-
✅የጥቅምት ወር የት/ቤት ወርሃዊ ክፍያ ያለቅጣት የሚከፈልበት የመጨረሻ ቀን ዛሬ ጥቅምት 07 ቀን 2019 ዓ.ም መሆኑን አውቀዋል?
ታዲያ ውድ የት/ቤታችን ወላጆች የትምህርት ቤት ክፍያ ዛሬውኑ በመክፈል አላስፈላጊ የቅጣት ወጪ ያስቀሩ እንላለን።
#Birhan_School_Pay_System
#ሰሲሊያትምህርትቤትአላሙራካምፓስ
#CARPEDIEMSEIZETHEDAY
⚠️ማሣሰቢያ
ይህ የጥናት መርሃግብር ተማሪዎችን ለሚኒስትሪ ፈተና የምናዘጋጅበት ቁልፍ ተግባር በመሆኑ ጥናቱ ላይ በጊዜ እንድትገኙ በጥብቅ እየገለፅን የጥናት መርሃግብሩ ላይ የማይገኝ ተማሪ ላይ ት/ቤቱ አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ በጥብቅ እናሳስባለን‼️
+3
ጥቅምት 05 ቀን 2019 ዓ.ም
🌞 የጠዋት እንቅስቃሴ 🤸♀️🏃♂️
ዛሬ ጠዋት የአፀደ ሕፃናት ተማሪዎች የጠዋት የአካል ብቃት እንቅስቃሴን በደስታ አከናውነዋል።
ይህ እንቅስቃሴ የሕፃናትን አካላዊ እድገት፣ ቅልጥፍና፣ ትብብርና የትምህርት ዝግጁነት ለማጎልበት የሚያግዝ ከመሆኑም በላይ ቀናቸውን በንቃት እንዲጀምሩ ያስችላቸዋል።
ጤናማ አካል፣ ንቁ አዕምሮና ደስተኛ ተማሪዎችን እናበረታታለን!🥳
#ሰሲሊያትምህርትቤትአላሙራካምፓስ
#CARPEDIEMSEIZETHEDAY
ጥቅምት 05 ቀን 2019 ዓ.ም
ለት/ቤታችን ወላጆች በሙሉ
ነገ አርብ ጥቅምት 06 ቀን 2019 ዓ.ም
ለ6ኛ፣ 7ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች
👉አርብ ከ7:30-9:30
👉ቅዳሜ ከ2:00-5:45
የሚሰጠው የጥናት ፕሮግራም በይፋ ይጀመራል።
ስለሆነም:- ከነገ ጀምሮ ዘወትር አርብ በየሳምንቱ ከ6-8ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች ከግቢ የመውጫ ሰዓት 9:30 ላይ መሆኑን በመረዳት የምሳ፣የትራንስፖርትና መሠል ጉዳዮችን ከወዲሁ እንድታመቻችሁ እንገልፃለን።
⚠️ማሳሰቢያ
✅ ከ1-4ኛ ክፍል ላሉ የጥናት ተሳታፊ ተማሪዎች የመውጫ ሰዓት 9:30 እንዲሁም የኤል ኬጂ፣ዩኬጅ እና የ5ኛ ክፍል የጥናት ተሳታፊ ተማሪዎች መውጫ ሰዓት 8:30 መሆኑን እየገለፅን በጥናት መርሃ-ግብሩ ላይ የሚሳተፉ ተማሪዎች ለምሳ ከግቢ መውጣት እንደማይችሉ እና ምሳ ቋጥረው/ ይዘው መምጣት እንዳለባቸው ጭምር ለማሣሰብ እንወዳለን።
#ሰሲሊያትምህርትቤትአላሙራካምፓስ
#CARPEDIEMSEIZETHEDAY
+3
ጥቅምት 05 ቀን 2019 ዓ.ም
🔬 የ7ኛ ክፍል ተማሪዎች የሳይንስ ቤተ ሙከራ ጉብኝት
ውድ የት/ቤታችን ማህበረሰብ፣
የትምህርት ሂደታችንን በተግባር ለማጠናከር የ7ኛ ክፍል ተማሪዎቻችን ወደ ሳይንስ ቤተ ሙከራ በመግባት የተግባር ትምህርት ላይ ተሳትፈዋል። 🧪🔍
ይህ እንቅስቃሴ ተማሪዎቻችን በክፍል ውስጥ የሚማሯቸውን ሳይንሳዊ እውቀቶች በተግባር እንዲረዱ፣ የምርምር ፍላጎታቸውን እንዲያዳብሩና በሳይንስ ዘርፍ ያላቸውን የመማር ፍላጎት እንዲያጎለብቱ ይረዳል።
👏 ለተማሪዎቻችን የተሳካ የተግባር ትምህርት እንመኛለን!
ለዚህ ትምህርታዊ እንቅስቃሴ አስተዋጽኦ ላደረጉ መምህራንም ምስጋናችንን እናቀርባለን።
📚 በተግባር እንማራለን፤ በእውቀት እናድጋለን!
#ሰሲሊያትምህርትቤትአላሙራካምፓስ
#Carpe_Diem_Seize_The_Day
+7
ጥቅምት 05 ቀን 2019 ዓ.ም
🔬 የ7ኛ ክፍል ተማሪዎች የሳይንስ ቤተ ሙከራ ጉብኝት
ውድ የት/ቤታችን ማህበረሰብ፣
የትምህርት ሂደታችንን በተግባር ለማጠናከር የ7ኛ ክፍል ተማሪዎቻችን ወደ ሳይንስ ቤተ ሙከራ በመግባት የተግባር ትምህርት ላይ ተሳትፈዋል። 🧪🔍
ይህ እንቅስቃሴ ተማሪዎቻችን በክፍል ውስጥ የሚማሯቸውን ሳይንሳዊ እውቀቶች በተግባር እንዲረዱ፣ የምርምር ፍላጎታቸውን እንዲያዳብሩና በሳይንስ ዘርፍ ያላቸውን የመማር ፍላጎት እንዲያጎለብቱ ይረዳል።
👏 ለተማሪዎቻችን የተሳካ የተግባር ትምህርት እንመኛለን!
ለዚህ ትምህርታዊ እንቅስቃሴ አስተዋጽኦ ላደረጉ መምህራንም ምስጋናችንን እናቀርባለን።
📚 በተግባር እንማራለን፤ በእውቀት እናድጋለን!
#ሰሲሊያትምህርትቤትአላሙራካምፓስ
#Carpe_Diem_Seize_The_Day
ጥቅምት 03 ቀን 2019 ዓ.ም
ለት/ቤታችን ወላጆች በመሉ
ለስፖርታዊ እንቅስቃሴ ምቹ የሆነ የስፖርት ትጥቅ ለተማሪዎች ከታች በገለፅነው መሠረት እንድታሟሉ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን።
✅ለአፀደ ህፃናት(ኬጂ)-ቢጫ የስፖርት ቁምጣና ቲሽርት ከስፖርት ጫማ ጋር
✅ከ1ኛ-4ኛ ክፍል- ውሃሰማያዊ የስፖርት ቁምጣና ቲሸርት ከስፖርት ጫማ ጋር
✅ከ5ኛ-8ኛ ክፍል-ቀይ የስፖርት ቁምጣና ቲሸርት ከስፖርት ጫማ ጋር
ማሳሰቢያ:-
የአፀደ ህጻናት ተማሪዎች ዕለተ ሐሙስ እንድሁም ከ1ኛ-5ኛ ክፍል ድረስ ያሉ ተማሪዎች ዕለተ ሰኞ የስፖርት ትጥቅ ይዘው መምጣት ይኖርባቸዋል‼️
ጤናማ አዕምሮ ከጤናማ ሰውነት ጋር!
#ሰሲሊያትምህርትቤትአላሙራካምፓስ
#Carpe_Diem_Seize_The_Day
አስደሳች ዜና ለተማሪዎችና ለወላጆች በሙሉ
የ2019 ዓ.ም የኢትዮጵያ ስፔሊንግ ቢ ውድድር ምዝገባ መጀመሩን በታላቅ ደስታ እንገልፃለን!!
ውድድሩ ከ 1ኛ እስከ 4ኛ፤ ከ 5ኛ እስከ 8ኛ እና ከ 9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ባሉ ተማሪዎች በሶስት ምድቦች እንደሚካሄድ እና የ2019 ሀገር አቀፍ ውድድር በክፍለ ከተማ እና በተለያዩ ሀገር አቀፍ ደረጃ ለማካሄድ የሁሉን ክልሎችና የከተማ አስተዳደር ተማሪዎች እንዲሳተፉ ይጋብዛል::
በየደረጃው ያሉ አሸናፊዎች ሽልማቶችን ያገኛሉ በተጨማሪም የአሸናፊዎች አሸናፊ ተማሪዎች በአፍሪካ ውድድር የሚሳተፉ ይሆናል።
ምዝገባ፡- @Ethiopianspellingbeebot ብለው መመዝገብ ይችላሉ።
ለምዝገባ የተቀመጠው የገንዘብ መጠን፡ 2500 ብር የአንድ ጊዜ ክፍያ ሲሆን ይህም የመወዳደሪያ መፅሀፉ (ሀርድ ኮፒ) ለሁሉም ተመዝጋቢ ተማሪዎች በት/ት ደረጃቸው ልክ የተዘጋጀውን የመወዳደሪያ መፅሀፍ በት/ቤታችሁ በኩል የምንሰጥ ይሆናል፡፡ ከት/ት ቤት እስከ ሀገር አቀፍ ውድድር ድረስ የመወዳደሪያ ቁሳቁስን ጨምሮ፤ በተጨማሪም ተማሪዎችን በት/ታቸው የበለጠ ውጤታማ እንዲሆን የሚያስችል የኦንላይን ማጠናከሪያ ት/ት ያካተተ ክፍያ ነው፡፡
ምንም አይነት ተጨማሪ ክፍያ በየትኛውም ዙር የለም ፡፡
ለተወዳዳሪዎች፡ በት/ት ቤት ደረጃ ለተሳተፉ ተማሪዎች በሙሉ የተሳትፎ ሰርተፍኬት ከተቋሙ የሚሰጥ ይሆናል፡፡ በክ/ከተማ ፤በከተማ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚሳተፉ ተማሪዎች ደግሞ ተጨማሪ ሰርተፍኬቶች፤ ሜዳሊያዎች ፤ የብሪቲሽ ካውንስል የ English proficiency exam ፤ መፅሐፍቶች ፤ የከተማ ጉብኝት ፤ ለመጨረሻ ስድስት የአሸናፊዎች አሸናፊ ተማሪዎች በ9ኛው የአፍሪካ ስፔሊንግ ቢ ውድድር ዛምቢያ ላይ የሚሳተፉ ይሆናል፡፡ዝርዝር ሂደቱን በየደረጃዎች የምናሳውቅ ይሆናል፡፡
የኢትዮጵያ ስፔሊንግ ቢ ከሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር
+5
ጥቅምት 02 ቀን 2019ዓ.ም
ወርሃዊ ፈተና
ዛሬ ሰኞ ጥቅምት 02 ቀን 2019 ዓ.ም ከ5ኛ-8ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች የአመቱ የመጀመሪያ ዙር ወርሃዊ ፈተና በወጣላቸው የፈተና ፕሮግራም መሰረት ከመማር ማስተማር ጎን ለጎን የዕለቱ ፈተና መሰጠት ጀምሯል‼️
ወርሃዊ ፈተናው እስከ ዕለተ አርብ ጥቅምት 06 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ እያስታወስን ውድ ወላጆች በቤት ውስጥ ከምንጊዜውም በተለየ ሁኔታ እንድታግዟቸው ጥርያችንን እናስተላልፋለን።
#ሰሲሊያትምህርትቤትአላሙራካምፓስ
#CARPEDIEMSEIZETHEDAY
#Monthly_Test
+7
🏃♀️ A Healthy Start to the Day! 🏃♂️
This morning, our students took part in a lively mass sports session, filling the school grounds with energy and enthusiasm. The activity encouraged fitness, teamwork, and a positive start to the day.
Well done to all our students and staff who participated! 👏
#ሰሲሊያትምህርትቤትአላሙራካምፓስ
#CARPEDIEMSEIZETHEDAY
#SchoolLife #HealthyHabits #Teamwork
ጥቅምት 01 ቀን 2019 ዓ.ም
ለት/ቤታች ወላጆች እና ተማሪዎች በሙሉ፦
የነገ ዕለት ሰኞ ጥቅምት 02 ቀን 2019 ዓ.ም ዕለታዊ መረጃዎች
✅ ከኤል ኬጂ-5ኛ ክፍል ደረስ የሚሰጠው የቀን የጥናት መርሃግብር እንዲሁም
✅ ከ5ኛ-8ኛ ክፍል ደረስ ላሉ ተማሪዎች የመንፈቀ ዓመቱ የመጀመሪያ ዙር ወርሃዊ ፈተና መሰጠት የሚጀምርበት ዕለት መሆኑን ለማስታወስ እንወዳለን‼️
መውጫ
ጥናት ለሚያጠኑ ተማሪዎች የመውጫ ሰዓታቸው 10:30 መሆኑን እንገልፃለን‼️
#ሰሲሊያትምህርትቤትአላሙራካምፓስ
#CARPEDIEMSEIZETHEDAY
መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም
🏦ለትምህርት ቤታችን ወላጆች በሙሉ:-
የጥቅምት ወር የት/ቤት ወርሃዊ ክፍያ ያለ ቅጣት የመክፈያ የመጨረሻ ቀን ጥቅምት 07 ቀን 2019 ዓ.ም መሆኑን እየገለፅን የትምህርት ቤት ክፍያ በወቅቱ በመክፈል አላስፈላጊ የቅጣት ወጪ እንዲያስቀሩ ከወዲሁ እናሳስባለን‼️
#ሰሲሊያትምህርትቤትአላሙራካምፓስ
#CARPEDIEMSEIZETHEDAY
#School_Pay_System
መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም
የመጀመሪያ ዙር ወርሃዊ ፈተናን የተመለከተ መረጃ
✅አስቀድመን ባሳወቅነው የትምህርት መርሃግብር መሠረት በየወሩ መጨረሻ ሣምንት መደበኛ ወርሃዊ ፈተና ይሰጣል።
ስለሆነም:-
ከፊታችን ሰኞ ጥቅምት 02 ጀምሮ እስከ 06 ቀን 2019 ዓ.ም ባለው ሣምንት ከ5-8ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች በወጣው የፈተና ፕሮግራም መሠረት የዓመቱ የመጀመሪያ ዙር ወርሃዊ ፈተና ስለሚሰጥ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ታደርጉ ዘንድ ከወዲሁ እናሳስባለን።
⚠️ማሣሰቢያ
✅ፈተናው የሚሰጠዉ ከትምህርቱ ጎን ለጎን ስለሆነ ትምህርት ለመሉ ቀን እንደሚሰጥ እና የትምህርት ቁሳቁስ አሟልተው መገኘት እንደሚኖርባቸው እንገልፃለን‼️
✅የጥቅምት ወር የት/ቤት ወርሃዊ ክፍያ የመክፈያ ጊዜ ከመስከረም 25 ጀምሮ መሆኑን አውቃችሁ ከወዲሁ የት/ቤት ክፍያ እንድትከፍሉ እናሳስባለን‼️
#ሰሲሊያትምህርትቤትአላሙራካምፓስ
#CARPEDIEMSEIZETHEDAY
#Monthly_Test
መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም
ለት/ቤታችን ወላጆች በመሉ
የጥናት መርሃግብርን በተመለከተ
ሁሌም በየዓመቱ እንደምናደርገው ሁሉ
ከጥቅምት ወር ጀምሮ በግቢያችን ውስጥ ተማሪዎችን ለመደገፍ ሲባል ፦
✅ከሰኞ እስከ አርብ ከየዕለቱ መደበኛ ትምህርት መጠናቀቅ በኋላ ከ9:30 -10:30 ባለው ጊዜ ከ1-5ኛ ክፍል የሚሰጠው የቀን ጥናት
✅የሚኒስትሪ ፈተና ለሚፈተኑ የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ሁሌ በየሣምንቱ አርብ ከሰዓት እና ቅዳሜ በጠዋት ፈረቃ የሚሰጠው የሣምንት ቀናት ጥናት ይከናወናሉ ።
ከዚህ አንፃር በያዝነው የትምህርት ዓመትም የጥናት መርሃግብሩ የሚቀጥል ሆኖ ከምንጊዜውም በተለየ ሁኔታ፦
✅የ5ኛ እና የ7ኛ ክፍል ተማሪዎች በቀጣዩ ዓመት የሚኒስትሪ ፈተና ተፈታኞች ስለሆኑና የሚኒስትሪ ፈተና ጥያቄዎች የሚዘጋጁት ደግሞ ሁለት ተከታታይ ዓመታት ከተማሯቸው ትምህርቶች በመሆኑ ተማሪዎችን አበክረን ለክፍል እና ለሚኒስትሪ ፈተናዎች ለማዘጋጀት ስንል፦
1ኛ. የ7ኛ ክፍል ተማሪዎች ከሁሉም በተለየ ሁኔታ፦
➡️ በትምህርት ፖሊሲው መሠረት ሁሉንም ትምህርት በአማርኛ ሲማሩ ቆይተው ሁሉም ትምህርት በእንግሊዝኛ ሲማሩ በቋንቋው መቀየር ምክንያት የሚገጥማቸውን የመረዳት ችግር ለመቅረፍ(ባደረግነው የዳሰሳ ጥናት መሠረት ስለሚከብዳቸው)
👉 በቀጣዩ ዓመት ሚኒስትሪ ፈተና ተፈታኞች በመሆናቸው ለሚኒስትሪ ፈተናው ከወዲሁ ጠቅላላ ዕውቀትና ዝግጅት እንዲኖራቸው ለማድረግ ሲባል እንደ 6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች ሁሉ፦
አርብ ከሰዓት እና ቅዳሜ ግማሽ ቀን ቢያጠኑ በያዝነው ዓመት የጥሩ ዕውቀትና ውጤት ባለቤት ሆነው ወደ ቀጣዩ ክፍል እንዲዛወሩ እና በቀጣዩ ዓመት ደግሞ በሚኒስትሪ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ለማስመዝገብ ሊያግዛቸው የሚችል በጥናት የተደገፈ ልዩ የጥናት ፕሮግራም ዘርግተናል።
ስለሆነም፦
።።።።።።።።
የተከበራችሁ የት/ቤታችን ወላጆች ተማሪዎቻችንን ለክፍልና ለሚኒስትሪ ፈተናዎች ከወዲሁ ለማዘጋጀት ያግዙን ዘንድ በዘረጋናቸው የጥናት መርሃ-ግብሮች ላይ ልጆቻችሁን ተሣታፊ እንዲሆኑ በማድረግ ለትምህርት ጥራት የራሳችሁን በጎ ተፅዕኖ እንድታሳድሩ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
⚠️ማሳሰቢያ
1ኛ. ከ1-5ኛ ክፍል የሚሰጠው የቀን ጥናት ሰኞ ጥቅምት 02 ቀን 2019 ዓ.ም እንዲሁም
2ኛ. ከ6-8ኛ ክፍል የሚሰጠው የአርብ ከሰዓት እና የቅዳሜ ጠዋት ጥናት አርብ ጥቅምት 06 ቀን 2019 ዓ.ም እንደሚጀመር እየገለፅን የጥናት ክፍያ በአካል ት/ቤት እንደሚከፈል እንገልፃለን‼️
#ሰሲሊያትምህርትቤትአላሙራካምፓስ
#CARPEDIEMSEIZETHEDAY
መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም
የመጀመሪያ ዙር ወርሃዊ ፈተናን የተመለከተ መረጃ
✅አስቀድመን ባሳወቅነው የትምህርት መርሃግብር መሠረት በየወሩ መጨረሻ ሣምንት መደበኛ ወርሃዊ ፈተና ይሰጣል።
ስለሆነም:-
ከፊታችን ሰኞ ጥቅምት 02 ጀምሮ እስከ 06 ቀን 2019 ዓ.ም ባለው ሣምንት ከ5-8ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች በወጣው የፈተና ፕሮግራም መሠረት የዓመቱ የመጀመሪያ ዙር ወርሃዊ ፈተና ስለሚሰጥ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ታደርጉ ዘንድ ከወዲሁ እናሳስባለን።
⚠️ማሣሰቢያ
ፈተናው የሚሰጠዉ ከትምህርቱ ጎን ለጎን ስለሆነ ትምህርት ለመሉ ቀን እንደሚሰጥ እና የትምህርት ቁሳቁስ አሟልተው መገኘት እንደሚኖርባቸው እናሳስባለን!!
#ሰሲሊያትምህርትቤትአላሙራካምፓስ
#CARPEDIEMSEIZETHEDAY
#Monthly_Test
መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም
🏦ለትምህርት ቤታችን ወላጆች በሙሉ:-
የጥቅምት ወር የት/ቤት ወርሃዊ ክፍያ የመክፈያ ጊዜ ከመስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ መሆኑን እየገለፅን የትምህርት ቤት ክፍያ በወቅቱ በመክፈል አላስፈላጊ የቅጣት ወጪ እንዲያስቀሩ ከወዲሁ እናሳስባለን‼️
#ሰሲሊያትምህርትቤትአላሙራካምፓስ
#CARPEDIEMSEIZETHEDAY
#School_Pay_System
መስከረም 23 ቀን 2019 ዓ.ም
📢 ለክቡራን የት/ቤታችን ወላጆች
የልጆቻችንን የትምህርት ውጤት ለማሻሻልና ለክልል አቀፍ ፈተናዎች ለማዘጋጀት የጥናት መርሃ ግብር ተዘጋጅቷል‼️
መርሃ ግብሩ ባለፉት ዓመታት ለተማሪዎቻችን እውቀትና ክህሎት ብሎም ውጤት መሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል።
ባለፉት ተከታታይ ዓመታት በሚኒስትሪ ፈተና ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ከክልሉ ምርጥ 10 ተማሪዎች ውስጥ 60% የሚሆኑትም የትምህርት ቤታችን ተማሪዎች ነበሩ።
📚 የጥናት መርሃ ግብሩ
✅ለ6ኛ፣7ኛ እና 8ኛ ክፍል: ዓርብ ከሰዓት ከ7:30-9:10 እና ቅዳሜ ከ2:00-5:45
✅ለ5ኛ ክፍል: ከሰኞ እስከ ዓርብ ከመደበኛ ትምህርት በኋላ ከ9:30-10:30
✅ከ1ኛ–4ኛ ክፍል: ከሰኞ እስከ ዓርብ ከዕለቱ መደበኛ የትምህርት ክፍለጊዜ በኋላ ከ9:30-10:30
⚠️ ታዲያ የወላጆች ትብብር ወሳኝ ነው!
እባክዎ
✅ ልጆቻችሁ የመርሃግብሩ ተሣታፊ እንዲሆኑ፤
✅ ከትምህርት ቤቱ ጋር በቅርበት ይተባበሩ።
የዛሬ ትጋት የነገ ስኬት ነው!
የጥናት መርሃ ግብሩን እንደግፍ፤ ልጆቻችንን ወደ ስኬት እንምራ! 📚🏆
⚠️መውጫ
የጥናት መርሃግብሩ መቼ እንደሚጀመር በቀጣይ ስለምናሳውቅ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እያደረጋችሁ እንድትጠብቁ ከወዲሁ እናሳስባለን‼️
#ሰሲሊያትምህርትቤትአላሙራካምፓስ
#CARPEDIEMSEIZETHEDAY
መስከረም 21 ቀን 2019 ዓ.ም
ለት/ቤታችን ወላጆችና ተማሪዎች በሙሉ:-
✅ነገ ማለትም አርብ መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ.ም ትምህርት ለግማሽ ቀን/ፈረቃ ብቻ ስለሚሰጥ ወላጆች ልጆቻችሁን 6:20 ላይ እንድትወስዱ እናሳስባለን!
#ሰሲሊያትምህርትቤትአላሙራካምፓስ #CARPEDIEMSEIZETHEDAY
መስከረም 17 ቀን 2019 ዓ.ም
ለትምህርት ቤታችን ተማሪዎች እና ወላጆች በሙሉ:-
✅በድጋሚ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ እያልን ነገ ዕለተ ሰኞ መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ም በሁሉም የክፍል ደረጃዎች ትምህርት የማይኖር መሆኑን እየገለፅን ዕለተ ማክሰኞ መስከረም 19 ቀን 2019
ዓ.ም በሁሉም የክፍል ደረጃዎች ትምህርት ለመሉ ቀን/ፈረቃ እንደሚሰጥ ለማሳወቅ እንወዳለን‼️
በድጋሚ መልካም የመስቀል በዓል እንዲሆንላችሁ እንመኛለን!
#ሰሲሊያትምህርትቤትአላሙራካምፓስ
#CARPEDIEMSEIZETHEDAY
#Happy_Meskel
