cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

አኰቴት ማኅበርነ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን on You Tube > አኮቴት ማኅበርነ https://youtube.com/channel/UC_xyLazdSdBLXAIlvipDhDA አኮቴተ ስብሐት https://t.me/joinchat/WHRepgvlYu7bhEve

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
264
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-17 kunlar
-430 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

#የጥቅምት_11_ማኅሌተ_ጽጌ 1) ሰላም ለኲልያቲክሙ ሰላም ለኵልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወፀ ለሣህል፤ እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ ወበቀራንዮ ተተክለ መድኀኒት መስቀል፡፡ ዚቅ ሃሌ ሉያ (፱) ሐረገ ወይን እንተ በምድር ሥረዊሃ፡ ወበሰማይ አዕፁቂሃ፤ ሐረገ ወይን፤ እንተ በሥሉስ ትትገመድ፡ ወታፈሪ ለነ አስካለ በረከት፤ ሐረገ ወይን ፤ ሲሳዮሙ ለቅዱሳን፤ ሠርዓ ሰንበተ በቃሉ፡ ወጸገወ ሰላመ ለኵሉ። 2)  ትመስል እምኪ ትመስል እምኪ ማርያም ዕለተ ሣልስተ ወራብዕተ፤ ዘወለደት ጽጌ ወፀሐየ ዓለም ብርህተ፤ ወካዕበ ትመስል ሳብዕተ ዕለተ፤ እስመ ፈረየት ኪያኪ ተአምረ ግዕዛን ሰንበተ፤ ለእለ በሰማይ ወምድር ዘኮንኪ ዕረፍተ፡፡ ወረብ ትመስል እምኪ ማርያም ዕለተ ሣልስተ ወራብዕተ ትመስል እምኪ፤ ዘወለደት ጽጌ ጽጌ ጽጌ ወፀሐየ ዓለም። ዚቅ እምኲሉ ዕለት ሰንበተ አክበረ፤ ወእምኲሎን አንስት ማርያምሃ አፍቀረ፤ ከመ ትኲኖ ማኅደረ ለመንፈስ ቅዱስ፤ ወምስጋድ ለኲሉ ዓለም፡፡ 3) ከመ ታቦት ሥርጉት ከመ ታቦት ሥርጉት በወርቀ ዐረብ ወተርሴስ፤ በድንግልና ማርያም ሥርጉተ ሥጋ ወነፍስ፤ ተአምረ ነቢር አርአይኪ በቤተ መቅደስ፤ ኢያቄም ወሐና ቀንሞስ ቀናንሞስ፤ እምዘጸገዩኪ ለጳጦስ በዓመት ሠላስ። ወረብ እምዘጸገዩኪ ለጳጦስ በዓመት ሠላስ ኢያቄም ወሐና ቀንሞስ ቀናንሞስ፤ ተአምረ ነቢር አርአይኪ ተአምረ ነቢር አርአይኪ በቤተ መቅደስ። ዚቅ ሰአሉ ለነ ኢያቄም ወሐና፤ ዘፈረይክሙ በቅድስና፤  መሶበ ወርቅ እንተ መና። 4) እንዘ ተሐቅፊዮ እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤ አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፤ ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላሕ፤ ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፤ ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ፡፡ ወረብ እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤ ንዒ ርግብየ ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ። ዚቅ ዕፀ ጳጦስ ይእቲ እንተ በአማን፤ ይብልዋ ቅድስተ ቅዱሳን፤ ንዒ ርግብየ ሠናይት፤ ወይቤላ መልእከ ተፈሥሒ ፍሥሕት፤ ቡርክት አንቲ እምአንስት፤ ንዒ ርግብየ ሠናይት። 5) ክበበ ጌራ ወርቀ ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየኃቱ፤ ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤ አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፤ አንቲ ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፤ ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ፡፡ ወረብ ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ዘየሐቱ እምዕንቆ ባሕርይ፤ አክሊለ አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ። ዚቅ ይእቲ ተዓቢ እምአንስ፤ እሞሙ ለሰማዕት፤ ወእኅቶሙ ለመላእክት፤ መድኃኒቶሙ ለነገሥት፤ አክሊል ንጹሕ ለካህናት፤ ብርሃኖሙ ለከዋክብት። 6) ተንሥኢ ወንዒ ተንሥኢ ወንዒ ሌዋዊት ሐና፤ ትጼውዓኪ ወለትኪ ከመ ትርአዪ ኃዘና፤ እምርስትኪ ወፅአት ወተሰደት በድክትምና፣ ትበኪ እምዋዕየ ሐጋይ ኀጢኣ በፍና፤ ሕፍነ ማይ ዘታሰትዮ ለፅሙዕ ሕጻና። ወረብ ተንሥኢ ወንዒ ሌዋዊት ሐና ተንሥኢ ወንዒ፤ ትጼውዓኪ ወለትኪ ኃዘና ከመ ትርአዪ። ዚቅ ኢሀለዉ አሜሃ አቡኪ ወእምኪ፤ ከመ ይርአዩ ድክትምናኪ፤ ወይስምዑ ገዓረኪ፣ እስመ ሞቱ እምንእስኪ ወኃደጉኪ ባሕቲተኪ። +++ መዝሙር +++ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፤ ወመኑ ሐሪ ዘከማከ፤ ምስለ ኖኅ ኪዳነ ዘአቀምከ፤ ወመኑ ሐሪ ዘከማከ ፤ ምስለ ኖኅ ኪዳነ ዘአቀምከ ለደቂቀ ፳ኤል መና ዘአውረድከ ፡፡ ወመኑ ሐሪ ዘከማከ፤ ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ፤ ወመኑ ሐሪ ዘከማከ፤ ወስነ ገዳምኒ ምስለ ቅዱሳኒከ፤ ወመኑ ሐሪ ዘከማከ፤ ወከመ ወሬዛ ኃየል መላትሒሁ ጒርዔሁ መዓርዒር አምሳሉ ዘወይጠል፤ ወመኑ ሐሪ ዘከማከ፤ ሰማየ ወምድረ ዘአንተ ፈጠርከ ፀሐየ ወወርኃ ዘአስተዋደድከ፤ ወመኑ ሐሪ ዘከማከ፤ በከዋክብት ሰማየ ዘከለልከ ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ ፡፡ ወመኑ ሐሪ ዘከማከ ፤ ቀደሳ ወአክበራ አዕበያ ለሰንበት ወአልዓላ እምኩሉ ዕለት፤ ወመኑ ሐሪ ዘከማከ፤ ወኲሉ ይሴፎ ኪያከ፡፡ +++  አመላለስ +++ ወመኑ ሐሪ ዘከማከ፤ ወኲሉ ይሴፎ ኪያከ።
Hammasini ko'rsatish...
‹‹ሱላማጢስ ሆይ፥ ተመለሽ፥ ተመለሽ›› (መሓ.፯፥፩) ክፍል አራት ውድ አንባብያን! እንደምን ሰነበታችሁ? ከዚህ በፊት የእመቤታችንን የስደቷን ነገር አንሥተን ‹‹ሱላማጢስ ሆይ፥ ተመለሽ፥ ተመለሽ›› በሚል ርእስ ከክፍል አንድ እስከ ሦስት አድርሰናችሁ ነበር፡፡ ጥሩ ትምህርት እንዳገኛችሁበት ተስፋ እናደርጋለን፡፡ የዛሬው ትኩረታችን ያን ሁሉ መከራ የተቀበለችበት የስደቷን ምክንያትና ዓላማ መዳሰስ ነው፡፡ ከዚያ በፊት ግን ስለ ግብጻዊው ወንበዴ ማለትም በጌታ ቀኝና በግራ ስለተሰቀለው ፈያታዊ ዘየማን ትንሽ ታሪክ እንጨምርና ወደ ዋናው ሐሳባችን እንገባለን፡፡ ጥጦስና ዳክርስ የተባሉት ሁለት ወንበዴዎች እመቤታችንን በመንገድ አግኝተው እንደዘረፏት፣ በኋላ ጥጦስ አዝኖላት ንብረታቸውን እንደመለሰና ጌታን አቅፎ እንደሸኘ በክፍል ሦስት ቀንጨብ አድርገን አቅረበንላችሁ ነበር፡፡ ይህ ፈያታዊ ዘየማን ጥጦስ ጌታን አቅፎት ሲሸኛቸው ሳለ ሰይፉ ከእጁ ወድቃ ተሰበረችበትና በጣም አዘነ፡፡ ጌታም ‹‹ኦ ጥጦስ አስተጋብእ ስባራተ ሰይፍከ፤ ጥጦስ ሆይ፥ የሰይፍህን ስባሪ ወደ ሰገባው ክተተው›› አለው፡፡ ሰብስቦ ቢያቀርብለት እንደ ነበረ አድርጎ ሰጠው፡፡ ጥጦስም ደስ ብሎት ‹‹ዝንቱ ሕፃን እምደቂቀ ነቢያት፤ ይህ ሕፃን ከነቢያት ልጆች አንዱ ነው›› አለ፤ ዳክርስ ግን ‹‹እውነትም ከነቢያት ወገን ቢሆን አይደል አንተን ቀማኛውን ገነት ትገባለህ ማለቱ!›› ብሎ ዘበተበት፡፡
Hammasini ko'rsatish...
የዳክርስ ክፋቱ እስከ መስቀልም አብሮት ዘልቆ በግራው በተሰቀለ ጊዜ ፀሐይ ስትጨልም፣ ጨረቃ ደም ስትለብስ፣ ከዋክብት ሲረግፉ፣ መቃብራት ሲከፈቱ፣ ሙታን ሲነሡ፣ ተአምራቱን አይቶ እንኳን አላመነም፡፡ ይልቁንም ‹‹አንተስ ክርስቶስ አይደለህምን ራስህንም አድን፤ እኛንም አድን›› እያለ ይሰድበው ነበር፡፡ (ሉቃ.፳፫፥፴፱) የጥጦስ ግን ወሮታው እንዳይቀርበት ጌታን የታቀፈበትን ልብሱን ቢያጥበው ከወዙ ፫፻ ወቄት የሚያወጣ ሽቱ አግኝቷል፡፡ ጌታን ማርያም እንተ ዕፍረት በ፫፻ ወቄት ገዝታ የቀባችውና ይሁዳ ‹‹ይህስ ተሸጦ ለድሆች ይሆን ነበር›› ብሎ ያንገራጎረበት ሽቱ ይህ ነው፡፡ (ዮሐ.፲፪፥፫ እና ማቴ.፳፮፥፮) ምክንያተ ስደት፡- በቤተ ልሔም ሲወለድ አጋንንትን በእሳት ፍላጻ የነደፋቸውን፣ አሳዳጆቹን እንደ ፈርዖንና ሠራዊቱ የውኃ ሽታ ሊያድረጋቸው የሚቻለውን፥ ሁሉ በእጁ የሆነ ልጇን ይዛ ስለምን እመቤታችን በረሃ ለበረሃ ተንከራተተች? ግብጽስ ለምን ለስደቷ ተመረጠች? ‹‹እንዘ ኪሩቤል አፍራሲሁ ወሱራፌል ላእካኒሁ ወክነፈ ነፋስ ሠረገላሁ፤ ኪሩቤል ፈረሶቹ ሱራፌልም መልእክተኞቹ የነፋሳት ክንፎቹም ሰረገላዎቹ›› የተባለለት ጌታስ ስለምን ከናዝሬት እስከ ቁስቋም ተራራ በእግሮቹ ሄደ? (መጽሐፈ ሰዓታት) ሀ. አንዱና ዋናው ስለምን ተሰደደ ቢሉ የቤዛነት ሥራውን የሚፈጽመው ገና በቀራንዮ ነውና ጊዜው ሳይደርስ እንዳይሞት ወደ ግብጽ ነው፡፡ ለ. ትንቢቱና ምሳሌው ይፈጸም ዘንድ ነው፡፡ ትንቢቱ፡- በነቢዩ ኢሳይያስ ‹‹ወይወርድ እግዚእነ ውስተ ምድረ ግብጽ ተጽዒኖ ዲበ ደመና ቀሊል፤ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና እየበረረ ወደ ግብጽ ይመጣል›› ተብሎ የተነገረው ትንቢት ሊፈጸም ነው፡፡ (ኢሳ.፲፱፥፩) ‹‹እምግብጽ ጸዋእክዎ ለወልድየ፤ ልጄን ከግብጽ ጠራሁት›› የሚልም አለና ‹‹ትንቢት ይቀድሞ ለነገር›› እንዲሉ አስቀድሞ ይህ ትንቢት ተነግሮ ስለነበር፣ ትንቢትን የሚያናግር ደግሞ መንፈስ ቅዱስ በመሆኑ በመንፈስ ቅዱስ አናጋሪነት የተነገረ ትንቢት ሳይፈጸም አይቀርም፤ ጌታ ደመና ቀሊል በተባለች ድንግል ማርያም ጀርባ ታዝሎ ወደ ምድረ ግብጽ ወረደ፡፡ ደመና ያላት እመቤታችንን ነው፡፡ ዝናመ ሕይወት ክርስቶስን ያዘለች እውነተኛ ደመና እርሷ ናትና፡፡ ‹‹አንቲ ዘበአማን ደመና እንተ ለነ ማየ ዝናም፤ የዝናም ውኃ የታየብሽ እውነተኛ ደመና አንቺ ነሽ›› እንዳለ ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴ ማርያም፡፡ ምሳሌው፡- ዮሴፍን ወንድሞቹ ‹‹ሊሾምብን ሊገዛን ነው›› ብለው በክፋት ተነሥተውበት ሸጠውት ወደ ግብጽ ወርዶ ነበር፡፡ (ዘፍ.፴፯፥፩-፳፰) ጌታም ‹‹ሊሾምብን ሊነግሥብን ነው›› የሚሉ አጋንንትና ሄሮድስ በክፋት ተነሥተው አሳድደውት ወደ ግብጽ ወርዷልና ነው፡፡ ሐ. ክህደት በግብጽ ጸንቶ ነበርና ወደ ግብጽ ተሰደደ፡፡ ክህደት ወደ ጸናበት መሄድ ልማድ ነውና፡፡ በግብጽ አምልኮ ጣዖት የተስፋፋበት ነበር፡፡ ክህደትም በሰው ልቡና የጸናበት እንደነበረ አጋንንንትም በሰው ልቡና ሠልጥነው እንደነበር እና ቁራሽ ኀብስት፣ ጽዋዕ መጠጥ ከልክለዋት እመቤታችን እንዴት እንዳዘነች ቀድመን አይተናል፡፡ መለኮት ዕጓላ ሶበ ጸምዐ ከመ ደቂቅ-------ዘይሰፍሮ በኅፍኑ ለማየ ባሕር ዕሙቅ በከየት ወትቤ ማርያም ማዕነቅ------------አልቦ እምሰብአ ሀገር ዘየአምራ ለጽድቅ ሶበ ሰአልክዎሙ ማየ ኢወሀቡኒ በሕቅ---------ወአህጎልኩ ለወልድየ አሳዕኖ ዘወርቅ፡፡ ‹‹ጥልቅ የሆነ ባሕርን በእጁ የሚሰፍረውንና የማይመረመር መለኮት የተባለ የባሕርይ አምላክ ልጇ በተጠማ ጊዜ ከዚህች ሀገር ሰዎች ቸርነትን የሚያውቃት የለም፤ ውኃን በእጅጉ ለመንኋቸው፤ አልሰጡኝም፤ የልጄን የወርቅ ጫማውን አስጠፋሁ እያለች ዋኖስ ማርያም አለቀሰች፤›› (ሰቆቃወ ድንግል) በዚህም ወደ ግብጽ በመሰደዳቸው ጣዖታትን አፈራርሷል፤ አጋንንትን ከግብጽ ከሰው ልቡና አሰድዷል፡፡ ‹‹…በዚያች ሀገር ያሉ ጣዖታትም ወድቀው ተሰባበሩ፤ አማልክቱን የሚያመልኩትም ሁሉ ፈሩ፡፡ ወደ ቤታቸውም ገብተው ተደበቁ፤ ….ብዙ ሰዎችም አመኑ፤ የሀገር ሽማግሌዎቹም ጣዖት የሚያመልኩትን ለምን ተሰወራችሁ? አማልክቶቻችሁንስ ለምን ተዋችሁ? አሏቸው፡፡ ይህች ሴት ከልጇ ጋር በገባች ጊዜ ጣዖታቱ ተሰበሩ፤ የአማልክቶቻችን ቤቶችም ወደቁ፤ ሌሊት ሠርተናቸው ሲነጋ ተሰባብረው እናገኛቸዋለን አሉ›› ትላለች እመቤታችን፡፡ (ድርሳነ ማርያም ገጽ ፪፻፰) መ. ገዳማተ ግብጽን ለመባረክ ወደ ግብጽ ተሰደድዋል፡፡ በግብጽ ታላላቅና ደጋግ ገዳማት እነ ገዳመ ሲሐት፣ እነ ገዳመ አስቄጥስ አሉና ገዳማትን ለመባረክ ወደ ግብጽ ተሰድደዋል፡፡ ሠ. መልኩን አይተው የሚያምኑ አሉና ወደ ግብጽ ተሰደደ፡፡ ‹‹ወተበሀላ አዋልደ ሲሐት፤ ንዑ ንርአዮ ለወልደ መንክራት፤ የሲሐት ልጅ ተባለ፤ የወልድን ተአምር ኑ እዮ›› እንዲል፤ (ትርጓሜ ማቴ.፪፥፲፭) ረ. ሃይማኖት ከሁሉ ቢጠፋ ከግብጽ አይጠፋም ሲል ወደ ግብጽ ተሰደዋል፡፡ እስከ ዕለተ ምጽአት ወልድ ዋሕድ ስትል ትኖራለችና፡፡ ሰ. የበደለ አዳም ከገነት ተሰዶ ነበርና ያልበደለ ክርስቶስ ስለ አዳም ካሣ ሊሆን ወደ ግብጽ ተሰደደ፡፡ ሸ. ለሰማዕታት ስደትን ለመባረክ ተሰደደ/ተሰደደች፡፡ እመቤታችን ‹‹ሰማዕት ዘእንበለ ደም ናት፤ ሰማዕት ያለ ደም መፍሰስ›› ሰማዕትነት በእሳቱ መበላት፣ በስለቱ መወጋት ብቻ አይደለም፡፡ ስደቱ፣ ረኃቡ፣ ጥሙ፣ እርዛቱ፣ እንግልቱ ሁሉ ሰማዕትነት ነውና ለሰማዕታት ስደትን ልትባርክላቸው/ሊባርክላቸው ተሰደደች/ተሰደደ፡፡ ‹‹ወሶበ ይሰድዱክሙ እምዛቲ ሀገር ጒዩ ኀበ ካልእታ፤ …በአንዲቱ ከተማም መከራ ቢያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ ..›› እንዳለ ጌታ በወንጌል፡፡ (ማቴ.፲፥፳፫) በዚህም ብዙ ሰማዕታት ክብር አግኝተዋል፤ እመቤታችንና አብረዋት የነበሩት ዮሴፍና ሰሎሜ ሰማዕት ዘእንበለ ደም መሆናቸው ብቻ አይደለም፡፡ ሰማዕት በደም የሆነው ጊጋር መስፍነ ሶርያንም እናገኛለን፡፡ መልአከ እግዚአብሔር ለዮሴፍ ‹‹እናቱንና ሕፃኑን ይዘህ ወደ ግብጽ ሽሽ፤ ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይሻዋልና›› ባለው ጊዜ በስደታቸው መጀመሪያ መሽቶባቸው ያደሩት ከጊጋር መስፍነ ሶርያ እንደ ነበር እንረዳለን፡፡ (ማቴ.፪፥፲፫) ገሥግሰው የደረሱ የሄሮድስ ሠራዊት ግን ጊጋርን በሰይፍ ቀልተው ገድለውታልና፡፡ የሐዲስ ኪዳን የመጀመሪያው ሰማዕት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ በኢትዮጵያ የቅኔ ጉባኤ ቤቶች በትልቁ ከሚተረኩ ታሪኮችና ብዙ የቅኔ ተማሪዎች ቅኔ ከሚቆጥሩበት አንዱ ጊጋር ሰማዕት ነው፡፡ የተወዳጆችሁ የእግዚአብሔር ቤተ ሰቦች! መቼም የስደቷን ታሪክ ተርከን አንዘልቀውምና ከዚህ በላይ ልንጓዝበት አንችልም፡፡ ይሁን እንጂ የእመቤታችንን ስደትና የኢትዮጵያን ግንኙነት ሳይዳስሱ ማለፍ አይቻልም፡፡ ቸር ብንሰነብት፣ የእመቤታችን ከስደት መመለስ ከኢትዮጵያ ጋር አገናኝተን ክፍል አምስትና የመጨረሻውን ክፍል ይዘንላችሁ እንቀርባለን፡፡ ይቆየን!
Hammasini ko'rsatish...
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ሰላም እንደምን ዋላችሁ የግእዝ ቋንቋ ትምህርት ለመማር የተመዘገባችሁ በሙሉ እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃዱ ትምህርቱ የሚጀምረው እሁድ በ 25/02/2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 እስከ 10:00 ስለሆነ በሰዓቱ እንድትገኙ ስንል በቅዱስ ያሬድ ስም እንጠይቃለን። 🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️
Hammasini ko'rsatish...
በዚህ ይመዝገቡ
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ በዓመት ሁለት ጊዜ እንዲሆን በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 ላይ በተደነገገው መሠረት ምልዓተ ጉባኤው የመክፈቻውን ሥርዓተ ጸሎት ከፈጸመበት ከጥቅምት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባውን ሲያካሂድ ሰንብቷል፡፡ በመሆኑም ምልዓተ ጉባኤው ስለ ቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት፣ እየተከሰቱ ስላሉት ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎች እንዲሁም ስለ ሀገር ሰላምና አንድነት በስፋት በመወያየት ለቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡ በዚሁ መሠረት፡- 1. የ2016 ዓ.ም. የመንበረ ፓትርያርክ ዓለም አቀፍ አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ ያሳለፈውን የጋራ የአቋም መግለጫ በመመርመርና አስፈላጊውን ማሻሻያዎች በማድረግ የበጀት ዓመቱ የቤተ ክርስቲያናችን የሥራ መመሪያ እንዲሆን ጉባኤው አጽድቆታል፡፡ 2. ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን መዋቅራዊ አደረጃጀቱን የበለጠ ተደራሽ በማድረግ ሐዋርያዊ ተልዕኮዋን መወጣት ትችል ዘንድ በአዲስ እንዲደራጁ ተጠንተው የቀረቡትን የአህጉረ ስብከት ይደራጅልን ጥያቄዎችን በመመርመር፡- ሀ. የሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት፣ ለ. የሰሜን ጎጃም ዞን ሀገረ ስብከት ሐ. የጎፋና ባስኬቶ ዞን ሀገረ ስብከት መ. የምሥራቅ ጉራጌ ዞን ሀገረ ስብከት እራሳቸውን ችለው ሀገረ ስብከት ሆነው ተደራጅተው እንዲቀጥሉ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
Hammasini ko'rsatish...
15. ወጣቱ ትውልድ በእምነቱ ጸንቶና በቤተ ክርስቲያኒቱ አስተምህሮ በእውቀትና በሥነምግባር ይታነጽ ዘንድ በሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ተዘጋጅቶ የቀረበው ሥርዓተ ትምህርት በሁሉም የቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅር እና አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ተግባራዊ እንዲሆን ጉባኤው ወስኗል፡፡ 16. የ2016 ዓ.ም. ዓመታዊ በጀትን አስመልክቶ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በኩል ተዘጋጅቶ የቀረበውን የበጀት ድልድል ጉባኤው መርምሮ በማጽደቅ ሥራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡ 17. የቤተ ክርስቲያናችን የመልካም አስተዳደር ችግሮች የሚፈቱት እና የልማት ተቋማት የሚጠናከሩት ዘመኑን የዋጀ መዋቅራዊ አደረጃጀት በመፍጠር እና በእቅድ ተደግፎ በእውቀት ላይ የተመሠረተ የሀብትና የንብረት አስተዳደር ማስፈን ሲችል መሆኑን ጉባኤው በጽኑ ያምናል፡፡ በመሆኑም በባለፈው ጉባኤ የጸደቀው የ10 ዓመት የመሪ እቅድ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አስፈላጊው ድጋፍና ክትትል እየተደረገለት የመሪ ዕቅዱ አፈጻጸም እንዲቀጥል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ጥቅምት ፲፱ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም. ኢትዮጵያ አዲስ አበባ
Hammasini ko'rsatish...
3. ቤተ ክርስቲያናችን የመንፈሳዊ ኮሌጆቿን ቁጥር ከፍ በማድረግ የአገልጋይ መምህራንን ቁጥር ለማሳደግ ባላት እቅድ መሠረት ተጠንተው ከቀረቡት መካከል በ2016 ዓ.ም. የበጀት ዓመት በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ደብረ ብርሃን ከተማ ላይ፣ በደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ደብረ ታቦር ከተማ ላይ ሁለት መንፈሳዊ ኮሌጆች እንዲቋቋሙ፣ በማዕከላዊ ጐንደር ሀገረ ስብከት ርእሰ ከተማ ውስጥ ለሚገኙት የምስክር ጉባኤ ቤቶች በኮሌጅ ደረጃ በጀት እንዲመደብላቸው እና በከንባታ ሐድያ ስልጤ ሀገረ ስብከት ሆሣዕና ከተማ ላይ አንድ የካህናት ማሠልጠኛ እንዲከፈት ጉባኤው ወስኗል፡፡ 4. ቤተ ክርስቲያናችን ከውስጥና ከውጭ እየደረሱባት ያሉት ከፍተኛ የሆኑ ፈተናዎችን ተቋቁማ ሕልውናዋን አስከብራ መቀጠል ትችል ዘንድ ፡- ሀ. ውስጣዊ ችግሮቻችን ቀኖና ቤተ ክርስቲያን በጠበቀ በውይይት እንዲፈቱ፣ ለ. ውጫዊ ችግሮችንና የመብት ጥሰቶችን በተመለከተ በችግሮቹ ዙሪያ ከሚመለከታቸው መንግስታዊ ተቋማት ጋር በመነጋገር ችግሮቹ እንዲፈቱ እና የቤተ ክርስቲያናችን መብትና ሕልውና ተጠብቆ እንዲቀጥል እንዲደረግ፣ ሐ. ለቤተ ክርስቲያናችን ሕልውና አደጋ የሆኑና ሊሆኑ የሚችሉ ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎችን አስመልክቶ በአግባቡ ተጠንተውናበማስረጃ ተተንትነው ከመፍትሔ ሐሳብ ጋር እንዲቀርብ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡ 5. ትላንት በሰሜኑ ኢትዮጵያ የሀገራችን ክፍል በተካሄደው ጦርነት በጠፋው የሰው ሕይወትና በወደመው ንብረት ከደረሰብን ሐዘን እኛ ኢትዮጵያውያን ገና ሳንጽናና ዛሬም በሀገራችን ኢትዮጵያ በበርካታ አካባቢዎች የተከሰቱት ጦርነቶች፣ ግጭቶችና አለመግባባቶች እያስከተሉት ያለው የንጹሐን የሰው ሕይወት መጥፍትና የንብረት ውድመት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤን በእጅጉ አሳዝኖታል፡፡ በመሆኑም ችግሩ በውይይትና በስምምነት እንዲፈታ የፌዴራልን የክልል መንግሥታት፣ እንዲሁም በግጭቱ ተሳትፎና ድርሻ ያላችሁ በሁሉም አካባቢ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን በሙሉ የበኩላችሁን ሚና በመወጣት እናት አገራችን ኢትዮጵያ ሰላሟና አንድነቷ ተጠብቆ ይቀጥል ዘንድ ቅዱስ ሲኖዶስ ከአደራ ጭምር በድጋሚ ጥሪውን ያቀርባል፡፡ 6. በሀገራችንና በቤተ ክርስቲያናችን ላይ እየተከሠተ ያለው ችግርና ፈተና የሚወገደው ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በአንድነትና በሕብረት ለችግሮቹ መፈታት ድርሻ እንዳለን አውቀን እንደየእምነታችን አስተምህሮ በጸሎትና በምሕላ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር በንስሓ መመለስ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ በጽኑ ያምናል፡፡ በመሆኑም ስለ ሀገራችን ሰላምና ስለ ቤተ ክርስቲያናችን አንድነት በመላው ዓለም በሚገኙት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት በሙሉ ከህዳር 15 ቀን 2016 እስከ ታህሣሥ 27 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ ጸሎትና ምሕላ እንዲፈጸምና መላው ሕዝበ ክርስቲያንም በአንድነትን በሕብረት ከላይ በተጠቀሱት ዕለታት በቤተ ክርስቲያን በመገኘት የበረከቱና የሥርዓተ ጸሎቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኖ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ 7. የቤተ ክርስቲያናችንን ታሪክና ለሀገረ መንግስት ምሥረታና እድገት ያበረከተችውን አስተዋጽኦ በማዕከል ደረጃ በማስረጃ አስደግፎ በመጻፍና በማደራጀት ትውልዱ እንዲረዳው በማድረግ ለቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን የሕልውና አደጋ የሆነውን የሐሰት ትርክት መከላከል ይቻል ዘንድ የዝግጅት ሥራው በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በኩል በሊቃውንት ጉባኤ የበላይ ተቆጣጣሪነት ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንንና የታሪክ ተመራማሪዎችን በማሳተፍ ተግባራዊ እንዲሆን ጉባኤው ወስኗል፡፡ 8. ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በሀገራዊ የምክክር ሂደቱ ላይ ስለሚኖራት ተሳትፎና ሚና በተመለከተ ጉባኤው በስፋት የተወያየ ሲሆን ሀገራዊ ምክክሩ ሀገራዊ ችግራችንን እንደሚፈታና በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የሚነገሩትን የሐሰት ትርክቶች ሁሉ የሚታረሙበት እንደሚሆን ጉባኤው በጽኑ ያምናል፡፡ በመሆኑም በምክክር ሂደቱ ላይ ስለሚኖረን ተሳትፎና ሚና በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በኩል እየተጠና አስፈላጊው ሁሉ እንዲፈጸም ሆኖ የምክክር ኮሚሽኑም ይህን የቤተ ክርስቲያናችን እቅድ በመርሐግብሩ በማካተት ቤተ ክርስቲያናችን የድርሻዋን እንድትወጣ እድሉን እንዲያመቻችልን ጉባኤው ጥሪውን ያቀርባል፡፡ 9. የመረጃ ቋት መዋቅራዊ አደረጃጀትን በሁሉም ክልል አህጉረ ስብከት ደረጃ በማቋቋም እና እለት እለት በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የሚከሰቱትን ችግሮችና የመብት ጥሰቶች በመረጃና ማስረጃ አስደግፎ ለዋናው ማዕከል የመረጃ ቋት በፍጥነት ተደራሽ በማድረግ በአንዱ ቦታ ችግር ሲደርስ በመላ ሀገሪቱ እና በውጭው ክፍለ ዓለማት ባሉት አህጉረ ስብከት በአንድነት ድምፅ መሆን ይቻል ዘንድ ተጠሪነታቸው ለዋናው ማዕከል የሆኑ የመረጃ ቋት ማዕከላት በሁሉም አህጉረ ስብከት ተቋቁመው ወደሥራ እንዲገቡ ጉባኤው ወስኗል፡፡ 10. የቤተ ክርስቲያናችን ሀብትና ንብረት የሆኑት ቅዱሳት መጻሕፍትን፣ የሚዳሰሱና እና የማይዳሰሱ ቅርሶችንና በአጠቃላይ ንዋየ ቅድሳቶቻችን ግለሰቦች እና ተቋማት በሕገወጥ መንገድ አትመውና አሳትመው በማሠራጨትና ትክክለኛ ቅጅውን አዛብቶ በማተም ቤተ ክርስቲያናችን ለሐሰተኛ ትርክት እንድትዳረግ በማድረግ ከፍተኛ የሆነ በደል እየተፈጸመባት መሆኑን ጉባኤው በጽኑ ያምናል፡፡ በመሆኑም በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤቱ በኩል የተጀመረው የአዕምሯዊ ንብረት ምዝገባ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እና የቤተ ክርስቲያኒቱ መብትና ጥቅም እንዲከበር ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡ 11. በውጭው ክፍለ ዓለማት በሚገኙት አህጉረ ስብከት ሥር የተቋቋሙት አብያተ ክርስቲያናት የሚተዳደሩበት እራሱን የቻለ ሕግና ደንብ ባለመኖሩ በመዋቅራዊ አስተዳደራችን ላይ ከፍተኛ ክፍተት ሲፈጥር የቆየ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ቅዱስ ሲኖዶስ ለውጭው ክፍለ ዓለማት አህጉረ ስብከት እና አብያተ ክርስቲያናት እራሱን የቻለ መተዳደሪያ ደንብ ተዘጋጅቶ የፀደቀ በመሆኑ በውጭው ክፍለ ዓለማት በሚገኙት ሁሉም አህጉረ ስብከትና አብያተ ክርስቲያናት በጸደቀው መተዳደሪያ ደንብ ብቻ ሥራቸውንና አገልግሎታቸውን እንዲያከናውኑ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡ 12. የቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ ኮሌጆች ወጥ የሆነ የጋራ መተዳደሪያ ደንብ እንዲኖራቸው በማሰብ ጉባኤው አስቀድሞ ተዘጋጅ እንዲቀርብ ባዘዘው መሠረት ተዘጋጅቶ የቀረበውን ረቂቅ መተዳደሪያ ደንብ መርምሮ በማጽደቅ በሁሉም በተቋቋሙትም ሆነ ወደፊት በሚቋቋሙት ኮሌጆች ሥራ ላይ እንዲውል ጉባኤው ወስኗል፡፡ 13. ገዳማትና ገዳማዊ ሕይወት፣ የአብነት መምህራን እና ትምህርት ቤቶች እንዲሁም በአጠቃላይ ክብረ ክህነት እና ትምህርተ ኖሎት ተጠናክሮ እንዲቀጥል በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በኩል እየተጠና አስፈላጊው ሁሉ ድጋፍና ክትትል እንዲደረግ ጉባኤው ወስኗል፡፡ 14. የቤተ ክርስቲያናችን ሕጋዊ፣ ተቋማዊ፣ ሃይማኖታዊና ማህበራዊ መብቶች መከበርና የእምነት ነጻነታችንን እና የምእመናንን ደኅንነት በሕግ አግባብ ማስከበር ይቻል ዘንድ ልክ እንደ ዋናው መሥሪያ ቤት በሁሉም ክልሎች ውስጥ ባሉት አህጉረ ስብከት የሕግ ባለሙያዎች ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ሥራ እንዲገባ ጉባኤው ወስኗል፡፡
Hammasini ko'rsatish...
የ2016 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ተጠናቀቀ። ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ለኢኦተቤ ቴቪ በሰጡት ዕለታዊ መግለጫ ጥቅምት 17 ቀን 2016 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ አስተዳደራዊ ጉዳይን የያዘ የመሪ እቅድ ተጨማሪ ግብዓት ተጨምሮበት ለግንቦት ርክበ ካህናት እንዲቀርብ መወሰኑን ገለጹ፡፡ በጸደቁ አጀንዳዎች ላይ ላለፈው አንድ ሳምንት ሲወያይ የቆየው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ መንፈስ ቅዱስን አጋዥ በማድረግ መግባባት በሰፈነበት ሁኔታ ጉባኤውን ማጠናቀቁን የገለጹት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) በማጠናቀቂያው በሕግ በመሪ እቅድ ትግበራ እና በልዩ ልዩ ጉዳዮች ጥናት ላቀረቡ እና ማብራሪያ ለሰጡ ባለሙያዎች በብፁዕ ወቅዱስ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ምስጋና ማቅረባቸውን ገልጸዋል። በአጠቃላይ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎችንአስመልክቶ ቅዱስነታቸው ሰኞ ጥቅምት 19 ቀን 2016 ዓ.ም መግለጫ እንደሚሰጡ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ለኢኦተቤ ቴቪ በሰጡት ዕለታዊ መግለጫ አስታውቀዋል፡፡ ምንጭ የኢኦተቤክ ቴቪ
Hammasini ko'rsatish...
የ7ኛ አመት የ34ኛ ሳምንት @Memhir_sirak
Hammasini ko'rsatish...