cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

“ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም” ቅዱስ ያሬድ ይኽ በደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተክርስቲያን የውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት የቴሌግራም አውታር ነው፡፡ የውሉደ ያሬድ ሰንበት ት/ቤት መንፈሳዊ ጽሑፎችን፣ ወቅታዊ ኹኔታዎችን የሚገልጹ መረጃዎችን እንዲኹም ማስታወቂያዎችን በዚኽ ገጽ ለተከታታዮቹ ያስተላልፋል፡፡ መልእክት ወይም አስተያየትና ጥቆማ ካሎት ⬇️⬇️

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
6 071
Obunachilar
+824 soatlar
+97 kunlar
+15930 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Photo unavailableShow in Telegram
🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿 እንኳን #ለጻድቁ_ለኢትዮጵያዊው_ንጉሥ የመን አገር ድረስ ዘምቶ በናግራን ያሉ ክርስቲያኖችን ከአይሁዳዊው ንጉሥ ከፊንሐስ ነጻ ላወጣቸው፤ የነገሠበት ዘውድ በጌታ መቃብር በጎልጎታ አስቀምጦ ንግሥናውን ትቶ ለመነነ #ለዐፄ_ለቅዱስ_ለካሌብ ለዕረፍት በዓልና #ለደብረ_ሊባኖስ ዐሥራ ስድስተኛ #አበ_ምኔት (እጨጌ) #ለአባ_ዘትረ_ወንጌል ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። 🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿
Hammasini ko'rsatish...
🙏 1
01:16
Video unavailableShow in Telegram
✨️🎭🍁🌿✨️🎭🍁🌿✨️🎭🍁🌿✨️🎭🍁🌿 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ✨ዘመቻ ሰውን ፍለጋ በዘርዓ ያዕቆብ ዕልፍኝ✨ የማይቀርበት ልዩ መንፈሳዊ የሥነ ጥበብ ምሽት! 🗓ግንቦት 20  በዕለተ ማክሰኞ 🕛 ከምሽት 12፡00 ጀምሮ ኦርቶዶክሳዊ እግሮች ኹሉ ወደ ውሉደ ያሬድ አዳራሽ ያመራሉ! ✨ ግጥም ✨ መነባንብ ✨  ወግ በዕለቱ ተዘጋጅተው ይጠብቅዎታል የምንጽናናበት - የምንማርበት - ልባችን በበጎ ቦታ የሚያርፍበት ነውና ቤተሰብ እና ጓደኞቻችንን በመጋበዝ እንድንገኝ ተጠርተናል! አዘጋጅ: የውሉደ ያሬድ ሥነጥበባት ክፍል   https://vm.tiktok.com/ZMMoL3ALU/ ✨️🎭🍁🌿✨️🎭🍁🌿✨️🎭🍁🌿✨️🎭🍁🌿
Hammasini ko'rsatish...
🥰 11👍 1🙏 1
🍁🍁🍁🌿🌿🌿🍁🍁🍁🌿🌿🌿🍁🍁🍁🌿🌿🌿 "የሰው ልጆች ሁሉ አዋቂ ናቸው የሚባለው ስህተት ነው። አዋቂ ማለት መጽሐፍትን ጠንቅቆ ያወቀ ሳይሆን ከኃጢአት በመቆጠብ ነፍሱን የማይጎዳ፣ አምላክን በማመስገን በማያወላውል በቅድስና ሥራ መልካም በመሥራት ነፍሱን የሚመግብ ያ ሰው እሱ ብቻ አዋቂ ተብሎ ይጠራል።" 🍁🍁🌿ታላቁ ቅዱስ እንጦንስ “ተአምራትን ማድረግ ትፈልጋላችሁን? እንኪያስ በዘፈን የደነቆረን ጀሮ መዝሙር እንዲሰማ አድርጉት፡፡ ሴትን በመመኘት የታወረው ዐይን ፈጣሪውን እንዲያይ አድርጉት፡፡ በስርቆት የሰለለ እጅ በምጽዋት እንዲዘረጋ አድርጉት፡፡ ወደ ኃጢአት ቤት በመሄድ ሽባ የሆነውን እግር ወደ እግዚአብሔር ቤት እንዲሮጥ አድርጉት፡፡ ሐሜትን በማውራት ዲዳ የሆነውን ከንፈር መልካም ንግግርን እንዲናገር አድርጉት፡፡ ከተአምራት ሁሉ የበለጠ ተአምር ይሄ ነው፡፡" 🍁🍁🌿 ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "ጌታ ሆይ ዕውሩን ሂድ ብለህ ወደላክህበት ወደ ሰሊሆም መጠመቂያ አሁን ልንሔድ አንችልም።  ነገር ግን ሕይወትንና ብርሃንን የተሞላው የከበረ ደምህ ያለበት ጽዋ በእኛ ዘንድ አለ። ከእርሱ በተቀበልን ቁጥር እንነጻለን"  🍁🍁🌿 ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ 🍁🍁🍁🌿🌿🌿🍁🍁🍁🌿🌿🌿🍁🍁🍁🌿🌿🌿
Hammasini ko'rsatish...
👍 3
Photo unavailableShow in Telegram
🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁 እንኳን #ለኃይለኛ_ተጋዳይጌታችን አምስት ጊዜ ከሞት ላስነሣው ከዐሥራ ሁለት ዓመቱ ጀምሮ ለዐሥራ ሁለት ዓመት ሲጋደል ለነበረ #ለቅዱስ_ኤስድሮስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓልና #ከአባ_መቃርስ ገዳም ለሆነ ከምግቡም የማዕጠንት አመድ ጨምሮ እየበላ ብዙ ዘመናት ለኖረ ለቅዱስ አባት #ለቀሲስ_ይስሐቅ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡት፦ ከቅዱስ ኤስድሮስ እናት ቅድስት ሶፍያ፣ ከአባቱ ቅዱስ በድላዖን፣ ከእህቱ ቅድስት አፎምያ ከመታሰቢያቸውና ከቅዱስ ኤስድሮስ ጋራ ስምንት መቶ አምስት ሺህ ሰባት ሰዎች በሰማዕትነት ከዐረፉ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። 🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁
Hammasini ko'rsatish...
👍 3🙏 2
Photo unavailableShow in Telegram
✨️🎭🍁🌿✨️🎭🍁🌿✨️🎭🍁🌿✨️🎭🍁🌿 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ✨ዘመቻ ሰውን ፍለጋ በዘርዓ ያዕቆብ ዕልፍኝ✨ የማይቀርበት ልዩ መንፈሳዊ የሥነ ጥበብ ምሽት! 🗓ግንቦት 20 በዕለተ ማክሰኞ 🕛 ከምሽት 12፡00 ጀምሮ ኦርቶዶክሳዊ እግሮች ኹሉ ወደ ውሉደ ያሬድ አዳራሽ ያመራሉ! ✨ ግጥም ✨ መነባንብ ✨  ወግ በዕለቱ ተዘጋጅተው ይጠብቅዎታል የምንጽናናበት - የምንማርበት - ልባችን በበጎ ቦታ የሚያርፍበት ነውና ቤተሰብ እና ጓደኞቻችንን በመጋበዝ እንድንገኝ ተጠርተናል! አዘጋጅ: የውሉደ ያሬድ ሥነጥበባት ክፍል ✨️🎭🍁🌿✨️🎭🍁🌿✨️🎭🍁🌿✨️🎭🍁🌿
Hammasini ko'rsatish...
👍 13
✨✨✨🌿🌿🌿✨✨✨🌿🌿🌿✨✨✨🌿🌿🌿 ስለ ጥንተአብሶ
(Original Sin)
አጭር ነገር ✨🌿 ጥንተ አብሶ የተለያዩ ስያሜዎች አሉት አበሳ ዘትካት (Ancetral Sin) የቀደመ በደል፣ ኃጢአተ አዳም፣ የውርስ ኃጢአት (ኃጢአት ይወረሳል ብለው የሚያምኑ ደግሞ የውርስ ኃጢአት ይሉታል፤ ምንም እንኳን ሐሳቡ በኦርቶዶክሳዊው ትውፊት ተቀባይነት ባይኖረውም)፣ በብዙ ኦርቶዶክሳውያን ቅዱሳን አበው ደግሞ ንዴተ ህላዌ ወይም የባሕርይ መጎስቆል (Fallen Nature) ይባላል። ኃጢአት ይወረሳል የሚለው ተቀባይነት የሌለው ሐሳብ ነው። ምክንያቱም ኃጢአት የሚወረስ ከኾነ ባሕርያዊ ነው ማለት ነው! እንዲያ ከኾነ ማንም ሰው ምንም ቢኾን ኃጢአትን ካለመሥራት ውጭ አይኾንም ማለት ነው! ይህ ፍጹም ስሕተት ከመኾንም በተጨማሪ እንዲህ አድርጎ የፈጠረን እግዚአብሔር ነው ሊያሰኝና አልፎ ተርፎም ኃጢአትን በራሱ ትክክለኛ ነገር አድርጎ ወደ ማሰብም ሊወስድ የሚችል ስሑት አረዳድ ነው። በዘር ነው የሚተላለፈው ብሎም ማሰብ ኃጢአትን አካላዊት ነገር አድርጎ የማሰብ ችግርንም የሚፈጥር ነው። በአጭሩ ኃጢአት በዘር አይተላለፍም። በአዳምና በሔዋን ምክንያት እኛን ያገኙን የኃጢአቱ ውጤቶች (Consequences of Sin) ናቸው። እኒህም የባሕርይ መጎስቆል፣ የጸጋ መገፈፍ፣ መርገመ ሥጋ ወነፍስ ናቸው። መዋቲነት የሚስማማን፣ ልጅነትን ያጣን፣ ከገነት የተባረርን ሲኦል ብቻ የምንገባ ኾነን ነበር። ክርስቶስ አምላካችን ስለ እኛ ሰው ኾኖ በፈጸመው የማዳን ሥራ ይህን አስወገደልን። አምላካችን ክርስቶስ ሰው ኾኖ ተገልጦ የድኅነትን ሥራ በፈጸመልን ጊዜ በአካለ ሥጋ ያልነበሩትን በሲኦል ያሉ ነፍሳትን አስወጣቸው (ኹሉም ወጡ ወይስ ያልወጣ አለ የሚለውን የቅዱሳን ሊቃውንትን ሐሳብ እንተወውና)። ከሲኦል ወጥተው ወደ ገነት የገቡት አዳም ከመበደሉ በፊት ወዳለው ማንነት ቢመለሱም ገና በትንሣኤ ዘጉባኤ ድኅነታቸውን በፍጹም ለማግኘት በገነት የሚጠባበቁ ናቸው። አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው ድኅነተ ዓለምን ሲፈጽም በአካለ ሥጋ ያሉት ግን ከመርገመ አዳም ነጻ ቢወጡም የሐዲስ ኪዳኑን ጸጋ ገንዘብ የሚያደርጉት በኢየሱስ ክርስቶስ አምነው ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንን ሲፈጽሙ ነው። ይህን እስካላደረጉ ድረስ በክርስቶስ የተነቀለውን መርገም በፈቃዳቸው መልሰው በሰውነታቸው ይተክሏታል። አምኖ ምሥጢራትን መፈጸም ለድኅነት የግድ ነው። ✨🌿 ሕፃናትን በተመለከተ ምንም እንኳን መርገመ አዳም ባይኖርባቸውም የሐዲስ ኪዳኗን ጸጋ (ከቅድስት ሥላሴ ልጅነትን ከማግኘት ጀምሮ ክርስቶስን ለብሶ ሞቱን በሚመስል ሞት እና ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ በጥምቀት ከክርስቶስ ጋር እስካልተባበሩ ድረስ ከጸጋው ውጭ ናቸው) ማግኘት አይችሉም። ስለዚህ የግድ መጠመቅ ይኖርባቸዋል። ነገር ግን ሳይጠመቁ ቢሞቱ በአንድ በኩል ወቀሳ የሌለባቸው ሲኾን በሌላ በኩል ስላልተጠመቁ አክሊልን አያገኙም። ወደ ገነት የሚገቡ መኾናቸው በቅዱሳን ሊቃውንት ተነግሯል። እንደ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ፣ ጎርጎርዮስ ዘኑስ፣ ቅዱስ ኤፍሬም ዘሶርያ ያሉት ያልተጠመቁ ሕፃናትን መጨረሻ በዚህ መንገድ ያስረዳሉ። መርገመ አዳም ያለ ቢኾን ሕፃናትም ቢኾኑ ግድ መግቢያቸው ሲኦል ነበር የሚኾነው፤ ነገር ግን ይህ በታላላቅ ቅዱሳን ዘንድ ተቀባይነት የለውም። ይህ ማለት ግን ሕፃናት እንኳን ካልተጠመቁ አይድኑም የሚሉ የሉም ማለት አይደለም። ይህን ሐሳብ የሚያነሱም ብዙ ሊቃውንት አሉና። ለአብነት ያህል አባ መቃሪያዮስ፣ አምብሮስ ዘሚላን፣ ኦሪገን፣ አውግስጢኖስ ...! በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እንደነ ሊቀ መዘምራን ሞገስ ዕንቍ ጊዮርጊስ ያሉት ደግሞ ያልተጠመቁ ሕፃናት በኹለት መደብ አድርገው የክርስቲያን ልጆች ከኾኑ የእናት የአባታቸውን ርስት መንግሥተ ሰማያትን ይወርሳሉ፣ የአሕዛብ ልጆች ከኾኑ የእናት የአባታቸውን ርስት ሲኦልን ይወርሳሉ የሚሉ መኾኑም ይታወቃል። በአንዳንድ ሊቃውንት ዘንድ ያልተጠመቁ ሕፃናት መጨረሻ የሚታወቀው በእግዚአብሔር ነው፤ ወስኖ እዚህ ነው የሚገቡት ማለት አይቻልም የሚባለውም ጉዳዩ ለፍትሐ እግዚአብሔር የሚተው ስለ ኾነ ነው። እንዲህ ያሉ ሐሳቦች በራሱ መርገመ አዳም የመወገዱ ማሳያ ናቸው። መርገመ አዳም ቢኖር ኖሮ መግቢያቸው ግድ ሲኦል ብቻ ስለሚኾን ውዝግብ አይኖርም ነበርና! እንግዲህ ይህን በዚሁ እናቆየው! ✨🌿 ሌላው መሠረታዊው ጉዳይ አኹን መርገም ተወግዷል የለም ማለት የሐዲስ ኪዳኑ የድኅነት ጸጋ ሙሉ በሙሉ ተሰጥቶናል ወይም ደግሞ አምነው ሳይጠመቁ አዳም በገነት የእግዚአብሔር ልጅ ተብሎ፣ የጸጋ የብርሃን ልብስ እንደ ለበሰው ኾነናል ማለት አይደለም። ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ወደ መጠመቂያው ገንዳ ሕፃናት ዕርቃናቸውን የሚገቡት አዳም በገነት ለብሷት የነበረውን ልብስ ክርስቶስ በመጠመቂያው ገንዳ ውስጥ ስላስቀመጠ ነው ይለናል። አምነው ምሥጢራትን ሳይፈጽሙ አዳም በገነት ለብሷት የነበረውን የጸጋ ልብስ መልበስም ኾነ፣ የቅድስት ሥላሴን ልጅነት ማግኘት፣ ከክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ጋር መተባበርም ኾነ አካለ ክርስቶስ መኾን ተሰጥቷቸዋል ማለት አይደለም። ይህማ እንዳልኾነ ግልጽ ስለ ኾነ ነው በ40 እና በ80 ቀን እንዲጠመቁ ለሕፃናት ሥርዓት የተሠራው። ይህን የአበውን ሥርዓት ልብ ማለት ከስሐለት አረዳድ ይጠብቀናል። በሌላ በኩል ለሕፃናትም ቢኾን ከአዳማዊ ማንነት ወደ ክርስቶሳዊ ማንነት (ለባሴ ክርስቶስ መኾን) እንበለ ጥምቀት የማይቻል ጉዳይ ነው። ይህ ሕፃናትንም ቢኾን የሚመለከት ስለ ኾነ ነው ግድ መጠመቅ የሚኖርባቸው። ሌላው ቀርቶ 40 እና 80 ቀን ሳይደርስ ለሞት የሚያሰጋ ችግር ከገማቸውም ቶሎ እንዲጠመቁ ትውፊታችን የሚያዘው በዚህ መሠረታዊ ምክንያት ነው። ከፍ ያሉ አዋቂዎች ግን አምነው እስካልተጠመቁ ድረስ በፈቃዳቸው ጥመት ምክንያት ከመርገም ውስጥ ናቸው። መርገሙም የአዳም መርገም ሳይኾን ባለማመናቸው ምክንያት የበቀለባቸው መርገም ነው። በማንኛውም ጊዜ ቢኾን ኃጢአት ባሕርይን ያጎሰቁላል ጸጋን ያስገፍፋል መርገምንም ያመጣል። ስለዚህ አኹን በግል ባለማመን ምክንያት የሚፈጸም ኃጢአት ከአዳም መርገም የበለጠ ጉዳት የሚያመጣ መኾኑን ልብ ማለት ያስፈልጋል። 📝 ዲ/ን ዮሐንስ ጌታቸው 🌿🌿🌿✨✨✨🌿🌿🌿🌿✨✨✨🌿🌿🌿
Hammasini ko'rsatish...
👍 3
🌴🌷🌴🌷🌴🌷🌴🌷🌴🌷🌴🌷🌴 ''ስለ ሌሎች ሰዎች ያለማቋረጥ ፀልዩ፡፡ ወደ እግዚአብሔር ይደርሱ ዘንድ የንሰሐ እድል አላቸውና፡፡ ለእነርሱ ነቀፋ እናንተ መልሳችኹ ፀሎት ይሁን!''     ✨ቅዱስ አግናጥዩስ ምጥው ለአንበሳ✨ ''የሞትን ፍሬ ከሚያመርቱ ከነዚህ ክፋ የሰይጣን ልጆች መናፍቃን ተጠበቁ፡፡ ማንም ከእርሱ የቀመሰ ወዲያው ይሞታልና፡፡ እነዚህ አባት ያልተከበላቸው ናቸው::''    ✨ቅዱስ አግናጥዩስ ምጥው ለአንበሳ✨ ''የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ትምህርት የሚያስብ ክርስቲያን በሚሠራው ሥራ ሁሉ የእግዚአብሔር ጸጋ ሁሉ እንዲገለጥ ያደርጋል፡፡'' ✨ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ✨ ''እስካልበደልን ኃጢአትም እስካልሠራን ድረስ የምንኖረው በእግዚአብሔር ነው፡፡'' ✨ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ✨ ''የእግዚአብሔር ቃላት የነፍስን ሙቀት ያድሳሉ፡፡ እንድታድግ ከፈለግህ የእግዚአብሔርን ቃላት እንደ ህጻን ልጅ መጥባት አለብህ::'' ✨ቅዱስ አትናቴዎስ✨ ''የሰው ልጅ በወደቀ ግዜ እግዚአብሔርን መምሰል ተነጥቆ ነበር፡፡ ኢየሱስ ክርስቶሰ የመጣው ያጣነውን ክብር ሊመልሰልን ነው፡፡'' ✨ቅዱስ አትናቴዎስ✨ 🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴
Hammasini ko'rsatish...
👍 5
Photo unavailableShow in Telegram
🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁 እንኳን #ለጥንት #ጰራቅሊጦስ በዓልና #ለአባ አብርሃም ጓደኛ ለዐሥራ አራት ዓመታት የላማ የጣመ ሳይመገብና ሳይታኛ ለተጋደለ ለከበረ #ለአባ ገዐርጊ ለዕረፍት በዓልና በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ ከሰማዕት ሲኖዳ ከመታሰቢያው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። 🌿 🍁🌿🍁🌿 🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿
Hammasini ko'rsatish...
🙏 3
Photo unavailableShow in Telegram
"ኹለቱም አንድ አካል ይኾናሉ፤ ይኽ ነገር ጥልቅ፤ ረቂቅ ምሥጢር ነው፤ እኔም ለክርስቶስና ለቤተክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ እናገረዋለኹ፡፡"          ሃይማኖተ አበው  ዘስምዓት በዛሬው ዕለት ግንቦት ፲፯ ፳፻፲፮ ዓ.ም. ጋብቻችኹን በቅድስት ቤተክርስቲያን ሥርዓት የፈጸምማችኹት ወንድማችን ዲ/ን እስጢፋኖስ አድማሱ  እና እህታችን ትዕግስት ጫኔ የፈጸማችኹትን ጋብቻ፤ የአብርሃምንና የሳራን ጋብቻ የባረከ አምላክ፤ የትዳር ሕይወታችኹን ይባርክላችኹ፥ ያጣምራችኹ፥ ያዋሕዳችኹ 🙏 ካህኑ ቅዱስ ያሬድ በሕይወታችኹ ሞገስ ይኾናችኹ ዘንድ በፍቅርና በጤና ይባርካችኹ ዘንድ መልካም ምኞታችን ነው!
Hammasini ko'rsatish...
🥰 34🙏 10👍 9
“…..ቅንነቱማ ካለ ሁሉ ያለ በእጁ አይደለምን ከዚያው አውጥቶ ይስጥ ይህም ስርቆት አይሆንበት ቢሉ ይንገራት አይሆንም ብትለው ግን ይለያዩ ጥንቱን መጋባታቸው ሰጥተው መጽውተው ሊጸድቁ ነውና……”
በማለት የትዳር ምሰሶ መካከል አንዱ መመጽወት መሆኑን አስረድተዋል። 🌿️️️️️️✨✨ እንዲህ እያልን የምጽዋትን ጉልበትና ኃይል አብዝተን መግለጽ ይቻለናል። 🌿ምጽዋትና ውዳሴ ከንቱ 🌿ዲያቆን ሞገስ አብርሃም 🌿️️️️️️🌿️️️️️️🌿️️️️️️✨✨✨🌿️️️️️️🌿️️️️️️🌿️️️️️️✨✨✨🌿️️️️️️🌿️️️️️️🌿️️️️️️✨✨✨
Hammasini ko'rsatish...