uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling 👈

ᴛʜᴏᴜɢʜs.ᴘʟᴄ🔥

ᴛʜᴏᴜɢʜs.ᴘʟᴄ🔥

Kanalga Telegram’da o‘tish

...Quotes from different societies. Also👉https://t.me/LilOriIII

Ko'proq ko'rsatish
856
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-17 kun
-1530 kun
Postlar arxiv
I see ur shadow in ma room 🫪

🫠✨

Back w some thoughts 🙂 get ready

ስትከሳ ስትንገላታ ስታጣ ስትነጣ ባትሰርቅም ሌባ ይሉሀል ባልዋልክበት ያውሉሀል ... ማጣትንማ በደንብ ተጠየፈው ብሮ ... ያጣን ሰው አትጥላ እንጅ ማጣትህ ከሁሉም በላይ ልትጠላው የሚገባ መሆን አለበት።

ጦር ሜዳውን ለራሱ ለባለስልጣናቱ እና ስልጣኑን ለሚፈልጉ እንድሁም ለራሳቸው ዘመድ አዝማዶች አስረክቦ ሌላው በሰላም መኖር የሚችልበት ሁኔታ ቢፈጠር እንዴት ደስ ባለኝ ነበር ። ለማንኛውም ደህና እደሩ የነገ ሰው ይበለን✌️🏾

በሰዎች ለመወደድ ትግል ውስጥ አልገባም፤ ለሰዎች ጥሩ እና ቀና የሚያስብ ማንነት እንዲኖረኝ ግን ዋጋ እከፍላለሁ!! ምክንያቱም ለራሴ ሰላም እና እግዚአብሔር ደስ የሚሰኝበት ልብ እንዲኖረኝ ስል!!! 🙌

ጥርስ የለውም ማለት አይናከስም ማለት አይደለም
@ezreal_1

ለምወድሽ❤️
እኔ አንቺን ስወድሽ አንድ ቀን ሺ ሆነ፣ ሀዘኔ ጠፋና ደስታዬ ሰፈነ፣ እኔ አንቺን ሰወድሽ ቀናች ጨረቃይቱ፣ ተዘባረቀባት ቀንና ሌሊቱ፣ እኔ አንቺን ሰወድሽ ፀሀይት ደበነች፣ ቅናት አንገብግቧት በንዴት በገነች፣ እኔ አንቺን ሰወድሽ በጋና ክረምቱ ለፀብ ተጋበዙ፣ አመዳም ተራሮች አብረቅርቀው ወዙ፣ ብቻ እታለሜ እኔ አንቺን ስወድሽ፣ ተፈጥሮ ይናጣል ምን ብዬ ልንገርሽ፡፡ @ezreal_1

በአንድ ቅዳሜ ምሽት በካርኒቫል ውስጥ የሚጨፍሩትን በግማሽ እርቃናቸውን ያሉ ልጃገረዶችን በሴሰኝነት የሚመለከቱ ሰዎችን አያለሁ፣ በእሁድ ጠዋት ደግሞ በካርኒቫሉ ሌላኛው ጫፍ ለድንኳን ወንጌላውያን ኦርጋን ስጫወት፣ እነዚህኑ ሰዎች ከሚስቶቻቸው እና ከልጆቻቸው ጋር በቤተክርስቲያን ወንበሮች ላይ ተቀምጠው እግዚአብሔር ኃጢአታቸውን ይቅር እንዲላቸው እና ከስጋዊ ፍላጎት እንዲያነጻቸው ሲጠይቁ አያለሁ። እና በሚቀጥለው ቅዳሜ ምሽት ወደ ካርኒቫሉ ወይም ወደ ሌላ የሥጋዊ ደስታ ቦታ ይመለሳሉ።
በዚያን ጊዜ የክርስቲያን ቤተክርስቲያን በግብዝነት ላይ እንደምታድግ፣ እና የሰው ልጅ ሥጋዊ ተፈጥሮም ማሸነፉ እንደማይቀር አወቅሁ!
@ezreal_1

ለምን መኖር ደከመህ? ለምን ህይወት ድግግሞሽ ሆነብህ? ለምን ራስህን ለማጥፋት ወሰንክ? በስደት ስላለህ? በህመም ስለሆንክ? ያሰብከው ስላልተሳካ? ያመንከው ስለከዳህ? አሞታለሁ ብለህ ለምን ታስባለህ? አበቦች ሲፈኩ እንደሚደርቁ ያውቃሉ፡፡ ግን እደርቃለሁ ብለው ሳይፈኩ አይቀሩም፡፡ ሰውም ሟች ነው ግን ሟች ነኝ ብሎ መተው የለበትም፡፡ ሁሉም ሰው በየመስኩ ያብብ፡፡ ወዳጄ እፅፍልሀለው አንተ አላስፈልግም ትላለህ እንጂ ያላንተ የማይሆኑ ብዙ ነገር አለ ያላንተ የማይሞቅ ቤት አለ፡፡ ያላንተ የማይሳካ ህልም አለ፡፡ ያላንተ የማያምር ጨዋታ አለ፡፡ ያላንተ የማይደምቅ ቤት አለ፡፡ ይህቺ አለም ትልቅ ዳመራ ናት አንተ በዳመራው ስር ያለህ አንድ ችቦ ነህ አንተ ስትጠፋ የዳመራው ብርሀን ይቀንሳል፡፡ የቻልከውን ያህል ብራ አንተ ከነገሮች በላይ ነህ፡፡ በነገሮች አትረበሽ፡፡ እደግመዋለሁ ህይወት ልክ እንደ ክራር ጨዋታ ነው፡፡ አጨዋወቱን ያወቀ ጥሩ ሙዚቃ ይሰማል ያላወቀ ደግሞ ዝብርቅርቅ ጩኸቷን ለመስማት ይገደዳል፡፡ አሁንም እልሀለው ህይወት በደመነፍስ አትሄድም ስልቷን እወቀው፡ ፡ በህይወትህ ትላንት ያለፈውን መጥፎ ህይወትህን መቀየር ማስተካከል መሰረዝ አትችልም፡፡ የምትችለው አምኖ መቀበልና ለተሻለ ነገ መስራት ነው፡፡ "መቀየር የማንችለውን ነገር መቀበል ማለት ተስፋ መቁረጥ ወይም መሸነፍ ማለት ሳይሆን አቅማችንን የምንችለው ነገር ላይ ማዋል ማለት ነው::" በፍፁም ተስፋ አትቁረጥ ግን አቅምህን የምትችለው ነገር ላይ አውለው፡፡ ሳትኖር ለመሞት አትቸኩል ....😊

Repost from ጲንኤል
#ተስፋ የሚያስቆርጡ ነገሮች ወደ ሂወትህ ሲመጡ እነዚህን ሶስት ነገሮች አስብ 1. እግዚአብሔር ካንተ ጋር እንደነበር 2. እግዚአብሔር ከአንተ ጋር እንዳለ 3. ነገም ሁሌም እግዚአብሔር ካንተ ጋር እንደሚኖር❤️

.....በህይወት ጉዞአችን ውስጥ ስንብት የሚባል ነገር ትልቁ የነፍስ ፈተና ነው። አብዛኞቻችን ቻው ማለት ወይም መሰናበት እንደ ቀላል ጉዳይ ይታያል። ለአንዳንዶቻችን ግን ስንብት ቀላል የቃላት መለዋወጫ ሳይሆን በልብ ውስጥ የነበረን አንድ ውብ ገጽ በግድ የምንዘጋበት ያንኑ ቅርርብ በአንድ ቃል የምናቋርጥበት እጅግ ከባድ ስሜት ነው። ቻው ብለን.... ለሰዎች... መሰናበት ሲያቅተን እንደ መጥፎ ባህሪ ወይም እንደ ቸልተኝነት ሊቆጠር ይችላል። ነገር ግን ይህ ስሜት የሚመጣው ከመውደድ ነው። አንድን ሰው መሰናበት ማለት ያ ሰው በህይወታችን የነበረውን ድርሻ በአንድ ጊዜ የምንገታበት የጋራ ጊዜያችንን ወደ ትዝታነት የምንቀይርበት ሂደት ነው። መለያየትን ለመቀበል የሚከብደን ያንን የፍቅር ወይም የጓደኝነት ትስስር ማቋረጥ ስለማንፈልግ ነው። ስንብትን መሸሽ ማለት የልብን ባዶነት ለመቋቋም መሞከር ነው። ብዙ ጊዜ ዝም ብሎ መሄድ ወይም ሳይሰናበቱ መለየት ያንን የስንበት ሰላምታ ለመናገር የሚጠይቀውን የልብ መፍረስ ላለመጋፈጥ ነው። ያንን ቃል ከተናገሩና ከተቃቀፉ በኋላ የሚመጣው ርቀት ስንብትን ለሚጠሉት ሰዎች እጅግ ይከብዳል። አንዳንዴ ስንብት ሳይደረግ የሚደረግ ጉዞ ለራስ የምናደርገው ጥበቃ ነው። መለያየትን ለመቀበል መቅረት የሚችሉትን የልብ ትስስር ይዞ ለመቀጠል ነው። ቻው ማለት ከባድ ነው ምክንያቱም ልብ ሁሌም አብሮ መኖርን እንጂ መለያየትን ስላልተማረ። ራስ ወዳድነት ሊመስል ይችላል ግን ደግሞ ጠለቅ ብሎ ላየው ከልብ ላለመውጣት የሚደረግ ትግል ነው። ሁሌም አብሮ ያለ አይሰነባበትም😍 እስራኤል ሰይፉ (ቦዔዝ)

ሙሉ ደቂቃ ቁጭ ብዬ ኳስ ያየሁበትን ቀን እምብዛም አላስታውስም። ነገር ግን በተለይ ሃይስኩል እያለሁ በአጋጣሚ ሳልፍ አልያም ደግሞ መሄጃ ከሌለኝ ሻይ እየጠጣሁ ሀይላይት አይ እንደነበር ግን በደምብ ትዝ ይለኛል። ልጅ እያለሁ በራሱ ታላላቆቼ ብስራት ኤፍ ኤም ከፍተው ሲሰሙ ግን እማልክደው የልጅነት ሀቅ ነው። መሰለ መንግስቱ ያወጣው ዘፈን ዛሬም ጆሮዬ ላይ አለ። ''እግርኳስን በሬድዮ ተመልከቱ። መሰ...............ለ መንግስቱ!..'' የሚል ድምጽ.... በዚህ መሃል ግን አርሰናል ከሌሎች ክለቦች በተሻለ ለእኔ ጎልቶ እንዲታይ የሆነበትን ምክንያት ግን እነሆ.... ልጅ እያለሁ ከማልረሳቸው ኵነቶች አንዱ በታላላቅ ወንድሞቼ የሚደረገው የአርሰናል እና ማንችስተር ጨዋታ ነው። ምን DSTV ገብቼ የእውነተኛውን አርሰናል እና ማንችስተር ጨዋታ ባላይም፣ እውነተኞቹን ተጫዋቾች በመልክ ባላውቃቸውም (በስም ሲጠሩ ስለምሰማ) አርሰናል ልቤ እንዲገባ ግን የግድ DSTV መግባት አልተጠበቀብኝም ነበር። ...ሁሌም ቅዳሜ ቅዳሜ አዳሪ ትምህርት ቤቱ ውስጥ ጨዋታ አይጠፋም ነበር። ብዙውን ሳምንት ጨዋታው የሚደረገው በአርሰናል እና በማንችስተር ሲሆን (አንዳንዴ ቆላ እና ደጋ፣ ድፍን ምስር ክፍት ምስር....እየተባለ ቢከፈልም አብዛኛው እና ምቹው ግን የአርሰናልና ማንችስተር ክፍፍል ነበር) ... አሸናፊው ቡድን ታድያ ሳምንቱ የሱ ነው። ቀጣይ ሳምንት መጥቶ ተሸናፊው ቡድን መልሶ አሸንፎ ድሉን እስካላስመለሰ ድረስ ሳምንቷን ተሸማቆ ነው የሚጨርሰው። ሁሌም የምበሳጭበት ግን አንድ ነገር ነበር። ትንሹ ስለነበርኩ ለትዕዛዝ ተመችቼ ይሁን አልያም ፊትለፊት ተገኝቼ ባላውቅም ተጫዋቾቹ በሙሉ በተራ ተራ ውሀ እንዳመጣላቸው የሚልኩኝ ነገር... ...እንዳያመልጠኝ እልና እየፈጠንኩ ሄጄ በያዝኳት ማንቆርቆርያ የምትመስል የፕላስቲክ ጆግ (ትልቱ እኔን ይበልጣል😀) ውሀዬን ይዤ ልክ ሜዳ ስደርስ የላከኝ ልጅ ኳሷን ይዟል እየተጫወተ... ሌሎች ተጫዋቾች ይቀሙኝና ይጠጡታል... አልከለክል መቼስ ኩርኩሙስ🤛 የላከኝ ልጅ ሲመጣ ውሀው አልቋል። '' ለምን አባክ ሰጠሀቸው?...'' ይለኝና መልሶ ይልከኛል... ...እንዲህ ውሀ እያመላለስኩ የጓጓሁለትን ኳስ ሳላየው ያልቃል.. ሳምንቱን ደግሞ እቅድ አወጣለሁ። "...ሜዳው አጠገብ ያለው ትልቁ ዛፍ ጫፍ ላይ እወጣለሁ መቼስ ከዛ አያስወርዱኝም እንደውም በደምብ ይታየኛል ወደታች..'' ብዬ አቅድና ልክ ሳምንቱ ሲመጣ እወጣለሁ ዛፍ ላይ። ልክ ኳሱ ተጀምሮ ትንሽ እንዳየሁ አንዱ ተጫዋች ይጣራል "...እስራኤል አይቼሀለሁ ና ውረድ...'' እየተነጫነጭኩ እወርዳለሁ። ''..ኤጭ ምንድነው? ሌሎቹ ልጆች አያመጡም እንዴ? ወይስ እኔ ማመጣው ውሀ ይጣፍጣቸዋል?...'' ንጭንጭ እያልኩ ወደ ስራ.. ሙሉ ኳስ የማየው ከስንት አንዴ ነው እንደ እድል። ሰአት ያዝ ከተባልኩ...   ጥቁሯን እጅ ላይ የምትታሰረዋን ሰአይ ይሰጡኝና ኳስ ሲወጣ ሰአት እያቆምኩ...(ከሜዳው ጀርባ ያሽቆለቆለ ስለሆነ ኳሷ ሩቅ ሄዳ እስክትመጣ ይቆያል)  ኳሷ ስትመለስ ደግሞ እንዳስቀጥል። እሱም ደግሞ ኳሱን ሙሉ ደቂቃ እንዳይ ጥሩ እድል ቢሆንም ግንሌላ ጣጣ አለው። እየመራ ያለ ቡድን ሁሌም ማሸነፍ ይፈልጋል ስለዚህ ደቂቃው አላልቅ ሲለው እኔ ላይ ሲጮህ... እየተመራ ያለ ቡድን ደግሞ ኳሷ የእጅ እንኳን ስትሆን እንዳቆምለት ይጨቃጨቃል። ሌላው ጣጣ ደግሞ ድንገት እመሰጥና ኳሱ ሲወጣ ያቆምኩት ደቂቃ ኳሷ ስትመለስ አላስጀምረውም። ልክ ሁለተኛ ፎሪ ሲወጣ ሰአቱን ለማቆም ሳየው ለካ ቅድም እንዳቆምኩት ነው.... ...ያዩብኝ ይመስል ድንግጥ እልና ኳሱ ውጪ እንዳለ ማስቆጠር እጀምራለሁ... አንዳንዴ ደግሞ አጫውት የተባልኩት ደቂቃ ሳላውቀው አልቆ ሌላ አጫውት የተባልኩትን ግማሽ የሚያህል ደቂቃ... ሰአት መያዜን ሳላውቀው ረስቼ እያጫወትኩ በመሀል አንዱ የደከመው ''  ኧረ ዳኛ ምንድነው ሰአት..'' ሲል ድንግጥ እልና ''የባከነ አምስት ደቂቃ ጨምሬአለሁ..'' ብዬ እጮሀለሁ። ሰአት መያዙ ግን ለኔ አሪፍ መበቀያ መንገድ ሆኖልኝ ነበር። ሁሌ ውሀ አምጣ ብሎ የሚልከኝ የአርሰናል ተጫዋች ይሆንና ውሀውን ሳመጣው በግድ የሚወስድብኝ ካልሰጠሁትም የሚኮረኩሙኝ የማንችስተር ተጫዋች ነበር። (አጋጣሚ ይሁን ታስቦበት ግን አላውቅም) ...ውሀ እንዳመጣ የላከኝ ቢያናድደኝም ያመጣሁትን ውሀ ሳይልከኝ ኮርኩሞ ከወሰደ በኋላ መልሶ እንዳመጣ የሚያደርገኝ የማንችስተር ተጫዋችን መበቀያዬ ታድያ ሰአት ነው። ሌላው የማንችስተር ተጫዋቾች የሚያናድዱኝ ጉልበት ይጠቀማሉ። ኳስ ካለፈ እግር አይለፍ አይነት ነገር። ... ሁለቱም ቡድን ላይ የተሻለ ብቃት ያላቸው ልጆች ቢኖሩም አርሰናል ላይ ያሉት በብቃት በልጠው ጉልበት እንደሌላቸው (ከማንችስተር የበለጠ) ሳይ ለአርሰናል እንዳደላ የሚያደርገኝ  ምክንያት ነበር። ... አርሰናል ሲመራ ኳሷ ብትወጣ እንኳን ሰአቱ አይቆምም። ማንችስተር ሲመራ ግን የግድ አርሰናል እስኪያገባ እጠብቃለሁ። ማግባት ካቃታቸውና ተስፋ ካልቆረጡ በቀር ያልታወቀ ጭማሪ ግድ ነው። ...በዚህ መልኩ የእንግሊዙን አርሰናል ሳላይ የኛው አርሰናል ግን በትንሹ ልቤ ገብቶ ነበር። አድጌ ታድያ "ማናቸው እንዲህ በልጅነት ያስጨነቁኝ ክለቦች?" ብዬ ሳያቸው ምንም ለውጥ አላየሁባቸውም። ልክ በስልካችን ላይ ከምናስጭናቸው አኒሜሽን ጌሞች ሊለዩልኝ አልቻሉም። ውሃ አልቀዳላቸው፣ሰአት አልይዝላቸው...ወይ ኳስ አላቀብላቸው ወንበር ላይ ቁጭ ብሎ ዝም ብሎ ማየት... ኳስ ገብተው ባይጫወቱም የጫወታው አንዱ አካል መሆን ግን ደስ የሚል ጣዕም ያለው ይመስለኛል። እንግሊዝ ተኪዶ አንድ አካል አይኮን ነገር... ብቻ እንደኔዎቹ ማንችስተርና አርሰናሎች አልጥም አለኝ ጨዋታቸው። ከዛን ጊዜ በኋላ አርሰናል እና ማንችስተር ሲባል የልጅነቴ ይናፍቀኛል። አላገኘው መቼስ። አርሰናል ከ22 አመት በኋላ ዋንጫ በላ ሲሉኝ ታድያ ደስ አለኝ። ልክ በልጅነቴ ውሀ ያመጣሁላቸው እና  ሰአት የጨመርኩላቸው አርሰናሎች እኔ በሌለሁበት ዋንጫ የበሉ አይነት ነገር ነው ደስታው። አሸናፊነት የትናንት የጽናት ውጤት ነው። በውጣ ውረድ፣ በሽንፈትና በድል ውስጥ አብሮ የቆየ ሰው ውጤት።  አርሰናል ሻምፒዮን ሲሆን፣ እኔም ሻምፒዮን ነኝ። ይህ ዋንጫ የክለቡ ብቻ ሳይሆን፣ እኔን ጨምሮ በክለቡ ላይ እምነት ላሳዩ ደጋፊዎች ሁሉ የተበረከተ በልጅነት ያመላለስኩት ውሀ ውጤት ነው። ዛሬ የምደሰተው በዋንጫው ብቻ አይደለም፤ የልጅነቴ አርሰናል ደጋፊዎች እንደዛ ሲጫወቱ እና ሲለፉ አርሰናል ያልሰጣቸውን ዋንጫ ዛሬ እንደሰጣቸው ሳስብ ነው የምደሰት። ይህ ደስታ የዘመናት ጥያቄያቸው መልስ ነው። አርቴታ አርሰናል ሲጫወት ያላገኘውን ዋንጫ እልህ ይዞት አሰልጣኝ ሆኖ ተመልሶም ዋንጫውን ለማሳካት 7 አመት ፈጅቶበታል። ልቤን የነካው ደግሞ እንዲያ እየለፋ የሊቨርፑል ይሁን የሲቲ ደጋፊዎች ሚዜ አድርገው የሰሩበት ምስልን ሲያሳዩኝ ነበር ዘንድሮ ሙሽራ ሆኖ ስላሳያቸው ደስ ብሎኛል። ለሚያልፍ ቀን የማያልፍ ቃል አትናገር ማለት ይሄኔ ነው። ለማንኛውም የልጅነቴ አርሰናሎች እነ ራያችን እንኳን ደስ አላችሁ! ዛሬም የእናንተ ደጋፊ ነኝ!🏆🏆🏆🏆 አብረን ሆነን ባነብላችሁ ደስ ይለኝ ነበር ግን አብረን ስላልሆንን እናንተው አንብቡት። የእናንተው አርሰናለር እስራኤል ሰይፉ (ቦዔዝ)

ህእ! +++++++ ረጅም ዘመን ያስቆጠረ ትዳር ነው። ባል ስቅታ ይዞታል። ከነጋ ለሶስተኛ ጊዜ እንደ አዲስ ሲጀምረው ክፉኛ ተበሳጨ። “አረ ማናባቱ ነው ስሜን ሲያነሳና ሲጥል የዋለው? ህእ! ” አለ ለሚስቱ። “ስኳር ቃምክበት?” አለችው። “አዎ።” “ደረቅ እንጀራ በላህበት?” “ህእ! አዎ” “ቀዝቃዛ ውሃ ጠጣህበት?” “አዎ” "በረዶ ያለው?" "ህእ! አዎ አልኩሽ እኮ" “እሺ ትንፋሽህን ይዘህ ሞከርከው? ” “አዎ ” “እና አሁንም አልቆመልህም?” “ህእ! አልቆመልህም? እያየሽኝ አይደል? አሁንም እያነቀኝ? ህእ! " ትኩር ብላ አየችው። ከቅድሙ አሁን ንጭንጭ አብዝቷል። “እንጃ እንግዲህ” አለች። “እስቲ የፈረደበትን ቻት-ጂፒቲን ሌላ መፍትሄ ጠይቀው?” “አይ! እሱማ ‘ልትሞት ነው’ ብሎ ነው የሚያስበረግገኝ። ህእ! ካንሰር ነው ምናምን ብሎ ቆሌዬን እንዳይገፈው። ጉግል ይሻለኛል።” “እሺ ጉግል አርገዋ” ስልኩን አነሳ። በፍጥነት ተየበ። የስልኩ ሰማያዊ ብርሃን ፊቱ ላይ አርፎ ይታያል። ህእ! ህእ! ህእ! “ኦ!” አለ ከደቂቃዎች በኌላ። “ምነው? ምን አለህ?” ጠየቀችው “ለካስ ያልሞከርኩት ነገር አለ” “ምንድነው?” “ብነግርሽም አታምኚኝም” “ተናገር እንጂ። ለምንድነው ማላምንህ?" “መፍትሄው ላይ ትረጂኛለሽ?” “እንዴ! የምችለው ከሆነ ለምን አልረዳህም? ቀኑን ሙሉ አሸህ እኮ! ድምፅህ ራሱ ያሳዝናል፤ በዛ ላይ ነገ ስራ ነው። በጊዜ መተኛት አለብን።” ዝም ብሎ ቆየ። ከዚያ ደግሞ ህእ! አለ። "ንገረኝ እንጂ" “ያ ነገር ስቅታን ቶሎ ያስቆማል ይላል” አላት። ጮክ ብላ ሳቀችና... “አትለኝም?!” አለችው በለበጣ። “በእውነት!" " አታሹፍ" " እውነቴን ነው ስልሽ?" " ውይ አንተ! ቀልድና ቁምነገርህ አይለይ!" " እውነቴን ነው እያልኩሽ?" “አንተ ከምር አንበበኸው ቢሆን እንኴን አንድ ሰው ለቀልድ የጻፈው ይሆናል ።” “አይደለም፤ ‘ስዊዲሽ ጆርናል’ ነው ይላል፤ ሳይንሳዊ ጥናት ነው። ህእ!" “በእውነት?” “እውነት" አስተዋለችው። መኝታ ክፍላቸው ያው እንደተለመደው ነው። ሰላላ ብርሃን፣ አልጋ፣ ልብስ የተከመረበት ወንበር... “የሚገርም ነው” አለች ሰረቅ አድርጋ እያየችው። “እሱስ አዎ። ህእ! እና ታዲያ...?” አላት። ተጠጋችው። የሚደረገውን ካደረጉ በኋላ... ትሄዳለች ብሎ የሰጋ ይመስል እርቃን ገላዋን ከእርቃን ገላው አጣብቆና አጥብቆ አቀፋት። ፈገግ ብላ አየት አደረገችውና፣ “እሺ በል፤ ደህና እደር የኔ ጌታ” አለችው። “ደህና እደሪ የእኔ እመቤት” መለሰላት። “ሳመኛ” ሳማት። ጀርባዋን ሰጥታው ተኛች። ከኋላዋ አቀፋት። “ባሌ..” አለች ፀጉሯ ውስጥ ተደብቆ ሙቅ ትንፋሹ በአንገቷ በኩል ሽው ሲላት ደስ እያላት። " ሚስቴ" “ኢንተርኔቱ ምንም ይበል ምን” አለች ፊቷም ባዞረችበት ፈገግ ብላ። “በበኩሌ ስቅታ ስላስቸገረህ ደስ ብሎኛል።” ከት ብሎ ሳቀ። ተቃቅፈው ባሉበት ብዙ ደቂቃዎች በዝምታ አለፉ። ከዚያ ግን ባል እንዲህ ብሎ ዝምታውን ረበሸ.... "ህእ!"

አኩኩሉ አልነጋም አኩኩሉ አልነጋም ዐይኑን ለጨፈነ በቶሎ አይነጋም ገልጦ ሲቃኝ ብርሃን ናፍቆ ሁሉም ጠፍቷል ተደብቆ ሺ ቢለፋ ሊያገኛቸው ማይገኙለት ብዙ ናቸው . ህይወትም እንዲያው ናት ጨፍነው እስኪገልጡ ቆማ አትጠብቅም ለብርቱ ነው እንጂ አውቆ ለታወረ ቦታ ሰጥታ አታውቅም አኩኩሉ አኩኩሉ ያ ጨዋታ ያ ልጅነት ላስተዋለው መስታወት ነው ብርቱ ከሰነፍ የሚለይበት ህይወት ቆማ አትጠብቅም ለበረታ ፀሃይ አጠልቅም አይጋረድ ዐይናቹ አንድ እናንተው ያላችውት ለራሳቹ! . አኩኩሉ አኩኩሉ ሳይረፍድ ግለጡ ቶሎ በሉ!🔥🤫

አሻጋሪዎቹ! የጎጆ ቤት ጨዋታ። እንዲህ ባለ የግንቦት ወር ነበር ያረፉት:- የቡታጅራ መንገድ: መንገድ መሆን እንደሚችል ሳይታሰብ ገና ድሮ እርሳቸው በባዶ እግር ሄደው: ለገዳሙ ቤተሰብ ቀለብ እህል፣  በርበሬ ጭነው  በአህያ እየነዱ ይወስዳሉ። ከአዲስ አበባ ሰባት ቤት ጉራጌ  ምሁር ኢየሱስ ድረስ በእግር እየተጓዙ ጉዳይ ያስፈጽሙ ነበር:-  አባ ፈቃደሥላሴ (አባ ፈቃደ፣ በሀገሬው አጠራር "አቦች") ዘምሁር ኢየሱስ ገዳም። ይህንን በማደሪያቸው የሳር ጎጆ እሳት አቀጣጥለው ሻሂ እያፈሉ ያጫውታሉ። በዚያ እርጅና በጎጆዋ ውስጥ ካለው ቆጥ የተፈለጠ እንጨት አውርደው፣ እሳት አቀጣጥለው የሀገሩን ቅዝቃዜ ሲረቱ ማየት ግር ሊል ይችላል። ለእርሳቸው ድንቅ አይደለም። ያለፉትን ረዥም የምንኩስና፣ የአገልግሎት ሕይወት ሲነግሯችሁ ግን መደመማችሁን አታቆሙም። አባ ሙሉ ለሙሉ አቅም አጥተው ቤት እስከሚውሉ  ድረስ ከገዳሙ ወደ ሦስት ኪሎ ሜትር የሚርቀው የሃዋርያት ከተማ እየሄዱ  የደብረ ታቦርን በዓል  በሃዋርያት ቤተክርስቲያን ያከብሩ ነበር። ከተማሪዎቹ እንጨት የሚፈልጥላቸው፣ የሚላካቸው እና ደግፎ ወደ ቤተመቅደሱ የሚወስዳቸው ተማሪ ይመደብላቸዋል። አንድ ቀን ረዳታቸው ኃይለ ሚካኤል ሊያስመሰክር ከሄደበት ሀገር በአዲሳባ በኩል ወደ ገዳሙ ሲያልፍ አዲሳባ ላሉት የገዳሙ ቤተሰቦች በጨዋታ መሃል እንዲህ አላቸው:- "ስለ አባቴ በስልክም አልጠይቅም፤ ለኢየሱስ  ስዕለት ተስያለሁ፤  በሕይወት እንዳገኛቸው። እንደገና እግራቸውን እንዳጥብ፣ እንደገና እንጨት እንድፈልጥላቸው... እንዲባርኩኝ። አባቴ አሁንስ እየደከሙብኝ ነው" አብ ይባርክ ኃይለሚካኤል ሊያስመሰክር ሲሄድ  ተተካ። አንድ ሰው እጅጉን ውኃ ተጠምቶ ሲጠጣ እንደሚያረካው ያለ ነው የአባት እና የልጅ ፍቅራቸው! እድሜአቸው ከ100 ዓመት ያልፋል። በእርጅና ድምጻቸው "አዪዪ ዛሬስ ቤተክርስቲያን አልሄድም። ልጄ ደክሞኛል ሰዓታት መቆም አልችልም" ይሉታል። "እሺ አባ" ብሎ ቡራኬውን ተቀብሎ ይወጣል። አባም መደባቸው ላይ እግራቸውን ወደውጭ አድርገው ጋደም ይላሉ። ትንሽ እንዳሸለቡ ይነቃሉ። "ዛሬ መነኮሳቱ ምን ሆነዋል! አይደውሉም እንዴ?! ሰዓታት ሳይቆም ሊነጋ እኮ ነው!" ይላሉ። አለቃ* ይመልስላቸዋል። (*አለቃ የያኔው ሲራክ የአሁኑ የገዳሙ አበምኔት አባ ዘኢየሱስ።) "ሰዓት ገና ነው አባ ፈቃደ ትንሽ አረፍ በሉ" ሦስት አራቴ ለምን አይደወልም እያሉ ለመተኛት ሳይሆን ዓይናቸውን ትንሽ ለመጨፈን ብቻ መደባቸው ላይ ጋደም ብለው፣ እግራቸውን ከመደቡ ውጪ አድርገው ተዘጋጅተው ይጠብቃሉ። ኃይለሚካኤልም ይሁን አብ ይባርክ ጸባያቸውን ስለሚያውቁ ሰዓታቸውን ጠብቀው ይመጣሉ። አባም አልሄድም ማለታቸውን አያስታውሱም።  "ጎሽ ልጄ መጣህ ቤተመቅደሱ ናፍቆኝ ነበር" ይላሉ። የሰርክ ጸሎት ሲያልቅ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ላይ ወደ ጎጆአቸው የመጡ አይመስሉም ሌሊት አምስት ወይም ስድስት ሰዓት ላይ "ናፈቀኝ"  ሲሉ። መቋሚያቸውን ተደግፈው እያንዳንዱን ንባብ ያደምጣሉ። ካልተሰማቸው "ጮክ ብለህ አንብብ!" ይላሉ። ማረፍ ሲፈልጉ "መነኮሳት: ትፈቅዱልኛላችሁ? ትንሽ ልቀመጥ?" ይላሉ በሚጣፍጥ የጉራጊኛ ቅላጼ። ሲመለሱ በጎጆዋ ባለችው ክብ፣ በእበት የተለቀለቀች ባለ ሦስት ጉልቻ የእሳት ማንደጃ አጠገብ ይቀመጣሉ። እማሆይ ወለተማርያም (የአሁኗ እማሆይ ማርያ) እራት ያቀርባሉ። እርሳቸው ቆመው ይባርካሉ፤   በመዓድ መሀል ረስተው የቃል ጸሎታቸውን ሲቀጽሉ አለቃ "አባ ይብሉ እንጂ" ይላቸዋል፣ "የጨረስን መስሎኝ" ይሉና ደስ የምትል ሳቃቸውን ለአፍታ ብልጭ ያደርጋሉ፣ ምንም ደቂቃ ያለጸሎት መቀመጥ አይችሉም፣ መቁጠሪያቸውን መቼም አይለዩአትም 'ነፍሴ ናት' ይላሉ። ጭስ ባወረዛት ጥንታዊት የሳር ጎጆ ውስጥ ጭስ በጠገበች የጥንት  ማንቆርቆሪያ ሻሂ ይጣዳል። ምን  ላምጣልዎት ለሚላቸው ሁሉ መልሳቸው አንድ ነው:- ስኳር። ሳጥናቸው ውስጥ ይቆለፋል :-)  ለእንግዳ ሁሉ ይጋብዛሉ፤ ሰው ያመጣላቸውን መልሰው ያቀርባሉ።  ወፍራም ሻሂ በራሳቸው ኩባያ ይጠጣሉ። ከስብሐት በኋላ ሊያሳርጉ ይቆማሉ። ሲነሱ እድሜ ያጎበጠውን ሰውነታቸውን ታግለው ያንሰራሩታል። በመወዘቻው በሞቀ ውኃ ረዳቸው  እግራቸውን ያጥባል። ምርቃት ያወርዱለታል። ጉልበት ስሞ ወደ ማደሪያው ይሄዳል።.... እንደዛ እንደዛ.... ሁልጊዜ እንደዛ..... ያን የዕርገት በዓል ምሽት ግን አብ ይባርክ ለመጀመሪያ እና ለመጨረሻ ጊዜ አረፈደ። መነኮሳቱ ማኅሌት ቆመዋል። ደማቅ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የዕርገት በዓል! አባ ዓይናቸው በደንብ አያይም፤ ጉብጠታቸው ጭንቅላታቸው ከጉልበታቸው ሊደርስ ትንሽ ቀርቶታል፣ ምርኩዛቸውን የቱንም ያህል ቢያጠብቁት ሊደግፋቸው አይችልም ።   ከማደሪያ ጎጆአቸው ቤተመቅደሱ ቅርብ ቢሆንም አድራሽ ያስፈልጋቸው ነበር። የበዓል ልብስ የሚያለብሳቸው፣ እጃቸውን ያዝ፣ ጎናቸውን ደገፍ አድርጎ የሚያስገባቸው የሚመልሳቸው ሰው ያስፈልግ ነበር። ጠበቁት፣ ጮክ ብለው ጠሩት፣ እርሱ መኖሪያው እዚያ የተማሪዎች ጊቢ። "ልጄን ምን ነካብኝ?"  አሉ ለብቻቸው "ይህን ቀን ናፍቄ ነበረ!  ናፍቄ ነበረ! " ወረቡን እየሰሙ፣ መሄድ እየፈለጉ፣ እያሉበት እየኖሩበት የሚናፍቃቸውን ቤተመቅደስ ብድግ ብለው መሄድ እና መግባት ስላቃታቸው ሳግ እየተናነቃቸው። "አባ እኔ ነጭ ልብስዎት የት እንዳለ አውቃለሁ። አልብሼ ልውሰድዎት ?" አለቻቸው እንግዳዋ። እንደሕጻን ልጅ ተፍለቀለቁ። እጃቸውን ይዛ ደረጃው ጋር አደረሰቻቸው እና ለአንዱ ተማሪ አቀበለቻቸው። የማያልቅ ምርቃት መረቋት። እናም "ልጄ አሞት እንዳይሆን እዩት" ብለዋት ገቡ። አብ ይባርክ በዚያ መብራት በሌለው ድቅድቅ ጨለማ ጧፉን እያበራ ሲሮጥ መጣ። እርሱም እንዴት ሰዓት እንዳለፈበት አያውቅም። አባ ፈቃደ ሥላሴ(አባ ፈቃደ) (አቦች) ኑሮአቸው እንደዚህ ነበር። የቤተክርስቲያናችን አባቶች ሁሉ እንጂ! የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መነኮሳት ለማኅበረ መነኮሳቱ የሚያስፈልገውን ከሩቅ ቦታ ድረስ የቀናት፣ የሳምንታት፣ የወራት  ጉዞ በእግር እየተጓዙ እየገዙ፣ በማኅበር እየሠሩ፣ በማኅበር እየጸለዩ፣ የቤተ መቅደስ አገልግሎት ሳያቋርጡ፣ ስብሐተ እግዚአብሔር ሳያቋርጡ፣ እየኖሩበትም እየናፈቃቸውም በቤተመቅደሱ ጸንተው  አምላካቸው እግዚአብሔርን  በገዳማት እስከሞት ታምነው አገለገሉት። ለመንፈስ ልጆቻቸው ሃይማኖት ከምግባር፣ ሥራን ፣ ፍቅርን መከባበርን....  አስተምረው ኖረውት አወረሱ.. . ዘመንን አሻገሩ:- አሻጋሪዎቹ አባቶቻችን! እንጨት ፈልጠው እሳት አቀጣጥለው ቀዝቃዛውን አየር እንዳሞቁት ፣ በወንጌል ብርሃን፣ በወንጌል ትምህርት ምድሪቷን አበሯት፣ አሞቋት! አሻጋሪዎቹ!

አንችም በሐይማኖትሽ.... አንችም በሐይማኖትሽ እኔም በሐይማኖቴ.... የሚለው ግጥም ግን በእውነተኛው አለም ከቶ አይሰራም እቴ እኔም ካንቺ ፍቅር አንቺም ከኔ መውደድ እየተላመድን አንቺ ሌላ አምላክ እኔም ሌላ ጌታ ደግሞ ከወደድን... እዚህጋር ተሸዋወድን... እሺ ከዚያስ... ምን ሊሆን ፍጻሜው? የትስ ቦታ ሊሆን ፍቅራችን መድረሻው? ካልወሰድሽኝ በኒቃ ካላገባሁሽ በተክሊል ለቅዳሴ አብረን ካልነቃን ሶላት ካልወጣን አዛን ሲል ልጆችሽ ቁርአን ካልቀሩ ልጆቼ ካልሄዱ አብነት የሼሁም የቄሱም ትምህርት አይሄድም መቼም በአንድነት። ሰደቃ ካልሰራሽ፣ አስራቴ ካላጸደቀሽ የኔ ለልጄ ክርስትና ቀን ከሌለሽ ከጎኔ... በአንድ ጣራ እየኖርን ሁለት ጌታ ስናመሰግን ፍቅራችን ብቻውን ሆኖ ጽኑ ቤት ይሰራ ይሆን ግን?... አንሞኝ ግድ የለም እቴ.... አውቃለሁ እንደምወድሽ ያንቺም ፍቅር ሀያል ነው በጣም ፍቅረኛ የሆነ ሁሉ ግን አብሮ ጎጆ አይወጣም። ፍቅር ከምንዘራ... መውደድ ከምንዘራ የሚፈርስ ጎጆ ላይ እየተዋደድን... እየተፋቀርን እጣችን ነው ብለን እዚጋ እንለያይ። ✍️ሮቤል